የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- : ማር. 15:42–47፤
ማር. 16፣ ቆላ. 2:10–12፣ 1 ቆሮ. 15:1–8፣ ዳን. 9:24–27፣ ዮሐ. 20:11–18።
የመታሰቢያ ጥቅስ: “እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን
የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤
እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ” አለ (ማር. 16:6)።
የኢየሱስ መሰቀል ለደቀ መዛሙርቱ እምነትና ተስፋ መሞት ማረጋገጫ ነበር።
ይህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታቸው መሞት ጋር የታገሉበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን
ለራሳቸው ሕይወትም እጅግ የፈሩበት ጊዜ ስለነበር ጨለማ የሆነ የሳምንቱ
የመጨረሻ ጊዜ ነበር (ዮሐ. 20፡19)። የማርቆስ መጽሐፍ የመጨረሻው ምዕራፍ
በሆነው ማርቆስ ምዕራፍ 16 ውስጥ ሞቱን ተከትሎ ስለሆነው ነገር እንመለከታለን።
በመጀመሪያ፣ የኢየሱስ ከሙታን መነሳት ጊዜውን ጠብቆ ስለመሆኑና
ሴቶቹ ለምን ወደ መቃብሩ እሁድ ጧት እንደመጡ እንመለከታለን። የእሁድን
ቅድስና በሚደግፍ መልኩ በተሳሳተ መልክ ጥቅም ላይ ከመዋሉ የተነሣ
አድቬንቲስቶች አንዳንድ ጊዜ የትንሣኤ ማለዳን ይደብቃሉ። እንደ አለመታደል
ሆኖ ከዚህ የትንሣኤ ቀን የተነሳ የተሳሳተ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቢኖርም
እንኳን በእሁድ ትንሣኤ እንዴት መደሰት እንደምንችል እንመለከታለን።
ሁለተኛ፣ ትምህርቱ እነዚህን ቃላት በመላው መጽሐፍ ውስጥ ካለው ዋና
ሀሳብ ጋር በማገናኘት የማርቆስ 16ን የመጀመሪያ ቁጥሮች ያብራራል። ሰኞ እና
ማክሰኞ ላይ የምናደርጋቸው ጥናቶቻችን እነዚህን ጽንሰ ሀሳቦች ይመለከታሉ።
ሶስተኛ፣ ሳምንቱን ስንዘጋ፣ ረቡዕ እና ሀሙስ የማርቆስ ምዕራፍ 16ን
ቀሪ ክፍል በመመርመር በፊታችን የሚያስቀምጠውን ተልዕኮ ይመለከታል።
ይህ ጥናት የማርቆስ መጽሐፍን የሚያነበውን አንባቢ ወንጌልን ወደ ዓለም ሁሉ
እንዲወስድ ግድድሮሽ በመስጠት ይደመደማል።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለመስከረም 18 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ማር. 15:42–16:6ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ምንድር ነው የሆነው? ይህ ታሪክ ከትንሣኤው ታሪክ ጋር እጅግ የተገናኘ የሚሆነው ለምንድር ነው?
ኢየሱስ የሞተው “የመዘጋጀት” ቀን ተብሎ በሚታወቀው ቀን መሆኑን
ሁሉም የወንጌል ጸሐፊዎች ይስማሙበታል (ማቴ. 27:62፤ ማር. 15:42፤ ሉቃስ
23:54፤ ዮሐንስ 19:14፣ 31፣ 42)። አብዛኞቹ ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጡ ሰዎች
ይህ ከሀሙስ ጸሐይ ግባት እስከ አርብ ጸሐይ ግባት እንደሆነ አድርገው ይረዳሉ።
ኢየሱስ የሞተው አርብ ከሰዓት በኋላ ረፋድ ላይ ሲሆን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት
በጥድፊያ ተቀብሯል።
በሰንበት ቀን ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ ያረፈ ሲሆን ሁሉም የኢየሱስ ደቀ
መዛሙርትም በተመሳሳይ ሁኔታ አርፈዋል። “በሰንበትም እንደ ሕጉ አረፉ” (ሉቃስ
23:56)፣ ኢየሱስ በርግጥ አራተኛውን ትዕዛዝ የመጠበቅን ግዴታ አሳንሶ ወይም
ቢያንስ በአእምሮአቸው ውስጥ ዝቅ አድርጎ ቢሆን ኖሮ እንግዳ የሆነ ተግባር ይሆን
ነበር። ሴቶቹ ቅዳሜ ማታ ቅመማ ቅመሞችን ገዝተው የተለመደውን የቀብር ሂደት
ለመፈጸም በመፈለግ እሁድ ጧት ወደ መቃብር ሄዱ። በርግጥ ኢየሱስ በዚያ ቦታ
አልነበረም! ከሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ ኢየሱስ እሁድ ጧት መነሳቱ
ያለውን ወሳኝነት ክርስቲያኖች ተመልክተዋል። ይህ እሁድን በቅድስና ለመጠበቅ
መሰረት ሆነ። ነገር ግን አዲስ ኪዳን የሚያስተምረው ይህን ነው ወይ?
