የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት



1ኛ ሩብ ዓመት 2024


የካቲት 23 - 29

10ኛ ትምህርት

Mar 2 - 8




ትምህርት ካለፈው ታሪክ



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት መዝ 78፤ መዝ 105፤ ገላ 3፡29፤ መዝ 106፤ መዝ 80፤ ዘኍ 6፡ 22–27፤ መዝ 135


የመታሰቢያ ጥቅስ፡- የሰማነውንና ያውቅነውን፥ አባቶቻችንም የነገሩንን፥ ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም። የእግዚአብሔርን ምስጋናና ኃይሉን ያደረገውንም ተኣምራት ተናገሩ። (መዝሙር 78:3፣4)

በብዙ መዝሙሮች ውስጥ፣ ምስጋና የጌታን ኃያሉን የማዳን ስራዎች በትረካ መልክ ይገልጻል። እነዚህ መዝሙሮች ብዙውን ጊዜ “የመዳን ታሪክ መዝሙር” ወይም “ታሪካዊ መዝሙራት” ይባላሉ። አንዳንዶች ከታሪካቸው በተለይም ከቅድመ አያቶቻቸው ስህተት እንዲማሩ በመንገር የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ይማርካሉ። አንዳንድ ታሪካዊ መዝሙሮች ቀዳሚ የሙዚቃ ኖታ በመያዝ፣ ባለፈው ታሪክ እግዚአብሔር ሕዝቡን ወክሎ ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች የሚያጎሉ እና አሁን ካሉበት መከራ ሊያድናቸው በሚችለው እና ታማኝ በሆነው በጌታ ላይ ያላቸውን እምነት የሚያጠናክር ነው።

የታሪካዊ መዝሙራት ልዩ ተማጽኖ ህይወታችንን እንደ የእግዚአብሔር ሰዎች ታሪክ አካል አድርገን እንድንመለከት እና ያለፈውን ታሪካችንን እንድናይ ይረዱናል።

በክርስቶስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ታሪካዊ ሕዝብ ቤተሰብ እንደ ተወሰድን መጠን (ሮሜ 8:15፤ ሮሜ 9:24–26፤ ገላ 4:6፣ 7) የጥንት የእስራኤል ሕዝብ ታሪካዊ ቅርስ በእውነትም የመንፈሳዊ አባቶቻችን ታሪክ የሚያሳይ ነው። ። ስለዚህ ካለፈው ታሪካቸውና የራሳችንም ከሆነው መማር እንችላለን። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ትውልድ በታላቁ ተጋድሎ የመጨረሻው ግብ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ ዓላማዎች በታላቅ ታሪካዊ መገለጥ ውስጥ ትንሽ ነገር ግን ጉልህ ሚና እንደሚጫወት መገንዘብ ነው። ለየካቲት 30 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥኑ።

የካቲት 24
Mar 03

መቆሚያ የሌለው የጌታ ታማኝነት


መዝሙር 78ን ያንብቡ። በዚህ መዝሙር ውስጥ ጎላ ብለው የተገለጹት የትኞቹ ሦስት ዋና ዋና ታሪካዊ ዘመናት ናቸው? አሳፍ ከእያንዳንዱ ወቅት ምን ተደጋጋሚ ትምህርቶችን ይሰጣል?



የእስራኤል የቀድሞ ታሪኮች ሲገመገሙ የእግዚአብሔርን ታማኝነት እና የእስራኤልን ታማኝ አለመሆን ያጎላሉ። እንዲሁም የሚመጣው ትውልድ የአባቶቻቸውን ስህተት መድገም ሳይሆን፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር እንዲታመኑ እና ለቃል ኪዳኑ ታማኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ማስተማር አለባቸው። መዝሙረኛው ታሪክን እንደ ምሳሌ ይጠቀማል (መዝ 78: 2) ይህም ማለት ሰዎች የመዝሙሩን መልእክት በጥልቀት በማሰላሰል ለራሳቸው ትርጉም መፈለግ እንዳለባቸው ያሳያል።

መዝሙር 78፡2 የኢየሱስ በምሳሌ የማስተማር ዘዴ ትንቢታዊ መግለጫ ነው (ማቴ 13፡34፣ 35)። መዝሙሩም ስለ ዘጸአት ጊዜ (መዝ 78፡9-54)፣ በከነዓን ስለ ነበረው አሰፋፈር (መዝ 78፡55-64) እና የዳዊት ዘመን (መዝ 78፡65-72) ያንጸባርቃል። የጌታን የከበረ ተግባራት እና ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ማፍረስ ያስከተለባቸውን መዘዝ ያሳያል። የእስራኤል ታሪክ ህዝቡ ለእግዚአብሔር ታማኝ አለመሆንን በተለይም ጣዖት አምላኪነታቸውን ይተርካል (መዝ 78፡58)። መዝሙረኛው ግን የእስራኤልን ታማኝነት የማጉደል ምንጭ ምን እንደሆነ አበክሮ ገልጿል፡- እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ረሱ፣ በእግዚአብሔር አልታመኑም፣ እግዚአብሔርን ፈተኑ (መዝ 78:18፣ 41፣ 56) በእርሱ ላይ አመፁ፤ ሕጉንና ኪዳኑን፣ ምስክሩንም መጠበቅ አልቻሉም። (መዝ 78፡10፣ 37፣ 56)።

መዝሙረኛው እነዚህን የታማኝነት ማጉደል ዓይነቶች ጎላ አድርጎ በመግለጽ፣ እስራኤል በታሪክ ውስጥ በእግዚአብሔር ውድቅ መደረጉ ከአንድ ዋና ኃጢአት ይኸውም ሕዝቡ በጌታ አለመታመን የመጣ (መዝ 78፡7፣ 8) ነው በማለት ትኩረት ይሰጣል።

አንድ ሰው መዝሙሩን በሚያነብበት ጊዜ፣ በሰዎች የማያቋርጥ ግትርነት እና በመንፈሳዊ እውርነት፣ ከጌታ ወሰን የለሽ ትዕግስት እና ጸጋ በተቃራኒ ሲያይ ሊደነቅ ይችላል። እያንዳንዱ የሚመጣው ትውልድ ከዚህ ለመማር የዘገየው እንዴት ነበር? ያለፉትን ትውልዶች ከመጠን የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት በላይ ከመኮነናችን በፊት እራሳችንን ማጤን አለብን። እኛ ደግሞ ያለፈውን የእግዚአብሔርን ድንቅ ነገር የምንረሳና የቃል ኪዳኑን መስፈርቶች ቸል የምንል አይደለንም? መዝሙሩ ሰዎች በራሳቸው ሥራ እንዲታመኑ አያበረታታም። ይልቁንም፣ መዝሙር 78 የእግዚአብሔርን ታማኝነት በማያቋርጥ ግንዛቤ እና ጸጋውን በመቀበል ላይ እስካልተመሠረተ ድረስ የሰው ፈቃድ ከንቱ መሆኑን ያሳያል። መዝሙሩ የሚሰጠን ትምህርት ለእግዚአብሔር ታማኝ ከመሆን ውጪ የሰው ልጆች የሚያደርጉት ጥረትና የሚያደርጉት ጦርነት (መዝ 78:9፣ 62–64) ስኬታማ የማይሆንና በውድቀት ወደ ፍጻሜ እንደሚመጣ ያሳያል። ካለፉት ስህተቶችህ ምን ትምህርት ተማርክ ወይም መማር ነበረብህ? ካለፉት ስህተቶችህ ምን ትምህርት ተማርክ ወይም መማር ነበረብህ?

የካቲት 25
Mar 04



ታሪክን ማስታወስ እና እግዚአብሔርን ማመስገን


መዝሙር 105ን ያንብቡ። በዚህ መዝሙር ውስጥ ጎላ ብለው የተገለጹት ታሪካዊ ክንውኖችና ትምህርቶቻቸው ምንድን ናቸው?



መዝሙር 105 በጌታ እና በህዝቡ በእስራኤል መካከል ያለውን የቃል ኪዳን ግንኙነት የፈጠሩ ቁልፍ ክስተቶችን ያስታውሳል። መዝሙሩ የሚያተኩረው እግዚአብሔር የተስፋይቱን ምድር ለእርሱና ለዘሮቹ ለመስጠት ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን ላይ ነው፣ ይህ ለይስሐቅ እና ለያዕቆብ የተረጋገጠው የተስፋ ቃል በዮሴፍ፣ በሙሴ እና በአሮን በኩል ከነዓንን በተቆጣጠሩበት ጊዜ ሁኔታ ፍጻሜውን አግኝቷል። መዝሙሩ ለትውልድ ሁሉ የእግዚአብሔርን ተስፋ ይሰጣል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጥንት ጊዜ ያከናወናቸው ድንቅ ሥራዎች እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን የማይለወጥ ፍቅር በዘመናት ሁሉ ያረጋግጣሉ (መዝ. 105፡1-5፣ 7፣8)።

መዝሙር 105 ከመዝሙር 78 ጋር(የትናንት ትምህርትን ተመልከት) የእግዚአብሔርን ታማኝነት በታሪክ ማጉላት፣ እና እግዚአብሔርን ለማክበር እና ታማኝነቱን በማነሳሳት ይመሳሰላል። ይሁን እንጂ ከመዝሙር 78 በተቃራኒ መዝሙር 105 የሕዝቡን የቀድሞ ስህተቶች አይጠቅስም። ይህ መዝሙር የተለየ ዓላማ አለው። ይልቁንም፣ በመዝሙር 105 ላይ፣ በ እስራኤል ታላላቅ አባቶች የእግዚአብሔርን አጥጋቢ አመራር እና የአባቶችን በመከራ ውስጥ በትዕግሥት መጽናት በማሳየት ታሪክን በድጋሚ ያወሳል። የአበው ትእግስትና ታማኝነት በትልቁ ወሮታው ተከፍሎላቸዋል። ስለዚህ፣ መዝሙር 105 ሰዎች በእምነት አባቶችን እንዲመስሉ እና የእግዚአብሔርን ማዳን በጊዜአቸው እንዲጠብቁ ይጋብዛል። መዝሙር 105 የውዳሴ ዜማ አለው (መዝ 105፡1-7)፣ እግዚአብሔርን በእውነት ለማወደስ፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ የታሪካቸውን እውነታዎች ማወቅ እንደሚያስፈልጋቸው ያሳያል። ታሪክ ለእምነታችን ማረጋገጫ እና እግዚአብሔርን የምናመሰግንባቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ምክንያቶችን ይሰጣል። እግዚአብሔርን የሚያመልኩት የአብርሃም ዘር እና የያዕቆብ ልጆች ተብለው ተጠርተዋል (መዝ 105፡6)፣ በዚህም እግዚአብሔር አብርሃምን ታላቅ ሕዝብ ለማድረግ ለአብርሃም የገባው የተስፋ ቃል ፍጻሜ አድርገው ይቆጥሩታል (ዘፍ 15፡3-6)። መዝሙረኛው በአበው እና በሚቀጥሉት የአምላክ ሕዝቦች ትውልዶች መካከል ያለውን ቀጣይነት አጽንዖት ሰጥቷል። መዝሙረኛው “ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው” (መዝ 105፡ 7) በዚያም አማኞቹ “አምላካችንን እግዚአብሔርን” የዓለማት ሁሉ ሉዓላዊ ገዥ የሆነውን እንዲሁም ለህዝቡ ያሳየውን ቸርነት እንዳይረሱ ጥሪ ያደርጋል (መዝ 96፡1፣ መዝ 97፡1)።

ይህ ለእያንዳንዱ ለሚመጣ አማኝ ትውልድ የቀረበ ግልፅ የታማኝነት ጥሪ ነው። እኛ፣ እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች፣ እራሳችንን ከአብርሃም ጀምሮ በዚህ የሰዎች መስመር ውስጥ እንዴት ማየት አለብን? (ገላትያ 3:29ን ተመልከት።) ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርት ማግኘት አለብን?

የካቲት 26
Mar 05

ታሪክንና ንስሐን ማስታወስ


መዝሙር 106ን ያንብቡ። በዚህ መዝሙር ውስጥ ጎላ ብለው የተገለጹት የትኞቹ ታሪካዊ ክንውኖችና ትምህርቶቻቸው ናቸው?



በተጨማሪም መዝሙር 106 በእስራኤል ታሪክ ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ክንውኖችን ማለትም ከምድረ ግብጽ መውጣትን፣ በምድረ በዳ ያደረጉትን ጉዞና በከነዓን የነበራቸውን ሕይወት ጨምሮ ያሳያል። ወደ ግዞት እንዲወሰዱ ላደረጋቸው የአባቶች አስከፊ ኃጢአት አጽንዖት ይሰጣል። ስለዚህ መዝሙሩ የተጻፈው ሕዝቡ በባቢሎን በነበረበት ጊዜ ወይም ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ነው ማለት ይቻላል፤ መዝሙረኛው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እነዚህን ታሪካዊ ክንውኖችና ሕዝቡ ከእነሱ መማር የነበረባቸውን ትምህርቶች ለአምላክ ሕዝቦች ተርኳል። የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

እንደዚሁም ይህ መዝሙር፣ እንደ ሌሎቹ፣ እግዚአብሔር በጥንት ጊዜ ህዝቡን ያዳነበትን የጸጋውን ቃል ኪዳን ታማኝነት ያሳያል (መዝ 106፡45)። እግዚአብሔር እንደገና ለሕዝቡ ንስሐ ሞገስን እንደሚያሳይና ከአሕዛብም መካከል እንደገና እንደሚሰበስባቸው የገባውን ተስፋ ይገልጻል (መዝ 106፡47)። አሁን ነጻ ለመውጣት የህልም እንጀራ ዓይነት ምኞት አይደለም፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ማዳን ማረጋገጫ (መዝ 106፡1-3) እና እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር በገባው ቃል ኪዳን ታማኝነት ላይ የተመሰረተ የእምነት ጸሎት ነው። በመዝሙር 106 ላይ የተገለጸው የእስራኤል ታሪካዊ ውድቀቶችን ማስታወስ ሰዎች ኃጢአታቸውን የተናዘዙበት እና ከአባቶቻቸው ያልተሻሉ መሆናቸውን የተገነዘቡበት ዋነኛ አካል ነው። አሁን ያለው ትውልድ ከቅድመ አያቶቹ የበለጠ የከፋ መሆኑን ያምናል ምክንያቱን ያለፈው ትውልድ ኃጢአት የሚያስከትለውን መዘዝ እና እግዚአብሔር እነሱን ለማዳን እንዴት ያለ ታላቅ ትዕግሥትን እና ጸጋውን እንዳሳያቸው ያውቃልና። ይህ ለእነርሱ እውነት ከሆነ በኢየሱስና በመስቀል ላይ የተገለጸው የእግዚአብሔር ባሕርይና የማዳን ጸጋ ለእኛ ዛሬ ምን ያህል እንደሚበልጥ አስብ።

የመዝሙር 106 መልካሙ ዜና የእግዚአብሔር ትእግስት ከሰዎች ኃጢያት ሁል ጊዜ ይበልጣል (መዝ 106፡8-10፣ 30፣ 43-46)። የእግዚአብሔር ቁጣ እንዲመለስ ሙሴ እና ፊንሐስ የተጫወቱት ቁልፍ ሚና ክርስቶስ አማኞችን ወክሎ የሚያሳየውን ምልጃ አስፈላጊነት ያመለክታል። ያለፈውን ታሪክ ወደ ራሳችን ታሪክ ሊለውጠው የሚችለው የእግዚአብሔርን ጸጋ በግል የመለማመድ ተሞክሮ ብቻ ነው።

መዝሙር 106:13 እንዲህ ይላል:- “ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ በምክሩም አልታገሡም”። ለምንድነው እኛ በራሳችን ህይወት ውስጥ እንዲሁ ማድረግ ቀላል የሚሆነው?

የካቲት 27
Mar 06

የጌታ የወይን ግንድ ምሳሌ


መዝሙር 80ን ያንብቡ። በዚህ መዝሙር ውስጥ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዴት ተገለጠ ፣ ስለ ምን ታላቅ ተስፋ ነው ተማጽኖ የሚያቀርቡት?



እስራኤል የሚታየው እግዚአብሔር ከጭቆና ምድር ከግብፅ ነቅሎ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳጓጓዘው እንደ ወይን እርሻ ነው። የወይኑ ቦታ ተምሳሌት እግዚአብሔር እስራኤልን እንደመረጠውና እንደተንከባከበው ያሳያል (ዘፍ 49፡ 11፣ 12፣ 22፣ ዘዳ 7፡7-11 ያንብቡ)።

ነገር ግን፣ በመዝሙር 80፣ የእግዚአብሔር የወይን ቦታ ከቁጣው በታች ሆኖ እናገኘዋለን (መዝ 80፡12)። ነቢያት የወይኑ ቦታ ጥፋት ወይኑ መጥፎ (ክፉ) በመሆኑ የእግዚአብሔር ፍርድ ምልክት እንደሆነ አውጀዋል (ኢሳ 5፡1-7፣ ኤር 2፡21)። ይሁን እንጂ መዝሙር 80 ስለ መለኮታዊ ፍርድ አያሰላስልም። ከእግዚአብሔር የጸጋ ጥልቀት አንጻር፣ እግዚአብሔር የእርሱን መገኘት ከህዝቡ ለረጅም ጊዜ ሊከለክለው እንደሚችል በማሰቡ መዝሙረኛው ግራ ተጋብቷል። በአንድ በኩል የእግዚአብሔር ቁጣ እና ፍርድ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በጸጋ እና ይቅርታ መካከል ያለው ውጥረት መዝሙረኛው መለኮታዊ ቁጣ እንዳያሸንፍ እና ህዝቡን ሙሉ በሙሉ እንዳይበላው እንዲፈራ አድርጎታል (መዝ 80፡16)።

ዘኍልቍ 6፡22–27 ያንብቡ። ይህን በረከት መዝሙር 80 እንዴት ይጠቀምበታል?



በመዝሙሩ መጨረሻ ላይ የሚደገመው አጭሩ ክፍል የአሮንን የተስፋ ቃል እግዚአብሔር ሕዝቡን ለዘላለም እንደሚባርክ አሮን የሰጠውን ተስፋ በማስታወስ (ዘኍ 6፡22-27) ለሕዝቡ ስቃይ ምክንያት ከሚሆኑ ነገሮች በላይ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደሚያሸንፍ ያለውን ተስፋ አጉልቶ ያሳያል፡- “እግዚአብሔር ሆይ መልሰን፤ ፊትህን አብራ እኛም እንድናለን። (መዝ 80:3፣ 21፣ በተጨማሪም መዝ 80:7፣ 19 ተመልከት።)

እዚህ ላይ “መልሰን” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል የመጣው “መመለስ” ከሚለው የተለመደ ቃል ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር የጠፉትን ሕዝቡን ወደ እርሱ እንዲመለሱ በመጥራት ተደጋግሞ ተጠቅሷል። በንስሐ፣ ከኃጢአት መራቅ እና ወደ እግዚአብሔር መመለስ ከሚለው ሐሳብ ጋር በቅርበት የተሳሰረ ነው። “በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ። በፍጹም ልባቸውም ወደ እኔ ይመለሳሉና እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።” (ኤር 24:7) ንስሐ በመግባት ወደ እግዚአብሔር መመለስን ለራስህ እንዴት ተለማመድህ? የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት

የካቲት 28
Mar 07

በታሪክ ውስጥ የጌታ የበላይነት


መዝሙር 135ን ያንብቡ። በመዝሙሩ ውስጥ ጎላ ብለው የተገለጹት የትኞቹ ታሪካዊ ክንውኖች ናቸው? መዝሙረኛው ከእነርሱ ምን ትምህርት አግኝቷል?



መዝሙረ ዳዊት 135 በፍጥረት (መዝ 135:6፣ 7)፤ በእስራኤል የድነት ታሪክ ከግብጽ በወጡበት ጊዜ (መዝ 135:8፣ 9)፤ የተስፋይቱን ምድር በወረሱ ጊዜ(መዝ 135፡ 10–12)እና በድል አድራጊዎች ውስጥ ስለ ገለጠው ቸርነቱ እና ታማኝነቱ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ሕዝቡን ይጠራል።

ጌታ የእስራኤልን ሕዝብ እንደ ልዩ ሀብቱ በመምረጥ ጸጋውን ገለጠ (መዝ 135፡ 4)። “የተለየ ርስት” የሚለው አገላለጽ በጌታ እና በሕዝቡ መካከል ያለውን ልዩ የቃል ኪዳን ግንኙነት ይገልጻል (ዘዳ 7፡6–11፤ 1 ጴጥ 2፡9፣ 10)። የእስራኤል መመረጥ በጌታ ሉዓላዊ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነበር፣ ስለዚህ፣ እስራኤል ከሌሎች ህዝቦች በተለየ ሁኔታ የበላይ እንደሆነ እንዲሰማው የሚያደርግ ምንም ምክንያት የለም። መዝሙር 135:6፣ 7 የጌታ ሉዓላዊ ዓላማዎች በእስራኤል ሳይሆን በፍጥረት እንደጀመሩ ያሳያል። ስለዚህ፣ እስራኤላውያን በአምላክ የማዳን ዓላማዎች ውስጥ ለመላው ዓለም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በትሕትና መወጣት አለባቸው።

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያደረገውን ታላቅ ሥራ መተረክ (መዝ 135፡8-13) እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ “እንደሚፈርድ” እና እንደሚራራላቸው በሚሰጠው የተስፋ ቃል ይደመደማል (መዝ 135፡14)። እዚህ ላይ ፍርዱ የሚያሳየው የተጨቆኑትን እና የተቸገሩትን እግዚአብሔር እንደሚያጸድቅ ነው (መዝ 9:4፤ መዝ 7:8፤ መዝ 54:1፤ ዳን 7:22)።

የተስፋው ቃል ጌታ የህዝቡን ጉዳይ እንደሚሸከምና እንደሚጠብቃቸው ነው የሚያሳየው (ዘዳ 32፡36)። ስለዚህ፣ የመዝሙር 135 አላማ የእግዚአብሔር ህዝብ በጌታ እንዲታመኑ እና ከእርሱ ጋር በገቡት ቃል ኪዳን ታማኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ማነሳሳት ነው።

የጌታ ለህዝቡ ያለው ታማኝነት የጣዖታትን ከንቱነት እና በዓለም ላይ ያለውን የተለየ የጌታን ልዕልና እንዲያረጋግጥ መዝሙረኛውን ይመራዋል (መዝ 135፡15-18)። በጣዖት መታመን አምላኪዎቻቸውን እንደ ጣዖቶቻቸው ሁሉ ተስፋ ቢስ እና አቅመ ቢስ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል (መዝ. 135፡18)። መዝሙሩ እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪ እና እንደ ሕዝቡ አዳኝ ሊመሰገን እንደሚገባ ያሳያል። ይህ በአራተኛው ትእዛዝ በሁለቱ ማሟያ እትሞች በአስደናቂ ሁኔታ ተገልጿል (ዘጸ 20፡8-11፣ ዘዳ 5፡12-15)። የእግዚአብሔር በፍጥረት እና በታሪክ ውስጥ ያለው ሃይል በአለም ውስጥ ወደር የለሽ ስለሆነ የእግዚአብሔር ህዝብ ሁል ጊዜ በእርሱ መታመን እና እርሱን ብቻ ማምለክ አለበት። እንደ ፈጣሪያችን እና ቤዛችን እርሱ ብቻ ሊመለክ የሚገባው ሲሆን ማንንም ሆነ ምንንም ማምለክ ጣኦት አምልኮ ነው።

በሕይወታችን ውስጥ ጣዖታት እንደሌለን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? እኛ ከምንገነዘበው በላይ ጣዖት ማምለክ ቀላል ሊሆን የሚችለው ለምንድን ነው?

የካቲት 29
Mar 08


ተጨማሪ ሀሳብ


የሐዋርያት ሥራ 7ን እና ዕብራውያን 11ን ​ያንብቡ። አዲስ ኪዳን በታሪክ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ሕዝቡን የመምራት ሉዓላዊ ሥልጣን የመጨረሻ ግብ ምን ይላል?

ታሪካዊ መዝሙሮች እግዚአብሔር ለህዝቡ ያለውን ታማኝነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ ምስክር ናቸው። በአምላክ ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ክስተት ለዓለም አዳኝ ለናዝሬቱ ኢየሱስ የተገባው መለኮታዊ ተስፋ ፍጻሜ ላይ ለመድረስ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ነበር። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ህዝብ ግራ የሚያጋባ እና እግዚአብሔር ትቶናል ብለው እንዲያስቡ ያደረጉአቸው ፈተናዎች እንኳን በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ቁጥጥር ስር እና የምሪቱ አካል ነበሩ ምክንያቱም እግዚአብሔር የታሪክ የበላይ ጌታ ነው። መዝሙረኛው የህዝቡ ታማኝ አለመሆን እንኳን እግዚአብሔር በህዝቡ ላይ እምነት እንዳይጥል እና የገባውን ቃል እንዳይፈጽም ሊያግደው እንደማይችል እውነትን በዘዴ አቅርቧል። ነገር ግን፣ ንስሃ የማይገቡ ግለሰቦች እና ቡድኖች ከቃል ኪዳኑ በረከቶች ተገለሉ፣ የእነሱ አሳፋሪ ፍጻሜ ከእግዚአብሔር ውጭ ያለ ወይም የተቃውሞ ህይወት ሰዎችን እንዴት እንደሚያጠፋ ዘላቂ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ያገለግላል። መዝሙራት ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር ልጆች በጌታ እንዲተማመኑ እና ለእርሱ ታማኝ ሆነው እንዲቀጥሉ ያበረታታሉ። “ጌታ እኛን የመራበትን መንገድ እና ባለፈው ታሪካችን ያስተማረንን ካልረሳን በስተቀር ለወደፊቱ የምንፈራው ምንም ነገር የለም።”—Ellen G. White፣ Life Sketches of Ellen G. White፣ p. 196።

የእግዚአብሔር ሕዝቦች ያለ ፍርሃት ወደ ፊት እንዲሄዱ፣ የታሪካቸውን የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት መምሪያ መጽሐፈ መዝሙረ ዳዊት እውነታዎች ማወቅ አለባቸው። ኤለን ጂ ዋይት አማኞች መዝሙር 105 እና 106ን “ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ እንዲያነቡ ትመክራለች።”— Testimonies to Ministers and Gospel Workers, p. 98።

የእግዚአብሔር ህዝብ ታሪክ እንደሚያሳየው እግዚአብሔር በቃሉ ከገባው ተስፋ አንድም ሳይፈጸም እንደማይቀር ነው። ይህም አሁን በዚህ ምድር ለእያንዳንዳችን መለኮታዊ ጥንቃቄ እና የሰላም እንደሚሰጠንና በክርስቶስ ዳግም ምጻት በአዲሱ ምድር የሚያጸናውን የክርስቶስን መለኮታዊ የወደፊት ተስፋዎችን ያካተተ ነው።


የመወያያ ጥያቄዎች




1. እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ ህዝቡን በታማኝነት የመራበትን የሚያስታውሱ እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ ህዝቡን በታማኝነት የመራበትን የሚያስታውሱ በረከቶች ምንድን ናቸው? ያለፈውን ጊዜ ትምህርቶች መርሳት ወይም ችላ ማለት ምን መዘዝ ያስከትላል? እኛ እንደ ቤተ ክርስቲያን የጥንቷ እስራኤል እንድትሰራ የተጠራችበትን ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ያንኑ መርሕ መተግበር የምንችለው እንዴት ነው?

2. ነገሮች ለምን እንደሚከሰቱ ለመረዳት ቀላል በማይሆንበት ጊዜም እንኳ መዝሙራት ነገሮች ለምን እንደሚከሰቱ ለመረዳት ቀላል በማይሆንበት ጊዜም እንኳ መዝሙራት በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን የድጋፍ እንክብካቤ እንድንገነዘብ፣ ትዕግሥት እንድናሳይና በእግዚአብሔር ሉዓላዊ መንገዶች እንድንታመን የሚያበረታቱን እንዴት ነው?

3. በግልም ሆነ በጋራ አምልኮ አገልግሎታችን ውስጥ የአምላክን ሕዝቦች ታሪክ በግልም ሆነ በጋራ አምልኮ አገልግሎታችን ውስጥ የአምላክን ሕዝቦች ታሪክ በማጥናት ረገድ ይበልጥ ጎልቶ እንዲታይ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ስለ አምላክ ሕዝቦች የቅርብ ጊዜ ታሪክ ለልጆቻችን ለመንገር ይበልጥ ፍላጎት ያለን ልንሆን የምንችለው እንዴት ነው?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL