የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:-ራዕይ 12:9፤ 16:13 14፤ 1ኛ ተሰ. 4:16፣ 17፤ ሕዝ. 8:16፤ 20:1–20፤ ራዕይ18:4፣ 5።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ:- “በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው” (ዮሐ. 17:17)።
ቀኑ በችካጎ ከሚታዩት ከእነዚያ ውብ የመስከረም ማለዳዎች አንዱ ነበር።
ፀሐይ ከሚሺጋን ሀይቅ በላይ ብቅ ስትል ከቤት ወደ ሥራ የሚሄዱ
መንገደኞች በኬኔዲና ኢሴንሆዌር የፍጥነት መንገድ ላይ ከትራፊክ
መጨናነቅ ጋር ሲታገሉ ሳለ፣ ልጆችም ወደ ት/ቤት እየሄዱ ሳለ፣ የችካጎ ኗሪዎች ልብ
በፍርሃት እንዲመታ ያደረገ ዘግናኝ ታሪክ ብቅ ማለት ጀመረ። ሰዎች በሚያሳዝን
ሁኔታ እየታመሙ ሲሆን አንዳንዶቹ ታይሌኖል የሚባል መድሃኒት እንክብሎችን
በወሰዱ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እየሞቱ ነበር። መድሃኒቱ ሲመረመር እያንዳንዱ
እንክብል ፖታሲየም ሳይናይድ በተባለ ገዳይ መርዝ የተለበጠ ነበር። ያበደ ግለሰብ
በመድኃኒቱ ላይ ያልተገባ ንክኪ ፈጽሟል። ይህን ተግባር የፈጸመው ማን እንደሆነ
እስከ ዛሬ ድረስ አይታወቅም።
አስቀድመን እንደተመለከትነው “የምድር ኗሪዎች” “የባቢሎን ወይን
ጠጅ” የሚባለውን ገዳይ መርዝ እንደሚጠጡ የራዕይ መጽሐፍ ያስጠነቅቀናል።
በመጨረሻ ወደ ሞት ብቻ የሚመሩ የሀሰት አስተምህሮዎችና ትምህርቶች
አሉ። ነገር ግን ዓለም ለዚህ መንፈሳዊ መርዝ ያለ ማርከሻ፣ ወይም መከላከያ
አልተተወም። ማርከሻውም የሶስቱ መላእክት መልእክት ነው።
በዚህ ሳምንት ትምህርት የባቢሎንን ማታለያዎች ብቻ ሳይሆን ከእነዚህ
ማታለያዎችና እነርሱ ከሚያመጡት ሞት ሊያድነን ኢየሱስ ያቀደውን ዕቅድም
እንመለከታለን።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለግንቦት 26 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
በመጨረሻው ቀናት አውድ ኢየሱስ እንዲህ በማለት ኃይለኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ ተናግሯል፡- “ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ” (ማር. 13:22)። እርሱ የጠቀሳቸው “ምርጦች” እነማን ናቸው? በሌላ ጊዜ እንዲህ ብሏል፡ - “መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ” (ማቴ. 24:31)። በመጨረሻው ዘመን የሚኖረው ማታለያ ታማኝ የሆኑት እንኳን የመታለል አደጋ እስኪደቀንባቸው ድረስ እጅግ ትልቅ መሆኑ ትንሽ የሚያስፈራ ነው፣ አይደለም? ራዕይ 12:9ን ያንብቡ። በሰይጣን የተታለለው ማን ነው? እነዚህን ቃላት የምንረዳው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር በየዘመናቱ እንደነበረው ሁሉ በመጨረሻዎቹ ቀናትም ታማኝ የሆነ ጥቂት ሕዝብ ይኖረዋል። ነገር ግን እዚህ ላይ የተቀመጠው የቃላት አጠቃቀም ማታለያው በርግጠኝነት ምን ያህል የተስፋፋ እንደሆነ ያሳያል። ምሳሌ 14:12ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ምን ዓይነት ኃይለኛ ማስጠንቀቂያ ነው የቀረበው?
