የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ኤፌ. 6:1-9፤ ማር.
10:13-16፤ ቆላ. 3:21፤ 1ኛ ጴጥ. 2:18-25፤ 2ኛ ቆሮ. 5:10፤
ቆላ. 3:24፣ 25።
የመታሰቢያ ጥቅስ:- “እናንተም ጌቶች ሆይ፣ ዛቻውን ትታችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፣ በእነርሱና በእናንተ ላይ የሚገዛ ጌታ በሰማይ እንዳለ ለሰውም ፊት እንዳያደላ ታውቃላችሁና።” (ኤፌ 6:9)።
በ2018 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቤተ መዘክር
ውስጥ ያለ ሰው ሰራሽ ነገር ብዙ ትኩረት አገኘ። እርሱም ባሪያዎች
እንዲያምጹ የሚቀሰቅስ ማንኛውም ንባብ ከውስጡ እንዲወጣና
የእምነትን መሰረታዊ ነገሮች ለማስተማር እንዲያጥር ተደርጎ የተሰራ መጽሐፍ
ቅዱስ ነበር። መጽሐፉ የታተመው በ1808 ዓ.ም ሲሆን እዚህም እዚያም
ከውስጡ ንባቦች የተወገዱበት ብቻ አይደለም። ከብሉይ ኪዳን ከመቶ ዘጠና እጅ
የሌለበት ሲሆን ከአዲስ ኪዳን ደግሞ ከመቶ ሃምሳ እጅ የለበትም። ከመጽሐፍ
ቅዱስ 1189 ምዕራፎች መካከል ያሉት 232 ምዕራፎች ብቻ ናቸው።
በተለይም የመጽሐፍ ቅዱስን የምሥራች ታሪክ የሚገልጹ ብዙ ነገሮች
በሌሉበትና ብዙ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ ጥቅም ላይ የዋለውን “ባሪያዎች ሆይ፣
ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በልባችሁ ቅንነት በሥጋ
ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ” (ኤፌ. 6:5) የሚለውን ጥቅስ ጨምሮ የባርነት
ተቋምን የሚያጠናክሩ ንባቦች ባሉበት እንዲቆዩ ተደርገዋል።
ዛሬ፣ በእኛ ዘመንና ባህል፣ ወሳኙ ተግዳሮታችን የሚሆነው ኤፌሶን 6፡1-9ን
በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጸው በተሟላ የድነት ታሪክ አውድ ማንበብ
ነው። ጳውሎስ የወንጌልን እሴቶች በእርሱ ዘመን ለነበረው ጉድለት ለነበረነበት
ማህበራዊ መዋቅሮች ሲተገብረው ስንመለከት ሳለ ምን መማር እንችላለን?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለጳጉሜ 4 ሰንበት ለመዘጋጀት አጥኑ።
ጳውሎስ ለልጆች የሰጠው ምክር ምን ነበር? ይህን ምክር ከብሉይ ኪዳን መረጃን በመውሰድ የሚደግፈው እንዴት ነው? ኤፌ. 6:1- 3። (ደግሞ ማቴ. 18:1-5፣ 10፤ ማር. 10:13-16 ይመልከቱ)።
ጳውሎስ ለልጆች የሰጠውን ምክር ሙሉ በሙሉ ለማድነቅ፣ እያደገ
በነበረው የኤፌሶን ከተማ በነበሩ የቤት ውስጥ ቤተ ክርስቲያናት እንደሚነበብ
አድርገን ማሰብ አለብን። በግሪኮች ባህል አባት ስልሳ ዓመት እስኪሆነው ድረስ
ወይም በሮማውያን ባህል እስኪሞት ድረስ ልጆች በአባታቸው ሥልጣን ሥር
ስለሚሆኑ “ልጆች” (በግሪክ ታ ተክና) የሚለው ቃል በርካታ የዕድሜ ክልሎችን
የሚያካትት ሊሆን ይችላል። እነዚህ ልጆች በወላጅ ሥልጠና ሥር (ኤፌ. 6፡4)
በሚሆኑበት የልጅነት ዕድሜ ውስጥ ቢሆኑም በራሳቸው መብት ደቀ መዛሙርት
ለመሆን በሚችሉበት ዕድሜ ውስጥም ያሉ ናቸው።
ጳውሎስ በክርስቲያን ጉባኤዎች እግዚአብሔርን እያመለኩ የነበሩ
ልጆች “በጌታ” ማለትም በክርስቶስ ወላጆቻቸውን እንዲታዘዙና እንዲያከብሩ
ይማጸናቸዋል።(ከኤፌ.. 5:22፤ ኤፌ. 6:4፣ 5፣ 7-9 ጋር ያነጻጽሩ)። በዚህ
ቦታ ልጆችን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደሆኑ አድርገን እንድናከብራቸውና
በአምልኮ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንድናደርጋቸው ተጋብዘናል። ይህ ልጆችን
ለማሳደግና ለልጆች አገልግሎት ንባቡን መሰረታዊ ያደርገዋል።
ጳውሎስ እንዲታዘዙ የሚሰጠው ትዕዛዝ ፍጹማዊ አይደለም። የወላጆች ትዕዛዝ
“የክርስቶስን መስፈርቶች የሚቃረን ከሆነ፣ የሚያም ቢሆንም፣ ልጆች እግዚአብሔርን
መታዘዝና ይህን ተከትሎ የሚመጡ ነገሮችን ለእርሱ መተው አለባቸው።”-Ellen
G. White, The Adventist Home, p. 293.
ጳውሎስ ለልጆች የሰጠውን ማሳሰቢያ የሚያጠናቅቀው አምስተኛውን
ትዕዛዝ በመጥቀስ ሲሆን ይህም አሥርቱ ትዕዛዛት ለክርስቲያን አማኞች የምሪት
ምንጭ እንደሆኑ አድርጎ ለሚሰጠው ከፍ ያለ ዋጋ ምስክርነት እየሰጠ ነው (ይህ
ግልጽ የሆነ የኤፌሶን 4፡1-6፡9 ባህርይ ነው። በተለይ ኤፌ. 4፡25፣28፤ ኤፌ.
5፡ 3-14)። ‘አባትህንና እናትህን አክብር’ (ኤፌ. 6:2) የሚለውን ጥቅስ
ይጀምርና ተጨማሪ አስተያየት ለመስጠት የጀመረውን ሀሳብ በማቋረጥ “እርሱም
ተስፋ ያለው የመጀመሪያው ትዕዛዝ ነው” (ኤፌ. 6:2) የሚል ሀሳብ ከሰጠ
በኋላ ተመልሶ ‘ደህና እንድትሆንና በምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ’(ኤፌ.
6:3) በማለት ጥቅሱን ያጠቃልላል። ሰብአዊ ዘር እንዲያድግ ወላጆችን ማክበር
የእግዚአብሔር ዕቅድ አካል መሆኑን አምስተኛው ትዕዛዝ ይመሰክራል። ፍጹም
እንኳን ባይሆኑ ወላጆችን ማክበር ጤንነትንና ደህንነትን ያጎለብታል።
እነዚህ ጥቅሶች የቤተሰብ ግንኙነቶች ምን ያህል ወሳኝ እንደሆኑ
የሚያጠናክሩት እንዴት ነው?
ኤፌሶን 6፡4ን እና ቆላስይስ 3፡21ን አነጻጽሩ። ቆላስይስ 3፡21 የሰውን ልጆች ከማናደድ እንድንርቅ ምን ማበረታቻ ይሰጠናል?
ሲራክ የሚባል በጳውሎስ ዘመን የነበረ የአይሁዶች ሰነድ፣ አባቶች ወንድ
ልጆቻቸውን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ይመክራል፡- “ልጁን የሚወድ ሰው
አዘውትሮ ይገርፈዋል።… ልጅን ካቀበጥከው ያሸብርሃል፤ አብረኸው ከተጫወትክ
ያሳዝንሃል።…በልጅህ እፍረተ ቢስነት ማዘን ካልፈለግክ ቅጣው፣ ቀንበሩንም
አክብድበት።” (Sirach 30:1, 9, 13, NRSV).
የጳውሎስ ምክር ከዚህ የተለየ ለዛ አለው። በመጀመሪያ ለወላጆች
የሚሰጠው ትዕዛዝ አሉታዊ ነው፡- “ልጆቻችሁን አታስቆጡአቸው” ካለ በኋላ
ቀጥሎ “በጌታ ምክርና በተግሳጽ አሳድጉአቸው” በማለት አዎንታዊ ትዕዛዝ
ይሰጣል፣ (ኤፌ. 6:4)። በጳውሎስ ዘመን ልጆች እንደ ወላጅ ንብረት ይቆጠሩ
ስለነበር አባቶች በልጆቻቸው ላይ ፍጹም የሆነ ሕጋዊ ሥልጣን ነበራቸው ። አባቶች
ልጆቻቸውን በኃይል መቅጣት የሚችሉ ሲሆን ሊገድሉአቸውም ይችሉ ነበር።
በአንዳንድ ሁኔታዎች አባት በልጆቹ ላይ የነበረው ሥልጣን ጌታው በባሪያዎቹ
ላይ ከነበረው ሥልጣን ይበልጥ ነበር። ጳውሎስ የዚህ ዓይነቱን ሥልጣን ሕጋዊ
እያደረገ ሳይሆን የቤተሰብን ግንኙነቶች በድፍረት ግልጽ እያደረገና እንደገና መልክ
እያስያዘ ነበር። የተቆጡ ልጆች “የጌታን ምክርና ተግሳጽ” ስለማይቀበሉ (ኤፌ.
6:4) ከሁሉ በላይ ለክርስቶስ ታማኝ ከመሆን አውድ ክርስቲያን ወላጆች ስለ
ኃይል አጠቃቀማቸው እንደገና እንዲያስቡበት ጳውሎስ ይጋብዛቸዋል።
“አባቶችና እናቶች ሆይ፣ በቤት ውስጥ የእግዚአብሔርን ጠባይ መወከል
አለባችሁ። ልጆቻችሁ እንዲታዘዙአችሁ የምትጠይቁት ከባድ ቃላት በመናገር
ሳይሆን በደግነትና በፍቅር ነው።. . .
“በቤት ውስጥ የምትመቹ ሁኑ። ያልተቀደሰ ቁጣን የሚቀሰቅስን
እያንዳንዱን ቃል ተቆጣጠሩት። ‘አባቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁን አታስቆጡአቸው’
የሚለው መለኮታዊ ትዕዛዝ ነው።. . .
“በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ለወላጆች ጭካኔ ወይም ጭቆና ወይም
ልጆች ወላጆቻቸውን እንዳይታዘዙ የሚል ፈቃድ አልተሰጠም። በቤተሰብ
ሕይወትና በአገራት አስተዳደር ውስጥ ሥራ ላይ የሚውለው የእግዚአብሔር ሕግ
የሚፈልቀው ዘላለማዊ ፍቅር ካለው ልብ ነው።”-Ellen G. White,
Child Guidance, p. 259.
ይህ ትምህርት የተሰጠበት አውድ የሚናገረው ስለ ልጆችና ወላጆች
ቢሆንም ከሌሎች ሰዎች ሁሉ ጋር እንዴት መኖር እንዳለብን
ከእነዚህ ጥቅሶች ምን መርሆዎች ሊወሰዱ ይችላሉ?
በሚከተሉት ንባቦች ውስጥ ለባሪያዎችና ለጌቶቻቸው የተሰጠውን ምክር ያንብቡ፡- ኤፌ. 6:5-9፤ ቆላ. 3:22-4:1፤ 1ኛ ቆሮ. 7:20- 24፤ 1ኛ ጢሞ. 6:1፣ 2፤ 1ኛ ጴጥ. 2:18-25። ይህንን ምክር እንዴት በአጭሩ ያስቀምጡታል?
ጳውሎስ ክርስቲያን ለሆኑ ባሪያ አሳዳሪዎች ሲናገር መስማትና ክርስቲያን
የሆኑ ባሪያዎችና ክርስቲያን የሆኑ ጌቶቻቸው በኤፌሶን በቤት ውስጥ በነበሩ ቤተ
ክርስቲያናት ውስጥ አብረው ሲቀመጡ ማሰብ የሚያስገርም ነው። በግሪክና በሮም
ዓለም የነበረው ባርነት ኋላ በአዲሱ ዓለም ከነበረው ወሳኝ በሆኑ መንገዶች ይለያል።
በአንድ ዘር ቡድን ላይ የሚያተኩር አልነበረም። በከተማ የሚኖሩ የቤተሰብ ባሪያዎች
አንዳንድ ጊዜ የትምህርት ዕድል ስለሚሰጣቸው የንድፍ መሃንዲሶች፣ ሀኪሞችና
ፈላስፋዎች ሆነው ሊሰሩ ይችላሉ። ምንም እንኳን አብዛኞቹ ባሪያዎች ነጻነታቸውን
ባያገኙም አንዳንድ ጊዜ ለእነዚህ የቤተሰብ ባሪያዎች ከተወሰነ የአገልግሎት ጊዜ
በኋላ ነጻነት ይሰጣቸው ነበር። ለእነዚህ ልዩነቶች እውቅና ለመስጠት በሚደረግ
ጥረት የቅርቦቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ዱሎስ (“ባሪያ”) የሚለውን የግሪክ
ቃል በኤፌሶን 6፡5-8 ውስጥ “አገልጋይ” ብለው ተርጉመውታል።
ነገር ግን በገጠር አከባቢ ያሉ ባሪያዎች ከባድ ሥራ ስለሚሰሩ እነዚህ
ባህርያት ተመሳሳይ ባልሆነ ሁኔታ የሚተገበሩ ናቸው። ባሪያዎች የሚያገለግሉበት
ቦታ የትም ቢሆን እነርሱን፣ ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ለሚገዛው ጌታ ያልተገደበ
ኃይልና ሥልጣን ተገዥ ናቸው። ፑብሊሊያስ ሲይረስ የተባለ የቀድሞ ባሪያ እንዲህ
እያለ የጮኸው ጩኸት ወደ አእምሮ እየተመላለሰ የሚመጣና የሚያስጨንቅ
ነው፡- “እንደ ባሪያ ከመዋረድ መሞት የተሻለ (ውብ) ነገር ነው።“ እነዚህ
ባሪያዎች በጌቶቻቸው ከሚደርስባቸው ጭቆና የተነሣ በስጋት ስለሚኖሩ እነዚህን
እውነታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት በግሪክ ዱሎስ የሚለውን ቃል “ባሪያ”
ብሎ መተርጎሙ ይመረጣል (ኤፌ. 6፡9)።
በጳውሎስ ዓለም ባርነት ሁልጊዜም ነበር። እርሱ ስለ ባርነት የሚያወራው
እንደ ማህበራዊ ተሃድሶ አምጪ ሳይሆን በወቅቱ ያለውን እውነታ እንዴት
መያዝ እንዳለባቸው ለማሳወቅና ኋላ በሕብረተሰቡ ላይ ሰፊ እንደምታ እንዲኖር
የሚያደርገውን የአማኙን መለወጥ ማዕከል ያደረገ አዲስ ራዕይ ለመፍጠር
አማኞችን እንደሚመክር ፓስተር ነው። “ተልዕኮው በሮም ግዛት የነበሩ
ባሪያዎችን ነጻ ማውጣት አልነበረም። ይልቁን የእርሱ አመለካከት የነበረው
ከሕጋዊ ነጻ መውጣት የተለየ ነገር፣ የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆኑ ከአዲስ
ፍጥረት የተነሣ ስለመጣው በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ሕብረት መፍጠር
ነበር። ለጳውሎስ ማህበራዊ ለውጥ መካሄድ ያለበት የክርስቶስ አካል በሆነችው
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ በአጥቢያ ደረጃ፣ በክርስቲያን ቤት ውስጥ ባለችው ቤተ ክርስቲያንና በቤተሰብ ውስጥ ነው።”-Scot McKnight, The Let-
ter to Philemon (Grand Rapids, MI: Eerdmans
Publishing Company, 2017), pp. 10, 11.
በክርስትና ታሪክ ውስጥ ከተፈጠሩ ታላላቅ እንከኖች ውስጥ አንዱ
የባርነት ልምምድን ትክክል እንደሆነ ለማረጋገጥ አንዳንድ ሰዎች
እነዚህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንባቦች የተጠቀሙበት መንገድ ነው።
የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት በጥንቃቄ መያዝ እንዳለብን ምን
የሚያስፈራ መልእክት ነው ከዚህ የምንወስደው?
ጳውሎስ ለባሪያዎች በሰጠው ዝርዝር መመሪያ ላይ ከክርስቲያን ባሪያዎች ይፈልግ የነበረው ምን ነበር? ኤፌ. 6:5-8.
ጌቶቻቸውን እንዲያገለግሉ ጳውሎስ ይጠይቃቸዋል። በደንብ ጎልቶ የሚታየው
እነርሱ እንዲፈጽሙት በተደጋጋሚ የሚጠቅሰው ታላቅ የመተካት ተግባር ነው።
ባሪያዎች ለአሳዳሪዎቻቸው ለክርስቶስ ብቻ ሊሰጥ የሚገባውን ታማኝነት
በማቅረብ እነርሱን በክርስቶስ ቦታ ማስቀመጥ የለባቸውም። ነገር ግን ልባዊ
የሆነ ጥሩ አገልግሎት እንዲሰጡ በሚያነሳሳቸው መሰጠትና ታማኝነት በጌታቸው
ፋንታ ጌታ ክርስቶስን መተካት አለባቸው። ይህንን ወሳኝ የሆነ የመተካት ተግባር
በማደፋፈር ጳውሎስ በባሪያና በጌታ መካከል ስለሚኖረው ግንኙነት የተለወጠ
ክርስቲያናዊ መረዳት እየሰጠ ነው።
ይህንን የመተካት ተግባር እንዲፈጽሙ ጳውሎስ ጫና ይፈጥርባቸው የነበረባቸውን
በርካታ መንገዶች ልብ በሉ፡-
* ጳውሎስ ባሪያዎችን ወደ እውነተኛው ሰማያዊ ጌታቸው በማመልክት
ባሪያ አሳዳሪዎቻቸውን ወደ “ምድራዊ ጌቶች” ደረጃ ዝቅ ያደርጋቸዋል
(ኤፌ. 6፡5)።
* “ለክርስቶስ እንደሚያደርጉ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በእውነተኛ ልብ”
ሊያገለግሉ ይገባል (ኤፌ. 6:5)።
* ክርስቲያን ባሪያዎች እንደ ጌቶቻቸው ባሪያዎች ሳይሆኑ እንደ “ክርስቶስ
ባሪያዎች” ትክክለኛ አገልግሎት መስጠት አለባቸው ብሎ በመከራከር
ይህንን የመተካት ተግባር እጅግ ግልጽ ያደርገዋል (ኤፌ. 6፡6)።
* አገልግሎታቸውን ሲያከናውኑ ወደ እግዚአብሔር የተመላከተ ልባዊ
አገልግሎት በመስጠት “ከልባቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ” ይፈጽማሉ።
(ኤፌ. 6:6)።
* ጳውሎስ “ሰውን ሳይሆን ጌታን” እንደሚያገለግሉ በማሰብ አዎንታዊ በሆነ
ሁኔታ የተነሳሳ አገልግሎት እንዲሰጡ ይጋብዛል(ኤፌ. 6:7)።
ክርስቲያን ባሪያዎች ለልባዊ አገልግሎታቸው ክርስቶስ ሲመለስ ከእርሱ
ሙሉ ሽልማት ሊጠብቁ ይችላሉ። ሥራውን የሰሩት ለእርሱ ስለሆነ ሽልማቱን
የሚጠብቁትም ከእርሱ ነው፤ ይህ ደግሞ ለማይከፈላቸው ባሪያዎች ወርቃማ የሆነ
ሀሳብ ነው። ባሪያው ምድራዊ ጌታው ልፋቱን እንደማያደንቅለት ወይም ከዚያም
የከፋ ነገር ሊያስብ ይችላል (ከ1ኛ ጴጥሮስ 2፡19፣ 20 ጋር አነጻጽሩ)። ሆኖም
ለክርስቲያን ባሪያ የሚከታተለውና “እያንዳንዱ ሰው የሚሰራውን መልካም ሥራ”
የሚመለከት (ኤፌ. 6:8, NASB) ጌታ ያለው ሲሆን እርሱ እውነተኛውን
ሽልማት ይሰጠዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን አስከፊ ልምምድ በግልጽ እንዲኮንን አብዝተን
ብንፈልግም አያደርግም። ነገር ግን አብረናቸው ከምንሰራቸው
ሰዎች ጋር የሚኖረን ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት በዚህ
አውድ ከጳውሎስ ቃላት ምን መርሆዎችን ማውጣት እንችላለን?
ጳውሎስ “ባሪያ ወይም ጨዋ ቢሆን” (ኤፌ. 6:8) በማለት
ለባሪያዎች በተናገራቸው የመጨረሻዎቹ ቃላት ውስጥ “ጨዋ” የሚለው ቃል
የሚያመለክተው ባሪያ አሳዳሪዎችን ሲሆን ባሪያዎችና ጌቶቻቸው በፍርድ ቀን
በክርስቶስ ፊት እኩል እንደሚቆሙ በማሰብ ወደ ምክሩ እንዲሻገር እድል
ይሰጠዋል። (ከ2ኛ ቆሮ 5:10፤ ቆላ. 3:24፣ 25 ጋር ያነጻጽሩ)።
የኤፌሶንን መጽሐፍ እቤትዎ ባለችው ቤተ ክርስቲያን እየተነበበ
እንደሚሰማ ክርስቲያን ባሪያ አሳዳሪ እንደሆኑ አድርገው ራስዎን
ያስቡና ባሪያዎችዎ በተገኙበት ለተሰጠው ለዚህ ምክር ምላሽ
የሚሰጡት እንዴት ነው? ኤፌ. 6:9.
ጳውሎስ ለጌቶች፣ ለባሪያ አሳዳሪዎች፣ የሰላ ልባዊ ምክር የሰጠ ሲሆን
ጌቶች የሚለው ቃል የመጣው በግሪክ ሆይ ኩሪኦይ ከሚለው ቃል ሲሆን ትርጉሙ
ባሪያዎቻቸውን የማስፈራራት ልማድ ያላቸው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሆ ኩሪኦስ
ከሚለው የግሪክ ቃል የተተረጎመው ጌታ ከሚለው ጋር የተነጻጸረ ሲሆን ለሰው
ፊት የማያደላውን ክርስቶስን የሚወክል ቃል ነው።
ጳውሎስ ጌቶች ለባሪያዎቻቸው “ለእነርሱ እንዲደረግላቸው የሚፈልጉትን
ነገር እንዲያደርጉ” ያሳሰበ ሲሆን ይህም በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን
ለነበረው ባሪያ አሳዳሪ አስደንጋጭ ነገር ነው። ጌቶች ለባሪያዎቻቸው ለክርስቶስ
ባላቸው ታማኝነት በሚገዙና ከመልካም ፈቃድ በሚመጡ ተግባሮች ምላሽ
መስጠት አለባቸው። ይህም ጳውሎስ ባሮች እንዲያደርጉ ከጠየቃቸው ጋር
የሚመሳሰል ነው (ኤፌ. 6፡5-8)። በዚያን ዘመን ጌቶች በባሪያዎቻቸው ላይ
ድብደባን (1ኛ ጴጥ. 2፡20)፣ የወሲብ ጥቃትን፣ መሸጥን፣ ከአቅም በላይ
ማሰራትን፣ ረሃብን፣ በብረት መታሰርን፣ ያልተገባ ስም መስጠትንና ሞትን ጨምሮ
የተለያዩ ዓይነት ቅጣቶችን ይፈጽሙ ስለነበር ጌቶች ባሪያዎቻቸውን ማስጨነቅን
እንዲያቆሙ ይነግራቸዋል።
ጳውሎስ የባሪያ አሳዳሪዎች ከግሪክና ከሮም ዓለም ማህበራዊ መዋቅር ባሻገር
እንዲመለከቱ በሚያደርጉ ሁለት መነቃቂያዎች ትዕዛዞቹን ይደግፋል። እነርሱም:-
1. እነርሱና በእነርሱ ዘንድ እንደ ባሪያ የተቆጠሩት በአንድነት የአንድ ጌታ ባሪያዎች
ናቸው (“የእናንተም የእነርሱም ጌታ በሰማይ እንዳለ በማወቅ”፣ ከቆላ. 4፡1 ጋር
አነጻጽሩ)፤ 2. ሰማያዊው ጌታ ለማንም ሳያዳላ በእኩል ይፈርዳል። የራሳቸው ጌታ
እንደ ባሪያ የተቆጠሩትን ከሌሎች ጋር በእኩል የሚያይ ከሆነ እነርሱም እንደዚህ
ማድረግ አለባቸው (ከፊሌሞን 15፣ 16 ጋር አነጻጽሩ)።
ጳውሎስ በኤፌሶን መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀመው አብዛኛው ቋንቋ
ክርስቲያን ባሪያዎችን የሚያበረታታ ነበር፡- የልጅነት ማዕረግ (ኤፌ. 1:5)፤
ቤዛነት (ኤፌ. 1:7)፤ ርስት (ኤፌ. 1:11፣ 14፤ ኤፌ. 3:6)፤ ከኢየሱስ
ጋር በዙፋን ላይ መቀመጥ (ኤፌ. 2:6)፤ “ዜጎች፣” “የእግዚአብሔር ቤተሰብ
አባላት” መሆን (ኤፌ. 2:19፤ ከኤፌሶን 3:14፣ 15 ጋር አነጻጽሩ)፤ እና
የክርስቶስ አካል ክፍሎች (ኤፌ. 3:6፣ ኤፌ. 4:1-16ን ይመልከቱ)።
ኤፌሶን 6:5-9 ስለ ንግግር የተሰጠውን ምክር (ኤፌ. 4፡25-32) እና
የወሲብ ሥነ-ምግባርን (ኤፌ. 5፡1-14) ጨምሮ በደብዳቤው ውስጥ
የተካተተው ትምህርት በሙሉ በባሪያዎችና በጌቶቻቸው መካከል ባሉ ግንኙነቶች
ውስጥ እንደሚሰራ አድርጎ ቀሰቀሰው።
ጳውሎስ እንደ መሰል አማኞች በመቁጠር ልጆችን
ማክበሩ (ኤፌ. 6፡1-3) ዛሬ በዓለማችን ልጆች እየተያዙ ስላሉበት ሁኔታ ያለንን
ጭንቀት ከፍ ያደርጋል። ለአባቶች የተናገረው ቃሉ (ኤፌ. 6፡4) ለወላጅነት
ኃላፊነቶች ትኩረት እንድንሰጥ ይጋብዘናል። ማህበራዊ ዳራው ከብዙዎቻችን እጅግ
ሩቅ ስለሆነ እና ባርነት በማንኛውም መልክ ቢሆን እጅግ ትላልቅ ከሆኑ የግብረገብ
ክፋቶች አንዱ መሆኑን ስለምናውቅ ጳውሎስ ለባሪያዎች የሰጠው ምክር (ኤፌ.
6፡5-8) እና በተለይም ለባሪያ አሳዳሪዎች የሰጠው ምክር (ኤፌ. 6፡9) ብዙ
ተግዳሮት ያለበት ነው። እነዚህ ቃላት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተሰጡና የመጽሐፍ
ቅዱስ አካል እስከሆኑ ድረስ ዛሬ እንዴት እንደምንተገብራቸው ማሰብ አለብን።
በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን በኤፌሶን ከነበሩ አማኞች ጋር የወንጌልን እሴቶች
በግንኙነቶቻችን ውስጥ የመተግበር ዕድልና ኃላፊነት አለብን። ከዚህ በታች ያሉት
የውይይት ጥያቄዎች ያንን ወሳኝ ሥራ ለማበረታታት የተዘጋጁ ናቸው።
1. ልጆችን መውደድ “ጌታን ለመገናኘት የተዘጋጀ ሕዝብ” ማስረጃ ሆኖ
ይታወቃል ማለት ለአድቬንቲስቶች ምን ማለት ነው? ሉቃስ 1:17
(ከሚልክያስ 4:6 የተጠቀሰ)።
2. ጳውሎስ ለልጆች ያለው ግልጽ አክብሮት የሚከተለውን ወሳኝ ጥያቄ
ይጠቁማል፡- በልጅነት ዕድሜያቸው ዓመጽ፣ የወሲብ ጥቃትና ውርደት
ለደረሰባቸው ልጆች የክርስቶስን እንክብካቤ ለመስጠት የእኛ ኃላፊነት
ምንድር ነው? In view of research on the pro-
found impact of Adverse Childhood Ex-
periences (or ACEs; see https://www.
cdc.gov/violenceprevention/)፣ ለእነርሱ ያለን
ኃላፊነትስ ምንድር ነው?
3. ጳውሎስ ለልጆች ያለውን አክብሮትና ኢየሱስ ለእነርሱ ያለውን ጥንቃቄ
ለማራዘም ቤተ ክርስቲያን ለእነዚህ ልጆች ጥበቃ ለማድረግና ለመንከባከብ
ያሏት ኃላፊነቶች ምንድር ናቸው? ይህን ለማድረግ መዘጋጀት ያለባቸው
ሥርዓቶችና ሂደቶች ምንድር ናቸው?
4. ጳውሎስ በኤፌሶን 6፡5-9 ላይ ለባሪያዎችና ለጌቶቻቸው የሰጠው ምክር
ብዙ ጊዜ በአሰሪዎችና በሰራተኞች መካከል ላለው ግንኙነት ጥቅም ላይ
ውሏል። ይህ ተገቢ የሚሆነው በምን መንገዶች ነው? ይህን በማድረግ
የሚመጡ አደጋዎች ምንድር ናቸው?
5. እንደ ዓለም አቀፉ የባርነት አመላካች መረጃ መሰረት ከ40 ሚሊዮን
የሚበልጡ ሰዎች በባርነት ውስጥ ስላሉ ባርነት በዓለማችን የሚያም
እውነታ እንደሆነ ቀጥሏል። http://www.globalslave-
ryindex.org/).
እንደ ነጻ ሕዝብ ባርነትን ለመገርሰስ ቀደምት መንፈሳዊ አባቶች በጽናት
የተሰጡ ስለሆነ ”ባሪያው ወንድማችን ስለሆነ እና በእርሱ ስም ጭቆና በሙሉ
ስለሚያበቃ ሰንሰለቶች ይሰበራሉ” ብለን እየዘመርን ሳለ ለእነዚህ ለባርነት
ለተሸጡ በጌታ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለሆኑት የእኛ ኃላፊነቶች ምንድር
ናቸው)? (lyrics to “O Holy Night,” public do-
main)?