የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት



1ኛ ሩብ ዓመት 2024


የካቲት 2 - 8

7ኛ ትምህርት

Feb 10 - 16




ምህረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት፡- መዝ 136፤ መዝ 51፤ መዝ 130፤ መዝ 113፤ መዝሙር 123ን ያንብቡ።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡- አቤቱ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ። በአሕዛብ መካከል እዘምርልሃለሁ። ምሕረትህ እስከ ሰማያት ድረስ ከፍ ብላለችና እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ። (መዝ 57:9፣ 10)

መዝሙረኞቹ በመንፈሳዊነት ድሆች እንደሆኑና ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ምንም መልካም ነገር እንደሌላቸው ተገንዝበዋል፤ ማለትም በእግዚአብሔር ቅዱስ ዙፋን ፊት እንዲቀርቡ ብቁ የሚያደርጋቸው የራሳቸው የሆነ በውስጣቸው ምንም ነገር እንደሌላቸው ተረድተዋል (መዝ 40፡17) ። እነርሱ እንደ ማናችንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንደሚያስፈልጋቸው ገብቷቸዋል። ባጭሩ እነሱም ወንጌል ያስፈልጋቸዋል።

መዝሙራቱ ሰዎች በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ የመሆናቸውን እውነታ ያጎላሉ። እንደ መታደል ሆኖ፣ በእግዚአብሔር ፍጥረት እና በሕዝቡ ታሪክ ውስጥ እንደሚታየው ምህረቱ ዘላለማዊ ነው (መዝ 136)። በዘላለማዊ አምላክ ፊት፣ የሰው ሕይወት እንደ ሣር አላፊ ነው፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ይራራል ኃይላቸውንም ያድሳል (መዝ 103፡3፣ 5፣ 15)፣ በእርሱም የዘላለም ተስፋ አላቸው። ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ስለሆነ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ይጽናናሉ። የሕዝቡ ልመና በአስቸጋሪ ጊዜያት ወደ ርኅሩኁ ሰማያዊ አባታቸው ስለሚመራ ብዙ ጊዜ በተስፋ የተሞላ ነው (መዝ 103፡13፣ መዝ 68፡5፣ መዝ 89፡26)። የእግዚአብሔር ጸጋ እና ፍቅር ትኩስ ልምምዶች ከእግዚአብሔር በቀር ምንንም ወይም ማንንም እንዳያመልኩ እና እንዳያገለግሉ ውሳኔአቸውን ያጠነክርላቸዋል። ለየካቲት 9 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥኑ። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

የካቲት 3
Feb 11

ምህረቱ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል


መዝ 136ን ያንብቡ። በዚህ መዝሙር ውስጥ የበላይ የሆነው የትኛው ሀሳብ ነው? መዝሙረኛው በሰፊው ለሚናገረው ነገር ማስረጃ ከየት አገኘ?



መዝ 136 በፍጥረት (መዝ 136፡4-9) እና በእስራኤል ታሪክ (መዝ 136፡10-22) ስለተገለጸው ምህረቱ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይጠራል።

“ምሕረት” (ዕብራይስጥ ኬሴድ፣ “ጽኑ ፍቅር”) እግዚአብሔር ለፍጥረታቱ እና ከእስራኤል ጋር የገባውን የቃል ኪዳን ቸርነቱን እና ታማኝነቱን ያሳያል። መዝሙር የእግዚአብሔርን ታላቅ ኃይል እና ታላቅነቱ በጽኑ ፍቅሩ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያሳያል።

ጌታ “የአማልክት አምላክ” እና “የጌቶች ጌታ” የዕብራይስጥ አይዲኦም idiom ሲሆን ትርጉሙም “ታላቅ አምላክ” (መዝ 136:1-3)፣ ሌሎች አማልክት እንዳሉ ሳይሆን እርሱ ብቻውን አምላክ ነው ይላል።

የጌታ ድንቅና ተአምራት፣ በሌላ በማንም ሊደገሙ የማይችሉ፣ የማይካዱ የገዢነቱ ማሳያዎች ናቸው (መዝ 136፡4)። እግዚአብሔር አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሰማያትን፣ ምድርንና ሰማያዊ ኃይላትን ፈጠረ (ዘዳ 4፡19)። መዝሙራት የአረማውያን አማልክትን እና በሰዎች ላይ የተመሰረተ የመተማመን ምንጫቸውንና ስልጣናቸውን ሁሉ ይገፏቸዋል። እነርሱ ተራ ፍጡራን ብቻ ናቸው። ዋና መለያቸው ፈጣሪ ሳይሆኑ የተፈጠሩ ነገሮች መሆናቸው ነው።

የጌታ ብርቱ እጅ እና የተዘረጋ ክንድ ምስል (መዝ 136፡12) የእግዚአብሔርን ኃይል ፍቱንነት እና የምሕረቱን ሰፊነት ያጎላል።

እግዚአብሔር በፍጥረት እና በታሪክ ውስጥ ያለው ምሕረት ህዝቡ በእርሱ እንዲታመኑ እና ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ማነቃቃት አለበት። “ምሕረቱ ለዘላለም ነውና” የሚለው ሐረግ በመዝሙራት ውስጥ 26 ጊዜ ተደግሟል፣ ይህም ጌታ እንደማይለወጥ እና ያለፈውን ጸጋውን ለእያንዳንዱ አዲስ ትውልድ እንደሚደግም ለሚያመልኩት አረጋግጦላቸዋል። እግዚአብሔር ሕዝቡን ያስባል (መዝ 136፡23)፣ ለጸጋውም ቃል ኪዳን ታማኝ ነው። በጌታ በማይለወጥ ምሕረት ላይ መታመን የመጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት እምብርት ነው፣ ይህም በደስታ የተሞላ አምልኮ እና መተማመንን፣ እንዲሁም መጸጸትን እና ንስሐን ያካትታል።

መዝሙር 136፡23-25 የእግዚአብሔርን ዓለም አቀፋዊ ጥንቃቄ በመግለጽ ይደመድማል። የእግዚአብሔር ምሕረት ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተዘረጋ ነው። ስለዚህ መዝሙራት ስለ እግዚአብሔር የማዳን ጸጋ ዓለም አቀፋዊነት ይናገሩና መላው ዓለም ጌታን በማወደስ እስራኤልን እንዲቀላቀል ያድማሉ (በተጨማሪም ሉቃስ 2፡ 10፣ ዮሐንስ 3፡16፣ የሐዋርያት ሥራ 15፡17 ይመልከቱ)።

በመስቀል ላይ የታየው የኢየሱስ መልክ፣ ለኃጢአታችን ምትክ ሆኖ ሲሞት፣ “ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል” የሚለውን ታላቅ እውነት በኃይል የሚገልጠው እንዴት ነው?

የካቲት 4
Feb 12

ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ


መዝሙር 51:1-5ን ያንብቡ። መዝሙረኛው የአምላክን ምሕረት የጠየቀው ለምንድን ነው?



ንጉሥ ዳዊት በሕይወቱ ውስጥ በመንፈሳዊ ጨለማ ጊዜያት የኃጢአትን ይቅርታ በመጠየቅ ልቡን በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰ (2ሳሙ 12) ። ይቅርታ የእግዚአብሔር ልዩ የጸጋ ስጦታ ነው፣ ​“የምህረትህ ብዛት” (መዝ 51፡1) ውጤት ነው። ንጉሥ ዳዊት ለኃጢአቱ የሚገባውን ሳይሆን (መዝ 103፡10)፣ እንደ አምላካዊ ባህሪው ማለትም እንደ ምሕረቱ፣ ታማኝነቱና ርኅራኄው (መዝ 51:1፣ ዘጸ 34:6፣ 7) ብዛት እንዲያደርግለት ይማጸናል።

መዝሙር 51:6–19ን ያንብቡ። እዚህ የኃጢአት ይቅርታ እንዴት ተገለጸ? የመለኮታዊው ይቅርታ ግብ ምንድን ነው?



መለኮታዊ ይቅርታ ከሕጋዊ ነጻ መውጣት አዋጅ የበለጠ ነገርን ያጠቃልላል።

በሰው ልጅ እስከ ውስጣዊ ማንነት ድረስ የሚደርስ ጥልቅ ለውጥ ያመጣል (መዝ 51፡ 6፣ ዕብ 4፡12)። አዲስ ፍጥረትን ያመጣል (መዝ 51:10፤ ዮሐ 3:3-8)። “ፍጠር” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ግስ bara (ባራ) መለኮታዊ የመፍጠር ኃይልን ያሳያል (ዘፍ 1፡ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት 1)። እግዚአብሔር ብቻ መፍጠር ይችላል’ በንስሐ በተመለሰ ሰው ልብ ውስጥ ሥር ነቀል እና ዘላቂ ለውጥ ማምጣት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው (2ቆሮ 4፡6)።

ዳዊት በሂሶጵ ለመንጻት ጠየቀ (ዘሌ 14፡2–8፣ መዝ 51፡7)። ልክ ለምጻም ከለምጹ መንጻቱ እንኪረጋገጥ ድረስ ከማህበረሰቡ እንደሚገለል ጥፋቱ ከጌታ ፊት እንዲታገድ እንዳገለለው ተሰማው (መዝ 51፡11)። የዝሙትና የግድያ ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ ሊያስተሰርዩ የሚችሉ መሥዋዕቶች ስለሌሉ መስዋእቶች ወደ አግዚአብሔር ሊመልሱኝ አይችሉም ብሎ ፈራ (ዘጸ 21፡14፣ ዘሌ 20፡10)።

የዳዊትን “የተሰበረና የተዋረደ ልብ” እንደ መስዋዕት ተቀብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ነበረው አንድነት ሊመልስ የሚችለው ያለ ቅድመ ሁኔታ መለኮታዊ ጸጋ ብቻ ነው (መዝ 51፡16፣ 17)። በሂሶጵ ለመንጻት በመጠየቅ ወደ እግዚአብሔር መገኘት ለመመለስ ፈለገ።

እግዚአብሔር ዳዊትን ስለ ዝሙት፣ ስለ ማታለልና ስለ መግደል ኃጢአቱ ይቅር ባይለው እርስዎስ ምን ተስፋ አለዎት?

የካቲት 5
Feb 13

ጌታ ሆይ፣ አንተ በደልን ምልክት አድርገህ የምትይዝ


ቢሆን መዝሙር 130ን ያንብቡ። የኃጢያት አስጊነት እና የኃጢአተኞች ተስፋ እንዴት ይገለጻል?



የመዝሙረኛው ታላቅ መከራ ከራሱ እና ከህዝቡ ኃጢአት ጋር የተያያዘ ነው (መዝ 130፡3፣ 8)። የሕዝቡ ኃጢአት በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ከእግዚአብሔር ለዘላለም እንዳይለዩ የሚያስፈራ ነበር (መዝ 130፡3)። ቅዱሳት መጻሕፍት መዛግብት ኃጢአትን ለፍርድ ቀን እንደሚጠብቁ (ዳን 7፡10፣ ራዕ 20፡12) እና የኃጢአተኞች ስም ከሕይወት መጽሐፍ እንደሚወገድ (ዘጸ 32፡32፣ መዝ 69፡28፣ ራዕ 13፡8) ይናገራሉ።

ስለዚህ መዝሙረኛው እግዚአብሔር በይቅርታው ኃጢአትን እንዲደመስስ የእግዚአብሔርን ይቅርታ ጠየቀ (መዝ 51:1፣ 9፤ ኤር 31:34፤ ሚክ 7:19)። እግዚአብሔር በተፈጥሮው ቁጡ እንዳልሆነ ያውቃል። ፍቅሩ ዘላለማዊ እንደሆነና ‘ቁጣው’ የሚቀሰቀሰው የሰው ልጅ ፍቅሩን ባለማድነቁ ብቻ እንደሆነ ተረዳ። . . . የቁጣው አላማ ለማቁሰል ሳይሆን ሰውን ለመፈወስ ነው፤ ለማጥፋት ሳይሆን የቃል ኪዳን ሕዝቡን ለማዳን ነው (ሆሴ. 6:1 እና 2 Hans K. LaRondelle, Deliverance in the Psalms (Berrien Springs, MI: First Impressions, 1983), pp. 180, 181 እንዲህ በማለት በአስደናቂ አገላለጽ ገልጾታል፡ - እግዚአብሔርን እንድናመልክ ሊያነሳሳን የሚገባው ቅጣትን መፍራት ሳይሆን ኃጢአትን ይቅር ለማለት ያለው ዝግጁነቱ ነው (መዝ 130፡4፤ ሮሜ 2፡4)። እውነተኛ አምልኮ ሊገነባ የሚገባው የእግዚአብሔርን የፍቅር ባሕርይ በማድነቅ እንጂ ቅጣትን በመፍራት አይደለም።

የእግዚአብሔር ልጆች ጌታን እንዲጠብቁ ተጠርተዋል (መዝ 27:14፤ መዝ 37:34)።

የዕብራይስጥ qawah ቃዋህ፣ “ቆይ፤ ጠብቅ” ቀጥተኛ ትርጉሙ “መዘርጋት” ማለት ሲሆን “ተስፋ” ለሚለው የዕብራይስጥ ቃል መሰረት ነው። ስለዚህ፣ ጌታን መጠበቅ በአስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ በመሸነፍ የሚደረግ ሳይሆን በተስፋ የተሞላ “መዘርጋት” ወይም የጌታን ጣልቃገብነት በጉጉት መጠበቅ ማለት ነው። የመዝሙረኛው ተስፋ የተመሠረተው በግል ተስፈኛነቱ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል ነው (መዝ 130፡5)። ጌታን በታማኝነት መጠበቅ ከጨለማው ምሽት በኋላ መለኮታዊ የማዳን ጠዋት ስለሚመጣ ከንቱ አይደለም።

መዝሙረኛው ያቀረበው የግል ልመና እንዴት የመላው ማህበረሰብ እንደሚሆን ይመልከቱ (መዝ 130፡7፣ 8)። የአንድ ሰው ደህንነት ከመላው ማህበረሰብ ደህንነት የማይነጣጠል ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡም ይፀልያል።

እንደ አማኞች፣ እኛ የማህበረሰቡ አካል ነን፣ ስለዚህ አንድ የማህበረሰብን ክፍል የሚነካው ነገር ሁሉንም ሰው ይነካል።

“አቤቱ፣ አንተ ኃጢአትን ብትመለከት፣ አቤቱ፣ ማን ሊቆም ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ ያስቡ። (መዝ 130:3) ይህ ለእርስዎ በግል ምን ማለት ነው? ጌታ በደልዎን ቢመረምር የት ይሆኑ ነበር?

የካቲት 6
Feb 14

ባለግርማና መሐሪ አምላክ ይመስገን


መዝ 113 እና 123ን ያንብቡ። በእነዚህ መዝሙሮች ውስጥ የተገለጹት ሁለት የተለያዩ የአምላክ ባሕርያት የትኞቹ ናቸው?



የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

መዝ 113 እና 123 የጌታን ግርማ እና ምሕረት ያወድሳሉ። የጌታ ክብር በስሙ ታላቅነት እና በዙፋኑ ከፍ ያለ ቦታ መሆን የተገለጠ ሲሆን ይህም በአሕዛብ ሁሉ እና በላይ በሰማያት ከፍ ያለ ነው (መዝ 113: 4፣ 5፤ መዝ 123: 1)። “እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” (መዝ 113፡5)። ከዚህ ዓለም ውስጥም ሆነ ውጭ ያለ ኃይል የእስራኤልን አምላክ ሊገዳደረው እንደማይችል የእምነት መግለጫ ነው።

ማንም ሊቀርባቸው የማይችላቸው የጌታ መኖሪያ ከፍታዎች የተገለጹት ጌታ “ራሱን ዝቅ ለማድረግ” ወይም “ሰማያትንና ምድርን ለማየት ቁልቁል” (መዝ 113፡6 አጽንዖት የተሰጠው) የወረደ በመሆኑ ነው። የእግዚአብሔር በከፍታ ላይ መገኘቱ በታች ያለውን ነገር ከማየት አያግደውም። የጌታ ምህረት ከአለም ጋር ለመቀላቀል እና ችግረኞችን እና ድሆችን ከችግራቸው ለማዳን ባለው የጸጋ ዝግጁነቱ ተገልጦአል። ምንም እንኳን መኖሪያው በሩቅ ሰማያት ቢሆንም ለጋስ የሆነው እጁ ከአገልጋዮቹ አልተሰወረችም።

በእግዚአብሔር አስደናቂ ልህቀቱ ሙሉ በሙሉ ተለይቶ ሊታወቅ የማይችለው የእግዚአብሔር ታላቅነት እና እንክብካቤ በእርሱ የምሕረት እና የርኅራኄ ሥራዎች ውስጥ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ችግረኞች፣ ድሆች እና የተጨቆኑ ሰዎች እግዚአብሔር ለእነርሱ በሚያደርጋቸው አስደናቂ ለውጦችና ችሮታዎች ሉዓላዊ ኃይሉን ሊለማመዱ ይችላሉ።

ከፍ ያለው እግዚአብሔር የተናቁትን ከፍ ከፍ ለማድረግ ኃይሉን በመጠቀም ታላቅነቱን ይገልፃል። የእርሱ ሉዓላዊነት እና ከፍ ያለ ቸር ፈጣሪያቸውና ረዳታቸው መሆኑ ሕዝቡ የእርሱ አገልጋዮችና የተወደዱ ልጆቹ መሆናቸውን ስለማይለውጥ ሕዝቡ በነጻነት ወደ ጌታ መቅረብ ይችላል።

ስለዚህ አምልኮ በእግዚአብሔር ታላቅነት ብቻ ሳይሆን በቸርነቱም በመነቃቃት የሚቀርብ ነው። ምስጋና በጊዜና በቦታ የተገደበ አይደለም (መዝ 113፡2፣ 3)።

የእግዚአብሔር ታላቅነት እና ምሕረት በተሻለ ሁኔታ የተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ እርሱ የወደቀውን የሰው ልጅ ለማንሳት ከሰማይ ወርዶ በመስቀል ላይ እስከመሞት ዝቅ አለ (ፊልጵ 2፡6-8)። እዚህ ላይ፣ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ ለእኛ ስላደረገልን ነገር እርሱን ለማምለክ እና ለማመስገን የሚቻልባቸው ታላላቅ ምክንያቶች አሉን።

በመስቀሉና በዚያ ቦታ ላይ ለእርስዎ በግል ምን እንደተደረገ ይነጋገሩ። ኢየሱስ ከምን አዳነዎ? መስቀልን በአእምሮዎ ውስጥ ከሁሉም ማስቀደም በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የካቲት 7
Feb 15

ውለታውን ሁሉ አትርሺ


መዝ 103ን ያንብቡ። እዚህ የእግዚአብሔር ምሕረት እንዴት ነው የተገለጸው?



መዝሙር 103 የጌታን ልዩ ልዩ በረከቶች ይዘረዝራል። በረከቶቹ እያደገ ላለ ሕይወት (መዝ 103፡3-6) ያሉ “ጥቅሞቹን ሁሉ” (መዝ 103፡2) ያካትታሉ ። እነዚህ በረከቶች በእግዚአብሔር የደግነት ባህሪ እና ከእስራኤል ጋር በገባው ቃል ኪዳን ታማኝነት ላይ የተመሰረቱ ናቸው (መዝ 103፡7-18)። ጌታ የሰውን የባህሪ ድክመቶች እና ጊዜያዊነት “ያስብ” እና ለህዝቡ ይራራል (መዝ 103፡13–17 ይመልከቱ)።

ማስታወስ ከተራ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) እንቅስቃሴ በላይ ነው። በተግባር የተገለጸ ቁርጠኝነትን ያካትታል፡- እግዚአብሔር ሕዝቡን ያድናል እና ይደግፋልም (መዝ 103፡3-13)።

በመዝሙር 103፡11-16 ላይ ያሉት ኃይለኛ ምስሎች የእግዚአብሔርን የማይለካውን ጸጋ ታላቅነት ያሳያሉ፣ ይህም ከማይገደበው የሰማይ ስፋት ጋር ብቻ ሊወዳደር ይችላል (ኢሳ 55፡9)።

ታዲያ ሰዎች ለአምላክ የፍቅር ደግነት ምላሽ መስጠት ያለባቸው እንዴት ነው? ______________________________________________________ ______________________________________________________

በመጀመሪያ፣ እግዚአብሔርን በመባረክ (መዝ 103፡1፣ 2)። በረከት በአጠቃላይ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ጥቅማ ጥቅሞችን ለአንድ ሰው የመስጠት ተግባር እንደሆነ ያስረዳል (ዘፍ 49:25፣ መዝ 5:12) ። እግዚአብሔር የበረከት ሁሉ ምንጭ ሆኖ ሳለ የሰው ልጅ እንዴት እግዚአብሔርን ይባርካል? የበታች ሰው የበላይ የሆነን እርሱን ምስጋና ወይም ውዳሴ በመስጠት መባረክ ወይም ማመስገን ይችላል (1ኛ ነገ 8፡66፣ ኢዮብ 29፡13)።

እግዚአብሔር ለሰዎች መልካምን በመስጠት ይባርካል፣ ሰዎችም በእርሱ ያለውን መልካም ነገር በማመስገን ይባርካሉ። ማለትም ስለ ቸርነቱ እርሱን በማክበር ነው።

ሁለተኛ፣ ልክ ጌታ ደካማ የሆነውን የሰውን ሁኔታ እና ከህዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንደሚያስታውስ (መዝ 103፡3–13) የአምላክን ውለታዎች ሁሉ እና ቃል ኪዳኑን በማስታወስ (መዝ 103፡2፣ 18–22)። ማስታወስ በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት ላለው ግንኙነት ወሳኝ ገጽታ ነው። እግዚአብሔር ለሰዎች የገባውን ቃል እንደሚያስታውስ ሁሉ፣ ሰዎችም የእግዚአብሔርን ታማኝነት በማስታወስ በፍቅር እና በመታዘዝ ለእግዚአብሔር ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለባቸው።

ይህንን ሃሳብ በአእምሯችን እንደያዝን፣ እነዚህ ታዋቂ የኤለን ጂ ዋይት ቃላት ለዚህ በጣም ገጣሚ ሆነው እናገኛቸዋለን፡- “በየቀኑ የክርስቶስን ህይወት በማሰላሰል የተወሰነ ሰዓት ብናሳልፍ መልካም ነበር። እያንዳንዱን ነጥብ በተለይም የህይወቱን መዝጊያ ክፍል በምናባችን እናሰላስለው። ስለዚህ ለእኛ በተከፈለው ታላቅ መስዋዕትነት ላይ ስንነጋገር፣ በእርሱ ላይ ያለን እምነት ይበልጥ ጽኑ ይሆናል፣ ፍቅራችን ሕያው ይሆናል፣ በመንፈሱ በጥልቅ እንሞላለን። በመጨረሻ ለመዳን የምንፈልግ ከሆነ በመስቀሉ ሥር የንስሐን እና የትህትናን ትምህርት መማር አለብን።”— The Desire of Ages, p 83

የካቲት 8
Feb 16


ተጨማሪ ሀሳብ


ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ ከሚለው የኤለን ጂ ዋይት መጽሐፍ “የኃጢአተኛው ክርስቶስን መፈለግ” የሚለውን ርዕስ ገጽ 17–22ን ያንብቡ።

