የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ያዕ. 2:8–13፤ ዘዳ. 5:12–15፤ መዝ. 33:6፣ 9፤ ራዕይ 14፤ 2ኛ ጴጥ. 3:13፤ ራዕይ 21:1።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፥ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ” (ኤፌ. 3:9)።
የሰብአዊ ዘር ስብዕና እጅግ ጠቃሚው ነገር ፍጥረታችን የጋራ መሆኑ ነው።
በእግዚአብሔር የተለየን ሆነን መፈጠራችን የእያንዳንዱን ሰብአዊ ፍጡር
ዋጋ ይጨምራል። ገና በእናቱ ማህጸን ያል ልጅ፤ እጆቹና እግሮቹ በሙሉ
ሽባ የሆነ ታዳጊ፣ ደምረ ህመም (ዳውን ሲንድሮም) ያለበት ጎልማሳ፣ እና በመርሳት
በሽታ የተጠቃች አያት በሙሉ ለእግዚአብሔር ዋጋ አላቸው። እግዚአብሔር
አባታቸው ነው። እነርሱ ደግሞ የእርሱ ወንድና ሴት ልጆች ናቸው። “ዓለሙንና
“ዓለሙንና
በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ
በሠራው መቅደስ አይኖርም፤…… በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች
ሁሉ ከአንድ ፈጠረ” (
ሁሉ ከአንድ ፈጠረ” (የሐዋ. 17:24–26)።
የእኛ ውርስ የምንጋራው ውርስ ነው። የአንድ ቤተሰብ አባላት ነን። አንድ
አምላክ ቀርጾ የሰራን ወንድማማቾችና እህትማማቾች ነን። ፍጥረት ለራሳችን
ትክክለኛ የሆነ ዋጋ የመስጠት ስሜት እንዲኖረን ያደርጋል። የእርስዎን ማንነት
ልዩ ተፈጥሮአዊ መዋቅር ለመመስረት ዘረመሎች (ጂን) እና ሃብለበራሂዎች
(ክሮሞሶሞች) አንድ ላይ በተጣመሩ ጊዜ ንድፉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው።
በመላው ዩኒቨርስ ውስጥ እርስዎን የሚመስል ማንም የለም። እርስዎ የተለዩ፣
ከፍጥረት ውስጥ እርስዎን የሚመስል ማንም የሌለ፣ ዩኒቨርስን የፈጠረው አምላክ
የእኛን ሥጋ በመልበስ ለእርስዎና ለእኔ ኃጢአት ራሱን መስዋዕት እስከሚያደርግ
ድረስ ትልቅ ዋጋ ያለዎት የተለዩና አንድም እርስዎን የሚመስል ሰው በፍጥረተ
ዓለም ውስጥ የሌለ ሰው ነዎት።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለግንቦት 12 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
እኛ እንዲሁ በዘፈቀደ የተፈጠሩ ዘረመሎች ስብስብ ወይም የአጋጣሚና በእድገት ለውጥ ያመጣ የአፍሪካ ጦጣ ውጤት ብንሆን ኖሮ ሕይወት ትርጉም የለሽ ይሆን ነበር። ምድር ተብላ በምትጠራው ፕላኔት ላይ የመኖሪያ ቦታ ለማግኘት እየተሻሙ ካሉ በግምት ወደ ስምንት ቢሊዮን ከሚጠጉ ሰዎች መካከል አንዱ ብቻ ከሆንን ሕይወት ዝም ብሎ ከመኖር ያለፈ ነገር ስለማይኖረው ዓላማውን ይስታል። ከዚህ በተቃራኒ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የፍጥረት ዘገባ የመኖር ምክንያትንና የመኖራችንን የግብረገብ ግዴታ ይሰጣል። በእግዚአብሔር ስለተፈጠርን ለምናደርጋቸው ነገሮች በእርሱ ዘንድ ተጠያቂዎች ነን። የፈጠረን ተጠያቂም ያደርገናል። “የግብረገብ አንጻራዊነት” ባለበት ዓለም እንኳን ፍጹምነትን መስርቷል። ራዕይ 14:7፣ ሮሜ 14:10 እና ያዕቆብ 2:8–13ን ያንብቡ። ፍርድ ተጠያቂነትንና ሀላፊነት መውሰድን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በተመለከተ በተዘዋዋሪ መንገድ ምን ይጠቅሳል? ፍርድ፣ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት እና አምልኮ የሚገናኙት እንዴት ነው?
በራዕይ ምዕራፍ 14 ላይ በሰማይ መካከል የሚበሩ ሶስቱ መላእክት
“የፍርዱ ሰዓት መጥቶአልና” (ራዕይ 14:7)እያሉ ያውጃሉ። እግዚአብሔር የሞራል
ምርጫዎችን ከማድረግ ችሎታ ጋር ስለፈጠረን ስለምንወስናቸው ውሳኔዎች
ኃላፊነት አለብን። በዘፈቀደ የተሰባሰቡ የዘረመሎች ስብስብ፣ ከወላጆቻችን
በውርስ ያገኘናቸው ባህርያትና የአከባቢያችን ውጤት ብቻ ከሆንን ድርጊቶቻችን
በአብዛኛው የሚወሰኑት እኛ መቆጣጠር በማንችላቸው ኃይሎች ይሆናል።
ነገር ግን ፍርድ የሞራል ኃላፊነት እንዳለ ያመለክታል። በዚህ የምድር
አስጨናቂ ሰዓት፣ በፍርድ ሰዓት፣ ውሳኔዎቻችንን በዘላለማዊነት ብርሃን
እንድናደርግ እግዚአብሔር ጥሪ ያቀርብልናል። የመጀመሪያው መልአክ ልባዊ
ተማጽኖ “ሰማይንና ምድርን፣ ባህርንም የውኃውንም ምንጮች ለፈጠረ ስገዱ”
(ራዕይ 14:7) የሚል ሲሆን ለአምልኮ ሁሉ መሰረቱ በእግዚአብሔር መፈጠራችን
ስለመሆኑ እውቅና ይሰጣል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለሰባተኛ ቀን ሰንበት ተገዥ መሆናችን ኢየሱስ
እንደ ፈጣሪ መመለክ እንደሚገባው ማመናችንን ይገልጻል። የአሥርቱ ትዕዛዛት
ሕግ ሕይወትን በሙላት መኖር እንድንችል በመለኮት ምሪት የተሰጡ መርሆዎች
መሆናቸውን መቀበላችንን ያሳያል። ሕግ የእግዚአብሔር መንግስት መሰረትና
የእርሱ ባህርይ መገለጥ ስለሆነ የፍርድ መስፈርት ይሆናል። ለሰንበት ትዕዛዝ ያለን
ታማኝነት የመታዘዝ ሕይወት ለመኖር ያለን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው።
ስለ ፍጥረት ያለን መረዳት በባህርያችን ላይ ተጽእኖ የሚኖረው
እንዴት ነው? ከወላጆቻችን የወረስናቸው ባህርያትና አከባቢያችን
በየቀኑ ከምንመርጣቸው ምርጫዎቻችን ጋር ምን ግንኙነት አላቸው?
አስቀድሞውኑ እንዲኖሩን ያልመረጥናቸውን የባህርይ ግድፈቶች
በእግዚአብሔር ፀጋ ማሸነፍ የምንችለው እንዴት ነው?
ስለ ፍጥረት ማረጋገጫ የሚሰጥ መልእክት ለዓለማችን እጅግ ስለሚያስፈልገው እግዚአብሔር ሰንበትን ሰጠን። እግዚአብሔር አስደናቂ የሆነ ተስፋ የሚሰጠውን መልእክት የላከው የዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሀሳብ የተማረውን ዓለም እያጥለቀለቀ በነበረበት በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ነበር። በራዕይ 14፡6፣ 7 ላይ ያለውን ይህን መልእክት ስናጠና ቆይተናል። ሰይጣን ኢየሱስን ስለሚጠላና እንደ ፈጣሪና አዳኝ የሚገባውን ስግደት (አምልኮ) እንዲቀበል ስለማይፈልግ የፍጥረትን ሀሳብ ለማዛባት የሚቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጓል። ክርስቶስ እንደ ፈጣሪያችን ስግደትን ለመቀበል የተገባ በመሆኑ ላይ ባለው ታላቁ ተጋድሎ እምብርት ላይ ሰንበት አለ። የእግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን መልእክት ክርስቶስን እንደ ሰማይና ምድር ፈጣሪ አድርገው እንዲያመልኩት ሰብአዊ ዘርን በሙሉ የሚጠራ መልእክት ነው። የስግደት (የአምልኮ) ሁሉ መሰረት እርሱ ፈጣሪያችን መሆኑ ነው። ዘፍ. 2:1–3፣ ዘጸ. 20:8–11 እና ዘደ. 5:12–15ን በራዕይ 14፡ 6፣ 7 አውድ ያንብቡ። በሰንበት ትዕዛዝ ውስጥ በፍጥረትና በድነት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት መመልከት እንችላለን?
ሰንበት በእርሱ የሚኖረን ዘላለማዊ እረፍት ምልክት ነው። ለፈጣሪ
ታማኝ የመሆናችን ልዩ ምልክት ነው (ሕዝ. 20:12፣ 20)። በዘፈቀደ የመጣ ሕጋዊ
መስፈርት ሳይሆን ከጽድቅ በሥራ በእርሱ ያገኘነውን እውነተኛ እረፍት የሚያሳይ
ነው። ሰንበት እኛ በራሳችን በፍጹም ማሳካት የማንችለውን ነገር ለእኛ ስላሳካልን
አምላክ ይናገራል።
ቅዱሳት መጻሕፍት በየሰንበቱ በእርሱ ፍቅርና ጥንቃቄ ላይ እንድናርፍ
ይጠሩናል። ሰንበት የሥራ ሳይሆን የእረፍት ምልክት ነው፤ ሰንበት የሕጋዊነት
ሳይሆን የጸጋ ምልክት ነው፤ ሰንበት የኩነኔ ሳይሆን መተማመኛ የማግኘት
ምልክት ነው፤ ሰንበት በራሳችን ሳይሆን በእርሱ የማረፍ ምልክት ነው። በየሰንበቱ
በእርሱ መልካምነት እንደሰታለን፣ በክርስቶስ ብቻ ሊገኝ ስለሚችለው ድነትም
እናወድሰዋለን።
ደግሞ ሰንበት በቀድሞው ኤደን ፍጽምና እና ወደ ፊት በሚመጣው አዲስ
ሰማይና አዲስ ምድር ክብር መካከል አገናኝ ድልድይ ነው (ኢሳ. 65:17፤ ራዕይ 21:1)።
ሰንበት ወደ መነሻችን እንድንመለስ ይጠራናል። ከቤተሰባችን መነሻ ጋር
ያገናኘናል። ሰንበት ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በቀጣይነት ሲጠበቅ ኖሯል። ወደ ኋላ
ከተፈጠርንበት ጊዜ ጋር የሚያገናኝ የማይበጠስ ሰንሰለት ነው። የእግዚአብሔር
ልጆች በመሆናችን የከበረ እውነት ላይ ትኩረት እንድናደርግ ያስችለናል። ከእርሱ
ጋር የቀረበ ግንኙነት እንድንፈጥር ይጠራናል።
በራዕይ 14፡ 6፣ 7 ላይ ስለ ሰንበት ትዕዛዝ ፍንጭ የተሰጠው እንዴት
ነው? ለመጨረሻው ዘመን መልእክታችን ወሳኝ የሆነውስ ለምንድር
ነው? (ዘጸ. 20:8–11ን ይመልከቱ)።
ሰይጣን ልዩ ሆነን የመፈጠራችንን እውነታ ለማጥፋት በሚያደርገው ጥረት ብዙም ያልተወሳሰበ ማስመሰያ አስተዋውቋል። ማስመሰያው ከእኛ መካከል በአንዳንዶች ዘንድ እንኳን ሳይቀር ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን እንደሚከተለው ተገልጾአል፡- በመሰረታዊነት ፍጥረትን ወደ መኖር ያመጣው እግዚአብሔር ነው፣ ነገር ግን ሕይወትን ወደ መኖር ለማምጣት ብዙ ዘመናትን ወስዶበታል። ፍጥረትን ወደ መኖር ለማምጣት የተጠቀመው ዘዴ ዝግመተ ለውጥ ነው። ይህ አቀራረብ “ሳይንሳዊ ጭብጥን” ከፍጥረት ዘገባ ጋር ለማጣጣም ይሞክራል። የፍጥረት ቀናት ረዥምና ያልተወሰነ ዘመን የሸፈኑ ሲሆን ሕይወት በምድር ላይ ከተፈጠረ ቢሊዮኖች ዓመታት እንደሆነ ያረጋግጣል። መዝ. 33:6፣ 9 እና ዕብ. 11:3ን ያንብቡ። እነዚህ ግልጽ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እግዚአብሔር ዓለምን እንዴት እንደፈጠረ ምን ይነግሩናል?
መጽሐፍ ቅዱሳዊው የፍጥረት ዘገባ ግልጽ ነው። እርሱ (እግዚአብሔር)
ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም” ይላል(መዝ. 33:9)። “ዓለሞች
በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት
እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን” (ዕብ. 11:3)። የዘፍጥረት መጽሐፍ
የመጀመሪያው ምዕራፍ እግዚአብሔር ዓለምን እያንዳንዱ ቀን 24 ሰዓት ባለው
ስድስት ቀናት ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን እንዳረፈ ያረጋግጣል። በዘፍጥረት ምዕራፍ
1 እና 2 ላይ ያለው የቋንቋ መዋቅር ከዚህ የተለየ ምንም ነገር አይፈቅድም።
በስድስት ቀን ፍጥረት የማያምኑ ምሁራን እንኳን የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ዕቅድ
ፍጥረት በስድስት ቀናት መፈጠሩን ለማስተማር እንደሆነ ያምናሉ።
በዘፍጥረት ምዕራፍ 1ላይ “ቀን” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጡ ቃል
“ዮም” የሚል ነው። በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዮም” የሚለውን ቃል ቁጥር
እንደ ቅጽል በመግባት (ሶስተኛ ቀን፣ የመጀመሪያ ቀን፣ ወዘተ) ሲያጎለው ጊዜውን
በ24 ሰዓታት ይገድባል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቁጥር “ዮም” የሚለውን ቃል
በማጉላት ያልተወሰነ ሰዓትን ያመለከተበት አንድም አጋጣሚ የለም። በሁሉም
አጋጣሚዎች ያመለከተው 24 ሰዓት ያለውን ጊዜ ነው።
እግዚአብሔር በስድስት ቀን ዓለምን ካልፈጠረ ሰባተኛው ቀን ሰንበት ምን
ጥቅም ይኖረዋል? ስድስት ቀናትን የወሰደ የፍጥረት ሳምንት ባይኖር ኖሮ ሰንበትን
በሳምንቱ ስድስት ቀናት ለተፈጠረው ፍጥረት መታሰቢያ አድርጎ ማስቀመጥ
ምንም ትርጉም አይኖረውም። ፍጥረትን ለመፍጠር ረዥም አመታትን ፈጅቷል
የሚለውን ሀሳብ መቀበል የሰባተኛ ቀን ሰንበትን መገዳደር ነው። በመጽሐፍ
ቅዱስ እውነተኛነት ላይም አሳሳቢ የሆኑ ጥያቄዎችን ያስነሳል።
ሰይጣን በሰንበት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የእግዚአብሔር ሥልጣን
እምብርት የሆነውን ነገር እየተገዳደረ ነው። የስድስት ቀናት ፍጥረትን ካለመቀበል
የበለጠ የስድስት ቀናት ፍጥረት መታሰቢያ የሆነውን ለማጥፋት ውጤታማ የሆነ
ሌላ ምን ይኖራል? ክርስቲያኖችን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ሰባተኛ ቀን ሰንበትን
አለመቀበላቸው አያስገርምም። ለመጨረሻው ማታለያ እንዴት ያለ ምቹ ሁኔታ
ነው።
ከሚሊዮኖች አመታት በፊት በሰማይ የተጀመረው ታላቁ ተጋድሎ መነሻው በእግዚአብሔር ሥልጣን ላይ የተነሳው ጥያቄ ነበር። ዛሬም ያ ተግዳሮት አለ። ራዕይ 14:7፣ 9 እና 12ን ያንብቡ። ከዚህ በታች ባሉ መስመሮች ላይ ያሉ አረፍተ ነገሮችን በመሙላት እነዚህን ጥቅሶች አጠቃልሉአቸው። ራዕይ 14:7 የምን ጥሪ ነው?
ራዕይ14:9 ምን እንዳናደርግ የቀረበ አስፈሪ ተማጽኖ ነው?
ራዕይ 14:12 ምን የሚያደርግ ሕዝብን ነው የሚገልጸው?
በመጨረሻው ዘመን በክፉና በመልካም፣ በክርስቶስና በሰይጣን መካከል
የሚደረገው ጦርነት ማዕከላዊው ጉዳይ የአምልኮ ጉዳይ እንደሆነ እነዚህ ንባቦች
ግልጽ ያደርጋሉ። የምናመልከው ፈጣሪን ነው ወይስ አውሬውን? ፍጥረት
የእምነታችን ሁሉ መነሻ ስለሆነ (እግዚአብሔር ፈጣሪያችን እንደሆነ ከማመን
የበለጠ ትርጉም የሚሰጥ ሌላ ምን ነገር እናምናለን?)በራሱ በዘፍጥረት የፍጥረት
ዘገባ ውስጥ የተቀመጠው የሰባተኛው ቀን ሰንበት (ዘፍ. 2፡1-3) የዚያ ፍጥረት
ዘላለማዊና የማይጠፋ ምልክት ሆኖ ይቆማል። እጅግ መሰረታዊ ለሆነው
አስተምህሮ እጅግ መሰረታዊ ምልክት ነው። ከዚህ የበለጠ መሰረታዊ የሆነው
እግዚአብሔር ራሱ ብቻ ነው።
ስለዚህ የሰባተኛውን ቀን ሰንበት ሥልጣን መንጠቅ ማለት የሚቻለውን
መንገድ ሁሉ በመጠቀም የእግዚአብሔርን ሥልጣን፣ ያውም የፈጣሪነቱን
ሥልጣን መንጠቅ ነው። ጉዳዩ ለማንኛውም ነገር ድጋፍ በመስጠት የፈጣሪነቱን
ሥልጣን ከመሰረቱ መንግሎ የመጣል ጉዳይ ነው። እንዲያውም የእግዚአብሔርን
የራሱን ቦታ ለመውሰድ መሻት ነው (2ኛ ተሰ. 2፡4)።
በመጨረሻው ዘመን የምንጋፈጠው እርግጠኛው ጉዳይ ለኢየሱስ ያለን
ፍቅርና ታማኝነት ነው። ነገር ግን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ ይህ ፍቅር
የሚገለጸው ለትዕዛዛቱ በመታዘዝ ነው (1ኛ ዮሐ. 5፡3)። ከትዕዛዛቱ መካከል
እግዚአብሔር ፈጣሪ መሆኑን የሚያመለክተው ሰንበት ብቻ ለሁሉም ነገር ድጋፍ
ይሰጣል (ዘጸ. 20፡8-11)። ስለዚህ እግዚአብሔርን በሚያመልኩና አውሬውን
በሚያመልኩ መካከል የመጨረሻው መለያ ውጫዊ ምልክት መሆኑ አያስደንቅም
(ራዕይ 14፡11-12)። ከሁሉም ነገር ይበልጥ ሰንበት ምን ያህል መሰረታዊና ዋና
እንደሆነ ስንመለከት የመጨረሻው ፈጣሪን የማምለክ ጉዳይ ከማንኛውም ነገር
ይልቅ ምን ሊሆን እንደሚችል ማየት ይከብዳል።
ከቀናቶቹ መካከል አንዱን ቀን እስከጠበቅን ድረስ ግለሰቡ የትኛውንም
ቀን እንደ ሰንበት ቢጠብቅ ልዩነት አያመጣም በማለት ብዙ ሰዎች
ይከራከራሉ። ለዚህ ጥያቄ ከመጽሐፍ ቅዱስ መልስ መስጠት የምንችለው
እንዴት ነው?
ሰንበት አድካሚ በሆነ ዓለም ውስጥ የመጠጊያ ሥፍራ ነው። በየሳምንቱ
የዚህን ዓለም ጭንቀቶች እርግፍ አድርገን በመተው ወደ እግዚአብሔር መሸሸጊያ
ማዕከል፣ ወደ ሰንበት እንገባለን። አብርሃም ሄስክል የተባለ ዝነኛ አይሁዳዊ
ደራሲ ሰንበትን “በጊዜ ውስጥ ያለ ቦታ” ብሎ ይጠራል። በየሰባተኛው ቀን
የእግዚአብሔር ሰማያዊው ዙፋን ወደ ምድር ስለሚወርድ ይህን 24 ሰዓታት
ያለውን ቀን ከእርሱ ጋር የቀረበ ወዳጅነት በመፍጠር እንድናሳልፍ ወደ እርሱ
መገኘት ክብር ይጋብዘናል።
ሄስኬል ስለ ሰንበት ውበትና ክቡርነት በጻፈው መጽሐፉ ውስጥ
የሰንበትን ወሳኝነት በሚከተሉት ቃላት ይገልጻል፡- “ሰንበት ገነትን የሚገልጽ
ምሳሌና የእግዚአብሔር መገኘት ምስክር ነው፤ በጸሎቶቻችን ሰንበት የሚሆንልንን
የመሲሁን ዘመን ተስፋ እናደርጋለን። እያንዳንዱ ሰንበት ለዚያ ልምምድ
ያዘጋጀናል። አንድ ሰው የሰንበትን ቅምሻ ማጣጣም ካልተማረ በቀር በሚመጣው
ዓለም የምንለማመደው የዘላለም ቅምሻ አያስደስተውም።”
በፍጥረት ጊዜ እግዚአብሔር ልዩ የሆነ መኖሪያ ቦታ ሰራልን። በዚያ ቦታ
መጠጊያ እናገኛለን። በዚያ ቦታ ደህንነት ይሰማናል። ሥራው የተሟላ (ፍጹም)
ነው። ተፈጽሞአል። በሰንበት ስናርፍ በእርሱ የፍቅር ጥንቃቄ ውስጥ እያረፍን
ነን። በቅርብ ሊመጣ ባለው በአዲሱ ሰማይና በአዲሲቷ ምድር የምናገኘውን
ዘላለማዊውን እረፍት ተስፋ በማድረግ እናርፋለን።
ኢሳ 65:17፣ ኢሳ 66:22፣ 2ኛ ጴጥ. 3:13፣ እና ራዕይ 21:1ን ያንብቡ።
ሰንበትን መጠበቅ ወደፊት ወደሚመጠው ዘላለም የሚያመለክተው
እንዴት ነው?
በመጀመሪያ ምድርን የፈጠረው ያው አምላክ እንደገና ይፈጥራትና ሰንበት
የእርሱ ፈጣሪነት ዘላለማዊ ምልክት ሆኖ ይኖራል (ኢሳ. 66፡23ን ይመልከቱ)።
እንዲያውም አይሁዶች ሰንበትን እንደ ምልክት፣ በዕብራይስጥ ኦላም ሃባ
የሚባለው ሊመጣ ያለው ዓለም ቅምሻ አድርገው ተመልክተውት ነበር።
ፈጣሪን እንድናመልክ እየተማጸኑ በሰማይ መካከል የሚበሩት የሶስቱ
መላእክት መልእክት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሚያሳዝን ተስፋ መቁረጥ
ውስጥ ላሉ ብዙዎች ሰማያዊ መልስ ነው። በመጀመሪያ ሁሉንም ነገር ወደፈጠረው
ወደ ፈጣሪያችን እና ከፍርድ በኋላ እና ኃጢአት ከተወገደ በኋላ ሁሉንም ነገር
አዲስ ወደሚያደርገው ወደ አዳኛችን ያመለክታል። “ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥
ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት
ይቀደስ አለ” (ራዕይ 21:5)።
እርስዎ በግልዎ ሰንበትን በራስዎና በቤተሰብዎ ሕይወት የሰማይ
ቅምሻ ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው?
“እግዚአብሔርን ለማምለክ የቀረበው ምክንያት
ፈጣሪ መሆኑ ነው። በሰማይ ያለውን የአምልኮ ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ ሰማያዊ
ፍጡራን እጅግ አጭርና ግልጽ በሆነ ሁኔታ እንዲህ በማለት ገልጸውታል፡- ‘ሁሉን
ነገር ፈጥረሃልና’ (ራዕይ 4:1)። በምድር ላይ በተቻለ መጠን የእግዚአብሔር
ፈጣሪነት አጽንዖት ሊሰጠው እንደሚገባ ለማሳየት መላእክት ‘ሰማይንና ምድርን
ባህርንም የውኃውንም ምንጮች ለፈጠረ ስገዱ’ብለዋል (ራዕይ 14:7)። መልአኩ
ለእግዚአብሔር ለመስገድ ያቀረበውን ጥሪ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የአራተኛውን
ትዕዛዝ ቋንቋ መጠቀሙ በትክክል ተመልክቷል። (ዘጸ. 20:11)።…
“በአስርቱ ትዕዛዛት ውስጥ ሰንበት እግዚአብሔር ፈጣሪ መሆኑን
በማመልከት እንደ ማህተም ሆኖ ተቀምጧል፤ የእርሱን የግዛት ክልል--ፍጥረቱን
ሁሉ እንደሚገዛ ያረጋግጣል፤ ሁሉን ነገር ስለፈጠረ የመግዛት መብት እንዳለውም
ያሳያል። ዘንዶው ስኬት ለማግኘት በሆነ መንገድ ይህን መታሰቢያ ወደ ጎን
ማድረግ ነበረበት።”—Ángel Manuel Rodríguez, ”The Closing of the
Cosmic Conflict: Role of the Three Angels’ Messages,” pp. 40, 41.
1.ከየት መጣሁ? እዚህ ያለሁት ለምንድር ነው? የዘላለም መዳረሻዬስ
ምንድር ነው? ለሚሉ ታላላቅ ጥያቄዎች የሰንበት መልእክት መልስ
የሚሰጠው እንዴት ነው?
2. በተፈጥሮ አስደናቂነት ላይ ጊዜ ውሰዱ። በዚህ ሰፊ ዩኒቨርስ
ውስጥ ስለ ራሳችን መኖር ተዓምር አስቡ። የዚህ ፍጥረት መታሰቢያ
የሆነ ሰንበት አንዴም ዝንፍ ሳይል በየሳምንቱ ዞሮ መምጣቱ (እኛ
ወደ እርሱ መሄድን በተቃረነ መልኩ) የፍጥረት አስተምህሮ ምን
ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ምን አስተማረን?
3. በዳንኤል ምዕራፍ 3 እና ምዕራፍ 6 ላይ በእነዚህ በመንፈስ
ምሪት በተጻፉ መረጃዎች ውስጥ የአምልኮ ጉዳይ የመጣበትን ሁኔታ
እንዴት ይመለከቱታል? በእነዚህ መረጃዎች ውስጥ “በአውሬው
ምልክት” ዙሪያ በሚከሰት ችግር ወቅት የእግዚአብሔር ታማኝ
ሕዝብ ስለሚገጥማቸው ተግዳሮት መዘጋጀትና ማሰብ እንድንችል
ሊረዱን የሚችሉ ምን ነገሮች ይገኛሉ?
4. ፍጥረት የተፈጠረው በሚሊዮኖች፣ እንዲያውም በቢሊዮኖች
ዓመታት አዝጋሚ ለውጥ እንደሆነ ለሚያምን ሰው ሰባተኛውን
ቀን ሰንበት የዚህ ፍጥረት መታሰቢያ አድርጎ መጠበቅ ምክንያታዊ
አለመሆኑን የምናሳየው እንዴት ነው?