የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት ፡ መዝ 134፤ ኢሳ 42:10–12፤ ራእይ 14:3፤ መዝ 15፤ መዝ 101:1–3፤
መዝ 96፤ ራእይ 14:6-12፤ ዮሐ 4:23፣ 24ን ያንብቡ ።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡- በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፥
ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ። (መዝሙር 104:33)።
ስለ እግዚአብሔር ጸጋ እና ኃይል ያለን ልምምድ ሲጨምር፣ ከመዝሙረኛው ጋር፡
- “ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምንን እመልሳለሁ?” ብለን እንድንጠይቅ
እንነሳሳለን። ( መዝ 116:12)። ለዚህ ጥያቄ የማይቀር መልስ ለእግዚአብሔር
ታማኝ በመሆን የራስን ሕይወት መስጠት ነው። በመዝሙራት፣ እስራኤል ዝም ብሎ
ተራ ሕዝብ አይደለም፣ ነገር ግን “ታላቅ ጉባኤ” (መዝ 22፡22፣ 25፤ መዝ 35፡18)ነው።
ይህ የእስራኤል ቀዳሚ ጥሪ እግዚአብሔርን ማመስገን እና ለሌሎች አሕዛብ ስለ እርሱ
መመስከር ነው፣ ምክንያቱም ዓለም ሁሉ ከሕዝቡ ጋር በአምልኮ እንዲተባበር ጌታ
ይፈልጋል። የእግዚአብሔር ሕዝቦች ጌታን የሚያመልኩ ተስፋቸው በእርሱ እና በፍቅሩ
ላይ ስለሆነ ከጻድቃን ጋር ተቆጥረዋል። ጌታን በጉባኤ ውስጥ ማመስገን ጥሩ አምልኮ
ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ማለት በእስራኤል ውስጥ የግለሰብ ጸሎት እና ውዳሴ እንደ
ሁለተኛ ደረጃ አምልኮ ተደርጎ ይወሰዳል ማለት አይደለም። በአንጻሩ ግለሰቡ ለአምላክ
የሚያቀርበው አምልኮ የኅብረቱን አምልኮ በአዲስ ውዳሴ ይመግባል (መዝ 22:22፣
25) በሌላ በኩል ደግሞ የግለሰብ አምልኮ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት በደንብ
ያዳብራል። የሚያመልከው ማኅበረሰብ “የቅኖች ማኅበር” ተብሎ ተጠርቷል (መዝ 111፡1)።
ቅኖች እግዚአብሔርን ያውቃሉ (መዝ 36፡10) በእግዚአብሔርም ይታወቃሉ (መዝ 37፡
18) ይህ ልምምዳቸው በሁሉም የሕይወታቸው ገጽታ ላይ ሰፍኖ ይታያል።
ለመጋቢት 14 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥኑ።
መዝሙር 134ን ያንብቡ። እዚህ ላይ እንደተመለከተው ይህ የሚቀርበው አምልኮ የት ነው? ጌታን ማምለክ መጨረሻው ምንድን ነው?
መዝሙር 134 በዘኍልቍ 6፡24-26 የሚገኘውን የአሮናዊውን የክህነት በረከት
ያስታውሳል (እንዲሁም መዝ 67፡1) በረከት በእግዚአብሔር እና በእስራኤል መካከል
ላለው ግንኙነት እንደ መሰረታዊ መርህ እና ውጤት መሆኑን ያጎላል። ሕዝቡ በመቅደሱ
እግዚአብሔርን ይባርካል፣ እግዚአብሔርም ከጽዮን ሕዝቡን ይባርካል።
ጌታ የሰማይና የምድር ፈጣሪ በመሆኑ በረከቱ ለሕይወት ሁሉ ይደርሳል። ጽዮን
የመለኮታዊ ልዩ በረከቶች መገኛ ቦታ ሆና መጠቀሷ ጌታ ከህዝቡ ጋር ያለውን የቃል
ኪዳን ትስስር ያሳያል። ስለዚህም እስራኤል በዚህ የጸጋ ቃል ኪዳን ውስጥ ሆና ነው ጌታን
የመባረክ እድልን የምትጠቀመው እና የእርሱን በረከት የምትቀበለው።
መዝሙር 18:1ን፤ መዝ 36:1፤ መዝ 113:1፤ መዝ 134:1፣ 2፤ እና መዝ 135:1፣
2ን ያንብቡ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት እዚህ ጋር የተገለጹት እንዴት ነው?
መዝሙራት ብዙውን ጊዜ አምላኪዎችን እንደ ጌታ አገልጋዮቹ ይገልጻሉ።
“በሌሊት በእግዚአብሔር ቤት የሚቆም” ( መዝ 134:1) የሚለው አባባል የሌዋውያንን
የሌሊት ዘበኞች (1 ዜና 9:23-27) ወይም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቀንና ሌሊት
የሚያቀርቡትን ውዳሴ (1ኛ ዜና 9፡33) ሊያመለክት ይችላል።
እስራኤላውያን በምንም ዓይነት ምስል ሊገለጽ በማይችል ሁኔታ የማይታየውን
አምላክ ያመልኩ ስለነበር መቅደሱ የጌታን ክብር ለማንፀባረቅ እና ኃጢአተኛ የሆኑ ሰዎች
ወደ ቅዱሱ ንጉሣቸው የሚቀርቡበት አስተማማኝ ቦታ ሆኖላቸዋል። ይህ ገጠመኝ በጌታ
በራሱ የተጀመረ ሲሆን በስርአቱ እና በአዋጅ የተደነገገ ነው።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
“በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ
ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች
ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን
ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ። ” ( 1 ጴጥ
2:4፣ 5)። በጴጥሮስ አነጋገር የምናየው፣በእነዚህ መዝሙሮች ውስጥ የቀረቡትን ተመሳሳይ
ሃሳቦችን የአዲስ ኪዳን መግለጫ አድርጎ በማቅረብ፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ ቅዱስ ካህናት
ሆነው፣ ፈጣሪያቸውና አዳኛቸው ለሆነው ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስላደረገላቸው
መልካም ነገር ሁሉ ምስጋናና ውዳሴ ሲያቀርቡ ነው።
የአዲስ ኪዳን አማኞች እንደመሆናችን መጠን የወንጌልን የምስራች ለዓለም ለማወጅ
በተጠራንበት የምልጃ አገልግሎት የክህነት ሚና አለን። ይህን ማድረግ የምንችልባቸው
በጣም ውጤታማ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
መዝ 33:3፣ መዝ 40:3፣ መዝ 96:1፣ መዝ 98:1፣ መዝ 144:9 እና መዝ 149:1ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተገለጸው የጋራ ዘይቤ ምንድን ነው?
መዝሙራት “አዲስ መዝሙር” እንዲዘምሩ ሰዎችን ይጠሯቸዋል። እዚህ “አዲስ
መዝሙር” የተባለው ምንድን ነው? “አዲስ መዝሙር” የመዘመር ምክንያቱ ለጌታ
ግርማ እና ዓለም አቀፋዊ ሉዓላዊነት አዲስ እውቅና መስጠት፤ ለእርሱ እንክብካቤና
ማዳን እንደ የምድር ፈጣሪ እና ዳኛ ምስጋና ለማቅረብ ነው። ከጠላቶችና ከሞት ማዳን
እንዲሁም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ያለው ልዩ ሞገስ “አዲስ መዝሙር” ለመዘመር
ከሚያነሳሱ ምክንያቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። ሌሎች መዝሙሮችም ጌታን ስለ
ፍቅሩ እና ተአምራቱ ሲያወድሱ፣ “አዲሱ መዝሙር” እንደገና ራስን የመስጠት ደስታን
እና ለእግዚአብሔር የመታደስ ተስፋን የሚገልጽ ልዩ መዝሙር ነው። አዲሱ የመለኮታዊ
ማዳን ልምምድ ሰዎች ጌታን እንደ ፈጣሪያቸው እና ንጉሳቸው እንዲቀበሉ አነሳስቷቸዋል።
በመዝሙራት ውስጥ ስለ “አዲስ መዝሙር” የሚናገሩት የተለመዱ መሪ ሃሳቦች በተለይም
በእግዚአብሔር ስለመታመን፣ ለድንቅ ስራዎቹ ውዳሴ ማቅረብ እና ከመከራ ስላዳናቸው
የሚቀርቡ ናቸው።
ኢሳ 42:10–12፣ ራእ 5:9 እና ራእ 14:3ን ያንብቡ። ከእነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ጥቅሶች ስለ “አዲስ መዝሙር” ምን ማለት እንችላለን?
የእግዚአብሔር ሕዝቦች እስራኤል በፍቅር አገላለጽ “ወደ እርሱ [እግዚአብሔር]
የቀረበ ሕዝብ” ተደርገው ተገልጸዋል (መዝ 148:14) ከፍጥረት ሁሉ እስራኤል ከሁሉ የላቀ
ቦታ እንዳላት ያመለክታል፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን ለማመስገን ከሁሉ የላቀ ግዴታና
መብት ተሰጥቷታል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ትውልድ የበጉ ደም ስላለው
ማዳን ልዩ ምስክርነት በመስጠት በአዲስ መዝሙር እንዲያወድሱ ያበረታታል። “አዲስ
መዝሙር” ከዚህ በፊት ማንም ሰምቶት የማያውቀውን በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ
የእግዚአብሔርን ፀጋ ልምምዶች የሚዘክር አዲስ መዝሙር ነው። በተጨማሪም “አዲሱ
መዝሙር” የመዝሙሩ አዲስነት ወደፊት ታይቶ የማይታወቅ የአምላክን ግርማ ተሞክሮ
በመጠባበቅ ላይ ያለውን ተስፋ መግለጽ ይችላል። እውነተኛው አምልኮ ከመሥዋዕቶችና
ከስጦታዎች ባለፈ ከአምላክ ጋር ያለውን ሕያው ዝምድና የሚያንጸባርቅ ሲሆን ሁልጊዜም
ትኩስና ተለዋዋጭ ነው። አንድ ሰው “አዲሱ መዝሙር” አምላክ ላደረገልን ነገሮች ያለንን
ፍቅርና አድናቆት በየዕለቱ የሚገልጽ አዲስ መግለጫ ነው ማለት ይቻላል።
በህይወትዎ በተደረጉልዎ የእግዚአብሔር በረከቶች ላይ ትኩረት ያድርጉ። አዲስ መዝሙር
መዘመር ቢፈልጉ መዝሙርዎ ምን ይሆን?
መዝሙር 15ን ያንብቡ። በእግዚአብሔር ፊት ማምለክ የሚገባቸው ሰዎች እነማን ናቸው?
በዚህ መዝሙር ውስጥ የሚሰጠው መልስ አስቀድሞ በእግዚአብሔር ሕግና
በነቢያት የተሰጡት መስፈርቶች ማጠቃለያ ነው፡ እነዚያ በተግባራቸው (“ጽድቅን
የሚያደርጉ”) እና ባሕርያቸው (“በልባቸው”) (ዘዳ 6፡5፣ ሚክ 6፡6-8) የእግዚአብሔር
ባህርይ ነጸብራቅ ናቸው። መቅደሱም የተቀደሰ ስፍራ ነበር፤ ካህናቱን ጨምሮ በውስጡ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
ያለው ሁሉም ነገር የተቀደሰ ነው። ስለዚህ፣ ቅድስና ወደ እግዚአብሔር መገኘት ለመግባት
አስገዳጅ መስፈርት ነው። የእስራኤል ቅድስና ሁሉን አቀፍ፣ አምልኮን ከሥነ ምግባር ጋር
አንድ የሚያደርግ እና በሁሉም የሕይወት ዘርፎች የሚለማመዱት መሆን ነበረበት። ህጉ
ለእግዚአብሔር ህዝብ የተሰጠው የሚጠቀምባቸውን ማለትም፣ እንደ መንግስት ካህናት
የመኖር መስፈርት እንዲያሟሉ ለማስቻል ነው፣ ። የንጉሥ ካህናት መሆን በእግዚአብሔር
ፊት የቅድስና ሕይወትን መኖርንና የቃል ኪዳኑን በረከቶች ለሌሎች ሕዝቦች ማምጣትን
ያካትታል።
መዝሙር 24፡3–6 እና መዝሙር 101፡1–3ን ያንብቡ። ቅዱስ መሆን ማለት ምን ማለት
ነው?
“ፍጹም ልብ” በእግዚአብሔር ፊት የአምላኪዎቹ ታላቁ የባሕርይ ደረጃ(ጥራት)
ነው። የዕብራይስጥ ታሚም “ፍጹም” የሚለው “ፍጹምነት” እና “ምሉዕነት” የሚለውን
ሐሳብ ያስተላልፋል። “ፍጹም” የሆነ የወይን ግንድ ምሉዕ፣ ያልተጎዳ እና ጤናማ ነው
(ሕዝ 15፡5)። ለመሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሳት ተሚም ወይም ነውር የሌለባቸው መሆን
አለባቸው (ዘሌ 22፡21–24)። “ፍጹም” ንግግር ሙሉ በሙሉ እውነት ነው (ኢዮብ 36፡
4)። ስለዚህ “ፍጹም ልብ” “ንጹሕ ልብ” (መዝ 24፡4) ወይም ሀቀኛ ልብ (መዝ 15፡2)
ነው። እግዚአብሔርን የሚፈልግ (መዝ. 24፡6) እና በእግዚአብሔር ይቅርታ እንደገና
የታደሰ ነው (መዝ 51፡2-10)። ነቀፋ የሌለበት ሕይወት የሚመነጨው ለእግዚአብሔር ጸጋ
እና ጽድቁ እውቅና ከመስጠት ነው።
መለኮታዊ ጸጋ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እግዚአብሔርን በመፍራት እንዲኖሩ
ያነሳሳቸዋል ያስችላቸዋልም፣ ይህም ማለት ከእግዚአብሔር ጋር በማይደናቀፍ ህብረት ውስጥ
ለቃሉ በመገዛት ይኖራሉ ማለት ነው። የታመነ እና የቀና ህይወት ምስክርነት ለራስ ሳይሆን
ለእግዚአብሔር ምስጋናን ያመጣል። በመዝሙር 15 ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ መስፈርቶች
የተሰጡት በአሉታዊ መልኩ መሆኑን እናስተውል (መዝ 15፡3-5)። ይህ የእግዚአብሔርን
ሞገስ ስለማግኘት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ከሚለዩን ነገሮች ስለመራቅ ነው።
ከእግዚአብሔር እንድንርቅ ከሚያደርጉን ነገሮች ለመራቅ ምርጫችንን በጥንቃቄ ማድረግ
የምንችለው እንዴት ነው? ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው? እነዚህን
ነገሮች ከማድረግ መቆጠብ የምንችለውስ እንዴት ነው?
መዝሙር 96ን ያንብቡ። በዚህ መዝሙር ውስጥ የተገለጹት የአምልኮ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?
አምልኮ ለእግዚአብሔር መዘመርን (መዝ 96፡1፣ 2)፣ ስሙን ማወደስን (መዝ 96፡
2)፣ ቸርነቱንና ታላቅነቱን ማወጅን (መዝ 96፡3፣ 4) እንዲሁም ስጦታዎችን ወደ መቅደሱ
ማምጣትን ያካትታል (መዝ 96፡8)። ከእነዚህ የተለመዱ የአምልኮ ባህሪያት በተጨማሪ፣
መዝሙር 96 በጣም ግልጽ ያልሆነውን የአምልኮ ገጽታ ማለትም፣ የጌታን መንግስት
ለሌሎች ህዝቦች የማወጅ የወንጌላዊነትን ገጽታ ያጎላል (መዝ 96፡2፣ 3፣ 10)።
ነገር ግን መዘመር፣ ማመስገን፣ ስጦታ ማምጣት እና ወንጌልን ማወጅ የተለዩ
ተግባራት ሳይሆኑ የተለያዩ የአምልኮ ሥርዓቶች ናቸው። የእግዚአብሔርን ማዳን
ለአሕዛብ ሁሉ ማወጅ ለምስጋና ምክንያትንና ለአምልኮ ይዘትን ይሰጣል። የአምልኮ
ምክንያቶች ለሌሎች ከሚታወጅ መልእክት ጋር እንዴት እደሚጣጣም የሚከተሉት
ጥቅሶች ልብ ብለው ይመልከቱ፡- “እግዚአብሔር ታላቅ ነውና” ( መዝ 96:4 ) “የአሕዛብ
አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸውና፣ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ” (መዝ 96:4)፣
“እግዚአብሔር ይነግሣል“ (መዝ. 96፡10)፣ እና “እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል“
(መዝ. 96፡13)። ለሌሎች ሕዝቦች ከታወጀው መልእክት ጋር የአምልኮ ምክንያቶች
እንዴት እንደሚመሳሰሉ ልብ ይሏል። (መዝ 96፡5)፣ “‘እግዚአብሔር ነገሠ’” (መዝ 96፡10)
“በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል” (መዝ 96፡13)። ስለዚህ፣ የወንጌል ስርጭት ግብ ሌሎች
ህዝቦችን ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር በመጨረሻም ፍጥረትን ሁሉ በጌታ አምልኮ ውስጥ
አንድ ማድረግ ነው (መዝ 96፡11-13)።
አምልኮ የሚመነጨው ጌታ ማን እንደ ሆነ ማለትም ፈጣሪ፣ ንጉሥ እና ፈራጅ
መሆኑን ከማወቅ ነው (መዝ 96፡5፣ 10፣ 13)። ስለዚህ አምልኮ የእግዚአብሔርን ያለፈውን
ሥራ (ፍጥረትን) ማስታወስን፣ አሁን ያለውን ተአምራቱን (እግዚአብሔር ዓለምን መደገፉን
እና የአሁን ገዥነቱን) ማክበርን እና የወደፊቱን ሥራዎቹን (የፍጻሜውን ጊዜ ፍርድ እና
በአዲስ ሰማይና ምድር አዲስ ሕይወት) ማክበርን ያካትታል።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
በመዝሙራት ውስጥ ፍርድ ማለት በአሁኑ ጊዜ በፍትህ መጓደልና በመከራ
በተጨናነቀው ዓለም ውስጥ መለኮታዊውን የሰላም፣ የፍትህ እና የደህንነት ስርዓት
መመለስ ማለት ነው። ስለዚህም ምድር ሁሉ የእግዚአብሔርን ፍርድ በመጠባበቅ ደስ
ይላታል (መዝ 96፡10–13፣ መዝ 98፡4–9)። በተጨማሪም ጌታ ጻድቅ ፈራጅ የመሆኑ
እውነታ ሰዎች እርሱን በቅድስና እንዲያመልኩ እና በፊቱ “እንዲንቀጠቀጡ” ሊያነሳሳ
እና አምልኮን ቀላል አድርገው እንዳይመለከቱ ሊያስጠነቅቃቸው ይገባል (መዝ 96፡
9)። አምልኮ ትልቅ ደስታን እና መተማመንን (መዝ 96፡1፣ 2፣ 11-13) እንዲሁም የተቀደሰ
ፍርሃትና አክብሮትን ያካትታል (መዝ 96፡4፣ 9)።
ፈጣሪንና ፈራጅን እንዲያመልኩ በመዝሙር 96 ላይ የቀረበው ዓለም አቀፋዊ
ተማጽኖ እግዚአብሔር ለዓለም ባቀረrበው የመጨረሻው የወንጌል አዋጅ፣ በራእይ 14፡
6–12 ባሉት በሦስቱ መላእክት መልእክቶች ውስጥ ተንጸባርቋል። ይህ መዝሙር በብዙ
መልኩ ይህን የፍጻሜ ዘመን መልእክት፡- ፍጥረትን፣ መቤዠትን (“የዘላለም ወንጌልን”)፣
አምልኮን እና ፍርድን ሁሉንም ያካተተ ይመስላል። ሁሉም ነገር እዚያ አለ።
ይህን መዝሙር ከሦስቱ መላእክት መልእክቶች ጋር አነጻጽሩት (ራዕ 14፡6-12)። ለዓለም
ልንሰብከው የሚገባን ይህ የፍጻሜ ዘመን መልእክት ተመሳሳይ መሠረታዊ እውነቶችን
የሚያስተምረው በምን መንገዶች ነው?
መዝሙር 40፡6–8፣ መዝሙር 50፡7–23 እና መዝሙር 51፡16–19 ያንብቡ።
እነዚህ ጥቅሶች የትኛውን ወሳኝ ጉዳይ ነው የሚያብራሩት? እግዚአብሔር በቃሉ ባዘዘው
መሥዋዕት የማይደሰትበት ምክንያት ምንድን ነው? (ዘጸ 20፡24)
እንደ ነቢያት ሁሉ መዝሙረኞቹም የተለያዩ የአምልኮ ሥርዓቶችን አላግባብ
መጠቀምን አውግዘዋል። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ እንዲህ ላለው ንቀት ምክንያት የሆነው
ዋናው ነጥባቸው ጌታ የእስራኤልን መሥዋዕቶችና በዓላትን መጥላት ሳይሆን በአምልኮና
በመንፈሳዊነት መካከል ያለው አደገኛ ርቀት ነው።
እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚገሥጸው ስለ መሥዋዕታቸውና ስለሚቃጠል
መሥዋዕት ሳይሆን በግል ሕይወታቸው ስላደረጉት ክፋትና ኢፍትሐዊ ሥራቸው
ነው (መዝ 50፡8፣ 17-21)። መዝሙራት ማሳሰቢያ የሚሰጡት መስዋዕትንና አምልኮን
በመቃወም ሳይሆን በእነዚህ አምላኪዎች በደል የታየውን ከንቱ መሥዋዕትንና ከንቱ
አምልኮን ነው ።
በውጫዊው የአምልኮ መገለጫ እና በትክክለኛ ውስጣዊ አምልኮ ተነሳሽነት
መካከል ያለው አንድነት ሲበላሽ የአምልኮ ሥርዓቶች ወደ አምላክ ከመቅረብ ይልቅ
ስርአቶቹ በራሳቸው የአምልኮ ልማድ ሆነው ይቀራሉ። ይኸውም እነዚያ የአምልኮ
ሥርዓቶች ሊጠቁሙና ሊገልጹት ከታሰበው አምላክ በተቃራኒ ሥርዓቶቹ በራሳቸው
ፍጻሜ ይሆናሉ።
ዮሐ 4:23፣ 24ን ያንብቡ። ኢየሱስ እየተናገረ ያለው መዝሙራት ከሚያስጠነቅቁት ጋር
የሚስማማ ነጥብ የትኛው ነው?
መስዋዕትነት ብቻውን በቂ አይደለም። እነዚህን መሥዋዕቶች የሚያቀርቡት
ሰዎች ልብ በንስሐ፣ በእምነት እና ለኃጢአት በማዘን ካልተሞላ መስዋእቶቹ ምን ፋይዳ
አላቸው? የኮርማ መሥዋዕቶች እንደ እ “የጽድቅ መስዋእት” በመሆን እግዚአብሔርን
ደስ የሚያሰኙት በንስሐና ልባዊ ምስጋና ሲታጀቡ ብቻ ነው (መዝ 51፡19፣ መዝ 50፡
14 ተመልከት)። ኢየሱስ ኢሳይያስን በመጥቀስ እንዲህ ሲል ገልጿል፡- “እነዚህ ሰዎች
በአፋቸው ወደ እኔ ይቀርባሉ በከንፈራቸውም ያከብሩኛል ልባቸው ግን ከእኔ የራቀ ነው”
(ማቴ. 15፡8)። መዝሙረኞቹ ያዩአቸው ችግሮች ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት
ከአንዳንድ ሰዎች በተለይም ከመሪዎቹ ጋር ያጋጠመው ተመሳሳይ ችግሮች ነበሩ።
እኛ እንደ አድቬንቲስቶች፣ ይህንን ሁሉ ብርሃንና እውቀት ይዘን፣ እውነትን ማወቅ
እና የእውነትን ስርዓት ማከናወን ብቻውን በቂ ነው ብሎ በማሰብ ወጥመድ ውስጥ
እንደማንወድቅ እርግጠኛ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
ኤለን ጂ ዋይትን “እንዴት መጸለይ እንዳለብን” A Call to Stand
Apart ገጽ 39–42ን ያንብቡ።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
የአምልኮ ማዕከሉ የንስሐ፣ የእውነተኛ ንስሐ አስፈላጊነት ነበር፡- “ንስሐ ለኃጢአት
ማዘንንና ከእርሱ መራቅን ያጠቃልላል። የኃጢአትን አስከፊነት ካላየን በቀር ኃጢአትን
መካድ አንችልም፤ በልባችን ለኃጢአት ፊታችንን እስካላዞርን ድረስ በሕይወታችን ውስጥ
እውነተኛ ለውጥ አይኖርም።
“ብዙዎች የእውነተኛ ንስሐን ተፈጥሮ መረዳት አቅቶአቸዋል። ኃጢአታቸው
በራሳቸው ላይ መከራን ያመጣል ብለው ስለሚፈሩ ብዙዎች ኃጢአት በመሥራታቸው
ያዝናሉ ውጫዊ ተሓድሶም ያደርጋሉ። ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ስሜት ይህ ንስሐ
መግባት አይደለም። ከኃጢያት ይልቅ ስለመጣባቸው መከራ ያዝናሉ። ዔሳው የብኩርና
መብቱ ለዘላለም እንደተወሰደበት ባየ ጊዜ እንዲህ ነበር ያዘነው። በለዓም በመንገዱ
ላይ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ የቆመውን መልአክ ባየው ጊዜ ፈርቶ የተንቀጠቀጠው ነፍሱን
እንዳያጣ ፈርቶ ነው እንጂ በደሉን ስላመነ አልነበረም፤ ለኃጢአቱ እውነተኛ ንስሐ፣
ዓላማውን መለወጥ፣ ክፋትን መጸየፍ አልነበረበትም። የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታውን ከካደ
በኋላ ‘ንጹሑን ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ ’ አለ። ማቴዎስ 27:4 — Ellen G.
White, Steps to Christ, pp. 22, 23.
“እግዚአብሔር በእጅ በተሠራ መቅደስ ውስጥ የሚኖር ባይሆንም የሕዝቡ
ጉባኤ በፊቱ የከበረ ነው። እርሱን ለመፈለግ፣ ኃጢአታቸውን ለመናዘዝና እርስ በርሳቸው
አንዱ ለሌላው ለመጸለይ በሚሰበሰቡበት ጊዜ በመንፈሱ ከእነርሱ ጋር እንደሚገናኝ ቃል
ገብቷል። ነገር ግን እርሱን ለማምለክ የሚሰበሰቡ ክፉውን ሁሉ ማስወገድ አለባቸው።
በመንፈስና በእውነት እንዲሁም በቅድስና ውበት ካላመለኩት በስተቀር መሰባሰባቸው
ምንም ጥቅም የለውም። ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‘ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ
ይቀርባል በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ነገር ግን ልባቸው ከእኔ በጣም የራቀ ነው።’ ማቴዎስ
15:8, 9 እግዚአብሔርን የሚያመልኩ “ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና
በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ
ያሉትን ይሻልና፤።’ — ዮሐንስ 4: 23 ”— Ellen G. White, Prophets and Kings, p. 50.
1. አምላኪዎቹ ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ትልቁ መባ ምንድን ነው(መዝ 40፡
አምላኪዎቹ ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ትልቁ መባ ምንድን ነው(መዝ 40፡
6–10፤ ሮሜ 12፡1፣ 2)?
2. የግልና የጋራ አምልኮ እንዴት ይዛመዳሉ? ለምንድን ነው እኛ በእርግጥ ሁለቱም
የግልና የጋራ አምልኮ እንዴት ይዛመዳሉ? ለምንድን ነው እኛ በእርግጥ ሁለቱም
የሚያስፈልጉን? አንዱ ሌላውን የሚያጎለብተው እንዴት ነው?
3. ብዙ ሰዎች አምልኮን የሚገነዘቡት መጸለይ፣ መዝሙር መዘመርን፣ እና መጽሐፍ
ብዙ ሰዎች አምልኮን የሚገነዘቡት መጸለይ፣ መዝሙር መዘመርን፣ እና መጽሐፍ
ቅዱስን እና መንፈሳዊ ጽሑፎችን በማንበብ ብቻ እንደሆነ ነው። እነዚህ ተግባራት
ለአምልኮ አስፈላጊ ቢሆኑም አምልኮ በእነርሱ ብቻ የተወሰነ ነውን? ስለ ሌሎች
የአምልኮ ዓይነቶች አንዳንድ ምሳሌዎችን ስጡ።
4. ኤለን ጂ ዋይት እንዲህ በማለት ጽፋለች፡- “አገልግሎት ልብን እንደሚያሳዝን፣
ኤለን ጂ ዋይት እንዲህ በማለት ጽፋለች፡- “አገልግሎት ልብን እንደሚያሳዝን፣
የሚያስጨንቅ ተደርጎ መታየት የለበትም። ጌታን ማምለክና በሥራው መካፈል
የሚያስደስት ሊሆን ይገባል።”—Steps to Christ, p. 10
3. ጌታን
ማምለክ ተድላ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?