የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ሶስት ዓለም አቀፋዊ መልእክቶች



2ኛ ሩብ ዓመት 2023


ሚያዝያ 7 - 13

4ኛ ትምህርት

Apr 15 - 21




እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ራዕይ 14፤ ዘፍ. 22:12፤ መክ. 12:13፣ 14፤ ቆላ. 3:1፣ 2፤ ዕብ. 12:1፣ 2፤ 1ኛ ቆሮ. 3:16፣ 17።


የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው” (ራዕይ 14:12)።

የዴንማርክ ደራሲ የሆነ ሶሬን ኪርኬጋርድ ስለ መጨረሻው ዘመን ምሳሌ ተናግሮ ነበር። ምሳሌው ይህን ይመስላል፡-

ከትልቅ የቲያትር መድረክ በስተጀርባ እሳት ተነሳ። ከተዋንያኑ አንዱ የሆነውና እየቀለደ ሕዝቡን የሚያዝናና ሰው ጉባኤውን፡- ውጡ፣ ቦታው በእሳት ተያይዟል! ብሎ ለማስጠንቀቅ መጣ። ሕዝቡ ትልቅ ቀልድና የቲያትሩ አንዱ ክፍል ነው ብሎ በማሰብ አጨበጨበ። አሁንም ውጡ! ውጡ! በማለት ማስጠንቀቂያውን ደጋግሞ አስተላለፈ። እሱ በአንክሮ ባስጠነቀቀ ቁጥር ጭብጨባውም እየጨመረ ሄደ። እንደ ኪርኬጋርድ አገላለጽ ዓለም የሚያበቃው በዚህ መልክ ነው፤ ይህ ማለት ቀልድ እንደሆነ ለሚያምኑና በፈጠራ ችሎታቸው ሰዎችን ለሚያዝናኑ ሰዎች ዓለም የሚያበቃው በዚህ ሁኔታ ነው። እንደምናውቀው የዓለም ፍጻሜና ወደ ፍጻሜው የሚመሩ ክስተቶች ቀልድ አይደሉም። ከውኃ ጥፋት አንስቶ ዓለም እጅግ አሳሳቢ ቀውስ እየተጋፈጠ ነው። ጴጥሮስ ራሱ የጥንቱ ዓለም በውኃ እንደጠፋ ሁሉ በመጨረሻ ዘመን “ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል” ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል” (2ኛ ጴጥ. 3:10) ብሎ በማስጠንቀቅ የውኃ ጥፋትን የፍጻሜው ምልክት አድርጎ ይጠቀማል። እየመጣ ስላለው ነገር ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠን መዘጋጀት አለብን። *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሚያዝያ 14 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።

ሚያዝያ 8
Apr 16


እግዚአብሔርን ፍሩ

የራዕይ መጽሐፍ ለእኛ ትውልድ ያለው ዓላማ ሰዎችን ለኢየሱስ በቶሎ መመለስ ለማዘጋጀትና የእርሱን የመጨረሻ ዘመን መልእክት ለዓለም ለማስተላለፍ ከእርሱ ጋር እንድንተባበር ለማድረግ ነው። የራዕይ መጽሐፍ የእግዚአብሔርን ዕቅድ ግልጽ በማድረግ የሰይጣንን ዕቅዶች ያጋልጣል። የእግዚአብሔርን የመጨረሻ ተማጽኖ እና የእርሱን አንገብጋቢ፣ ዘላለማዊና ዓለም አቀፋዊ መልእክት ለሰብአዊ ዘር በሙሉ ያቀርባል። የሐዋርያው ዮሐንስን የፍጻሜ ዘመን አንገብጋቢ መልእክት በራዕይ 14፡7 ላይ ያንብቡ። (ደግሞ ዘፍ. 22:12፤ መዝ. 89:7፤ ምሳሌ 2:5፤ መክብብ 12:13፣ 14፤ ኤፌ. 5:21ን ያንብቡ።) ምን የተለየ ማስጠንቀቂያ ነው የሚሰጠን?



በራዕይ 14፡ 7 ላይ “ፍሩ” ለሚለው ቃል የግሪክ አዲስ ኪዳን አቻው ፎቢኦ የሚል ነው። በዚህ ቦታ ጥቅም ላይ የዋለው እግዚአብሔርን እንደ ጨካኝ ግለሰብ መፍራት ሳይሆን ማክበር፣ የአክብሮት አምልኮ ማቅረብ፣ የአክብሮት ፍርሃት ማሳየት በሚል ስሜት ነው። ለእግዚአብሔር ፍጹም የሆነ መታዘዝንና ሙሉ በሙሉ ራስን አሳልፎ የመስጠትን ሀሳብ ያስተላልፋል። ራስን ማዕከል ያደረገ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማዕከል ያደረገ የአእምሮ አመለካከት ነው። በኢሳይያስ 14፡13፣14 ላይ ሉሲፌር በልቡ “ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር “ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ” እቀመጣለሁ፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ” ብሎ ካሰበው ሀሳብ ተቃራኒ ነው።

እንዲያውም “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ” ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ” ተብሎ የተገለጸው የክርስቶስ ሀሳብ ነው (ፊል. 2:6፣ 8)።

የታላቁ ተጋድሎ ሀሳብ የሚሽከረከረው ለእግዚአብሔር በመገዛት ዙሪያ ነው። ሉሲፌር በራሱ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነበር። ከራሱ ሥልጣን በቀር ለማንኛውም ሥልጣን መገዛትን እምቢ አለ። በዙፋኑ ላይ ላለው ከመገዛት ይልቅ ራሱ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ መግዛት ፈለገ። በቀላሉ ስንገልጸው እግዚአብሔርን መፍራት ማለት በሀሳባችን ውስጥ እርሱን ማስቀደም ማለት ነው። ራስ ወዳድነታችንን እና ኩራታችንን ክደን ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ አሳልፈን በመስጠት መኖር ማለት ነው።

ይህ ሀሳብ ከሶስቱ መላእክት የመጀመሪያው ከሆነው መልአክ አፍ ስለወጣ እጅግ አስፈላጊ (ወሳኝ) ነገር መሆን አለበት። ስለዚህ ልብ ልንለው ይገባል። እግዚአብሔርን ስለመፍራት የእርስዎ ልምምድ ምንድር ነው? “እግዚአብሔርን መፍራት” ጥሩ ነገር እንደሆነ አዎንታዊ በሆነ መልኩ ለሆነ ሰው እንዴት ማብራራት ይችላሉ?

ሚያዝያ 9
Apr 17

እግዚአብሔርን መፍራትና መታዘዝ


እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ሌላ ነገር ያስተምረናል? ዘዳግም 6:2፤ መዝሙር 119:73፣ 74፤ እና መክብብ 12:13፣ 14ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች “እግዚአብሔርን መፍራት” ስለሚያስገኘው ውጤት ምን ይገልጹልናል?



እነዚህ ንባቦች እግዚአብሔርን በመፍራትና ትዕዛዛቱን በመጠበቅ መካከል ያለውን ግንኙነት ይገልጻሉ። እግዚአብሔርን መፍራት ወደ መታዘዝ የሚመራ አክብሮታዊ አመለካከት ነው። ሰማይ በጸጋ ለዳኑት ያለው አንገብጋቢ ተማጽኖ ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት እንዲታዘዙ ነው (ኤፌ. 2፡8-10)። ጸጋ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ከመታዘዝ ነጻ አያደርገንም። ወንጌል ነጻ የሚያወጣን ከሕግ ኩነኔ እንጂ ሕግን እንድንታዘዝ ካለብን ሀላፊነት አይደለም።

ጸጋ ካለፈው የበደለኝነት ስሜት ነጻ የሚያወጣን ብቻ ሳይሆን አሁን እግዚአብሔርን የሚመስል የመታዘዝ ሕይወት እንድንኖርም ኃይል ይሰጠናል። ሐዋርያው ጳውሎስ “በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ “በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን” መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን” ብሎ አውጆአል (ሮሜ 1:5)።

በጸጋ መዳን በሆነ መንገድ የእግዚአብሔርን ሕግ እንደሚቃወም ወይም የመታዘዝን አስፈላጊነት እንደሚቀንስ አድርገው የሚያስቡ አንዳንድ ሰዎች አሉ። ማንኛውም ስለመታዘዝ የሚደረግ ንግግር ሕጋዊነት እንደሆነ ያምናሉ። እኔ የምፈልገው ኢየሱስን ብቻ ነው ብለው ይናገራሉ። ጥያቄው “የትኛውን ኢየሱስ?” የሚል ነው። እኛ ራሳችን የፈጠርነው ኢየሱስ ወይስ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው ኢየሱስ? በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው ኢየሱስ የባህርዩ ቅጂ የሆነውን ሕጉን ዝቅ ወደማድረግ በፍጹም አይመራንም። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው ክርስቶስ እርሱ ማን እንደሆነ እና ለዚህ ዓለም ያለው ዕቅድ ምን እንደሆነ በግልጽ የሚገልጹትን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎች ዝቅ ወደማድረግ በፍጹም አይመራንም። የቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ የእርሱን ትምህርቶች አስፈላጊ ወዳልሆኑ ኃይማኖታዊ አስተያየቶች ዝቅ እንድናደርገው በፍጹም አይመራንም። ክርስቶስ የሁሉም ኃይማኖታዊ ህግጋት ተምሳሌት ነው። ኢየሱስ ሥጋ የለበሰ እውነት ነው። እርሱ አስተምህሮ በሕይወት (በተግባር) ሲገለጥ ነው።

የራዕይ የመጨረሻው ተማጽኖ በኢየሱስ ባለን እምነት አማካይነት እርሱ የሚሰጠውን ነገር ሁሉ በሙላት እንድንቀበል ተማጽኖ ያቀርባል። እግዚአብሔርን የሚመስል የመታዘዝ ሕይወት እንድንኖር በሚያስችለን በእርሱ የሚያድን ኃይል በማመን ወደሚገለጽ “እግዚአብሔርን መፍራት” ይጠራናል። በዚህ ቦታ “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ” (ማቴ. 10:28 ) በማለት የተገለጹት ቃላት እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንድናስተውል እንዴት ይረዱናል?

ሚያዝያ 10
Apr 18

እግዚአብሔርን ማዕከል ያደረገ ሕይወት መኖር


ሰዎች መሰረታዊ ላልሆኑ ነገሮች ወጪ ለማውጣት በማያመነቱበትና ዓለማዊ እሴቶች ራስን ማዕከል ባደረጉበት በዚህ ዘመን የሰማይ ተማጽኖ ራስን ማዕከል ከማድረግ ጭካኔና ለራስ ከሚገባ በላይ ቦታ ከመስጠት እንድንመለስና እግዚአብሔርን የሕይወታችን ማዕከል እንድናደርግ ነው። ለአንዳንዶች ገንዘብ የሕይወታቸው ማዕከል ነው። ለሌሎች መደሰት ወይም ስልጣን የሕይወታቸው ማዕከል ነው። ለሌሎች ደግሞ ስፖርት፣ ሙዚቃ ወይም መዝናናት የሕይወታቸው ማዕከል ሊሆን ይችላል። የራዕይ መልእክት እግዚአብሔርን የሕይወት እውነተኛ ማዕከል አድርጎ ለመፍራት፣ ለማክበርና ከፍ ለማድረግ የቀረበ የማስጠንቀቂያ ጥሪ ነው። ማቴ. 6:33፣ ቆላ. 3:1፣ 2፤ እና ዕብ. 12:1፣ 2ን ያንብቡ። እግዚአብሔርን የሕይወታችን እውነተኛ ማዕከል ስለማድረግ እነዚህ ንባቦች ምን ይነግሩናል?



በምድር የመጨረሻው ተጋድሎ ማዕከላዊው ጉዳይ አእምሮን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጦርነት ነው። በርግጥ ለእግዚአብሔር ፈቃድ የመገዛት፣ ለሥልጣኑ እውቅና የመስጠትና ፈቃዱን ለማድረግ የመሰጠት ጉዳይ ነው።

በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ በክፉና በመልካም መካከል የሚደረገው የመጨረሻው ጦርነት ሀሳባችንን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጦርነት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ የሚከተለውን ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል፡- በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ (አእምሮ) በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን” (ፊልጵስዩስ. 2:5)። አእምሮ (አሳብ) እኛነታችን በጥንቃቄ የተቀመጠበት ቦታ ነው። የተግባሮቻችን ምንጭ ነው። “ይሁን” የሚለው ቃል ትርጉም መፍቀድ ወይም መምረጥ ነው። ወዳን ስለምናደርገው የፈቃድ ድርጊት ይናገራል። የክርስቶስ አሳብ እንዲኖረን መምረጥ ማለት ኢየሱስ አእምሮዎቻችንን በዘላለማዊ ጉዳዮች በመሙላት አስተሳሰባችንን መልክ እንዲያስይዝ (እንዲቀርጽ) መፍቀድ ነው። ድርጊቶቻችን የአስተሳሰብ ሂደታችን ያለበትን ቦታ ያሳያሉ። እግዚአብሔርን መፍራት ማለት እርሱን በሕይወታችን ማስቀደም (የመጀመሪያ ማድረግ) ነው።

አስተሳሰባችሁን መቆጣጠር፣ ቢያንስ አእምሮአችሁን መቆጣጠር እንዳለባቸው ስትገነዘቡ፣ ምን ያህል ቀላል እንደሆነ አስቡ። ብዙ ጊዜ ችግሩ ትክክል የሆኑ ነገሮችን፣ “በምድር ያሉ ሳይሆኑ በሰማይ ያሉ ነገሮችን” ለማሰብ ሆነ ብለን ጥረት ካላደረግን በቀር አእምሮዎቻችን የወደቁና ኃጢአተኛ ከመሆናቸው የተነሣ ተፈጥሮአዊ በሆነ ሁኔታ ተራ ወደሆኑ ዓለማዊ ነገሮች ያዘነብላሉ። ስለዚህ ጳውሎስ እንዳለው የፈቃድ ነጻነትን ቅዱስ ስጦታ በመጠቀም ሀሳቦቻችንን በሰማያዊ ነገሮች ላይ ለማድረግ አስበንና አቅደን መምረጥ አለብን። “በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ” (ፊልጵስዩስ 4:8)። እዚህ ላይ ጳውሎስ የሚነግረንን ለማድረግ እንዴት እንማራለን?

ሚያዝያ 11
Apr 19

ለእግዚአብሔር ክብርን መስጠት


“ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ” (ራዕይ 14፡7) የሚለው ሀረግ በመጀመሪያው መልአክ መልእክት ውስጥ ጥቅም ላይ በዋለበት ሁኔታ በብሉይ ኪዳን ውስጥም ጥቅም ላይ የዋለበትን ሁኔታ ስናጠና ብዙ ጊዜ ከመለኮታዊ ፍርድ አውድ ተገልጾ እናገኛለን (ኢያሱ 7:19፤ 1ኛ ሳሙ. 6:5፤ ኤር. 13:15፣ 16፤ ሚል. 2:2)። ይህ ሀሳብ በራዕይ 19:1፣ 2 ላይም “ሃሌ ሉያ፤ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ “ሃሌ ሉያ፤ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው” ናቸውና ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው” በማለት ተገልጾ እናገኛለን። 1ኛ ቆሮ. 3:16፣ 17፤ 1ኛ ቆሮ. 6:19፣ 20 እና 1ኛ ቆሮ. 10:31ን ያንብቡ። እነዚህ ንባቦች እግዚአብሔርን ማክበር የምንችልበትን አንድ መንገድ እንድናስተውል እንዴት ይረዱናል?



ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው አካሎቻችን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያድርባቸው፣ በእግዚአብሔር መገኘት የተቀደሱ ቤተ መቅደሶች ናቸው። ቅዱሳት መጻሕፍት በሕይወታችን በሁሉም ገጽታ እግዚአብሔርን እንድናከብር ግልጽ የሆነ ጥሪ ያስተላልፋሉ። እግዚአብሔር የሕይወታችን ማዕከል ሲሆን የሚኖረን ብቸኛው ፍላጎት በአመጋገባችን ቢሆን ወይም በአለባበሳችን፣ በመዝናኛችን ወይም ከሌሎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት፣ ለእርሱ ክብርን መስጠት ይሆናል። ለእግዚአብሔር ክብርን የምንሰጠው የእርሱን ፈቃድ ለመፈጸም ባለን መሰጠት የእርሱን የፍቅር ባህርይ ለዓለም ስንገልጥ ነው። ይህ በምድር የመጨረሻው ዘመን ፍርድ ብርሃን ስንመለከተው ጠቀሜታው እጅግ ጉልህ ይሆናል። ሮሜ 12:1፣ 2ን ያንብቡ። አጠቃላይ የሕይወት ምርጫዎቻችንን በተመለከተ ሐዋርያው ጳውሎስ ያስተላለፈው ተማጽኖ ምንድር ነው?



በዚህ ንባብ ውስጥ አካሎች ለሚለው የአዲስ ኪዳን ቃል የግሪኩ ቃል ሶማታ ሲሆን በተሻለ ሁኔታ ሲተረጎም የአንድ ግለሰብ ማንነት ጥቅል ድምር -አካል፣ አእምሮና ስሜቶችን የሚያመለክት ነው። የፊሊፕስ ትርጉም የሚባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም “ለአእምሮ የሚመች (ምክንያታዊ የሆነ) አገልግሎት” የሚለውን አባባል “በእውቀት ላይ የተመሰረተ የአምልኮ ተግባር” ብሎ ይተረጉመዋል። በሌላ አገላለጽ “እግዚአብሔርን ለመፍራት” እና በምታደርጉት ነገር ሁሉ አእምሮአችሁን፣ አካላችሁንና ስሜቶቻችሁን ለእርሱ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ስትሆኑ ይህ “በእውቀት ላይ የተመሰረተ የእምልኮ ተግባር” ነው። በእግዚአብሔር ፍርድ ብርሃን ስንመለከት እርሱን ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆን በርግጥ ጥሩ ሀሳብ ነው። አካላችሁን እንዴት እንደምትጠቀሙበት አስቡ። በአካላችሁ እግዚአብሔርን እያከበራችሁ ለመሆናችሁ እርግጠኛ ለመሆን ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ሚያዝያ 12
Apr 20

የራዕይ መጽሐፍ ድል አድራጊዎች


“የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው” (ራዕይ 14:12)። ይህ በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩትን የእግዚአብሔርን ታማኝ ሕዝብ ያሳያል። ሆኖም ማንኛውም ሰው ከዚህ በፊትም ሆነ አሁን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ እምነት አማካይነት ነው። በኢየሱስ ማመን እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም ጥቅሱ “በኢየሱስ በማመን” እንደማይል ልብ በሉ። “የኢየሱስ እምነት” የሚለው ቃል ከዚህ የበለጠ ነገር ነው። ክርስቶስ የሰይጣንን ብርቱ ፈተናዎች ድል እንዲያደርግ ያስቻለው የእምነት ዓይነት ነው። እምነት ለእያንዳንዱ አማኝ የተሰጠ ስጦታ ነው። መንፈስ ቅዱስ በልባችን የሚያስቀምጠውን እምነት ስንለማመድ ያ እምነት ያድጋል። የምናሸንፈው በራሳችን የፈቃድ ኃይል ሳይሆን በእኛ ውስጥ በሚሰራው የህያው ክርስቶስ ኃይል ነው። የምናሸንፈው ከእኛ ማንነት የተነሣ ሳይሆን ከእርሱ ማንነት የተነሣ ነው።

እርሱ ስላሸነፈ እኛም ማሸነፍ እንችላለን። እርሱ ድል እንደነሣ እኛም ድል መንሳት እንችላለን። እርሱ ፈተናን ስላሸነፈ እኛም ፈተናን ማሸነፍ እንችላለን።

ዕብ. 4:14–16 እና ዕብ 7:25ን ያንብቡ። ድል የመንሣትን እና እግዚአብሔርን የመፍራትንና ለእርሱ ክብርን የመስጠትን ሕይወት መኖር የሚቻልበት መንገድ ምንድር ነው?



ኢየሱስ፣ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ልጅ፣ የክፉውን ማታለያዎች ድል ነስቷል። በእግዚአብሔር ተስፋዎች በመታመን፣ ፈቃዱን ለአባቱ ፈቃድ አሳልፎ በመስጠትና በአባቱ ኃይል በመደገፍ ፈተናዎችን ተጋፈጠ። እኛም በእርሱ በመታመን፣ ወደ እርሱ በመመልከትና በእርሱ በማመን አሸናፊዎች መሆን እንችላለን። ኢየሱስ ለእኛ ሁሉ በሁሉ ሲሆን የሶስቱ መላእክት መልእክቶች ሙሉ በሙሉ ስለ እርሱ ናቸው። የራዕይ መልእክት የድል እንጂ የሽንፈት መልእክት አይደለም። በጸጋና በእርሱ ኃይል አማካይነት ስለሚያሸንፍ ሕዝብ ይናገራል።

“ማሸነፍ” የሚለው ቃል በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ 11 ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል። ከመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ጀምሮ እስከ እኛ ጊዜ ያለችውን የክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን በሚወክለው የሰባቱ ቤተ ክርስቲያናት ራዕይ ውስጥ ዮሐንስ እንደሚለው በየትውልዱ “ድል የነሱ” አማኞች አሉ። በመጨረሻው ዘመን “ድል የነሱት” ሁሉን ይወርሳሉ (ራዕይ 21፡7)። ይህ ህጋዊነት አይደለም። የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚሰጣቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሕይወትና ፍጹም ጽድቅ አማካይነት በሚገኝ ድል ነው። እምነትን በተግባር መተርጎም ነው። በአማኙ ሕይወት ውስጥ የሚለውጥ፣ ሕይወትን የሚቀይርና ተዓምራዊ ጸጋ ነው። በሕይወትዎ ማሸነፍ የሚፈልጉአቸው ነገሮች አሉ? ፍላጎቶቻችንን ወደ ተግባር መለወጥ የምንችለው እንዴት ነው? በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ከተጠቀሱ “አሸናፊዎች” አንዱ ለመሆን ምን ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ ይቻላል?

ሚያዝያ 13
Apr 21

ተጨማሪ ሀሳብ


ጳውሎስ በዕብራውያን 7፡25 ላይ ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን ስለመሆኑ እየተናገረ “ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” እያለ ስለተናገራቸው አስደናቂ የጳውሎስ ቃላት አስቡ። ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። “ፈጽሞ” ለሚለው ቃል የግሪክ አቻው “ሙሉ፣ የተሟላ፣ ጠቅላላ” የሚል ነው። የሚያድነን ኢየሱስ ነው፤ የእኛ ሥራ ራሳችንን ለእርሱ አሳልፈን መስጠትና የእርሱን ድል እንደ እኛ ድል አድርጎ መቁጠር ነው። መታመን ያለብን በራሳችን ሳይሆን በእርሱ መሆን አለበት። “በራዕይ መጽሐፍ ‘እግዚአብሔርን ፍሩ’ የሚለውን አባባል እግዚአብሔርን በግርማና በክብር የተሞላ፣ እርሱንና እርሱ ለሰብአዊ ዘር ያለውን እቅድ በሚቃወሙ የክፉ ኃይሎች ላይ ድል የሚቀዳጅ አምላክ አድርገው እንዲመርጡት ለሰብአዊ ዘር የቀረበ የእግዚአብሔር የመጨረሻው ጥሪ ነው ብለን ማጠቃለል እንችላለን (ራዕይ 14፡9-11)። ይህ ፍርሃት ራሱን የሚገልጠው በሽብርና በመንቀጥቀጥ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ሕግ በደስታና በፍቅር በመገዛትና ለእርሱ ብቻ በመስገድ ነው። ሌላ ማንኛውም ኃይል ይህን የመሰለ መሰጠትና መታዘዝ እንደሚገባው እውቅና ሊሰጥ አይገባም። በዓለም አቀፋዊው ግጭት አድማስ ላይ እንደ አማራጮች አድርገው ራሳቸውን የሚያቀርቡ ነገሮች ለጥፋት የተዘጋጁ ሰይጣናዊ ኃይሎች ስለሆኑ ሌሎች አማራጮች የሉም (ራዕይ 16፡13፣ 14፤ 17፡ 14፤ 20፡11-15)። ስለዚህ እግዚአብሔርን መፍራት ሰዎች ከእርሱ ጋር ከፈጠሩት ሕብረት የተነሣ በዘላለማዊ ደስታ ተሞልተው እጅግ በግርማ በተሞላው በእርሱ ፊት በደስታ መቆም እንዲችሉ በዓለም አቀፋዊው ጦርነት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲቆሙ ከአምላክ የቀረበ አዎንታዊ ግብዣ ነው። (ራዕይ 21፡3-4፤ 22፡ 3-5)።” —Ángel Manuel Rodríguez, “The Closing of the Cosmic Con- flict: Role of the Three Angels’ Messages,” p. 27.


የመወያያ ጥያቄዎች



1.መላውን ዓለማት ስለፈጠረውና ደግፎ ስለሚያኖረው የእግዚአብሔር አስደናቂ ኃይል ያስቡ። የዩኒቨርስን ሀሳብ መረዳት በጣም ይከብዳል፤ ታዲያ የዩኒቨርስ ፈጠሪ ስለሆነው አምላክ ለመረዳት መጀመር እንኳን እንዴት ነው የምንችለው? እርሱ ከእኛ ይልቅ ምን ያህል እጅግ ትልቅ፣ ሰፊና ኃይለኛ እንደሆነ አስቡ። ይህ አምላክ አንድ ቀን እንደሚፈርድብንም አስቡ። እነዚህ እውነታዎች “እግዚአብሔርን ፍሩ” የሚለውን ሀሳብ እና ይህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንድንረዳ እንዴት ሊረዱን ይችላሉ?

2. እንደ ቅድስና፣ ማሸነፍና ድል መንሳት ስላሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽንሰ-ሀሳቦች ስንወያይ ሕጋዊነትን ማስወገድ የምንችለው እንዴት ነው? አሁን ከምናገኛቸው ድሎች ወይም ከሚገጥሙን ውድቀቶች ባሻገር የመዳን ተስፋችን ብቸኛው መሰረት የሚሆነው ክርስቶስ ለእኛ በመስቀል ላይ የተቀዳጀው ድል መሆኑን ሁለጊዜ መገንዘብ ያለብን ለምንድር ነው?

3. በኃጢአት ላይ ድልን እንድንቀዳጅ እነዚህ ሁሉ ተስፋዎች ተሰጥተውን ሳለ እና እነዚህም ተስፋዎች የእኛ እንደሚሆኑ ቃል ተገብቶልን ሳለ ስንወድቅ የምንገኝበትና ኢየሱስ ምሳሌ ሰጥቶን ባለፈው የጽድቅ መስፈርት የማንኖርበት ምክንያት ምንድር ነው? እግዚአብሔር ቃል የገባልንን ነገር በውስጣችን እንዲፈጽም ባለመፍቀድ እየፈጸምን ያለናቸው ስህተቶች ምንድር ናቸው?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA union SSL