የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት መዝ 84፤ ራእይ 21:3፤ መዝ 122፤ መዝሙረ ዳዊት 87፤ ገላ 3:28፣
29፤ ማቴ 28:18–20፤ መዝ 46፤ መዝ 125ን ያንብቡ።
የመታሰቢያ ጥቅስ፡- ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወድዳለች ትናፍቅማለች፤ ልቤም ሥጋዬም በሕያው አምላክ ደስ ተሰኘ።
(መዝሙረ ዳዊት 84፡2)።
የጽዮን መዝሙሮች የጽዮንን ውበት እና ከቅዱሱ ተራራ ላይ የነገሠውን
የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት የሚያጎሉ የደስታ ዝማሬዎች ናቸው። እነዚህ
መዝሙሮች በሌሎች መዝሙሮች ውስጥ እንደሚገኘው ሁሉ ብዙውን ጊዜ የጌታን
ቤት መልካምነት የሚያወድሱና ለመቅደሱ ያላቸውን ፍቅርም የሚገልጹ ናቸው። ከእነዚህ
መዝሙሮች ውስጥ ብዙዎቹ የተቀናበሩት የጌታን ቤት ለመባረክ እንደ ቤተ መቅደሱ
ሙዚቀኞች (1 ዜና 6፡31-38) እና የቤተ መቅደሱን በሮች ጠባቂዎች በተደረጉት በቆሬ
ልጆች ነበር (1 ዜና 9፡19)።
ጽዮንን የተስፋና የደስታ ምንጭ ያደረጋት ምንድን ነው? ጽዮን በሕዝቡ መካከል
የእግዚአብሔርን ሕያው መገኘት ትወክላለች። የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር
የተመረጠ ሕዝብ እንደ ሆነ (ዘዳ 7፡6) ጽዮንም በእግዚአብሔር የተመረጠ ተራራ ናት
(መዝ 78፡68፣ መዝ 87፡2)። እግዚአብሔር በጽዮን ነገሠ (መዝ 99፡1፣2) መቅደሱንም
በጽዮን ላይ መሰረተ (መዝ 87፡1)። ስለዚህም ጽዮን የመለኮታዊ በረከት እና መጠጊያ ቦታ
ናት። ጽዮን ብዙ ጊዜ በኢየሩሳሌም እና መቅደሱ ለጥንቱ ዓለም የእግዚአብሔር የማዳን
ሥራ ማዕከል ሆና በንጽጽር ትጠቀሳለች።
የጌታ ማንነት እና ፀጋ ከማንኛውም የተቀደሰ ቦታ ወሰን በላይ ስለሆነ የጽዮን
በረከቶች እስከ ምድር ዳርቻ ሞልተው ይትረፈረፋሉ። ጽዮን የምድር ሁሉ ደስታ ናት
(መዝ 48፡2) ምድር ሁሉ የእግዚአብሔር መሆኗን ያረጋግጣል።
ለመጋቢት 7 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥኑ።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
መዝሙር 84:1–4ን ያንብቡ። መዝሙረኛው በመቅደሱ ውስጥ ለመኖር የሚፈልገው ለምንድን ነው?
መዝሙረኛው መቅደሱን ቋሚ መኖሪያው ለማድረግ “ይናፍቃል፣” “ይወዳል”
(መዝ 84፡1፣ 2)። የሕያው እግዚአብሔር መገኘት (መዝ 84፡2) መቅደሱን ልዩ ቦታ
ያደርገዋል። በመቅደሱ ውስጥ አማኞች “የእግዚአብሔርን ውበት ማየት ይችላሉ” (መዝ
27: 4፤ ደግሞ መዝ 63: 2 ን ተመልከት)፤ “በቤትህ ቸርነት ይረካሉ” (መዝ 65: 4)።
በመዝሙር 84፣ ወደር የለሽ ደስታ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ግንኙነት ነው፣
እሱም እግዚአብሔርን ማመስገን (መዝ 84፡4)፣ በእርሱ ብርታት ማግኘት (መዝ 84፡
5) እና በእርሱ መታመንን ያካትታል (መዝ 84፡12)። መቅደሱ እንዲህ ያለውን የአምልኮ
ህብረትና ከእምነት ባልንጀሮቻቸው ጋር በመገናኘት መንፈሳዊ በረከቶችን የሚመገቡበት
ቦታ ነው። በመቅደስ ውስጥ የሕያው እግዚአብሔር መገኘት አማኞቹ የእግዚአብሔርን
የክብር መንግሥት ጨረፍታ እና የዘላለም ሕይወት ጣዕም ይሰጣቸዋል።
መዝሙር 84:5–12ን ያንብቡ። በመቅደሱ ሌላ ማን ሊባረክ ይችላል?
