የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ራዕይ 1:9፣ ኢሳ. 40:26፣ 2ኛ ቆሮ. 5:17፣ ቆላ. 1:17፣ ራዕይ 4:11፣ ዮሐ. 19:16–30።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል” (ራዕይ 4:11)።
ነገሮችን ያለ አንዳች ጥያቄ፣ በተለይም ሁልጊዜ የምናውቃቸውን ወይም
የተለማመድናቸውን ነገሮች መቀበል ቀላል ነው። ለምሳሌ ለትንንሽ ልጆች
በኖሩባት አጭር ዕድሜያቸው ያወቁአቸውን ወላጆች ያለ ጥያቄ መቀበል
ምን ያህል ቀላል ነው? እኛም ፀሐይን፣ ሰማይን፣ አየርን ወይም ከእግራችን ሥር
ያለውን መሬትን ያለ አንዳች አመስጋኝነት መቀበል ምን ያህል ቀላል ነው።
ነገር ግን መኖራችንን ራሱን ምን ያህል ያለ አንዳች ጥያቄና ምሥጋና
እንደምንቀበል ቆም ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ከምንም ነገር ይልቅ
የሆነ ነገር መኖሩ ለምንድር ነው የሚለውን ዝነኛ ፍልስፍናዊ ጥያቄ ቆም ብለን
የምንጠይቀው ምን ያህል ጊዜ ነው?
ለመጀመር ያህል ዩኒቨርሳችንና በውስጡ ያሉ ግርማ ሞገስ የተላበሱ
አስደናቂ ነገሮች ያሉት ለምንድር ነው? ዩኒቨርሳችንና በውስጡ ያለን እኛ በዚህ
ቦታ ባንኖር ኖሮ ምን ያክል ታላቅ አመክኖያዊ ተቃርኖ ሊከሰት ይችል ነበር?
በቅርብ እንደወጣው ሳይንሳዊ መላምት በአንድ ወቅት ዩኒቨርሳችን አልነበረም።
በሌላ አገላለጽ፣ የእኛ መኖር ድንገተኛ ሲሆን በዚህ ቦታ መገኘታችንም ተዓምር
ነው። ዩኒቨርስ ሙሉ በሙሉ ከምንም ነገር ወይም ከሆነ ዓይነት ሂሳባዊ ቀመር
ስለመነሳቱ የተነገሩ የተለያዩ ዓይነት ተረታ ተረቶች ቢኖሩም ዩኒቨርሳችንና
በውስጡ ያሉ ነገሮች ያሉት ፈጣሪያችን የሆነው እግዚአብሔር ስለፈጠራቸው
ነው።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለግንቦት 5 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ (የሐዋ. 1፡9) በሕይወት ከነበሩት ሐዋርያት የመጨረሻው የነበረው ዮሐንስ ጨካኝ በነበረው የሮም ገዥ ዶሚቲያን ተሰዶ በነበረበት በፍጥሞ ደሴት ላይ ጎበኘው። ራዕይ 1:9ን ያንብቡ። ደግሞ ማቴ. 13፡21፣ የሐዋ. 14፡22 እና ዮሐ. 16፡33ን ይመልከቱ። ኢየሱስን በዚህች ዓለም ላይ ለመከተል ለሚሹ ሁሉ እዚህ ያለው መልእክት ምንድር ነው?
ዮሐንስ ከቤተሰቡ፣ ከወዳጆቹና ከክርስቲያኑ ማህበረሰብ ተለይቶ እንደ
ኢየሱስ ተከታይ በተጋፈጣቸው መከራዎችና ፈተናዎች ብቻውን አልተተወም
ነበር። አገልግሎቱ አላለቀም ነበር። ምስክርነቱ አልተጠናቀቀም ነበር። በዚያች
ተነጥላ ባለች ደሴት ላይ አስደናቂ ብሩህነት የነበረው ጎብኚ መልአክ ዮሐንስን
ጎበኘውና ከእግዚአብሔር ዙፋን በቀጥታ መልእክት አመጣለት። ይህ ከኢየሱስ
የመጣው መልእክት በዘመናት ሁሉ ማስተጋባት ነበረበት። ለሁሉም የሚሆን
የተስፋ መልእክት ቢሆንም በተለየ ሁኔታ የእግዚአብሔርን የመጨረሻ
ዘመን ሕዝብ ለኢየሱስ መምጣት የሚያዘጋጅ መልእክት ነው። ጠንከር ያለ
የማስጠንቀቂያ መልእክት እና የመጨረሻ ዘመን ፈተናዎችን (ወይም አሁን
እየተጋፈጣችሁ ያሉአቸውን የትኞቹንም ፈተናዎች) ለመጋፈጥ እየተዘጋጃችሁ
ባላችሁበት ወቅት ለማበረታታት የተሰጠ የመጨረሻ ዘመን መልእክት ነው።
ዮሐንስ የራዕይን ትንቢታዊ መልእክት ይዞ በመጣው ሰማያዊ መልአክ
እንደተጎበኘ ወደተገለጸበት ዋሻ መግባት ብትችሉ ኖሮ ወዲያውኑ የራዕይ
መጽሐፍን አጠቃላይ ሀሳብ በማጠቃለያ መልክ የሚያቀርቡ የሚከተሉት ቃላት
በድንጋይ ወይም በሸክላ ላይ ተቀርጸው በዋሻው መግቢያ ላይ ተቀምጠው ማየት
ትችሉ ነበር፡- “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤
“የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤
ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ”
(ራዕይ 14:7)።
በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ማዕከላዊው ጉዳይ አምልኮ ነው። እኛ
የተፈጠርነው እንደሚያመልኩ ፍጡራን ነው። እያንዳንዳችን የሆነ ነገር ወይም
የሆነ ሰው እናመልካለን። እውነተኛው አምልኮ፣ ፈጣሪን ማምለክ፣ የሕይወትን
እውነተኛ ዓላማ እንድናገኝ ይረዳናል። ለመኖራችን ምክንያት ይሰጠናል። የሆነ
የምንሞትለትን ነገር ብቻ የሚሰጠን ሳይሆን ከዚህ ያለፈ የምንኖርለትን እና
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም መከራዎችን በትዕግስት የምንቀበልለትን ምክንያት
ይሰጠናል። በርግጥ የመጨረሻው አስጊ ሁኔታ ሲመጣ “ወደ እግዚአብሔር
ወደ እግዚአብሔር
መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል”
መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል” (የሐዋ 14:22)የሚሉትን
ቃላት በተሻለ ሁኔታ እንረዳለን።
እንደ ዮሐንስ ያሉ ታማኝ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ችግርና መከራ
ከደረሰባቸው እኛ ራሳችን መከራ እንደማይደርስብን እንድናስብ
የሚያደርገን ነገር ምንድር ነው?
የሚያደርገን ነገር ምንድር ነው? (1ኛ ጴጥ. 4:12–15)።
ራዕይ 14:7ን ያንብቡ። የመጀመሪያው መልአክ መልእክት የሚጠናቀቀው እንዴት ነው? ይህ የፍርድ ሰዓት መልእክት የሚያስተላልፈው የመጨረሻው ተማጽኖ ምንድር ነው? (ኢሳ. 40:26፣ ዮሐ. 1:1–3፣ እና ሮሜ 1:20ን ያንብቡ።)
ራዕይ 14፡17 ፈጣሪን እንድናመልክ ጥሪ በማስተላለፍ ያበቃል፤ አብዛኛው
የሳይንስና የክርስትና ዓለም መጽሐፍ ቅዱሳዊና ክርስቲያናዊ በሆነ ነገር እምብርት
ላይ ጥቃት የሚያደርሰውን ዝግመተ ለውጥን በተቀበሉበት በአሁኑ ወቅት ይህ
ጥሪ በተለየ ሁኔታ አስፈላጊ ነው። ዝግመተ ለውጥ እውነት ከሆነ እምነታችን
ውሸት ይሆናል ማለት ነው። ጉዳዩ አሳሳቢ የሚሆነው እስከዚህ ድረስ ነው።
ስለዚህ የራዕይ የመጨረሻው ጥሪ የተመሰረተው በመጽሐፍ ቅዱስ
የመጀመሪያ መጽሐፍ በሆነው ዘፍጥረት ላይ ነው። የፍጥረትን ወሳኝነት ካልተረዳን
በቀር በአምልኮ ላይ የሚደረገውን በዚህ ዓለም አቀፋዊ ጦርነት ውስጥ ያለውን
ጉዳይ በፍጹም ሙሉ በሙሉ መረዳት አንችልም። “በመጀመሪያ እግዚአብሔር
ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ. 1:1)። ይህ ጥቅስ የቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ
መሰረት ነው። “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ፈጠረ።” በዚህ ንባብ ውስጥ
“መፍጠር”ለሚለው ቃል የዕብራይስጡ አቻው ባራ ሲሆን ባለቤቱ እግዚአብሔር
ብቻ ሲሆን ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው።
የእግዚአብሔር ኃይል ውስን ስለአለመሆኑ ጥቂት ሀሳብ ለማግኘት
ከፍጥረቱ አንዱ የሆነውን ፀሐይን እንመልከት። ፀሐይ ከጊዜ ጅምር ጀምሮ ሰብአዊ
ዘር ዘይትን፣ ጋዝን፣ የድንጋይ ከሰልን ወይም እሳትን በመጠቀም ካመነጨው
ኃይል የበለጠ ኃይል በአንድ ሰከንድ ታመነጫለች።
የፀሐይ ስፋት በግምት 86,5000 ማይል ሲሆን መጠናቸው መሬትን
የሚያህሉ አንድ ሚሊዮን ፕላኔቶችን መያዝ ትችላለች። ነገር ግን ፀሐይ ሚልኪዌይ
በሚባለው በእኛ ጋላክሲ ውስጥ ካሉ ቢያንስ 100 ቢሊዮን ክዋክብቶች መካከል
አንዷ ነች። ፒስቶል የተባለ አንድ ኮከብ ፀሐይ የምትሰጠውን ኃይል 10 ሚሊዮን
ጊዜ የሚበልጥ ኃይል ይሰጣል። የእኛ ፀሐይ መጠን ያላቸው አንድ ሚሊዮን
ክዋክብት ፒስቶል በሚባለው ኮከብ ክበብ ላይ በቀላሉ ይገጥማሉ። በፍጥረት
ዙሪያ ያለውን ነገር መረዳት የምንችልበትን መንገድ ለማግኘት መጀመር እንኳን
የምንችለው እንዴት ነው?
ፍጥረት አስደናቂ ጉልበትና ያልተገደበ ኃይል ያለውን እግዚአብሔር
ይገልጣል። የእርሱ የመፍጠር ኃይል ሰማያትንና ምድርን ወደመኖር ያመጣ ብቻ
ሳይሆን በዘመናት ሁሉ ስለ ሕዝቡ ሲሰራ የነበረ ነው። እርሱ ይህን ዓለም የጀመረ፣
በዚህ ዓለም ላይ ሁልጊዜ የነበረ እና ሕዝቡን በዚህ ዓለም ላይ የማይተው አምላክ
ነው።
እኛ ከፍጥረት ጋር ስንነጻጸር እጅግ ትንሽ ብንሆንም የፍጥረቱ
ለመረዳት የሚከብድ መጠን (ግዝፈት) ክርስቶስ ለእኛ መሞቱን
ስለሚያሳይ የእግዚአብሔርን ፍቅር እርግጠኝነት የሚያጎላው
እንዴት ነው?
ፀሐይን፣ ጨረቃንና ክዋክብትን ወደመኖር ያመጣው የፍጥረት አምላክ፣ አስደናቂ ኃይሉ ይህቺን ምድር በመፍጠር ሕይወት ባላቸው ነገሮች የሞላት አምላክ፣ በእያንዳንዳችንም ላይ ፍላጎት ያለው አምላክ ነው። እርሱ ሕዝቡን ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጣ፣ በምድረ በዳ ሲቅበዘበዙ የመራቸው፣ ከሰማይ መና ያዘነበ፣ የኢያርኮን ግንብ ያፈራረሰና የእሥራኤላውያንን ጠላቶች ድል ያደረገ አምላክ ነው። ዩኒቨርስን ለመፍጠር ገደብ የለሽ ኃይሉን የተጠቀመው ያው አምላክ ነፍሶቻችንን ለመቆጣጠር ጦርነት የከፈቱብንን የክፉ ኃይላት ለማሸነፍም ኃይሉን ይጠቀማል። 2ኛ ቆሮ. 5:17፣ መዝ. 139:15–18 የሐዋ. 17:27 እና ቆላ. 1:17ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ቅርብነት ምን ያስተምሩናል?
እግዚአብሔር ከተለመደው አካላዊ ደረጃ ባሻገር የሚኖር ስለመሆኑ
የስነ-መለኮት ምሁራን ይናገራሉ። ይህ ሀሳብ እግዚአብሔር ከፍጥረት ሁሉ
በላይ እንደሚኖር ይገልጻል። ነገር ግን እግዚአብሔር በውስጣችን ስለመኖሩም
ይናገራሉ። ይህ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር በዓለማችን እንደሚኖር እና
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደሚያሳየው ከዓለማችን ጋር ውስብስብ በሆነ ሁኔታና
በቅርበት ተሳትፎ እንዳለው የሚያሳይ ሀሳብ ነው። ምንም እንኳን እግዚአብሔር
“ከፍ ባለና ቅዱስ ቦታ” ቢኖርም “የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር”
“የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር”
ይኖራል(ኢሳ. 57:15). ኢየሱስ ስለ ታማኝ ተከታዮቹ “እኛም አንድ እንደ ሆንን
አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን
እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ
ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል”
ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል” (ዮሐ.
17:23) ብሎ ከተናገረው ከዚህ የበለጠ የቀረበ መሆን አይችልም።
ስለ አምላካችን ያለው ታላቁ የምሥራች የእርሱ ታላቅነትና ኃይል እጅግ
ሰፊ ከመሆኑ የተነሣ ወደ ዩኒቨርስ በሙሉ እና ወደ እያንዳንዳችን ሕይወት
መድረስ መቻሉ ነው። እኛን እንደገና ሊሰራን፣ ሊቀርጸን፣ በራሱ አምሳል እርሱን
እንድንመስል ሊለውጠን ቃል ገብቶልናል። ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ
አስቡ። በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ጋላክሲዎችን የፈጠረና ደግፎ የሚያኖር አምላክ
“በእርሱ ሕያዋን ሆነን የምንንቀሳቀስና የምንኖር”
“በእርሱ ሕያዋን ሆነን የምንንቀሳቀስና የምንኖር” ብቻ ሳይሆን (የሐዋ. 17:28)፣
አዲስ ልብ ሊሰጠን፣ ከኃጢአታችን ሊያነጻን እና በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት
ሊያደርገን በልባችን ውስጥ የሚሰራ አምላክም ነው። እንደዚህ ያለ ኃይል ያለው፣
የሚወደንና የሚጠነቀቅልን አምላክ መኖሩን መገንዘብ እንዴት ያለ የሚያጽናና
ሀሳብ ነው።
እግዚአብሔር በውስጣችን መኖሩን ከማስተዋላችን የተነሣ ተስፋና
መጽናናትን ማግኘትን መማር የምንችለው እንዴት ነው? ወይም
እግዚአብሔር ድብቅ ምስጢሮችዎን ማወቁ ያስፈራዎታል? በዚህ
አውድ ወንጌል እንዴት ሰላም ሊሰጥዎ ይችላል?
የመጀመሪያ መልአክ መልእክትን ተመልከቱ። የዘላለም ወንጌል።
የፍርድ ሰዓት። ለፈጣሪ መስገድ። እነዚህ ሀሳቦች ምን ያህል የተገናኙ እንደሆኑ
ተመልከቱ። በፍርድ ሰዓት በፈጣሪያችን ፊት ስንቆም ተስፋ የሚሰጠን ወንጌል
ብቻ ነው። “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት፣ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ
“እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት፣ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ
ሥጋ ፈቃድ ለማይመላለሱ አሁን ኵነኔ የለባቸውም”
ሥጋ ፈቃድ ለማይመላለሱ አሁን ኵነኔ የለባቸውም” (ሮሜ 8:1)። አሁንም ሆነ
በፍርድ ሰዓት ኩነኔ የለባቸውም።
ዝግመተ ለውጥ “የክርስትና” ልብስ ለብሶ የክርስትና እምነትን ጠቅላላ
መሰረት ለመናድ አደጋ ደቅኖ ባለበት ወቅት የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት
የሚገልጸው መልእክት ለወቅቱ እምነት ማዕከላዊ መልእክት ነው።
ሆኖም በዝግመተ ለውጥ አስተሳሰብ ኃይለኛ ጥቃት መካከል እግዚአብሔር
ቤተ ክርስቲያንን፣ ስማቸው ራሱ የዝግመተ ለውጥን ሀሳብ የሚቃወሙ
ለመሆናቸው ምስክር የሆነ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ፈጣሪያችንና አዳኛችን መሆኑን
የሚገልጸውን መሰረታዊ እውነት የሚያውጅ ሕዝብ አስነስቷል።
ኤፌ. 3:9፣ ቆላ. 1:13–17፣ ራዕይ 4:11፣ እና ሮሜ 5:17–19ን
ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ ፈጣሪና አዳኝ ስለመሆኑ ምን
ያስተምሩናል?
የኢየሱስ ፈጣሪነት ከኢየሱስ አዳኝነት ጋር እንዴት በቅርበት የተገናኘ
እንደሆነ ይመልከቱ። የፈጣሪነቱ ሚና በቀነሰበት ቅጽበት የአዳኝነት ሚናውም
በጥያቄ ውስጥ ይገባል። ኢየሱስ የመጣው እኛን ከኃጢአት፣ ከሞት፣ ከስቃይና
ከአመጽ ሊያድነን ነው። ኢየሱስ ሊያድነን የመጣው ኃጢአት፣ ሞት፣ ስቃይና
ዓመጽ የፍጥረት የራሱ ዋና መንገድ ነው ተብሎ በሚስተማርበት ሰዓት ነው።
ለመጀመር ያህል፣ እግዚአብሔር እኛን ለመፍጠር የተጠቀመበትን ያንኑ ሂደት
ነው ሊያድነንም የሚጠቀመው? ይህ አደገኛ ውሸት ነው።
ነገሩን የከፋ የሚያደርገው ዝግመተ ለውጥ ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞቱ
ላይ መቀለዱ ነው። ለምን? ጳውሎስ ኃጢአት በአዳም ምክንያት መግባቱን
ከኢየሱስ ሞት ጋር በማይነጣጠል ሁኔታ ያገናኛል (ሮሜ 5፡17-19ን ይመልከቱ)።
ስለዚህ በአዳምና በኢየሱስ መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት አለ። ነገር ግን በማንኛውም
የዝግመተ ለውጥ ሞዴል ሞት-የሚሊዮኖች ዓመታት ሞት-አዳምን ለመፍጠር
አስፈላጊ የነበሩ ኃይሎች ናቸው ተብሎ ስለሚወሰድ ማንኛውም ኃጢአት የለሽ
አዳም ሞትን ሊያመጣ አይችልም ማለት ነው።
ስለዚህ ከጅምሩ ጀምሮ ዝግመተ ለውጥ የመስቀልን መጽሐፍ ቅዱሳዊ
መሰረት የሚያፈርስ ነበር። ከዚህ በተቃራኒ፣ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች፣ ዓለም
ፈጣሪን እንዲያመልክ ጥሪ በማስተላለፍ ይህን ስህተት የሚቃወሙ ሕያው
ምስክሮች ሆነው ቆመዋል።
እግዚአብሔር ፈጣሪያችን በመሆኑ አብዝተን መደነቅ ወይም ማምለክ
ብንችልም ከዚህ የበለጠ ነገር አለ። አስቀድመን እንደተመለከትነው፣ ነገር ግን
አሁንም በድጋሚ መመልከት የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ፈጣሪያችን አዳኛችንም
መሆኑ ነው። የፈጠረን አምላክ ያዳነንም አምላክ ነው። “ሰውን በመልካችን እንደ
“ሰውን በመልካችን እንደ
ምሳሌአችን እንፍጠር”
ምሳሌአችን እንፍጠር” (ዘፍ. 1:26) ያለው ያው አምላክ በመስቀል ላይ “ኤሎሄ
ኤሎሄ
ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?”
ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ የጮኸ ሲሆን ትርጓሜውም “አምላኬ አምላኬ፥ ስለ
“አምላኬ አምላኬ፥ ስለ
ምን ተውኸኝ?”
ምን ተውኸኝ?” (ማቴ. 27:46) ማለት ነው። እግዚአብሔርን ስለምንፈራበት
ምክንያት ወይም ከዚህም በላይ ለእርሱ ክብር ስለምንሰጥበትና ስለምናመልክበት
ምክንያት አውሩ!
የወደቅን ሰብአዊ ፍጡራን እንደመሆናችን እንደዚህ ላለው አስደናቂ
እውነት በበቂ ሁኔታ ምላሽ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው? በምላሹ ምን
ማድረግ እንችላለን? ምን ማድረግ እንዳለብን በመጀመሪያው መልአክ መልእክት
ተነግሮናል፡- “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤
“የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤
ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት”
ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት” (ራዕይ
14:7)።
ዮሐንስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለደረሰበት ነገር የጸፈውን ታሪክ
በዮሐንስ ወንጌል 19፡16-30 ላይ ያንብቡ። እያነበቡ ሳለ ስለ ኢየሱስ
ፈጣሪነት፣ በእርሱ “የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ
ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና
በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ መፈጠራቸውንና ከፍጥረት ሁሉ በፊት
በኵር መሆኑን፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ መፈጠራቸውን” (ቆላ.
1:16) ስለተመለከትንባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያስቡ። ለዚህ
አስደናቂ የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫ መልስ የምሰጠው እንዴት
ነው?
ፈጣሪን ለማምለክ የቀረበው የመጀመሪያው መልአክ መልእክት የመጣው
ከመስቀል በኋላ፣ እየተመለከተ ለነበረው ዩኒቨርስ እና ለክርስቶስ ተከታዮች
“ሰማይንና ምድርን ባህርንም የውኃንም ምንጮች የፈጠረ” እርሱ አምላክ ቢሆንም
እንኳን “ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ በማድረግ፥
በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን በማዋረድ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል
ሞት እንኳ የታዘዘ” (ፊልጵ. 2:7፣ 8) መሆኑ እንዲታወቅ ከተደረገ በኋላ ነበር።
ኢየሱስ እንደ ሰብአዊ ፍጡር ሆኖ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት
እርሱን ለሚያውቁት ይህ ምንኛ አስደናቂ ዕይታ ይሆን። ሰማያዊ ፍጡራንም
የሚያመልኩት መሆኑ አያስደንቅም። እኛ በደሙ ስለተዋጀን ፈጣሪያችንን እና
አዳኛችንን ከማምለክ ሌላ ምን ማድረግ እንችላለን?
በመስቀል ብርሃን ስንመለከት፣ የወደቁ ሰብአዊ ፍጡራን ክርስቶስ
በመስቀል ላይ ባደረገላቸው ነገር ላይ የሆነ ነገር መጨመር
እንደሚችሉ የሚገልጸው ሀሳብ የክህደት ሀሳብ የሚሆነው ለምንድር
ነው? ፈጣሪያችን አስቀድሞ ባደረገልን ነገር ላይ የትኛው ስራችን
ነው ተጨማሪ መሆን የሚችለው?
እግዚአብሔርን ማምለክ በቅዱሳት መጻሕፍት
ውስጥ ማዕከላዊ ነገር ስለሆነ በሰዎችና በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ሁልጊዜ
የክርክር ርዕስ ነው። በመላው ብሉይ ኪዳን ውስጥ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሌሎች
አማልክትን ስላመለኩ ወይም የአህዛብን ዓለም የአምልኮ ልምምዶችን በመጠቀም
እግዚአብሔርን ስላመለኩ ነቢያት የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሲገስጹ ነበር።
እግዚአብሔርን በማምለክ ወይም ሌሎች አማልክትን በማምለክ መካከል ያለው
ግጭት በዩኒቨርስ ውስጥ ያለው ጦርነት እምብርት ሲሆን የእግዚአብሔርን ሕግ
ባለመቀበል የታጀበ ነው።
“አምልኮ ሰብአዊ ዘር እንደ ሕያው ፍጡራን በፈጣሪ ሀልዎት ውስጥ
ሲሆኑ ማድረግ ስላለባቸው ነገር የሚገልጽ ሲሆን የሰብአዊ ዘርን የመኖር እጅግ
መሰረታዊ ገጽታ የሚገልጽ ነው። እግዚአብሔርን ማምለክ የሚችሉት ሕያዋን ብቻ
ናቸው፤ ሙታን ሊያመሰግኑትና ሊያመልኩት አይችሉም።….የፈጠረን አምላክ
በአምልኮ ተግባር ራሳችንን ለእርሱ አሳልፈን እንድንሰጥ ይጋብዘናል፤ በምላሹ
ሕይወታችን ለሌሎች ጥቅም እንዲውል በልጽጎ ከእርሱ መልሰን እንቀበላለን።
አምልኮ ከተፈጥሮአችንና ከመኖር ዓላማችን ጋር የተገናኘ ሲሆን ከራስ ወዳድነት
ነጻ ሊያደርገን የሚችል ከእኛ ውጭ የሆነ ማዕከል እንደሚያስፈልግ የሚያሳይ
ነው። እግዚአብሔርን አለማምለክ ማለት የመኖራችንን ምክንያት ማጣት ማለት
ነው፤ ይህ ማለት አቅጣጫ በሳተ ሁኔታ መኖርና መሞት፣ ከሕይወት ምንጭ
ከሆነው ከመለየታችን የተነሣ ወደ ፍጹም ጥፋት ማምራት ማለት ነው።”—Án-
gel Manuel Rodríguez,“The Closing of the Cosmic Conflict: Role of
the Three Angels’ Messages,” p. 42.
1.በወደቀ ዓለም ውስጥ በእግዚአብሔር መፈጠር ብቻውን በቂ
የማይሆነው ለምንድር ነው? በሚለው ሀሳብ ላይ ጊዜ ውሰዱ።
የድነት ተስፋ የሚያስፈልገን ለምንድር ነው?
2. በሕይወትዎ በማያሻማ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ሥራ ኃይል
ስለተመለከቱበት የሆነ ልምምድ ያስቡ፤ የእግዚአብሔርን ፍቅር
በግልዎ ያሳየዎትን ልምምድ ማለት ነው። ከዚያም ይህ አምላክ
መላውን ዩኒቨርስ የፈጠረ አምላክ መሆኑን ልብ ይበሉ! ይህ አምላክ
ለእርስዎ ሕይወት ግድ ስለሚለው ይወድዎታል። ይህ እውነታ
የሚያጽናና ብቻ ሳይሆን ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ (ትሁት
እንድንሆን) ለምን አያደርገንም?
3. ዝግመተ ለውጥ እውነት ቢሆን ኖሮ ስለ እኛ አፈጣጠር
በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ የተለየ ታሪክ እየሰጠን በሌላ በኩል
ደግሞ እኛን ለመፍጠር በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የሞት፣ የአመጽ፣
የጥፋት፣ የስቃይና የጅምላ እልቂት ዓመታትን የተጠቀመን አምላክ
እንድናመልክ እንዴት እንደምንጠራ ያስቡ። እንዲህም ሆኖ እርሱን
ማምለክ ይጠበቅብናል ማለት ነው? ለምንድር ነው የምናመልከው?
እዚህ እንዴት እንደተገኘን ለብዙ ሺህ አመታት ስለዋሸን?