የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ትምህርት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያጥኑ:- 2ኛ ዜና 20:1–22፣ 1ኛ ዜና 21:1–14፣ 2ኛ ጴጥ. 3:3–12፣ 1ኛ ዮሐ. 2:15–17፣ ራዕይ 13:11–17።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ” (መዝሙር 50:14፣ 15)።”
አ
ንዳንድ ጊዜ ዓለማችን ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ይመስላል። ጦርነት፣ ደም
መፋሰስ፣ ወንጀል፣ የግብረገብ ውድቀት፣ የተፈጥሮ መቅሰፍቶች፣ ዓለም
አቀፍ ወረርሽኝ፣ ኢኮኖሚያዊ ፍርሃቶች፣ የፖለቲካ ብልሽት እና ሌሎችም
የዚህ ማሳያ ናቸው። ግለሰቦችና ቤተሰቦች ስለ ራሳቸው ኑሮ አስቀድመው
እንዲያስቡ ጠንከር ያለ ግፊት አለ። ከዚህ የተነሣ ለመረዳት በማያስቸግሩ በእነዚህ
እርግጠኛ ባልሆኑ ጊዜያቶች ደህንነትን ለመፈለግ ብዙ ትኩረት ተሰጥቶአል።
የሕይወት ልፋቶች ከዕለታዊ ትኩረታችን አብዛኛውን ይወስዳሉ። መከፈል
ያለበት ዕዳ፣ ማደግ ያለባቸው ልጆችና መጠበቅ ያለበት ንብረት መኖሩ ጊዜንና
አስተሳሰብን ወስዷል። በርግጥ ልብስ፣ ምግብና መጠለያ እንፈልጋለን። ኢየሱስ
በተራራ ላይ ስብከቱ እነዚህን መሰረታዊ ፍላጎቶች በመግለጽ እንዲህ ብሎ ነበር፡“ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ
ያውቃልና” (ማቴ. 6:32፣ 33)።
ከመቼውም በበለጠ በእግዚአብሔር መደገፍ በሚያስፈልገን ፈታኝ ጊዜያቶች
መካከል መከተል ያለብን በመጽሐፍ ቅዱስ መርሆዎች ላይ የተመሰረቱ አንዳንድ
ግልጽ እርምጃዎች አሉ።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለመጋቢት 9 ሰንበት ለመዘጋጀት አጥኑ።
2ኛ ዜና 20:1–22ን ያንብቡ። እየተጋፈጥን ያለናቸው ትግሎች ምንም ቢሆኑ ከዚህ ታሪክ ለራሳችን ምን ወሳኝ የሆኑ መንፈሳዊ መርሆዎችን መውሰድ እንችላለን?
የኢዮሳፋጥ መንግስት መጨረሻ አከባቢ ይሁዳ ተወርሮ ነበር።
ኢዮሳፋጥ ደፋርና ብርቱ ሰው ነበር። ለዓመታት ጦሩንና የተመሸጉ ከተሞቹን
ሲያጠናክር ነበር። ማንኛውንም ጠላት ለመጋፈጥ በደንብ ተዘጋጅቶ ነበር።
ሆኖም ችግር በገጠመው ጊዜ በራሱ ብርታት አልተማመነም ነበር፣ ነገር ግን
በእግዚአብሔር ኃይል ተማመነ። እግዚአብሔርን ለመፈለግ ራሱን ያዘጋጀ ሲሆን
በመላው ይሁዳ ጾም አውጆ ነበር። ችግር ሲገጥማቸው ማድረግ ስለሚገባቸው
ነገር ሰለሞን እንደጸለየው ሕዝቡ በሙሉ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ተሰበሰቡ።
የይሁዳ ወንዶች በሙሉ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በእግዚአብሔር ፊት
ቆሙ። እግዚአብሔር ለስሙ ክብር ጠላቶቻቸውን እንዲያውክ ጸለዩ። ከዚያ
በኋላ ንጉሱ እንዲህ በማለት ጸለየ፡- “ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም
ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ
ናቸው” (2ኛ ዜና 20:12)።
በዚህ ሁኔታ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አሳልፈው ከሰጡ በኋላ በእግዚአብሔር
ሰው ላይ የእርሱ መንፈስ መጣና እንዲህ አለ፡-“ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው
እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።.
. . . እናንተ በዚህ ሰልፍ የምትዋጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥
ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ፤
እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም” (2ኛ ዜና 20:1517)።
ስለዚህ በቀጣዩ ቀን ማለዳ ንጉሡ ለእግዚአብሔር ውዳሴ እንዲዘምሩ የሌዋውያን
መዘምራንን ከፊት በማቆም ሕዝቡን ሰበሰበ። ከዚያ በኋላ ሕዝቡን እንዲህ በማለት
አስጠነቀቀ፡- “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢያቱም
እመኑ፥ ነገሩም ይሰላላችኋል አለ” (2ኛ ዜና 20:20)። በመቀጠልም መዘምራኑ
መዘመር ሲጀምሩ ጠላቶቻቸው እርስ በርሳቸው የተጠፋፉ ሲሆን ‹‹አንድም ሰው
አላመለጠም›› ነበር (2ኛ ዜና 20፡24)። የጦርነቱን ምርኮ ለመሰብሰብ ለይሁዳ
ሰዎች ሶስት ቀን የፈጀባቸው ሲሆን በ4ኛው ቀን እየዘመሩ ወደ ኢየሩሳሌም
ተመልሰዋል።
ነጻ ያወጣቸው አምላክ እኛ የምንወደውና የምናመልከው አምላክ ሲሆን ኃይሉም
ያኔ ታላቅ እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ያው ነው። የእኛ ግድድሮሽ በእርሱና በእርሱ
ምሪት መተማመን ነው።
2ኛ ዜና 20:20ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ ለሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች
ያለው ልዩ ጠቀሜታ ምንድር ነው?
ንጉሡ ዳዊት የተሻለ እውቀት ሊኖረው ይገባ ነበር። ከምርጥ ወዳጁ
ከዮናታን ልምምድ በመነሳት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የቃል ኪዳን ግንኙነት
ውስጥ ሲሆን ያሉት ሰዎች ብዙ ወይም ጥቂቶች ቢሆኑ ልዩነት እንደማያመጣና
እግዚአብሔር ድል እንደሚሰጠው ማወቅ ነበረበት። በ1ኛ ሳሙኤል 14፡1-23
ላይ የሳዖል ልጅ የነበረው ዮናታን እና ጋሻ ጃግሬው በእግዚአብሔር እርዳታ
መላውን የፍልስጤም ሰራዊት እንዳሸነፉ መጽሐፍ ቅዱስ ዘግቦታል። ነገር ግን
በእግዚአብሔር ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ይህና ሌሎች ብዙ ተመሳሳይ ልምምዶች
ቢኖሩም ንጉሡ ዳዊት ከባድ ጊዜ ሲገጥመው በራሱ ብርታትና ቅልጥፍና
እንዲታመን ሰይጣን ፈተነው።
1ኛ ዜና 21:1–14ን ያንብቡ። ዳዊት የእሥራኤልን ሕዝብና ሰራዊቱን
ለመቁጠር የወሰነው ለምን ነበር? የጦር አዛዡ ኢዮአብ ከዚህ በተቃራኒ
የመከረው ለምን ነበር?
ወታደሮቹን የመቁጠር ሀሳብ የሰይጣን ሀሳብ እንደሆነ ልብ ይበሉ። ራሱን
ለመከላከል በእግዚአብሔር መሰናዶ ከመታመን ይልቅ በራሱ ብርታት እንዲታመን
ዳዊትን ፈተነው። የእስራኤል ሰራዊት አዛዥ የነበረው ኢዮአብ እግዚአብሔር
ለእሥራኤል ሕዝብ ሲሰራ ስላየ ዳዊት ሕዝቡን እንዳይቆጥር ለማሳመን ጥረት
አደረገ፣ ነገር ግን ዳዊት ሕዝቡ መቆጠር አለበት አለ። ጥቅሱ እንደሚገልጸው
ድርጊቱ ለመላው ህዝብ መቅሰፍትን አመጣ።
ማንም ሰው በከንቱ በእግዚአብሔር ታምኖ አያውቅም። ለእግዚአብሔር ልትዋጉ
ራሳችሁን አዘጋጁ። በደንብ ተዘጋጁ። የእንግሊዝ ገዥ የነበረ ኢሊቨር ክሮምዌል
የተባለ ሰው (1599-1658) ከጦርነት በፊት ለሰራዊቱ ከተናገረው የተወሰደ ጥቅስ
እንዲህ ይላል፡- “ልጆቼ ሆይ፣ በእግዚአብሔር ታመኑ፣ ዱቄቱንም ከእርጥበት
ተከላከሉ!” (ዱቄቱ የጠብመንጃ ዱቄት ነው)። በሌላ አነጋገር ስኬት ለማግኘት
ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፣ ነገር ግን በመጨረሻ ድል የሚሰጣችሁ
እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ተገንዘቡ ማለቱ ነበር።
በእኛ አውድ ስንመለከት በመንግሥታችን ኃይል ወይም በባንክ ባለን ገንዘብ
የመታመን ፈተና አለ፣ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሰው በእያንዳንዱ
ችግር ውስጥ ሰዎች በእግዚአብሔር ሲታመኑ መታመናቸውን አክብሮላቸው
የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሰጣቸው።
ያለብንን የእግዚአብሔርን ዕዳ ለመክፈል፣ ከዕዳ ነጻ ለመውጣትና በተሰጠን
ነገር ለጋሶች ለመሆን አሁን ያለንን ጊዜ መጠቀም አለብን። በጥንት የወንጌል
መዝሙር አገላለጽ “ከዚህ በፊት እግዚአብሔርን ፈልገን የምናውቅ ከሆነ አሁንም
በእርግጠኝነት እንፈልገዋለን።”v
የምንችለውን በማድረግ እና (ለምሳሌ ከገንዘብ ሥጋት ነጻ መሆን)
ለሁሉም ነገሮች በእግዚአብሔር መታመን መካከል ትክክለኛ ሚዛን
መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?
አስቸጋሪ ጊዜያቶችን በተመለከተ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ምን ማድረግ አለባቸው? በመኖር ዘዴ ዝም ብለን መቀመጥ አለብን ወይ? አይደለም፣ እውነታው የዚህ ተቃራኒ ነው። የዓለም መጨረሻና የክርስቶስ ዳግም ምጻት ቅርብ መሆኑን ስለምናውቅ ንብረታችንን ለሌሎች የወንጌልን የምሥራች እና እርሱን ለሚወዱት እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸውን ነገር ለመንገር መጠቀም እንፈልጋለን። በቅርቡ አንድ ቀን በምድር ላይ ያለው ነገር ሁሉ እንደሚቃጠል እናውቃለን። 2ኛ ጴጥሮስ 3:3–12ን ያንብቡ። በእናዚህ ቃሎች አማካይነት ጳውሎስ እየነገረን ያለው ነገር ምንድር ነው?
ዕቃዎቻችንን ወደ ሰማይ ለመውሰድ ዕቃ ጫኝ ተሸከርካሪዎችን
እንደማይልክልን ከእግዚአብሔር ቃል መረዳት እንችላለን። ከክርስቶስ የእጁ
ጠባሳዎች በስተቀር የኃጢአትና የክፋት ርዝራዦች ሁሉ በመጨረሻው እሳት
ይቃጠሉና ለዘላለም ይጠፋሉ።
ስለዚህ ንብረታችንን ምን ማድረግ ነው ያለብን? “ወንድሞቻችን ንብረቶቻቸውን
እየጨመሩ ከመሄድ ይልቅ እየቀነሱ መምጣት ያለባቸው ጊዜ አሁን ነው።
ወደሚሻል አገር፣ ያውም ወደ ሰማያዊ አገር ልንሄድ ነው። ስለዚህ የምድር ኗሪዎች
አንሁን፣ ነገር ግን በተቻለ መጠን ነገሮችን በትክክለኛ ቦታቸው እንዲቀመጡ
እናድርግ”—Ellen G. White, Counsels on Stewardship, p. 59.
በርግጥ እነዚህን ቃላቶች የጻፈችው ከአንድ መቶ ዓመት በፊት ነው። ነገር ግን
መርሁ አሁንም ያው ነው፡-ሕይወታችን አጭር ስለሆነች ጊዜ ሁልጊዜም አጭር
ነው። ከዘላለም ጋር በንጽጽር ስንመለከት ዕድሜያችን 60 ወይም 80 ወይም
ዘረመላችሁ ጥሩ ከሆነና ጥሩ የሆነ ጤናማ የአኗኗር ልምምድ ካላችሁ 100 ዓመት
ነው። የዚህን ሳምንት ትምህርት አንብባችሁ ሳትጨርሱ ሕይወታችሁ ሊያበቃ
ስለሚችል ቀጥሎ የምታውቁት ነገር ቢኖር የክርስቶስ ዳግም ምጻት ነው። (ዋው፣
ነገሩ ይህን ያህል ፈጣን ነበር፣ አይደለም?)
እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ክርስቲያንነታችን ሁልጊዜ መኖር ያለብን
በዘላለማዊነት ብርሃን ነው። ለራሳችንና ለቤተሰቦቻችን የሚያስፈለጉ ነገሮችን
ለማቅረብ ጠንክረን መስራት በርግጥ ያስፈልጋል። በሀብት ተባርከን ከሆነ
ስስታም እስካልሆንን ድረስ ወይም ችግረኞች ለሆኑ ሰዎች በልግስና እስከሰጠን
ድረስ በዚያ ሀብት አሁን መደሰት ስህተትነት የለውም። ነገር ግን ማንኛውም
በዚህች ምድር ላይ የምናካብተው ነገር አላፊና ጠፊ ስለሆነ ጠንቃቆች ካልሆንን
ባስተቀር መንፈሳዊነትን የማበላሸት አቅም አለው።
እርስዎ ኢየሱስ በአሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚመጣ አውቀው
ቢሆን ኖሮ ሕይወትዎን እንዴት ይቀይሩት ነበር? ወይም በአምስት
ዓመት ውስጥ ወይም በሶስት ዓመት ውስጥ የሚመጣ ቢሆን ኖሮስ?
የክርስቶስ ምሳሌዎችና ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ገጸ-ባህርያት ታሪኮች እና የኤለን ጂ ኋይት ምክሮች በሙሉ ለክርስቶስ ግማሽ መሰጠት የሚባል ነገር እንደሌለ በግልጽ ያመለክታሉ። የቆምነው በእግዚአብሔር ወገን ወይም በተቃራኒው ወገን ነው። አንድ ጸሐፊ ከትዕዛዛቱ የምትበልጠው የትኛይቱ ናት ብሎ ኢየሱስን በጠየቀው ጊዜ እንዲህ ብሎት ነበር፡- “አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት” (ማርቆስ 12:30)። ሁሉን ለክርስቶስ ስንሰጥ ለሌላ ጌታ የሚቀር ምንም ነገር አይኖርም። ነገሩ አንደዚህ ነው። መሆን ያለበት እንደዚህ ነው። ማቴዎስ 6:24ን ያንብቡ። የእነዚህን ቃላት እውነት በተመለከተ የእርስዎ ልምምድ ምን ነበር?
ኢየሱስ ገንዘብንና እግዚአብሔርን ማገልገል ከባድ ነው አለማለቱን ወይም ሁለቱንም እንዴት እንደምታገለግል ተጠንቀቅ አለማለቱን ልብ ይበሉ። እርሱ ያለው ሁለቱን ማገልገል በፍጹም አይቻልም ነው። አራት ነጥብ። ይህ ሀሳብ በነፍሶቻችን ውስጥ ፍርሃትንና መንቀጥቀጥን ማስቀመጥ አለበት (ፊልጵስዩስ 2:12)። 1ኛ ዮሐንስ 2:15–17ን ያንብቡ። እነዚህ ሶስቱ ነገሮች በዓለማችን የተገለጡት እንዴት ነው? አንዳንድ ጊዜ እነርሱ የሚያመጡት አደጋ እኛ ከምንገነዘበው በላይ ብልጠት ያለበት የሚሆነው ለምንድር ነው?
ጳውሎስ “ፍቅራችሁን በምድራዊ ነገሮች ላይ ሳይሆን በላይ በሰማይ ባሉ ነገሮች
ላይ አድርጉ” (ቆላ. 3:2) ብሎ መጻፉ የሚያስገርም አይደለም። በዓለም ያሉ ነገሮች
ሁልጊዜ በፊታችን ስላሉ የእርሱ ንግግር ከመተግበር ይልቅ ለመናገር ይቀላል።
‹‹በዓለም ያለው ነገር ሁሉ›› ማታለያው ከባድ ነው። ጊዜያዊ ፍላጎቶችን ለማርካት
ያለው ስበት ሁልጊዜ ያለ ሲሆን በጆሮዎቻችን ያንሾካሹካል ወይም የሸሚዝ
ኮሌታዎቻችንን ይዞ ይጎትተናል ወይም ሁለቱንም ያደርጋል። እጅግ ታማኝ የሆኑ
ክርስቲያኖች እንኳን ‹‹በዓለም ያሉ ነገሮች›› ፍቅር ተሰምቶአቸው አያውቅምን?
አንድ ቀን ሁሉም ነገር እንደሚያበቃ ብናውቅም ስበቱ አሁንም ይሰማናል፣
አይሰማንም? ነገር ግን መልካሙ ዜና ከእግዚአብሔር እንዲያርቀን መተው
አያስፈልገንም።
2ኛ ጴጥሮስ 3:10–14ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ የተነገረው ነገር
ግብዓቶቻችንን በመጠቀም የምናደርጋቸውን ነገሮች ጨምሮ
በአኗኗራችን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ከኢየሱስ ዳግም ምጻት በፊት የሚኖረውን ዓለም አሳዛኝ ስዕል ይስላል። ዳንኤል “ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል” (ዳን. 12:1) በማለት ይናገራል። ከዚህ በፊት የነበሩትን አንዳንድ አስጨናቂ ጊዜያቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት እርሱ እዚህ ላይ እየጠቀሰ ያለው ነገሮች በጣም መጥፎ መሆናቸውን ነው። የራዕይ መጽሐፍም ከክርስቶስ ዳግም ምጻት በፊት ስለሚኖሩት አስጨናቂ ጊዜያቶች ይጠቁማል። ራዕይ 13:11–17ን ያንብቡ። ከመጨረሻ ዘመን ስደት ጋር የገንዘብ ጉዳዮች የሚገጥሙት እንዴት ነው?
መግዛትና መሸጥ አትችሉም ማለት ነው? ዛሬ ከሕይወታችን ምን ያህሉ ነው
በመግዛትና በመሸጥ ዙሪያ የሚሽከረከረው? ሥራችን ራሱ ለመግዛት ለሚፈልጉ
ሰዎች ጊዜያችንን፣ ክህሎታችንን እና ዕቃዎቻችንን መሸጥ ነው። ሁሉንም ነገር
መግዛትና መሸጥ አለመቻል ማለት በሕብረተሰቡ ውጥ ምንም ነገር ማድረግ
አለመቻል ማለት ነው። ያኔ ታማኝ በሆኑት ላይ የሚኖረው ጫና ከባድ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ገንዘብ ካላችሁ በዚህ ዓለም የሚኖራችሁ ድርሻም ብዙ
ስለሚሆን ቢያንስ ቁሳዊ ሀብትን በተመለከተ፣ ከዓለም ጋር እንድትስማሙ
የሚመጣው ጫና ከባድ ይሆናል።
ታዲያ እንዴት ነው የምንዘጋጀው? አሁን የምንዘጋጀው በእግዚአብሔር ጸጋ
ለገንዘባችንና ለዓለማዊ ነገሮች ባርያዎች አለመሆናችንን በማረጋገጥ ነው። አሁን
የእነዚህ ነገሮች እሥረኞች ካልሆንን ለእርሱ ታማኝ ለመሆን እነዚህን ነገሮች
መተው ባለብን ጊዜም ባርያዎች አንሆንም።
ዘዳግም 14:22 እና የቁጥር 23ን የመጨረሻውን ክፍል ያንብቡ።
የእግዚአብሔር ሕዝብ በየዓመቱ ምርታቸውን ወይም ትርፋቸውን
ምን ማድረግ ነበረባቸው? ይህን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለምን
ጠየቃቸው?
እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት አስራትን የመመለስ ሥርዓትን
ከመሰረተባቸው ምክንያቶች አንዱ “ሁልጊዜ አምላክህን እግዚአብሔርን
መፍራት ትማር ዘንድ” (ዘዳ. 14:23) ነው በማት አብራርቷል። በመዝሙር 31፡
19 ላይ በተቀመጠው ግጥማዊ ንጽጽር ውስጥ ፍርሃት የሚለው ቃል መታመን
ከሚለው ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ እናያለን። “በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት
ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት፥ ቸርነትህ እንደ ምን በዛች።”
እነዚህ ተነጻጻሪ መስመሮች እግዚአብሔርን መፍራት በእርሱ መታመን እንደሆነ
ያሳዩናል። ስለዚህ እግዚአብሔር አሥራትን የመመለስ ሥርዓት ያቋቋመው
ከራስ ወዳድነት ሊጠብቀንና የሚያስፈልገንን ነገር እርሱ እንደሚሰጠን
እንድንተማመንበት ለማደፋፈር እንደሆነ እንገነዘባለን። አሥራትን በመመለስ
ታማኝ መሆን ሰዎች በመጨረሻም ታማኝ እንደሚሆኑ ዋስትና ባይሰጥም
አሥራትን በመመለስ ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች በእርግጠኝነት ራሳቸውን ለችግር
እያዘጋጁ ናቸው።
:- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሀብት እንዳናፈራ የሚያስጠነቅቅ
ምንም ነገር ባይኖርም ሀብት የአንድን ሰው መንፈሳዊ መሰጠት እንደሚጨምር
የሚናገር አንዳች ነገር የለም። እንዲያውም ተቃራኒ አደጋ መኖሩ እውነት ነው።
‹‹የገንዘብ ፍቅር፣ ሀብታም የመሆን ፍላጎት፣ ሰዎችን ከሰይጣን ጋር የሚያቆራኝ
ወርቃማ ሰንሰለት ነው።”—Ellen G. White, Steps to Christ, p. 44.
ክርስትና ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ዛሬ በዓለም ያሉ ብዙ ቤተ ክርስቲያናት
እንደሚያደርጉት አንድም ቤተ ክርስቲያን ይህንን ከመሰለ ሀብትና የፍጡር
ምቾት አልተጋራም። ጥያቄው ምን ዋጋ አስከፍሎ? የሚለው ነው። ይህን
የመሰለ ሀብታምነት በእርግጠኝነት በመንፈሳዊነታችን ላይ ተጽእኖ ያደርጋል።
ተጽእኖው ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ነው። እንዴት? ሀብትና ቁሳዊ ብልጽግና
የክርስትና መልካም ባህርያትንና ራስን መካድን አሳድገው የሚያውቁት ከመቼ
አንስቶ ነው? መብላት ከምንችለው በላይ የሆኑ የምግብ ዓይነቶች የታጨቁበት
ማቀዝቀዣ ወዳለበት ቤት መምጣት፣ የአንድ ወይም የሁለት መኪናዎች ባለቤት
መሆን፣ ዓመታዊ እረፍት መውሰድና ከቤት ሆነህ በኦን ላይን መሸመት፣ ዘመናዊ
የሆነ ኮምፒዩተርና ስማርት ፎን ባለቤት መሆን ዓለምን ወይም በዓለም ያሉ
ነገሮችን እንዳንወድ ነገሮችን ሊያቀልሉልን ይችላሉን? ምንም እንኳን ብዙዎቹ
የቤተ ክርስቲያናችን አባላት እነዚህ የቅንጦት ዕቃዎች ባይኖሩአቸውም አብዛኞቹ
ደግሞ አሉአቸው። ይህን የሚያደርጉት ነፍሶቻቸውን ለአደጋ አጋልጠው ነው።
ይህ ክፍል አሁን እየተናገረ ያለው ስለ ሚሊየናሮችና ከዚያ ያለፋ ሀብት ስላላቸው
ሰዎች ነው። ቢያንስ ሀብታም መሆናቸውን ስለሚያውቁ ከፈለጉ የተሰጡአቸውን
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስጠንቀቂያዎች ሊሰሙ ይችላሉ። አሁን እየተናገርን ያለነው
በስማርት ስልኮች፣ አይ ማይኮች፣ የአየር ንብረትን የሚያስተካክሉ ማሽኖች፣
ኤስ ዩ ቪዎች መካከል ሆነው ‹‹መካከለኛው የህብረተሰብ ክፍል›› ስለሆኑ ብቻ
መንፈሳዊነታቸው ከራሳቸው ብልጽና ጋር የመደባለቅ አደጋ የለውም በማለት
ለተታለሉት ስለ በርካታ መካከለኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ነው። አሥራትን
መመለስ፣ ‹‹ሀብታም ለሆኑት ጭምር፣ ሀብት ለሚደቅናቸው አደጋዎች ኃይለኛ
መንፈሳዊ ማርከሻ ሊሆን የሚችለው ከዚህ የተነሣ ነው።
1.በዓለም መስፈርት መሰረት ሀብታም ባንሆንም ገንዘብንና ሀብትን
በተመለከተ ስላለን አመለካከት መጠንቀቅ ያለብን ለምንድር ነው?
2.አሥራት ከመመለስ ባሻገር በዚህ ዓለም ባሉ ነገሮች እንዳንጠመድ
በእርግጠኝነት ሊረዱን የሚችሉ አንዳንድ ማድረግ የምንችላቸው
ተግባራዊ ነገሮች ምንድር ናቸው?
3.“የእግዚአብሔርን ትዕዛዛትና የኢየሱስን እምነት ከሚጠብቁ”
(ራዕይ 14:12) መካከል ከመቆጠርዎ የተነሣ በድንገት መግዛትና
መሸጥ ባይችሉ ነገ ምን የሚሆኑ ይመስሎታል? እምነትዎ ምን
ያህል እድገት የሚያሳይ ይመስልዎታል?