የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ራእ. 1፡1-7፤1 ጴጥ. 2:9፤ ራእይ
14:6-12፤ሉቃስ 11:23; 1 ጢሞ. 2:4፤ራእይ 21:1-4።
መግቢያ ጥቅስ፡- “እንግዲህ ይህ ሁሉ የሚቀልጥ ከሆነ የእግዚአብሔርን ቀን
መምጣት እየጠበቃችሁና እያቻኮላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመም
ሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? (2ጴጥ. 3፡11-12)
የራዕይ መጽሐፍ ስለመጨረሻ ዘመን አእምሮአችንን በሚሞሉ ትእይንቶች የተሞላ
ነው።
የመጽሐፉ ዋና ማዕከል በክርስቶስ እና በሰይጣን መካከል ስላለው
አለማቀፋዊ ግጭት ይናገራል። ሰይጣን በምድር ላይ በበላይነት ተቆናጦ የነበረበትን
ስፍራ አጥቷል፤ አሁን ደግሞ ለአምላክ ታማኝ የሆኑትን ያሳድዳቸዋል። መጽሐፉ ከፍ
ወዳለ ደረጃ ላይ ሲደርስ ኢየሱስ አዳምና ሔዋን ከወደቁ በኋላ የሞቱትን ታማኝ ሰዎች
እና ሕያው የሆኑ ጻድቃንን የሆኑ ልጆቹን ለማዳን በሚመለስበት ወቅት ስለሚሆነው
ነገር ነው። መጽሐፉ ሰይጣንና ክፉዎች በእሳት መውደማቸውን እና ኢየሱስ በምድር
ላይ ዘላለማዊ መንግሥቱን በመመስረት አዲስ ምድርን እንደሚፈጥር ያሳየናል።
የራዕይ ተማሪዎች ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አንስቶ ስለ ቤተክርስቲያን
ታሪክ አስቀድሞ የተተነበዩ ምልክታዊ ትንቢቶች እና ክስተቶችን ለመረዳት በጉጉት
በመጣራቸው ትክክል ናቸው።
ስለዚህም፣ በዚህ የሩብ ዓመት የመጨረሻ ትምህርት፣ ራዕይ መጽሐፍ
የሚሲዮናውያን ቤተ ክርስቲያን እንድንሆን በሚጠራን በሚስዮናውያን አምላክ ላይ
ያተኮረ የሚሲዮናውያን መጽሐፍ እንደሆነ እንመለከታለን። የእኛ ጥሪ “ወቅታዊውን
እውነት” ለዓለም ማወጅ ሲሆን ሁሉም ሰው ለእግዚአብሔር ምርጫውን እስኪያደርግ
ወይንም በተቃራኒው መቆሙን እስኪያረጋግጥ ድረስ ጥሪያችን ይቀጥላል።
*ለታህሳስ 20 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ይህ መጽሐፍ በእግዚአብሔር ተልዕኮ ላይ ያተኮረ መሆኑን የራዕይ መክፈቻ
መስመሮች ለአንባቢው ያመለክታሉ።
ራእይ 1:1-7ን ያንብቡ። የራዕይ መጽሐፍ በመጨረሻው ዘመን
በእግዚአብሔር ተልእኮ ላይ ያተኮረ መሆኑን የሚያረጋግጡት በየትኞቹ
መንገዶች ነው?
በመጀመሪያ ጥቅሶች ላይ ኢየሱስ የራዕይ ምንጭና ትኩረት መሆኑን ከገለጸ
በኋላ፣ ራእይ 1:4-5 ላይ ደግሞ ስላሴ የሰውን ልጅ ለማዳን በአንድነት እየሠሩ እንዳሉ
ሦስት የመለኮት አባላት ይጠቅሳል። አብ የነበረውና ያለውም የሚመጣውም ዘላለማዊ
ነው። በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን በነበሩት አብያተ ክርስቲያናት መካከል በኃይል
እየሠራ ያለው መንፈስ ቅዱስ ስሙ ተጠርቷል። ከዚያም ዮሐንስ የዚህች ፕላኔት ሕጋዊ
ባለቤትነት ያለው “ታማኝ ምሥክር”፣ “የሙታን በኵር” (ራእይ 1:5) የሆነው ኢየሱስ
ክርስቶስ ያለበትን ሁኔታ ያወሳል። ሰይጣን በዚህች ምድር ተጠቅሞ መንግሥቱን
ለመመሥረት ያደረገው ሙከራ ከሽፎበታል። እግዚአብሔር በሰይጣን ላይ ከተቀዳጀው
ድል በተጨማሪ የፈሰሰው የፈጣሪያችን ደም በደላችንንና እፍረታችንን ያጥባል።
ራእይ 1:6 እና 1 ጴጥሮስ 2:9 ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ
ለተዋጁት የሚሰጣቸው የማዕረግ ስሞች ምን ያመለክታሉ?
የእግዚአብሔር ተልዕኮ ትኩረት የሚጠፉ ሰዎችን ወደ ደኅንነት ስቦ ማምጣት
ብቻ አይደለም። የእግዚአብሔር ማዳን አዲስ እና የተከበረ ደረጃን ይሰጣል ምክንያቱም
የእግዚአብሔር መልክ በእኛ ውስጥ ስለተመለሰ። በፈሰሰው በኢየሱስ ደም አማካኝነት
ከአጽናፈ ዓለሙ ንጉሥ ጋር በደም የተገናኘን ስለሆንን የተዋጁ ንጉሳዊ ቤተሰብ (ነገሥታት)
ሆነዋል። አሁን፣ እንደ ንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት፣ ለሌሎች የሰው ልጆች መዳን የንጉሣዊ ቤተሰብ
ተልእኮን እንቀላቀላለን። ይህ እኛን ካህናት ያደርገናል! ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያኑን “መንግሥት”
እና ግለሰቦቹን “ካህናት” አድርጎ አቋቁሟል። የመንግሥቱ አባል መሆን ካህን መሆን ነውና።
በራዕይ 1፡7 ላይ፣ የተልእኮውን አጣዳፊነት እናገኛለን፡ ኢየሱስ ይመጣል፣
አሕዛብም ጠፍተዋልና ያዝናሉ። እግዚአብሄርም ከእርሱ የራቁትን እንዲመጡ
ይናፍቃል።የራዕይ መጽሐፍ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ባለው ተልዕኮ ይከፈታል።
በእግዚአብሔር የተፈጠርን ብቻ ሳንሆን በእርሱም የተዋጀን ነን፣ እና
በሚያስደንቅ ዋጋም የተገዛን። አሁን ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን
ምን ይህ እውነት ብዙ ተስፋ ሊሰጠን የሚገባው ለምንድን ነው?
የራእይ መጽሐፍ በራእይ 12:12 ላይ የተገለጸውን ታላቁን ተጋድሎ ጭብጥ
ኃይለኛና ግልጽ በሆነ መንገድ ይገልጽልናል:- “ ‘ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው
የምትኖሩ ሆይ፣ ደስ ይበላችሁ። ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው! ዲያብሎስ ጥቂት ጊዜ
እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና”። በመጨረሻው ቀን ፍጻሜ
ከሆነው ከታላቁ ተጋድሎ ሃሳብ ውጭ ማንም ሰው በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለውን
ማንኛውንም ነገር እንዴት ሊረዳ እንደሚችል መገመት ከባድ ነው።
ራእይ 14:6-12ን ያንብቡ። እዚህ የምናገኘው ሃሳብ ምንድን ነው? እና እነዚህ
ጥቅሶች ከተልዕኳችን እና ከመልእክታችን ጋር ምን ግንኙነት አላቸው?
ማዕከላዊ ተልእኮ፣ የእግዚአብሔር ተልእኮ፣ የእግዚአብሔር መልእክት ወንጌል ነው። መልእክቱ፣ በተጨባጭ ሁኔታ፣ ተልእኮው ነው። ዓለም በእርሷ ላይ ስለሚመጣው ነገር ማስጠንቀቂያ ሊሰጣት ይገባል እና እያንዳንዱ ሰው ምርጫ ለማድረግ ይገደዳል፤ ለሕይወት ወይም ለሞት! “ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል” ( ሉቃስ 11:23)። ኢየሱስ እዚህ ላይ ስለ ተልእኳችን በቀጥታ ሲናገር ምን እያለ ነው?
የራዕይ 14 የሦስቱ መላእክት መልእክቶች እኛ እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች
ለዓለም እንድንሰብክ የተጠራንበትን ዋና ሃሳብ ይመሰርታሉ። ለዚህም ማዕከላዊ፣
መሠረተ ያላቸው ሁለት ጭብጦች አሉ፡- “የዘላለም ወንጌል” (ራእ. 14፡6) እና ፈጣሪን
ማምለክ። እነዚህ ሁለት ጭብጦች በዚህ የቅዱሳን ሥዕላዊ መግለጫ ውስጥ ይገኛሉ፡
- “የቅዱሳን ትዕግሥት ይህ ነው፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚጠብቁ የኢየሱስንም
እምነት የሚጠብቁ እነዚህ ናቸው” (ራዕ. 14፡12)። ሌላ ምንም ነገር ብናደርግ—ሰዎችን
ለመርዳት የምናደርገውን መልካም ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ— ልዩ ጥሪያችንን እና
ተልእኳችንን ግን ልንዘነጋው አይገባም፣ ይህም “በዘላለም ወንጌል” ውስጥ የሚገኘውን
ተስፋ ለጠፋው አለም ማወጅ እና እንዲሁም አንድ ቀን በዚህ የተነሳ ስለሚመጣው
ነገር ለአለም ማስጠንቀቅ ነው።”ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል” (ሉቃስ 11:23)። ኢየሱስ
እዚህ ጋ የሚለንን ነገር እንዴት ተረዱት? እነዚህ ቃላት ልባችን የት እንዳለ እንድንመረምር
የሚያደርጉን ለምንድን ነው?
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱንና እኛን እንዲህ ብሎናል:- “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን
ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ
እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። እነሆም እኔ እስከ
ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።’ (ማቴ. 28:19-20.) ይህ ታላቁ ተልእኮ
ነው፣ እና በብዙ መልኩ የሦስቱ መላእክት መልእክት፣ “ለሁሉም ሕዝብ፣ ነገድና ቋንቋ”
(ራእ. 14፡6) ጥሪ ያለው፣ በቀላሉ ሲገለጽ“ወቅታዊ እውነት” ነው።
( 2 ጴጥ. 1:12 ) የታላቁ ተልእኮ መግለጫ ጥቅስ ነው።
1 ዮሐንስ 4:8፣ 2 ጴጥሮስ 3:9፣ 1 ጢሞቴዎስ 2:4 እና ዘፍጥረት
12:3 ያንብቡ። ለምንድነው እያንዳንዱ የሰዎች ልጆች ቡድን አባላት
ለእግዚአብሔር ዋጋ ያላቸው?
የክርስቶስ ፍቅር ለሰው ልጆች ሁሉ ነው፣ ይሄ ፍቅር የማያካትተው ቡድን የለም።
ክርስቶስ የሞተው አስቀድሞ ለተወሰኑ ሊቃውንት ብቻ እንደሆነ ከሚያስተምረው የሥነ
መለኮት ትምህርት በተቃራኒ፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የክርስቶስ ሞት፣ ዘር፣ ብሄር ወይንም
ነገድ ሳይለይ ለሁሉም ሰዎች እንደሆነ በግልጽ ያስቀምጣል። ሰው ከሆንክ ክርስቶስ
ሞቶልሃል። አለቀ። ለሁሉም ሰው የሚቀርበው ብቸኛው ጥያቄ፣ ለሞቱ ምን አይነት
ምላሽ ይሰጣሉ? የሚል ነው።
ኢየሱስ ሲመለስ ሁለት ጎራዎች ብቻ ይኖራሉ፤-በራእይ 13 እና 17 ላይ
እንደተገለጸው በሃይማኖት እና በፖለቲካዊ ተቋማት አማካኝነት ለሰይጣን ሥልጣን
የተገዙ እና ሙሉ በሙሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ የተገዙት ። “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ
መጠበቅ” እምነታቸውን የገለጹ ሰዎች ናቸው (ራዕ. 14፡12)።
ከመጀመሪያው አንስቶ፣ የሰው ልጆች እግዚአብሔር ማን እንደሆነ እና የፅድቁንና
የፍቅሩን መንገድ የሚያሳይ ማስረጃ ነበራቸው (ሮሜ 1፡18-21)። ስለዚህ፣ ከዘመናት
ጀምሮ ያሉ ሁሉም የሰው ልጆች የሚፈረድባቸው ምንም ያህል ነገሩን ቢረዱም ወይም
ባይረዱትም ከእግዚአብሔር ጋር በተባበሩት መጠን እና ህይወታቸውን በኖሩበት
መንገድ ነው (ሮሜ. 2፡11-16)።
ነገር ግን በዚህ የፍጻሜው ዘመን፣ በሃሳብ የተቃረኑ ቡድኖች እየተስፋፉ ነው፣ እናም
ከእንግዲህ የህሊና ነፃነት አይከበርም። ሰዎች ከሰይጣን ወገን ጋር እንዲሰለፉ ይገደዳሉ።
ወንጌል ይሰበክና ስለ ሰይጣን ስልቶች የሚናገረው ከባድ ዜና መጋለጥ ይጀምራል። እናም
የሦስቱ መላዕክት መልእክቶች፣ እና ተልእኳችን፣ ስለ ሁሉም ነገር ያለው ሃሳብ ያ ነው።
ክርስቶስ ለእናንተ በግል እንደሞተላችሁ አጽንኦት ሰጥታችሁ አስቡ።
ያደረጋችሁት ማንኛውም ነገር፣ የቱንም ያህል መጥፎ ቢሆን፣ ክርስቶስ
በመስቀል ላይ መሞቱ በቂ ክፍያ ሊሆን አይችልም ብላችሁ እንድታስቡ
የሚያደርግ ምን ነገር ይኖር ይሆን?
በተልዕኮ ውስጥ ስኬት ምንድነው? ብዙ ጥምቀቶች፣ ትልልቅ አብያተ
ክርስቲያናት እና ፈጣን የእድገት ደረጃዎች እንደሆኑ ለማሰብ ልንፈተን እንችላለን። ስለ
ስኬት ስናስብ በምድር ላይ ወደ እያንዳንዱ ነገድ እና ህዝብ እውነትን ይዞ መግባት እና
በሬዲዮ፣ ኢንተርኔት እና ቲቪ በመጠቀም መመስከራችንን ማፋጠን እንዳለብን ሊሰማን
ይችላል። ይህ ሁሉ ጥሩ ሊሆን ቢችልም ጳውሎስ ለቆሮንቶስ የእምነት ማህበረሰብ “እኔ
ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ አሳደገ” (1 ቆሮ. 3:6) ሲል
የጻፈውን ማስታወስ አለብን። በሌላ አነጋገር ትኩረታችን በሂደቱ ላይ መሆን አለበት
የእግዚአብሔር ትኩረት ደግሞ በእድገት ላይ ይሆናል።
የእግዚአብሔር ተልእኮ ዓላማ በወንጌል ተልእኮው ውስጥ የሚሳተፉትን ታማኝ
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በማድረግ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ የጠፉትን ማዳን
መሆኑን አስቀድመን አይተናል።
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። የኢየሱስ ተከታዮች ስለሆኑት ሰዎች
ባሕርይ ምን ይነግሩናል?
2 ቆሮ. 11፡2
ኢሳ. 30:21፤ ዮሐንስ 10:27፤ ዮሐንስ 16:12-13
2 ተሰ. 2:9–11፤ ዕብ. 3:12-13; 1ኛ ዮሐንስ 1፡8
1ዮሐ 1፡9፣ ራእ.7፡14፣ ራእ.19፡8
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ንጹሐን ናቸው፣ እንደ ንጹሕ ሙሽራ ለኢየሱስ ታማኝ
ሆነው ይቀጥላሉ። ኢየሱስ ዝግ ባለ የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ሲመራቸው ይከተሉታል።
ይህ እኛን ለሌሎች ሚስዮናዊ ሆነን እንድንሰራ መምራትንም ይጨምራል። በእነዚህ
ደቀ መዛሙርት ውስጥ ማታለል የለም። በሚያዳክም ጥርጣሬ፣ የሐሰት ትምህርት
ወይም የሥነ ምግባር ብልግና ወደ ጎዳና አይመሩም። በሥነ ምግባርም ከሌሎች
እንደሚበልጡም አይሰማቸውም። ፍጹማን እንዳልሆኑ ስለሚገነዘቡ የአምላክ የማንጻት
ጸጋና ምሕረት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንደሆኑ ያውቃሉ። ይህንን በመረዳት ከሌሎች
አማኞች እርማት እና መመሪያ ለመቀበል ክፍት ናቸው። የተልእኮ ስኬት የዚህ አይነት
ደቀመዝሙር ማድረግን ያካትታል።
ለክርስቶስ ንጽሕት ድንግል መሆን ማለት ምን ማለት ነው( 2 ቆሮ.
11:2 )? እኛ ኃጢአተኞች እንደመሆናችን መጠን በእግዚአብሔር
ፊት ይህን መሆን እና ሌሎችን ለክርስቶስ ንጹሕ ድንግል እንዲሆኑ
መጠቆም የምንችለው እንዴት ነው?
ራእይ 21:1- 4 እና ራእይ 21:22-22:5 ያንብቡ። እዚህ ላይ የተገለጸው ትዕይንት ምንድን ነው?
አዲሲቷ ምድር እንዴት ያለች ገነት ትሆናለች! ሞትና ኃጢአት ይጠፋሉ፤
ሰይጣንና ክፋትም ይጠፋሉ። ከአፍቃሪ አዳኛችን ጋር እንገናኛለን፤ ከምንወዳቸው ሰዎች
ጋርም አንድ ላይ እንሆናለን። አዲሲቱ ምድር ደግሞ ከሁሉም ነገድና ቋንቋ በተውጣጡ
ተወካዮች ትሞላለች።
የጀነራል ኮንፈረንስ ሚሽን ቦርድ የተለያዩ ሰዎችን መድረሳችን ወይም
አለመድረሳችንን ለመወሰን የሚያገለግሉ የአለም አቀፍ ተልዕኮ መለኪያዎችን አጽድቋል።
‹‹ወንጌል የደረሳቸው የቡድን አባላት›› የውጭ እርዳታን ሳይጠይቁ ለተቀረው ቡድን
በብቃት ለመመሥከር በቂ ቁጥሮች እና ሀብቶች ያላቸው ናቸው። በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው
የአምልኮ አገልግሎቶች፣ መጽሐፍ ቅዱሶች እና ሌሎች ጽሑፎች አሏቸው። አስተርጓሚ
ሳያስፈልጋቸው ለቀሪው ሕዝብ የሚመሰክሩ የአገር ተወላጅ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች
ናቸው።
“ወንጌል ያልደረሳቸው ህዝቦች” ማለት ደግሞ ከባህላቸው ውጭ ያለ እርዳታ
ለራሳቸው ቡድን በብቃት ለመመስከር በቂ ቁጥር እና ሃብት ያለው የአድቬንቲስት
ተወላጅ ማህበረሰብ የሌላቸው ናቸው።
እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እና ጉባኤ በማኅበረሰባቸው ውስጥ ካሉት
ሰዎች መካከል የትኞቹ ወንጌልን ማግኘት እንዳለባቸው መወሰን አለባቸው። በሁሉም
ቡድኖች ውስጥ ደቀ መዛሙርት የማድረጉን፣ የአዳኛችንን ዳግም መምጣት በማፋጠን እና
በመጨረሻም፣ እዚህ ቃል በተገባልን መሰረት በአዲሱ ሰማይ እና አዲስ ምድር ከእነርሱ
ጋር የመኖርን የእግዚአብሔር ተልዕኮ ላይ ኢንቨስት የምናደርግበት ጊዜ አሁን ነው።
ግድድሮሽ፡- የክርስቶስን መምጣት እንዴት እያፋጠንክ ነው? ምሥራቹን
መስማት በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ልብ ውስጥ የተስፋ ዘር እየዘራህ ነው? አዲስ
አማኞችን ለክርስቶስ በታማኝነት በመታዘዝ መኖር ምን ማለት እንደሆነ እንዲማሩ
በመርዳት እንዲያድጉ “እያጠጣሃቸው” ነው? በየእለቱ የጸሎት ዝርዝርህ ውስጥ ከሰዎች
ጋር አዲስ የገባኸውን ምድራዊ ቃል ለመፈጸምና እድሎችን ለመጠቀም ጸልይ።
ከፍ ያለ ግድድሮሽ፡- አንዳንድ ያፈራሃቸው “ደቀ መዛሙርትህ” ክርስቶስን
ለመቀበል ዝግጁ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም የአማኞች ቡድን
መቀላቀልን ይጨምራል። እራስህን በእነሱ ቦታ አስቀምጠውና ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ
ቤተክርስቲያንህ እንደምትሄድ አስብ። እሱ ወይም እሷ ምን ዓይነት ልምድ ይኖራቸዋል?
ቤተክርስቲያናችሁ አዲስ ሰዎችን ለመቀበል እና ደቀ መዝሙር ለማድረግ ምን ያህል
ተዘጋጅታለች? የራሳችሁን ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት ብቻ ሳይሆን አዳዲስ አማኞችን
ለመመሥረት ክፍት ነዎት? ወንጌል ያልተዳረሰባቸውን ደከም ያሉ አካባቢዎችን
ለመድረስ ስትራቴጂ ይፍጠሩ ሀሳቦቻችሁን ለቤተ ክርስትያን አመራር አካፍሉ፣ እና
ከእነሱ ጋር የበለጠ ደቀዛሙርትን የሚገነባ ቤተክርስትያን የመሆን እቅድን ተግባራዊ
ለማድረግ አብራችሁ ስሩ።
“ታላቁ የቤዛነት ዕቅድ ዓለምን ወደ እግዚአብሔር ሞገስ ሙሉ
በሙሉ ማምጣትን
ያስከትላል። በኃጢአት የጠፋው ሁሉ ይታደሳል። ሰው ብቻ ሳይሆን ምድር
የተዋጀችው የታዛዥዎች የዘላለም መኖሪያ ትሆን ዘንድ ነው። ለስድስት ሺህ ዓመታት
ሰይጣን ምድርን ለመያዝ ሲታገል ቆይቷል። አሁን እግዚአብሔር በፍጥረቱ ውስጥ
የነበረው የመጀመሪያ ዓላማ ተፈጽሟል። “ የልዑል ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ
መንግሥቱንም ይወርሳሉ ከዘላለም እስከ ለዘላለም።’”—Ellen G. White፣ Patri-
archs and Prophets, p. 342.
ነገር ግን ያ እውን ከመሆኑ በፊት ሰዎች የእግዚአብሔርን ዳግም የመፍጠር
ተስፋ መቀበል እና የዛ አካል እንዲሆኑ የማስጠንቀቂያ መልእክት ወደ አለም ማድረስና
በተልዕኮው ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር አጋር መሆን የእኛ ግዴታ ነው።
“የእምነታችንን ማስረጃ ለማያውቁት ለማሳወቅ ብዙ ሠራተኞች ሲሠሩ ለማየት
እጓጓለሁ። ብዙዎች የሦስቱን መላእክት መልእክት በመስማት ታላቅ ብርሃን አግኝተዋል፣
እና አሁን እነዚህን መልእክቶች በሁሉም የዓለም ክፍሎች ማወጅ አለባቸው። የበኩሌን
ለመወጣት እና ሌሎች የእውነትን ብርሃን እንዲሸከሙ መንገድ ለመክፈት እመኛለሁ።
ትጥቁን እንድንለብስ ጌታ ይርዳን። አማኞች ለዓለም የመጨረሻውን የማስጠንቀቂያ
ማስታወሻ በመስጠት በተከበረው ሥራ አንድ መሆን አለባቸው።- Ellen G. White,
Letter 390, 1907 (unpublished).
በዚህ ሩብ አመት ውስጥ ከእግዚአብሔር ተልእኮ ጋር የተያያዙ የተለያዩ
ገጽታዎችን እና ጉዳዮችን አጥንተናል። በዚህ ሳምንት ጥናታችንን የደመደምነው
ከእግዚአብሔር ጋር የታደሰ ግንኙነት ምን እንደሚመስል ለመረዳት የራእይን መጽሐፍ
ቁልፎችን መመርመር ሲሆን የተልዕኮ መደምደሚያ የሆነውም የምድርን ዳግም መፈጠር
እና መታደስን በማየት ነው። የኃጢአትና የሥቃይ ጥፋት በምድር ታሪክ ውስጥ እጅግ
አስፈሪ ቀናት እንደሚሆኑ እውነት ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ራእያችንን ከዚህ ጥፋት
ባለፈ ጊዜ ላይ በማድረግ እና እንደገና በታደሰችው ምድር ላይ ማጽናኛ እና ማበረታቻ
ይሰጣል።
1. “የዘላለም ወንጌል” ምንድን ነው? ለምንድን ነው “ዘላለማዊ” የሆነው?
ለተልዕኳችን መሠረት መሆን እንዳለበት የምንማረው እንዴት?
2. በሦስቱ መላእክት መልእክት ላይ እንዲህ ያለ ትኩረት የምንሰጠው ለምንድን ነው? በጣም ጠንካራ ማስጠንቀቂያዎችን ካካተቱ እንደ እነዚህ ካሉ መልእክቶች
“አሉታዊ” ሐሳብ ይልቅ በኢየሱስ ላይ ማተኮር አለብን ለሚለው መከራከሪያ
እንዴት ምላሽ ይሰጣሉ?
3. ይህ ሩብ ዓመት የተልእኮውን አስፈላጊነት ብቻ ሳይሆን እናንተ እና ቤተ
ክርስቲያናችሁ እንዴት በተሻለ ሁኔታ መሳተፍ እንደምትችሉ የሆነው እንዴት ነው፣
እኛ የተጠራነው ይህንን እንድናከናውን ነው?
ማሳሰቢያ
ድርጅቱ