የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ:- ኤፌ. 6:10-20፤
ዘደዳ. 20:2-4፤ ሮሜ. 13:11-14፤ 1ኛ ተሰ. 5:6-8፤ 1ኛ ቆሮ.
15:23፣ 24።
የመታሰቢያ ጥቅስ:- “በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።” (ኤፌ. 6:10፣ 11).
ዓይኖቹ የፈዘዙበት አገልጋይ ከመኖሪያው እየተደናቀፈ ይወጣና የሚያስፈራ
ነገር--ትልቅና በደንብ የታጠቀ የጠላት ሰራዊት ከ“ወታደሮች፣ ፈረሶችና
በየቦታው ከነበሩ ሰረገላዎች” ጋር ይመለከታል። ስላየው ነገር ለነቢዩ
ኤልሳዕ እየተንተባተበ ከነገረ በኋላ በጥድፊያ “ ‘ጌታዬ ሆይ፣ አሁን ምን
እናደርጋለን?’ የሚል ጥያቄ አቀረበለት።”
ኤልሳዕ “ ‘አትፍራ! . . . ከእነርሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት
ይበልጣሉና!’ በማለት መለሰለት።” ኤልሳዕ ወደራሱ ስቦት እንዲህ በማለት
ጸለየለት፡- “‘ጌታ ሆይ፣ ዓይኖቹን ክፈትለትና ይመልከት!’” የነቢዩ ጸሎት
ወዲያውኑ ምላሽ አገኘ። አገልጋዩ በድጋሚ ወደ ግንቡ ጫፍ ወጣ፣ ነገር ግን አሁን
በሚታየውና በማይታየው መካከል ያለው መጋረጃ ተነሳ። አሁን አንድ ሰራዊት
ብቻ ሳይሆን ሁለት ሠራዊቶችን ተመለከተ። “እግዚአብሔርም የብላቴናውን
ዓይኖች ገለጠ፣ አየም እነሆም፣ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች
ተራራውን ሞልተውት ነበር።” (2ኛ ነገሥት 6:15-17)።
ጳውሎስ ኤፌሶን 6:10-20ን ሲጽፍ አማኞች የታላቁን ተጋድሎ ሙሉ
እውነታ ማየት እንዲችሉና ይህ ከሚገልጥላቸው ነገር ተስፋ እንዲያገኙ ፈጣን
ዕይታ እንዲሰጣቸው ጸለየ።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለመስከረም 5 ሰንበት ለመዘጋጀት አጥኑ።
ጳውሎስ ደብዳቤውን ሲደመድም የጻፈውን የሚያቃጭል መደምደሚያ፣ ኤፌሶን 6፡10-16ን ያጥኑ። የጳውሎስ የጦርነት ጩኸት ዛሬ በታላቁ ተጋድሎ ውጊያ ውስጥ ላለን ለእኛ ምን ማለት ነው?
ጳውሎስ የኤፌሶንን መጽሐፍ የሚደመድመው ለጦርነት ጥሪ በማቅረብና
ቤተ ክርስቲያን ከክፉው ጋር በምታደርገው ጦርነት አማኞች አቋማቸውን እንዲለዩ
በማደፋፈር ነው (ኤፌ. 6፡10-20)። የሚጀምረው “በጌታ የበረታችሁ ሁኑ”
(ኤፌ. 6:10) በሚለው ሁሉን አካታች ልባዊ ምክር ሲሆን “የእግዚአብሔርን
ዕቃ ጦር በሙሉ ልበሱ” (ኤፌ. 6:11) በሚል ጥሪ ይደግመዋል። ይህንን ጥሪ
ዓላማውን ለይቶ በማሳወቅ (የዲያቢሎስን ሽንገላ መቋቋም እንድትችሉ ኤፌ.
6:11) በማለት ይደግፈዋል። ከዚያ በኋላ ጳውሎስ ዘርዘር ባለ ሁኔታ የጦር
መሣሪያዎችን እንዲያነሱ እንደገና ጥሪ ያስተላልፋል። አማኞች በጦርነቱ ፀንተው
መቆም እንዲችሉ “የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ማንሳት” አለባቸው (ኤፌ.
6:13)። እነዚህ የጦር መሣሪያዎች ቀበቶ፣ ጥሩር፣ ጫማ፣ ጋሻ፣ የራስ ቁር እና ሰይፍ ናቸው (ኤፌ. 6:14-17)። አሁን ጳውሎስ በደንብ የታጠቁትንና
የተዘጋጁትን አማኞች በጥንት የጦር ሜዳ ላይ ወታደሮች የሚያደርጉትን ነገር
እንዲያደርጉ--ያውም እንዲጸልዩ ይጋብዛቸዋል (ኤፌ. 6፡18-20)።
ጳውሎስ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ የጦርነት ማስጠንቀቂያዎችን
በማስተጋባት ወይም የጦርነት ዋዜማ ንግግሮችን በመናገር የቤተ ክርስቲያኗን
ተልዕኮ በወታደራዊ ጦርነትና የጦር መሣሪያዎች አማካይነት ይናገራል። ጳውሎስ
ይህንን ሀሳብ ሁሉን አካታች በሆነው በመጀመሪያው ትዕዛዝ ውስጥ ይጠቁማል፡
- “በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ” (ኤፌ. 6:10)።
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለ ጦርነት የተሰጡ ምክሮች በጦርነት ላይ የእሥራኤል
ስኬት የሚደገፈው በጦር መሣሪያዎቻቸው ብልጫ ወይም ከጠላት ቁጥር እጅግ
በሚበልጥ ሰራዊት አለመሆኑን ያሰምርበታል። (ለምሳሌ፣ ዘዳ. 20:2-4፤ መሳ.
7:15-18፤ 2ኛ ዜና 20:13-20፤ 2ኛ ዜና 32:6-8፤ ነህ. 4:14፣ 19፣
20)። ነገር ግን የድላቸው ውጤት የሚደገፈው በእግዚአብሔር ኃይል መገኘት ነው።
የስኬታቸው ቁልፍ በራሳቸው መተማመናቸው ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ባላቸው
ጽኑ መታመንና ለስኬታቸው እርሱ ባዘጋጀላቸው መሰናዶ ነበር። ጳውሎስ አማኞች
ይህን ሆነው እንዲገኙ ለማሳመን እነዚህን ርዕሰ ጉዳዮች በድፍረት ይጠቀማቸዋል፡-
(1) የቤተ ክርስቲያኗን ተልዕኮ በመተግበር ረገድ ንቁ መሆን (2) በሕይወታቸውና
በምስክርነታቸው ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ የማይታዩ አቅጣጫዎችን መከታተል
(3) ስኬት ያስገኘላቸው መለኮታዊ መሰናዶ እንደሆነ በደንብ መረዳት (4)
በአማኞች መካከል አንድነትና መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ሁልጊዜ ማስገንዘብ።
መጋደላችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከተፈጥሮ ውጭ ከሆኑ
ጠላቶች ጋር እንደሆነ በመግለጽ ጳውሎስ የሰጠን ማስጠንቀቂያ
የድላችን ብቸኛው ተስፋ የት እንደሆነ ምን ሊያስተምረን ይገባል?
ጳውሎስ ደብዳቤውን የሚያጠናቅቀው በአጠቃላይ ለደብዳቤው አስፈላጊ የሆኑ
ርዕሰ ጉዳዮችንና ሀሳቦችን ለሚይዝ ብርቱ ለሆነ ጦርነት ጥሪ በማድረግ ነው። የሚጀምረው
ሁሉንም የሚያካትተውን የማጠቃለያውን ርዕሰ ጉዳይ በማሳወቅ ሲሆን ያሳወቀውም
አንድ የጦር አዛዥ ለጦርነት በሚያሰማው የጩኸት ቃና ነበር፡- “በመጨረሻም በጌታና
በኃይሉ ብርታት የበረታችሁ ሁኑ” (ኤፌ. 6:10)። የንባቡ ቀሪው ክፍል፣ ኤፌሶን 6፡
11-20፣ ይህንን ታላቅ ፍሬ ሀሳብ የሚያብራራና የሚገልጥ ነው።
በድጋሚ ኤፌሶን 6፡10-20ን ያንብቡ። ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ኃይሎችን
የሚያካትተውን የታላቁ ተጋድሎን እውነታ ጳውሎስ ማሳወቅ ለሚፈልገው
ነጥብ ማዕከላዊ አድርገው የሚመለከቱት እንዴት ነው? ይህን በፊታችን
ያለውን ወሳኝ እውነት በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ጋር ለምናደርገው
እርምጃችን እጅግ አስፈላጊ አድርገን መጠበቅ ያለብን ለምንድር ነው?
ጳውሎስ “በጌታና በኃይሉ ብርታት” (ኤፌ. 6:10) በሚለው ሀረግ
ውስጥ ክርስቶስን የአማኞች ብርታት ምንጭ አድርጎ ያሳውቃል። “ጌታ” የሚለው
ቃል በኤፌሶን መጽሐፍ ውስጥ በቀጣይነት እንደተገለጸው የሚያመለክተው
ክርስቶስን ነው(ኤፌ. 2:21፤ 4:1፣ 17፤ 5:8፤ 6:1፣ 21)። “የቤተ ክርስቲያን ብርታት የሚደገፈው ከሙታን በተነሳውና የጦርነቱ መሪ በሆነው ጌታ
ሁሉን ቻይነት (ኃያልነት) ነው።”-G. G. Findlay, The Epis-
tle to the Ephesians (New York: Ray Long &
Richard R. Smith, 1931), p. 398.
ጳውሎስ ለመግለጽ የሚፈልገውን ነጥብ ለማጉላት ኃይልና ብርታት
የሚሉ ተመሳሳይ ቃላትን በመጠቀም ድግግሞሽን ይጠቀማል፡- ቤተ ክርስቲያን
ማሳየት ያለባት ኃይል አማኞች በውርስ የሚያገኙት ሳይሆን የሚሰጥ ነው። ይህ
ኃይል የሚመጣው ከጌታ ክርስቶስ ነው። ጳውሎስ በዚህ ቦታ የደብዳቤውን
ወሳኝ የሆነ ርዕሰ ጉዳይን፣ አማኞች የሚጋሩትን የእግዚአብሔርን ኃይል በአጭር
ያስቀምጠዋል(ኤፌ. 1:19-22፤ 2:4-6፤ 3:16፣ 17)። ለአሁኑም ሆነ
ለወደፊት ለሚመጣው ለእያንዳንዱ ጦርነት ብርታት የሚገኘው አማኞች ከሞት
ለተነሳውና ከፍ ከፍ ላለው ክርስቶስ ባላቸው ታማኝነት ነው።
የመጀመሪያው ትዕዛዝ ክርስቶስ ለአማኞች ብርታትን ለመስጠት ነቅቶ
እንደሚሰራ የሚያሳውቅ ሲሆን (ኤፌ. 6፡10) የሥላሴ ሶስቱ አካላት አማኞች
ከክፉ ጋር ለሚያደርጉት መንፈሳዊ ጦርነት ብርታት በመስጠት ላይ ተሰማርተዋል።
እግዚአብሔር አብ የራሱን የጦር መሣሪያዎች እንደ “የእግዚአብሔር ጦር ዕቃ”
ያዘጋጃል(ኤፌ. 6:11፣ 13፤ ከኢሳይያስ. 59:17 ጋር ያነጻጽሩ)። ጳውሎስ
ቀደም ብሎ “በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ …እንደ ክብሩ
ባለጠግነት መጠን ይስጣችሁ” (ኤፌ. 3:16) በማለት መንፈስ አማኞችን
በጸሎት እንዲበረቱ በማድረግ ሥራ ላይ እንደሆነ ገልጾአል። በዚህ ቦታ ሰይፍን፣
“የመንፈስን ሰይፍ፣ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል” (ኤፌ. 6:17) የሚሰጥ
መንፈስ ነው። ደግሞ አማኞች “ሁልጊዜ በመንፈስ” መጸለይ አለባቸው (ኤፌ.
6:18)። ጳውሎስ አድማጮቹ ከእነዚህ ክፉ ኃይሎች ጋር ለሚያደርጉት ጦርነት
ሥላሤ በማስታጠቅ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠምዶ እንዳለ እንዲረዱ ይመኛል።
ሮሜ 13:11-14፣ 1ኛ ተሰ. 5:6-8 እና 2ኛ ቆሮ. 10:3-6ን ያንብቡ።
እነዚህ ጥቅሶች ከኤፌሶን 6፡10-12 ጋር የሚነጻጸሩት እንዴት ነው?
ጳውሎስ የዚህን ዓይነት ምሳሌ የሚጠቀመው ለምን ይመስሎታል?
ጳውሎስ በደብዳቤዎቹ ብዙ ጊዜ ወታደራዊ ቋንቋንና ምሳሌዎችን በመጠቀም
አማኞች ምሳሌ የሚሆን ወታደራዊ ባህርይን እንዲኮርጁ ይጋብዛል። ኤፌሶን 6፡10-
20 ከሁሉ ረጅምና እጅግ ትኩረት የተደረገበት አጠቃቀም የተስተዋለበት ክፍል
ሲሆን ወታደራዊ ቋንቋ የወንጌልን ታሪክ ካስተዋለባቸው አብይ መንገዶች መካከል
አንዱ መሆኑን ያሳያል። ከፍ ከፍ ያለው ክርስቶስ በመስቀል ላይ “ኃይላትንና
ሥልጣናትን”(ቆላ. 2:15) በማሸነፉ ከዚያ ከፍ ካለው ቦታ ሆኖ አሁን በኃይላት
ላይ የዚያን ድል ውጤቶች ይሰራል (ፊል. 2:9-11)። ዓለማትን በሙሉ
ባካተተው በዚህ ጦርነት ተከታዮቹን እንደ ወታደሮች በመመልመል ክርስቶስ
የብርሃን ሠራዊትን ወደ ታላቁ የድል ቀን ይመራል (1ኛ ቆሮ. 15:54-58፣ 2ኛ
ተሰ. 2:8 ሮሜ. 16:20)። ጳውሎስ ወታደራዊ ምልክቶችን የተጠቀመበትን
ሀሳብ ሰብሰብ ስናደርግ በክፉና በመልካም መካከል ያለው ጦርነት “ብዙ ጊዜ የቆየ
ዓለም አቀፋዊ ጦርነት ሲሆን በመጨረሻ አንዱ እስኪያሸንፍ ድረስ በሁለት ተፋጥጠው
ባሉ ሰራዊቶች መካከል በዘመናት ሁሉ ሲፈስ የመጣ ጦርነት” መሆኑን እንዳስተዋለ
እንመለከታለን። -Peter W. Macky, St. Paul’s Cosmic War
Myth: A Military Version of the Gospel (New
York: Peter Lang Publishing, Inc., 1998), p. 1.
ጳውሎስ ዓለም አቀፋዊ ስለሆነው ጦርነት በተደጋጋሚ የሚያነሳው
ርዕሰ ጉዳይ የኤፌሶን መልእክት የተሰራበት ፍሬ ነገር አካል ነው። ለጦርነት ጥሪ
ሲያደርግ(ኤፌ. 6:10-20) የሚከተሉትን አስቀድሞ ተጠቅሞአቸው የነበሩትን
የዓለም አቀፋዊ ጦርነት ጥንተ ነገሮች ይሰበስባል፡- እግዚአብሔር አማኞችን ታላቅ
“ኃይል” ሲያስታጥቃቸው (ኤፌ. 1:18-20፤ ኤፌ. 3:16፣ 20)፤ ክርስቶስ
ኃይላትን ድል ሲያደርግና ከፍ ከፍ ሲል (ኤፌ. 1:20-23)፤ አማኞች በአንድ
ወቅት ከሞተው ነገር ግን አሁን ከፍ ከፍ ካለው ክርስቶስ ጋር አንድ በመሆናቸው
ኃይል እንደተሰጠውና ትንሣኤ እንዳገኘ ሰራዊት የቀድሞውን የጨለማ ጌታቸውን
መዋጋት እንዲችሉ መደረጋቸው (ኤፌ. 2:1-10)፤ በኃይላቱ ላይ እየመጣ
ያለውን ጥፋት በመግለጥ ረገድ የቤተ ክርስቲያን ሚና (ኤፌ. 3:10)፤ ክርስቶስን
እንደ ድል አድራጊ መለኮታዊ ጦረኛ አድርጎ ለማሳየት መዝሙር 68፡18ን መጠቀሙ
(ኤፌ. 4:7-11)፤ እና አማኞች የወንጌልን ልብስ “እንዲለብሱ” ጥሪ ማቅረቡ
(ኤፌ. 4:20-24ን ይመልከቱ) በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው። የእግዚአብሔርን
“ሙሉ የጦር ዕቃ” እንድንለብስ ስንጠራ የዓለም አቀፋዊ ጦርነቱን ማዕከላዊ
ሚና ለማስተዋል በደንብ ተዘጋጅተናል፣ ነገር ግን በክርስቶስ የመጨረሻው ድል
እንደምንሳተፍ በተሰጠን መተማመኛ ላይ ጸንተን መቆም አለብን።
እርስዎ በግልዎ የዚህን ዓለም አቀፋዊ ጦርነት እውነታ ብቻ ሳይሆን
በኢየሱስ የእኛ እንዲሆን መጠየቅ የምንችለውን ድል የተለማመዱበት
አንዳንድ መንገዶች ምንድር ናቸው? የእርሱን ድል መረዳት ለእኛ
ተስፋና ልምምድ መሰረት የሚሆነው ለምንድር ነው?
ጳውሎስ ቁም የሚለውን ግሥ በተለያየ መልኩ በየጊዜው መጠቀሙን ልብ እያሉ ኤፌሶን 6፡10-20ን ያንብቡ። ይህ ሀሳብ ለእርሱ ይህን ያህል እጅግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድር ነው?
ጳውሎስ የሚጠቀማቸውን ወታደራዊ ዘይቤያዊ አነጋገሮችን መረዳት
ያለብን ከጥንቱ የጦር ሜዳ አውድ ነው። “መቆም” ማለት ምን ማለት ነው?
(ኤፌ. 6:11፣ 13 14)። ግሡ የሚያሳየው መከላከልን ብቻ ነውን? ስለ
ጦር ሜዳ ሥነ-ጽሁፍ ድርሰቶችን ከጻፉ ታላላቅ ዘመን ተሻጋሪ ደራሲዎች መካከል
አንዱ በሆነው በታሲዲደስ ጽሁፎች ውስጥ የተካተተው የጦርነት ንግግር አንዱ
ወገን አሸናፊ መሆን ካለበት ሶስት ተከታታይ ተግባሮች መፈጸም እንዳለባቸው
አስምሮባቸዋል፡- (1) ወታደሮች ወደ “ጠላት መቅረብ አለባቸው።” ይህ ማለት
ጠላቶቻቸውን ለመገናኘት መሄድ አለባቸው፤ (2) ከዚያም ከጠላቶቻቸው ጋር
የጨበጣ ውጊያ በማድረግ ጥቃት ማድረስና “ፀንተው መቆም” ወይም “ቦታቸውን
አለመልቀቅ” ይጠበቅባቸዋል፤ (3) በመጨረሻ “ጠላትን መክተው መመለስ”
አለባቸው (see Thucydides, The Peloponnesian War
[New York: E. P. Dutton, 1910], 4.10.1-5).
የጥንቱ ጦርነት የተከሰተበት ቁልፍ ሰዓት የተገለጸው ከእነዚህ ሶስት
ተግባራት ከሁለተኛው ጋር፣ ሁለቱ ተቃራኒ ሰልፎች “ከተሰባበረ ነሃስ፣ እንጨትና
ሥጋ በሚወጣ አሰቃቂና የሚያስጠላ ድምጽ” እየተጋጩ ሲቀላቀሉ ነበር፣ ይህንን
የጥንቱ ደራሲ የነበረው ዜኖፎን “ ‘አስደናቂ ግጭት’ይለዋል። ”-Victor
Davis Hanson, The Western Way of War (New York:
Oxford University Press, 1989), pp. 152, 153.
በዚህ ወሳኝ ስልታዊ ቅጽበት ፀንቶ መቆምና ቦታን አለመልቀቅ የጥንቱ
ጦርነት ታላቅ ተግዳሮት ነበር። በዚህ በቅርብ ሊጀመር ባለው ጦርነት እያንዳንዱ
ወገን ጠላትን “ለመግፋት” ኃይል ይፈልጋል።
ጳውሎስ የጦር መሣሪያን እንዲያነሱ ያስተላለፈው ጥሪ የሚያንጸባርቀው
ወታደሮች “ተሰባስበውና በቅርበት ሆነው በመቶዎች የሚቆጠሩ ምቶችን በጠላት
ላይ ሲያሳርፉና በእነርሱም ላይ ሲያርፉባቸው” የሚደረገውን ጦርነት ነው።-Vic-
tor Davis Hanson, The Western Way of War, p. 152.
ይህ የተረጋገጠው ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ከጠላቶቿ ጋር ትግል
እንደገጠመች አድርጎ በማሳየቱ(ኤፌ. 6:12፤ የሀሙስን ትምህርት
ይመልከቱ) እና በቁጥር 13 ላይ “ለመቆም” የሚል ግሥ በመጠቀሙ ነበር፡-
“በክፉው ቀን ለመቃወም፣ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ” በማለት
ገልጾታል (NKJV, ESV, emphasis added)።
ይህ መዝናናትን የሚያሳይ አስተያየት አይደለም! ስለዚህ “መቆም” ማለት
ሥራ ላይ ሊውል የሚችለውን እያንዳንዱን መሣሪያ ይዞ በቅርበት ሆኖ በኃይል
ጦርነትን መግጠም ማለት ነው። ይህ ነጥብ ጳውሎስ አስቀድሞ “በአንድ ልብ ስለ
ወንጌል ኃይማኖት እየተጋደላችሁ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ” (ፊልጵ. 1:27)
በማለት በሰጠው ልባዊ ምክሩ በገለጸው ወታደራዊ ምሳሌ ውስጥ ይገኛል።
ዕብራውያን 12:4ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ በጌታ መቆም ማለት
ምን ማለት እንደሆነ ለማጠቃለል የሚረዳው እንዴት ነው? የዚህ
መቆም የጋራ ተፈጥሮው ምንድር ነው?
ጳውሎስ በኤፌሶን 1፡21፤ 3፡10 እና 6፡10-20 ላይ ለተገለጹ ክፉ መንፈሳዊ ኃይላት የተለያዩ ማዕረጎችን በመስጠት የዘረዘረበት ዓላማው ምንድር ነው ብላችሁ ፍርድ ትሰጣላችሁ?
ጳውሎስ “መጋደላችን” (ኤፌ. 6:12) በማለት የሚገልጸው (ፓሌ)
የሚለውን የግሪክ ቃል በመጠቀም ሲሆን ቃሉ በሚታገሉ ሰዎች መካከል
የሚካሄደውን ውድድር የሚያሳይ ነው። ትግል ለጦርነት ለመዘጋጀት ምርጥ
ዝግጅት እንደሆነ ተደርጎ ይወሰድ ስለነበር ይህ አገላለጽ ሰራዊቶች ወደ ጦርነት
በሚገቡበት ጊዜ መሣሪያ ከመሣሪያ ጋርና በጨበጣ ለሚያደርጉት ጦርነት ተገቢ
የሆነ መግለጫ ነው። ጳውሎስ አጽንዖት እየሰጠ ያለው አማኞች ከክፉ ኃይላት ጋር
በቅርበት ሆነው በሚያደርጉት ጦርነት እውነታ ላይ ነው።
ለእነዚህ ኃይላት የሰጣቸው ስሞች (ማዕረጎች) ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ቀርበዋል፡-

ጳውሎስ “ከሚጠራው ስም ሁሉ” (ኤፌ. 1:21) በሚለው ሰፊ
መግለጫው ውስጥ “በሰማያዊ ሥፍራ ያሉ መንፈሳዊ ኃይላት” ኤፌ. 6:12)
በማለት የክፉና ከተፈጥሮ ውጭ ያሉ ኃይላት በሙሉ ለክርስቶስ እንደሚገዙ
ያረጋግጣል(ኤፌ. 1:21)። ነገር ግን በማንኛውም ጦርነት በተቃራኒ
ወገን ያሉ ኃይሎችን ዝቅ አድርጎ መገመት በፍጹም ጥሩ ስልት አይደለም።
የምንጋፈጠው ሰብአዊ ጠላቶችን ሳይሆን አጭበርባሪ በሆነ ጄነራል፣ በዲያብሎስ
የሚመራ “በሰማያዊ ሥፍራ ያሉ የክፋት መንፈሳዊ ሰራዊትን” እንደሆነ ጳውሎስ
ያስጠነቅቀናል(ኤፌ. 6:11)። ነገር ግን ኃይለኛ የሆኑ ጠላቶቻችንን ለመቃወም
ሁልጊዜ መንቃት ቢኖርብንም በእነርሱ ልንስፈራራ አይገባም። በጦርነቱ ውስጥ
እግዚአብሔር አብሮን ስላለ (ኤፌ. 6፡10)፣ ከጦር መሣሪያዎቹ ሁሉ የተሻለውን
የራሱን የጦር ዕቃ፣ “የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር” ይሰጠናል (ኤፌ. 6:11፤
ከኢሳ. 59:15-17 ጋር ያነጻጽሩ)። የእርሱን እውነት፣ ጽድቅ፣ ሰላም፣
እውነት፣ ድነትና መንፈስ ቅዱስ ልንደርስባቸው በምንችልበት ቦታ አስቀመጠልን
(ኤፌ. 6፡13-17)። እግዚአብሔር ከፊታችን ስለሚሄድ እና እርሱ የሰጠንን
የጦር መሣሪያ ከራስ እስከ እግር ስንታጠቅ አንሸነፍም (ሮሜ. 16:20፤ 1ኛ
ቆሮ. 15:23፣ 24፤ 2ኛ ተሰ. 2:8)።
የእነዚህ እኛ በፍጹም ልንቋቋማቸው የማንችላቸው ከተፈጥሮ
በላይ የሆኑ ክፉ ኃይላት እውነታ ከእነዚህ ኃይላት የሚበልጥ
ብቻ ሳይሆን አስቀድሞውኑ ያሸነፋቸውን ጌታ ኢየሱስን አጥብቀን
መያዝ ያለብን ለምን እንደሆነ ምን ያስተምረናል?
“ሥራችን በኃይል መሰራት ያለበት ሥራ ስለሆነ
እንደ ታማኝ የኢየሱስ ወታደሮች ወደ ጠላት ምሽጎች በደም የተቀለመውን አርማ
(ባንዲራ) ይዘን መሄድ አለብን። ‘መጋደላችን ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምና
፣ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዥዎች ጋር በሰማያዊም
ሥፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።’ የጦር መሣሪያችንን
ለማስቀመጥ፣ በደም የተቀለመውን ባንዲራ ዝቅ ለማድረግ፣ የሰይጣን ምርኮኞችና
ባሪያዎች ለመሆን የምንስማማ ከሆነ ከጦርነቱና ከሥቃዩ ነጻ ልንሆን እንችላለን።
ነገር ግን ይህ ሰላም የሚገኘው ክርስቶስንና ሰማይን በማጣት ብቻ ነው። በዚህ
ሁኔታ ሰላምን መቀበል አንችልም። በክህደትና በኃጢአት ሰላምን ከማግኘት ይልቅ
እስከ ምድር ታሪክ ፍጻሜ ድረስ ጦርነት፣ አሁንም ጦርነት ይሁን።”-Ellen G.
White, The Review and Herald, May 8, 1888.
ኤፌሶን 6:10-20 ከራዕይ መጽሐፍ ጋር የሚገናኘው እንዴት ነው? ንባቡ
በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ተደጋግመው የቀረቡትን የጦርነት ጭብጥ የሚመስሉ
የመጨረሻ ዘመን ክስተቶችን መሰረታዊ አመለካከት ያሳያል (ራዕይ 12፤ 16፡12-
16፤ 19፡17-21፤ 20፡7-10ን ይመልከቱ)። በሁለቱም ውስጥ የእግዚአብሔር
ሕዝብ “በሰማያዊ ሥፍራዎች” በሚኖር እና “በአሁኑ ዘመን በሥራ ላይ ባለና
ኃይለኛ በሆነ” ጠላት ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። በሁለቱም ውስጥ የእግዚአብሔር
ሕዝብ “በመጨረሻው ዘመን የሚሆነውን ነገር በማየት” ተበረታትቷል።
በተጨማሪ፣ “ሁለቱም እይታዎች ጠላት ሙሉ በሙሉ ወደሚሸነፍበትና አዲስ
ዘመን ለዘላለም ወደሚመሰረትበት ወደ የመጨረሻው ጦርነት፣” “የእግዚአብሔር
ሕዝብ የመጨረሻው በግርማ የተሞላ ሁኔታ” እና “የጠላት ዘላለማዊ ጥፋት”
እርግጠኛ የሚሆንባትን አዲስ ዘመን ይጠቁማሉ። (See Yordan Kalev
Zhekov, Eschatology of Ephesians (Osijek,
Croatia: Evangelical Theological Seminary,
2005), pp. 217, 233-235.)
1. የጨለማን ኃይላት እጅግ ግልጽ በሆነ ሁኔታ የተጋፈጡት መቼ ነው?
በእነዚህ ጊዜያቶች እጅግ ጠቃሚ ሆነው ያገኙአቸው ስልቶች ምን ነበሩ?
2. በኤፌሶን 6፡10-20 ላይ ባገኙት መረጃ መሰረት በተለየ ሁኔታ “በክፉ
መንፈሳዊ ሰራዊት” እንደተጨቆነ የሚሰማውን ሰው እንዴት ሊያገለግሉት
ይችላሉ (ኤፌ. 6:12)?
3. “የዲያብሎስን ሽንገላ” በተሻለ ሁኔታ መለየትና መቃወም የምንችለው
እንዴት ነው (ኤፌ. 6:11)? ለምሳሌ፣ መዳን እስከማይችሉ ድረስ
እጅግ ኃጢአተኛ፣ እጅግ የተበላሹ መስሎ ስለተሰማዎ እምነትዎን
ለመተው ዝግጁ መሆንዎ የተሰማዎት ምን ያህል ጊዜ ነው? ያንን ሀሳብ
በአእምሮዎ ውስጥ እያስቀመጠ ያለው ማን ነው--ክርስቶስ ነው ወይስ
የጨለማ ኃይላት? በተለየ ሁኔታ እነዚህን በሚመስሉ ጊዜያት በኢየሱስ
የተሰጡንን በርካታ ድንቅ ተስፋዎች መጠየቅ ያለብን ለምንድር ነው?