ሰዎች ትክክል ወይም ስህተት፣ መልካም ወይም ክፉ የሆነውን ነገር
ለራሳቸው ወስነው በዚያ መሰረት እንዲኖሩ ብዙ ጊዜ የራሳቸውን ህሊና
እንዲከተሉ ይነገራቸዋል። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም ኃጢአተኞችና
ጥፋተኞች ስለሆንን (ኤር. 17፡9፣ ሮሜ 3፡9-18) በራሳችን ስሜቶች (ሀሳቦች)
መተማመን ይፍጠንም ይዘግይም መሳሰታችንን ወይም ስህተት መፈጸማችንን
የሚያረጋግጥ መንገድ መሆኑን ይገልጻል። በየዘመናቱ ሥራቸው ትክክል እንደሆነ
በሚያምኑ ሰዎች ብዙ ክፋቶች ተፈጽመዋል። ይህ ማለት ለራሳቸው “ቅን
የምትመስል መንገድ” ተከትለዋል ማለት ነው።
ከዚህ ይልቅ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በመዝፈቅ እኛነታችንን
ለመንፈስ ቅዱስ አሳልፈን ስንሰጥ እውነትን ከውሸት፣ ትክክለኛውን ከስህተት፣
መልካምን ከከፉ መለየትን እንማራለን። ለራሳችን ዘዴዎች ወይም ለራሳችን
ስሜቶች ከተተውን በቀላሉ የሰይጣን ማታለያዎች ሲሳይ እንሆናለን።
ትክክል እንደሆነ ባመኑት ነገር ላይ ተመስርተው ወይም
የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብለው ባመኑት ነገር ላይ ተመስርተው
ያን ያመኑትን ነገር የተገበሩ፣ ነገር ግን ክፉ ነገሮች የፈጸሙ ሰዎችን
ምሳሌዎች ያስቡ። ከእነዚህ አሳዛኝ ክስተቶች ምን መማር እንችላለን?
ራዕይ 16:13፣ 14 እና 18:2፣ 23ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ መናፍስትን ስለመጥራት ምን መግለጫ አገኙ?
እንደ “የአጋንንት ማደሪያ” ወይም “የአጋንንት መናፍስት” እና “ጥንቆላ”
ያሉ መግለጫዎች በሙሉ አጋንንታዊ እንቅስቃሴን የሚያመለክቱ ናቸው።
በመጨረሻዎቹ ቀናት ከሚመጡት ሁለት ታላላቅ ማታለያዎች መካከል
አንዱ “ነፍስ አትሞትም”የሚለው እንደሚሆን ማስጠንቀቂያ ማግኘታችን
የሚያስደንቅ አይደለም። (ኤለን ጂ ኋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ ምዕረፍ 588ን
ይመልከቱ)።
ይህ ዛሬ ለማየት እጅግ ቀላል ነው። ነፍስ አትሞትም የሚለው ሀሳብ
በክርስቲያኑ ዓለም እንኳን የተመጠነ የክርስትና አስተምህሮ ነው። ብዙ
ክርስቲያኖች ሰው ሲሞት የዳኑት እየበረሩ ወደ ሰማይ ሲሄዱ የጠፉቱ ደግሞ ወደ
ሲዖል ይሄዳሉ ብለው ያምናሉ። ለምሳሌ ያህል ታላቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራም ከሞተ
በኋላ “ቢሊ ግራም አሁን በሰማይ፣ አፍቃሪ በሆኑ የኢየሱስ እጆች ውስጥ በደህና
ተቀምጧል” የሚለውን ወይም ይህን የሚመስል ንግግር የምንሰማው ምን ያህል
ጊዜ ነው? የዚህ ዓይነት ነገር በክፍል ውስጥ፣ በመድረኮችና በተለይም በቀብር
ሥነ-ሥርዓቶች ይስተማራል።
መክ. 9:5፤ ኢዮብ 19:25–27፤ 1ኛ ተሰ. 4:16፣ 17 እና ራዕይ 14፡13ን ያንብቡ።
ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወትና ተስፋችንን ስለምናገኝበት ቦታ እግዚአብሔር
ለሕዝቡ የሰጠው እንዴት ያለ ግልጽ መመሪያ ነው?
___________________________________________________________________________________
ከባቢሎን የማታለያ ምሶሶዎች መካከል አንዱ ነፍስ አትሞትም የሚለውን
ሀሳብ ማዕከል በማድረግ ለመናፍስት መጥራት አታላይ ተጽእኖ መንገድ የሚያዘጋጅ
ስለ ሞት ያለው የውሸት መረዳት ነው። ሙታን በሆነ መልክ እንደሚኖሩና
እንዲያውም ከእኛ ጋር ግንኙነት መፍጠር እንደሚችሉ ካመንክ ሰይጣን ካለው
የተለያዩ ዓይነት ማታለያዎች የሚጠብቅህ ምን አለ? የምትወዳት እናትህ ወይም
ልጅህ ወይም እጅግ የምትወደው ወዳጅህ በድንገት ተገልጦ የሚያናግርህ ቢሆን
በስሜቶችህ መታለል ምን ያህል ቀላል ይሆን? ይህ ከዚህ በፊት ሆኗል፣ አሁንም
ይሆናል፣ በእርግጠኝነት ወደ መጨረሻዎቹ ቀናት እየቀረብን ስንሄድ በድጋሚ
ይሆናል። ብቸኛው መከላከያችን መጽሐፍ ቅዱስ በሚያስተምረው ነገር ላይ
ሥር ሰደን ጸንተን መቆምና እስከ ኢየሱስ ዳግም ምጻት ድረስ ሞት እንቅልፍ ነው
የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት የሙጥኝ ብለን መያዝ ነው።
ዛሬ በባህልዎ ውስጥ ለዘመናዊው መናፍስትን መጥራት ምሳሌ
የሚሆኑ ምን ነገሮች አሉ? ብቸኛው መከላከያችን የእግዚአብሔርን
ቃል አጥብቀን መያዝ የሚሆነው ለምንድር ነው?
የፀሐይ አምልኮ በግብጽ፣ በአሦር፣ በፋርስ እና በባቢሎን ታዋቂ ነበር። የተፈጥሮ አምልኮ በሚለው መጽሐፉ ጄምስ ጂ ፍራዜር እንዲህ በማለት አስተያየቱን ይሰጣል፡- በጥንቷ ባቢሎን ከጥንት ዘመን ጀምሮ ፀሐይ ይመለክ ነበር።”—Volume 1, p. 529. ሊያስገርም ቢችልም አንዳንድ ጊዜ የባቢሎናውያን የፀሐይ አምልኮ በብሉይ ኪዳን ዘመን በነበረው የእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተጽእኖ አሳድሯል። ሕዝ. 8:16 እና 2ኛ ነገሥት 23:5፣ 11ን ያንብቡ። የፀሐይ አምልኮ በእሥራኤልና ይሁዳ ስላሳደረው ተጽእኖ ነቢያት ምን ጻፉ? (በተጨማሪ ሮሜ 1:25ን ይመልከቱ)።
ደንኤል በነበረበት ዘመን የነበረው ነቢዩ ሕዝቅኤል ከእግዚአብሔር
ሕዝብ መካከል አንዳንዶቹ ጀርባቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣
ፊታቸውን ደግሞ ወደ ምሥራቅ አዙረው ለፀሐይ ይሰግዱ እንደነበር ይገልጻል።
የፀሐይን ፈጣሪ በማምለክ ፋንታ ፀሐይን አመለኩ።
በራዕይ 17 ላይ የፀሐይ አምልኮን ጨምሮ የባቢሎን መርሆዎች በድርድር
ዘመን ወደ ቤተ ክርስቲያን የገባበትን ጊዜ ዮሐንስ ይገልጻል። በ4ኛው መቶ ክፍለ
ዘመን ጅምር ላይ የቆስጣንጢኖስ የይስሙላ መለወጥ በሮም ግዛት ትልቅ ደስታ
አምጥቶ ነበር። ቆስጠንጢኖስ ለፀሐይ አምልኮ ከፍተኛ ፍቅር የነበረው ሰው
ነበር። ታዋቂው የታሪክ ምሁርና ፀሐፊ ኤድዋርድ ጊቦን እንዲህ በማለት ጽፏል፡-
“ፀሐይ ለቆስጣንጢኖስ የማይበገር መሪና ጠባቂ እንደሆነ ተደርጎ በመላው ዓለም
ይከበር ነበር።”—The History of the Decline and Fall of the Roman Em-
pire, chapter 20.
ቆስጣንጢኖስ በ321 ዓ.ም የመጀመሪያውን “የእሁድ ሕግ” አስተላለፈ።”
ይህ አዋጅ እንዲህ ይላል፣ “በተከበረው (በተቀደሰው) የፀሐይ ቀን ዳኞችና
በከተማ የሚኖር ሕዝብ ይረፍ፣ ሁሉም የሥራ ቦታዎች ይዘጉ።”—በ321 ዓ.ም
የተላለፈው የቆስጣንጢኖስ ትዕዛዝ። ይህ በቆስጠንጢኖስ ግዛት ሥር ያሉ ሁሉ
እሁድን እንዲጠብቁ የሚያስገድድ ሕግ አልነበረም፣ ነገር ግን በሮም አገር በሚኖር
ሕዝብ አእምሮ እሁደን በቅድስና የመጠበቅን ስሜት አጠናክሮላቸዋል።
ነገስታትና ጳጳሳት በመንግስት አዋጆችና በቤተ ክርስቲያን መማክርት
ጉባኤ አማካይነት እሁድ ብቸኛው የአምልኮ ቀን እንዲሆን ያደረጉት ቀጥለው
በመጡ አሥርት ዓመታት ሲሆን ይህ ልምምድ በአብዛኞቹ ክርስቲያኖች እስከ
ዛሬ ድረስ ቀጥሏል። አብዛኛው ሕዝብ በሆነ ነገር ማመኑ ወይም ያንን ነገር
መለማመዱ ትክክል ሊያደርገው እንደማይችል ስለሚያሳየው ጠንካራ እውነት
ይህ እንዴት ያለ ኃይለኛ ምሳሌ ነው።
በክርስቲያን ቤተ ክርስቲያናት የእሁድ አምልኮ ምን ያህል የተስፋፋ
እንደሆነ ዙሪያዎን ይመልከቱ። የሰይጣን ማታለያዎች ምን ያህል
የተስፋፉ እንደሆኑ ይህ ጭብጥ ምን አሰተማረዎት? ልክ ሙታን
ስላሉበት ሁኔታ እንደነበረው ሁሉ ለዚህኛው ማታለያም ያለን
ብቸኛው ጥበቃ ምንድር ነው?
በራዕም ምዕራፍ 14 ላይ የቀረበው የሁለተኛው መልአክ መልእክት
“ባቢሎን ወደቀች ወደቀች” የሚል ነው። በምዕራፍ 17 ላይ በመንፈሳዊቷ ባቢሎን
የምትታወቀው ሴት ሀምራዊና ቀይ ልብስ ተጎናጽፋ በቀይ አውሬ ላይ ተቀምጣ
የወይን ጠጇን ጽዋ እያሳለፈች ዓለምን በስህተት ትምህርቷ ታሰክራለች። ቤተ
ክርስቲያንና መንግስት ሕብረት ይፈጥራሉ። ውሸት ያሸንፋል። አጋንንት አሳሳች
ተዓምራቶችን ይፈጽማሉ። ዓለም ወደ መጨረሻው ጦርነት ተወርውሮ ይገባል።
በዚህን ሰዓት የእግዚአብሔር ሕዝብ የጭካኔ ተግባር ይፈጸምባቸዋል፣
ይቀለድባቸዋል፣ ጭቆና ይደርስባቸዋል፡ ይሰደዳሉም። ነገር ግን በክርስቶስና
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለገቡት ቃል ኪዳን ጽኑዎች ይሆናሉ። የገሃነምና የክፉ
ኃይሎች በሙሉ ለክርስቶስ ያላቸውን ታማኝነት ሊያቋርጡ አይችሉም። በእርሱ
ደህንነት አላቸው። እርሱ “መጠጊያቸውና ኃይላቸው፥ ባገኛቸው በታላቅ መከራም
ረዳታቸው ነው” (መዝ. 46:1)።
እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን የሚኖረውን ሕዝብ ለቃሉ ታማኝ
ወደመሆን እየጠራቸው ነው። ኢየሱስ እንዲህ በማለት ጸልዮአል፡- “ በእውነትህ
ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው” (ዮሐ. 17:17)። በዚህ የምድር ታሪክ ወሳኝ ሰዓት
ወደ መዳረሻችን የሚመራን የሰው አመለካከት ወይም ወግ ሳይሆን የእግዚአብሔር
ቃል እውነት ነው።
ዶክተር ኤድዋርድ ቲ ሂስኮክስ የተባለ ለመጥምቃውያን ቤተ ክርስቲያን
ደረጃውን የጠበቀ መመሪያ የፃፈ ደራሲ ያስቀመጠው አስደናቂ አረፍተ ነገር
ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል። በ1893 ዓ.ም በመቶዎች የሚቆጠሩ የመጥምቃውያን
አገልጋዮችን ለያዘ ቡድን ሲናገር እሁድ ወደ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን እንዴት
እንደመጣ በማብራራት እጅግ አስደነገጣቸው።
“[እሁድ]የአህዛባዊነት መለያ ስም ተሰጥቶት፣ በፀሐይ ጣዖት ስም
ክርስትና ተነስቶ፣ በጳጳሳዊ ክህደት ተቀባይነት አግኝቶና ፈቃድ ተሰጥቶት እንደ
ቅዱስ ቅርስ ለፕሮቴስታንቶች መተላለፉ እንዴት የሚያሳዝን ነገር ነው!”—Ed-
ward Hiscox, before a New York ministers’ conference, Nov. 13, 1893.
ሕዝ. 20:1–20ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ የሕዝቅኤል መልእክት ጭብጥ
(ዋናው ሀሳብ) ምንድር ነው? በዚህ ለታማኝነት በቀረበው ጥሪ
ውስጥ ሰንበት የሚገጥመው እንዴት ነው?
ሕዝቅኤል ምዕራፍ 20 እሥራኤላውያን የአህዛብ ልምምዶችን
እንዲያቆሙና በውሸት አማልክቶቻቸው (“የግብፃውያን ጣዖቶች”) ፋንታ ፈጣሪን
እንዲያመልኩ የቀረበ ልባዊ ተማጽኖ ነው። በሶስቱ መላእክት መልእክት ውስጥ
“ባቢሎን ስለወደቀች” “ፈጣሪን እንድናመልክ” እግዚአብሔር ተመሳሳይ የሆነ
ተማጽኖ እያቀረበ ነው። አስቀድመን እንደምናውቀው ሰንበትና ለእርሱ ታማኝ
መሆን በመጨረሻዎቹ ክስተቶች ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
በሕዝቅኤል ምዕራፍ 20፡1-20 ላይ ከተጻፈው ውስጥ እኛ ለራሳችን ምን
ትምህርቶችን እንወስዳለን? (1ኛ ቆሮ. 10:11ን ይመልከቱ)።
በሀምራዊና ቀይ ልብስ የተጎናጸፈችውና በቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠችው
ሴት የወይን ጠጅ ጽዋዋን ለሁሉም ስላሳለፈች ዓለም በባቢሎን የሀሰት
አስተምህሮዎች ሰክሯል። ኤለን ጂ ኋይት ስለ “ባቢሎን ወይን ጠጅ” ስትናገር
እንዲህ ብላለች፡- “ወይን ጠጁ ምንድር ነው? የሀሰት አስተምህሮቿ ናቸው።
ለዓለም በአራተኛው ትዕዘዝ ሰንበት ፋንታ የሀሰት ሰንበት በመስጠት ሰይጣን
በመጀመሪያ በኤደን ለሄዋን የነገረውን-ነፍስ አትሞትም የሚለውን ውሸት
ደግማለች።”—Ellen G. White, Review and Herald, Dec. 6, 1892. እነዚህ
የስህተት ትምህርቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን አስተዋል። ከዚህ የተነሣ እስከ
አሁን በውሸት ውስጥ ሥር ሰደው ላሉት ሕዝቡ እግዚአብሔር የመጨረሻ ዘመን
ተማጽኖ እያቀረበ ነው።
ራዕይ 18:4፣ 5ን ያንብቡ። በወደቁ የኃይማኖት ድርጅቶች ውስጥ
ላሉ እጅግ ብዙ ሕዝቦች የእግዚአብሔር ተማጽኖ ምንድር ነው?
አስቀድመን እንደተመለከትነው(ነገር ግን መድገም ተገቢ ስለሆነ)፣
ከእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል አብዛኞቹ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች
ላይ በተደራደሩ ኃይማኖታዊ ድርጅቶች ውስጥ ይገኛሉ። የመጽሐፍ ቅዱስን
እውነቶች አይረዱም። የእግዚአብሔር የፍቅር ተማጽኖ ቀጥተኛ ሲሆን እንዲህ
ይላል፡- “ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ
ከእርስዋ ዘንድ ውጡ” (ራዕይ 18:4)።
1ኛ ዮሐ. 3:4ን ያንብቡና ከሮሜ 14:23 ጋር ያነጻጽሩ። መጽሐፍ
ቅዱስ ኃጢአትን እንዴት ይተረጉመዋል? እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ
ንባቦች የሚጣጣሙት እንዴት ነው?
ኃጢአት የእግዚአብሔርን ሕግ መተላለፍ ወይም መጣስ ነው። ማንም
ቢሆን የእግዚአብሔርን ሕግ መታዘዝ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ በሕያው
ክርስቶስ ባለው እምነት አማካይነት ነው። እኛ ደካማ፣ ተሳሳች፣ የምንወድቅና
ኃጢአተኛ ሰብአዊ ፍጡራን ነን። ክርስቶስን በእምነት ስንቀበል ላለፈው
ኃጢአታችን ጸጋው ያስተሰርይልንና ለዛሬአችን ኃይል ይሰጣል። “መታዘዝ
እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን” ይሰጠናል (ሮሜ 1:5)። የእግዚአብሔርን ሕግ
በማያከብሩና በማይታዘዙ ቤተ ክርስቲያናት ላሉት ሕዝቡ የሰማይ ተማጽኖ
በእምነት እንዲወጡ ነው። ሰንበትን በሚጠብቁ ጉባኤዎች ውስጥ ላሉት
አድቬንቲስቶች ያለው ተማጽኖ መታዘዝን በተመለከተ ራስን ማዕከል ያደረጉ
ሰብአዊ ጥረቶችን በሙሉ በመተው በክርስቶስ ጸጋ በእምነት እግዚአብሔርን
የሚመስል ሕይወት እንዲኖሩ ነው። ይህ ደግሞ ከኃጢአት ኩነኔና ግዛት ነጻ
የሚያወጣን ነው። የእሥራኤላውን ለእግዚአብሔር ሕግ የነበራቸው ታማኝነት
ለዓለም ኃይለኛ ምስክር እንደነበረ ሁሉ (ዘዳ. 4፡6) የእኛ ታማኝነትም ኃይለኛ
ምስክር በመሆን ሰዎች ከባቢሎን እንዲወጡ ይመራቸዋል።
በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የተገለጸችው“ ‘ታላቂቱ
ባቢሎን’በተለየ ሁኔታ የምትወክለው በዘመን መጨረሻ የሚኖሩትን ከሃዲ
ኃይማኖቶች ጥምረት ነው።…‘ታላቂቱ ባቢሎን’የሚለው ስም የትንቢት
መንፈስ ለታላቁ የሶስትዮሽ ኃይማኖታዊ ጥምረት ማለትም ለጳጳሳዊነት፣ ከሃዲ
ፕሮቴስታንታዊነት እና መናፍስትን መጥራት ሕብረት የተሰጠ ስም ነው።…
‘ባቢሎን’የሚለው ቃል በዋነኛነት የሚያመለክተው ከአባላቱ ይልቅ ድርጅቶችንና
መሪዎቻቸውን ነው። አባላቱ ‘ብዙ ውኆች’ (ራዕይ 17:1፣ 15) በመባል
ተገልጸዋል።”— The SDA Bible Commentary, vol. 7, pp. 851, 852.
“ነፍስ አትሞትም በሚለውና እሁድ በቅድስና እንዲጠበቅ በሚያስተምረው
በሁለቱ ታላላቅ ስህተቶች አማካይነት ሰይጣን ሕዝብን በማታለያው ሥር
ያደርጋል። የመጀመሪያው መናፍስትን ለመጥራት መሰረት ሲጥል ኋለኛው ደግሞ
ከሮም ጋር ቁርኝነት እንዲፈጠር ያደርጋል።”—Ellen G. White, The Great
Controversy, p. 588.
በብሉይ ኪዳን ዘመን በባቢሎናውያን ኃይማኖት ውስጥ የሙታን
መናፍስት አብይ ሚና ተጫውተዋል። ባቢሎናውን በነፍስት አትሞትም
አስተምህሮ ላይ ጠንካራ እምነት ነበራቸው። ሰው ሲሞት ነፍስ ወደ መናፍስት
ዓለም እንደምትገባ ያምኑ ነበር። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የነፍስ
አለመሞት ጽንሰ ሀሳብ እንግዳ ነገር ነው። የአይሁዶች እንሳይክሎፒዲያ (አውደ
ጥበብ) ነፍስት አትሞትም የሚለውን የስህተት ሀሳብ መነሻ በግልጽ ለይቶ
አስቀምጦአል። “አካል ከሞተ በኋላ ነፍስ መኖሯን ትቀጥላለች የሚለው እምነት
በቅዱሳት መጻሕፍት በአንድም ቦታ በግልጽ ትምህርት ያልተሰጠበት ነው።…ነፍስ
አትሞትም የሚለው ሀሳብ ወደ አይሁዶች የመጣው ከግሪክ አስተሳሰቦች ጋር፣
በተለይም ለዚህ ምሳሌ ከሆነው የፕላቶ ፍልስፍና ጋር ግንኙነት በመፍጠር ነበር።
ፕላቶ ወደዚህ ፍልስፍና የተመራው የባቢሎናውያንና የግብጻውያን አመለካከቶች
ባልተለመደ መልኩ በተዋሃዱበት በኦርፊክ እና ኤሉሲኒያውያን ምስጢራት
አማካይነት ነበር።”— Kaufmann Kohler, The Jewish Encyclopedia, “Im-
mortality of the Soul,” (1906).
1.ስለ ሞት እውነቱን ማወቅ ይህን ያህል አስፈላጊ የሆነው ለምንድር
ነው? ከምን ይጠብቀናል? ስለዚህ ጉዳይ ማወቃችን ይህን ያህል
የሚያጽናናን ለምንድር ነው?
2. አንዳንድ የሰይጣን ማታለያዎች ግልጽ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በቀላሉ
ለመለየት የሚያስቸግሩ ናቸው። በሁለቱም ከመታለል ማምለጥ
የምንችለው እንዴት ነው?
3. በክፍላችሁ ውስጥ በእሁድ ጥናት ውስጥ ስለተነሳው ጥያቄ፣
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ
እያደረጉ እንደሆነ በማመን ክፉ ስለሚያደርጉ ሰዎች ስለተነሳው
ጥያቄ፣ ተወያዩ። ይህን ምን ብለን ነው የምናስረዳው? በማብራሪያችን
ውስጥ የእግዚአብሔር ሕግ ምን ሚና መጫወት አለበት?