የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት መዝ 119፡1–16፣ መዝ 90፣ ዮሐ 3፡16፣ መዝ 95፡7–11፣ መዝ 141፣
መዝ 128ን ያንብቡ።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡- እንግዲህ ልባችንን ለጥበብ እናስገዛ ዘንድ
የዘመኖቻችንን ቁጥር አስታውቀን። (መዝ 90፡12)።
ከዚህ ቀደም እንደተመለከትነው፣ የእግዚአብሔር ጸጋ የኃጢአትን ስርየት ይሰጣል፣
እንዲሁም ንስሐ በመግባት በእምነት በሚኖረው ኃጢአተኛ ውስጥ አዲስ ልብ
ይፈጥራል።
የእግዚአብሔር ቃል በጽድቅ ሕይወት የመኖር መመሪያዎችንም ይሰጣል (መዝ
119፡9-16)። የእግዚአብሔርን ህግ መጠበቅ በምንም መንገድ ህጋዊነት አይደለም። ነገር
ግን ከእግዚአብሔር ጋር ባለው የጠበቀ ግንኙነት ውስጥ ያለ በበረከት የተሞላ ህይወት
ነው (መዝ 119፡1፣ 2፤ መዝሙር 128)።
ይሁን እንጂ የጻድቅ ሰው ሕይወት ከፈተና ውጪ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ጻድቅ
በኃጢአት አታላይ ተፈጥሮ ሊፈተን (መዝ 141፡2-4) አልፎ ተርፎም በዚያ ፈተና ሊወድቅ
ይችላል። እግዚአብሔር የልጆቹ ታማኝነት ወይም ታማኝ አለመሆን በግልፅ እንዲገለጥ
የፈተና ጊዜዎችን ይፈቅዳል። የእግዚአብሔር ልጆች የእግዚአብሔርን መመሪያ እና ምክር
የሚከተሉ ከሆነ፣ እምነታቸው ይነጻል፣ በጌታ ላይ ያላቸው እምነትም ጠንካራ ይሆናል።
ለጽድቅ የመኖር ጥበብ የሚገኘው በፈተናዎችና በግድድሮሾች መካከል ከእግዚአብሔር
ጋር በሚኖረን የሕይወት መስተጋብር ነው። ስለዚህ፣ አስተዋይ ልብ እንድናገኝና
እግዚአብሔር ቀኖቻችንን እንድንቆጥር እንዲያስታውቀን መጸለይ (መዝ 90፡12)፣ በጌታ
ፊት በታማኝነት ለመመላለስ ያለንን ቀጣይነትና ቁርጠኝነት ያሳያል።
ለየካቲት16 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥኑ።
መዝ 119:1–16፤ 161–168ን ያንብቡ። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ ያለብን እንዴት ነው? ይህን በማድረጋችንስ የሚመጡልን በረከቶች ምንድር ናቸው?
መጽሐፍ ቅዱስ የዕለት ተዕለት የእምነት ሕይወትን ከእግዚአብሔር ጋር በጽድቅ
መንገድ እንደ መጓዝ (“መራመድ”) አድርጎ ይገልጻል። የእምነት ሕይወት የሚገነባው
“በእግዚአብሔር ትእዛዝ” በመመላለስ (መዝ 119፡1፣ ) እና “በፊቱ ብርሃን” በመራመድ
ነው (መዝ 89፡15)። እነዚህ በምንም መልኩ ሁለት የተለያዩ ጉዞዎች ሊሆኑ አይችሉም።
በእግዚአብሔር ፊት መመላለስ የእግዚአብሔርን ህግ ከፍ ማድረግን ያመለክታል።
በተመሳሳይም “በእግዚአብሔር ሕግ” መመላለስ እግዚአብሔርን በሙሉ ልብ መፈለግን
ይጨምራል (መዝ 119፡1፣ 2፣ 10)።
“በመንገዳችን ንጹህ” መሆን መዝሙራት የሚገልጹት ሌላው በጽድቅ ሕይወት
የመመላለስ መንገድ ነው (መዝ 119፡1)። “ያልረከሰ” በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት
ያለውን “ነውር የሌለበትን” መሥዋዕት ይገልጻል (ዘፀ 12: 5)። እንደዚሁም፣ ሕያው
መስዋዕት የሆነው የጻድቅ ሰው ሕይወት (ሮሜ 12፡1) በኃጢአት ፍቅር የረከሰ መሆን
የለበትም። ለእግዚአብሔር የተሰጠ ሕይወት “ፍጹም መንገድ ነው።” ይህ ማለት ግለሰቡ
እግዚአብሔርን የሚያስደስት ትክክለኛ የሕይወት አቅጣጫ መያዙን ያሳያል (መዝ 101:2፣
6፤ በተጨማሪም መዝ 18:32ን ይመልከቱ)።
የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ መለኮታዊ ህጎችን ህጋዊ በሆነ መንገድ
ከማክበር ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። በተቃራኒው፣ በትክክለኛና በተሳሳተው፣
በመልካምና በክፉ መካከል ያለውን ልዩነት “በጥሩ ሁኔታ ማስተዋልን” (መዝ 111:10፤
በተጨማሪም 1 ዜና 22:12ን ይመልከቱ)፣ ውጫዊ ድርጊቶችን ብቻ ሳይሆን መላውን
ማንነት ያካትታል። “የረከሱ አለመሆን፣” የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ እና
እግዚአብሔርን በሙሉ ልብ መፈለግ በህይወት ውስጥ ሊነጣጠሉ የማይችሉ ሁኔታዎች
ናቸው (መዝ 119: 1፣ 2)።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
የእግዚአብሔር ትእዛዛት ለዓለም የእግዚአብሔር ፈቃድ መገለጥ ናቸው። ሰዎች
እንዴት ጥበበኞች እንደሚሆኑ እና በነጻነት እና በሰላም እንደሚኖሩ ያስተምራሉ (መዝ
119፡7-11፣ 133) ። መዝሙረኛው ሕጉ የእግዚአብሔርን ታማኝነት ስላረጋገጠለት በሕጉ
ይደሰታል (መዝ 119:77፣ 174) ።
“ሕግህን ለሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው፣ የሚያሰናክላቸውም ምንም የለም” (መዝ
119፡165) ። መሰናከል የሚያሳየው የሞራል ውድቀትን ነው። ለመዝሙረኛው እግሮች እንደ
መብራት የሆነው (መዝ 119፡105) የእግዚአብሔር ቃል ከፈተና ይጠብቀናል (መዝ 119፡110)።
ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቃል በህይወቱ ስላለው ሃይል ያሳየው እንዴት ነው? (ማቴ 4፡
1-11)? የአምላክን ሕግ በመታዘዝ ከልብ ስለሚመነጨው ኃይል ይህ ምን ሊነግረን ይገባል?
መዝ 90፣ መዝ 102፡11ን እና መዝ 103፡14–16ን ያንብቡ። የሰው ልጅ ችግሩ ምንድር ነው?
የወደቀው የሰው ልጅ ሕልውና በዘላለማዊ ብርሃን እይታ ውስጥ እንፋሎት
ነው። በእግዚአብሔር ፊት አንድ ሺህ ዓመት ለሦስት ወይም ለአራት ሰዓት እንደሚቆየው
“እንደ ሌሊት ትጋት” ነው (መዝ 90: 4፣ 14)። ከመለኮታዊ ጊዜ ጋር ሲወዳደር የሰው
ልጅ የሕይወት ዘመን ይበርራል (መዝ 90፡10)። በሰዎች መካከል በጣም ጠንካራ የሆኑት
ከዕፅዋት መካከል በጣም ደካማ ከሆኑት ጋር ይመሳሰላሉ (መዝ 90: 5፣ 6፤ መዝ 103: 15፣
16)። ሆኖም፣ ያቺ አጭር ሕይወት እንኳን በድካምና በሐዘን የተሞላች ናት (መዝ 90፡
10)። በእግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎች እንኳን ስለ ህይወት አጭርነት ያዝናሉ ይተክዛሉ፤
በተለይም ከዘላለማዊነት በተቃራኒ እነርሱ ከሚያውቁት ውጭ ለሚሆነው ይፈራሉ።
መዝሙር 90 እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪነቱ ለሰዎች ባለው እንክብካቤ አውድ
ውስጥ የሰውን ችግር ገልጾአል። እግዚአብሔር ለትውልድ ሁሉ የሕዝቡ ማደሪያ ነው
(መዝ 90፡1፣ 2)። (ma‘on )ማኦን የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ጌታን የሕዝቡ መጠጊያ
ወይም መሸሸጊያ አድርጎ ያሳያል (መዝ 91፡9)።
እግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣውን በመግታት ጸጋውን ያድሳል። መዝሙረኛው
“የቁጣህን ኃይል ማን ያውቃል?” በማለት ተናግሯል ( መዝ 90:11)። ይህ የሚያመለክተው
ማንም ሰው በኃጢአት ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ የሚያስከትለውን ውጤት በሙላት
ስለማያውቅ፤ ሰዎች ንስሐ ሊገቡና በጽድቅ ሕይወት በጥበብ ሊመላለሱ ተስፋ አላቸው።
ጥበብ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸው እንደ ተራ የማሰብ ችሎታ ብቻ ሳይሆን
እግዚአብሔርን እንደ ማክበር ነው። የሚያስፈልገን ጥበብ “ዘመኖቻችንን እንዴት
እንደምንቆጥር” ማወቅ ነው (መዝ 90፡12)። ቀኖቻችንን መቁጠር ከቻልን ቀኖቻችን
የተገደቡ እና የተወሰኑ መሆናቸውን እናውቃለን ማለት ነው። በጥበብ መኖር ማለት ወደ
እምነት እና ታዛዥነት የሚመራውን የህይወት ጊዜያትን በማወቅ መኖር ማለት ነው።
ይህ ጥበብ የሚገኘው በንስሐ (መዝ 90፡8፣ 12) በእግዚአብሔር የይቅርታ፣ የርኅራኄ እና
የምሕረት ስጦታዎች ብቻ ነው (መዝ 90፡13፣ 14)።
የእኛ መሰረታዊ ችግራችን ሰው ሆነን ከመፈጠራችን ሳይሆን ከኃጢአትና
በዓለማችን ላይ ኃጢአት ካመጣው ነገር የመነጨ ነው። የእርሱ አስከፊ ውጤቶች
በሁሉም ቦታ እና በእያንዳንዱ ሰው ላይ ይታያል።
ለኢየሱስ ምስጋና ይግባውና እኛ ከሰብዓዊ ችግር የምንወጣበት መንገድ
ተዘጋጅቶልናል (ዮሐ 1፡29፣ ዮሐ 3፡14–21)። ያለበለዚያ ምንም ተስፋ አይኖረንም ነበር።
ሕይወታችን ምንም ያህል በፍጥነት ቢያልፍ በኢየሱስ ምን ተስፋ አለን? (ዮሐ 3:16ን
ይመልከቱ።) ያለ እርሱ ምን ተስፋ ይኖረን ነበር?
መዝ 81:7፣ 8፤ መዝ 95:7-11፤ እና መዝ 105:17-22ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ መለኮታዊ ፈተና ምን ምን ነገሮችን ያጠቃልላል?
መሪባ እስራኤላውያን እግዚአብሔር የሚያስፈልጋቸውን የማሟላት ታማኝነቱን
እና ኃይሉን በመቃወም እግዚአብሔርን የተፈታተኑበት ቦታ ነው (ዘጸ 17፡1-7፤ መዝ
95፡8፣ 9)። መዝሙር 81 ትኩረት በሚስብ ተገላቢጦሽ እግዚአብሔር እስራኤልን
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
የፈተነበት ክስተት እንደሆነ አድርጎ ይተረጎማል (መዝ 81፡7)። በአለመታዘዛቸው እና
ባለመተማመናቸው (መዝ 81፡11) በእግዚአብሔር ፈተና ወድቀዋል።
መሪባ የተጠቀሰበት ሁኔታ ሁለት መልእክቶችን ያስተላልፋል። የመጀመሪያው
የእግዚአብሔር ሕዝቦች ያለፈውን ትውልድ ስህተት መድገም የለባቸውም። ይልቁንም
በእግዚአብሔር በመታመን በመንገዱ ሊሄዱ ይገባቸዋል (መዝ 81፡13)። ሁለተኛው፣
ሕዝቡ በፈተናው ወድቀው በመከራ ውስጥ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር አዳናቸው
(መዝ 81፡7)። ባለፈው ዘመን የታየው የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ ለአዲስ ትውልድም
የእግዚአብሔርን ጸጋ ማረጋገጫ ይሰጣል።
መዝሙር 105 ፈተናዎቹ ዮሴፍ ስለ ወደፊት ህይወቱ በእግዚአብሔር ቃል ላይ
ያለው እምነት የሚፈተንበት መንገድ እንደ ነበር ያሳያል (ዘፍ 37፡5-10፣ መዝ 105፡19)።
በቁጥር 19 ላይ “የተፈተነ” የሚለው የዕብራይስጥ Tsarap ጻራፕ “ማንጻት፣” “ማጥራት”
ወይም “ማንጻት” የሚል ስሜት ይገልጻል። ስለዚህ፣ አምላክ የዮሴፍን እምነት የፈተነበት
ግብ፣ በአምላክ ተስፋ ላይ የሚነሱ ጥርጣሬዎችን ለማስወገድ እና ዮሴፍ በእግዚአብሔር
አመራር ላይ ያለውን እምነት ለማጠናከር ነበር።
በዮሴፍ ምሳሌ የተመለከተው የመለኮታዊ ተግሣጽ ግብ የእግዚአብሔርን ልጆች
ማጠናከር እና ለተስፋው ቃል ፍጻሜ ማዘጋጀት ነው (መዝ 105፡20-22)። ይሁን እንጂ
የአምላክን መመሪያ አለመቀበል የሰውን ልብ እልከኛና ደንዳና እንዲሆን ያደርጋል።
“እግዚአብሔር ለሕጉ ፈጣን እና ከሙሉ ልብ የሆነ መታዘዝን ይፈልጋል፤ ነገር ግን
ሰዎች በሰይጣን ማታለያዎች ተዘናግተው ወይም ሽባ ሆነው በኤደን ገነት ውስጥ ለሔዋን
‘ሞትን አትሞቱም’ ብሎ እንዳታለለ በሚያቀርብላቸው የተንኮል አሰራሩ ይታለላሉ።
አለመታዘዝ የበደለኛውን ሰው ልብና ሕሊና የሚያደነድን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም
እምነት ያበላሻል። መጀመሪያ ላይ ኃጢአት መስሎ ይታይ የነበረው ስህተት ቀስ በቀስ
ይህን መልክ ያጣል፣ በመጨረሻም በእርግጥ ያ ድርጊት ኃጢአት መሆኑን እስኪጠራጠሩ
ድረስ ሳያውቁት ተመሳሳይ ስህተት ውስጥ ይወድቃሉ።”—Ellen G. White, Testimo-
nies for the Church, vol. 4, p. 146።
ኃጢአት እንዴት ልብን እንደሚያደነድን ምን የራስዎ ተሞክሮ አለ? ያ ሐሳብ የመታዘዝ
ኃይልን ወደምናገኝበት ወደ መስቀል የሚመራን ለምንድር ነው?
መዝሙር 141ን ያንብቡ። መዝሙረኛው ስለ ምንድር ነው የጸለየው?
መዝሙር 141 ከውስጥ እና ከውጭ ከሚመጡ ፈተናዎች ለመጠበቅ የሚደረግ
ጸሎት ነው። መዝሙረኛው በክፉዎች ሴራ መውደቅ (መዝ 141:9፣ 10) ብቻ ሳይሆን
ክፉዎች እንደሚያደርጉት የማድረግ አደጋ ላይ ለመውደቅም ይፈተናል። የመጀመሪያው
ደካማ ጎን በንግግር ራስን የመግዛት ችግር ስለሆነ መዝሙረኛው ጌታ የከንፈሩን ደጅ
እንዲጠብቅ ይጸልያል (መዝ 141: 3)። ይህ ምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘመን የከተማን
በሮች መጠበቅን ያመለክታል።
ፈተናው ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ በጻድቃን ምክር መሸነፍ ወይም በክፉዎች
ልስላሴ መታለል ነው (መዝ 141: 4፣ 5)። መዝሙረኛው ልቡን እንደ ዋነኛ ስጋት አድርጎ
ይገልጻል፤ ምክንያቱም እውነተኛው ጦርነት የሚጀምረው እዚያ ነው። የእግዚአብሔርን
ልጅ ከፈተና ሊያድነው የሚችለው (መዝ 141፡2) ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ መሰጠት፣
መታመን እና የማያቋርጥ ጸሎት ብቻ ነው። መዝ 1:1 እና መዝ 141:4ን ያንብቡ። የፈተናን
ቀስ በቀስ መጨመርና የአታላይነት ባህሪ እንዴት ይገለጻል?
መዝሙር 141፡4 የፈተናውን ቀስ በቀስ የመጨመር ተፈጥሮ ያሳያል። በመጀመሪያ
ልብ ወደ ክፋት ያዘነብላል። ሁለተኛ፣ ክፉ ሥራዎችን ይለማመዳል (በዕብራይስጥ
ትርጉሙ ድርጊቱን በተደጋጋሚ ማድረግን ያሳያል)። በሶስተኛ ደረጃ ልብ የክፉዎችን
ጣፋጭ ድግስ (ኃጢአት) ይበላል ወይም ተሳታፊ ይሆናል፤ ማለትም ክፉ ተግባራቸውን
እንደ ተፈላጊ ነገር ይቀበላል።
ልክ እንደዚሁ፣ በመዝሙር 1፡1 ፈተናው የሚመጣው የእግዚአብሔር ልጆች
ከክፉዎች ጋር እንዲሄዱ በማድረግ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ላይ እንዲቆሙ እና
በመጨረሻም ከዋዘኞች ጋር እንዲቀመጡ በማድረግ በጌታ መንገድ እንዳይሄዱ ማድረግ
ነው። ኃጢአተኞች፣ ክፉዎች እና ዋዘኞች:- እንደ እነርሱ መሆን የለብንም ወይም ከጌታ
እንዲያርቁን መፍቀድ የለብንም።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
መዝሙራት የፈተናውን ቀስ በቀስ መጨመር፣ ማራኪነት እና ተንኮለኛ ባህሪን
ይገልፃሉ፣ ይህም በጌታ ላይ ሙሉ ጥገኛ መሆን ብቻ የአንድን ሰው ድል እንደሚያረጋግጥ
አጉልቶ ያሳያል። መዝሙራት አንድ ሰው የሚናገራቸው እና የሚያዳምጣቸው ነገሮች
በፈተና መካከል ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ አጽኖት ይሰጣሉ። የኃጥአንም ሆነ
የጻድቃን መጨረሻ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብን እንዲፈልግ ማስተማር አለበት
(መዝ 1፡4-6፣ መዝ 141፡8-10)። ሆኖም በሁለቱም መዝሙሮች ውስጥ፣ የእግዚአብሔር
ልጆች የመጨረሻው ፍርድ ወደፊት እንደሚሆን ተደርጎ ተገልጾአል። ይህ ማለት አማኞች
በእግዚአብሔር በትዕግሥት እንዲታመኑ እና እርሱን እንዲጠብቁ ተጠርተዋል ማለት
ነው።
መዝ 1:1–3፣ መዝ 112:1–9 እና መዝሙር 128ን ያንብቡ። ይሖዋን ለሚያከብሩ ሰዎች ምን የበረከት ተስፋ ተሰጥቷቸዋል?
ጌታን ለሚያከብሩ ሰዎች ቃል ከተገባላቸው ብዙ በረከቶች መካከል ምናልባትም
ሰላም ከታላላቆቹ አንዱ ሊሆን ይችላል። መዝሙር 1 ጻድቅን በውሃ ፈሳሾች ዳር
በተተከለችና ፍሬዋን በወቅቱ በምትሰጥ ቅጠሏም በማይረግፍ ዛፍ ይመስለዋል (መዝ
1፡3፣ ኤር 17፡7፣ 8፣ ሕዝ 47፡12)። ይህ ንጽጽር የበረከቶች ሁሉ ምንጭ የሆነውን፣
ማለትም በእግዚአብሔር ፊት በመቅደሱ ውስጥ ለዘላለም መኖርን እና ከእግዚአብሔር
ጋር በማያቋርጥ የፍቅር ግንኙነት መደሰትን ይገልጻል። መረጋጋት፣ ቦታና የወደፊት ተስፋ
በሌለው ገለባ መልክ ከተገለጹት ኃጢአተኞች በተቃራኒ ጻድቃን እንደ ፍሬያማ ዛፍ ሥር
የሰደዱ፣ በእግዚአብሔር አጠገብ የሚኖሩና የዘላለም ሕይወት ያላቸው ናቸው።
በራስህ የወይን ወይም የበለስ ዛፍ ሥር መቀመጥ የሰላምና የብልጽግና ምልክት
እንደመሆኑ (ሚክ 4:4) መዝሙር 128፡2ና 3 የመሲሃዊ መንግስት በረከቶችን ትውስታ
ወደ አእምሮአችን ያመጣል። በኢየሩሳሌም ላይ የሰላም በረከት (መዝ 122:6-8፤ መዝ
128:5፣ 6) ክፋትን በሚያስወግድና በዓለም ላይ ሰላም በሚያሰፍን መሲህ ላይ ያለውን
ተስፋ ያሳያል።
“በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዳኑ ሰዎች ርስት ‘ሀገር’ ተብሎ ተጠርቷል።
ዕብራውያን 11፡14-16። እዚያ ሰማያዊው እረኛ መንጋውን ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ
ይመራቸዋል። የሕይወት ዛፍ በየወሩ ፍሬውን ይሰጣል፣ የዛፉም ቅጠሎች ለአሕዛብ
ፈውስ ናቸው። እንደ መስታወት የነጹና ሁልጊዜ የሚፈሱ ጅረቶች አሉ፣ በአጠገባቸው
ቅጠሎቻቸውን የሚያውለበልቡ ዛፎች በጌታ የዳኑት እንዲሄዱ በተዘጋጀላቸው ጎዳና ላይ
ሲሄዱ ጥላቸውን ያጠሉላቸዋል። እዚያም የተንሰራፋው ሜዳ ወደ ውበት ኮረብታነት
ይለወጣል፣ የእግዚአብሔር ተራሮች ከፍ ብለው ይቆማሉ። በእነዚያ ሰላማዊ ሜዳዎች፣
ከሕያዋን ጅረቶች አጠገብ፣ የአምላክ ሕዝቦች፣ የረጅም ዘመን መጻተኞች ተጓዦች፣
መኖሪያ ያገኛሉ።”—Ellen G. White፣ The Great Controversy፣ p. 675።
አዲስ ኪዳን የዚህ ተስፋ ፍጻሜ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት እና በአዲሱ ዓለም
መፈጠር እንደሚፈጸም (ማቴ 26፡29፣ ራእይ 21) ይገልጻል። ስለዚህ፣ ጻድቃን በዚህ
ህይወት ውስጥ ብዙ በረከቶችን የሚያገኙ ቢሆንም፣ በዘመን ፍጻሜ የእግዚአብሔር
መንግስት ሲመጣ ሙሉ የሆነ የእግዚአብሔር ሞገስ ሙላት ይጠብቃቸዋል።
መስቀሉ እና በመስቀል ላይ የተፈጸመው በአዲስ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሔር ያዘጋጀልን
የተስፋ ቃል ዋስትና የሆነው ለምንድነው? ከእነዚህ ተስፋዎች አሁንም ማጽናኛ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?
በዚህ ዘመን ጥበብን ማግኘት ደስታን ለማስገኘት ያን ያህል
የሚፈለግ አይመስልም። ሰዎች ከጥበብ ይልቅ ደስተኛ መሆንን ይመርጣሉ። ይሁን እንጂ
ከአምላካዊ ጥበብ ውጪ በእውነት ደስተኛ ሆነን የተሟላ ሕይወት መምራት እንችላለን?
መዝሙረ ዳዊት በግልጽ አንችልም ይላል። መልካሙ ዜና ከጥበብና ከደስታ መካከል
አንዱን እንድንመርጥ አለመጠየቃችን ነው። አምላካዊ ጥበብ እውነተኛ ደስታ ያስገኛል።
ከዕብራይስጥ ቋንቋ የተወሰደ ቀላል ምሳሌ ይህን ነጥብ ያሳያል። በዕብራይስጥ
“እርምጃ” (’ashurey)የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ሲገለጽ “ደስታ” (‘ashurey’) ከሚለው
ቃል ጋር ይመሳሰላል። በእንግሊዘኛ ትርጉሞች ይህን ዓይነት የትርጉም መመሳሰል
ባናገኝም ኃይለኛ መልእክት ያስተላልፋል፡ “እርምጃዎች” የእግዚአብሔርን መንገድ
በመከተል ወደ “ደስተኛ” ሕይወት ይመራሉ (መዝ 1፡1፣ መዝ 17፡5፣ መዝ 37፡31፣ መዝ
44፡18፣ መዝ 89፡15፣ መዝ 119፡1)። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ ጥበብም ሆነ ደስታ ረቂቅ
ፅንሰ-ሀሳብ አይደሉም፣ ግን እውነተኛ ተሞክሮ ናቸው።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
እነዚህ ነገሮች እግዚአብሔርን ማክበርን፣ ማመስገንን፣ ከእርሱ ብርታት
ማግኘትን እና ለእርሱ መታመንን በሚያካትተው ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት
ውስጥ ይገኛሉ። መዝሙር 25፡14 “የእግዚአብሔር ምሥጢር ከሚፈሩት ጋር ነው፥ ቃል
ኪዳኑንም ያሳያቸዋል” ይላል።
“ስላቀረቡልን ብሩህ እይታዎች እግዚአብሔርን አመስግኑት። የተባረከውን
የፍቅሩን ማረጋገጫዎች ያለማቋረጥ እንመለከታቸው ዘንድ በቡድን በቡድን አድርገን
አንድ ላይ እናስቀምጣቸው፡- የእግዚአብሔር ልጅ ሰውን ከሰይጣን ኃይል ለማዳን
የአባቱን ዙፋን ትቶ አምላክነቱን በሰብአዊነት ሸፈነ፤ ሰማይን ለሰው ስለሚከፍትና መለኮት
ክብሩን የሚገልጥበትን የእርሱን መገኘት ክፍል ዕይታ ለሰው ልጅ ስለሚገልጥ እርሱ ድል
ያደረገው ለእኛ ነው። የወደቀው ሰብአዊ ዘር በኃጢአት ምክንያት ከገባበት ከጥፋት
ጕድጓድ ተነሥቶ ዳግመኛ ወሰን ከሌለው አምላክ ጋር ግንኙነት መፍጠሩን፤ በቤዛችን
ላይ በማመን መለኮታዊ ፈተናን መታገሱን፣ የክርስቶስን ጽድቅ መልበሱን እና ወደ ዙፋኑ
ከፍ ከፍ መደረጉን—እነዚህ እግዚአብሔር እንድናጤናቸው የሚፈልጋቸው ምስሎች
ናቸው።”—Ellen G. White፣ Steps to Christ፣ p. 118.
1. የአምላክ ቃል መመሪያ ብቻ ሳይሆን የደስታ ምንጭ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
የአምላክ ቃል መመሪያ ብቻ ሳይሆን የደስታ ምንጭ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
የአምላክን ቃል መመገብ ቃሉ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ከመኖር (ዮሐ 1:1፤
ዮሐ 15:5፣ 7) ጋር የሚዛመደው እንዴት ነው?
2. ሰዎች እያወቁ በቀጣይነት የእግዚአብሔርን ትምህርት ሲጥሉ ምን ይሆናል (መዝ
ሰዎች እያወቁ በቀጣይነት የእግዚአብሔርን ትምህርት ሲጥሉ ምን ይሆናል (መዝ
81፣ መዝ 95)? ይህ ለምን የሚሆን ይመስላችኋል?
3. አንዳንድ ጊዜ ከጻድቃን ምክር ይልቅ የክፉዎች መንገድ የሚሻል የሚመስለው ለምንድር
አንዳንድ ጊዜ ከጻድቃን ምክር ይልቅ የክፉዎች መንገድ የሚሻል የሚመስለው ለምንድር
ነው? (መዝ 141)? ይህ ማለት ብዙ ጊዜ ክፉዎች በጣም የሚከናወንላቸው
ሲመስል ይህን ግልጽ እውነታ እንዴት እንይዘዋለን?