በመዝሙራት ውስጥ፣ የእግዚአብሔር ሰዎች ድምፅ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” የሚለውን ዝማሬ በመድገም እንደ መዘምራን ቡድን የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ፍቅር በማክበር (መዝ 106፡1፣ መዝ 107፡1፣ መዝ 118፡1-4፣ 29፣ መዝ 136) አንድ ሆናል። “እግዚአብሔርን አለማመስገን ማለት ጥቅሞቹን ሁሉ መርሳት ማለት ነው እንጂ የእግዚአብሔርን ስጦታዎች ማድነቅ አይደለም። እነዚያ የሚያመሰግኑት ብቻ አይረሱትም። ስለ እግዚአብሔር ማሰብ እና መናገር ብቻ እርሱን ማመስገን ማለት አይደለም። ውዳሴ የሚጀምረው የአምላክን ታላቅነት አምኖ በመቀበልና ቸርነቱን፣ ምሕረቱንና ጥበቡን በማድነቅ ምላሽ ሲሰጥ ነው።”— Hans LaRondelle, Deliverance in the Psalms, p. 178።

የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ምህረት አምነን የመቀበላችን ወሳኝነት የበለጠውን ጥልቀት እያገኘ የሚሄደው የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን የፍቅር ቸርነትና ታማኝነት (khesed) በሰብአዊ ኃጢአትና አመጽ መካከል ሳይለወጥ ጸንቶ ሲቆም ነው።

“እኛ በድለናል፥ ለጸጋውም የተገባን አይደለንም። እርሱ ራሱ ግን እጅግ የሚያስደንቀውን ልመና በከንፈሮቻችን ያኖራል፡- ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፥ የክብርህንም ዙፋን አታስነውር፤ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ።’ ኤር 14፡21። ብቁ አለመሆናችንን አምነን ኃጢአታችንን እየተናዘዝን ወደ እርሱ ስንመጣ፣ ጩኸታችንን ሊሰማ ለራሱ ቃል ገብቷል። ቃሉን ለእኛ በማክበር ዙፋኑ ይከበራል።”— Ellen G. White፣ Christ’s Object Lessons፣ ገጽ. 148.

የእግዚአብሔርን ርህራሄ መለማመድ (መዝ 103፡2) መዝሙረኛው “እግዚአብሔር ለተጨቆኑ ሁሉ ጽድቅንና ፍርድን ያደርጋል” ሲል እንዲናገር ያበረታታዋል። ስለዚህ፣ የመዝሙረኛው የግል ምስክርነት የመጨረሻ አላማ፣ በህይወቱ እግዚአብሔርን ስለምህረቱ ማመስገን፣ ለሌሎችም የእግዚአብሔርን የፍቅር ደግነት ማረጋገጥ ነው፣ ስለዚህም እነርሱም ልባቸውን ለእግዚአብሔር እንዲከፍቱ፣ የማዳን ጸጋውን እንዲቀበሉ እና እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ማረጋገጫ መስጠት ነው (መዝ 9፡11፣ 12፤ መዝ 22፡ 22-27፤ መዝ 16፡ 66) ።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. የእግዚአብሔር ምሕረት ለሰዎች መዳን ዘላለማዊ ነው የሚለው ተግባራዊ አንደምታ የእግዚአብሔር ምሕረት ለሰዎች መዳን ዘላለማዊ ነው የሚለው ተግባራዊ አንደምታ ምንድን ነው? ይህ ማለት የአምላክ ምሕረት ለዘላለም ስለሆነ ያይደለው ለምንድነው?

2. የእግዚአብሔርን ለኃጢአታችን ይቅርታ ሰጪነት እግዚአብሔር በኃጢአት ላይ ካለው የእግዚአብሔርን ለኃጢአታችን ይቅርታ ሰጪነት እግዚአብሔር በኃጢአት ላይ ካለው የፍርድ ሃሳብ ጋር የምናስታርቀው እንዴት ነው?

3. በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ የእግዚአብሔር ምሕረት መግለጫዎች በመዝሙር ውስጥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ የእግዚአብሔር ምሕረት መግለጫዎች በመዝሙር ውስጥ ካሉት ጋር እንዴት ይስማማሉ (ኤፌ.2:4፣ 5፤ 1 ጢሞ 1:16፤ ቲቶ 3:5፤ ዕብ 4:16)?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL