የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ኤፌ. 6:10-20፤ 1ኛ ጴጥ. 4:1፤ 1ኛ ጴጥ. 5:8፤ ኢሳ. 59:17፤ ኢሳ. 52:8-10፤ 1ኛ ተሰ. 5:16-1።.
የመታሰቢያ ጥቅስ:- “በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሱ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።” (ኤፌ. 6:16, 17)።
ጆን ባኒያን ወህኒ ቤት እያለ በጻፈው የመናኝ ጉዞ በሚለው ዘመን ተሻጋሪ
መጽሐፉ ውስጥ አንድ ክርስቲያን ወደ ቤተ መንግሥት የጦር ማከማቻ
ታጅቦ ተወሰደና “ጌታቸው ለተጓዦቹ የሰጣቸው እንደ ሰይፍ፣ ጋሻ፣ የራስ
ቁር፣ ጥሩር፣ ጸሎትና የማያረጁ ጫማዎች ያሉበትን ሁሉንም ዓይነት ቁሳቁሶች [የጦር
መሣሪያዎች]እንዲያይ ተደረገ። በዚህ ቦታ በሰማይ ብዛት ያላቸው ክዋክብት
እንዳሉ ሁሉ ብዙ ሰዎችን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ብቁ ለማድረግ የሚያስችል
በቂ ነገር ነበር።” ክርስቲያኑ ከዚያ ወጥቶ ከመሄዱ በፊት “በመንገድ ላይ ጥቃት
እንዳይገጥመው የጦር መሣሪያ ጥሶ ማለፍ የማይችላቸውን መሣሪያዎች ከራስ ፀጉሩ
እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ ወዳስታጠቁት” የጦር መሣሪያ ማከማቻ ታጅቦ ተወሰደ።
ባኒያን በ1678 ዓ.ም የጻፈው ሰነድ ጳውሎስ ከ1600 ዓመታት በፊት
በወህኒ ቤት ሆኖ የጻፈውን የኤፌሶንን መልእክት ያስታውሳል። በዚህ መልእክቱ
ታላቁ ሚስዮናዊ ሐዋርያ ታላቅ ሰራዊት፣ ቤተ ክርስቲያን፣ የእግዚአብሔርን የጦር
መጋዘን እንደምትጎበኝና ከራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍር የሚሸፍነውን ሙሉ
መለኮታዊ የጦር መሣሪያ (በግሪክ ፓኖፕሊያ) እንደምትለብስ አድርጎ ያስባል።
የእግዚአብሔር ሰራዊት በስሙ ሰላምን ለመጠበቅ ሲንቀሳቀስ “ከራስ ጸጉር እስከ
እግር ጥፍር መልበስ የሚያስችል የማይዝግ ብረት፣” ለእያንዳንዱ ወታደር በቂ የሆኑ
ምርጥ የጦር መሣሪያዎች በእግዚአብሔር የጦር መሣሪያ መጋዘን ውስጥ አሉ።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለመስከረም 12 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ኤፌሶን 6:10-20ን ያንብቡ። ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን እየተካፈለች ስላለችው የጦርነት ዓይነት ምን ይላል? ጳውሎስ በመጀመሪያ ደረጃ እያሳየ ያለው አንድ ግለሰብ ከክፉ ጋር እያደረገ ያለውን መንፈሳዊ ጦርነት ነው ወይስ ቤተ ክርስቲያን በጥምረት ከክፉ ጋር የምታደርገውን ጦርነት ነው?
በግሪኮችና በሮማውያን ጦርነቶች ድል የሚደገፈው በአንድ የጦር ክፍል
ውስጥ ያሉ ወታደሮች ባላቸው ትብብር፣ በተለይም በጋመው ጦርነት መካከል
ለእርስ በርሳቸው በሚያደርጉት ድጋፍ ነው። ጦርነት ውስጥ ግላዊነት በድሮ
ዘመን ያልሰለጠኑ ጨካኝ ጦረኞችን ለሽንፈት የዳረጋቸው ባህርይ ነው።
ጳውሎስ ከዚህ የተለመደ ወታደራዊ መረዳት አንጻር በኤፌሶን 6፡10-20
ላይ እየተናገረ ያለው በመጀመሪያ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን ከከፉ ጋር የምታደርገውን
የጋራ ጦርነት ነው የሚለውን ሀሳብ ለመደገፍ ወሳኝ ምክንያቶች አሉ፡- 1.
ንባቡ ስለ ቤተ ክርስቲያን ብቻ የሚገልጽ ደብዳቤ መደምደሚያ ነው። ለጳውሎስ
ብቸኛ የሆነ ክርስቲያን ተዋጊ ከጨለማ ጠላቶች ጋር ጦርነት እንደሚያደርግ
በሚያሳይ ስዕል ደብዳቤውን መደምደም እንግዳ ነገር ይሆናል። 2. ጳውሎስ
በንባቡ መጨረሻ ላይ “ለቅዱሳን ሁሉ” (ኤፌ. 6:18-20) እንዲጸልዩ
ጥሪ ሲያቀርብ ክርስቲያናዊ ወዳጅነትን እያጎላ ነው። 3. ከሁሉም እጅግ ወሳኝ
የሆነ ነገር ቢኖር ጳውሎስ በደብዳቤው ጅምር ላይ ስለ ክፉ ኃይሎች ሲናገር
የሚያስቀምጠው አንድን ግለሰብ እንደሚዋጉ አድርጎ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን
እንደሚዋጉ አድርጎ ነው፡- “ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ሥፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ
ዘንድ” ይላል(ኤፌ. 3:10)።
ስለዚህ ኤፌሶን 6:10-20 የሚያሳየው ክፉን እየተጋፈጠ ያለን ብቸኛ
ወታደር አይደለም። ጳውሎስ በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ሰራዊት አድርጎ
ያቀርባል። አንድነት እንዳለው ሰራዊት የጦር መሣሪያን በሙሉ አንስተን በትጋትና
በሕብረት ጦርነቱን ወደ ፊት እንድንገፋ ይጠራናል። ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን
ሲገልጽ እንደ ክርስቶስ አካል(ኤፌ. 1:22፣ 23፤ ኤፌ. 4:1-16)፣ እንደ
ሕንፃ/ የእግዚአብሔር መቅደስ (ኤፌሶን 2፡19-22) እና የክርስቶስ ሙሽራ
(ኤፌ. 5፡21-33) በሚሉ መግለጫዎች ከገለጸ በኋላ በመጨረሻ እንደ
የሕያው እግዚአብሔር ሰራዊት አድርጎ የሚያሳይ ዘይቤያዊ አነጋገር በመጠቀም
ይገልጻታል። ወደ “ክፉ ቀን” (ኤፌ. 6:13) እና ከክፉው ጋር ለረዥም ጊዜ
ሲካሄድ ወደነበረው ጦርነት ወደ መጨረሻው ደረጃ እየተቃረብን ስለሆነ እንደ
ክርስቶስ ወታደሮች ለእግዚአብሔር ስላለን መሰጠት ወይም ለእርስ በርሳችን
ስላለው ታማኝነት ግራ የምንጋባበት ጊዜ አይደለም።
እኛ እንደ አንድ አካል፣ በምንም ዓይነት መልኩ ቢመጣ፣ ከክፉ
ጋር በምናደርጋቸው ተጋድሎዎች አንዳችን ሌላውን ለመርዳት
አብረን መስራት የምንችለው በምን መንገዶች ነው?
አማኞች ከክፉ ጋር ለሚያደርጉት ጦርነት ዝግጅታቸውን ስለሚጀምሩበት ሁኔታ ጳውሎስ የሚያስበው እንዴት ነው? ኤፌ. 6:14፤ ደግሞ 1ኛ ጴጥ. 4:1 1ኛ ጴጥ. 5:8፤ ሮሜ. 8:37-39ን ይመልከቱ።
ጳውሎስ ብርቱ ስለሆነ ጦርነት የሚሰጠው ማስጠንቀቂያ (ኤፌ.
6:13) እንዲቆሙ ለሚያቀርበው (ከኤፌሶን 6፡11፣13 ጋር አነጻጽሩ)
የመጨረሻው ጥሪ እና ለጦርነት እንዲዘጋጁ ለሚያቀርበው ዝርዝር ጥሪ
(ኤፌ. 6፡14-17) አንባቢዎችን ያዘጋጃል። ጳውሎስ “ወገባችሁ የታጠቀ
ይሁን” በማለት ወገብን የመታጠቅ ድርጊትን ይገልጻል(ከኢሳ.. 11:5 ጋር
አነጻጽሩ)። የድሮዎቹ ልቅ የሆኑ ልብሶች ከሥራ ወይም ከጦርነት በፊት ወገብ ላይ
መታሰር ነበረባቸው(ከሉቃስ 12:35፣ 37፤ ሉቃስ 17:8 ጋር ያነጻጽሩ)።
ጳውሎስ እያሰበ ያለው አማኙ የጦር ዕቃውን መልበስ ያለበት አንድ የሮም ጭፍራ
አባል ከቆዳ ከተሰራ ቀበቶ ጀምሮ እንደሚለብሰው ሲሆን ቀበቶው የታተመበት
አራት ማዕዘን ባለው ብረት የተዋበና ዘለበት ያለው ነበር። ከቀበቶው ላይ ደግሞ
በብረት ዲስኮች (ክብና ጠፍጣፋ ብረቶች) የተሸፈኑ የቆዳ ጥብጣቦች ወደ ታች
ተንጠልጥለውበት እንደ ሽርጥ የሚለበስ ሲሆን እነዚህ ነገሮች ለሚያያቸው ሰው
ማዕረግን የሚያሳይ አርማ ሆነው ያገለግላሉ። ልብሶችን የማሰርና ሌሎች ነገሮችን
በቦታቸው እንዲቆዩ የማድረግ ወሳኝ አገልግሎት ይሰጣል።
እውነት ከአማኙ ከራሱ የሆነ ነገር አይደለም፤ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው
(በኤፌ. 2፡8 ላይ ከተገለጸው ድነት ጋር አነጻጽሩ)። ነገር ግን በሕይወታቸው
ምንም የመለወጥ ተጽእኖ የሌለው የማይታይና በርቀት ያለ ንብረት መሆን
የለበትም። ይህንን መለኮታዊ ስጦታ ለመለማመድና ለመጠቀም የእግዚአብሔርን
እውነት “መልበስ” አለባቸው። የእግዚአብሔር እውነት እነርሱን የራሱ
እንደሚያደርጋቸውና እንደሚጠብቃቸው ያህል እነርሱ የእግዚአብሔርን እውነት
የራሳቸው አያደርጉም።
ጳውሎስ ቀጥሎ አማኞች “የጽድቅን ጥሩር” እንዲለብሱ
ያደፋፍራቸዋል(ከ1ኛ ተሰ. 5፡8 ጋር ያነጻጽሩ)። እርሱ መለኮታዊ ጦረኛ
ስለሆነ እንደ እውነት ቀበቶ ሁሉ ይህም የእግዚአብሔር የጦር መሣሪያ አካል
ስለሆነ መነሻው ከእግዚአብሔር ነው (ኢሳ. 59፡17)። በጳውሎስ ዘመን
ወታደሮች የሚጠቀሙአቸው አካላዊ የጦር መሣሪያዎች ከትናንሽ የተጠላለፉ
የብረት ቀለበቶች፣ እርስ በርሳቸው ከተደራረቡ የነሃስ ወይም የብረት ቅርፊቶች
ወይም እርስ በርሳቸው ከተደራረቡ የብረት ገመዶች የተሰሩ ነበሩ። ይህ
አካላዊ የጦር መሣሪያ ወይም ጥሩር ወሳኝ የሆኑ የአካል ክፍሎችን ከጠላት
ምቶች ወይም ከሚወጉ ነገሮች ይከላከል ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ አማኞችም
ከእግዚአብሔር የሚሰጣቸውን መንፈሳዊ መከላከያ፣ ከጠላት የሚከላከሉ የጽድቅ
ስጦታዎችን መለማመድ አለባቸው። በኤፌሶን መጽሐፍ ውስጥ ጳውሎስ ጽድቅን
ከቅድስና፣ ከበጎነት እና ከእውነት ጋር ያገናኛል (ኤፌ. 4፡24፤ ኤፌ. 5፡9)።
ይህን ያደረገበት ምክንያት ሌሎችን በተለይም የቤተ ክርስቲያን አባሎቻቸውን
በፍትሃዊነትና በጥሩ ሁኔታ መያዝን የሚያሳይ ችሎታ አድርጎ ስለተመለከተ ነው።
መልካምነት፣ ቅድስና እና እውነት ጥበቃ መሆን ይችላሉ
የሚለውን ሀሳብ እርስዎ የተለማመዱት በምን መንገዶች ነው?
ለጦርነት የሚዘጋጅ የሮም ወታደር ጠንካራ የሆኑ የወታደር ነጠላ
ጫማዎችን ይጫማ ነበር። የጫማዎቹ ተረከዝ (ሶል) ብዙ ንብርብር የነበረበት
ሆኖ ከሥሩ ኩርንችት (የጫማ ምስማር) የተለጠፈበት ስለነበር ወታደሩ መሬትን
ቆንጥቶ በመያዝ “እንዲቆም” ይረዳው ነበር (ኤፌ. 6፡11፣13፣14)።
ጳውሎስ ይህንን ወታደራዊ ጫማ የሚያብራራው ከኢሳይያስ 52፡7 በተወሰደ
ቋንቋ ሲሆን የእግዚአብሔር ጦርነት በድል የመጠናቀቁንና ሰላም የመንገሱን ዜና
መልእክተኛው ባመጣለት ጊዜ ደስታውን የገለጸበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነበር።
“የምሥራች የሚናገር፣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ
ያማረ ነው” (ኢሳ. 52:7)።
ጳውሎስ በኤፌሶን መጽሐፍ ውስጥ ስለ ሰላም ስምንት ጊዜ
አጉልቶ የጠቀሰውን ከልሱ። ስለ ሰላም ይህን ያህል ፍላጎት ካለው
የዚህን ያህል ስለ ውትድርና የሚገልጸውን ዝርዝር ዘይቤያዊ
አነጋገር የሚጠቀመው ለምንድር ነው? ኤፌ. 1:2፤ ኤፌ. 2:14፣
15፣ 17፤ ኤፌ. 4:3፤ ኤፌ. 6:15፣ 23።
ሰላም “ሰላማችን” የሆነው፣ “ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን
ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ የሰበከው” (ኤፌ. 2:14-17)፣
አይሁዶችንና አህዛብን “ከሁለታቸውም አንድን አዲስ ሰው የፈጠረው” (ኤፌ.
2:15) የክርስቶስ ሥራ መሆኑን ጳውሎስ በደስታ ይገልጻል። የክርስቶስን
የማዳንና ሰላም የመፍጠር ሥራውን የወንጌል ታሪክ ሕያው አድርጎ በመጠበቅ፣
ከዚህ በፊት በፈጸመው ድል በመደሰትና ወደ ፊት የሚመጣውን የድል ጩኸት
በመጠበቅ አማኞች እግሮቻቸውን ተጫምተው ለጦርነት ተዘጋጅተው ይቆማሉ።
በኢሳይያስ 52፡7 ላይ እንዳለው መልእክተኛ አማኞች የክርስቶስን ድልና የእርሱን
ሰላም የሚያውጁ መልእክተኞች ናቸው።
ነገር ግን ጳውሎስ የጦር መሣሪያዎችን እንድናነሳ ሲጠራን በጠላቶቻችን
ላይ ወታደራዊ የጦር መሣሪያዎችን እንድናነሳ እንደጠራን አድርገን እንድናስተውል
አይፈልግም። አማኞችን “የሰላምን ወንጌል” (ኤፌ. 6:15) እንደሚያውጁ
አድርጎ የሚገልጸው ከዚህ የተነሣ ነው። ጳውሎስ የሚያደፋፍረው አንድነትን፣
የሚያንጽ ንግግርን፣ ገርነትን ስለሆነ አማኞች ከእርስ በርሳቸው ጋር በሚኖራቸው
ግንኙነት ጦረኞች እንዲሆኑ አይፈልግም (በተላይ ኤፌሶን 4፡25-5፡2 ያለውን
ይመልከቱ)። ቤተ ክርስቲያን የክርስቲያን መልካም ባህርያትን የሚወክለውን
የወንጌልን ጦር መሣሪያ (ትህትናን፣ ትዕግሥትን፣ ይቅርታን፣ ወዘተ) እና ልምዶች
(ጸሎትና አምልኮ) በመጠቀም “ሰላምን መጠበቅ” አለባት። እነዚህን
የመሳሰሉ ተግባራት እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በክርስቶስ አንድ ለማድረግ
ወዳለው ታላቅ ዕቅድ የሚያመለክቱ ስልቶች ናቸው (ኤፌ. 1፡9፤10)።
ከዚህ ቀጥሎ ያለው ጥቅስ ጳውሎስ የሚጠቀማቸው ወታደራዊ ምሳሌዎች
ለእኛ እንደ አማኞች ምን ማለት እንደሆኑ እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው?
“እግዚአብሔር የጦር መሣሪያዎቹን እንድንለብስ ይጠራናል። የሚያስፈልገን
የጳውሎስ የጦር መሣሪያ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሙሉ የጦር መሣሪያ ነው። ይህ
ሲሆን ልቦች ክርስቶስን በሚመስል ገርነት፣ ርኅራኄና ፍቅር ተሞልተው ወደ ሥራው
መሄድ እንችላለን።”-Ellen G. White, [Australasian]
Union Conference Record, July 28, 1899.
አማኞች በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ እንደ ተዋጊዎች ጋሻን፣ የራስ ቁርን እና ሰይፍን መጠቀም ያለባቸው እንዴትና መቼ ነው? ኤፌ. 6:16፣ 17።
የጳውሎስ ጋሻ የሮም ጭፍራ አባል የሆነ ወታደር የሚጠቀመው ትልቅ
አራት ማዕዘን ያለው ጋሻ ነው። ከእንጨት የተሰራና በቆዳ የተሸፈነ ሲሆን ከጎን
የሚመጡ ጥቃቶችን ለመከላከል እንዲችል ጠርዞቹ ወደ ውስጥ የታጠፉ ናቸው።
ጋሻዎቹ በውኃ ሲዘፈዘፉ በሙጫ ተነክረው እሳት የተለኮሰባቸውን “እንደ እሳት
የሚንቦገቦጉ ፍላጻዎችን ማጥፋት ይችሉ ነበር። ጳውሎስ “የእምነት ጋሻ” የሚለው
መግለጫ በብሉይ ኪዳን ዘመን ጋሻን ሕዝቡን ከአደጋ የሚከላከል የእግዚአብሔር
ምልክት አድርገው ይጠቀሙበት የነበረውን የሚያንጸባርቅ ነው (ዘፍ. 15፡
1፤ መዝ. 3፡3)። “የእምነትን ጋሻ” ማንሳት ማለት (ኤፌ. 6:16)
በአማኞች ፋንታ በሚዋጋው (ኤፌ. 6፡10)፣ ምርጥ የሆነውን የጦር መሣሪያ
በሚሰጠው(ኤፌ. 6:11፣ 13) እና ድልን በሚያረጋግጠው በእግዚአብሔር
በመተማመን ወደ ዓለም አቀፋዊው ጦርነት መግባት ማለት ነው።
በተመሳሳይ ሁኔታ ለጦርነት የሚያገለግል የሮማውያን የራስ ቁር የተሰራው
ከብረት ወይም ከነሃስ ነው። ጭንቅላትን እንዲከላከል ተደርጎ በተሰራው የራስ
ቁር ላይ አንገትን የሚከላከል ጠፍጣፋ ብረት፣ የጆሮ መጠበቂያ፣ ቅንድብ መከለያ
እጥፋቶችና ጉንጮችን የሚከላከሉ ተጣጣፊ ከብረት የተሰሩ ነገሮች ተጨምረው
ተሰርተዋል። የራስ ቁር የሚሰጠውን የተለየ ጥበቃ ከግምት ውስጥ በማስገባት
“የመዳን ራስ ቁር” (ኤፌ. 6:17) የሚወክለው አማኞች ከሙታን ከተነሣው፣
ወደ ሰማይ ካረገውና ከፍ ከፍ ካለው ክርስቶስ ጋር ባላቸው አንድነት አሁን
የሚለማመዱትን ድነት ነው (ኤፌ. 2፡6-10)። “የመዳን ራስ ቁርን” ማጥለቅ
ማለት በጊዜው እጅግ የተለመዱ መንፈሳዊ ኃይሎችን አለመፍራትና በክርስቶስ
ታላቅ ኃይል መታመን ማለት ነው። (ከኤፌ. 1:15-23፤ ኤፌ. 2:1-10
ጋር ያነጻጽሩ)።
ከጦር መሣሪያዎቹ መካከል የመጨረሻው “የመንፈስ ሰይፍ የሆነው
የእግዚአብሔር ቃል ነው” (ኤፌ. 6:17)። ይህ የሚያመለክተው የሮም ጭፍራ
አባል የሚታጠቀውን አጭርና በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ ነው። የተለመደው
የጦርነት ስልት ሁለት ጦሮችን (ጳውሎስ ያልጠቀሳቸውን) ከወረወሩ በኋላ
አጭሩን ሰይፍ ከአፎቱ በማውጣት ለመውጋት ወደ ፊት መንደርደርን ነው።
የአማኞች ሰይፍ፣ “የእግዚአብሔር ቃል” ተብሎ የሚታወቀው፣ “የመንፈስ
ሰይፍ” ሲሆን የሚሰጠውም በመንፈስ ነው። ጳውሎስ እንደ ጦር መሪ ወደ ፊት
በመምጣት ከመለኮታዊው የጦር አዛዥ ስለተሰጡ ተስፋዎችና ድሎች በመናገር
የጦር መሣሪያዎችን እንድናነሳ ጥሪ ያቀርባል። ከክፉ ጋር በምናደርገው ጦርነት
እንደ ዋና መሣሪያ የሚያገለግለውን “የእግዚአብሔርን ቃል” የሚመሰርቱት እነዚህ
በኤፌሶን 6፡ 10-20 ላይ የተሰጡ ተስፋዎች ናቸው። ስለዚህ “የእግዚአብሔር
ቃል” የሚያመለክተው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኛቸውን ሰፊ የወንጌል
ተስፋዎችን ነው
በርካታ የውትድርና ምልክቶችን አብዝተን ባንወዳቸውም እነዚህ
ምልክቶች ታላቁ ተጋድሎ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነና ምን ያህል
ትኩረት ልንሰጠው እንደሚገባ ምን ሊያስተምሩን ይገባል?
ጳውሎስ የጦርነት ልባዊ ምክሩን ሲያጠናቅቅ አማኞች እንደ ወታደሮች
“ለቅዱሳን ሁሉ” (ኤፌ. 6፡18) በሚደረግ ወሳኝና ቀጣይነት ባለው ጸሎት
እና ለእርሱም እሥረኛ እንደሆነ መልእክተኛ (ኤፌ. 6፡19፣ 20) እንዲሳተፉ
ያደፋፍራቸዋል። በጥንቶቹ የጦር ሜዳዎች አምላክን ወይም አማልክትን መጥራት
የተለመደ ልምምድ ስለነበር ይህ የጸሎት ጥሪ ከወታደራዊ ምሳሌ የመጣ ሊሆን
ይችላል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌን ለመጥቀስ ያህል፣ የሕዝኤል ያቀረበውን
የጦርነት ምክር ተከትሎ ኢዮሣፍጥ “ይሁዳ ሁሉ እና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ”
“በእግዚአብሔር ፊት እንዲወድቁና ለእግዚአብሔርም እንዲሰግዱ” ይመራቸዋል
(2ኛ ዜና 20:18)። ጸሎት ከጦር መሣሪያዎቹ ሰባተኛው ባይሆንም ጳውሎስ
ስለ ጦርነት የሚሰጣቸው ምክሮችና ወታደራዊ ዘይቤያዊ አነጋገሮች ዋና አካል ነው።
ከሁለቱ የጸሎት ጥያቄዎች በመጀመሪያው ውስጥ ጳውሎስ
የሚናገራቸውን ሰዎች “ለቅዱሳን ሁሉ” (ኤፌ. 6:18) ልባዊ፣ አንገብጋቢና
የማያቋርጥ ጸሎት እንዲደረግላቸው ይጠይቃል። ቤተ ክርስቲያን ከክፉ ኃይሎች
ጋር በምታደርገው ጦርነት ስኬታማ መሆን ካለባት በመንፈስ በተመራ ጸሎት
በእግዚአብሔር መደገፍን መለማመድ ያስፈልጋታል።
የጳውሎስ ሁለተኛው የጸሎት ጥያቄ ለራሱ ነበር፡- “ለእኔም ደግሞ
