የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ራዕይ 12:6፣ 14፤ ዳን. 7:25፤ 2ኛ ተሰ. 2:3፣ 4፤ ዘደ. 6:8፤ 11:18፤ ዘጸ. 20:8–11።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “የሕያው አምላክ ማኅተም ያለውም ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ ሲወጣ አየሁ፥ ምድርንና ባሕርንም ሊጐዱ ለተሰጣቸው ለአራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኸ፦የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ አላቸው” (ራዕይ 7:2፣ 3)።
በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሰሜን ኢጣሊያ በሚገኙ የአልፕስ ተራራዎች
አከባቢ ባለው የፕድሞንት ሸለቆዎች ውስጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ ባላቸው
መረዳት ታማኝ ሆነው ለመኖር የወሰኑ የዋልዴንሶች መኖሪያዎች
ነበሩ። ለክርስቶስ ከነበራቸው የማያወላውል ታማኝነት የተነሣ አስከፊ ስደት
ደርሶባቸዋል። በ1488 ዓ.ም በሎይስ ሸለቆ የነበሩ ዋልዴንሶች ለእምነታቸው
በሮም ቤተ ክርስቲያን በጭካኔ ተገድለዋል።
ሌላኛው የስደት ማዕበል የመጣው የሳቮሪው መስፍን ወደ መኖሪያ
ክልላቸው 8000 ወታደሮችን በመላክ የአከባቢው ሕዝብ ወታደሮቹን
በቤቶቻቸው እንዲያኖሩ በጠየቀበት በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነበር። ሕዝቡ
የመስፍኑን ጥያቄ የፈጸሙ ቢሆንም ዘዴው ግን ወታደሮቹ በቀላሉ ጥቃት
እንዲያደርሱባቸው ለማመቻቸት ነበር። ሚያዝያ 24 ቀን 1655 ዓ.ም ሊነጋጋ ሲል
በ10 ሰዓት ላይ መግደል እንዲጀምሩ ምልክት ተሰጣቸው። በዚህ ወቅት የተገደሉ
ሰዎች ቁጥር ከ4000 ይበልጥ ነበር።
እንደ አለመታደል ሆኖ ብዙ ጊዜ ታሪክ ይደገማል። “የአውሬው ምልክት”
ትንቢት የሚናገረው በዘመናት ውስጥ ከወደ ኋላ ስለሚመዘዝ እግዚአብሔርን
የማይመስል ኃይማኖታዊ ስደት ሰንሰለት ነው። ባለፉት ጊዜያቶች እንደተፈጸሙ
ስደቶች ሁሉ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ የተቀናበሩ እምነቶችንና ተቀባይነት
ያገኘውን የአምልኮ ሥርዓት እንዲቀበል ለማስገደድ የታቀደ ነው። ነገር ግን
ሁልጊዜ እንደነበረው ሁሉ እጅ የማይሰጥ ሕዝብ እግዚአብሔር ይኖረዋል።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሰኔ 10 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
አስቀድመን እንደተማርነው ሁሉ ራዕይ ምዕራፍ 13 እና 14 የተጠቀሱት የአውሬው ኃይሎች ዓለም አቀፋዊ የሀሰት አምልኮ ሥርዓትን ይወክላሉ። ነገር ግን ከዚህ ተጨማሪ የሆነ ነገር አለ። ራዕይ 13፡5፤ 12፡6፣ 14፤ እና ዳንኤል 7፡25ን ያንብቡ። ይህ ኃይል ባለፉት ምዕተ ዓመታት ኃይማኖታዊ መልክዓ ምድሩን በበላይነት የተቆጣጠረው ለምን ያህል ጊዜ ነበር?
አውሬው በታሪክ ውስጥ የሚቀጥለው ለተወሰነ ጊዜ ነበር። ምሳሌያዊ
በሆኑ የጊዜ ትንቢቶች አንድ ትንቢታዊ ቀን አንድ ዓመትን ይወክላል። ቀንን
ለዓመት የሚቆጥረውን የመጽሐፍ ቅዱስ መርህ በመተግበር በዘሁልቁ 14፡34
ላይ “ስለ አንድ ቀንም አንድ ዓመት” የሚል እናነባለን። በድጋሚ እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል፡- “አንድን ዓመት አንድ ቀን አድርጌ አርባ ቀን ሰጥቼሃለሁ” (ሕዝ.
4:6)። ይህ መርህ በዳንኤል 9፡24-27 እንደተጠቀሱ 70 ሳምንታት ያሉ መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ትንቢቶች ሲተረጎሙ ትክክለኛነቱ በተደጋጋሚ ተረጋግጧል። በራዕይ
13፡5 ላይ የተጠቀሱት 42 ወራት እያንዳንዱ ወር 30 ቀናት ያሉት ሆኖ ሲሰላ
1260 ትንቢታዊ ቀናትን ወይም 1260 ቀጥተኛ ዓመታትን እናገኛለን። የጥንት
የጊዜ መቁጠሪያዎች በዓመት ውስጥ 360 ቀናት አላቸው።
በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሮም ገዥ የነበረው ቆስጣንጥኖስ በግዛቱ
ሁሉ ለክርስትና ሕጋዊ እውቅና ሰጠ። በ330 ዓ.ም የግዛቱን ምዕራብና ምሥራቅ
ለማዋሃድ የግዛቱን ርዕሰ ከተማ ወደ ባይዛንቲየም ሲያንቀሳቅስ በሮም የአመራር
ክፍተት ተፈጠረ። በዚህን ጊዜ ጳጳሱ ይህን ክፍተት ሸፈነ። ጳጳሱ ኃይለኛ
ኃይማኖታዊ መሪ ብቻ ሳይሆን አውሮፓ እምነት የሚጥልበት ፖለቲካዊ ኃይልም
ሆነ። በ538 ዓ.ም ጁስቲንያን የተባለ አረመኔያዊ የሮም ገዥ ለሮም ጳጳስ የእምነት
ጠባቂነትን ሚና ሰጠው። ከ538 ዓ.ም -1798 ዓ.ም የነበረችው የመካከለኛው
ዘመን ቤተ ክርስቲያን፣ በትምህርቱ መግቢያ የተጠቀሰውን አሰቃቂ ስደት
ጨምሮ፣ ታላቅ ተጽእኖ ፈጣሪ ነበረች። በርቲየር የተባለ የናፖሊዮን ጄኔራል
በ1798 ዓ.ም ጳጳሱን በመማረኩ ይህ ትንቢት በትክክል ተፈጻሚነትን አገኘ።
በርቲየርና ሰራዊቱ ፒያስ 6ኛው የተባለውን ጳጳስ በመያዝ ያለ አንዳች
ግርግር ከጳጳሳዊው ዙፋን አስወገዱት። ጳጳሱ የደረሰበት ምት ከባድ ነበር፣ ነገር
ግን በራዕይ 13፡ 12 ላይ እንደተጠቀሰው የሞቱ ቁስል ሽሮለት ዓለም በሙሉ ከዚህ
ኃይል ብዙ ነገር፣ እጅግ ብዙ ነገር ይሰማል።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢት እንዴት አስደናቂ እንደሆነ እና እግዚአብሔር
የወደ ፊት ክስተቶችን እንደሚያውቅ ለእኛ እንዴት እንደሚገልጽልን
ያስቡ። ይህ እውነታ በእግዚአብሔር ተስፋዎች ላይ፣ ተፈጽመው
ያላየናቸውም ቢሆኑ፣ ለምን መታመን እንዳለብን ምን ሊያስተምረን
ይገባል?
2ኛ ተሰ. 2:3፣ 4፣ 9–12ን ያንብቡ። ጳውሎስ ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት የሚተነብየው ምንድር ነው? ለአውሬው፣ የክርስቶስ ተቃዋሚ ለሆነው ኃይል፣ ምን መለያ ምልክቶች ነው የሚሰጠን?
ሐዋርያው ጳውሎስ ከእግዚአብሔር ቃል እውነት ስለ “መውደቅ”
የክርስቲያኑን ማህበረሰብ ያስጠነቅቃል። በአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን
አስቀድሞውኑ ያሉት እና ከክርስቶስ ዳግም ምጻት በፊት ባሉት በመጪዎቹ ምዕተ
ዓመታት ሊያብቡ ያሉት የክህደት ዘሮች ጉዳይ አስጨንቆታል። የማስመሰል
ወንጌል የእግዚአብሔርን ቃል በማጣመም ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣል።
ከዚህ ክህደት በስተጀርባ ያለው ሰይጣን ነው። እርሱ “አምላክ ከሚባል
ነገር ሁሉ በላይ” ራሱን ከፍ ማድረግ የሚፈልግ እውነተኛው “የኃጢአት ሰው”
እና “በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ” የሚቀመጥ ነው (2ኛ ተሰ. 2፡4)። ነገር ግን
“ታላቁ አታላይ” ዓላማውን ለመፈጸም በሰብአዊ ወኪሎች አማካይነት ይሰራል።
በዳንኤልና ራዕይ ላይ የተገለጹት መለያ ባህርያት በዳንኤል 7 ላይ የተጠቀሰው
ትንሹ ቀንድ፣ ራዕይ 13 እና 14 ላይ የተጠቀሰው አውሬ እና በ2ኛ ተሰሎንቄ
ምዕራፍ 2 ላይ የተገለጸው “የአመጽ ሰው” የሚወክሉት ተመሳሳይ አካልን ነው።
የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ሐተታ (ትርጓሜ)
እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል፡- “አረመኔያዊውን ሮም ተከትሎ ስለሚመጣው
ተሳዳቢ ኃይል ከዳንኤል ትንቢት ጋር የሚደረግ ንጽጽር እና ዮሐንስ ነብር
ስለሚመስለው አውሬ ከሰጠው የቃል ስዕል ጋር የሚደረግ ንጽጽር በሶስቱ
መግለጫዎች መካከል ያሉትን በርካታ መመሳሰሎች ያሳያል (ትንሹ ቀንድ፣
አውሬውና የአመጽ ሰው)። ይህ ዳንኤል፣ ጳውሎስና ዮሐንስ ተመሳሳይ ስለሆነ
አንድ ኃይል፣ ስለ ጳጳሳዊ ሥርዓት፣ እያወሩ ነው ወደሚል መደምደሚያ
ይመራናል።”—Volume 7, p. 271.
የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተደራደረ፣
በወንጌል ፋንታ ሰብአዊ ልማዶችን ስለተካ እና ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ስላፈነገጠ
ኃይል እየገለጸ መሆኑን ማስታወስ እጅግ አስፈላጊ ነው። እነዚህ ትንቢቶች
ሕዝብን ለኢየሱስ ዳግም መምጣት ለማዘጋጀት የተሰጡት አስደናቂ ፍቅር
ባለው አምላክ ነው። ከእግዚአብሔር ቃል ላፈነገጡና ከሃዲ ለሆኑ የኃይማኖት
ድርጅቶች ተግሳጽ ናቸው፤ ይህ በውስጣቸው ስላለው ሕዝብ በግል የሚገጥም
ላይሆን ይችላል (ራዕይ 18፡4ን ይመልከቱ)። መልእክታችን በሚሊዮኖች
የሚቆጠሩትን ስላሳሳተው ሥርዓት ነው። እነዚህ ሕዝቦች ቢታለሉም ኢየሱስ
እጅግ ይወዳቸዋል። እኛም በዚህ አግባብ ልንይዛቸው ይገባል።
“እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ
እንዲሁ አድርጉላቸው ፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና” (ማቴ. 7:12)።
በራዕይ 13 እና 14 ላይ ከተገለጸው የአውሬው ኃይላት አብይ ሀሳብ
ጋር ይህን መርህ ተግባራዊ ማድረግ ያለብን እንዴት ነው?
በተቋማትና በመንግስታት ላይ ጥልቅ የሆነ እምነት ማጣት እንዳለ ጥናቶች ያመለክታሉ። ሚሊዮኖች በመደነቅ “ዓለምን ለመምራት የሞራል ብቃት ያለው ሰው ያለው የት ነው?” ብለው ይጠይቃሉ። የራዕይ ትንቢቶች በኃይማኖትና በፖለቲካ አንድነት ጥላ ሥር ይህን ሚና መጫወት የሚችል ኃይል የአውሬው ኃይል እንደሆነ ያመለክታሉ። ራዕይ 17:12–14ን ያንብቡ። ዮሐንስ እነዚህን የምድር ታሪክ የመጨረሻዎቹን ትዕይንቶች የሚገልጻቸው እንዴት ነው? በዚህ ቦታ የታየው ኃይለኛ ንጽጽር ምንድር ነው?
በዚህ ንባብ ውስጥ ዮሐንስ የሚናገራቸው ሶስት ወሳኝ ነጥቦች አሉ።
በመጀመሪያ የፖለቲካ ኃይሎቹ “አንድ ሀሳብ” ያላቸው ሲሆን “ኃይላቸውንና
ሥልጣናቸውን” ለአውሬው ይሰጣሉ። ሁለተኛ፣ የስህተት ጥርቅም ከበጉ ከኢየሱስ
ጋር ጦርነት ይገጥማል። ሶስተኛ፣ በምድር የመጨረሻው ጦርነት ክርስቶስና
ተከታዮቹ አሸናፊዎች ናቸው። አውሬው አያሸንፍም፤ ኢየሱስ ያሸንፋል።
አገሮችን አንድ ለማድረግ ሰይጣን ምን ስልት ሊጠቀም እንደሚችል
አስባችሁ ታውቃላችሁ? ብዙ ጊዜ ታሪክ ራሱን ይደግማል። ከሮም መንግስት
መውደቅ ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶችን እናገኛለን። ከሰሜን አቅጣጫ የተነሱ
የጀርመን ወረራዎች ምዕራባዊ አውሮፓን ባወደሙ ጊዜ የሮም ገዥ የነበረው
ቆስጣንጥኖስ ወደ ኃይማኖት ተመለሰ። የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ከመንግሥት
ኃይል ጋር ተቀላቅሎ ቆስጣንጢኖስ ለፈለገው ነገር ዋና መሣሪያ ሆነ። በአራተኛው
መቶ ክፍለ ዘመን የእሁድ ቅድስናን ማጠንከር ቀውስ በነበረበት ወቅት መንግስቱን
አንድ ለማድረግ ተሰልቶ የተደረገ ፖለቲካዊና ኃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ነበር።
ቆስጣንጢኖስ መንግስቱ አንድ አንዲሆን ሲፈልግ የሮም ቤተ ክርስቲያን ደግሞ
እርሱ “እንዲለወጥ” ፈለገች። አርተር ዌይጋል የተባለ ታዋቂ የታሪክ ምሁር እንዲህ
በማለት በግልጽ ተናግሯል፡- “ቤተ ክርስቲያን እሁድን ቅዱስ ቀን ያደረገችበት
ዋንኛው ምክንያት የፀሐይ ሳምንታዊ በዓል ስለሆነ ነው፤ በዚህ ዘመን በሰዎች
ልማድ እጅግ የከበሩ የአህዛብ በዓላትን ወስዶ የክርስትና ትርጉም እንዲኖራቸው
ማድረግ የተለመደ የክርስትና ፖሊሲ ነበር።”—The Paganism in Our Chris-
tianity (New York: G. P. Putnam’s Sons, 1928), p. 145.
ዓለም በሙሉ በፍርሃት በተዋጠበት፣ እየተጎዳ ባለበትና ትልቅ ቀውስ
(ችግር) ውስጥ ባለበት ወቅት ሰዎች የሚያረጋጋቸውንና ጥበቃ የሚያደርግላቸውን
ሰው ይፈልጋሉ። ከዚህ በፊት አረማኔያዊነት (ጭካኔ) የተነሳው በዚህ መንገድ ስለሆነ
በድጋሚ ይህ አይሆንም ብሎ ለማሰብ ምንም ምክንያት የለም። እንደ ትንቢት
አገላለጽ፣ የሆነ ነገር እነዚህን የመጨረሻ ክስተቶች ያመጣቸዋል።
ይህ ሁሉ እንዴት እንደሚሆን ለማወቅ ከባድ ቢሆንም ታላላቅ ለውጦች
እንዴት መምጣት እንደሚችሉና እንዴት በፍጥነት እንደሚከሰቱ ዓለም ተመልክቷል።
ምንም እንኳን ምን እየመጣ እንደሆነ ዝርዝሮቹን ባናውቅም ለሚመጣው ለማንኛውም
ነገር መዘጋጀት ያስፈልጋል።
ራዕይ 14:9ን ያንብቡና ከራዕይ 14:12 ጋር ያነጻጽሩ። የአውሬው ምልክት የሚደረገው የት ነው? (ዘዳ. 6:8፤ 11:18ን ይመልከቱ)። የእግዚአብሔርን ሕዝብ የአውሬውን ምልክት ከሚቀበል ሕዝብ የሚለዩ ሁለት ባህርያት ምንድር ናቸው?
አንዱ ቡድን ለአውሬው ሲሰግድ ሌላኛው ቡድን የእግዚአብሔርን
ትዕዛዛት ይጠብቃል (እነዚህ ትዕዛዛት የአውሬው ኃይል ሊለውጠው የፈለገውን
አራተኛውን ትዕዛዝ ያካትታል)፣ የኢየሱስ እምነትም አላቸው። ልዩነቱ ይህ ነው።
ሰይጣን ከባህርና ከምድር በወጡ አውሬዎች አማካይነት በመስራት የአምልኮ
እምብርት በሆነው ሰንበት ላይ ጥቃት በመሰንዘር የእግዚአብሔርን ሥልጣን ዝቅ
ለማድረግ ይሞክራል። የአውሬው ምልክት የሚደረገው በግንባር ወይም በእጅ
ላይ ነው። ግንባር ህሊና፣ ማገናዘብና ውሰኔ የሚከናወንበትን አእምሮን የሚወክል
ምልክት ሲሆን እጅ ደግሞ ስራና ተግባር የሚከናወንበት ምልክት ነው።
የኃይማኖት ነጻነታችንን የሚገድቡ ሕጎች የሚተላለፉበት ቀን እየመጣ
ነው፣ ምናልባትም እኛ ከምናስበው በፈጠነ ሁኔታ እየመጣ ነው። የእግዚአብሔርን
ቃል አውቀው የሚከተሉና የጌታን እውነተኛ ሰንበት የሚጠብቁ ሰዎች የአንድነት
ተቃዋሚዎችና የማህበረሰቡን ስኬት የማይፈልጉ የሚል ስም ይሰጣቸዋል።
“የመጽሐፍ ቅዱስን ሰንበት የሚጠብቁ ሰዎች የሕግና ሥርዓት ጠላቶች፣
የማህበረሰቡን የግብረገብ ልጓም በመስበር ሥርዓት አልበኝነትና ጥፋት
የሚያመጡ፣ እና በምድር ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እንዲወርድ የሚጠሩ
ተብለው ውግዘት ይደርስባቸዋል። በማስተዋል ላይ የተመሰረተው ጥርጣሬያቸው
እንደ ችኮ፣ ትዕቢተኛና ባለሥልጣንን የሚንቁ ተብለው እንዲወገዙ ያደርጋቸዋል።
መንግሥትን የሚጠሉ ተብለው ይወነጀላሉ።”—Ellen G. White, The Great
Controversy, p. 592.
የሮም ቤተ ክርስቲያን እሁድ የቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ ሥልጣን
“ምልክት” ነው ትላለች። ”ለውጡ የራሷ ተግባር እንደሆነ የካቶሊክ ቤተ
ክርስቲያን ትናገራለች።…ተግባሯም በኃይማኖታዊ ጉዳዮች የቤተ ክርስቲያንዋ
መንፈሳዊ ሥልጣንና ኃይል ምልክት ነው።”—The American Catholic Quar-
terly Review, January 1883.
ወደ ፊት ዓለም አቀፋዊ ቀውስ በሚከሰትበት ጊዜ ዓለማችን መሰረታዊ
ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኃይማኖታዊና ግብረገባዊ ለውጦችን እንደሚጋፈጥ የራዕይ
መጽሐፍ ይተነብያል። በዚህ ለውጥ ወቅት የእሁድ ጥበቃ አስገዳጅ በመሆን
“የአውሬው ምልክት” ይሆናል። ይህ ሁሉ እንዴት እንደሚሆን አልተነገረንም።
መጽሐፍ ቅዱስ ዋናውን ሀሳብ ብቻ ሰፋ ባለ ሁኔታ የሚሰጠን ሲሆን ይህ ደግሞ
ለአውሬው ወይም ለፈጣሪ በመስገድ ጉዳይ ዙሪያ ታላቁ ተጋድሎ ወደ መጨረሻው
እየሄደ መሆኑን ለማሳየትና ሰባተኛው ቀን ሰንበት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት በቂ
ሀሳብ ይሰጣል።
ሰብአዊ ዘር ከእግዚአብሔር ወገን ወይም ከሰይጣን ወገን ለመቆም
ሁልጊዜ በምን መንገዶች ነበር ሲከፋፈል የኖረው? አማካይ ቦታ
የሚባል ነገር ሊኖር የማይችለው ለምንድር ነው? ከማን ወገን
እንደቆምን እርግጠኛ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
ምናልባት አሁን እንኳን በቅርቡ ሊሆን ላለው አስጊ ስደት መድረኩ
እየተዘጋጀ ሊሆን ይችላል። ጳጳስ ቤኔድክት 16ኛው ሰኔ 6 ቀን 2012 ዓ.ም
በሮም ባለው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰበው ከ15000 በላይ ለሚሆን
ሕዝብ ንግግር ባደረገበት ወቅት ሰዎች ከቤተሶቻቸውና ከእግዚአብሔር ጋር
የሚያሳልፉበት ነጻ ጊዜ እንዲኖራቸው እሁድ ለሁሉም ሕዝብ የእረፍት ቀን
እንዲሆን አንገብጋቢ ተማጽኖ አቅርቧል። “እሁድን ከጥቃት የሚከላከል ሰው
ሰብአዊ ነጻነትን ከጥቃት እየተከላከለ ነው።” በርግጥ ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ሰንበት ጋር በሚቃረን መልክ ሌሎች ይህን ቀን እንዲጠብቁ ከመጠየቅ ጋር
ተመሳሳይ ባይሆንም እሁድን “የእረፍት ቀን” ማድረግ ዋና ጉዳይ መሆኑን በግልጽ
ያሳያል። ይፍጠንም ይዘግይም ሕግ ስለሚወጣ የእግዚአብሔርን ቃል የሚታዘዙና
እውነተኛውን ሰንበት የሚጠብቁ ሁሉ የህብረተሰብ ፍላጎት ተቃዋሚዎች የሚል
ስም ይሰጣቸዋል።
በዚህ አስጨናቂ ጊዜ የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ በእርሱ ኃይል
በፀጋው እርሱን ለመከተል ባላቸው እምነት ጸንተው ይቆማሉ። ለጫናው እጅ
አይሰጡም።
ከአውሬው ምልክት በተቃራኒ የእግዚአብሔርን ማህተም ይቀበላሉ።
በጥንት ዘመን ማህተሞች የሕጋዊ ሰነዶችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ጥቅም
ላይ ይውሉ ነበር። ስለዚህ የእግዚአብሔር ማህተም በሕጉ ውስጥ ተቀምጦ
እንደምናገኝ እንጠብቃለን። ጥንታዊ ማህተሞች ግለሰባዊ ምልክቶች ነበሩ። ነቢዩ
ኢሳይያስ እንዲህ ይላል፡- “ምስክሩን እሰር፤ በደቀ መዛሙርቶቼም መካከል ሕጉን
አትም” (ኢሳ. 8:16)።
ዘጸ. 20:8–11ን ያንብቡ። በሰንበት ትዕዛዝ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ
ማህተም የሚይዛቸውን ምን ነገሮች ያገኛሉ? የሰንበት ትዕዛዝ
ከሌሎች ትዕዛዛት ሁሉ የሚለየው እንዴት ነው?
4ኛው ትዕዛዝ ሕጋዊ ማህተም የሚይዛቸውን ሶስት ነገሮች ይይዛል።
የመጀመሪያው፣ የማህተም አድራጊውን ስም ሲሆን “እግዚአብሔር አምላክህ”
(ዘጸ. 20:10) ተብሎ ተገልጾአል። ሁለተኛው፣ የማህተም አድራጊውን ስልጣን
ሲሆን “የፈጠረ” (ዘጸ. 20:11) ወይም ፈጣሪ ተብሎ ተጠቅሷል። ሶስተኛው
የማህተም አድራጊውን የአስተዳደር ክልል ሲሆን “ሰማይንና ምድርን፣ ባህርን፣
በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ” (ዘጸ. 20:11)ተብሎ ተገልጾአል። እንደ ራዕይ
7:1፣ 2 አገላለጽ የእግዚአብሔር ማህተም የሚደረገው የአእምሮአችን ምልክት
በሆነው በግንባራችን ብቻ ነው። እግዚአብሔር የምርጫ ነጻነታችንን ያከብራል።
በእግዚአብሔር ቃል ላይ ካለን የእምነት መልህቅ እንዳንነቃነቅ አእምሮዋችንን
በመንፈስ ቅዱሱ ቅርጽ ለማስያዝ ይጋብዘናል (ኤፌ. 4፡30)። ስለዚህ ታማኞች
የሚባሉት “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስ እምነት ያላቸው”
(ራዕይ 14:12)እንደሆኑ የምንረዳ ሲሆን በእነዚህ ትዕዛዛት ውስጥ በአውሬው
ኃይል የተለወጠው አንድ ትዕዛዝ፣ ያውም አራተኛው ትዕዛዝ ተካትቷል።
አሁን በማደግ ላይ ያለና የኃይማኖት ነጻነታችንን ወደመገደብ
ሊያመራ የሚችል ምን ሁኔታን መመልከት ይችላሉ? በተመሳሳይ
ሁኔታ ምን እንቅፋቶች ይጠብቁናል?
“ፕሮቴስታንታዊነት የሮምን ኃይል እጅ ለመጨበጥ
ባህረ ሰላጤን አሻግራ እጇን ስትዘረጋ፣ መናፍስትን ከመጥራት እምነት ጋር እጅ
ለእጅ ለመጨባበጥ ከገደሉ ባሻገር ስትዘረጋ፣ ከዚህ የሶስትዮሽ ህብረት ተጽእኖ
ሥር አገራችን (አሜሪካ) እንደ ፕሮቴስታንትና ሪፓብሊክ ያላትን እያንዳንዱን
የሕገ-መንግስት መርህ ስትክድ፣ እና ጳጳሳዊ ውሸቶችንና ማታለያዎችን
ለማሰራጨት ሁኔታዎችን ስታመቻች ያኔ ሰይጣን በሚያስደንቅ ሁኔታ የሚሰራበት
ሰዓት እንደደረሰ እና ፍጻሜው ቅርብ እንደሆነ እናውቃለን።”—Ellen G. White,
Testimonies for the Church, vol. 5, p. 451.
“በራዕይ መጽሐፍ የታሪክ መስመር ላይ እሁድ የተቃዋሚ ኃይሎች
የአምልኮ ቀን መሆኑን ችላ ወደማለት አዘንብለናል።…እሁድ የዘንዶውን ለማመን
የሚያስቸግር ማጭበርበሪያና ማታለያ ስለሚገልጥ እጅግ ወሳኝ የሆነ ምልክት
ነው። ይህ የእግዚአብሔር ሕግ ለውጥ በዓለም አቀፋዊ ጦርነት ውስጥ ዘንዶው
በእግዚአብሔር ላይ ያለውን ጥላቻ በአንድ ቀላል ተግባር ይገልጻል። ራሱን ትሁት
አድርጎ ማቅረቡ እጅግ አሳሳች ነው። ዘንዶው ራሱን እንደ እውነተኛ የአምልኮ
ማዕከል አድርጎ በማቅረብና የእግዚአብሔር ህግ ፍትሃዊ ስላልሆነ መቀየር አለበት
ብሎ በመከራከር የእግዚአብሔርን ቦታ መቀማት (መንጠቅ) ፈልጓል። ዘንዶው
የእግዚአብሔርን ሕግ የለወጠው በአስርቱ ትዕዛዛት ውስጥ እግዚአብሔር እንደ
ፈጣሪና አዳኝ፣ ሊመለክ የሚገባ እርሱ ብቻ መሆኑን በሚገልጽ መጋጠሚያ
ቦታ ላይ ስላለ ነበር (ዘጸ. 20፡8-11፤ ዘዳ.5፤ ራዕይ 4፡11፤ 5፡ 9፣ 13፣ 14)። የህጉ
መለወጥ ዘንዶው ለእግዚአብሔር ፈቃድ (ለሕጉ) ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ ብቻ
ሳይሆን የአምልኮ ርዕስ በመሆን የእግዚአብሔርን ቦታ ለመቀማት የሚያደርገውን
ጥረትም የሚያሳይ ነው። …ይህን በሕግ ላይ የፈጸመውን ለውጥ ዓለም አቀፋዊ
ማድረግ ድሉን እርግጠኛ ያደርግለታል።”—Ángel Manuel Rodriquez, “The
Closing of the Cosmic Conflict: Role of the Three Angels’ Messages,”
pp. 53, 54.
1.ምንም እንኳን የመጨረሻዎቹን ክስተቶች በጉጉት እየጠበቅን
ያለን ቢሆንም ወደ አክራሪነት/ወግ አጥባቂነት፣ ቀንን ወደመወሰን
ወይም በእግዚአብሔር መንፈስ ከተገለጠልን ባሻገር ከመገመት
መጠንቀቅ ያለብን ለምንድር ነው? ይህንን የማድረግ አደጋዎች
ምንድር ናቸው? ሰዎች መቼና እንዴት እንደሚከሰቱ የጠበቁቸአው
ክስተቶች ሳይፈጸሙ ሲቀሩ ያስከተሉአቸው ውጤቶች ምን ነበሩ?
2. አስቀድሞ በነበረው የውይይት ጥያቄ ላይ ከተገለጹ አደጋዎች
እየራቅን ሳለን አሁን ካለው የዓለም ሁኔታ አንጻር ስንመለከት ስለ
አውሬው ምልክትና ስለ ስደት ያለን ሀሳብ የሚሆን ነገር አይመስልም
ለሚሉ ሰዎች እንዴት መልስ መስጠት እንችላለን? የዚህን ዓይነት
ምክንያት መስጠት ላይ ላዩን ስናይ ስሜት የሚሰጥ (ትክክል) ቢመስልም
በፍጹም ስሜት የማይሰጥ የሚሆነው ለምንድር ነው? (በዓለም ላይ
ታላላቅ ለውጦች እንዴት በፍጥነት ሊመጡ እንደሚችሉ ይመልከቱ)።