የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት



1ኛ ሩብ ዓመት 2024


ታህሣሥ 27 - ጥር 3

2ኛ ትምህርት

Jan 6 - 12




ፀሎትን አስተምረን



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት መዝ. 105፡5፤ ቆላ. 3፡16፤ ያዕ. 5፤ መዝ. 44፤ መዝ. 22፤ መዝ. 13፤ መዝ. 60፡1-5ን ያንብቡ።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡- እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው። (ሉቃ 11፡1)።

እውነተኛ ጸሎት ሳይታሰብ በድንገት እንዲሁም ያለ ትምህርት የሚደረግ ጸሎት ብቻ ነው የሚለው እምነት በአንዳንድ ክርስቲያኖች ዘንድ ተስፋፍቶ ይታያል። ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ፀሎት እንዲያስተምራቸው የጠየቁት ጥያቄ እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ ሽልማት ይዞላቸው መጣ። እግዚአብሔር የፀሎት መጽሐፍ የሆነውን መዝሙረ ዳዊት በመጽሐፍ ቅዱስ ልብ ውስጥ ያስቀመጠው ዝም ብሎ በጥንት ዘመን የነበሩ ሕዝቦቹ እንዴት ይፀልዩ እንደነበር ለማሳየት ሳይሆን እኛም ዛሬ እንዴት መፀለይ እዳለብን ለማስተማር ነው።

ከቀደምት ዘመናት ጀምሮ የመዝሙር መጽሐፍ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ጸሎት የኢየሱስንም ጭምር አቃንቶአል (1ዜና 16፡7፣9፤ ነህ 12፡8፤ማቴ 27፡46፤ኤፌ 5፡ 19)። በዚህ ሳምንት ጥናታችን መዝሙር የእግዚአብሔርን ሕዝብ በጉዞአቸው እንዴት እንዳሻገራቸውና ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዴት እንዳሳደገላቸው እንመለከታለን። መዝሙራት ጸሎቶች ስለሆኑ ስነ-መለኮታዊ መረዳትን ስለሚሰጡ ብቻ ሳይሆን የግል እና የጋራ ጸሎታችንንም ስለሚለውጡና ስለሚያዳብሩ ትልቅ ዋጋ እንዳላቸው ማስታወስ ይገባናል።

በመዝሙራት የተጻፈውን ጸሎት መጸለይ ብዙ ክርስቲያኖች መደበኛ የጸሎት ሕይወታቸውን እንዲያዳብሩ እና እንዲያደላድሉ መሰረት ጥሎላቸዋል። በዚህ ሳምንት መዝሙራትን ማጥናታችንን ስንቀጥል በተለይም ነገሮች እኛ እንደምንፈልገው ሳይሄዱ ሲቀሩ ምን ማድረግ እንዳለብን እንመለከታለን። *የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለጥር 4 ሰንበት ይዘጋጁ

ታህሣሥ 28
Jan 07

መዝሙራትን በጸሎት ውስጥ መጠቀምን ማደፋፈር


መዝ 105፡5፤ ቆላ 3፡16 እና ያዕ 5፡13ን ያንብቡ። መዝሙራት በአማኞች የአምልኮ ልምምድ ውስጥ ያላቸው ቦታ ምንድር ነው?



መዝሙራትን በየቀኑ ህይወታችን ውስጥ ለመለማመድ ቀላሉ መንገድ የመዝሙር መጽሐፍን ከምእራፍ አንድ ጀምሮ በመዝሙረኛው በተሰጠው መመሪያ መሰረት ለማጥናት ጊዜ መስጠት ነው። ሌላኛው መንገድ ደግሞ እያለፍንበት ያለው ሁኔታ ምንም ቢሆን እያለፍንበት ካለው አሁናዊ ሁኔታ ጋር በማመሳሰል ማጥናት ነው። የሰቆቃ መዝሙሮች፤ በጋራ የሚዘመሩ መዝሙሮች፤ የምስጋና መዝሙሮች፤ የውዳሴ መዝሙሮች፤ የንስሃ መዝሙሮች፤ የጥበብ መዝሙሮች (የእግዚአብሔርን ጥበብና ምሪት ለመጠየቅ)፤ ታሪካዊ መዝሙሮች፤ ቁጣንና ብስጭትን የያዙ መዝሙሮች፤ እና የመናኝ ጉዞ መዝሙሮች አሉ። በዚህ ሩብ ዓመት ጥናታችን ከእነዚህ መዝሙሮች ብዙዎቹን የምንዳስስ ሲሆን በቀረቡበት አውድ እናጠናቸዋለን።

ታዲያ መዝሙሮቹን የምናነበው እንዴት ነው?

በመጀመሪያ ቀለል ባለ ሁኔታ በማሰላሰል ያንብቡና ከዚያም ይጸልዩ።

መዝሙሩን መልሶ መላልሶ ማንበብ (ማመንዠግ) በመዝሙሩ የተለያዩ ገጽታዎች ላይ፣ መዝሙረኛው እግዚአብሔርን ባቀረበበት ሁኔታና ለጸሎቱ ምክንያት በሆኑ ነገሮች ላይ ማሰላሰልን ያካትታል። የእርስዎ ሁኔታ ከመዝሙረኛው ልምምድ ጋር እንዴት ሊመሳሰል እንደሚችልና እና መዝሙሩ እርስዎ ልምምድዎን እንዲናገሩ እንዴት ሊረዳዎ እንደሚችል ያገናዝቡ። ከዚያም ካነበቡት ነገር ጋር እራስዎን ምን ያህል ጊዜ ለመስማማትና ለማዛመድ እንደሞከሩ በመመልከት ይደነቃሉ።

በመዝሙሩ ላይ የሚገዳደርህ አንድ ነገር የሚያጋጥምህ ከሆነ፣ ለምሳሌ መዝሙሩ እያጋጠመህ ስላለው ነገር ያለህን የተሳሳተ ተስፋ ያስተካክል እንደሆነ አስብ። የመዝሙሩን መልእክት በክርስቶስ ማንነት እና የማዳን ስራ ብርሃን እንዲሁም የክርስቶስ ስራ በሚሰጠን የረጅም ጊዜ ተስፋ ላይ አሰላስል። እንደምናውቀው ወይም ማወቅ እንዳለብን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ነገሮች ሁል ጊዜ በክርስቶስ እና በመስቀል ብርሃን መመልከት ይረዳል። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

እንዲሁም፣ መዝሙሩ የሚያቀርባቸውን አዲስ የጸሎት ተነሳሽነቶችን ይፈልጉና እነዚህ ተነሳሽነቶች ለእርስዎ፣ ለቤተ ክርስቲያንዎ እና ለአለም ያላቸውን ጠቀሜታ ያስቡ።

እግዚአብሔር ቃሉን በልብዎ እና በአእምሮዎ ላይ እንዲያደርግ ይጠይቁ። መዝሙሩ ከምታውቁት ሰው ሁኔታ ጋር የሚዛመድ ከሆነ ስለዚያ ሰው በጸሎት አማልዱ። ዋናው ቁም ነገር መዝሙረ ዳዊት ብዙ የሕይወት ዘርፎችን ስለሚሸፍን እኛም እነዚህ መዝሙሮች የሚሉንን ነገር በማንበብና ወደ ልባችን በማስረጽ ራሳችንን ማበልጸግ እንችላለን።

“የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ” (ቆላ. 3:16) ማለት ምን ማለት ነው? ለዚያ ተሞክሮ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የመጀመሪያው እና በጣም አስፈላጊው እርምጃ የሆነው ለምንድን ነው?

ታህሣሥ 29
Jan 08

በችግር ጊዜያት መታመን


ሁሉም ክርስቲያኖች በተስፋ መቁረጥ እና በስቃይ ጊዜያት፣ እግዚአብሔር ምን እያደረገ እንደሆነ ወይም እነዚህ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ለምን እንደፈቀደ ባለማወቅ ግራ የተጋቡባቸውን ጊዜያት ያውቃሉ፣ ተለማምደውታልም። መዝሙረኞቹ ራሳቸው ተመሳሳይ ነገር አጋጥሞአቸው ነበር።

እናም፣ በመለኮታዊ አነሳሽነት፣ ያጋጠሟቸውን ነገሮች መዝግበዋል። መዝሙር 44ን ያንብቡ። ምን እያለን ነው? ይህ በሁሉም ዘመናት ላሉ አማኞች ገጣሚ የሆነው ለምንድር ነው?



በቤተ ክርስቲያን የአምልኮ አገልግሎቶች ውስጥ የመዝሙራት ተመራጭነት ብዙውን ጊዜ በጋራ ጸሎታችን ውስጥ የምንገልጻቸውን ስሜቶች እና ቃላት የማያካትት መሆኑን ያንፀባርቃል። እንዲህ ያለው ቁጥብነት ጨለማ የሆኑ የህይወት እውነታዎችን ለመጋፈጥ ያለመቻላችን ወይም ምቾት የማጣታችን ምልክት ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ መከራ ሲደርስብን እግዚአብሔር ፍትሃዊ እንዳልሆነ ሊሰማን ቢችልም በሕዝብ አምልኮ ወይም በግል ጸሎታችን ጊዜ ሐሳባችንን መግለጹ ተገቢ ሆኖ አናገኘውም።

ይህ ዳተኝነታችን የአምልኮን ነጥብ እንድናጣ ሊያደርግ ይችላል። በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ስሜታችንን እና አመለካከታችንን በሐቀኝነት እና በግልፅ አለመግለጽ ብዙውን ጊዜ ለራሳችን ስሜቶች እስራኞች እንድንሆን ያደርገናል። ይህ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ መተማመን እና እምነት እንዳይኖረን ያደርጋል። መዝሙራትን መጸለይ፣ ስንጸልይ እና ስናመልክ፣ ልምዳችንን መንቀፍ ወይም መካድ እንደማይጠበቅብን ማረጋገጫ ይሰጣል።

ለምሳሌ መዝሙር 44 አምላኪዎች ያለ ጥፋታቸው ያጋጠማቸውን ስቃይ በነፃነትና በበቂ ሁኔታ እንዲገልጹ ሊረዳቸው ይችላል። መዝሙራትን መጸለይ ሰዎች በጸሎት የመናገር ነፃነት እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። መዝሙረ ዳዊት ልናገኛቸው የማንችላቸውን ወይም ለመናገር የማንደፍራቸውን ቃላት ይሰጡናል። “ልባችን አልተመለሰም፥ አካሄዳችንም ከመንገድህ ፈቀቅ አላለም። አንተ ግን በቀበሮዎች ስፍራ ክፉኛ ሰበርኸን በሞት ጥላም ከደንኸን” ( መዝ. 44:18, 19)።

ይሁን እንጂ መዝሙር 44 እንዴት እንደሚጀምር ልብ እንበል። ጸሃፊው እየተናገረ ያለው በጥንት ጊዜ እግዚአብሔር ለህዝቡ እንዴት ታላቅ ነገር እንዳደረገ ነው። ስለዚህም ጸሐፊው እምነቱ በእግዚአብሔር ላይ እንጂ “በቀስቱ” እንዳልሆነ እየገለጸ ነው(መዝ. 44: 6)።

ይህ ቢሆንም፣ አሁንም ችግር በአምላክ ሕዝቦች ላይ መጥቶአል። የዋይታውና የሰቆቃው ዝርዝር ረጅም እና የሚያም ነው። ነገር ግን፣ በዚህ ሁሉ መካከል እንኳን፣ መዝሙረኛው እግዚአብሔር እንዲያድነው “ስለ ምህረትህ ተቤዠን” በማለት ይጮኻል፣ (መዝ. 44፡26። ይህ ማለት፣ በችግር ውስጥም ቢሆን፣ የእግዚአብሔርንና የማዳን የፍቅሩን እርግጠኝነት ያውቃል።

የአምላክ መገኘት በጣም እውን ሆኖ ሲሰማዎ ወዳለፉት ጊዜያት መቅረብ፣ ችግሮች አምላክ የራቀ እንደሆነ እንዲያስቡ የሚያደርጉዎትን ጊዜ እንዲቋቋሙ የሚረዳዎት እንዴት ነው?

ታህሣሥ 30
Jan 09

የተስፋ መቁረጥ መዝሙር


በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ያሉ ጸሎቶችን መድገም አምላኪዎች ጸሎታቸውን በነፃነት እንዲናገሩ ከማስቻል የበለጠ ነገር ያደርጋል። መዝሙራት በእግዚአብሔር መመዘኛዎች መሰረት ልምዳቸውን በመቆጣጠር የእግዚአብሔርን መገኘት ተስፋ እና ማረጋገጫ በማስተዋወቅ ቀላል ያደርጉታል።

መዝሙር 22ን ያንብቡ። ከዚህ መዝሙር በታላቅ መከራ መካከል በእግዚአብሔር ስለመታመን ምን እንማራለን?



የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

በመዝሙር 22:​1 ላይ የሚገኙት የሐዘን ቃላት መከራ የደረሰባቸው ሰዎች ሐዘናቸውንና የብቸኝነት ስሜታቸውን እንዲገልጹ ሊረዱዋቸው ይችላሉ:- “አምላኬ፣ አምላኬ፣ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከመርዳትና ከጩኸቴ ቃል ለምን ራቅህ?“

እነዚህ ቃላት ኢየሱስ ራሱ በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው ቃላት ስለሆኑ እና መዝሙሮቹ ምን ያህል የክርስቶስ ልምምድ ማዕከል እንደሆኑ ስለሚያሳዩን በክርስቲያኖች ዘንድ የታወቁ ሆነዋል (ማቴ. 27፡46ን ይመልከቱ)።

ይሁን እንጂ፣ በመከራና በፈተናዎች መካከል እንኳን የሚከተሉት ቃላት ተነግረዋል፡ - “ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ፤ በጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ ( መዝ. 22:22)።

በሌላ አገላለጽ፣ ምንም እንኳን እነዚህ ትክክለኛ ስሜቶች ደራሲው አሁን ካለበት እንቆቅልሽ ጋር ላይስማሙ ቢችሉም፣ መዝሙረኛው አሁንም በአምላክ ላይ ያለውን እምነት በመግለጽ ምንም ቢሆን አምላክን እንደሚያወድስ ያውጃል።

ዋና ነጥቡ መዝሙራት እንድንጸልይ ቃላትን በመስጠት፣ አሁን ካለንበት ሁኔታ ባሻገር እንድንመለከትና በእምነት ሕይወታችን በእግዚአብሔር ጸጋ የሚታደስበትን ጊዜ እንድናይ ያስተምረናል።

ስለዚህ መዝሙራትን መጸለይ አምላኪዎችን ወደ አዲስ መንፈሳዊ አድማስ ይወስዳቸዋል። መዝሙረ ዳዊት አምላኪዎች ስሜታቸውን እና ግንዛቤያቸውን እንዲገልጹ፣ ነገር ግን አሁን ባሉበት እንዳልተተው እንዲገነዘቡ ያስችላቸዋል። አምላኪዎቹ የመከራ፣ የብስጭት፣ የቁጣ እና የተስፋ መቁረጥ ሸክማቸውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲተው እና ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን በእርሱ እንዲታመኑ ይመሩአቸዋል።

በብዙ መዝሙራት ላይ የተስተዋለው ከዋይታ ወደ ውዳሴ የሚደረገው እንቅስቃሴ አማኞች በጸሎት መለኮታዊ ጸጋንና መጽናናትን ሲያገኙ የሚያጋጥማቸውን መንፈሳዊ ለውጥ የሚያሳይ ነው።

አሁን ምንም ነገር ቢገጥመንም፣ እየገጠሙን ካሉ ፈተናዎች ባሻገር ማየትን እና በአምላክ ቸርነት መታመንን መማር የምንችለው እንዴት ነው?

ጥር 1
Jan 10

ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ


ሁላችንም ምናልባት የእግዚአብሔር መገኘት ከእኛ በጣም የራቀ የሚመስሉ ጊዜያት አጋጥመውን ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ ያላሰበ ማን አለ? ______________________________________________________ ______________________________________________________

መዝሙረኞቹ፣ እንደ እኛው ሰብአዊ ፍጡራን የሆኑ፣ በእርግጠኝነት ተመሳሳይ ነገሮች አጋጥመዋቸዋል። አዎን፣ አንዳንድ ጊዜ ኃጢአታችን ፈተናዎችን ቢያመጣብንም፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ ፍትሐዊ ያልሆነ ይመስላል፣ እናም አሁን እያጋጠመን ያለው ነገር ሊደርስብን የማይገባን ሆኖ ይሰማናል። እንደገና፣ እንደዚያ ያልተሰማው ማን ነው? መዝሙር 13ን ያንብቡ። በዚህ መዝሙር ውስጥ የትኞቹን ሁለት ዋና ስሜቶች መለየት መዝሙር 13ን ያንብቡ። በዚህ መዝሙር ውስጥ የትኞቹን ሁለት ዋና ስሜቶች መለየት ይችላሉ? በመዝሙረኛው አጠቃላይ አመለካከት ላይ ሥር ነቀል ለውጥ ያመጣው ምን ውሳኔ ይመስልዎታል?



“አቤቱ እስከ መቼ ነው? ለዘላለም ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?“ (መዝ 13:1)። ታዲያ፣ እነዚህ ስሜቶች ስህተት ቢሆኑም የማይጋራቸው ማን ነው? (አምላክ ማናችንንስ ቢሆን ይረሳል?)

እንግዲያውስ መዝሙር 13 ሌላ የተለመደ ስህተት፣ እርሱም በጸሎት ጊዜ በራሳችንና በችግሮቻችን ላይ ማተኮርን፣ ማስወገድ የምንችልበትን መንገድ ይጠቁማል።

ይህ መዝሙር እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ባለው ግንኙነት ታማኝ እና የማይለወጥ ባህሪይ ያለው መሆኑን እንድናረጋግጥ በመምራት ጸሎታችንን ሊለውጥ ይችላል።

እርግጥ ነው፣ መዝሙሩ በሐዘንና በቅሬታ ቢጀምርም፣ በዚህ አያበቃም።

ይህ ወሳኝ ነጥብ ነው። መዝሙሩ ፍርሃትና ጭንቀታችን (መዝ. 13፡1-4) ቀስ በቀስ ለእግዚአብሔር ማዳን መንገድ ይለቅ ዘንድ፤ ከማልቀስ ወደ ማመስገን፣ ከተስፋ መቁረጥ ወደ ተስፋ መለወጥ እንድንጀምር (መዝ. 13፡5፣6) ሆን ብለን በእግዚአብሔር የማዳን ኃይል ለመታመን ወደመምረጥ ይመራናል (መዝ. 13፡5)። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

ይሁን እንጂ የመዝሙረኛውን ቃላት ትርጉማቸውን በውል ባለመረዳት መደጋገም ብቻ የታሰበውን ትክክለኛ ለውጥ አያመጣም። መዝሙረ ዳዊትን በምንጸልይበት ጊዜ፣ መዝሙሩ በሚጠይቀው መንገድ እንድንሠራ መንፈስ ቅዱስን መፈለግ አለብን።

መዝሙረ ዳዊት የአማኞች ባህሪ እና ተግባር የሚለወጥበት የእግዚአብሔር ቃል እንጂ ተራ መረጃ አይደለም። በእግዚአብሔር ፀጋ፣ የመዝሙር ተስፋዎች በአማኞች ሕይወት ውስጥ ተገልጠዋል። ይህም ማለት የእግዚአብሔር ቃል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲቀርጸን እና ሥጋ ለብሶ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሙላት ከገለጠውና መዝሙረ ዳዊት ውስጥ ያሉ የጸሎት መዝሙራትን ከጸለየው ከክርስቶስ ጋር አንድ እንዲያደርገን እንፈቅዳለን።

ፈተናዎችዎ ይበልጥ ወደ አምላክዎ እንዲቀርቡ የሚያደርጉት እንዴት ነው? ካልተጠነቀቁስ ከእርሱ ሊያርቁዎ የሚችሉት ለምንድር ነው?

ጥር 2
Jan 11

አቤቱ እንደገና መልሰን


መዝ 61፡1-5ን ያንብቡ። ይህ መዝሙር ለምን ዓይነት ጊዜያት ገጣሚ የሚሆን ጸሎት ይመስልዎታል? በደስታ የተሞሉ የሕይወት ጊዜያት እንኳን ከሀዘን መዝሙራት ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?



የሀዘን መዝሙሮች በአካላዊ፤ በስነልቦናዊ ወይም በመንፈሳዊ ወይም በሶስቱም ዓይነት መከራ ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች ጸሎት እንደሆነ ይስተዋላል።

የሆነ ሆኖ እነዚህን መዝሙሮች በመልካም ጊዜያት ማስወገድ አለብን ማለት ግን አይደለም። አንዳንድ ጊዜ የመዝሙሩ ሀሳብና የአምላኪው አሁናዊ ሁኔታ የማይገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ማለት የሀዘን መዝሙሮች በመከራ ውስጥ ላልሆኑ አምላኪዎችም ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ ማለት ነው።

በመጀመሪያ፣ መከራ አጠቃላይ የሰብአዊ ዘር ልምምድ አካል እንደሆነ እና ይህም ደግሞ ለጻድቁም ለኃጢአተኛውም ሊደርስ እንደሚችል ግንዛቤ ይሰጡናል።

መዝሙራቱ እግዚአብሔር ሁሉን ነገር እንደሚቆጣጠርና በመከራ ጊዜያት ብርታትንና መውጫ መንገዶችን እንደሚያዘጋጅልን ማረጋገጫ ይሰጡናል። በመከራ መካከል እንኳን (“ምድርን አናወጥካት” መዝ 60፡2፣6) በሚለው በዚህ መዝሙር እንኳን፣ መዝሙረኛው በእግዚአብሔር ማዳን ያለውን የመጨረሻ ተስፋ አሳይቷል።

በሁለተኛ ደረጃ፣ የለቅሶ መዝሙራት ለሚሰቃዩት ርህራሄ እንዲኖረን ያስተምሩናል። ለእግዚአብሔር በተለይ በጉባኤ ምስጋናችንንና ደስታችንን ስንገልጽ እድል ያልቀናቸው እንዳሉ ልንረሳ አይገባም። በእርግጥም ነገሮች ለኛ መልካም ሆነው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በዙሪያችን ሁሉ ከምናስበው በላይ በመከራ ውስጥ የሚያልፉ እንዳሉ ማን ሊዘነጋ ይችላል? እንደዚህ ዓይነት መዝሙሮችን መዘመር በከባድ ጊዜያት ውስጥ በማለፍ ላይ ያሉትን እንዳንረሳ ይረዳናል። መዝሙሮቹ ልክ እንደ ኢየሱስ በመከራ ውስጥ ያሉትን እንድንረዳቸው በውስጣችን መሻትን ሊያስከትሉ ይገባቸዋል።

“ይህ ዓለም የብዙ መከራ መፍለቂያ ነው፤ ነገር ግን ኢየሱስ በሽተኞችን ሊፈውስና የሰይጣንን ምርኮኞች ነጻ ሊያወጣቸው መጣ። እርሱ በራሱ ጤናና ብርታት ነበር።

ሕይወቱን ለበሽተኞች፤ ለሚሰቃዩት፤በአጋንንት ለታሰሩት አካፈላቸው። ፈዋሽ ኃይሉን ለመቀበል ከመጡት ማናቸውንም ወደ ኋላ አልመለሳቸውም። እነዚያ ለእርዳታ ወደ እርeሱ የመጡት በራሳቸው ላይ በሽታ እንዳመጡ ያውቅ ነበር፡ር ነገር ግን ማናቸውንም ለመፈወስ እንቢ ብሎ አያውቅም። ኃይል ከኢየሱስ ወጥቶ ወደ እነዚህ ምስኪን ነፍሳት ሲገባ ኃጢአተኛ መሆናቸውን ይገነዘቡ ነበር፤ ስለዚህ ብዙዎች ከአካላዊና ከመንፈሳዊ ደዌአቸው ተፈወሱ። ወንጌል አሁንም ተመሳሳይ ኃይል አለው፤ ታዲያ ለምንድር ነው ዛሬ ተመሳሳይ ውጤቶች የማይታዩት?”- Ellen G. White, Welfare Ministry, pp. 24, 25 አሁን፣ በዚህ ሰዓት፣ ጸሎትዎ ብቻ ሳይሆን የአርስዎ የአገልግሎት መንካት የሚያስፈልገው የሚያውቁት ሰው ማነው?

ጥር 3
Jan 12


ተጨማሪ ሀሳብ


መዝሙር 42፡8ን እና ስነ-ትምህርት ከሚለው መጽሐፍ “ስነ- ግጥምና መዝሙር“ የሚለውን ሀሳብ ገጽ 159-168 (በእንግሊዝኛ) ላይ ያንብቡ። በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፉ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጸሎትና መዝሙር የተገናኙት እንዴት ነው?

ዳዊት ንስሃ የገባበትን መዝሙር (ለምሳሌ መዝሙር 51ን) ኤለን ኋይት እንደ የነፍሱ ቋንቋና ለኃጥአት የማዘን እውነተኛ ሁኔታ እንደሆነ ትገልጻለች (ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ ገጽ 24፣25 በእንግሊዝኛው)። አማኞች ከመዝሙራት ጥቅሶችን በአእምሮአቸው እንዲያሰላስሉና በህይወታቸው የእግዚአብሔርን ህልዎት እንዲለማመዱ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት እንዲሁም አስፈሪ ፍርሃትና ፈተና ህይወቱን በሚያናውጥ ጊዜ ኢየሱስ ያደርግ እንደነበረ ሁሉ ድምጻቸውን በመዝሙር ከፍ እንዲያደርጉ ታደፋፍራለች። እንደገና የሚከተለውን አስተያየት ትሰጣለች፡- “በቅዱስ ዝማሬ ቃላት አማካይነት በነፍስ ውስጥ የንስሃና የእምነት፤ የተስፋና የፍቅር እና የደስታ ምንጮች የተከፈቱት ምን ያህል ጊዜ ነው!... በእርግጥ አብዛኛው መዝሙር ጸሎት ነው።” ስነ ትምህርት 162-168።

መዝሙራትን ስንጸልይና ስንዘምር የመዝሙረኞቹ የአቋም ጽናት፤ ግልጽነት፤ ጉብዝና እና ተስፋ ምን ያህል እንደሆነ እንገምታለን። መንፈሳዊ ጉዞአችንን እድንቀጥልና ብቻችንን እንዳይደለን በመንገር ያደፋፍሩናል። ሌሎች ሰዎችም እንደ እኛው በጨለማ ጊዜያት ውስጥ አልፈው በእግዚአብሔር ጸጋ አሸናፊዎች ሆነዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቶስ ስለ እኛ እያደረገልን ያለውን ከፍ ያለ የማማለድ አገልግሎት በውልብታ ያሳዩናል፤ ሁል ጊዜም እንደሚጸልይልን ይነግሩናል (እብ 7፡25)።

መዝሙራትን በጸሎታችንና በአምልኮአችን መካከል ማስገባት የአማኞች ማህበረሰብ የሰብአዊ ዘርን ልምምድ በሙላት እንዲገነዘብ እንዲሁም በአምልኮ ውስጥ በተለያዩ ገጽታዎች ነገሮችን እንዲገነዘብ ያደርጋል። መዝሙራት የመለኮት-ሰብአዊነት መዝሙርና ጸሎት ናቸው። በዚህ ምክንያት መዝሙራትን በአምልኮ መካከል ማስገባት አማኙን ማህበረሰብ ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ ማዕከልና ኃይለኛ ወደሆነው ፈዋሽ ፀጋ ያመጣል።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. በድንገት የሚደረግ፣ ያልተመራ ጸሎት ብቸኛው የጸሎት አማራጭ የማይሆነው በድንገት የሚደረግ፣ ያልተመራ ጸሎት ብቸኛው የጸሎት አማራጭ የማይሆነው ለምንድነው? የጸሎት ሕይወታችን ከመዝሙረ ዳዊት፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጸሎት ጥቅም ማግኘት የሚችለው እንዴት ነው?

2. መዝሙረ ዳዊት የጋራ የጸሎት ሕይወታችንን እንዴት ሊያበለጽጉ ይችላሉ? የአጥቢያ መዝሙረ ዳዊት የጋራ የጸሎት ሕይወታችንን እንዴት ሊያበለጽጉ ይችላሉ? የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንዎ መዝሙራትን በአምልኮ አገልግሎቶች ለመጠቀም ስለሚያደርጋቸው አንዳንድ ተግባራዊ መንገዶች ተወያዩ።



3. መዝሙራት ስለ ሰው መንፈሳዊ የእምነት ጉዞ ውስብስብነት እና ፈዋሽ ስለሆነው መዝሙራት ስለ ሰው መንፈሳዊ የእምነት ጉዞ ውስብስብነት እና ፈዋሽ ስለሆነው የእግዚአብሔር ጸጋ ኃይል ምን ይገልጻሉ?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL