የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት



1ኛ ሩብ ዓመት 2024


ታህሣሥ 20 - 26

1ኛ ትምህርት

Dec 30 - Jan 5




መዝሙረ ዳዊትን እንዴት እንደምናጠና



ሰንበት ከሰዓት

ለሳምንቱ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- 1ኛ ዜና 16፡7፤ ነህ 12፡8፤ መዝ 25፡1-5፤ መዝ 33፡1-3፤ ሮሜ 8፡26፣27፤ መዝ 82፡8፤ መዝ 121፡7።


የመታሰቢያ ጥቅስ፡- እርሱም፦ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው። በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው። ሉቃ 24፡44፣45።

መዝሙረ ዳዊት ለአይሁዶችና ለክርስቲያኖች ለዘመናት የጸሎትና የዝማሬ መጽሐፍ ሆኖ ቆይቶአል። መዝሙሮቹ በዋነኛነት መዝሙረኛው በራሱ ቃል ሐሳቡን ወደ እግዚአብሔር ያቀረበበት ቢሆንም መዝሙራቱ እግዚአብሔር ሀሳባቸውን በማነቃቃት ሀሳቡን የገለጸበት ነው እንጂ በሟች ፍጡር የተጠነሰሰ አይደለም።

በእርግጥም የጻፉትን እንዲጽፉ እግዚአብሔር አነሳስቶአቸዋል፤ እግዚአብሔር በሌሎች መጻህፍት (2ጴጥ 1፡2) እንደሚናገረን ሁሉ በመዝሙራትም በአገልጋዮቹ አማካይነትና በመንፈሱ የሚናገረን ከዚህ የተነሣ ነው። ኢየሱስ፤ ሐዋርያት እና የአዲስ ኪዳን ጸሓፊዎች ከመዝሙራት የጠቀሱ ሲሆን እነርሱን እንደተቀደሱ መጻህፍት አድርገው አመልክተዋል (ማር 12፡10፤ ዮሐ 10፡34፣35፤ ዮሐ 13፡18)። ልክ እንደ ዘፍጥረትና የሮሜ መጻሕፍት በእርግጠኝነት የእግዚአብሔር ቃላት ናቸው።

በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ ያሉ መዝሙሮች መልእክቶች ዓለም አቀፋዊ ቢሆኑም በተለያዩ የጥንት እሥራኤላውያን ጸሐፊዎች በእብራውያን ስነ-ግጥም በመጻፋቸው የራሳቸውን የግል ዓለም የሚያንጸባርቁ ናቸው። እነዚህን መዝሙራት እንደ እግዚአብሔር ቃል መቀበልና ለስነ-ግጥማዊ ይዘታቸው ትኩረት መስጠት፤ እንዲሁም ለታሪካዊ፤ ስነ-መለኮታዊ እና ኃይማኖታዊ የአምልኮ ሥርዓት አውዳቸው ትኩረት መስጠት ብዙ ዘመናትን ተሻግረው ወደ እኛ ዘመን የደረሱ መልእክቶቻቸውን ለመረዳት ወሳኝ ነው። *የዚህን ሳምንት ትምህርት አንብበው ለታህሳስ 27 ሰንበት ይዘጋጁ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

ታህሣሥ 21
Dec 31

መዝሙራት በጥንቱ የእስራኤል አምልኮ


ኛ ዜና 16፡7፤ ነህ 12፡8፤ መዝ 18፡1፤ መዝ 30፡1፤ መዝ 92፡1፣ መዝ 95፡2፣ መዝ 105፡ 2፤ ቆላ 3፡16፤ ያዕ. 5፡13ን አንብቡ። አንዳንድ መዝሙራትን ለመጻፍ ያነሳሱ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? የእግዚአብሔር ህዝብ መዝሙራቱን የተጠቀሙት መቼ ነው?



መዝሙራት በግልና በጋራ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተጻፉ ናቸው።

የሙዚቃ መሣሪያዎችን (መዝ 61፡1)፣ የዜማ ቃናዎችን (መዝ 9፡1) እና የሙዚቃ መሪዎችን (መዝ 8፡1) በሚጠቅሱ በሙዚቃው ላይ በተሰጡ ተጨማሪ ማስታወሻዎች በተሰጡ ሀሳቦች መሰረት በቤተ መቅደስ አገልግሎት እንደ ውዳሴ መዝሙሮች ተዘምረዋል።

በእብራውያን መጽሐፍ ቅዱስ የመዝሙረ ዳዊት ርእስ ቴሂሊም፣ “ውዳሴ” የሚል ሲሆን ዋና ዓላማው የሆነውን እግዚአብሔርን ማመስገንን ያንጸባርቃል። Psalms የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2ኛውና በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበረው ሴፕቱጀንት ከሚል መጽሐፍ ቅዱስ ከግሪኩ psalmoi ከሚለው ቃል የተወሰደ ነው።

መዝሙራት የአይሁድ አምልኮ እጅግ አስፈላጊ ክፍል ነበሩ። ለምሳሌ በቤተ መቅደስ ምርቃት ወቅት፤ በሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ላይ፤ በሰልፍ ወቅት፤ እና የኪዳኑ ታቦት በኢየሩሳሌም ባረፈ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለዋል።

“የማእረግ መዝሙሮች” (መዝ 120-134)፤ የመንፈሳዊ ጉዞ መዝሙሮች በመባል የሚታወቁት፣ በሶስት የታወቁ ዓመታዊ በዓላት ወቅት ወደ ኢየሩሳሌም በሚደረገው የጉዞ ወቅት ይዘመሩ ነበር (ዘጸ 23፡14-17)። “የግብጻውያን ሃሌል” (መዝ 113-118) እና “ታላቁ ሃሌል” (መዝ 136) ደግሞ አዲሱን የጨረቃ ግብዣ እና የቤተ መቅደስ ምረቃ ወቅትን ጨምሮ በሶስት ዋና ዋና ዓመታዊ ግብዣዎች ወቅት ይዘመሩ ነበር። የግብጻውያን ሃሌል ደግም በፋሲካ ክብረ በዓል ወቅት ትልቅ ቦታ አግኝቷል። መዝ 113 እና 114 በፋሲካው ድግስ መግቢያ ላይ ይዘመሩ ነበር፤ መዝ 115-118 ደግሞ በድግሱ መጨረሻ ላይ ይዘመሩ ነበር (ማቴ 26፡30)። ”ዕለታዊው ሃሌል” (መዝ.145-150) በምኩራብ በሚደረጉ የማለዳ አገልግሎቶች ዕለታዊ ጸሎቶች ውስጥ ተጠቃልሎ ነበር።

መዝሙራት የህዝቡን አምልኮ የሚያጅቡ ብቻ ሳይሆኑ ሰዎች እግዚአብሔርን በቤተ መቅደሱ እንዴት ማምለክ እንዳለባቸው መመሪያ የሚሰጡም ናቸው። ኢየሱስ በመዝ. 22 ውስጥ ያሉትን ቃላት በመጠቀም ጸልዮአል (ማቴ 27፡46)። መዝሙራት በጥንቱ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥም ወሳኝ ቦታ ነበራቸው (ቆላ 3፡16፤ ኤፌ 5፡19)።

እኛ በእርግጥ በምድራዊ ቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን ባናመልክም መዝሙራትን በግልም ሆነ በጋራ አምልኮ ወቅት መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

ታህሣሥ 22
Jan 01

መዝሙረኞቹን መገናኘት


ንጉሥ ዳዊት፤ ስሙ በብዙ መዝሙራት ርዕሶች ላይ ተጠቅሶ የምናገኘው፤ በእስራኤል ቤተ መቅደስ የሚደረገውን የአምልኮ ስርአት በማቀናጀት ተግቶ ይሰራ ነበር።

“የእስራኤል ምርጡ መዝሙረኛ” ተብሎ ተጠርቷል (2ኛ ሳሙ. 23፡1)። አዲስ ኪዳን ዳዊት ብዙ መዝሙሮችን እንደጻፈ ያረጋግጣል (ማቴ 22፡43-45፤ የሐዋ 2፡25-29፣34፣35፤ የሐዋ 4፡25፤ ሮሜ 4፡6-8)። ብዙ ቀጥር ያላቸው መዝሙራት የቤተ መቅደሱ ሙዚቃኞች በሆኑት በሌዋውያን ተደርሰዋል፤ ለምሳሌ መዝ 50 እና 73-84 በአሳፍ፤ መዝ 42፤44- 47፤49፤84፤85፤እና 88 በቆሬ ልጆች፤ መዝ 88 በይዝራኤላዊው በሄማን እና መዝ 89 በይዝራኤላዊው ኤታን ተደርሰዋል። ከዚያም ባሻገር ሰለሞን (መዝ 72፤ 127ን) እና ሙሴ (መዝ 90ን) አንዳንድ መዝሙሮችን ጽፈዋል።

መዝ 25፡1-5 መዝ 42፡1 75፡1፤ 77፡1፤ 84፡1፣2፤ 88፡1-3፤ እና 89፡1ን ያንብቡ። እነዚህ መዝሙሮች ጸሐፊዎቹ ስላለፉባቸው ልምምዶች ምን ይነግሩናል?





መንፈስ ቅዱስ መዝሙረኞቹን በማነሳሳት የፀጋ ስጦታቸውን ለእግዚአብሔር ክብርና ለአማኝ ማህበረሰባቸው አገልግሎት ተጠቅሟል። መዝሙረኞቹ የእውነተኛ መሰጠት እና የጥልቅ እምነት ሰዎች ቢሆኑም እንደ ማንኛችንም ለተስፋ መቁረጥና ለፈተና የተጋለጡ ነበሩ። መዝሙራት ከብዙ ጊዜ በፊት የተጻፉ ቢሆኑም ዛሬ ከምናልፋቸው ልምምዶች አንዳንዶቹን በእርግጥ ይገልጻሉ።

“ፀሎቴ ወደ ፊትህ ይድረስ፤ ጆሮህን ወደ ጩኸቴ አዘንብል። ነፍሴ በመከራ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት ተሞልታለችና ሕይወቴም ወደ መቃብር ተጠጋች” (መዝ 88፡2.3)። ይህ ከዛሬ 3000 ዓመታት በፊት እንደነበረ ሁሉ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነፍስ ጩኸት ነው።

አንዳንድ መዝሙራት መከራን ሲያስታውሱ ሌሎች ደግሞ በደስታ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። መዝሙረኞቹ እግዚአብሔር እንዲያድናቸው በመጮሃቸው የማይገባቸውን ሞገስ ተለማመዱ። እግዚአብሔርን ለታማኝነቱና ለፍቅሩ ሲያከብሩት ራሳቸውን ሳይቆጥቡ ለእርሱ ለመሰጠት ደግሞ ቃል ኪዳን ገቡ። በመሆኑም መዝሙረኞቹ የመለኮት መቤዠት እና የእግዚአብሔር ፀጋና ተስፋ ምስክር ናቸው። መዝሙራቱ የእግዚአብሔርን ይቅርታና አዲስ ሕይወት ስጦታዎች በእምነት ለሚቀበሉ ሁሉ የመለኮትን ቃል ኪዳን ያስተላልፋሉ። ይሁን እንጂ በተመሳሳይ ሁኔታ በወደቀው ዓለም ውስጥ የተስፋፋውን መከራና ችግር ለመደበቅ፣ ለመሸፋፈንና ለማሳነስ አይሞክሩም።

እንደ መዝሙረኞች ያሉ ታማኝ ሰዎች እንኳን እኛን እየገጠሙን ካሉ ነገሮች መካከል ከአንዳንዶቹ ጋር እንደታገሉ በማወቃችን ተስፋና መጽናናትን ልናገኝ የምንችለው እንዴት ነው?

ታህሣሥ 23
Jan 02

መዝሙር ለሁሉም ወቅት


መዝ 3፤መዝ 33፡1-3፤ እና መዝ 109፡6-15ን ያንብቡ። እነዚህ መዝሙሮች ምን ዓይነት የሰብአዊ ልምምድን የተለያዩ ገጽታዎች ያሳያሉ?



መዝሙራት የሰብአውያንን ልምምድ ለአማኝ ማህበረሰቦች በሙላት ሲያሳዩ፤ አማኞች በማናቸውም የህይወት ልምምድ ውስጥ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ ጥሪ ያቀርባሉ። በመዝሙራት ውስጥ የሚከተሉትን ነገሮች እንመለከታለን፡-

እግዚአብሔርን ለግርማውያና የፈጣሪነት ኃይሉ፣ ለንጉሣዊ ገዥነቱ፣ ለፍርዱ፣ እና ለታማኝነቱ የሚያጎሉ መዝሙራትን (2) ለተትረፈረፉ የእግዚአብሔር በረከቶች ጥልቅ ምስጋና የሚያቀርቡ የምስጋና መዝሙሮችን (3) ከመከራ ለመዳን ልባዊ የሆነ የሰቆቃ ጩኸትን (4) የጽድቅ ሕይወት እንድንኖር ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚሰጡ የጥበብ መዝሙሮችን (5) ሉአላዊ ንጉሥና የእግዚአብሔር ሕዝብ ነጻ አውጪ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ የሚያመለክቱ ንጉሣዊ መዝሙሮችን (6) መጪው ትውልድ አያቶቻቸው የፈጸሙዋቸውን ስህተቶች እንዳይደግሙ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር እንዲታመኑና ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ሆነው እንዲቆዩ የእሥራኤልን ያለፈውን ታሪክ በማጉላት የእግዚአብሔርን ታማኝነትና የእሥራኤልን አለመታመን የሚያስታውሱ ታሪካዊ መዝሙሮችን እንመለከታለን።

የመዝሙራት ስነ-ግጥማዊ ይዘታቸው የአንባቢውን ቀልብ የሚስብ ልዩ ኃይል አላቸው። ምንም እንኳን ከእነዚህ ስነ-ግጥማዊ መሳሪያዎች አንዳንዶቹ በትርጉም ምክንያት ቢጠፉም፣ አሁንም በገዛ ራሳችን ቋንቋ አብዛኞቹን ማድነቅ እንችላለን።

ትይዩነት በተመዛዛኝ ሁኔታ የተገነቡ ቃላትን፣ሐረጎችን ወይም ሐሳቦችን ማደባለቅን ያካትታል። ትይዩነት ተዛማጅነት ያላቸውን ሀሳቦች ትርጉም እንድናስተውል ይረዳናል።

ለምሳሌ፡- ነፍሴ ሆይ፣ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ አጥንቶቼም (የውስጥ ሰውነቴም) ሁሉ የተቀደሰ ስሙን ባርኩ!”(መዝ 103፡1)። በዚህ ተመሳሳይነት “ነፍሴ ሆይ” ማለት “የውስጥ ሰውነቴ” ማለት ሲሆን የአንድ ሰው ሙሉ ማንነት ማለት ነው።

ምስላዊ አገላለጽ የአንባቢዎቹን አካላዊ ስሜቶች ለመሳብ ዘይቤአዊ ቋንቋን ይጠቀማል (ለምሳሌ፣ የእግዚአብሔር ምሽግ እንደ “የክንፎቹ ጥላ” ተገልጾአል) (መዝ 17፡8)።

አጠቃላይነት ተነጻጻሪ ጥንድ ቃላትን በመጠቀም የአንድን ነገር ሙሉነት ወይም ሁለንተናዊነት ይገልጻል። “በቀንና በሌሊት ወዳንተ ጮኽሁ” የሚለው ሀሳብ ያለማቋረጥ እንደሚጮኽ ያሳያል (መዝ 88፡1)።

የቃላት ጨዋታ የቃላትን ሰምና ወርቅ አጉልቶ በማሳየት ለመንፈሳዊ መልእክት ድምጽ ይሰጣል። በመዝ 94፡4፣5 የእብራይስጥ ’ኤሎሂም “አማልክት” እና ’ኤሊሊም “ጣኦታት” የሚለው የቃላት ጨዋታ የሚያሳየው የአህዛብ አማልክት ኤሎሂም፣ “አማልክት” ቢመስሉም ’ኤሊሊም “ጠኦታት” ብቻ እንደሆኑ ለመግለጽ ነው።

በመጨረሻም “ሴላ” የሚለው ቃል አጭር የእረፍት ጊዜ ወይም አንድ ነገር መቆም እንዳለበት ወይም የአንድን መዝሙር ክፍል እንዳበቃ ለመግለጽ ወይም የሙዚቃ መሳሪያ ቅኝት እስኪስተካከል ማቆምን የሚጠቁም ነው (መዝ 61፡4)። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

ታህሣሥ 24
Jan 03

በመንፈስ የተነሳሱ ፀሎቶች


2ኛ ሳሙ. 23፡1፣2 እና ሮሜ 8፡26፣27ን ያንብብ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ፀሎት ምን ያስተምሩናል?



መዝሙራት በመንፈስ አነሳሽነት የተዘመሩ የእስራኤል ጸሎቶችና ምስጋናዎች ናቸው፤ ስለዚህ በመዝሙራት ውስጥ የእግዚአብሔር ድምጽ ከሕዝቡ ድምጽ ጋር ተዋህዷል። መዝሙራቱ ከእግዚአብሔር ጋር በግልጽ የመገናኘት ሃይል እንደሆኑ ይታሰባል።

መዝሙረኞቹ እግዚአብሔርን “አምላኬ”፤ “ኦ ጌታ” እና “ንጉሴ” በማለት በግለሰብነት ይገልጻሉ (መዝ 5፡2፣ መዝ 84፡3)። መዝሙረኛው ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን “ጆሮህን አዘንብል” (መዝ 5፡1)፤ “ጸሎቴን ስማኝ” (መዝ 39፡12) “ወደ እኔ ተመልከት” (መዝ 25፡18)፣ “መልስ ስጠኝ” (መዝ 102፡2) እና “አድነኝ” (መዝ 6፡4) በማለት ይለምነዋል።

እነዚህ በግልጽ የአንድ ሰው ጸሎቶች ናቸው።

የመዝሙራቱ አስደናቂ ውበትና ተማጽኖ የሚደገፈው መዝሙራት እንደ ጸሎቶችና ምስጋናዎች በአማኞች ጸሎትና ምስጋና መልክ የቀረቡ የእግዚአብሔር ቃል የመሆናቸው እውነታ ላይ ነው። በዚህ ሁኔታ መዝሙራት በሮሜ 8፡26፣27 በተገለጸው ሁኔታ የእግዚአብሔር ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ቁርኝት እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡- ”እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።”

ኢየሱስም መዝሙር 110፡1 በቀጥታ በጠቀሰ ጊዜ እንደ ሉቃስ 20፡42፣42 ያሉ ጥቅሶችን ከመዝሙራት ጠቅሶ ነበር፡- “ዳዊት እራሱ በመዝሙራት መጽሐፍ / “ ጌታም ለጌታዬ ፣/ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ይላል።”።

ከመዝሙሮቹ አንዳንዶቹ የተወሰኑ ታሪካዊ ክስተቶችን የሚያመለክቱ ወይም ከራሳቸው ከመዝሙረኞቹ ልምምዶችና እንደ ሕዝብ ከእሥራኤል ሕዝብ ልምምድ የመነጩ ቢሆንም የመዝሙሮች መንፈሳዊ ጥልቀት ሁሉንም ባህላዊ፤ ሃይማኖታዊ፤ ሕዝባዊ፤ እና ጾታዊ ድንበር በመሻገር ስለተለያዩ የህይወት ሁኔታዎች ይናገራል። በሌላ አባባል የመዝሙራት መጻሕፍትን ስናነብ በየትኛውም የዓለም ክፍል እና በማንኛውም ዘመን ውስጥ የሚገኙ ሰዎች፣ የሚጋፈጡአቸው ሁኔታዎች ምንም ቢሆኑ፣ ተስፋን፤ ምስጋና፣ ፍርሃትን፤ ቁጣን፤ ሀዘንን እና የልብ መሰበርን ሲናገሩ እናገኛለን። በራሳችን ልምምዶች ቋንቋ ለሁላችንም ይናገራሉ።

ኢየሱስ መዝሙሮችን መጠቀሙ በእኛ የእምነት ልምምድ ውስጥ ስለሚኖራቸው አስፈላጊነት ምን ሊነግረን ይገባል?

ታህሣሥ 25
Jan 04

የመዝሙራት ዓለም


መዝ 16፡8፤ መዝ 44፡8፤ 46፡1፤ 47፡1፤ 57፡2፤ 62፡8፤ 82፡8፤ እና መዝ 121፡7ን ያንብቡ። ኢየሱስ በመዝሙረኛው ሕይወት ውስጥ የሚይዘው ቦታ ምንድር ነው?



የመዝሙራት ዓለም በአጠቃላይ (ሙሉ በሙሉ) እግዚአብሔርን ማእከል ያደረገ ነው፤ በጸሎትና በምስጋና የህይወት ልምምዱን በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፎ ሊሰጥ ይሻል። እግዚአብሔር ሉአላዊ ፈጣሪ፤ የምድር ሁሉ ገዥና ፈራጅ ነው።

ለልጆቹ አስፈላጊውን ሁሉ ይሰጣቸዋል። ስለዚህ እርሱ ሁል ጊዜ ሊታመን ይገባዋል። የእግዚአብሔር ሕዝብ ጠላቶች “አምላካችሁ ወዴት አለ?” ብለው ሲጠይቋቸው፤ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ለተስፋ መቁረጥ እጃቸውን ሊሰጡ ሲቃረቡ እንኳን (መዝ 42፡10) እርሱ ሊታመን ይገባዋል። እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ የሚገኝ እና ፈጽሞ የማይጥል እንደሆነ ሁሉ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ ከፊታቸው ሊያኖሩት ይገባል። በመጨረሻም መዝሙራት ሁሉም ሕዝቦችና ፍጥረታት በሙሉ እግዚአብሔርን የሚያመልኩበትን ጊዜ አሻግረው ይመለከታሉ (መዝ 47፡1፤ 64፡9)።

የእግዚአብሔር በሕይወት ማእከላዊ መሆን የአምልኮ ማእከላዊነትን ይፈጥራል።

መዝሙረኛው የኖረበት አምልኮና ያሁኑ ትውልድ የአምልኮን ሕይወት ያስተዋለበት መንገድ በመሰረታዊነት ልዩነት አላቸው፤ ለዚህም ምክንያቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ባህል አምልኮ ተፈጥሮአዊና ክርክር የሌለበት የማህበረሰብ ሕይወት ማዕከል ነበር። ስለዚህ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት በእግዚአብሔር ሕዝብ ሕይወት የተከሰተው ማንኛውም ነገር፣ መልካምም ሆነ መጥፎ፣ በአምልኮ ይገለጽ ነበር። መዝሙረኛው የትም ቢሆን እግዚአብሔር ይሰማውና በራሱ ምርጥ ጊዜ ምላሽ ይሰጠው ነበር (መዝ 3፡4፤ 18፡6፤20፡6)።

የእግዚአብሔር ማደሪያ ስፍራ በሰማይ እንደሆነ መዝሙረኛው ያውቅ ነበር፤ ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ እግዚአብሔር በጽዮን፣ በሕዝቡ መካከል በቤተ መቅደሱ ያድራል።

በተመሳሳይ ጊዜ እግዚአብሔር በቅርብም በሩቅም፤ በሁሉም ስፍራ፣ በመቅደሱ (መዝ 11፡ 4)፤ ተሰውሮ (መዝ 10፡1) እንዲሁም ራሱን ገልጦ (መዝ 41፡12) ይገኛል። በመዝሙራት ውስጥ እነዚህ በተመሳሳይ ጊዜ የማይከሰቱ የእግዚአብሔር ባህርያት በአንድነት ተገልጸዋል።

መዝሙረኛው የእግዚአብሔር ቅርብነትና ሩቅነት የማይነጣጠሉ መለኮታዊ ባህርያት እንደሆኑ ተገንዝቦአል (መዝ 24፡7-10)። ዘማሪዎቹ የዚህን መንፈሳዊ ውጥረት አሰራር ተረድተዋል። እየተለማመዱት ያለው ነገር ምንም ቢሆን፣ እግዚአብሔር ሊፈጽመው በፈለገው መንገድና በመረጠው ጊዜ ጣልቃ እንዲገባ ሲጠብቁት ሳለ፣ ተስፋቸውን የሚያጠነክርላቸው ስለ እግዚአብሔር መልካምነትና ሕልዎት ግንዛቤ ማግኘታቸው ነው።

እግዚአብሔርን በተወሰኑ የራሳችን የኑሮ ገጽታዎች ብቻ መገደብ እንደማንችል መዝሙረኛው ምን ይነግረናል? እግዚአብሔርን በርቀት እንዲቆይ ለማድረግ እየፈለጉ ያሉባቸው የሕይወትዎ ክፍሎች የትኞቹ ሊሆኑ ይችላሉ?

ታህሣሥ 26
Jan 05


ተጨማሪ ሀሳብ


ነብያትና ነገስታት በሚለው መጽሐፍ ገጽ 35-50 ላይ መቅደሱና አገልግሎቱ የሚለውን ምእራፍ (በእንግሊዝኛው)፤ መልእክት ለወጣቶች በሚለው መጽሐፍ የሙዚቃ ጥቅም የሚለውን ርእስ ገጽ 291፣292 ያንብቡ። የመዝሙራት መጽሐፍ በአምስት መጽሐፍ የሚመደቡ ማለትም መጽሐፍ 1 (መዝሙር 1-41)፣ መጽሐፍ 2 (መዝሙር 42-72)፤ መጽሐፍ 3 (መዝሙር 72-89)፤ መጽሐፍ 4 (90-106)፤ እና መጽሐፍ 5 (መዝሙር 107-150) ክፍሎች ያሉት ሲሆን 150 መዝሙሮችን አጠቃልሎ ይዟል። የመዝሙር መጽሐፍ በአምስት ክፍል መከፈል የቀደምት አይሁዶች ባህል ሲሆን ከአምስቱ የሕግ መጻሕፍት ክፍሎች ጋር ይነጻጸራል።

የመዝሙራት መጽሐፍ አስቀድመው የነበሩ የመዝሙር ስብስቦች እንዳሉ ማስረጃ ይሰጠናል፡- የቆሬአውያን ስብስብ (መዝ 42-49፣84፣85፣87፣88)፤ የአሳፋውያን ስብስብ (መዝ 73-83)፣ የክብር (መዝ 120-134) እና የሃሌሉያ መዝሙራት (መዝ 111-118፣146- 150)። መዝ 72፡20 ለዳዊት መዝሙሮች ትንሹ ስብስብ ምስክርነት ይዞአል።

አብዛኞቹ መዝሙራት ከዳዊት ዘመነ መንግስትና ከቀደመው ንጉሳዊ አገዛዝ ጋር የተገናኙ ሲሆን (በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክ.ል.በፊት) መዝሙራቱን የማሰባሰቡ ሂደት በቀጣዮቹ መቶ ክፍለ ዘመናት ማደጉን ቀጠለ፡- በተከፋፈለው የነገስታት ዘመን፤ በስደት ጊዜ፣ እንዲሁም ከስደት ዘመን በኋላ በነበረው ዘመን ማደጉን ቀጠለ። የእብራውያን ጸሐፊዎች በእዝራ መሪነት ስር ሆነው የአዲሱን ቤተ መቅደስ አገልግሎት በመሰረቱበት ጊዜ የነበሩ ትናንሽ የመዝሙራት ስብስብን በአንድ መጽሐፍ መሰብሰባቸው አሳማኝ ነው።

እነዚህ ፀሐፊዎች የመዝሙር መጽሐፍን ማጠናከራቸው (ማጽናታቸው) ከመለኮታዊ አመራር ውጭ ሆነው እንዳልነበረ ያሳያል። ፀሐፊዎቹ እንደ መዝሙረኞቹ ሁሉ ታማኝ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ስለነበሩ ስራቸውም በእግዚአብሔር መንፈስ የተመራ ነበረ (እዝ 7፡6፣10)። የመዝሙሮቹ መለኮታዊና ሰብአዊ ተፈጥሮ ሥጋ በለበሰው ጌታ ኢየሱስ ከታየው የመለኮትና ሰብአዊነት ውህደት ጋር የሚነጻጸር ነው። “ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ቋንቋ ከተገለጹ በእግዚአብሔር ከተሰጡ እውነቶቹ ጋር የመለኮትንና የስብዕናን ጥምረት ይገልጻል። የዚህ ዓይነቱ አንድነት የተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ እና የሰው ልጅ በሆነው በክርስቶስ ነው። በዚህ ሁኔታ ‘ቃልም ስጋ ሆነ በመካከላችንም አደረ‘ የተባለው ለክርስቶስ እውነት እንደሆነ ሁሉ ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ነው።” ታላቁ ተጋድሎ ገጽ 8 በእንግሊዝኛው።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. መዝሙራት የመለኮት- ሰብአዊነት ጸሎቶችና መዝሙሮች ናቸው ሲባል ምን ማለት መዝሙራት የመለኮት- ሰብአዊነት ጸሎቶችና መዝሙሮች ናቸው ሲባል ምን ማለት ነው? ይህን ሀሳብ በሙላት ለመጨበጥ ከባድ ቢሆንም እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያለውን ቅርበት እንድንመለከት እንዴት ሊረዱን ይችላሉ? እግዚአብሔር ለሰብአውያን እና ለእያንዳንዳችን ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ በራሱ መንገድ እንዴት ይገልጽልናል?

2. በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ስለ እርስዎ ሁኔታ የሚናገረውን የሆነ ነገር ስላገኙበት ጊዜ በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ስለ እርስዎ ሁኔታ የሚናገረውን የሆነ ነገር ስላገኙበት ጊዜ በክፍልዎ ውስጥ ያውሩ። በዚያ ቦታ ምን ማጽናኛና ተስፋ አገኙ?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL