የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡-ዳን. 8፣ ዳን. 9፣ እዝራ 7፣ ማቴ. 3:13–17፣ ሮሜ 5:6–9፣ ማር. 15:38፣ ዘሌ. 16:16።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና። ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ”። (ሮሜ 13:11፣ 12)
ከብዙ ዓመታት በፊት ናሽናል ጂኦግራፊክ የሚባል መጽሔት በአሜሪካ
አገር የሎው ስቶን በሚባል ብሄራዊ ፓርክ ስለተከሰተ የሰደድ እሳት
ተናግሮ ነበር። እሳቱ ከጠፋ በኋላ ደን ጠባቂዎች የጉዳቱን መጠን
ለማጥናት ተራራው ላይ ወጡ። ከደን ጠባቂዎቹ አንዱ አንዲት የተቃጠለች ወፍ
ከዛፍ ሥር አገኘ። ይህን የሚያም እንግዳ ክስተት ከተመለከተ በኋላ ወፏን በበትር
ገፋ አደረጋት።
ሲገፋት ከሞተችው እናታቸው ክንፎች ሥር ሶስት ጫጩቶች ግራ
ተጋብተው ተንቀሳቀሱ። አፍቃሪዋ እናት የማይቀረውን አደጋ ስለተገነዘበች
ጫጩቶቿን ወደ ዛፉ ሥር በመውሰድ በክንፎቿ ሥር ሰብስባ ነበር። ከእሳቱ በርራ
ማምለጥ ስትችል ጫጩቶቿን ትታ ለማምለጥ አልፈለገችም። ከአደጋ በክርስቶስ
ላመለጠ አማኝ እንዴት ያለ አስደናቂ ስዕል ነው!
የእግዚአብሔር ፍርድ እሳት በቀራኒዮ ላይ በእርሱ ላይ በመንደዱ
በክርስቶስ የሆኑ ሁሉ በእርሱ ክንፎች ሥር ለዘላለም ከአደጋ አምልጠዋል። እኛ
የሰማይ መንግሥት ጻድቃን ዜጎች እንድንሆን እንዲፈረድልን ክርስቶስ በመስቀል
ላይ እንደተኮነነ ኃጢአተኛ ተፈረደበት። የዘላለም ጥፋት ከሚያስከትል አጥፊ
እሳት በምሳሌም ሆነ በገሃድ ነጻ እንድንወጣ እርሱ እንደ ወንጀለኛ ተፈረደበት።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሚያዝያ 28 ሰንበት ለመዘጋጀት አጥኑ።
አስቀድመን እንደተመለከትነው ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ፍርድ መኖር አለበት። መልአኩ ከፍ ባለ ድምጽ “የፍርዱ ሰዓት መጥቶአልና” (ራዕይ 14:7) በማለት ያውጃል። የዳንኤል መጽሐፍ ይህ ፍርድ የሚጀምርበትን ጊዜ ይሰጠናል። ዳን. 8:14ን ያንብቡ። ዳንኤል ስለ ቤተ መቅደሱ መንጻት የሚሰጠን የጊዜ ሰሌዳ ምንድር ነው?
እያንዳንዱ አይሁዳዊ የምድራዊውን ቤተ መቅደስ መንጻት ትርጉም በግልጽ ይረዳል። ይህ የሚሆነው የፍርድ ቀን በሆነው የስርየት ቀን ነበር። ዳንኤል የቤተ መቅደስ መንጻትንና የፍርድ ጽንሰ ሀሳብን የሚረዳ ቢሆንም ስለ 2300 ቀናት ግራ ተጋብቶ ነበር። ዳን. 8:27 እና ዳን. 9:21፣ 22ን ያንብቡ። ስለ 2300 ቀናት የዳንኤል ምላሽ ምን ነበር? እግዚአብሔር ለእርሱ የሰጠው ምላሽስ ምን ነበር?
በዳንኤል 8 መጨረሻ ላይ ዳንኤል ከራዕዩ የተነሣ ታሞ የተኘ ሲሆን
እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡- “ስለ ራእዩም እደነቅ ነበር፥ የሚያስተውለው
“ስለ ራእዩም እደነቅ ነበር፥ የሚያስተውለው
ግን አልነበረም”
ግን አልነበረም” (ዳን. 8:27)። ይህ ማለት ስለ 2300 ቀናት የሚናገረው ራዕይ
ማለት ነው (ሌላው ራዕይ ተብራርቷል፤ ዳንኤል 8፡19-22ን ይመልከቱ)። ቀጣዩ
ምዕራፍ፣ ዳንኤል 9፣ መልአኩ ገብርኤል ስለ 2300 ቀናት ትንቢት ለዳንኤል
ለማብራራት መምጣቱን መዝግቦአል። “ ‘ዳንኤል ሆይ፥ ጥበብንና ማስተዋልን
“ ‘ዳንኤል ሆይ፥ ጥበብንና ማስተዋልን
እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ”
እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ” (ዳን. 9:22)።
ገብርኤል ለዳንኤል ጸሎት እርሱ ካሰበው በላይ እጅግ ሰፋ ያለ
መልስ በመስጠት አስደመመው። መልአኩ ገብርኤል ዳንኤልን በጊዜ ጅረት
ውስጥ በመውሰድ በዳንኤል 8 ላይ ከተጠቀሰው የቤተ መቅደስ መንጻት ጋር
በቀጥታ ስለተገናኙ ክስተቶች፣ ማለትም ስለ መሲሁ መምጣት፣ አገልግሎቱን
ስለሚጀምርበት ጊዜና ስለሚደርስበት የጭካኔ ሞት ትክክለኛውን ጊዜ ገለጠለት።
በሌላ አገላለጽ፣ የክርስቶስ ሞትና ፍርድ ሊነጣጠሉ በማይችሉበት ሁኔታ የተገናኙ
ናቸው።
በዳንኤል 9፡24-27 ላይ በተገለጸው መሰረት፣ የኢየሱስ ሞት፣
በዳንኤል 8፡14 ላይ ከተገለጸው ፍርድ ጋር በቀጥታ መገናኘቱ ወሳኝ
የሚሆነው ለምንድር ነው? በዚህ ግንኙነት አማካይነት የተሰጠው
ታላቅ እውነት ምንድር ነው?
ዳኔኤል 8:17፣ 19፣ 26ን ያንብቡ። የዳንኤል 8 እና የ2300 ቀናት ራዕይ ምንን የሚመለከቱ እንደሆኑ በተመለከተ መልአኩ ምን የጊዜ ቀመርን ነው ያወጀው? ይህን ማስተዋል ለምን ያስፈልጋል?
አንዳንድ ሰዎች 2300 ቀናት እውን ቀናት ናቸው ብለው ይከራከራሉ።
ምንም እንኳን 2300 ቀናት ከጊዜው ማዕቀፍ ጋር ባይገጥምም፣ በዳንኤል 8 ላይ
የተጠቀሰው ትንሹ ቀንድ የሚወክለው ኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ያደረሰውንና
የአይሁዶችን ቤተ መቅደስ ያረከሰውን አንቲዎካስ ኤፒፋኔስ (216 ዓዐ.-164 ዓ.ም)
የተባለ አለማዊ ወታደራዊ መሪ እንደሚወክል ያምናሉ። ነገር ግን ይህ ትርጉም
ራዕዩ “ለፍጻሜ ዘመን” የሚሆን እንደሆነ የተነገረው ግልጽ መመሪያ ተቃራኒ ነው።
በእርግጠኝነት አንቲዎካስ በፍጻሜ ዘመን አልኖረም።
በዳንኤል 8 ላይ ገብርኤል የ2300 ቀናትን ትንቢት ማብራሪያ መስጠት
ይጀምራል። አውራ በጉ ሜዶንና ፋርስን እንደሚወክልና አውራ ፍየሉ
ደግሞ ግሪክን እንደሚወክል ገለጸ(ዳን. 8:20, 21)። አስቀድመው ስማቸው
እንደተጠቀሱት ስም ባይሰጠውም ቀጣዩ አካል፣ ትንሹ ቀንድ፣ በግልጽ ሮም ነው
(ዳን. 8:9፣ 23፣ 24)። እርሱ “እውነትን ወደ ምድር የጣለውን” (ዳን. 8:10–12፣
25) ኃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ገጽታ የያዘውን የሮምን ክፍልና በክርስቶስ ሰማያዊ
አገልግሎት ላይ ያሳየውን ጣልቃ ገብነት ያሳያል (ዳን. 8:10–12)።
በእግዚአብሔር ትንቢታዊ የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ያሉትን ዝርዝሮች
ለማብራራት ገብርኤል ዝግጁ ነው። በዳንኤል ምዕራፍ 8 መጨረሻ ላይ ስለ 2300
ቀናት የተሰጠውን ራዕይ በከፊል እንዳላስተዋለው በግልጽ ማየት እንችላለን(ዳን.
8:27)። ስለ አውራ በጉ፣ ስለ አውራ ፍየሉና ስለ ትንሹ ቀንድ የተነገረው ቀደምት
ክፍል በደንብ የተብራራ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ኃይሎች በስም ተለይተው
ታውቀዋል (ዳን. 8:20፣ 21)። ነገር ግን የቤተ መቅደሱ መንጻት አልተብራራም
ነበር።
በዳንኤል 8 ላይ የተገለጠው መልአኩ ገብርኤል አሁንም በዳንኤል 9 ላይ
ተገልጦ እንዲህ ይላል፡- “አንተ እጅግ የተወደድህ ነህና በልመናህ መጀመሪያ ላይ
“አንተ እጅግ የተወደድህ ነህና በልመናህ መጀመሪያ ላይ
ትእዛዝ ወጥቶአል፥ እኔም እነግርህ ዘንድ መጥቻለሁ፤ አሁንም ነገሩን መርምር፥
ራእዩንም አስተውል”
ራእዩንም አስተውል”(ዳን. 9:23)። የትኛውን ራዕይ? ነገ እንደምንመለከተው፣
በዳንኤል ምዕራፍ 8 ላይ የተጠቀሰው ራዕይ ብቸኛው አካል የሆነውና ለዳንኤል
ገና ማብራሪያ ያልተሰጠው ክፍል፣ የ2300 ቀናት ራዕይ ነው።
ገብርኤል ዳንኤልን “እጅግ የተወደድክ” ሰው ብሎ ጠርቶታል።
ይህ በሰማይና በምድር መካከል ስላለው የቅርብ ግንኙነት ምን
ይነግረናል?
ዳን. 9:23ን ያንብቡ። መልአኩ ለዳንኤል ምን የተለየ መመሪያ ሰጠው? ይህ በዳንኤል 8፡14 ላይ የተጠቀሰውን የቤተ መቅደስ መንጻት ትርጉም ለመረዳት ወሳኝ የሚሆነው ለምንድር ነው? ዳን 8፡14።
መልአኩ ለዳንኤል “ነገሩን መርምር፥ ራእዩንም አስተውል “ነገሩን መርምር፥ ራእዩንም አስተውል” (ዳን. 9:23) በማለት ግልጽ መመሪያ ሰጥቶታል። የቱን ነገርና የትኛውን ራዕይ? በዳንኤል 9 ውስጥ ተመዝግቦ ያለ ራዕይ ስለሌለ ነቢዩ እየተናገረ ያለው በዳንኤል 8 ላይ ስለተገለጸውና ነቢዩ ስላላስተዋለው ስለ 2300 ቀናት ራዕይ ክፍል መሆን አለበት(ዳን. 8:27)። በዳንኤል 9፡24-27 ላይ ገብርኤል ይቀጥላል። በኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ ስለተገለጡት ምን ክስተቶች ነው እየተናገረ ያለው?
የዚህ ትንቢት የመጀመሪያው ክፍል የእግዚአብሔር ሕዝብ ከሆኑት
አይሁዶች ጋር የተገናኘ ነው። በአይሁድ ሕዝብ ላይ፣ “በሕዝብህ ላይ ሰባ
በሕዝብህ ላይ ሰባ
ሱባዔ ተቀጥሮአል”
ሱባዔ ተቀጥሮአል” (ዳን. 9:24፣)። በመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት መሠረት አንድ
ትንቢታዊ ቀን አንድ እውን ትንቢታዊ ዓመትን ይወክላል(ሕዝ. 4:6፣ ዘሁ.
14:34)። በዳንኤልና በራዕይ መጻሕፍት ውስጥ ምሳሌያዊ መግለጫዎች ሲኖሩ
ምሳሌያዊ የጊዜ ትንቢቶችም ይኖራሉ። በዚህ ቦታ የቀን ለዓመት ትንቢታዊ መርህ
መተግበሩን እርግጠኛ ከምንሆንባቸው መንገዶች አንዱ በዳንኤል ትንቢት ውስጥ
ስንጠቀምበት በጊዜ መስመር ላይ ያለው እያንዳንዱ ክስተት ፍጹም ገጣሚ ሆኖ
እናገኛለን (የነገውን ትምህርት ይመልከቱ)። ይህን መርህ ሥራ ላይ ካዋልን 70
ሳምንታት 490 ቀናትን ይይዛሉ። አንድ ትንቢታዊ ቀን ከአንድ እውን አመት ጋር
እኩል ስለሆነ 490 ቀናት 490 ዓመታት ይሆናሉ።
ገብርኤል 490 ዓመታት “ተቆርጠዋል” ያለ ሲሆን ተቆርጧል የሚለው
ቃል የዕብራውያኑ ቻታክ ቃል በቃል ትርጉም ሲሆን አንዳንድ ጊዜ “ተቆርጦአል”
ተብሎ ተተርጉሟል። ከምንድር ነው የተቆረጠው? በዚህ ቦታ ከተጠቀሰው
ብቸኛው ሌላ የጊዜ ትንቢት፣ በዳንኤል 8፡14 ላይ ከተጠቀሰው 2300 ቀናት ላይ
ነው። እነዚህ 490 ዓመታት በዳንኤል 8፡14 ላይ ከተሰጡት ትንቢቶች መካከል
ሳይብራራ ከቀረው ብቸኛው የጊዜ ትንቢት ጋር በቀጥታ የተገናኙ ናቸው።
ስለዚህ በዚህ ትንቢት ላይ ገብርኤል ዳንኤል አስቀድሞ በነበረው ምዕራፍ
ሳያስተውል የቀረውን ነገር፣ 2300 ቀናትን እንዲረዳ ለመርዳት እየመጣ መሆኑን
ማየት እንችላለን።
ገብርኤል የ490 ዓመታትን ትንቢት የጀመረው ለዳንኤልና ለአይሁድ
ሕዝብ እጅግ ወሳኝ በሆነውና ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመገንባት በተሰጠው
አዋጅ ነው። ኢየሩሳሌምን በተመለከተ የተለያዩ አዋጆች የተላለፉ ቢሆንም በዕዝራ
7 ላይ በ457 ዓ.ዓ ላይ የተላለፈው አዋጅ አይሁዶች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ
ብቻ የፈቀደ ሳይሆን ራሳቸውን እንደ ኃይማኖታዊ ማህበረሰብ እንዲመሰርቱም
የፈቀደ ነበር (እዝራ 7፡13፣ 27ን ይመልከቱ)።
የአርጤክሰስ አዋጅ የተላለፈው በመከር ወቅት በ457 ዓ.ዓ እንደሆነ ልብ
ማለት አስፈላጊ ነው። እንደ ዳንኤል ገለጻ ከሆነ በ457 ዓ.ዓ ላይ ከተላለፈው አዋጅ
ጀምሮ እስከ መሲሁ ድረስ 69 ሳምንታት ወይም 483 ዓመታት ይሆናል። በ457
ዓ.ዓ ላይ ጀምረን በታሪክ ፍሰት ወደ ፊት ብንንቀሳቀስ ወደ 27 ዓ.ም እንደርሳለን።
መሲህ የሚለው ቃል ትርጉሙ “የተቀባ” ማለት ነው። በ27 ዓ.ም ኢየሱስ
ክርስቶስ፣ መሲሁ ተጠምቋል (ማቴ. 3፡13-17ን ይመልከቱ)። ዳንኤል ከብዙ መቶ
ዓመታት በፊት ክርስቶስ የሚጠመቅበትን ትክክለኛውን ዓመት፣ ኢየሱስ የሶስት
ዓመት አገልግሎቱን የሚጀምርበትን ጊዜ ተንብዮ ነበር።
ሮሜ 5:6–9ን ከዳንኤል 9:26 ጋር ጎን ለጎን ያንብቡ። በዚህ ቦታ
የተገለጹት ታላላቅ እውነቶች ምንድር ናቸው?
ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ ግን ለራሱ አይደለም”
ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ ግን ለራሱ አይደለም”
(ዳን. 9:26)። መሲህ “ይገደላል” ወይም ይሰቀላል። ጥቅሱ አክሎ “ግን ለራሱ
አይደለም” ይላል። በሌላ አገላለጽ የክርስቶስ በቀራኒዮ መስቀል መሞት ለራሱ
ሳይሆን ለእኛ ነው። ከዚህ የተነሣ ጳውሎስ እንዲህ በማለት ጽፏል፡- “ነገር ግን
ነገር ግን
ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን
የራሱን ፍቅር ያስረዳል”
የራሱን ፍቅር ያስረዳል” (ሮሜ. 5:8)።
በዳንኤል 9፡27 ላይ በሳምንቱ አጋማሽ፣ በመጨረሻዎቹ ሰባት ዓመታት
ላይ፣ ክርስቶስ “መስዋዕትንና ስጦታን ያስቀራል።” በዚህ ሰባኛው ሳምንት
አጋማሽ ላይ፣ 31 ዓ.ም ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞት በደሙ የዘላለም ኪዳን
ያጸና ሲሆን የመስዋዕት ሥርዓቱ ያለውን ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ትንቢታዊ
ወሳኝነት አጣ። እነዚህ ትንቢቶች መሲሁ ክርስቶስ በመሰቀል የመስዋዕት ሥርዓቱ
ትንቢታዊ ጠቀሜታውን በጸደይ ወር 31 ዓ.ም እንዲያጣ እንደሚያደርግ የሚገልጹ
ናቸው። እነዚህ ትንቢቶች በሙሉ በዝርዝር ተፈጻሚ ሆነዋል። በፋሲካ ጊዜ ሊቀ
ካህኑ የፋሲካውን በግ እያቀረበ ሳለ ክርስቶስ ለእኛ መስዋዕት ሆኗል።
ከላይ የተጻፈውን ነገር በአእምሮዎ ይዘው ማር. 15 38 እና ማቴ 3፡
15፣ 16ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች የዳንኤል 9፡ 24-27 ትንቢቶችን
እንድናስተውል የሚረዱት እንዴት ነው?
ከ2300 ዓመታት ትንቢት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ 490 ዓመታት ለጥንቱ
የአይሁድ ሕዝብ እና ለመሲሁ መምጣት የተሰጠ ጊዜ ነበር። የ2300 ዓመታት
የመጨረሻው ክፍል ከሰማያዊ ቤተ መቅደስ መንጻትና በመጨረሻም ከክርስቶስ
ዳግም ምጻት ጎን ለጎን አይሁድንና አህዛብን ጨምሮ የእግዚአብሔርን ሕዝብ
የሚመለከት ነው።
የመጀመሪያዎቹ 490 ዓመታት የሚመለከቱት የመጀመሪያውን የመሲህ
መምጣት ሲሆን በ34 ዓ.ም ከፍጻሜ ላይ ደርሷል። ከ2300 ዓመታት 490
ሲቀነስ 1810 ዓመታት ይቀራሉ። እነዚህ ቀጥለው ያሉት 1810 የሚመለከቱት
የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነው። በ34 ዓ.ም ከጀመርንና 1810 ዓመታትን ከደመርን
ወደ 1844 ዓ.ም እንደርሳለን።
በማንጻት ወይም ስለ ቤተ መቅደሱና በሰማይ ስለሚካሄደው የመጨረሻው
ዘመን ፍርድ እውነቱን በመመለስ ብርሃን ሰዎች ሁሉ ለፍቅሩ ምላሽ እንዲሰጡና
ጸጋውን በመቀበል እግዚአብሔርን የመምሰልና የመታዘዝ ኑሮ እንዲኖሩ
እግዚአብሔር ለሰብአዊ ዘር በሙሉ የመጨረሻውን ተማጽኖ ያቀርባል።
ዘሌ. 16:16ን ያንብቡ። ቤተ መቅደሱ የሚነጻበት ምክንያት ምን
ነበር? ይህ ስለ ወንጌል ምን ያስተምረናል?
ከሕዝቡ ኃጢአትና በደል የተነሣ ቤተ መቅደሱ መንጻት የነበረበት ሲሆን ይህ ይደረግ የነበረው በእንስሳት ደም ብቻ ነበር። እኛንም በተመለከተ የሚሆነው ተመሳሳይ ነገር ነው። እኛም በፍርድ ነጻ እንድንወጣ የሚያደርገንን ብቸኛ መንገድ ለማዘጋጀት በስርየት ቀን በሚታረዱ እንስሳት የተመሰለ አዳኝ ያስፈልገናል። ዘሌ. 23:26–29ን ያንብቡ። እግዚአብሔር በስርየት ቀን ሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ አዘዛቸው? ይህ ዛሬ ለእኛ ምን ማለት ነው?
እሥራኤላውያን “ነፍሳቸውን ማስጨነቅ” ነበረባቸው። ይህ አባባል
የሚያመለክተው ራሳቸውን ዝቅ ማድረግና ልቦቻቸውን መመርመር፣
ኃጢአቶቻቸውን መናዘዝ፣ ንስሃ መግባት እና ሊቀ ካህኑ ምድራዊውን ቤተ
መቅደስ እንደሚያነጻ ሁሉ እግዚአብሔርም እነርሱን እንዲያነጻ መጠየቅ
እንዳለባቸው ነው።
ዳንኤል ምዕራፍ 7-9 እና ራዕይ 14 ላይ ያሉ ትንቢታዊ ምዕራፎች
በተለየ ሁኔታ የሚያተኩሩት ለፍርዱ ሰዓት ለመዘጋጀት በቀረቡ
አስቸኳይ ተማጽኖዎች ላይ ነው። ከ1844 ጀምሮ እየኖርን
ያለነው በፍርዱ ሰዓት ስለሆነ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የቀረበው
የመጀመሪያው መልአክ መልእክት “የፍርዱ ሰዓት ደርሷልና” (ራዕይ
14:7) በማለት ያውጃል። ታዲያ ዛሬ “ነፍሶቻችንን የምናስጨንቀው”
እንዴት ነው?
በዳንኤል 9፡24-27 ያሉትን 70 ሳምንታት ለመመልከት
ፈጣንና ቀላል መንገድ የሚከተለው ነው።
መጀመሪያ፣ ሰባ ሱባኤ (ሰባ ሳምንት) (ዳን. 9:24).
ቀጥሎ፣ የ70 ሳምንቱ ሰባት ሳምንትና 62 ሳምንት ወይም 69 ሳምንት (ዳን.
9:25)።
የመጨረሻው ሳምንት፣ ሰባኛው ሳምንት (ዳን. 9:27).
በመጨረሻም፣ የመጨረሻው ሳምንት —“በሳምንቱ አጋማሽ” (ዳን. 9:27)በመባል
በሶስት ዓመት ከግማሽ አከፋፈል በሁለት ተከፍሏል።
ይህ ነው። 70 ሳምንት የተሰራው ከ69 ሳምንትና ከአንድ ሳምንት ነው።
አንዱ ሳምንት ደግሞ ለሁለት ተከፍሏል። 457 አመተ ዓለምን እንደ መነሻ ከያዝን
በቀላል ስሌት ወደ 1844 ዓ.ም እንደርሳለን።
ዳንኤል 8 ስለ 2300 ቀናት ሲናገር 2300 ቀናት መቼ እንደሚጀምሩ
በፍጹም አልተናገረም። “እርሱም፦ እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ማታና ጥዋት
ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ መቅደሱ ይነጻል አለኝ” (ዳን. 8:14)። 2300 ቀናት
ከመቼ ጀምሮ ነው የሚቆጠሩት? ለምን ዳንኤል ራዕዩን ካየበት ዓመት ፣“ንጉሡ
ብልጣሶር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት” አይጀምርም (ዳን. 8:1)?
ይህ አይሰራም። በዳንኤል ምዕራፍ 8 ላይ ያለው ራዕይ ባቢሎንን አላካተተም።
ከእርሱ በኋላ ካሉት ክስተቶች ነው የጀመረው፤ ማለትም ከሜዶንና ፋርስ፣ ግሪክ፣
ሮም እና እስከ “ፍጻሜ” ባሉት ክስተቶች። ስለ ቤተ መቅደሱ መንጻት የተገለጸውን
ክስተት በክስተቱ ላይ ካልተገለጸው ከባቢሎን መጀመር ለምን ያስፈልጋል?
ለራዕዩ የመጨረሻው ጭብጥ የሚሆን የመነሻ ቀን መምጣት ያለበት ከሜዶንና
ፋርስ በመነሳት እስከ “ፍጻሜ” ከሚዘልቀው ከራዕዩ ከራሱ መሆን አለበት። ይህ
ብዙ ዓመታትን የሚሸፍን ጊዜ ነው።
ይህ ጊዜ የተጀመረው የት ነው? በዳንኤል 8 ላይ አልተነገረንም። የተነገረን
በዳንኤል 9 ላይ ነው።
1.በክፍላችሁ አንድ ትንቢት ሆኖ በሁለት ክፍሎች ቀርቦ በታየው
ወንጌልና ፍርድ መካከል ስላለው የቀረበ ግንኙነት ተወያዩ። በሁለቱ
መካከል ያለው ግንኙነት ለእኛ የምሥራች የሚሆነው ለምንድር ነው?
በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ስለ ፍርድ ሀሳብ ብዙዎች ያላቸውን
ፍርሃት መቅረፍ ያለበት እንዴት ነው?
2. መሲሁ “ለራሱ ሳይሆን” ለሌሎች መገደሉን በሚገልጸው በዳንኤል
9፡ 26 ላይ ባለው እውነት ላይ ትኩረት አድርጉ። ይህ እየተናገረ
ያለው ስለ ምንድር ነው? ለማን ነው የተገደለው? ለምን?
3. በድጋሚ ዘሌ. 16:16 እና ዘሌ. 23:26–29ን ያንብቡ። ስለ ቤተ
መቅደስ መንጻት አስፈላጊነትና (ዘሌ. 16:16) ይህ በሚሆንበት ጊዜ
ሰዎቹ ምን ማድረግ እንደሚገባቸው(ዘሌ. 23:26–29) ተነጋገሩ።
እዚህ እየሆነ ባለው ነገርና ይህ ዛሬ ለእኛ እየነገረን ባለው ነገር
መካከል ያለው ግንኙነት ምንድር ነው?