ጸልዩልኝ” ብሏል(ኤፌ. 6:19)። ጸሎት እንዲደረግለት የጠየቀው
እግዚአብሔር ትክክለኛውን መልእክት እንዲሰጠው (“ቃል ይሰጠው ዘንድ”)፣
በትክክለኛው ጊዜ እንዲሰጠው (“አፌን ስከፍት”)፣ መልእክቱ በትክክለኛው
መንገድ እንዲተላለፍ (“በድፍረት ማወጅ እንድችል”) እና እጅግ ወሳኝ
የሆነ ሀሳብን ለማቅረብ እንዲችል “የወንጌልን ምስጢር” (ኤፌ. 6:19)
ነበር። ይህ የመጨረሻው ሀረግ የሚያመለክተው በክርስቶስ “ሁሉን ነገር አንድ
ለማድረግ” (ኤፌ. 1፡10) የተዘጋጀው ሁሉን የሚያካትት ዕቅድ ምልክት
በመሆን አህዛቦችን ከአይሁድ ጋር ለማዳን እግዚአብሔር ጣልቃ የገባበትን “ግልጽ
ምስጢር” (ኤፌ. 3፡1-13ን ይመልከቱ)፣ “አንድ አዲስ ሰው” መፍጠሩን
(ኤፌ. 2:15፤ ደግሞ ኤፌ. 2:11-22ን ይመልከቱ) ያመለክታል።
ከዚህ ቀጥሎ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉትን “የጸሎት ጥሪዎች”
ከልሱአቸው። ከሁሉም የበለጠ የሚያነሳሰዎ የትኛው ነው? ለምን?
ሉቃስ 18:1-8፣ ፊልጵ. 4:6፣ ቆላ. 4:2፣ 1ኛ ተሰ. 5:16-18።
አማኞች ልባዊ በሆነና ትጋት ባለበት ጸሎት እንዲሳተፉ ይህን ያህል ግፊት
የሚደረገው ለምንድር ነው? የጳውሎስ ዘይቤያዊ አነጋገር ሁለት መልሶችን
ይሰጣል፡- (1) ከተፈጥሮ ውጭ ከሆኑ ጠላቶች ጋር የሚደረገው መንፈሳዊ
ጦርነት ስጋት አስጨናቂና ግልጽ ነው። (2) እግዚአብሔር መንፈሳዊ ብርታትና
ድል ለመስጠት የሰጣቸው ተስፋዎች በጳውሎስ ወታደራዊ ምሳሌዎች አማካይነት
ተገልጸዋል (ኤፌ. 6:10-17)። ልባዊ የሆነና ትጋት ያለበት ጸሎት እነዚህን
ተስፋዎች በጥንቃቄ እንድንሰማ፣ እንድንደሰትባቸውና እግዚአብሔርን ለጸጋው
በረከቶች እንድናመሰግን ዕድል ይሰጣል።
“ሁሉም በሕብረት ካልሰሩ በቀር በጦርነት ላይ ያለው
ሰራዊት ይወዛገብና ይዳከማል። ወታደሮቹ ከእርስ በርሳቸው ቦታዎችና ሥራ ጋር
ሳይናበቡ የራሳቸውን ስሜታዊ ሀሳቦች የሚተገብሩ ከሆኑ አንዱ ከሌላው ጋር
ግንኙነት የሌላቸው አቶሞች ስብስብ ይሆናሉ። የተቀናጀ አካልን ሥራ መስራት
አይችሉም። ስለዚህ የክርስቶስ ወታደሮች ተጣጥመው መስራት አለባቸው።
እነርሱ ብቻ እንክብካቤ ሊደረግላቸው አይገባም። ይህንን ካደረጉ በአንድ ሀሳብ፣
በአንድ ዓላማ እና ለአንድ ታላቅ ዓላማ ተቀድሶ ፍጹም መጣጣም ባለበት ቦታ
መሆን ያለበት የእግዚአብሔር ሕዝብ ጥረቶቻቸው ፍሬ ቢስ ሆነው ጊዜያቸውና
ችሎታዎቻቸው ይባክናሉ። አንድነት ጥንካሬ ነው። ጥቂት የተለወጡ ነፍሳት
ተጣጥመው፣ ለአንድ ታላቅ ዓላማ፣ በአንድ አእምሮ የሚሰሩ ከሆነ በሁሉም
አጋጣሚዎች ድሎችን ይቀዳጃሉ።”-Ellen G. White, Spalding
and Magan Collection, p. 121.
ጳውሎስ ለራሱ “በሰንሰለት መልእክተኛ” የሚል ስም ሲሰጥ ጠቀሜታው
ምንድር ነው (ኤፌ. 6:20)?
መልእክተኞች (አምባሳደሮች) በጦርነት ጊዜያት ከባድ ሚናዎችን
ይጫወታሉ። ስለዚህ ጳውሎስ ራሱን የገለጸበት ሁኔታ ወታደራዊ ዘይቤያዊ አነጋገርን
ለተጠቀመበት አውድ ገጣሚ ነው። አምባሳደሮች ለግለሰብ ወይም ለላካቸው
አገር የሚገባውን አክብሮት ሊያገኙ ይገባል። ስለዚህ ጳውሎስ የዓለማት ገዥ
የሆነው የታላቁ አለቃ መልእክተኛ (አምባሳደር) በመሆኑና በሰንሰለት በመታሰሩ
በታየው አክብሮት ማጣት መካከል ያለው ንጽጽር አስገራሚ ነው (ቃል በቃል
“ሰንሰለት” ተብሎ ተገልጾአል)። ነገር ግን አምባሳደሮች “የሀላፊነት ሰንሰለትን”
ስለሚያጠልቁ ጳውሎስ “ሰንሰለትን” መጥቀሱ ሰንሰለቱን “ ላገኘው ከፍተኛ
ስኬት እንደተሰጠ የክብር ሽልማት” አድርጎ ስለሚያይ “ውስጠ ወይራ ከሆነ
ሀሳብ ጋር የተቀመመ” ሊሆን ይችላል።”-David J. Williams,
Paul’s Metaphors: Their Context and Charac-
ter (Peabody, MA: Hendrickson, 1999), p. 152.
1. እርስዎ ባሉበት በተከፋፈለና በጦርነት ላይ ባለው የዓለም ጥግ ለእርስዎና
ለጉባኤዎ “ሰላምን መጠበቅ” ማለት ምን ማለት ነው”? ከጊዜ ወደ
ጊዜ እየጨመረ በሚሄድ ወረራና ጠብ ተለይቶ በሚታወቅ ዓለም ውስጥ
የሰላም ወኪሎች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
2. እርስዎ ባሉበት አቅጣጫ እየተወረወሩ ያሉ “የሚንበለበሉ ፍላጻዎች”
ምንድር ናቸው? እነዚህን ፍላጻዎች ለማጥፋት “የእምነት ጋሻ” በቦታው
መሆኑን ማረጋገጥ የሚችሉት እንዴት ነው?
3. አንዳንድ ጊዜ ስለ “የጸሎት አርበኞች” እናወራለን። በኤፌሶን 6፡ 18-
20 መሰረት “የጸሎት አገልግሎት” እንዴት ማካሄድ እንችላለን?
4. በታላቁ ተጋድሎ የጦር ሜዳ ላይ የቆሰሉትን መያዝ ያለብን እንዴት ነው?
ጦርነቱ በተጋጋለበት ጊዜ ከፍርሃት የተነሣ የሚሸሸውን ወይም ሽንፈትን
በመቀበል በግልጽ ወደ ሌላኛው ወገን የሄደውን ክርስቲያን አማኝ እንዴት
መያዝ አለብን?