ቆላ 2:10–12ን ያንብቡ። የኢየሱስን ትንሣኤ በተመለከተ የአዲስ ኪዳን መታሰቢያ
ምንድር ነው?
የትንሣኤ መታሰቢያ እንደሆነ አድርጎ ስለ እሁድ ቅድስና ፍንጭ የሚሰጥ
አንድ ቃል እንኳን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። መታሰቢያው ጥምቀት ነው።
“እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ
ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር
ተቀበርን።” (ሮሜ 6:4)።
እንደ አድቬንቲስቶች የእሁድን አምልኮ በተመለከተ ያለውን ሀሰተኛ የስነ-
መለኮት አምልኮ ከግምት ውስጥ ሳናስገባ እሁድ ማለዳ በተፈጸመው የኢየሱስ
ትንሣኤ መደሰት አለብን። ኢየሱስ በሞቱና በትንሣኤው ሞትን ድል የነሳ ሲሆን
በትንሣኤው እኛም የራሳችንን ትንሣኤ ዋስትና አግኝተናል።
“ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም
ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ” (1 ጴጥ. 1:3)። ጳውሎስ ስለ
ኢየሱስ ትንሣኤ የነበረውን እርግጠኝነት ይመልከቱ። እኛም ያ እርግጠኝነት ሊኖረን
የሚችለው እንዴት ነው?
ማር. 16:1–8ን እና 1 ቆሮ 15:1–8ን ያንብቡ። እነዚህ ንባቦች የጋራ የሆነ ምን አላቸው?
የትንሣኤ ታሪክ በእያንዳንዱ ወንጌል ውስጥ ይገኛል። እያንዳንዱ የወንጌል
ጸሐፊ ታሪኩን በተለየ መልኩ ይጀምራል፣ ነገር ግን ሁሉም ወንጌላት በ1ኛ ቆሮ. 15፡
1-8 ላይ የሚገኙትን አንኳር ጽንሰ ሀሳቦች ይይዛሉ።
አራት ሀሳቦች ደግመው ደጋግመው ይታያሉ። እነርሱም ሞተ፣ ተቀበረ፣
ተነሳ፣ ታየ የሚሉ ናቸው። በማርቆስ ወንጌል ውስጥ ሞተ እና ተቀበረ የሚሉ
ቃላት በምዕራፍ 15 ውስጥ ይገኛሉ። ተነሳ እና ታየ የሚሉ ቃላት በምዕራፍ 16
ውስጥ የሚታዩ ቢሆኑም ትንሽ ለየት ባለ ሁኔታ ነው። ማርቆስ 16፡7 በገሊላ
ስለነበረው ስብሰባ ስለሚናገር በዚያ ቦታ እርሱን ትመለከቱታላችሁ (ዮሐ. 21ን
ይመልከቱ)።
አንዳንድ ሰዎች ክርስቲያኖች ከሙታን በተነሣው ጌታ ማመናቸው
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ያስደንቃቸዋል። ነገር ስለ ትንሣኤው ያለው ማስረጃ ትልቅና ከምክንያቱ ጋር
የተጣጣመ ነው።
ለመጀመር ያህል፣ አንድ ሰው ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር እግዚአብሔርን
እንደ ፈጣሪ ማመን ሲሆን (ዘፍ. 1 እና 2ን ይመልከቱ) የትንሣኤ እና የተዓምራት
ሀሳብ ምክንያታዊ ይሆናል። ዩኒቨርስን (ዓላማትን) እና ከዚያም በምድር ላይ
ሕይወትን የፈጠረው አምላክ ከፈለገ ኢየሱስንም ከሙታን የማስነሳት ኃይል
በእርግጠኝነት ነበረው። የእግዚአብሔር መኖር ትንሣኤን ማስቀረት የማይቻል
ብቻ ሳይሆን ምክንያታዊም ያደርገዋል።
በመቀጠል፣ መቃብሩ በርግጥም ባዶ ነበር። ይህንን እውነታ ከሃዲ የታሪክ
ምሁራንም ይቀበሉታል። እንዲህ ባይሆን ኖሮ የእርሱ አካል በዚያ ቦታ መገኘት
እርሱ ተነስቷል የሚለውን አባባል ስለሚያበላሽ ስለ መነሳቱ የሚነገረው ሀሳብ ገና
ከመነሻው ውድቀት ይገጥመው ነበር።
በመቀጠል፣ ሥጋውን (አካሉን) ደቀ መዛሙርቱ ሰረቁት የሚለው
ማብራሪያ አይሰራም። በእርግጠኝነት ደቀ መዛሙርቱ ጥበቃዎቹን ጥሰው
ማለፍ አይችሉም ነበር። ጥሰው ማለፍ ችለው ሥጋውን ወስደው ቢሆን እንኳን
ደቀ መዛሙርቱ በስርቆት ምክንያት ያልተያዙት ለምንድር ነው? ለዚህ መልሱ
የኃይማኖት መሪዎች ደቀ መዛሙርቱ አለመስረቃቸውን ያውቁ ነበር።
ደግሞ የተነሣውን ክርስቶስን መመልከታቸውን ብዙ ሰዎች መስክረዋል።
ደቀ መዛሙርቱን ጨምሮ ብዙዎች በመጀመሪያ አላመኑም ነበር። አንድ ብርቱ
ጠላቱ የነበረው ጳውሎስ የተነሣውን ጌታ ማየቱን የተናገረ ብቻ ሳይሆን ያ
ልምምድ የሕይወቱን አቅጣጫ አስገራሚ በሆነ መንገድ መለወጡንም ተናግሯል።
በመጨረሻ (ሌሎች ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም)አንድ ግለሰብ ከሙታን
የተነሣውን ጌታ እንዳዩ በሚናገሩ ሰዎች የተመሰረተችውን የክርስቲያን ቤተ
ክርስቲያን አነሳስ የሚያብራራው እንዴት ነው? እነዚህ ሰዎች ውሸት መሆኑን
ላወቁት ነገር ለመሞት ለምን ፈቃደኞች ይሆናሉ? ከሞቱ በኋላም ሆነ (የሐዋ. 3፡
15) ከዓመታት በኋላ (1ኛ ጴጥ. 1፡3) የተሰጠው ይህ ተመሳሳይ (የማይለዋወጥ)
ምስክርነታቸው ስለ ትንሣኤው ኃይለኛ የሆነ ማስረጃ ይሰጣል።
የሆነ ሰው ክርስቶስ ከሙታን ስለመነሳቱ ምን ማስረጃ አለህ ብሎ ቢጠይቅዎ ምን
ብለው ይመልሳሉ?
“በክርስቶስ መስቀል አጠገብ የቆሙ ሴቶች የሰንበት ሰዓታት እስኪያልፉ
ድረስ ነቅተው ጠበቁ። በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ እጅግ በማለዳ፣ የአዳኙን
ሰውነት ለመቀባት ውድ ቅመማ ቅመሞችን ይዘው ወደ መቃብሩ አመሩ። ከሞት
ስለመነሳቱ አላሰቡም ነበር። የተስፋቸው ፀሐይ ጠልቃ በልባቸው ሌሊት ነግሷል።
በመንገድ እየሄዱ ሳለ የክርስቶስን የምህረት ተግባራትና የማጽናኛ ቃላት ለሌሎች
ተናገሩ። ነገር ግን ‘እንደገና አያችኋለሁ’ (ዮሐ. 16:22) ብሎ የነገራቸውን ቃላት
አላስታወሱም።”—Ellen G. White, The Desire of Ages, p. 788.
ማር. 16:1–8ን ያንብቡ። ምን ሆነ? ሴቶቹስ በመጀመሪያ ምላሽ የሰጡት እንዴት ነበር?
ከወንጌል ጅምር ጀምሮ ኢየሱስ መሲህ መሆኑን አንባቢው ያውቃል።
ነገር ግን ማርቆስ 8፡29 ውስጥ ኢየሱስን መሲህ ነህ ያለው በአጋንንት ያልተያዘ
የመጀመሪያው ሰው ጴጥሮስ ነው። የመጽሐፉ አጋማሽ እስኪደርስ ድረስ ይህ
መሲህ መሆኑን በእምት የመግለጥ ተግባር አልተፈጸመም!
በመላው የማርቆስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ስለ ማንነቱ ወይም
ስላደረገላቸው ፈውስ እንዳይነገሩ ለሰዎች ሲነግር ነበር። ማርቆስ 1፡44 ላይ
ለምጻሙ ስለመፈወሱ ለማንም እንዳይናገር ነገረው። ማርቆስ 5፡43 ላይ ልጃቸውን
ስለ ማስነሳቱ ለማንም እንዳይነግሩ ለኢያኢሮስና ለሚስቱ ነገራቸው። ማርቆስ 7፡
36 ላይ ደንቆሮና ኮልታፋ የሆነውን ሰው ስለ መፈወሱ ለማንም እንዳይናገሩ
በዚያ ለነበሩት ነገራቸው። ከዚያ ደቀ መዛሙርቱ እርሱ መሲህ መሆኑን ለሕዝብ
እንዳይናገሩ አዘዛቸው (ማር. 8፡30፣ ደግሞ ማር. 9፡9ን ይመልከቱ)። ኢየሱስ
ለማንም እንዳይናገሩ ያለበት ዋና ምክንያቶች ዳንኤል 9፡24-27 ላይ በተነገረው
የጊዜ ትንቢት መሰረት አገልግሎቱን ለመጨረስ እንዲችል ጊዜ ለማግኘት ነበር።
አሁን፣ በዚህ ትዕይንት ውስጥ፣ ስለ ኢየሱስ ከሙታን መነሳት ከተነገራቸው
በኋላ እንኳን፣ ሴቶች በመፍራትና በመደነቅ ከመቃብሩ ቦታ ሸሹ። ቢያንስ
በመጀመሪያ ስለሆነው ነገር አልተናገሩም ነበር።
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
ነገር ግን ዝምታው ብዙም አልቆየም። ወደ ማርቆስ መጽሐፍ መጨረሻ
ስንደርስ ከዚህ ሌላ ምን እናነባለን? “እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥
ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።”
(ማር. 16:20)።
ከዚህ የተነሳ ስለ ኢየሱስና ስለ ማንነቱ እንዲሁም ስላደረገው ነገር ዝም
የማለት ሀሳብ ከሸፈ። መጽሐፉ የሚጠናቀቀው “በየስፍራው” መስበካቸውን
በመግለጽ ነው።
ስለ ኢየሱስና እርሱ ስላደረገው ነገር ዝም ማለት የሌለብን ለምንድር ነው? ዛሬ ስለ
ኢየሱስና ስለ ድነት እቅድ ለማን መንገር ይችላሉ?
ማርቆስ 16:9–20ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች በትንሣኤው ታሪክ ላይ ምን ይጨምራሉ?
ማርቆስ 16፡9-20 ያሉ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በአዲስ
ኪዳን ውስጥ ባሉ ሌሎች ንባቦች ውስጥ ተመሳሳዮች አሉአቸው። መቅደላዊቷ
ማርያም በመቃብር ቦታ ኢየሱስን ማየቷ (ማቴ. 28፡1፣ 9፣ 10፤ ዮሐ.. 20፡11-18፤
ከሉቃስ 8፡2 ጋር ያነጻጽሩ)፤ በገጠር ሁለት ሰዎች እርሱን ማየታቸው (ሉቃስ 24፡
13-35)፤ አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት የወንጌል ተልዕኮ መቀበላቸው (ማቴ. 28፡
16-20፣ ሉቃስ 24፡36-49፣ ዮሐ. 20፡19-23)።
ኢየሱስን ሕያው ሆኖ ካዩት ሰዎች የመጀመሪያዋ ሰው መቅደላዊት
ማርያም ነበረች (ዮሐ. 20፡11-18)። ሌሎች ሴቶችም አይተውታል (ማቴ. 28፡
8-10)። ከሙታን የተነሳውን ጌታ ያዩት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ሴቶች መሆናቸው
ወሳኝ ነገር ነው። በጥንቱ ዓለም ሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ ምስክር ለመሆን ከፍ
ያለ ቦታ ስለማይሰጣቸው፣ ታሪኩ ፈጠራ ታክሎበት ቢሆን ኖሮ፣ የመጀመሪያዎቹ
ምስክሮች አድርጎ ወንዶችን መጥቀስ ይቻል ነበር። ነገር ግን ወንዶች አልነበሩም፣
አሥራ ሁለቶቹም አልነበሩም፣ ነገር ግን ሴት ነበረች። ለአሥራ ሁለቱ የምስራቹን
ለመንገር ሄደች፤ ነገር ግን የነገረቻቸው ነገር እጅግ ጥሩ ስለሚመስልና እንደ
አለመታደል ሆኖ ማርያም ሴት ስለነበረች አላመኗትም ነበር። ይህም የሚያስደንቅ
አልነበረም። የኢየሱስ ትንሣኤ ታሪክ ደጋፊዎች ይህን ጭብጥ፣ ኢየሱስን ለማየት
የመጀመሪያዎቹ ሴቶች መሆናቸውን፣ ለታሪኩ እውነተኛነት ኃይለኛ ማስረጃ
አድርገው ተጠቅመዋል።
ማርቆስ 16፡ 14 ላይ ይህ ታሪክ የፈጠራ ቢሆን ኖሮ ምንም ትርጉም እንደማይኖረው
የሚገልጽ ምን ሆነ?
ታሪኩን ራሳቸው እየፈጠሩት ከሆነ ለምን ራሳቸውን ይህን ያህል ክፉ
አድርገው ያስቀምጣሉ? ኢየሱስ ስለ “ልብ ድንዳኔአቸው” ዘለፋቸው። የወንጌል
ዘገባዎች ኢየሱስ ከተያዘበት ጊዜ አንስቶ ከትንሣኤ በኋላ እስከታየባቸው ጊዜያቶች
ድረስ ተከታዮቹን እጅግ አሉታዊ በሆነ ስዕል ይስሉአቸዋል። ለምሳሌ፣ መሸሽ፣
መካድ፣ አለማመን፣ ወዘተ። ታሪኩ የፈጠራ ቢሆን ኖሮ ይህ ስሜት አይሰጥም።
ከዚህ በተቃራኒ ኋላ የተነሳውን ክርስቶስን በድፍረትና ሳይናወጡ
ማወጃቸው እና ይህ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሰጠው ተስፋ እነርሱ ስለሚናገሩት
ነገር እውነተኛነት ኃይለኛ የሆነ ማስረጃ ያቀርባል።
በጥርጣሬና ያለማመን መንፈሳዊ ወጥመድ ውስጥ እንዳንወድቅ ራሳችንን መከላከል
የምንችለው እንዴት ነው? በየዕለቱ ከተነሳው ክርስቶስ ጋር ራሳችንን ማገናኘት ያለብን
ለምንድር ነው?
ማርቆስ 16:14–20ን ያንብቡ። ኢየሱስ ለቀደ መዛሙርቱ በተገለጠ ጊዜ ምን አላቸው? እነዚህ ቃላት ዛሬ ለእኛ ምን እያሉ ነው?
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገራቸው የመጀመሪያዎቹ ቃላት ማርቆስ
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
16፡14 ላይ ቀጥተኛ ባልሆነ ንግግር ውስጥ ተመዝግበዋል። ስለ አለማመናቸውና
የልብ ድንዳኔያቸው ገሰጻቸው። ይህ ያለማመን ጥያቄ ዝም ብሎ የአሁኑ ዘመን
ችግር አይደለም። አስቀድመን እንደተመለከትነው የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ደቀ
መዛሙርትም ካለማመን ጋር ታግለዋል (ማቴ. 28፡17፣ ዮሐ. 20፡24-29)። እነርሱ
ከኢየሱስ ጋር በአካል አብረው የነበሩና ተዓምራቶቹንም ደግመው ደጋግመው
የተመለከቱ ነበሩ።
ነገር ግን በተለያዩ ማረጋገጫዎች የእርሱን ትንሣኤ እርግጠኝነት
አሳያቸው። ከዚያም፣ ምስክርነታቸው በሰኞ ትምህርት ተጠቃልሎ ከቀረበው
ማስረጃ ጋር ተዋህዶ ለእምነታቸው ጽኑ መሰረት ጣለላቸው።
ከዚያም ኢየሱስ ወንጌልን ወደ ዓለም እንዲወስዱ ደቀ መዛሙርቱን
ሾማቸው። ትዕዛዙ ሰፊ ቦታን የሚሸፍን ነው። ወደ ዓለም ሁሉ በመሄድ ወንጌልን
ለፍጥረት ሁሉ ማወጅ ነበረባቸው። ከዚያም ሥራቸው መልካም ወይም መጥፎ
ውጤት እንደሚኖረው ኢየሱስ አብራራ። ያውም ያመኑት እንደሚድኑና ያላመኑት
እንደሚፈረድባቸው (እንደሚኮነኑ) ነው።
ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን ሥራ የሚያጅቡ ምልክቶችንም ገለጸ--
አጋንንትን ማውጣት፣ በልሳን መናገር፣ ከጉዳት መጠበቅ እና የታመሙትን
መፈወስ። አንዳንድ ሰዎች ማርቆስ 16፡18ን በተሳሳተ መልክ በመተርጎም
ክርስቲያኖች መርዘኛ እባቦችን በእጃቸው መያዝ እምነት እንዳላቸው ማረጋገጫ
አድርገው ወስደውታል። በዚህ ቦታ ይህን የሚመስል ከገደብ ያለፋ (ሥርዓት
ያጣ) ተግባር ፈቃድ አልተሰጠውም። ኢየሱስ እየገለጸ ያለው በሐዋርያት ሥራ
28፡3-6 እንደተገለጸው ጳውሎስ ለሌሎች እንዳደረገው አገልግሎት ባለ ተልዕኮ
ለሚሳተፉት እግዚአብሔር ስለሚያደርግላቸው ጥበቃ ነው።
በርግጥ ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ከጉዳት ይጠበቃሉ ብሎ አያስተምርም።
አንዳንድ ጊዜ የወንጌል ሥራ ወደ ፊት እንዲሄድ ለማድረግ ገጣሚ ሆኖ ሲያይ
እግዚአብሔር ተዓምራትን ይሰራል። ነገር ግን ክርስቲያኖች አንዳንድ ጊዜ
ከምስክርነታቸው የተነሣ ይሰቃያሉ። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ መከራን
በትዕግሥት መሸከማቸው ለማያምኑት የእምነት ኃይል ሌላ ምልክት ነው።
ከዚያም፣ በዚህ ቦታ ያደረገውን ነገር ሁሉ ካደረገ በኋላ “ወደ ሰማይ ዐረገ
በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” (ማር. 16:19)። ኢየሱስ የክፉ ኃይላትን በሙሉ
ስላሸነፈ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ፣ እጅግ ትልቅ ኃይል ባለበት፣ ለመቀመጥ ወደ
ሰማይ አረገ። የመጨረሻውን ጥቅስ ልብ በሉ። ወንጌልን ለመስበክ ወደ “ሁሉም
ሥፍራ” ቢሄዱም ብቻቸውን አልሄዱም። “ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥
በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር” (ማር. 16:20)። ያኔ አብሮአቸው
የነበረ ሲሆን እኛም እነርሱ የጀመሩትን ሥራ ስንቀጥል አሁን ከእኛም ጋር ለመሆን
ቃል ገብቶልናል።
“እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ማቴ. 28:20)።
እኛም ወንጌልን “በሁሉም ስፍራ” ማወጅ ስለምንፈልግ ከዚህ ተስፋ ምን ማጽናኛ
ማግኘት እንችላለን? ወይም ምን ማጽናኛ ማግኘት አለብን?
የዘመናት ምኞት በሚለው የኤለን ጂ ኋይት መጽሐፍ
“‘ጌታ ተነስቷል” የሚለውን ርዕስ ገጽ 779-787 ላይ እና “ሂዱና አህዛብን ሁሉ
አስተምሩ” የሚለውን ርዕስ ገጽ 818-
828 ላይ ያንብቡ።
“ለአማኙ ክርስቶስ ትንሣኤና ሕይወት ነው። በኃጢአት ምክንያት የጠፋው
ሕይወት በአዳኛችን ተመልሷል። ይህ የሆነበት ምክንያት እርሱ የፈቀደውን
ከሙታን ለመቀስቀስ በራሱ ሕይወት ስላለው ነው። የዘላለም ሕይወትን የመስጠት
መብት ተሰጥቶታል። በሰብአዊነት ውስጥ ለሞት አሳልፎ የሰጠውን ሕይወት መልሶ
በማንሳት ለሰብአዊ ዘር ይሰጣል። ‘እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም
መጣሁ።’ ‘እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ
የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ
ይሆናል።’ ‘ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም
በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።’ ዮሐንስ 10:10; 4:14; 6:54.
“ለአማኝ ሞት ትንሽ ነገር ነው። ክርስቶስ ስለ ሞት ሲናገር ትንሽ
ቅጽበት እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል። ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን
አያይም፣’ ‘ለዘላለም ሞትን አይቀምስም።’ ለክርስቲያን ሞት እንቅልፍ፣ የአፍታ
ዝምታና ጨለማ ነው። ሕይወት በክርስቶስ በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውሯል፣
‘ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ
ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።’ ዮሐንስ 8:51፣ 52፤ ቆላ. 3:4.”—Ellen G.
White, The Desire of Ages, pp. 786, 787.
የጎልማሶች ሰንበት ትህርት የማርቆስ መጽሐፍ
የትንሣኤ እውነትነትን የማይቀበሉ ከሃዲ የታሪክ ምሁራን እንኳን
ኢየሱስ መገደሉን ብቻ ሳይሆን ብዙ ሰዎች የተነሣውን ክርስቶስ አይተናል
ማለታቸውንና ከዚህም የተነሣ እነዚህ ሰዎች የክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን አስኳል
(መነሻ) መሆናቸውን ይቀበላሉ። አንዳንዶች ለምን ኢየሱስ ተነስቷል እንደተባለ
ለማብራራት ሲሞክሩ ኢየሱስ መንታ ወንድም ነበረው ወይም የጥንቶቹ ደቀ
መዛሙርት ኢየሱስን ያዩ እየመሰላቸው ቃዥተዋል ብለዋል። ሌሎች ደግሞ
ኢየሱስ በፍጹም አልሞተም፣ ነገር ግን ለጊዜው ራሱን ከሳተ በኋላ ቆይቶ ወደ
ህሊናው ተመልሷል ይላሉ። ሌላ ሰው ከዚህ ዓለም ውጭ የሆኑ ፍጡራን መጥተው
አካሉን (ሥጋውን) ወስደዋል ብሏል። እነዚህን ሁሉ መከራከሪያዎችና እንዴት
እንደማይሰሩ ለመመልከት ክሊፎርድ ጎልድእስቴይን የተባለ ሰው ተነስቷል፡
- በባዶ መቃብር ውስጥ ተስፋን ማግኘት በሚል ርዕስ የጻፈውን ይመልከቱ።
(Pacific Press, 2021).
1. ደቀ መዛሙርት ስለ ኢየሱስ ትንሣኤ መዋሸት ለምን ያስፈልጋቸዋል? እስካሁን
በምናውቃቸው ነገሮች ሁሉ ላይ ተመስርተን ስንመለከት ለእምነታቸው
የተጋፈጡት ጥላቻን፣ መገለልን እና ስደትን ነበር። ይህን ታሪክ ፈጥረው
በማቅረብ ምን ጥቅም ያገኙ ነበር?
2. ከሁሉ በለይ ለእርስዎ አሳማኝ የሆነው የትኛው የኢየሱስ ትንሣኤ ማስረጃ ነው?
ምክንያትዎን ለሰንበት ትምህርት ክፍልዎ ያጋሩ።
3. የኢየሱስ ከሙታን መነሳት በሚሰጠን ታላቅ ተስፋ ላይ የበለጠ ትኩረት ያድርጉ።
1ኛ ቆሮንቶስ 15ን ያንብቡ። ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ትንሣኤ አስፈላጊነት የሰጠው
ትኩረት ምን ያህል ነው?
ማሳሰቢያ
ድርጅቱ