የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ:- ዕብ. 11:6፣ ኢሳ. 62:11፤ ሮሜ 6:23፣ ዮሐንስ 14:1–3፣ ራዕይ 21፣ ማቴ. 25:20–23፣ ሮሜ 8:16–18።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው” (ማቴ. 25:21)፡፡
ም
ንም እንኳን ድነትን በሥራችን በፍጹም ማግኘት ባንችልም መጽሐፍ
ቅዱስ በታማኝነት ለሚኖሩት ማነቃቂያ እንዲሆን ለማይገባቸው
የሚሰጠውን የእግዚአብሔር ጸጋ ሽልማት ተስፋ ይጠቅሳል።
በመጨረሻ፣ ምንም ነገር ብንቀበል፣ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ
የምንቀበለው ነው።
ዳዊት እንደጻፈው “የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤
የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሔር
ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥
ዓይንንም ያበራል። የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤
የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው። ከወርቅና ከክቡር
ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል። ባሪያህ ደግሞ
ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል” (መዝ. 19:7–11)።
መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታዎች ከዳግም ምጻት በኋላ በክርስቶስ አማካይነት
ተስፋ ስለተሰጡን ሽልማቶቻችን ይናገራል። ይህ አስከፊ የሆነ የኃጢአት አማራጭ
መንገድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያበቃል።
የተሰጠን ተስፋ ምንድር ነው? የተሰጠንን ተስፋ ስለማግኘታችንስ ምን
መተማመኛ አለን?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለመጋቢት 16 ሰንበት ለመዘጋጀት አጥኑ።
ዕብራውያን 11:6ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ ለእኛ ምን ማለት ነው? ጥቅሱ ለሚለው ነገር የእኛ መልስ ምን መሆን አለበት? ራዕይ 22:12፣ ኢሳ. 40:10፣ እና ኢሳ. 62:11ን ደግሞ ይመልከቱ። እነዚህ ጥቅሶች በሙሉ ምን ያስተምሩናል?
እግዚአብሔር ለታማኝ ልጆቹ ያዘጋጀው ሽልማት ልዩ ሲሆን እንደ ብዙዎቹ
መንፈሳዊ ነገሮች ሁሉ ከእኛ ውስን መረዳት ያለፈ ነው። “የጻድቃንን ሽልማት
ለመግለጽ ሰብአዊ ቋንቋ ብቃት የለውም። የሚያውቁት የሚመለከቱት ብቻ
ናቸው። የእግዚአብሔርን ገነት ክብር ማንኛውም ውስን አእምሮ ሊረዳው
አይችልም።”—Ellen G. White, The Great Controversy, p. 674.
ኢየሱስ የተራራውን ስብከት በመክፈት ለብሩካን ሕዝብ ያደረገውን ንግግር
እንዲህ በማለት ደምድሞታል፡- “ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም
ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት
ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን
ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና” (ማቴ. 5:11፣ 12)። የዕብራውያን መጽሐፍ
ደራሲ በዕብራውያን ምዕራፍ 11 ላይ የእምነት ሰዎችን ስም ከዘረዘረ በኋላ
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለመሞት ለምን ፈቃደኛ እንደሆነ በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ
ማብራራቱን ይጀምራል።
“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ
ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም
ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት
እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ
በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና” (ዕብ. 12:1፣ 2)።
ነገር ግን ለታማኝነት መሸለም በስራ ከመዳን ጋር ተመሳሳይ አይደለም።
ከመካከላችን ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ገጸ-ባህርያት መካከል
በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የሚያሰጥ ያህል ጥሩ ስራ የሰራ ሰው ማን ነው?
ማንም የለም። የመስቀል መላው ነጥብ ይህ ነው። በሥራችን ራሳችንን ማዳን
ብንችል ኖሮ ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት አያስፈልግም ነበር። መዳን መሆን
ያለበት በጸጋ ነው። “በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ
መሆኑ ቀርቶአል” (ሮሜ 11:6)። ስለዚህ ሽልማቶች እግዚአብሔር ለእኛና በእኛ
ያደረገው ነገር በውጭ የሚታይባቸው መንገዶች ናቸው።
ድነት በጸጋ እና ሽልማት በሰሩት መጠን መካከል ያለውን ልዩነት እንዴት
እናስተውለዋለን? መልስዎን በሰንበት ቀን ወደ ክፍል ያምጡ።
እንደ ሰብአዊ ፍጡራን (ብንወድም ባንወድም) ዘላለም ይጠብቀናል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ ይህ ዘላለም፣ ቢያንስ ለእያንዳንዳችን በግላችን፣ ከሁለት መገለጫዎቹ በአንዱ ይመጣል። ያውም ዘላለማዊ ሕይወት ወይም ዘላለማዊ ሞት ነው። ይኸው ነው። አማካይ ቦታ የሚባል ነገር የለም። በአንዱ ወይም በሌላኛው ወገን ትንሽ መራመድ የሚባል ነገር የለም። ሊሆን የሚችለው ከሁለቱ አንዱ ብቻ ነው (ሕይወት ወይም ሞት)። እውነታው ይህ ነው። ሮሜ 6:23 እና ዮሐ. 3:16ን ያንብቡ። የቀረቡልን አማራጮች ምንድር ናቸው?
እንደዚህ በግልጽ ልዩ ስለሆኑ ወይም ተለይተው ስለሚታወቁ ምርጫዎች ማሰብ ይከብዳል፣ አይደለም? ይህን ክፍል እያነበብክ ከሆነ ያለው ዕድል የዘላለምን ሕይወት መርጠሃል ወይም በእርግጠኝነት እያሰብክበት ነው የሚል ነው። እግዚአብሔር ማድረግ እንደሚችል የተናገረውን ማንኛውንም ነገር የማድረግና ተስፋዎቹን ሁሉ የመፈጸም የተለየ ችሎታ አለው። የእኛ ድርሻ ዝም ብሎ በእርሱ ማመን፣ ኢየሱስ ባደረገልን መልካምነት ማረፍና በእምነት ቃሉን ማመን ነው። ዮሐንስ 14:1–3ን ያንብቡ። በቁጥር አንድ ላይ ጌታ የሰጠን ምክር ምንድር ነው? በቁጥር 2 እና 3 ላይ የሰጠን ተስፋ ምንድር ነው?
ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ የመጨረሻ ቀናት ላይ እነዚህን አስደናቂ
የተስፋና የማበረታቻ ቃላት ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። እነዚህ ቃላት ተስፋ
በቆረጡና በተፈተኑ ጊዜ መንፈሳቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር። ለእኛም ተመሳሳይ
ነገር ማድረግ አለባቸው። ኢየሱስ ከሰማይ መጥቶ ወደ ሰማይ ተመልሶ ሄዷል፣
እንዲሁም “እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ
እኔም እወስዳችኋለሁ”ብሎ ቃል ገብቶልናል።
ኢየሱስ ዳግም የማይመጣ ከሆነ የመጀመሪያ ምጻቱ ምንም ፋይዳ ስለሌለው
ክርስቶስ በመጀመሪያ በመጣ ጊዜ በመስቀል ላይ መሞቱ ዳግም ስለመምጣቱ
ከማንኛውም ነገር ይበልጥ ታላቅ ማረጋገጫ ነው። ኢየሱስ ለእኛ በመስቀል
ስለመሞቱ እርግጠኛ የሆንነውን ያህል እርሱ ቃል እንደገባው እኛም ከእርሱ
ጋር የመሆናችን ተስፋ እርግጠኛ ነው። “እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ
ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ” (ዮሐንስ 14:3)።
የክርስቶስ የመጀመሪያው ምጻት ለዳግም ምጻቱ ዋስትና ነው በሚለው
ሀሳብ ላይ የበለጠ ትኩረት አድርጉ። በመጀመሪያ ምጻቱ ጊዜ በዳግም
ምጻቱ ተስፋ ማመን እንድንችል የሚያደርገን ምን ነገር ሆነ?
መጽሐፍ ቅዱስ ለአዲሲቱ ኢየሩሳሌም የሚሰጠው መግለጫ አብርሃም
በእምነት ያየውን ነው። “መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን
ከተማ ይጠብቅ ነበርና” (ዕብ. 11:10)። አዲስቱ ኢየሩሳሌም እግዚአብሔርን
ለሚወዱና ትዕዛዛቱን ለሚጠብቁ የተገነባች የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ነች።
አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በሺህ ዓመት ጊዜ በሰማይ የእግዚአብሔር ታማኝ ልጆች
መኖሪያ ስትሆን ከዚያ በኋላ ደግሞ በታደሰችው ምድር የዘላለም መኖሪያቸው
ትሆናለች። ዕቃችንን ጭነን ማናቀሳቀስ ለማንወድ ሰዎች መልካም ዜና
አለ። እግዚአብሔር የሁሉንም ነገር ሀላፊነት ይወስዳል። ዮሐንስ ከተማዋን
እንደተመለከተ ይናገራል። “ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ
እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ
አየሁ” (ራዕይ. 21:2)።
ራዕይ ምዕራፍ 21ን ይመልከቱ። ቃል የተገቡልን አንዳንድ ነገሮች
ምንድር ናቸው?
አእምሮዎቻችን በኃጢአት ከመጎዳታቸውና የሚያውቁት የወደቀውን በኃጢአት
የተበላሸ ዓለም ከመሆኑ የተነሣ ማስተዋል የማይችሉአቸው በርካታ ነገሮች በዚህ
ቦታ ተጠቅሰዋል። ነገር ግን ማስተዋል የምንችለው በተስፋ የተሞላ ነው።
መጀመሪያ ኢየሱስ በሥጋ በተገለጠ ጊዜ በዚህ የወደቀ ዓለም ውስጥ ከእኛ ጋር
አብሮ እንደኖረ ሁሉ በአዲሱ ዓለምም ከእኛ ጋር አብሮ ይኖራል። ኢየሱስን
በቅርብ ሆነው በአካል ላዩት ሰዎች እንዴት ያለ ዕድል ነበር! እኛም የምናየውን
ነገር የኃጢአት መጋረጃ ሳያዛባው በድጋሚ እርሱን የማየት እድል ይኖረናል።
ስለዚህ እንባን፣ ሀዘንን፣ ማልቀስንና ስቃይን ብቻ የምናውቅ እኛ በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ ከተሰጡ ታላላቅ ተስፋዎች መካከል አንዱ የሆነውን፣ “እንባዎችንም ሁሉ
ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን
ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት
አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ፣” (ራዕይ 21:4) የሚለውን ተስፋ እንዴት
ማስተዋል እንችላለን?
“የቀደመው ነገር” ሁሉ፣ ከመጀመሪያው እዚህ ቦታ መገኘት የሌለባቸው ነገሮች፣
ያልፋሉ።
ከእግዚአብሔር ዙፋን የሚፈልቅ ንጹህ የሕይወት ወንዝ ያለ ሲሆን ከወንዙ
ወዲህና ወዲያ የሕይወት ዛፍ አለ። የእግዚአብሔር ዙፋን በዚያ ይሆንና “ፊቱን
ያያሉ” (ራዕይ 22:4)። በድጋሚ የዳኑት ሕዝቦች በአብዛኛው ተለማምደው
በማያውቁት ቅርበት ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ይኖራሉ።
ሁለተኛውን ሞት የሚጋፈጡ ሰዎች ስለሚገጥማቸው ዕጣ ፋንታ ራዕይ
21፡ 8ን ያንብቡ። በዚህ ቦታ ከተጠቀሱ ኃጢአቶች መካከል ኢየሱስ ይቅር
ሊለው የማይችለው ኃጢአት የትኛው ነው? ታዲያ ተመሳሳይ ኃጢአት
የፈጸሙ ሰዎች ሲድኑ እነዚህ ሰዎች የጠፉበት ምክንያት ምንድር ነው?
በእነዚህ ሁለት ቡድኖች መካከል ያለው ወሳኝ ልዩነት ምንድር ነው?
በክርስቶስ አገልግሎት ማብቂያ አከባቢ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው
በመምጣት እንዲህ ብለው ጠየቁት፡- “ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና
የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” (ማቴ. 24:3)። ኢየሱስ ጥያቄአቸውን
ለመመለስ ሁለት ምዕራፎችን ወስዶበታል። ማቴዎስ ምዕራፍ 24 እንደ ጦርነትና
ቸነፈር ያሉ በዙሪያችን ባለው ዓለም ውስጥ ስላሉ ምልክቶች ይናገራል። ማቴዎስ
ምዕራፍ 25 ደግሞ ክርስቶስ ዳግም ከመምጣቱ በፊት ስለሚኖረው የቤተ
ክርስቲያን ሁኔታ ይናገራል። እነዚህ ሁኔታዎች በሶስት ታሪኮች የተገለጹ ሲሆን
ከእነዚህ ታሪኮች መካከል አንዱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ስጦታዎች ሕዝቡ
እንዴት እንደተጠቀሙበት የሚናገረው የመክሊቶች ምሳሌ ነው።
ማቴዎስ 25:14–19ን ያንብቡ። ወደ ሩቅ አገር የተጓዘው ማን ነው?
ንብረቱን በአደራ የሰጠው ለማን ነበር? “ንብረትን መቆጣጠር” ማለት
ምን ማለት ነው? (ማቴ. 25:19ን ይመልከቱ)
አንዳንድ ጊዜ መክሊቶችን እንደ መዘመር፣ መናገር፣ ወዘተ ያሉ የተፈጥሮ ስጦታዎች
እንደሆኑ አድርገን እናስባለን፣ ነገር ግን በሉቃስ 19፡ 12-24 ላይ በተጠቀሰው
የምናን ምሳሌ ገንዘብና አያያዙ በተለየ ሁኔታ ተገልጾአል። ኤለን ጂ ኋይትም
እንዲህ በማለት ገልጻለች፡- “የመክሊቶቹ ታሪክ ሙሉ በሙሉ እንዳልተስተዋለ
እንዳይ ተደርጌያለሁ። ይህ ጠቃሚ ትምህርት ለደቀ መዛሙርቱ የተሰጠው
በመጨረሻ ዘመን ለሚኖሩ ክርስቲያኖች ጥቅም ነበር። እነዚህ መክሊቶች ዝም
ብሎ ከእግዚአብሔር ቃል የመስበክ ወይም የማስተማር ችሎታን አይወክሉም።
ምሳሌው የሚሆነው እግዚአብሔር ለሕዝቡ በአደራ የሰጠውን ዓለማዊ ንብረት
ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 1, p. 197.
ማቴዎስ 25:20–23ን ያንብቡ። ሥራውን በመደገፍ ታማኝ የሆኑ
የገንዘብ አስተዳዳሪዎችን በተመለከተ እግዚአብሔር ምን ይላል? “ወደ
ጌታ ደስታ መግባት” ማለት ምን ማለት ነው (ማቴ. 25:23)?
ከእኛ ይልቅ ሌላኛው ሰው የሚበልጡ መክሊቶች አሉት ብሎ ማሰብ ተፈጥሮአዊ
ሲሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ተጠያቄነቱም የበለጠ ነው ብለን እናስባለን።
ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከሁሉ ያነሰ ገንዘብ፣ አንድ ታለንት፣ የነበረው ሰው
ነበር ታማኝነትን በማጉደል የእግዚአብሔርን መንግስት ያጣው። ስለ ሌሎች
ሰዎች ሀላፊነቶች ከማሰብ ይልቅ እግዚአብሔር በአደራ ስለሰጠን ነገርና እንዴት
ለእርሱ ክብር መጠቀም እንደምንችል ትኩረት እናድርግ።
እግዚአብሔር የሰጠህን መክሊት “ሊቆጣጠር” ሲመጣ ለእርሱ
የምትመልሰው እንዴት ነው?
ጳውሎስ ከተለወጠ በኋላ ሙሉ በሙሉ በክርስቶስ ሥራ ውስጥ ገባ። ከትምህርቱና ብሩህ አእምሮው የተነሣ ከዓለማዊ እይታ ሲታይ እጅግ ስኬታማ ሰው መሆን ይችል ነበር። እንደ ሙሴ ጳውሎስም ከእግዚአብሔር ታማኝ ልጆች ጋር ለክርስቶስ መሰቃየትን መረጠ። ድብደባ፣ በድንጋይ መወገር፣ እስራት፣ የመርከብ መሰበር፣ ራሃብ፣ ብርድ፣ እና በ2ኛ ቆሮንቶስ 11፡ 24-33 ላይ የተጠቀሱ ብዙ መከራዎች ደርሰውበታል። ይህን ሁሉ እንዴት መሸከም ቻለ? ሮሜ 8:16–18ን ያንብቡ። የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ማወቁ ለታማኝነቱ ምክንያት የሆነለት እንዴት ነበር?
ጳውሎስ ለክርስቶስ መሰቃየትን በደስታ እንዲቀበል ያደረገው ለታማኞች
ለተዘጋጀው ሽልማት ዋጋ መስጠቱ ነበር። ወህኒ ቤት ሆኖ እንዲህ በማለት ጽፎ
ነበር፡- “ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ
ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥
በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ
ምልክትን እፈጥናለሁ” (ፊልጵስዩስ 3:13፣ 14)።
ከዚህ በፊት አስቀድመን የተመለከትነውን ግን እንደገና መመልከት
ተገቢ የሆነውን 1ኛ ጢሞቴዎስ 6:6–12ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች
ውስጥ ለእኛ እንደ ክርስቲያኖች ወሳኝ የሆነው መልእክት ምንድር ነው?
ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጸር ስንመለከት ብልጽግና ማለት የምትፈልጉትን ነገር
በምትፈልጉበት ጊዜ ማግኘት ማለት ነው። የሀብት ክምችት ማለት አይደለም።
ብልጽግና በፊልጵስዩስ 4፡19 ላይ “አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር
በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል” ተብሎ የተገለጸውን
ተስፋ የራስ እንደሆነ አድርጎ መውሰድ ማለት ነው። በመጨረሻ ብልጽግና ማለት
በጌታ ባላችሁ ነገር አመስጋኝ መሆንና በሁሉም ነገር በእርሱ መታመን ነው።
ጌታ በዓለማዊ ንብረት ሀብታም ትሆናላችሁ ብሎ ለልጆቹ ቃል አልገባላቸውም።
ይልቁንም እግዚአብሔርን እየመሰሉ የሚኖሩ ሁሉ እንደሚሰደዱ ነገራቸው።
እርሱ የሚሰጠን ነገር ከማንኛውም ዓለማዊ ሀብት የተሻለ ነው። እንዲህ
ይላል፡- ‹‹የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እሰጣችኋለሁ፣ የትም ብትሄዱ አብሬአችሁ
እሆናለሁ።›› በመጨረሻም ታማኞች ለሆኑት ልጆቹ እውነተኛ ሀብትና ሀላፊነት
እንዲሁም ዘላለማዊ ሕይወት ይሰጣቸዋል። እንዴት ያለ ድንቅ ሽልማት ነው!
ጳውሎስ በሕይወቱ መጨረሻ አከባቢ እንዲህ ማለት ችሎ ነበር፡- በመሥዋዕት
እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን
ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት
የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ
ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም”
(2ኛ ጢሞ. 4:6–8)። ሁላችንም በእግዚአብሔር ጸጋ በተመሳሳይ እርግጠኝነት
እርሱ ያለውን ለማለት ያስችለን።
:- በምድር ላይ ባለው የእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ በገንዘብ
አያያዝ ታማኝ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን ቤተሰብ የሚያሳይ የቃል ስዕል
እንደሚከተለው ቀርቧል።
በመላው ዓለም ዙሪያ ላለችው የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ
ክርስቲያን የመጋቢነት ራዕይ
ነገሩ ወደ ፊት የሚሆን ነው፤ ቄሶችና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በቤተ
ክርስቲያን ውስጥ የመጋቢነትን አከባቢ በመፍጠር ረገድ ተሳክቶላቸዋል።
በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የገንዘብ አያያዝ ላይ የቤተ ክርስቲያንን ቤተሰብ አስተምረዋል፣
አሰልጥነዋል፣ ደግፈዋል፣ አደፋፍረዋልም።
ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎችን በሕይወታቸው እየተገበሩ ናቸው።
ሳይጠበቁ በድንገት ለሚከሰቱ ነገሮች በቋሚነት እየቆጠቡና ከተጠቃሚዎች የእዳ
ባርነት እየወጡ በልግስና እያደጉ ናቸው።
የአኗኗር ዘይቤያቸው በመጠን በመኖር፣ ራስን በመግዛትና ባላቸው በመርካት
ተለይቶ ይታወቃል። ገንዘብ ተቀናቃኝ አምላክ መሆኑ ቀርቶ ከፈጣሪ እግዚአብሔር
ጋር ባላቸው ግንኙነት እያደጉ ናቸው።
ቀኑ እለተ ሰንበት ጧት ሲሆን ሰዎች ለአገልግሎት እየመጡ ናቸው። በፊታቸው
የሰላም ስሜት-- ገንዘብን በተመለከተ አለመስጋት፣ ባላቸው የመርካትና
አመስጋኝነት ስሜት ይታይ ነበር።
በገንዘብ ላይ የሚከሰቱ የባለትዳሮች ግጭት በከፍተኛ ደረጃ ተወግዶ ነበር። ወደ
አምልኮ የሚገቡት የእግዚአብሔርን መገኘትና በእነርሱ መካከል የሚሰራውን
ሥራ በማሰብና በመጠበቅ ነበር።
የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች በቂ ገንዘብ ስላላቸው ጠንካራ የሆነ ሌሎችን
የመድረስ ሥራ ይሰራ ነበር። ከዚህ የተነሣ በችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች የክርስቶስ
ፍቅር ተጨባጭ በሆነ መንገድ ይደርስ ነበር።
አገልግሎትን በአስደናቂ ሁኔታ ለሚደግፉና በብቃት እንዲጠበቅ ለሚያደርጉ
የቤተ ክርስቲያን መገልገያዎች በቂ ገንዘብ ቀርቦ ነበር።
በፊታችን ለሁላችንም ቀርቦልን ያለው ጥያቄ “እግዚአብሔር በአደራ በሰጠን
በማንኛውም ሀብት ምን እንድናደርግለት እየጠራን ነው?” የሚል ነበር።
1. በክፍላችሁ እጅግ ግልጽ የሆኑ ሁለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ
አስተምህሮችን እንዴት ማስተዋል አለብን በሚለው ጥያቄ ላይ
ተወያዩ፡- እነርሱም ድነት በእምነት እና ሽልማት በሥራ የሚሉ
ናቸው። እነዚህን ሁለቱን ጽንሰ ሀሳቦች እንዴት እናጣጥማቸዋለን?
2. አሁን ባለን ነገር በቃኝ ማለትን መማር ገንዘብን በተመለከተ
ያለንን አቋም ለማሻሻል መሻት አንችልም ማለት ያልሆነው
ለምንድር ነው? እነዚህ ሀሳቦች እርስ በርሳቸው የማይጋጩት
ለምንድር ነው?
3. ዘላለም እንደሚጠብቀን ምንም ጥያቄ የለውም። ዘላለምን የት
እንደምናሳልፍ እንድንወስን የሚረዱንን፣ ‹‹ትናንሽ›› ቢሆኑ
እንኳን፣ ምን ዓይነት ምርጫዎች ነው የምንመርጠው?