የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- መዝ 139:1–18፤ መዝሙረ ዳዊት 121፤ መዝ 17:8፤ ማቴ 23:37፤ 1 ቆሮ 10:1–4፤ ዕብ 4:15፣ 16
የመታሰቢያ ጥቅስ፡- ጻድቃን ጮኹ እግዚአብሔርም ሰማቸው
ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው (መዝሙር 34:17)
አጽናፈ ዓለምን የፈጠረው እና ደግፎ ያቆመው ሉዓላዊው ጌታ፣ ከህዝቡ ጋር
ግንኙነትን የመፍጠርና እና የመደገፍ ተነሳሽነትን የሚወስድ የግል አምላክ እንደሆነ
አድርጎ ራሱን የሚገልጥ አምላክ የመሆኑን እውነት መዝሙረ ዳዊት በተደጋጋሚ
ገልጿል። እግዚአብሔር በሰማይና በምድር ላሉ ሕዝቦቹና ለፍጥረታቱ ቅርብ ነው (መዝ
73፡23፣ 25)። እርሱ “ዙፋኑን በሰማይ ያጸና” ቢሆንም (መዝ 103፡19) እንዲሁም “በደመና
ላይ ቢቀመጥም” (መዝ 68:4) እርሱ ደግሞ “ለሚጠሩት ሁሉ በእውነት ለሚጠሩት ቅርብ
ነው” (መዝ 145፡18)። መዝሙራት ጌታ ሕያው አምላክ፣ ለሚጠሩትም የሚሠራ የመሆኑን
እውነት ያለማወላወል ያረጋግጣሉ (መዝ 55፡16-22)። መዝሙራት እንዲጻፉ ያደረገው
እርሱ ስለሆነ እና መዝሙሮቹም የሚቀርቡት ጸሎትን ሰምቶ ወደሚመልስ ሕያው አምላክ
ስለሆነ በትክክል ትርጉም ያላቸው ናቸው።
ለጌታ ቅርበት ትክክለኛውን ምላሽ መስጠት በእርሱ የማመን ሕይወትን እና
ለትእዛዛቱ መታዘዝን እንደሚያካትት ማስታወስ አለብን። በእስራኤል ታሪክ ብዙ ጊዜ
እንደተገለጸው ከዚህ እምነት እና ታዛዥነት ያነሳ ምንም ነገር በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት
አይኖረውም።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለጥር 18 ሰንበት ይዘጋጁ።
መዝሙር 139:1–18ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔርን ኃይል (መዝ 139:1- 6)፣ መገኘት (መዝ 139:7-12) እና መልካምነቱን (መዝ 139:13-18) የሚገልጸው እንዴት ነው? የእግዚአብሔር ታላቅነት ስለ ተስፋዎቹ ምን ይላል?
አንድን ሰው መርዳት ፈልገው ነገር ግን አቅም አጥተው ያውቃሉ? በተመሳሳይ
ሁኔታ አንዳንድ ሰዎች ሊረዱዎ ቢሞክሩም ፍላጎትዎን ሊረዱ አይችሉም። እጅግ በጣም
አፍቃሪ እና ጥሩ ልብ ካላቸው ሰዎች በተለየ፣ እግዚአብሔር እኛን ለመርዳት መንገዶች
አሉት፤ እንዲሁም ስለ እኛና ስለ ሁኔታዎቻችን ፍጹም የሆነ እውቀት አለው ። ስለዚህ፣
የእርሱ የእርዳታ እና የማዳን ተስፋዎቹ ጥልቀት የሌላቸው ገለጻዎች ሳይሆኑ ጽኑ
ማረጋገጫዎች ናቸው።
እግዚአብሔር ስለ መዝሙረኛው ያለው እውቀት ታላቅ እና ልዩ ከመሆኑ የተነሳ
የእናቱ ማኅፀን እንኳ ከእግዚአብሔር ሊሰውረው አልቻለም (መዝ 139፡13፣ 15)። መለኮታዊ
እውቀት ከጊዜ (መዝ 139:2)፣ ከውስጣዊ ማንነት (መዝ 139:2፣ 4) እና ቦታ (መዝ 139:3)
--ከመዝሙረኛው አጠቃላይ መኖር ጋር ይገናኛል። የእግዚአብሔር አስደናቂ እውቀት
የፈጣሪነቱ እና ከሰዎች ጋር ያለው የቅርብ ትውውቅ ውጤት ነው፤ ይህም ለእነርሱ ባለው
እንክብካቤ ውስጥ ይገለጣል።
እግዚአብሔር እኛን በቅርበት የማወቁ ይህ አስደናቂ እውነት ሊያስፈራን ሳይሆን
ወደ ኢየሱስ እቅፍ ሊያስገባን እና በመስቀል ላይ ያደረገልን ነገር ወደ እርሱ ሊያቀርበን
ይገባል። በኢየሱስ በማመን የእርሱ ፅድቅ ማለትም “የእግዚአብሔር ጽድቅ” ተሰጥቶናል
(ሮሜ 3:5፣ 21)።
የአምላክን መገኘት እስከ “ሲኦል” (ሲኦል፣ “መቃብር”) እና “ጨለማ” (መዝ
139:8፣ 11፣ 12) እንደሚደርስ ተደርጎ ተገልጾአል፤ ይህ ማለት እነዚህ ቦታዎች አምላክ
የሚኖርባቸው ቦታዎች ናቸው ለማለት ግን አይደለም (መዝ 56: 13)። የእርሱ መገኘት
እስከ “የባሕር ዳርቻዎች” (ምእራብ) ድረስ ለመድረስ “የማለዳ ክንፎችን” (ምስራቅ)
(መዝ 139፡9) እንደመውሰድም ተደርጎ ተገልጾአል። እነዚህ ምስሎች የሚያስተላልፉት
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
መልእክት በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ከእግዚአብሔር ልንሰወር የምንችልበት ምንም ቦታ
ያለመኖሩን እውነታ ነው። አንዳንዶች እንደሚያምኑት፣ ምንም እንኳን እግዚአብሔር
የአጽናፈ ዓለም አካል ባይሆንም፣ ፈጣሪው ብቻ ሳይሆን ደግፎ የሚይዘውም ስለሆነ
ለእርሱ ቅርብ ነው (ዕብ 1፡3 ይመልከቱ)።
ስለ እኛ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ እንደመሆኑ መጠን ሊረዳንና እንደገና ሊያድሰን
ይችላል። የእርሱን ታላቅነት እንደ አዲስ መገንዘቡ ከመዝሙረኛው ውስጥ ምሥጋና ፈንቅሎ
እንዲወጣ በማድረግ እምነቱን ያድሳል። ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ዝምድና የሚረብሽ
ማንኛውንም ነገር ከህይወቱ ለማስወገድ የሚያስችል ጥልቅ መለኮታዊ ፍተሻን ይቀበላል።
አንዳንዶች እግዚአብሔር ስለ እነርሱ በጨለማ የተደበቁ ምስጢሮችም ሳይቀሩ ብዙ
የሚያውቅ የመሆኑን እውነታ በጣም አስፈሪ ሆኖ ያገኙታል። ታዲያ ወንጌል ብቸኛው
ተስፋችን የሆነው ለምንድን ነው?
መዝ 40:1–3፣ መዝ 50:15፣ መዝ 55:22 እና መዝ 121ን ያንብቡ። አምላክ በዕለት ተዕለት የሕይወት ጉዳዮቻችን ውስጥ የሚገባው እንዴት ነው?
ጌታ በቅዱሳት መጻሕፍት እርሱን የሚጠሩትን ወክሎ የሚሰራ ሕያው አምላክ
እንደሆነ አድርጎ ራሱን ገልጿል። ለመዝሙረኛው፣ “እግዚአብሔር ሁል ጊዜ በፊቱ ነው”
(መዝ 16፡8) ። ስለዚህም በእግዚአብሔር ታምኖ ወደ እርሱ ይጣራል (መዝ 7፡1፣ መዝ
9፡10) ። ምንም ዓይነት የሕይወት ሁኔታ ከእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ እንደማያመልጥ
በመግለጽ ጌታ “ከጥልቅ ውስጥ” (መዝ 130: 1፣ 2) እርሱን ይሰማዋል። ስለዚህ
የመዝሙረኛው ጩኸት ምንም ያህል አጣዳፊ ቢሆንም ፈጽሞ ተስፋ ቢስ አይደለም።
መዝሙር 121 ታማኝ በሆነ ሰው ሕይወት ውስጥ በሚሰራው የፈጣሪ ኃይል ደስታውን
ይገልጻል። ይህ ኃይል የሚከተሉትን ነገሮች ያጠቃልላል፡-
(1) “እግርህን ለመናወጥ አይሰጥም” (መዝ 121፡3)። የ“እግር” ምስል ብዙውን
ጊዜ የአንድን ሰው የሕይወት ጉዞ ገላጭ ነው (መዝ 66፡9፣ መዝ 119፡105፣ ምሳ 3፡
23)። “ተንቀሳቀስ” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል እግዚአብሔር ለዓለም እና ለጽዮን
የሚያደርገውን ጥበቃ (መዝ 93፡1፤ መዝ 125፡1) ይገልጻል።
(2) የእስራኤል አምላክ እንደማይተኛ እንደማያንቀላፋም የሚገልጸው ምስል
የጌታን የማያቋርጥ ንቃት እና ልጆቹን ወክሎ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ጎላ አድርጎ
ያሳያል (መዝ. 121:3፣ 4)።
(3) እግዚአብሔር “ጥላህ” ነው (መዝ 121:5፣ 6) የሚለው አባባል ከግብጽ በወጡ
ጊዜ የነበረውን የደመና ዓምድ ወደ ትውስታ ያመጣል። በተመሳሳይ፣ ጌታ ለህዝቡ አካላዊ
እና መንፈሳዊ መጠለያ እንደሆነ ያሳያል።
(4) እግዚአብሔር በቀኛቸው ነው (መዝ 121፡5) ። ቀኝ እጅ በተለምዶ የግለሰቡን
ጠንካራ እጅ፣ የተግባር እጅን ይወክላል (መዝ 74፡11፣ መዝ 89፡13)። እዚህ ላይ
የእግዚአብሔርን ቅርበት እና ሞገስ ያሳያል (መዝ 16:8፤ መዝ 109:31፤ መዝ 110:5)።
(5) እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚሰጠው ጥበቃ በመዝ 121፡6-8 ላይ በግልጽ
ተረጋግጧል። እግዚአብሔር ልጆቹን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃል። “ፀሐይ” ወይም
“ጨረቃ” አያቃጥላቸውም። አምላክ “መውጣታቸውን” እና “መግባታቸውን”
ይጠብቃል። እነዚህ ግጥማዊ ሥዕሎች የእግዚአብሔርን ሁሉን አቀፍና የማያቋርጥ
እንክብካቤ ያጎላሉ።
ዋናው ነገር መዝሙረኛው በእግዚአብሔር የፍቅር እንክብካቤ መታመኑ ነው። እኛም
እንዲሁ ማድረግ አለብን። የእግዚአብሔርን እንክብካቤ እውነታ በተሻለ ሁኔታ ለመለማመድ
የሚያስችሉዎት አንዳንድ ተግባራዊ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? እግዚአብሔር ለእርስዎና በእርስዎ
ውስጥ በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራ ለማስቻል ከርሱ ጋር መተባበር የሚችሉት እንዴት ነው?
መዝ 17፡7–9፣ መዝ 31፡1–3 እና መዝ 91፡2–7ን ያንብቡ። መዝሙረኛው በችግር ጊዜ ምን ያደርግ ነበር?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
መዝሙረኛው የተለያዩ ችግሮች ሲያጋጥሙት በመከራዎቹ ውስጥ ከሁሉም
መከራዎች መሸሸጊያ ወደሆነው ወደ ጌታ ዘወር ይል ነበር። እምነት መጣል ማለት በሁሉም
ሁኔታዎች ውስጥ በአንድ ሰው ህይወት ላይ የእግዚአብሔርን ጌትነት ለመቀበል ሆን ተብሎ
የሚደረግ ምርጫ ነው። እምነት በመከራ ውስጥ የማይሰራ ከሆነ የትም አይሰራም።
“እግዚአብሔርን፡- እርሱ መጠጊያዬና አምባዬ ነው፤ አምላኬ፥ በእርሱ
እታመናለሁ እላለሁ’” (መዝ 91:2) የሚለው የመዝሙረኛው ምስክርነት የመነጨው
ከዚህ በፊት ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ልምምድ ሲሆን አሁን ለወደፊቱ እምነቱን
ለማጠናከር ያገለግላል። መዝሙረኛው የአምላኩን ከአእምሮ በላይ የሆኑ ታላቅነት በማሰብ
እግዚአብሔርን ልዑል እና ሁሉን ቻይ (መዝ 91:1፣2) ብሎ ይጠራዋል።
መዝሙረኛው በእግዚአብሔር ስለሚገኘው ዋስትና ሲናገር፡- መሸሸጊያ ቦታ
(“መጠለያ” ወይም “መደበቂያ ምሽግ”) “ጥላ” (መዝ 91፡1)፣ “መሸሸጊያ ቦታ፣” “ትልቅ
ምሽግ” (መዝ 91፡2)፤ “ክንፎቹ”፤ “ጋሻ”፤ “መከላከያ” (መዝ 91፡4) እና “የማደሪያ ስፍራ”
(መዝ 91፡9) ይላል። እነዚህ ምስሎች በመዝሙረኛው ባህል ውስጥ አስተማማኝ ማረፊያ
ቦታዎችን ያመለክታሉ። አንድ ሰው የጥላን አስፈላጊነትና ጥቅም ለማድነቅ በዚያ የዓለም
ክፍል ያለውን ለመቋቋም የሚከብደውን የፀሐይ ሙቀት ማሰብ ያስፈልገዋል፤ እንዲሁም
ጋሻው ወይም ምሽግ የሚሰጠውን ደኅንነት ግምት ውስጥ ለማስገባት በእስራኤል ታሪክ
ውስጥ የጦርነት ጊዜያትን ማስታወስ ያስፈልገዋል።
መዝ 17:8 እና ማቴ 23:37ን ያንብቡ። እዚህ ውስጥ የተገለጸው ምስል ለምን
አገልግሎት ጥቅም ላይ ይውላል ወይም ምን ያሳያል?
በጣም ጥልቅ ከሆኑ ዘይቤዎች አንዱ “በክንፎችህ ጥላ ሥር” መሆንን የሚያመለክት
ነው (መዝ 17፡8፣ መዝ 57፡1፣ መዝ 63፡7)። ይህ ዘይቤ የእናት ወፍ ጥበቃንና ምቾትን
በማመልከት ማረጋገጫ ይሰጣል። ጌታ ጫጩቶቹን በክንፎቹ ከሚጋርድ ንስር ጋር (ዘፀ
19፡4፣ ዘዳ 32፡11) እና ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች ከምትሰበስብ ዶሮ (ማቴ 23፡37) ጋር
ተነጻጽሯል።
ይሁንና የጌታን ጥበቃ የማናይ እስኪመስለን ድረስ መከራ በሚደርስበት ጊዜ ከነዚህ
ስጋቶች ጋር እንዴት መፋለም እንችላለን? እንደነዚህ ዓይነት አእምሮን የሚያዛቡ ጉዳቶች
ሲደርሱብን ጌታ ከኛ ጋር አይደለም ለማለት የማንደፍረው ለምንድር ነው?
1ኛ ቆሮንቶስ 10:1-4ን ያንብቡ። ጳውሎስ የዘፀአትን ታሪክ እንዴት ነው የገለፀው? በዚህ ታሪክ አማካይነት ለማስተማር የሚፈልገው ምን መንፈሳዊ ትምህርት ነው?
መዝሙር 114ን ያንብቡ። እስራኤላውያን በመለኮት ኃይል ከግብፅ ነፃ መውጣታቸው በዚህ ስፍራ በግጥም የተገለጸው እንዴት ነው?
በመዝ 114 የተሰጠው እግዚአብሔር ልጆቹን ከግብፅ ባርነት ነፃ ማውጣቱን
የሚያመለክት እንዴት ያለ ቅኔያዊ መግለጫ ነው። በብሉይ ኪዳን ዘመን ሁሉ፣ በአዲስ
ኪዳንም ቢሆን፣ ከግብፅ ነፃ መውጣት የእግዚአብሔር ሕዝቡን የማዳን ኃይል ምልክት
ተደርጎ ይታይ ነበር። ጳውሎስ በእነዚህ በቆሮንቶስ ጥቅሶች ውስጥ ሙሉውን እውነተኛ
ታሪክ እንደ ምሳሌያዊ አነጋገር በመመልከት በኢየሱስ ክርስቶስ የመዳን ምልክት አድርጎ
ገልጾታል። መዝሙር 114 እንዲሁ የእግዚአብሔር መለኮታዊነትና ሉዓላዊ አዳኝነት
በዘፀአት ህዝቡን ያዳነበት መንገድ እንደ ፈጣሪ በተፈጥሮ ኃይሎች ላይ ስልጣን እንዳለው
ያሳያል። ባሕሩ፣ የዮርዳኖስ ወንዝ ፣ ተራሮች እና ኮረብታዎች እስራኤል ወደ ተስፋይቱ
ምድር ሲሄዱ ይቃወሙ የነበሩትን የተፈጥሮ እና የሰው ሃይሎች በመወከል በግጥም መልክ
ተቀምጠዋል (ዘዳ 1፡44፣ ኢያሱ 3፡14-17)። እግዚአብሔር ግን በሁሉም ላይ ሉዓላዊ ነው።
በእርግጥ፣ በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ቦታ ለሚገኙት ለብዙዎቹ የእግዚአብሔር
ልጆች፣ ወደ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም የሚወስደው መንገድ በአደጋ የተሞላ ነው።
መዝሙረኛው ከኮረብቶች ባሻገር ያለውን የሰማይና የምድር ፈጣሪን እንዲመለከቱ
ያበረታታቸዋል (መዝ 121፡1)።
የመዝሙር 114 መንፈስ ኢየሱስ የባህርን ማዕበል ጸጥ እንዲል በማድረጉና እና
እርሱ አለምን ስላሸነፈ ቤተ ክርስቲያንን ምንም የሚያስፈራ ነገር እንደሌለ በማወጅ
ተይዟል (ማቴ 8፡23-27፣ ዮሐ 16፡33)።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
ጌታ ለሕዝቡ ያደረጋቸው ታላላቅ ሥራዎች በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ
በፊቱ እንዲንቀጠቀጡ ሊያነሳሳ ይገባል (መዝ 114፡7)። መንቀጥቀጡ በመሸበር ሳይሆን
ለእግዚአብሔር እውቅና በመስጠትና በአምልኮ መሆን አለበት (መዝ 96: 9፤ መዝ 99:1)
እግዚአብሔር ከጎናቸው ከሆነ አማኞች የሚፈሩት ምንም ነገር የለም።
እንደ አማኞች የሚያጋጥሙን አንዳንድ መንፈሳዊ አደጋዎች ምንድን ናቸው? እነዚህ
አደጋዎች ለመዝሙረኛው እውን እንደነበሩ ሁሉ አሁን ለእኛም እውን በሆኑት በእነዚህ
አደጋዎች እንዳንሸነፍ በጌታ ኃይል መደገፍን መማር የምንችለው እንዴት ነው
መዝ 3:4፤ መዝ 14:7፤ መዝ 20:1-3፤ መዝ 27:5፤ መዝ 36:8፤ መዝ 61:4; እና መዝሙር 68:5፣ 35ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንደተገለጸው እርዳታ የሚመጣው ከየት ነው?
የመንፈሳዊ እና ሥጋዊ መሸሸጊያ እና እርዳታ ጭብጥ የቀረበው በቤተ መቅደሱ
አውድ ነው። መቅደሱ የእርዳታ፣ የደህንነት እና የመዳን ቦታ ነው። መቅደሱ ለተቸገሩ
ሰዎች መጠለያ ነው። እግዚአብሔር ድሀ አደጎችንና መበለቶችን ይጠብቃል፤ ለሕዝቡም
ከመቅደሱ ኃይልን ይሰጣል። “የውበት ፍጽምና ከሆነችው ጽዮን እግዚአብሔር ሲያበራ”
(መዝ 50:2) የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርድ ይታወጅና የጌታ በረከት ይወጣል (መዝ
84:4፣ መዝ 128:5፤ መዝ 134:3)።
በመቅደሱ ውስጥ ያለው መሸሸጊያ በዓለም ላይ ያሉት ማናቸውም ስፍራዎች
ከሚሰጠው ጥበቃ ይበልጣል ምክንያቱም በመቅደስ ውስጥ እግዚአብሔር በአካል
ይኖራል። የእግዚአብሔር መገኘት፣ መቅደሱ እንደ ጽኑ ሕንፃ ብቻ ሳይሆን፣ ደህንነትን
ይሰጣል። እንደዚሁም፣ ጌታ የሚኖርበት ተራራ፣ የጽዮን ተራራ በራሱ ምንም እንኳን ልከኛ
ኮረብታ ቢሆንም ከሌሎች ተራሮች ይበልጣል (መዝ 68:15, 16፤ ኢሳ 2:2) ።
“ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ እንጂ በድካማችን ሊራራልን
የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ
የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” (ዕብ 4:15፣ 16)። እነዚህ
ጥቅሶች መዝሙረኛው ስለ መቅደሱ ከተናገረው ጋር የሚመሳሰሉት በምን መንገዶች ነው?
የእግዚአብሔር መቅደስ ቅድስና መዝሙረኛው ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች
መሆናቸውንና የእግዚአብሔር ችሮታ ፈጽሞ የማይገባቸው መሆናቸውን እና የሕዝቡ ነጻ
መውጣት በእግዚአብሔር ታማኝነት እና ጸጋ ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆኑን እንዲገነዘብ
ያነሳሳው ነበር (መዝ 143፡2፣ 9–12)። በእግዚአብሔር ፊት ሊያቀርበን የሚችል ምንም ነገር
በእኛ ውስጥ የለም። ሰዎች የእግዚአብሔርን የመዳን ማረጋገጫ የራሳቸው ሊያደርጉት
የሚችሉት በንስሐ እና የእግዚአብሔርን ጸጋና ይቅርታ በመቀበል ከእግዚአብሔር ጋር
ትክክለኛ ግንኙነት ሲኖራቸው ብቻ ነው ። የቤተ መቅደስ አገልግሎት በኢየሱስ የሚገኘውን
ድነት ይወክላል።
ኤለን ጂ ኋይት “የትግል ምሽት” በሚል ርዕስ ሥር የሰጠችውን
ሀሳብ አበው እና ነቢያት ከሚለው መጽሐፏ ገጽ 195–203ን ያንብቡ። ከያዕቆብ ተሞክሮ
ስለ ጸሎት አስፈላጊነትና በአምላክ ላይ ያለ ገደብ መታመን ስላለው ኃይል ምን እንማራለን?
መዝሙራት ሕይወታቸውን በኃያሉ አምላክ እጆቹ ለሚሰጡ ሰዎች ፈጽሞ
የማይጠፋ መሸሸጊያ በሆነው በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ያጠናክራሉ።
“እግዚአብሔር በእርሱ ለሚታመኑት ታላቅ ነገርን ያደርጋል። የእርሱ ነን የሚሉ ሰዎች
የበለጠ ጥንካሬ ያጡበት ምክንያት በራሳቸው ጥበብ በጣም ስለሚተማመኑ እና ጌታ
ለእነርሱ ሲል ኃይሉን እንዲገልጥ እድል ባለመስጠታቸው ነው። አማኝ ልጆቹ በእርሱ
ላይ ሙሉ በሙሉ የሚታመኑና በታማኝነት የሚታዘዙ ከሆነ በማንኛውም ድንገተኛ ጊዜ
ይረዳቸዋል።”—አበው እና ነቢያት ገጽ 493
ሆኖም አንዳንድ መዝሙሮች የገቡት ቃልና ያለንበት ሁኔታ የማይጣጣሙ ሲሆን
ከባድ ፈተና ሊፈጥሩ ይችላሉ። እንደዚህ ባሉ ጊዜያት፣ በመስቀል ላይ በኃይል በተገለጠው
በእግዚአብሔር ቸርነት ብቻ መታመንን መማር አለብን። በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ
መዝሙራት የውሸት ተስፋዎችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ኢየሱስ በመዝ
91:11፣ 12 ላይ ሰይጣን በተሳሳተ መንገድ ለተጠቀመበት የሰጠው ምላሽ አምላክን ከመፈተን
(ማቴ. 4:5-7) ወይም ከፈቃዱ ጋር የሚጻረር ነገር እንዲፈጽም በትዕቢት ከመጠየቅ ጋር
መምታታት እንደሌለበት ያሳያል።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
“የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ወይም ክርስቲያን የሆነ ግለሰብ ያገኛቸው ትላልቅ ድሎች
የተገኙት በችሎታ ወይም በትምህርት፣ በሀብት ወይም በሰዎች ችሮታ አይደሉም። እነዚህ
ድሎች በስውር በሚያይ አምላክ ፊት በእልፍኝ ውስጥ በቅንነት በሚውተረተረው እምነት
ኃያል የሆነውን የኃይል ክንድ በመያዝ የሚገኝ ነው።”—አባው እና ነቢያት ፣ p. 203.
1. በማክሰኞው ጥናት በመከራ ውስጥ እና ነገሮች አስከፊ በሆነ ሁኔታ ወደተሳሳተ
በማክሰኞው ጥናት በመከራ ውስጥ እና ነገሮች አስከፊ በሆነ ሁኔታ ወደተሳሳተ
አቅጣጫ ሲያመሩ ምን ማድረግ አለብን በማለት ለቀረበው የመጨረሻው ጥያቄ
በተሰጠው መልስ ላይ በክፍላችሁ ተወያዩበት። በመዝሙር ውስጥ ስለ እግዚአብሔር
ጥበቃ በተሰጡት አስደናቂ ተስፋዎች እንኳን እነዚህን ነገሮች እና በሰዎች ላይ እንዴት
ሊደርሱ እንደሚችሉ አንድ ሰው እንዴት ይገነዘባል? እስቲ ደግሞ ስለዚህ ነገር ያስቡ:-
ስለ እነዚያ አስደናቂ ተስፋዎች የጻፈው መዝሙረኛው መከራ አልደረሰበትምን
ወይስ መከራ ስለደረሰባቸው ታማኝ ሰዎች አያውቅም ነበር?
2. በሁሉም ሁኔታዎች በአምላክ ላይ ያልተቆጠበ እምነት ማዳበር የምንችለው እንዴት
በሁሉም ሁኔታዎች በአምላክ ላይ ያልተቆጠበ እምነት ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው? (ለምሳሌ መዝ 91:14፤ መዝ 143:8፣ 10፤ መዝ 145:18-20)። ይህን
የመተማመን ስሜት እንድናጣ የሚያደርገን ምንድን ነው? በመጥፎ ጊዜ በእርሱ
መታመንን ለመማር በመልካም ጊዜ በእግዚአብሔር መታመን ወሳኝ የሆነው
ለምንድን ነው?