የእግዚአብሔር በረከቶች ከመቅደሱ ውስጥ በመጀመሪያ በመቅደስ ውስጥ
ለሚያገለግሉት (መዝ 84፡4)፣ ከዚያም ወደ መቅደሱ በሚጓዙት ምዕመናን ላይ (መዝ 84፡
5-10) እና በመጨረሻም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንደሚንፀባረቁ ተገልጿል። እግዚአብሔርን
በመቅደሱ ውስጥ የመገናኘት ተስፋ የእምነት ተጓዥ ምእመናንን እምነት ያጠናክራል (መዝ
84፡7)። የመናኝ መንገደኛ ብርታት ከአድካሚው ጉዞ ሸክም የተነሳ እየደከመ ሲሄድ፣ ወደ
መቅደሱ የሚሄዱ ተጓዦች ብርታት ወደ መቅደሱ በቀረቡ ቁጥር ይጨምራል።
ምንም እንኳን በአካል ከመቅደስ ቢርቁ፣ የእግዚአብሔር ልጆች ገጣሚ ህይወት
በመኖር የእግዚአብሔርን መቅደስ ማህተም ይዘው ይቀጥላሉ (መዝ 84፡11) ይህም ወደ
ጌታ መቅደስ የሚገቡትን ጻድቃን ያሳያል (መዝ 15፡1፣ 2)። ጌታ “ፀሀይ” ተብሎ ተጠርቷል፤
ይህም ከመቅደሱ የሚገኘው በረከቶች ልክ እንደ የፀሐይ ጨረሮች እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ
ይደርሳል (መዝ 84: 11) ማለት ነው። ስለዚህ፣ በእምነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖሩት
በቦታ ርቀት ሳይገደቡ ጸጋውን ይቀበላሉ።
ራእይ 21:3ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ በምድራዊው መቅደስ ተንጸባርቆ የነበረው ምን ተስፋ
ለእኛ ተገለጠልን? ይህ ተሞክሮ ምን እንደሚመስል መለማመድ እንዴት እንጀምራለን?
መዝሙር 122:1–5ን ያንብቡ። ምእመናኑ ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የሚሰማቸው ስሜት ምንድን ነው? በኢየሩሳሌም ለማግኘት ተስፋ የሚያደርጉት ምንድር ነው?
መዝሙር 122 ተጓዦቹ ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የተሰማቸውን ደስታና ግለት
ይገልጻል። ወደ ኢየሩሳሌም የሚደረጉ ጉዞዎች የእግዚአብሔር ሕዝቦች የእግዚአብሔርን
ቸርነት ለማክበር በዓመት ሦስት ጊዜ የሚሰበሰቡበት አስደሳች አጋጣሚዎች ነበሩ (ዘዳ
16፡16)። ኢየሩሳሌም “የእስራኤልን ምስክር” (መዝ 122፡4) እና የፍርድ ዙፋኖችን
ስለያዘች የሀገሪቱ የህይወት ማእከል ነበረች (መዝ 122፡5)። “የእስራኤል ምስክር”
የሚያመለክተው አንዳንድ ጊዜ “የምስክሩ ድንኳን” (ዘኁ 1፡50) ተብሎ የሚጠራውን እና
“የምስክሩን ታቦት” (ዘፀ 25፡22) የያዘውን መቅደስ ነው። ለፍርድ የተቀመጡት ዙፋኖች
የኢየሩሳሌምን የፍርድ ሥርዓት ያመለክታሉ (2ሳሙ 8፡15)። ስለዚህ አንድ ተጓዥ ፍትህን
የሚፈልግበት እና የሚያገኝበት ጊዜ ነበር። ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን እና ለሰዎች
ፍትህ መስጠት ፈጽሞ አይለያዩም ነበር።
መዝሙር 122:6–9ን ያንብቡ። የእግዚአብሔር ሕዝብ ዋና ጸሎት ምንድን ነው?
ለኢየሩሳሌም ሰላም መጸለይ በከተማይቱ እና በነዋሪዎቿ ላይ የእግዚአብሔርን
በረከቶች እንዲመጡ ያደርጋል፤ የሚያመልኩትንም አንድ ያደርጋቸዋል፣ በመካከላቸውም
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል (መዝ 122: 8)። በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል እና
በራሳቸው በእግዚአብሔር ልጆች መካከል ሰላም ካለብቻ ነው ኢየሩሳሌም የሰላም
ከተማ ልትሆን የምትችለው። ስለዚህ፣ ለኢየሩሳሌም ሰላም መጸለይ፣ የአምላክ ሕዝቦች
ከአምላክ ጋር እና እርስ በርሳቸው በሰላም እንዲኖሩ የተማጽኖ መልእክት ያስተላልፋል።
በኢየሩሳሌም ሰላም ሲኖር ሕዝቡ ይበለጽጋል (መዝ 147፡12-14)።
ለእምነት ማህበረሰብ ደህንነት የሚቀርበው ጸሎት የእግዚአብሔር ልጆች የጸሎት
ዋና ርዕሰ ጉዳይ ሊሆን ይገባል ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ሰላምና ማዳን የምስራች
ለአለም የሚሰብከው ብርቱ እና አንድነት ያለው የእግዚአብሔር ህዝብ ብቻ እንደሆነ
መዝሙራት ያስተምራሉ (ዮሐ 13:34፣ 35)።
ለኢየሩሳሌም ሰላም መጸለይ አሁንም የምእመናን ዕድል እና ኃላፊነት ነው
ምክንያቱም በፍጻሜው ጊዜ የሚመጣው የእግዚአብሔር የሰላም መንግሥት ተስፋን
የሚጠብቅ ሲሆን ይህም የኢየሩሳሌምን ከተማ ብቻ ሳይሆን መላውን ዓለም የሚያቅፍ
ነው (ኢሳ 52:7፣ ኢሳ 66:12፣ 13፣ ራእይ 21-22)።
አሁን እንደ ሕዝብ በመካከላችን ሰላም እንዲኖር ጥረት የምናደርግባቸው ተግባራዊ
መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
መዝሙር 87:1 2ን ያንብቡ። ጽዮንን እንደዚህ የተከበረ ቦታ ያደረጋት ምንድን ነው?
መዝሙር 87 ጽዮንን በእግዚአብሔር እንደተመረጠች ልዩ እና የተወደደ ከተማ
የሚያወድስ መዝሙር ነው። የእግዚአብሔር መቅደስ መሠረት በጽዮን ተራራ ነው (መዝ 2፡6፣
መዝ 15፡1)። በጊዜ ፍጻሜ፣ ጽዮን ከተራሮች ሁሉ በላይ ከፍ ብላ ትታያለች፣ ይህም በዓለም ሁሉ
ላይ የጌታን ሉዓላዊነት ያሳያል (መዝ 99:2፣ ኢሳ 2:2፣ ሚክ 4:1)። መዝሙር 87 የጽዮንን ግርማ
ለማጉላት “ተራሮች” በማለት ይጠቅሳል (መዝ 133፡3)። እግዚአብሔር “ከያዕቆብ ድንኳኖች ሁሉ
ይልቅ”(መዝ 87:2) የጽዮንን በሮች ይወዳቸዋል፤ ጽዮንን በጥንት ዘመን በእስራኤል ከነበሩት
ከሌሎቹ እንደ ሴሎና ቤቴል ያሉ የመሰብሰቢያ ስፍራዎች ሁሉ የላቀች መሆኑን ገልጿል።
ስለዚህ፣ መዝሙሩ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው እውነተኛ አምልኮ በመረጠው
ቦታና በደነገገው መንገድ መሆኑን ያረጋግጣል።
መዝሙር 87:3–7ን ያንብቡ። ስለ ጽዮን የተነገሩት የከበሩ ነገሮች ምንድን ናቸው?
የጽዮን ክብር አሕዛብን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ይስባል፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር
መንግሥት ድንበሮች መላውን ዓለም ለማካተት ተዘርግተዋል። ጽዮን ጌታን እንደ
አዳኛቸው ለሚቀበሉ ሰዎች ሁሉ መንፈሳዊ መፍለቂያ ቦታ ሆና ብትገለጽም እግዚአብሔር
ሌሎቹን ሕዝቦች እንደ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ እንደማይመለከታቸው እናስተውል።
የሕዝቡ ምዝገባ የተካሄደው እንደ የትውልድ ቦታቸው ነው (ነህ 7፡5፣ ሉቃ 2፡1–3)።
መዝሙሩ ሦስት ጊዜ ሕዝቦች በጽዮን መወለዳቸውን ይናገራል፣ ይህም ማለት ጌታ በሰጣቸው
አዲስ ማንነት የተወለዱ ሕጋዊ የጽዮን ልጆች የመሆን ዕድል (መዝ 87፡4-6) ነው።
መዝሙር 87 የአይሁድንም ሆነ የአሕዛብን መዳን እና በክርስቶስ የመቤዠት
አገልግሎት የአንዲት ቤተ ክርስቲያን አካል መሆናቸውን ያሳያል (ሮሜ 3፡22፤ ሮሜ 10፡12፤
ገላ 3፡28፣ 29፤ ቆላ 3፡11)። መዝሙሩ ስለ ጽዮን ብልጽግና በዳንኤል ራእይ የእግዚአብሔር
መንግሥት ምድርን ሁሉ የሚሞላ ትልቅ ተራራ እንደሚሆን (ዳን 2:34፣ 35፣ 44፣ 45) እና
ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በተናገረው ምሳሌ ትልቅ ዛፍ እንደሚሆንና የሰማይ
ወፎች ሁሉ የሚሰፍሩበት እንደሚሆን (ማቴ 13፡32) ይገልጻል።
ጽዮን ሰዎችን ሁሉ ለመቀበል መዘጋጀቷ በቤተ ክርስቲያኗ ታላቅ ተልእኮ ወንጌልን ለእያንዳንዱ
ሀገር በመስበክ ፍጻሜ የሚያገኘው እንዴት ነው? (ማቴ 28፡18-20)። ይህ ሀሳብ እንዴት
ነው የሦስቱን መላእክት መልእክት ለመስበክ ለኛ ከመጣልን ጥሪ ጋር የሚስማማው?
መዝሙር 46:1–7ን ያንብቡ። በዚህ ግጥም ዓለም እንዴት ነው የታየው?
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
መዝሙሩ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ኃይለኛ የተፈጥሮ አደጋዎች በሁከት
ውስጥ ስላለው ዓለም ምስሎች ቁልጭ ያለ መግለጫ ይሰጣል (መዝ 46:2፣ 3)። ብዙውን
ጊዜ ዓመፀኛ ሕዝቦችንና ክፉዎች በዓለም ላይ የሚያደርሱትን የተለያዩ ችግሮች በታወከ
ውኃ መልክ ስሎ ያሳያል (መዝ 93:3፣ 4፤ መዝ 124:2-5)። እንደዚሁም፣ በመዝሙር 46
ላይ በተፈጥሮ አደጋዎች እና በጦርነት የሚታወክ ሕዝብ የሚቆጣጠረውን ዓለም ያሳያል
(መዝ 46፡6)። ዓለም እግዚአብሔርን እንደማያውቅ ግልጽ ነው፤ ምክንያቱም በህዝቡ
መካከል እግዚአብሔር አለ፤ እግዚአብሔር ባለበት ደግሞ ብዙ ሰላም አለ (መዝ 46: 4፣ 5)።
ሆኖም፣ ዓለም ቢክደውም፣ እግዚአብሔር ዓለምን አልተወውም። እግዚአብሔር በሕዝቡ
መካከል በመሆን በዓለም ውስጥ አለ። በሌላ አነጋገር፣ የቱንም ያህል መጥፎ ነገሮች ቢታዩ፣
በዓለማችን ውስጥ የእግዚአብሔር ህልዎት አለ፣ ስለሆነም ይህን መሰረታዊ እውነት
በማወቅ የግላችን ተስፋ እና ማበረታቻ ማግኘት እንችላለን። ፍጹም መጠጊያ የሆነው ጌታ
የጽዮን ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ምንጭ ነው። “ቢሆንም” የሚለው ቃል የጽዮንን ደኅንነት
በመዝሙር 46፡3 ላይ አጉልቶ ያሳያል። ዓለም በትርምስ ውስጥ ብትሆንም የእግዚአብሔር
ሰዎች ግን ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው። ይህ የሚያሳየው ሰላም የፈተናዎች አለመኖር
ሳይሆን እግዚአብሔር ለሚታመኑት ልጆቹ የሰጣቸው ስጦታ መሆኑን ነው።
በእግዚአብሔር ላይ ያልተቆጠበ እምነት የእግዚአብሔርን ልጅ በማዕበል መካከል ሰላም
እና ደህንነቱ አስተማማኝ እንዲሆን ያደርጋል (ማቴ 8፡23–27)። እዚህ ጋ የሚነሳው ጥያቄ
ቢኖር፡- እግዚአብሔር ዓለምን ለአጥፊ ምርጫዎቿ እና ድርጊቶቿ ለዘላለም ይተዋት ይሆን?
መዝሙር 46:6–11ን ያንብቡ። እግዚአብሔር በዓለም ላይ ለሚደርሰው ዓመፅና ጥፋት የሚሰጠው ምላሽ ምንድን ነው?
የእግዚአብሔር ምድርን የፈጠረው ቃሉ አሁን ደግሞ ምድርን እንድትቀልጥ
እስኪያደርግ ድረስ በምሬት ኃይል ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል (መዝ 46፡6)። ሆኖም ያ
መቅለጥ የሚያበቃው እንደገና በማደስ እንጂ በጥፋት አይደለም። እግዚአብሔር ሰላሙን
ከጽዮን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንደዘረጋ አስተውል:: እግዚአብሔር ጦርነቶችን ያቆማል
ክፉ ሕዝቦች በዓለም ላይ ጭቆናን ለማምጣት የተጠቀሙባቸውን የጥፋት መሣሪያዎች
ያጠፋል (መዝ 46፡9)። ይህ በኢየሱስ ዳግም ምጽዓት ጊዜ የሚፈጸም ክርስቲያኖች
ያላቸው ታላቅ ተስፋ ነው።
ብዙ ግርግር ባለበት ዓለም ውስጥ ሰላም እንዲኖረን እና በእግዚአብሔር መታመንን እንዴት
እንማራለን?
መዝሙር 125:1፣ 2ን ያንብቡ። በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሰዎች እዚህ ጋ የተገለጹት እንዴት ነው?
በእግዚአብሔር የታመኑ የጽናትና የኀይል ምልክት ከሆነው ከጽዮን ተራራ ጋር
ይመሳሰላሉ። በኢየሩሳሌም ከተማ ዙሪያ ያሉትን ተራሮች አስደናቂ እይታ መዝሙረኛው
የመለኮታዊ ጥበቃን እርግጠኝነት እንዲገነዘብ አነሳሳው (መዝ 5:12፣ መዝ 32:7፣ 10)።
በክፉዎች ከሚገዙት ተራሮች በተለየ መልኩ (መዝ 46:2) ኢየሩሳሌም የታነጸችበት ተራራ
ለረጅም ጊዜ መቆየቱ ትልቅ እምነት እንዲጥል አድርጓል። ክፋት ብዙ ጊዜ የሚያሸንፍ
በሚመስለው የሚያም እውነታ ፊት በእግዚአብሔር ጥበቃ ላይ ያለው እምነት ይበልጥ
ደፋር እንዲሆን አድርጎአል። ሆኖም፣ በዚያ ክፋት ውስጥም እንኳ፣ የእግዚአብሔር
ሕዝቦች ተስፋ አላቸው።
መዝሙር 125:3–5ን ያንብቡ። ጻድቃን እንዴት ይፈተናሉ? እኛስ ምን ትምህርት
እናገኝበታለን?
የእግዚአብሔር ልጆች በክፉዎች ስኬት ተስፋ ሊቆርጡ እና ምናልባትም
መንገዳቸውን ለመከተል ሊፈተኑ ይችላሉ (መዝ 73፡2–13፣ መዝ 94፡3) ። የጽዮን ተራራ
ፍፁም ሰላማዊ መሆን ከጌታ የሚርቁትን ማዳን አይችልም። ሕዝቡ አሁንም “እጃቸውን
ወደ ኃጢአት እንዲዘረጉ” (መዝ 125፡3) እና “ወደ ጠማማ መንገዳቸው እንዲመለሱ”
(መዝ. 125፡5) ነፃነት ተሰጥቷቸዋል።
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት
ጌታ ጻድቅ ነው፤ በአመፅ ውስጥ የሚቀጥሉ ግለሰቦችን ከሌሎች ንስሃ ካልገቡ
ኃጢአተኞች ጋር ይፈርዳል። የጽዮን ተራራ የማይነቃነቅ መጠጊያቸው እንደሆነ ሁሉ
የእግዚአብሔር ሕዝብ በእምነት የማይነቃነቁ ሆነው እንዲቆዩ እና በጌታ እንዲታመኑ ጥሪ
ቀርቦላቸዋል። የነገሮችን ምንነት ባንረዳም እንኳን በእግዚአብሔር ቸርነት መታመን
እንችላለን።
“የኃጢአት ወደ ዓለም መግባት፣ የክርስቶስ መገለጥ፣ ዳግም መወለድ፣ ትንሣኤ፣
እና ሌሎች በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቀረቡት የሰው ልጅ አእምሮ
ሊረዳው ወይም ሙሉ በሙሉ ሊያስተውለው የማይችለው ምሥጢር ነው። ነገር ግን የእርሱን
ምስጢር ሙሉ በሙሉ መረዳት ስለማንችል የእግዚአብሔርን ቃል የምንጠራጠርበት
ምንም ምክንያት የለንም። . . . ከኛ መረዳት በላይ የሆኑ ድንቅ ነገሮች በሁሉም ቦታ አሉ።
ታዲያ በመንፈሳዊው ዓለም ልንመረምራቸው የማንችላቸው ምሥጢራት እንዳሉ ስናውቅ
ሊያስደንቀን ይገባልን? ችግሩ ያለው በሰው አእምሮ ደካማነት እና ጠባብነት ላይ ብቻ ነው።
እግዚአብሔር ስለ መለኮታዊ ባሕርይው በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ በቂ ማስረጃ ሰጥቶናል፣
እኛም ቃሉን መጠራጠር የለብንም ምክንያቱም የእሱን የአስተዋይነት ምሥጢር በሙላት
መረዳት አንችልም።”—Ellen G. White፣ Steps to Christ፣ ገጽ 106, 107
በኢሳይያስ 40 እና ምእራፍ 51:1–16 ላይ ያለውን መልእክት
አሰላስል። የጽዮን መዝሙሮች ጽዮንን ለማስታወስ እና የሚወክለውን በእግዚአብሔር
ሉዓላዊ አገዛዝ ላይ ያለውን ሕያው ተስፋ ለመጠበቅ ፍጹም ቁርጠኝነት አላቸው።
በዚህ ህይወት ውስጥ ብዙ የእግዚአብሔር መቅደስ በረከቶች ብንለማመድም፣ በጽዮን
ውስጥ ያለው የህይወት እና የደስታ ሙላት ተስፋ አሁንም ለወደፊት የተገባ ነው። ብዙ
የእግዚአብሔር ልጆች ሰማያዊቷን ጽዮንን በእንባ ይናፍቁአታል (መዝ 137፡1)። ጽዮንን
ማስታወስ የሚያመለክተው አልፎ አልፎ ማሰብን ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ሆን ብሎ
ማሰብን እና በዚያ ሕያው ትውስታ መሠረት ለመኖር መወሰንን ያመለክታል (ዘጸ 13፡3፣
ዘጸ 20፡8)። ስለዚህ፣ የጽዮንን መዝሙሮች መዘመር፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በአዲስ
ምድር ላይ የመመለሷን ተስፋ ሕያው ለማድረግ ልባዊ ውሳኔን ይሰጣል (ራዕ 21፡1-5)።
“ሕያው የሆነው አእምሮ በፍፁም የማይጠፉ የመፍጠር ሃይል ድንቆችንና የመቤዠት
ፍቅርን ምስጢር በሚያስደስት ሁኔታ ያሰላስላል። እግዚአብሔርን ለመርሳት የሚፈትን
ጨካኝ፣ የሚያታልል ጠላት አይኖርም። እያንዳንዱ ስጦታ ይዳብራል፣ እያንዳንዱ ችሎታ
ይጨምራል። እውቀትን ማግኘት አእምሮን አያደክመውም ወይም ጉልበትን አያደክምም።
እዚያም ታላላቅ እቅዶች ወደፊት ይሄዳሉ፤ ከፍተኛ ምኞቶች ይሳካሉ፤ ከፍ ያሉ ህልሞች
እውን ይሆናሉ፤ አሁንም ከፍ ከፍ ሊሉ የሚችሉ አዲስ ከፍታዎች፣ አዳዲስ አስደናቂ
ድንቆች፣ አዳዲስ እውነቶችን ለመረዳት፣ የአዕምሮንና የነፍስንና የአካልን ኃይል የሚያነሳሱ
ትኩስ ነገሮች ይኖራሉ።”—Ellen G. White፣ The Great Controversy፣ ገጽ. 677።
ጽዮንን ያለመርሳት ቁርጠኝነት የጌታ ተጓዦች ይህንን ዓለም እንደ ሀገራቸው
ፈጽሞ እንደማይቀበሉ ነገር ግን አዲሱን ሰማይ እና አዲስ ምድር እንደሚጠባበቁ ግልጽ
የሆነ ቃል ኪዳን ነው። ስለዚህም የጽዮን መዝሙር በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለመኖር
በሚናፍቁ ትውልድ ሁሉ አማኞች ሊዘመር ይችላል (ራዕ 3፡12)። የጽዮን መዝሙሮች
የወደፊቱን ዓለም በተስፋ እንድንጠባበቅ ያበረታቱናል፣ነገር ግን በዚህ ዓለም ውስጥ
የእግዚአብሔር ጸጋ ወኪሎች እንድንሆንም ያስገድዱናል።
1. በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የሚገኙትን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ያማከለውን
በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የሚገኙትን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ያማከለውን
መንፈሳዊ እና ሥነ-መለኮታዊ መርሆችን ወስደን ቤተ ክርስቲያን ለዓለም ያላትን
ተልእኮ ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
2. አማኞች ዛሬ በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ እንዴት ሊኖሩ ይችላሉ? (ዮሃንስ
አማኞች ዛሬ በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ እንዴት ሊኖሩ ይችላሉ? (ዮሃንስ
1:14-18፣ እብ 12:22-24)
3. በመዝሙር 87 ላይ እንደተገለጸው ጽዮን የአሕዛብ ሁሉ ከተማ የምትሆነው እንዴት
በመዝሙር 87 ላይ እንደተገለጸው ጽዮን የአሕዛብ ሁሉ ከተማ የምትሆነው እንዴት ነው? (ሮሜ 5፡10፣ ኤፌ 2፡11–16፣ ቆላ 1፡19–23)።
4. በዚህ ዓለም ውስጥ ብዙ “ደግ” ሰዎች ሲሰቃዩ ክፉዎች እየበለጸጉ መሆናቸውን
በዚህ ዓለም ውስጥ ብዙ “ደግ” ሰዎች ሲሰቃዩ ክፉዎች እየበለጸጉ መሆናቸውን
ለሚናገር ሰው ምን ብለህ ትመልሳለህ? አሁን እዚህ ለሁሉም ነገር ሙሉ መልስ
እንደሌለን መቀበል አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?