የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት



1ኛ ሩብ ዓመት 2024


ጥር 4 - 10

3ኛ ትምህርት

Jan 13 - 19




ጌታ ይነግሳል



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት መዝ 8፤ መዝ

100፤ መዝ 97፤ መዝ 75፤ መዝ 105፡7-10፤ ገላ 3፡26- 29፤ መዝ 25፡10ን ያንብቡ።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡- እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብርንም ለበሰ፤ እግዚአብሔር ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት (መዝ 93፡1)።

መዝሙራት በእግዚአብሔር ሉአላዊ ንጉስነት መሰረታዊ እምነት ላይ በማያወላውል ሁኔታ አጽንኦት ይሰጣሉ። ጌታ ሁሉንም ፈጥሮአል፤ የፈጠራቸውን ፍጥረታት ደግሞ በሕይወት ጠብቆ ያኖራል። እርሱ በዓለማት ሁሉ ላይ ሉአላዊ ገዥ ነው፤ ዓለማትን ሁሉ በፍትህና በጽድቅ ያስተዳድራል። ሕጎቹና ስርዓቶቹ ደግሞ መልካምና ለሚጠብቁአቸው ሕይወትን የሚሰጡ ናቸው። ጌታ ዓለም በስርአት እንድትመራ በእኛ ጊዜ ሳይሆን በራሱ ጊዜ ጻድቁን እየሸለመ ኃጢአተኛውን እየቀጣ የሚያስተዳድር ትክክለኛ ዳኛ ነው።

እግዚአብሔር ከእሥራኤል ሕዝብ ጋር የገባው ቃል ኪዳን የጌታን ማዳን ስለሚያበስር ዓለምን በመጠበቅ ልዩ ሚና ይጫወታል። እግዚአብሔር እስራኤልን ከምድር አሕዛብ ሁሉ ለይቶ የራሱ ሕዝብ በማድረግ ውድ ዋጋ የተከፈለበት የራሱ ርስት አድርጎ ወስዷቸዋል። እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ነው፤ ስለሆነም ምንም እንኳን እነርሱ ታማኝ ባይሆኑም፣ አንዳንድ ጊዜ በግልጽ ቢያምጹበትም፣ እንደ መንጋው ይንከባከባቸዋል።

ስለዚህ የጌታ ሉዓላዊ አገዛዝ ዓለምን በጽኑ የተመሰረተ እና አስተማማኝ ያደርገዋል። መዝሙረኛው አንባቢው ይህንን መሰረታዊ እውነት እንዲረዳ ይፈልጋል።

መዝሙረኛው አንባቢዎቹ ይህን የዓለም አተያይ እንደ ብርሃን ማማ አድርገው በመውሰድ እንዲያድጉና እግዚአብሔርን ባልተከፋፈለ አምልኮ እንዲያገለግሉ ይፈልጋል። *የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለጥር 11 ሰንበት ይዘጋጁ። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

ጥር 5
Jan 14

ጌታ ሰራን


መዝሙር 8ንና

100ን ያንብቡ። በእነዚህ መዝሙራት እግዚአብሔርና ሕዝቡ የተገለጹት እንዴት ነው? መዝሙሮቹ ስለ እግዚአብሔር ባህርይ ምን ይገልጻሉ?



ስነ ፍጥረት በመዝሙራት ውስጥ የእግዚአብሔርን ሉአላዊነት ከፍ አድርጎ በማሳየት ወሳኝ ሚና ይጫወታል። “የእርሱ እጅ ሥራዎች” የሆኑ ሰማያት የእርሱን ክብርና ኃይል ያውጃሉ (መዝ 19፡1-4፤ መዝ 97፡6)። የእግዚአብሔር ስም በምድር ሁሉ ላይ ከፍ ብሎ የገነነ ነው (መዝ 8፡1፣9)። ጌታ ሁሉንም ነገር ፈጠረ፤ መጀመሪያ የለውም (መዝ 93፡ 2) ፍጻሜም የለውም (መዝ 102፡ 25-27)። እርሱ ዘላለማዊና “የሰው የእጅ ስራ እንጂ ምንም ባልሆኑት” በአህዛብ አማልክት ሁሉ ላይ የበላይ ነው ( መዝ 115፡4)። አማልክት “እጅ አላቸው አይዳስሱም” (መዝ 115፡7)፤ ጌታ ግን “የምድር ጥልቆች ሁሉ በእጁ ናቸው… እጆቹም የብሱን ፈጠሩ” (መዝ 95፡4፣5)።

በርካታ መዝሙራት እግዚአብሔር በተፈጥሮ ኃይላት ላይ ሥልጣን እንዳለውና ሌሎች ህዝቦችም መለኮታዊ እንደሆነ እንደሚያምኑ ያሳያል (ለምሳሌ ም 29፡ መዝ 93፣መዝ 104)። እነዚህ መዝሙሮች ጌታ በፍጥረት ሁሉ ላይ እንደሚገዛ እና በኃይል እና በክብር የበላይ ነው የሚለውን አባባል በድጋሚ ያረጋግጣሉ። መዝ

100፡3 “እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም” በማለት እግዚአብሔር እንደፈጠረን አጽንዖት ሰጥቶ በመግለጽ አንድ ስውር የጣኦት ዓይነት እንዳለ ይነግረናል፤ ያም በራስ መተማመን ነው።

ፍጥረት ደግሞ የእግዚአብሔርን ፍቅር ይመሰክራል። ያለው ሁሉ መኖር ያለበት በአምላክ ነው፣ እርሱም ሕይወትን የሚደግፍ ነው(መዝ 95፡7፤ መዝ 147፡4-9)።

እግዚአብሔር ለሰዎች መኖርን ብቻ የሰጠ ሳይሆን የጥንቱን እስራኤልን “ሕዝቡና የማሰማርያው በጎች” እንዳደረጋቸው አስተውል (መዝ

100፡3)። “ህዝቡ” እና “በጎቹ” የሚለው አስተሳሰብ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመመሥረት ያለውን ፍላጎት ያሳያል።

ህዝቡን የመባረክ እና የመጨመር ሃይል ያለው ፈጣሪ ብቻ ነው። ስለዚህም ሊመለክና እና ሊታመኑበት የሚገባው እርሱ ብቻ ነው ። ብዙ መዝሙራት እስትንፋስ ያለው ሁሉ፣ ምድር ሁሉ፣ ባሕርና በውስጡ ያለው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በደስታ እልል እንዲሉ ጥሪ ያቀርባሉ።

የእግዚአብሔር ክብር በፍጥረት ውስጥ፣ በወደቀው ምድራዊ ፍጥረትም ቢሆን፣ ይታያል። መዝሙረ ዳዊትም አምልኮ የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ይጠቁመናል።

“ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጎበኘውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?“ (መዝ. 8:4)። እንደ ፈጣሪህ ለእግዚአብሔር ምላሽህ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ከዋክብትን በስማቸው ሲጠራ (መዝ 147፡4) ለእርስዎ ከዚያ የበለጠ ምን ያህል የሚያስብልዎ ይመስልዎታል?

ጥር 6
Jan 15

ጌታ ይገዛል


እንደ ፈጣሪነቱ ከጌታ ጋር በቅርበት--በእርግጥም በማይነጣጠል መልኩ ተሳስሮ ያለው የእርሱ ሉዓላዊ ገዥነት ነው። “እግዚአብሔር ነገሠ” የሚለው መግለጫ በመዝሙር 93፡1፣ መዝ 96፡10፣ መዝ 97፡1 እና መዝ 99፡1 ላይ በጥብቅ ታውጇል፣ ነገር ግን የእርሱ ድምጽ በመላው መዝሙረ ዳዊት ውስጥ እያስተጋባ ይሰማል።

ጌታ ክብርን፣ ግርማን እና ብርታትን ለብሷል (መዝ 93፡1፣ መዝ 104፡1)። እርሱ በደመናና በጨለማ ተከቧል (መዝ 97፡2)፣ ነገር ግን ራሱን “እንደ ልብስ በብርሃን ይሸፍናል” (መዝ 104፡2)። እነዚህ ዘይቤዎች የንጉሱን ኃይል እና ግርማ ከፍ የሚያደርጉ ሲሆን በጥንቃቄ የተመረጡት ከሰው መረዳት በላይ የሆነውን የእግዚአብሔርን ልዩ ታላቅነት ለመግለጽ ነው።

መዝሙር 97ን ያንብቡ። የጌታን አገዛዝ ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ( መዝ 97:2፣ 10) የግዛቱ ወሰን ምንድን ነው?( መዝ 97:1፣ 5፣ 9)



የጌታ አገዛዝ በፍጥረት ሥራው (መዝ 96፡5)፣ በድነት ሥራው (መዝ 98፡2) እና በፍርድ ሥራው (መዝ 96፡10) ተገልጧል። ጌታ ንጉሥነቱን በዓለም ሁሉ ላይ ያጸናል (መዝ 47፡6-9)። የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይልና በግርማ ወደር የሌለው ዘላለማዊ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት መንግሥት ነው (መዝ 45:6፤ መዝ 93:1፣ 2፤ መዝ 103:19)። የጌታ አገዛዝ በምህረት፣ በፍትህ እና በጽድቅ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ለተፈጠረው አለም ስርአትን እና መረጋጋትን ያመጣል (መዝ 98:3፤ መዝ 99:4)። የእግዚአብሔር መንግሥት ሰማያዊ እና ምድራዊ አምላኪዎችን በእግዚአብሔር ውዳሴ አንድ ያደርጋል (መዝ 103፡20-22፣ መዝ 148)።

ብዙ መዝሙራት የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ አገዛዝ እውቅና እንደሚሰጡ ያመለከታሉ (መዝ 96፡10፣ መዝ 97፡1፣ መዝ 99፡1፣ መዝ 145፡11–13)።

ነገር ግን ሰዎች ሁሉ፣ ወይም ምድራዊ ገዥዎችም ቢሆኑ፣ ቢያንስ ለጊዜው ለእግዚአብሔር ሉአላዊ መንግሥት እውቅና አይሰጡም። የጌታን መንግስት በሚክዱ፣ በሚሳለቁ እና ህዝቡን በሚጨቁኑ ክፉ ሰዎች የእግዚአብሔር ገዥነት ዘወትር ተቃውሞ ይደርስበታል (መዝ 14: 1፤ መዝ 74: 3-22)። ምንም እንኳን በአንዳንድ ክፉ ሰዎች ብልጽግና ግድድሮሽ ያጋጠመው እና በእግዚአብሔር ትዕግስት ምክንያት የተቸገረ ቢሆንም መዝሙረኛው በእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ ታምኖ በእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርዶች መተማመኛ አግኝቶ ማደጉን ይቀጥላል። የእግዚአብሔር ሰዎች በክርስቶስ የመቤዠት አገልግሎት የእግዚአብሔር መንግሥት በመመስረቱ በእምነት ደስታ የሚሰማቸው ሲሆን በክርስቶስ ዳግም ምጽዓት የሚሆነውን የመንግሥቱን ፍጻሜ ይጠባበቃሉ (ማቴ 12፡26-

28፣ 1ቆሮ 15፡20-28)።

“እግዚአብሔርን የምትወዱ ክፉን ጥሉ!” (መዝ 97:10)። ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ክፋትን እንድንጠላ የሚያደርገን ለምንድን ነው? እነዚህ ሁለት ጽንሰ-ሐሳቦች እንዴት ይዛመዳሉ?

ጥር 7
Jan 16

እግዚአብሔር ፈራጅ ነው


መዝ 75ን ያንብቡ። የክፉዎች ትምክህት ከንቱ የሆነው ለምንድን ነው?



እንደ ሉዓላዊ ንጉሥ፣ ጌታ ሕግ ሰጪ (መዝ 99፡7) እና ፈራጅም ነው (መዝ 98፡ 9፣ መዝ 97፡2)። ክፉዎች እግዚአብሔር በዓለም ላይ ባቋቋመው ፍትሐዊ ሥርዓት ላይ ያለማቋረጥ ስጋት ይፈጥራሉ፤ እግዚአብሔር ግን በዓለም ላይ በመፍረድ የክፉውን አገዛዝ ወደ ፍጻሜው ያመጣዋል (መዝ 75፡8-10፣ መዝ 96፡13)።

በመዝሙር 75 ላይ ያሉ በርካታ ምስሎች ክፉዎች ለማያዳግም ጥፋት እንደሚዳረጉ ያሳያሉ። ቀይ ወይን ያለበት የጽዋ ምስል (መዝ 75፡8) የእግዚአብሔርን ቁጣ መጠን ያሳያል (ኤር 25፡15፣ ራእ 14፡10)። የኃጥኣን ቀንዶች መቆረጥ የኃይላቸውንና የግዛታቸውን ፍጻሜ የሚያሳይ ሲሆን የጻድቃን ቀንዶች ከፍ ከፍ ይላሉ (መዝ 75፡10)። እግዚአብሔር ለፍርዱ “ትክክለኛውን ጊዜ” (መዝ 75፡2) ወይም “የተወሰነውን ጊዜ” ይመርጣል። ይህ ፍርድ በዘመን ፍጻሜ ላይ በግልጽ የሚፈጸም ነው (መዝ 96፡13፣ 1ቆሮ 15፡23-26)።

ጌታ እንደ የፍርዱ አካል አድርጎ የሰዎችን ልብ ይመረምራል። መዝ 14:2ን ያንብቡ።

ዘፍጥረት 6:5፣8ን ያስታውሳል። ሁለቱም ጽሑፎች እንደሚያሳዩት የእግዚአብሔር ፍርድ በዓለም ላይ ከመፈጸሙ በፊት እግዚአብሔር የሰዎችን ሕይወት እንደሚመረምርና ማዳን የሚችለውን ማንንም ቢሆን እንደሚፈልግ ነው። እግዚአብሔር ለጻድቃን ሲሟገት እና የክፉዎችን እጣ ፈንታ ሲወስን ይህ ፍርድ አንዳንዴ “የፍርድ ምርመራ” ይባላል። ይህ የሚሆነው እንዴት ነው?

በመጀመሪያ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከክፉዎች እጅ በማዳን (መዝ 97፡10፣ መዝ 146፡9) ለትሑታን የድነት አክሊል ይደፋላቸዋል (መዝ 149፡4)። ሁለተኛ፡- ንስሐ የማይገቡ ክፉዎች ለዘላለም ይጠፋሉ (መዝ 97፡3)። አንዳንድ መዝሙሮች በመለኮታዊው ዳኛ ላይ የሰው መሳሪያ ጥቅም እንደሌለው በግጥም ይገልፃሉ (መዝ 76፡3-6)።

ጌታ ሰዎችን በበደላቸው ቢቀጣም ይቅር ባይ አምላክ ነው (መዝ 99፡8) ።

ኃጢአተኞች ብቻ ሳይሆኑ፣ የእግዚአብሔር ሕዝብም ለእግዚአብሔር መልስ ይሰጣሉ (መዝ 50፡4፣ መዝ 135፡14)።

መዝሙራቱ የእግዚአብሔር ፍርድ በእግዚአብሔር ሕዝብ እንደሚጀምርና ከዚያም ወደ ምድር ሁሉ እንደሚስፋፋ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ የተገለፀውን ተመሳሳይ ሃሳብ ያስተላልፋሉ (ዘዳ 32፡36፣ 1 ጴጥ 4፡17)። መዝሙረኛው ለፍርድ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል፣ ነገር ግን እንደ መከላከያ በእግዚአብሔር ጽድቅ ይመካል (መዝ 7፡8-11፤ መዝ 139፡23፣ 24)።

መዝሙራት የእግዚአብሔርን ፍርድ በመጠባበቅ እንድንደሰት ጥሪ ያደርጉልናል (መዝ 67:4፣ መዝ 96:10-13፣ መዝ 98:4-9)። የአምላክ ፍርድ በክርስቶስ ደም ለተሸፈኑ ሰዎች የምሥራች የሆነው እንዴት ነው? የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

ጥር 8
Jan 17

ስለ ቃል ኪዳኑ ሁል ጊዜ የሚያስብ


የእግዚአብሔር ፍርድ ጭብጥ አንድ ጉልህ ጥያቄ ያስነሳል፡- የእግዚአብሔር ሕዝቦች በፍርድ ጊዜ ከአምላክ ጋር ሰላምና የመዳን ዋስትና እንዴት ሊያገኙ ይችላሉ? መዝ 94፡ 14፣ መዝ 105፡7-10፣ ዳን 7፡22 ያንብቡ።



እግዚአብሔር ማደሪያውን በጽዮን ስላደረገ (መዝ76:1፤ 2) እና የዘላለም ቃል ኪዳኑን እንደ ውድ ርስት አድርጎ ከእነርሱ ጋር ስለጸና የእግዚአብሔር ሕዝብ ደኅንነታቸው የተረጋገጠ ነው። እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕዝቡን እንዳይቀበል የሚያደርግ ተራ ቃል አልገባም፤ ደህንነታቸው በእርሱ የተጠበቀ እንዲሆን ተግቶ ይሰራል። ኃጢአታቸውን ይቅር ይላል (መዝ 103፡3)። ሕዝቡን ያስተምራል፣ ይባርካል፣ ያበረታታልም (መዝ 25፡ 8-11፣ መዝ 29፡11፣ መዝ 105፡24)። የእግዚአብሔር ፍርዶች የተሰጡት ሰዎችን ወደ ጽድቅ ለመመለስ እና እግዚአብሔር እንደሚያስብላቸው ለማሳየት ነው (መዝ 94፡8-15)።

መዝሙር 105 በአጠቃላይ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ጌታ ለቃል ኪዳኑ ያለውን ታማኝነት ያሳያል። በሆነው ነገር ሁሉ፣ በመልካሙም ሆነ በክፉው፣ እግዚአብሔር በዚያ ነበር። በእርሱ ዘንድ ባለው እቅድ ዮሴፍን ወደ ግብፅ በመምራት በእርሱ አማካይነት ሕዝቡንና በዚያ አካባቢ ያሉትን አሕዛብ ከከባድ ረሃብ አዳናቸው (መዝ 105፡16-24)።

እግዚአብሔር ተአምራትና ድንቅ እያደረገ ሕዝቡን ከግብፅ ባርነት እንዲያወጣ ሙሴን አስነሳ (መዝ 105፡25-38)።

ጌታ ለህዝቡ የተስፋይቱን ምድር ሰጣቸው(መዝ 105፡11፣44)፤ የማያቋርጥ ጥበቃም አደረገላቸው (መዝ 105፡12-15)። በቁጥርም አበዛቸው (መዝ 105፡24)፣ በላያቸው ከሰለጠኑባቸው አለቆች ነፃ አወጣቸው (መዝ 105፡37፣ 38)፣ የዕለት ተዕለት ፍላጎታቸውንም አሟላላቸው (መዝ 105፡39-41)። ጌታ ህዝቡን በሚመለከት ነገር ሁሉ ሉዓላዊ ቁጥጥር እንዳለው ጥርጥር የለውም—ህዝቡ ይህን እውነት እንዳይረሳ መዝሙረኞቹ ይፈልጉ ነበር።

እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን በሚያስታውስበት ጊዜ ሁሉ ወደ ተግባር ስለሚመራ ከማወቅ ወይም ከማስታወስ በላይ ነው (ዘፍ 8:1፣ 1 ሳሙ 1:19፣ መዝ 98:3፣ መዝ 105:42– 44)። በተመሳሳይ ሁኔታ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ተአምራት እና ፍርድ እንዲያስታውሱ ጥሪ ሲደረግላቸው ህዝቡ ለእግዚአብሔር ክብር መኖር አለባቸው ማለት ነው።

በዚህ ቃል ኪዳን ውስጥ፣ የእስራኤል ዋና ጥሪ የእግዚአብሔርን ህግጋት በመጠበቅ ለቃል ኪዳኑ ታማኝ መሆን ነው (መዝ 78፡5-7፣ መዝ 105፡45) ። ደግሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ ለሌሎች አሕዛብ ስለ እግዚአብሔር እንዲመሰክሩ ተጠርተዋል፣ ለዚህ ምክንያቱ ሕዝቦች ሁሉ የእርሱ ሕዝብ የሆነውን እስራኤልን እንዲቀላቀሉ እግዚአብሔር ስለሚፈልግ ነው (መዝ 105፡1፣ 2)። በዚህ ሁኔታ ዓለም ሁሉን ቻይና መሐሪ በሆነው አምላክ ጥበቃ ቃል ኪዳን ውስጥ አስተማማኝ ዋስትና ያገኛል (መዝ 89፡28-34)።

እነዚህ ለጥንቷ እስራኤል የተገቡት ተስፋዎች በእኛ ላይ ሊሠሩ የሚችሉት ለምን እንደሆነ ሊያሳይ የሚችል በኢየሱስ ውስጥ ምን አለን? (ገላ 3:26–29ን ይመልከቱ።)

ጥር 9
Jan 18

ምስክርነቶችህ በጣም እርግጠኛ ናቸው


መዝ 19:7፤ መዝ 93:5፤ መዝ 119:165፤ መዝሙረ ዳዊት 1:2፣ 6፤ መዝሙረ ዳዊት 18:30 እና መዝ 25:10ን ያንብቡ። ሁሉም ምን የጋራ ትስስር አላቸው?



ጌታ በዓለም ላይ እንደ ሉዓላዊ ፈጣሪ፣ ንጉስ እና ዳኛ የበላይ መሆኑ ለምስክርነቶቹ አስተማማኝነት ሥነ-መለኮታዊ አንድምታ አለው። ምስክነቶቹ (በዕብራይስጥ ‘edut፣ “አዋጅ”፣ “ሕግ”) ጌታ የሕዝቡን ሃይማኖታዊ እና ማኅበራዊ ሕይወት የሚመራበት የሕግ እና የሥርዓት አካል እንደሆነ ያመለክታሉ (ዘጸ 32፡15)። የእግዚአብሔር ዙፋን የማይነቃነቅ እና ዘላለማዊ መሆኑን እንዲሁም ዓለምን እግዚአብሔር እንደፈጠረው እና የሚደግፈውም እርሱ እንደሆነ ስለሚያንጸባርቁ “በጣም እርግጠኛ” ናቸው (መዝ 93: 5)። “እርግጠኛ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል (አሜን የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ከዚህ ቃል የተገኘ ነው) አስተማማኝነትን፣ ታማኝነትን እና ጽኑነትን ያመለክታል (2ኛ ሳሙ. 7፡16፣ 1ኛ ዜና 17፡23) ። የእግዚአብሔር ህግጋት የማይለወጡ እና የማይሻሩ ናቸው።

እግዚአብሔር ለቃሉ እና ለትእዛዛቱ ታኣማኒነት ማረጋገጫ ይሰጣል።

የእግዚአብሔር ታማኝነት ለማይለወጠው የህጉ ባህሪ ዋስትና የሚሰጥና ህዝቡ ሙሉ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት በሙሉ በእግዚአብሔር እንዲታመኑና እንዲታዘዙት የሚጠይቅ ነው።

በተመሳሳይ፣ በዓለም ላይ ያለው የፍትህ እጦት የምድርን መሠረት እንደማናወጥ ተደርጎ በግጥም መልክ ተገልጿል (መዝ 18፡7፣ ኢሳ 24፡18–21)። የእግዚአብሔር ሕግ ሰዎች የእግዚአብሔርን ፍርድ ሊቋቋም በሚችል የጽድቅ ሕይወት መንገድ ያስተምራቸዋል።

ስለዚህ ጻድቃን ጽኑነትን እና ደህንነትን በሚሰጠው በእግዚአብሔር ህግ ላይ ጸንተው ስለተመሰረቱ እና ልባቸው ጽኑ ስለሆነ አይናወጡም (በዕብራይስጥ ኩን ማለት ደግሞ በጌታ “ጽኑ፣” “የተደላደለ”) ማለት ነው (መዝ 112:1፣ 6፣ 7)። የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቁትን የሚያሰናክላቸው ምንም ነገር የለም (መዝ 119:165)። ይህም የእግዚአብሔርን ጥበቃ እና የሕይወት ምሪትን ያመለክታል (መዝ 1: 2፣ 3፣ 6)።

የእግዚአብሔር ቃል ለመዝሙረኛው እንደ የእግር መብራት ሆኖ ተገልጿል፣ ስለዚህም በጠላቶች ከተሰወረ ወጥመድ ይጠብቀዋል (መዝ 119፡105፣ 110)።

የእግዚአብሔርን ሕግ የሚወዱ (መዝ 119፡165) የሚያገኙት ታላቅ ሰላም፣ ከፈተናዎች ሙሉ በሙሉ ነጻ በመሆን የተገኘ እንዳልሆነ ግልጽ ነው (መዝ 119፡161)። ይልቁንም በእግዚአብሔር ፊት ከመኖር እና ከእርሱ ጋር ጤናማ ግንኙነት ከመመሥረት የተገኘ ነው።

የእግዚአብሔርን ህግጋት፣ ደንቦችን እና ምስክርነቶችን መጠበቅ በህይወትዎ የረዳዎ ተግባራዊ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? በሌላ በኩል፣ እነርሱን በመጣስዎ ምን ተጎዱ?

ጥር 10
Jan 19


ተጨማሪ ሀሳብ


መዝ 86:5፣ 15፤ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ ከሚለው የኤለን ጂ ዋይት መጽሐፍ፣ “እግዚአብሔር ለሰው ያለው ፍቅር፣” በሚለው ርዕስ ሥር ገጽ 9-15፣ ያንብቡ። እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚለው እውነት በመዝሙራት ውስጥ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ድርጊቶቹ የተሰጡ የተለያዩ መግለጫዎችን የበለጠ እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው?

የዚህ ሳምንት ጥናት ዓለምን በሚመሰርቱና ጽኑና አስተማማኝ በሚያደርጉ በአንዳንድ ቁልፍ የእግዚአብሔር መግለጫዎችና ተግባራት ላይ ያተኩራል። መዝሙረኞቹ ፈጣሪ፣ ንጉስ፣ ዳኛ፣ የቃል ኪዳን አዳኝ እና ህግ ሰጪ ወደሆነው እግዚአብሔር ይማጸናሉ።

በዚህ ዓለም ውስጥ እግዚአብሔር የሚኖረው ሚናዎች በሌሎች እንደ እረኛ (መዝ 23፡1፣ መዝ 80፡1)፣ የደህንነት ዓለት (መዝ 95፡1) እና አባት ( መዝ 68፡5፣ መዝ 89፡26) ባሉ ሌሎች የተለያዩ የእግዚአብሔር ስሞችና ማዕረጎች ተንጸባርቀዋል። እግዚአብሔር ሉአላዊ ስለሆነ እና በሚያደርጋቸውና በሚናገራቸው ነገሮች ሁሉ ታማኝ ስለሆነ በአለም ውስጥ በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ እንኳን ደህና እና ደኅንነታችን የተረጋገጠልን ልንሆን እንችላለን። ምንም እንኳን እነዚህ ሥነ-መለኮታዊ ጭብጦች በምንም መልኩ የተሟሉ ባይሆኑም፣ እግዚአብሔር በመዝሙር ውስጥ ራሱን የገለጠባቸውን የተለያዩ መንገዶች የሚጠቁሙ ናቸው።

መዝሙራትን ማጥናታችንን ስንቀጥል፣ በእግዚአብሔር የፍቅር እና የጸጋ ባህሪ እና አለምን ለማዳን እና ለማደስ ባለው እቅድ መሰረት ማጥናት አስፈላጊ ነው። “በመስቀሉ ብርሃን መለኮታዊውን ባሕርይ ባጠናን ቁጥር ምሕረትን፣ ርኅራኄን እና ይቅርታን ከእኩልነትና ከፍትሕ ጋር ተዋህደው እያየን እንሄዳለን፣ እናም አንዲት እናት ለዓመፀኛ ልጇ በምታሳየው ርኅራኄ ዓይነት የማያልቅ እና ርኅራኄው የላቀ ፍቅርን የሚያሳዩ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ማስረጃዎች በግልጽ እንገነዘባለን ።”—ኤለን ጂ ዋይት፣ ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ ገጽ 15። በመዝሙራት ውስጥ፣ ሰዎች በአመፃቸው ምክንያት የእግዚአብሔርን ፍርድ ሲጋፈጡ ቢታዩም፣ የእግዚአብሔር ቁጣ ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደሆነ፣ ምሕረቱ ግን ዘላለማዊ እንደሆነ ስለሚያውቁ እግዚአብሔርን መጥራታቸውን ቀጥለዋል (መዝ 103፡8)።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. ምንም እንኳን በዓለማችን ውስጥ ብዙ ብጥብጥና መከራ እንዳለ ብንረዳም ምንም እንኳን በዓለማችን ውስጥ ብዙ ብጥብጥና መከራ እንዳለ ብንረዳም በታላቁ ተጋድሎ እውነታና መስፋፋት የእግዚአብሔርን የበላይ ገዥነትና ሉዓላዊነት መረዳታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የታላቁ ተጋድሎ መሪ ሃሳብ ለእኛ በጣም ጠቃሚ የሆነው ለምንድነው?

2. አምላክ ፈጣሪ እንደሆነ ማመን ስለ ራሳችን ያለንን ግንዛቤና ከሌሎች ፍጥረታት ጋር አምላክ ፈጣሪ እንደሆነ ማመን ስለ ራሳችን ያለንን ግንዛቤና ከሌሎች ፍጥረታት ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያስተካክለው እንዴት ነው? ሰዎች ከዚያ እውነት ሲወጡ ምን ይሆናል (መዝ 106፡35-42)?

3. በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የአሕዛብ ጣዖታት ምን ችግር ነበረባቸው (መዝ 115፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የአሕዛብ ጣዖታት ምን ችግር ነበረባቸው (መዝ 115፡ 4-8)? ዘመናዊ ጣዖታትስ? ለእኛስ ከጌታ ጋር ለምናደርገው ጉዞ አደገኛ የሚሆኑት እንዴት ነው?

4. የእግዚአብሔር ሰዎች የእግዚአብሔር ፍርድ የሚጀምረው በሕዝቡ መሆኑን እያወቁ የእግዚአብሔር ሰዎች የእግዚአብሔር ፍርድ የሚጀምረው በሕዝቡ መሆኑን እያወቁ እንዴት መኖር አለባቸው? እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ የሚፈርደው እንዴት እና እስከ ምን ድረስ ነው?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL