የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት



1ኛ ሩብ ዓመት 2024


ጥር 18 - 24

5ኛ ትምህርት

Jan 27 - Feb 2




በባዕድ አገር የጌታን መዝሙር መዘመር



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት፡- መዝ 79፡5–13፤ መዝ 88:3–12፣ 12፤ መዝ 69፡1–3፤ መዝ 22:1፤ ​ መዝሙር 77፤ መዝ 73፡1–20፤ 1 ጴጥ 1፡17ን ያንብቡ።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡- የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ አገር እንዴት እንዘምራለን? (መዝ 137:4)።

መዝሙራቱ የተዘመሩት ፍጽምና በጎደለውና ክፋት፣ መከራ እና ሞት ባለበት ዓለም ውስጥ መሆኑን ለማወቅ ወደ መዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ጠልቆ መግባት አያስፈልገንም። በሉዓላዊው አምላክ የሚመራ የተረጋጋው ፍጥረት እና የጽድቅ ሕጎቹ ያለማቋረጥ ለክፋት ስጋት ተጋልጠዋል። ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ በኃጢአት እየተበላሸ ሲሄድ፣ ምድር ለአምላክ ሕዝቦች “ባዕድ አገር” ሆናለች። ይህ እውነታ ለመዝሙረኛው ችግር ፈጥሮበታል፡- በባዕድ አገር እንዴት የእምነት ሕይወት መኖር ይቻላል?

ቀደም ሲል እንደተመለከትነው፣ መዝሙረኞቹ ለአምላክ ሉዓላዊ አገዛዝና ኃይል እንዲሁም ለጽድቅ ፍርዶቹ እውቅና ይሰጣሉ። እግዚአብሔር ዘላለማዊ እንደሆነ እና በመከራ ጊዜ ሕዝቡን የማይጥል መሸሸጊያ እና ረዳት መሆኑን ያውቃሉ። በዚህ ምክንያት፣ መዝሙረኞቹ አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሔር አለመገኘት እና በሉዓላዊው እና ቸር ጌታ ፊት ክፋት በማበቡ ግራ ተጋብተዋል (ግራ ያልተጋባ ማን አለ?)። መዝሙራቱ እንደ ጸሎቶች ያላቸው እንቆቅልሻዊ ተፈጥሮ (እርስ በርስ የሚጋጭ የሚመስል) እግዚአብሔር ዝም ያለ ለመሰለበት ሁኔታ በሰጡት ምላሾች ውስጥ ታይቷል። በሌላ አነጋገር፣ መዝሙረኞቹ ስለ እግዚአብሔር የተገነዘቡትን ምላሽ ይሰጣሉ። *ለጥር 25 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

ጥር 19
Jan 28

ክፉ ቀናት


መዝ 74:18–22 እና መዝ 79:5–13ን ያንብቡ። እዚህ ጋ አደጋ ላይ ያለው ምንድን ነው?



መዝሙረኛው በእግዚአብሔር እና በክፉ ኃይሎች መካከል ያለውን ታላቁን ተጋድሎ ለመረዳት ይፈልጋል፣ ስለሆነም ወደ ማይመረመር የእግዚአብሔር ትዕግስት፣ እንዲሁም ማለቂያ ወደሌለው ጥበቡ እና ኃይሉ ይጠቁማል።

በመዝሙራት ውስጥ ያለው የክፋት ችግር በዋናነት ሥነ-መለኮታዊ ነው፤ ስለ አምላክ ያሉ ጥያቄዎችን የሚመለከት ነው። ስለዚህ የኢየሩሳሌምና የቤተ መቅደሱ መጥፋት አሕዛብ እግዚአብሔርን እንዲሰድቡ ዕድል በመስጠቱ በዋነኛነት እንደ መለኮታዊ ቅሌት የሚታይ ነው። የእግዚአብሔር ርስት (የእስራኤል ሕዝብ) በፍጹም የማይወድቅ የእርሱ መለኮታዊ ምርጫና ቃል ኪዳን ምልክት ነው (ዘዳ 4፡32-38፣ ዘዳ 32፡8፣ 9)። የእግዚአብሔር ርስት ጽንሰ-ሀሳብ አንድ ቀን ሁሉም ህዝቦች የእግዚአብሔር ርስት ስለሚሆኑና እርሱን ስለሚያገለግሉ የፍጻሜ ዘመን ገጽታም አለው። እነዚህ ሕዝቦች የአምላክን ርስት ወረሩ የሚለው አስተሳሰብ እነዚህን መለኮታዊ ተስፋዎች ስጋት ውስጥ ይጥላል።

መዝሙረኛው የሰዎች ኃጢአት ህዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን የቃል ኪዳን ግንኙነት እንዳበላሸው እና በሰዎች ላይ ሁሉንም መዘዞች እንዳመጣ ያለ አንዳች ጥያቄ ይቀበላል (መዝ 79፡8፣ 9)። የህዝቡ ህልውና የተደገፈው ቸርነት በተሞላው የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት እና በኃጢአት ስርየት በኩል ያለውን የቃል ኪዳኑ ትስስር ወደነበረበት ቦታ በመመለስ ላይ ብቻ ነው። ጌታ ለቃል ኪዳን ተስፋዎቹ የእግዚአብሔርን ታማኝነት የሚያስተላልፍ “የመድኃኒታችን አምላክ” ነው (መዝ. 79፡9)።

ነገር ግን፣ የእስራኤልን ሀብት ከመመለስ የበለጠ አስፈላጊ የሆነው ነገር በአለም ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ባህሪ ከጥቃት መከላከል ነው (መዝ 79፡9)። የአሕዛብ ክፉ ተግባር ሳይቀጣ ከቀረ፣ እግዚአብሔር ኃይሉን ያጣ ይመስላል (መዝ 74፡18-23፤ መዝ 83፡16–18፤ መዝ 106፡47)። የእግዚአብሔር ስም የሚከበረውና ከፍ ከፍ የሚለው እርሱ ሕዝቡን ሲያድን ብቻ ​​ነው።

እንደ ዛሬው ሁሉ፣ ያኔም የነበረው ተመሳሳይ መርህ ነበር። ኃጢአታችን፣ ክህደታችንና፣ ክፋታችን በራሳችን ላይ ብቻ ሳይሆን ስሙን በምንጠራው አምላክ ላይም ውርደት ሊያመጡ ይችላሉ። የተሳሳቱ ተግባሮቻችን በምስክርነታችን እና በተልእኮአችን ላይም ጎጂ የሆነ መንፈሳዊ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። የክርስቶስን ስም በሚጠሩት ሰዎች ድርጊት ምክንያት ምን ያህል ሰዎች ለእምነታችን ጀርባቸውን ሰጥተዋል? “የእግዚአብሔር ክብር፣ የክርስቶስ ክብር፣ የሕዝቡን ባሕርይ ፍጹም በማድረግ ላይ ድርሻ አለው።”—ኤለን ጂ ዋይት፣ የዘመናት ምኞት በእንግሊዝኛው ገጽ 671። ይህን ጠቃሚ እውነት እንዴት ይረዱታል? ይህ በክርስትና ሕይወትዎ ውስጥ ምን ማለት ነው?

ጥር 20
Jan 29

በሞት በር


መዝ 41:1-4፤ መዝ 88:3–12፤ እና መዝ 102:3–5፣ 11፣ 23፣ 24ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ምን ተሞክሮዎችን ይገልጻሉ? እዚህ ከተነገረው ጋር እንዴት ሊያዛምዱ ይችላሉ?



ከሕመምና ከሞት ለመዳን የተጸለዩ እነዚህ ጸሎቶች የአምላክ ልጆች ከዚህ ዓለም ስቃይ ነፃ እንዳልሆኑ ያሳያሉ። መዝሙራቱ የመዝሙረኛውን አስከፊ መከራዎች ይገልጻሉ። እርሱ ብርታቱ ከድቶት፣ እንደ ሳር ጠውልጎ፣ መብላት አቅቶት፣ ከሙታን ጋር ተቆጥሮ፣ በመቃብር እንደ አስከሬን ተኝቶ፣ በወዳጆቹ ተጠልቶ፣ ተሰቃይቶና ተስፋ ቆርጦ ነበር። አጥንቱ በቆዳው ላይ ተጣብቋል።

ብዙ መዝሙሮች እግዚአብሔር ችግሩ እንዲመጣ የፈቀደው ከእስራኤል አለመታዘዝ የተነሳ እንደሆነ ይናገራሉ። መዝሙረኛው ኃጢአት በሽታ ሊያመጣ እንደሚችል ተገንዝቧል፤ ስለዚህም እርሱ ከፈውስ በፊት ወደሚመጣው ይቅርታ ያመለክታል (መዝ 41፡3፣ 4)። ይሁን እንጂ እንደ መዝሙር 88 እና መዝሙር 102 ያሉ አንዳንድ መዝሙሮች በንጹሐን የአምላክ ሕዝቦች ላይ የሚደርሰው መከራ ለመረዳት አስቸጋሪ ቢሆንም የሕይወት እውነታ እንደሆነ እውቅና ይሰጣሉ።

በመዝሙር 88፣ እግዚአብሔር መዝሙረኛውን ወደ ሞት አፋፍ እንዳመጣ ተደርጎ ተከሷል (መዝ 88፡6-8)። ይሁን እንጂ እጅግ ድፍረት ያለባቸው ቅሬታዎች በሚነገሩበት ጊዜ እንኳን ሰቆቃው በግልጽ የእምነት ድርጊት ነው፤ ለዚህ ምክንያቱ ጌታ በሉዓላዊነቱ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት ችግርን ከፈቀደ የልጁን ደህንነት ሊመልስ ስለሚችል ነው።

በመቃብር ደጃፍ ላይ፣ መዝሙረኛው የእግዚአብሔርን ድንቅ፣ የፍቅር ደግነት፣ ታማኝነት እና ጽድቅ ያስታውሳል (መዝ 88፡10-12)። መዝሙረኛው በእግዚአብሔር እንደተመታ ቢሰማውም ከእግዚአብሔር ጋር ተጣበቀ። ምንም እንኳን መከራ ቢደርስበትም የእግዚአብሔርን ፍቅር አልካደም፤ እግዚአብሔር የእርሱ ብቸኛ መዳኛው እንደሆነ ያውቃል። እነዚህ ልመናዎቹ መዝሙረኛው መከራን ብቻ ሳይሆን ስለ አምላክ ጸጋ ጥልቅ እውቀት እንዳለው እና ሁለቱም አንደኛው ሌላኛውን እንደማያስቀር ግንዛቤ ይሰጣል።

በአጭሩ፣ ሁለቱም፣ እግዚአብሔር መከራን መፍቀዱ እና ማዳኑ የመጨረሻው የሉዓላዊነቱ ማሳያዎች ናቸው። እግዚአብሔር ሁሉን እንደሚቆጣጠር ማወቁ ተስፋን ያነሳሳል። መዝሙር 88ን በክርስቶስ የመከራ አውደ-ብርሃን ስናነብ፣ ለሰው ልጅ መዳን በሞት ደጃፍ ለማለፍ ፈቃደኛ የሆነበትን የፍቅሩን ጥልቅነት እናደንቃለን።

ስለ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለመሰቀሉ እና በኃጢአት ምክንያት ለምን እንደተሰቃየ ያስቡ። እግዚአብሔር አብ በክርስቶስ ከማናችንም በላይ መከራን ተቀብሏል የሚለው እውነታ በመከራና በፈተና ጊዜም እንኳ እምነትን እንድንጠብቅ ሊረዳን የሚገባው እንዴት ነው?

ጥር 21
Jan 30

እግዚአብሔር የት ነው?


መዝ 42:1–3፤ መዝ 63:1፤ መዝ 69:1–3 እና መዝሙር 102:1-7 ያንብቡ።

በመዝሙረኛው ላይ ከፍተኛ ሥቃይ ያመጣው ምንድን ነው?



መዝሙረኛውን ያስጨነቀው በግል እና በጋራ የሚደርስ ስቃይ ብቻ አልነበረም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ ላይ ለሚደርሰው ችግር ትኩረት የሰጠ አለመምሰሉ ነበር። የእግዚአብሔር ሀልዎት መታጣት በደረቅ ምድር ኃይለኛ ጥማት እንደ ያዘው (መዝ 42፡1-3፣ መዝ 63፡1) እና እንደ የሟች ጭንቀት ወይም ጣር ይሰማዋል (መዝ 102፡2-4)።

መዝሙረኛው ከአምላክ እንደተለየ ሆኖ ስለተሰማው ራሱን ብቻዋን ከሆነች ወፍ ጋር ያነጻጽራል። “እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ ተጋሁ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁኝ” (መዝ. 102:6፣ 7)።

ምድረ በዳ መጠቀሱ ከአምላክ የመገለልን ስሜት አጉልቶ ያሳያል። አንዲት ወፍ “በሰገነት ላይ ብቻዋን” ከጎጆዋ፤ ከማረፊያዋ ውጭ ነው ያለችው። መዝሙረኛው “ከጥልቅ ውስጥ” በኃይለኛ የውሃ ሞገድ እየተዋጠ እና “በጥልቅ የረግረግ ጭቃ” እየሰመጠ እንዳለ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል (መዝ 69፡1-3፤ መዝ 130፡1)። እነዚህ ምስሎች በመለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ካልሆነ በስተቀር ማምለጫ የሌለበትን ጨቋኝ ሁኔታ ያሳያሉ።

መዝ 10:12፣ መዝሙ 22:1፣ ​​መዝ 27:9 እና መዝ 39:12 ያንብቡ። መዝሙረኛው ለአምላክ መራቅ ምን ምላሽ ሰጠ?



መዝሙረኞቹ አምላክ ዝም ቢልም ዝም ላለማለት መወሰናቸው የሚያስደንቅ ነው። መዝሙረኞቹ ያለማወላወል በጸሎት ያምናሉ፣ ምክንያቱም ጸሎት የሚቀርበው ወደ ሕያው እና ቸር አምላክ ስለሆነ ነው። የእግዚአብሔር ሀልዎት በማይሰማን ጊዜም እንኳ እርሱ እዚያው አለ። እርሱ ጥንት የሰማቸው ያው አምላክ ነውና አሁንም እንደሚሰማቸው እርግጠኛ ናቸው። የእግዚአብሔር የዝምታ ጊዜያት መዝሙረኞቹ እራሳቸውን በጥልቀት እንዲመረምሩና በመናዘዝ እና በትህትና እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ አድርጎአቸዋል።

እግዚአብሔር ለዘላለም ዝም እንደማይል ያውቃሉ። መዝሙራት ሕይወት በምንም ዓይነት ሁኔታዎች ቢሆን ከእግዚአብሔር ጋር የሐሳብ ልውውጥ መቀጠል እንዳለበት ይገልጻሉ።

መዝሙረኛው የአምላክ ሀልዎት አለመኖርን አስመልክቶ ከሰጠው ምላሽ ምን እንማራለን? እግዚአብሔር ዝም ያለ በሚመስልዎ ጊዜ ምን ምላሽ ይሰጣሉ? እምነትዎን ሊደግፍ የሚችለው ምንድን ነው?

ጥር 22
Jan 31

ቃል ኪዳኑ ለዘላለም ከሽፏልን?


መዝሙር 77ን ያንብቡ። ደራሲው በምን አይነት ልምምድ መካከል እያለፈ ነው?



መዝሙር 77 የሚጀምረው ያለፈውን በሐዘን የተሞላ እና የሚያሳዝን ሁኔታ በማስታወስ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ነው (መዝ 77፡1-6)። መዝሙረኛው የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት በሙሉ ማንነቱ በሀዘን ወደ እግዚአብሔር ተመልሶአል። ከእግዚአብሔር ከሚመጣው መጽናናት በስተቀር በማንኛውም መንገድ ሊጽናና አልፈለገም።

ይሁን እንጂ እግዚአብሔርን ማስታወስ ጭንቀቱን የሚያባብስ ይመስላል።

“እግዚአብሔርን ባሰብኩ ጊዜ አለቅሳለሁ” (መዝ 77:3) የዕብራይስጥ ሀማ፣ “አለቀሰ”፣ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ የሚጮህ ወይም የሚያጓራ ውሃን ጩኸት ያሳያል (መዝ 46፡3)።

በተመሳሳይ፣ የመዝሙረኛው ሙሉ ማንነቱ በከባድ ሁከት ውስጥ ነው።

አምላክን ማስታወሱ ይህን የመሰለ ከባድ ጭንቀት ሊፈጥር የሚችለው እንዴት ነው? ተከታታይ የሚያስጨንቁ ጥያቄዎች ለጭንቀት እንዲጋለጥ መንስኤ ሆነዋል (መዝ 77፡7–9)። አምላክ ተለውጧልን? እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን ሊክድ ይችላልን?

ቀደም ባሉት ጊዜያት በነበሩ የአምላክ የማዳን ሥራዎች እና በአሁኑ ጊዜ በሚታየው የእግዚአብሔር ሀልዎት አለመኖር መካከል ያለው ልዩነት መዝሙረኛው በአምላክ እንደተተወ እንዲሰማው አድርጎታል። አምላክ ከተለወጠ መዝሙረኛው ምንም ተስፋ የለውም፣ ስለዚህ ውሳኔውን ለመቀበል ይገደዳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጌታ ነቅቶ እንዲቀር ስለሚያደርገው መዝሙረኛው መተኛት አይችልም (መዝ 77፡4) ። ይህ እንቅልፍ ማጣት እግዚአብሔር ዓላማውን ለማራመድ እንደ ቅድመ ዝግጅት የተጠቀመባቸውን ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ገፀ-ባህሪያትን ያስታውሳል (ዘፍ 41፡1-8፣ አስቴር 6፡1፣ ዳን 2፡1-3)። የመዝሙረኛው ረጅም እንቅልፍ የማጣት ሌሊት የጌታን ያለፈውን የማዳን ሥራ በአዲስ ውሳኔ እንዲያስብ ያደርገዋል (መዝ 77፡5፣ 10)።

መዝሙረኛው ከእግዚአብሔር የተቀበለው ማረጋገጫ ስለ ግላዊ ሁኔታው ​ ማብራሪያ የያዘ አይደለም፣ ይልቁንም የእግዚአብሔር ታማኝነት እና እምነት የሚጣልበት የመሆኑ (እንደ ኢዮብ) ማረጋገጫ ነው። መዝሙረኛው እግዚአብሔር ጥንት ለእስራኤል ተአምራትን ያደረገ ያው አምላክ መሆኑን አውቆ በእምነት ጌታን እንዲጠብቅ ተበረታትቶአል (መዝ 77፡11-18)።

በተጨማሪም መዝሙረኛው የእርሱ መገኘት ለሰው ዓይን ግልጽ በማይሆንባቸው ሁኔታዎች ውስጥም እንኳ ሆኖ “አረማመድህም አልታወቀም ነበር” (መዝ 77፡19) በማለት የአምላክን አመራር ይገነዘባል። መዝሙረኛው እግዚአብሔር በተመሳሳይ ጊዜ የተገለጠ እና የተደበቀ መሆኑን እውቅና ሰጥቶአል፣ ስለዚህ ለጌታ ምስጢራዊ እና ሉዓላዊ አሰራር ምስጋና አቅርቧል። ጌታ በህይወትዎ ውስጥ የሰራበትን ያለፈውን ጊዜ ያስቡ። ይህ እውነት አሁን የሚያጋጥሙዎትን ማናቸውንም ነገሮች እንዲቋቋሙ የሚረዳዎ እንዴት ነው?

ጥር 23
Feb 01

ጻድቃን እንዳይፈተኑ


መዝ 37:1፣ 8፤ መዝ 49:5-7፤ መዝ 94:3–7፤ እና መዝ 125:3 መዝሙረኛው ምን ዓይነት ትግል አጋጥሞታል? ምን ዓይነት ትግል አጋጥሞታል?



እነዚህ መዝሙሮች የኃጥአን መበልጸግና ይህ እውነታ በጻድቃን ላይ የሚያመጣውን ተግዳሮት በሀዘን ያንጎራጉራሉ። ክፉዎች መበልጸግ ብቻ ሳይሆን አንዳንዴም እግዚአብሔርን ይንቃሉ፣ ሌሎችንም ይጨቁናሉ። ግራ የሚያጋባው ጉዳይ “የክፋት በትር” (መዝ 125:3) ዓለምን ሲቆጣጠር፣ “የጽድቅ በትር” (መዝ 45:6) አቅም ያጣ ይመስላል። ታዲያ ለምን እንደ ሌሎች ተስፋ ቆርጠን ክፋትን አንቀበልም? መዝሙር 73:1–20፣ 27ን ያንብቡ። መዝሙረኛውን በችግር ውስጥ እንዲያልፍ ያደረገው ምንድን ነው? በከንቱ ነገር የሚታመኑ መጨረሻቸው ምንድር ነው? (1 ጴጥ. 1:17ን ይመልከቱ።)



መዝሙረኛው በመዝሙር 73 ላይ ያተኮረው በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ባለው ኃጢአት ላይ ቢሆንም፣ ከአምላክ እይታ አንጻር ትልቁን ገጽታ ማየት አልቻለም። የክፋት ማበብ በእምነቱ ላይ ያመጣው ችግር በጣም ብዙ ነበር፤ ስለ እምነቱ ከንቱነት ያቀረበው ክርክር በእውነታው ላይ የተመሰረተ እንደሆነም ያምን ነበር።

ይሁን እንጂ መዝሙር 73 “የዚህን መዝሙር የመጀመሪያ ጥቅስ ችላ በሚሉ ሰዎች ያፌዝባቸዋል፤ እርሱም የመዝሙሩ ማጠቃለያ፡ ‘ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው!’” ይላል።— Johannes Bugenhagen, Reformation Commentary on Scripture (Downers Grove, IL:InterVarsity Press, 2018), p. 11 የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

መዝሙረኛው የእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ ስፍራ ወደሆነው ወደ ቤተ መቅደስ በመመራት “ዛሬ” የሚለው ቃል የስዕሉ ትንሹ ክፍል ብቻ እንደሆነ እንዲያስታውስ የተደረገ ሲሆን ክፉዎች የእግዚአብሔርን ፍርድ የሚጋፈጡበትን “ፍጻሜውን” ማጤን ነበረበት። መዝሙረኛው በመቅደሱ ውስጥ ይህንን እውነት ተረድቶ የቀደመውን ሞኝነት መናዘዙ የሚያሳየው እውነታውን ማስተዋል የሚቻለው በመንፈሳዊ እይታ ብቻ እንጂ በሰው አመክኒዮ እንዳይደለ ነው።

አሁን በአለም ላይ ያለው ሁሉ ክፋት የሚቀጣበት የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን መምጣት የሚያፅናናዎት እንዴት ነው?

ጥር 24
Feb 02


ተጨማሪ ሀሳብ


፦ መዝሙር 56ን ያንብቡ። ኤለን ጂ. ዋይት፣ “በጌታ መደሰት፣” ገጽ 115–126፣ ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ

እንደ መዝሙረኛው ሁሉ፣ በሁሉም ዘመን የነበሩ የአምላክ ሕዝቦች የጌታን መዝሙር “በባዕድ አገር” እንዴት መዘመር እንደሚችሉ ዘወትር ይገረሙ ነበር። በሉዓላዊ አምላክ አገዛዝ ላይ ያለን እምነት አንዳንድ ጊዜ በከባድ ሁኔታ ይፈተናል፣ እግዚአብሔር ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት በእውነት ኃያል፤ መልካም እና ሁሉን በመቆጣጠር ላይ ስለመሆኑ በጥልቅ ልናሰላስል እንችላለን።

መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ብዙውን ጊዜ እርግጠኛ አለመሆን እና ጥርጣሬ እንዳለ ሁሉ መተማመን እና እርግጠኝነት እንዳለ ይነግረናል። አንዳንድ ጊዜ እርግጠኛ አለመሆን እና ጥርጣሬ፣ በተለይም በክፋት ፊት እና በእግዚአብሔር ሀልዎት መታጣት ውስጥ ሊቋቋሙት የማይችሉአቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ሆኖም፣ እርግጠኛ አለመሆን በፍፁም በእግዚአብሔር፣ አፍቃሪ እና ጻድቅ ባህሪው እና ታማኝነቱ ላይ መሆን የለበትም። መዝሙረኞቹ ስለ ወደፊቱ ጊዜ እርግጠኛ ላይሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ የማይጠፋውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ታማኝነት ይማጸናሉ (መዝ 36፡5–10፤ መዝ 89፡2፣ 8)።

እኛም ተመሳሳይ ምሳሌን እንከተል። “ወደ ታች ወደ ችግርህ ሳይሆን ሃይልህን ሁሉ አሰባስበህ ወደ ላይ ተመልከት፤ ይህን ስታደርግ በመንገድ ላይ ፈጽሞ አትደክምም።

ከደመናው ጀርባ ኢየሱስ አንተን ለመርዳት እጁን ሲዘረጋ ወዲያውኑ ታያለህ። አንተ ማድረግ ያለብህ ነገር ቢኖር በቀላል እምነት እጅህን ለእርሱ መስጠት እና እርሱ እንዲመራህ ፈቃደኛ መሆን ነው። በእርሱ ላይ ሙሉ እምነትህን ስትጥል፣ በኢየሱስ በማመን በተስፋ የተሞላህ ትሆናለህ።”—Ellen G. White፣ Testimonies for the Church፣ vol. 5፣ p 578፣ 579

እግዚአብሔር ‘ፊቱን የሚሰውርበት’ ጊዜ የጸሎትን ፍቱንነት አያሳንሰውም።

በተቃራኒው፣ እነዚህ አጋጣሚዎች መዝሙረኞቹ ራሳቸውን በጥልቀት እንዲመረምሩ፣ ያለፈውን የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራዎች እንዲያስታውሱ እና እግዚአብሔርን በመናዘዝ እና በትሕትና ልብ እንዲፈልጉ አድርጎአቸዋል (መዝ 77፡10–12፣ መዝ 89፡ 46-52) ። “እምነት ጥንካሬ የሚኖረውና የሚያድገው ከጥርጣሬዎች እና ከተቃራኒ ተጽዕኖዎች ጋር ሲጋጭ ነው። በእነዚህ ፈተናዎች ውስጥ የተገኘው ተሞክሮ በጣም ውድ ከሆኑ ጌጣጌጦች የበለጠ ዋጋ ያለው ነው።”—Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 3, p. 555።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. መዝሙረኛው ክፋት በገጠመው ጊዜ ምን ውጥረት አጋጥሞት ነበር? ምን ተመሳሳይ መዝሙረኛው ክፋት በገጠመው ጊዜ ምን ውጥረት አጋጥሞት ነበር? ምን ተመሳሳይ ውጥረቶች አጋጥሞዎታል? ይህንስ እንዴት ተወጡት? በእነዚህ ጊዜያት እምነትዎን እንዴት ይጠብቃሉ?

2. በአምላክ ላይ ያለን እምነት በፈተናዎች ወይም የራሳቸው መከራ የእግዚአብሔርን በአምላክ ላይ ያለን እምነት በፈተናዎች ወይም የራሳቸው መከራ የእግዚአብሔርን መልካምነትና ኃይል እንዲጠራጠሩ ባደረጋቸው ሰዎች ሲፈተን መልሱን መፈለግ ያለብን ከየት ነው?

3. ሁሉን ቻይ በሆነው የፍቅር አምላክ በተፈጠረ እና ተደግፎ በሚኖረው ዓለም ውስጥ ሁሉን ቻይ በሆነው የፍቅር አምላክ በተፈጠረ እና ተደግፎ በሚኖረው ዓለም ውስጥ ስላለው ስለ ክፋት የተለመደ ጥያቄ እንዴት ይመልሳሉ? የታላቁ ውዝግብ ጭብጥ ለዚህ ፈተና እንዴት መልስ ሊሰጥ ይችላል?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL