የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ያንብቡ።ማቴ. 27፡62-66፣ ዮሐ. 10፡17- 18፣ ማቴ. 27፡51-53፣ ዮሐ. 20፡ 11-29፣ 1ቆሮ. 15፡5-8።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ውሻ ሆኜ በእግሩ ስር ወደቅሁ፡፡ እርሱም ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ” አትፍራ፤ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ እኔ ሕያው ነኝ ሞቼ ነበር እነሆ አሁን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦል መክፈቻም በእጄ ነው” (ራዕይ 1፡17-18)
የ
ክርስቲያኖች የእምነት ማዕከል የክርስቶስ ትንሳኤ ነው። ጳውሎስ
ስለዚህ ጉዳይ ሲፅፍ እንዲህ በማለት የበለጠ አጽንኦት ይሰጣል
“ምክንያቱም ሙታን ካልተነሱ ክርስቶስም አልነተሳም። ክርስቶስም
ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው እናንተም እስካሁን ድረስ ከነሃጢያታችሁ
አላችሁ ማለት ነው እንዲህም ከሆነ በክርስቶስ ያንቀላፉት ጠፍተዋል ማለት
ነው። በሚቀጥለው ሳምንት ስለዚህ ጉዳይ በዝርዝር እናያለን።
“ኢየሱስ ክርስቶስን ያውም የተሰቀለውን እርሱን ብቻ እንጂ ሌላ እንዳላውቅ
ወስኜ ነበር።” (2ቆሮ 2፡2) በማለት ስለ ክርስቶስ ሞት ምንም ያክል ጳውሎስ
አጽንኦት ሰጥቶ ቢናገርም ከትንሳኤው ተነጥሎ ሲቀመጥ የሚሰጠን ምንም
ጥቅም የለም። እንግዲህ የየሱስ ትንሳኤ ለመላው የክርስትያን እምነት እና
ለድነት እቅድ ወሳኝ የሆነው ያንን ያክል ነው።
ብዙዎች እንደሚሉት በክርስቶስ አምነው የሞቱ አያሌ ሰዎች “ከጌታ ጋር
ለመሆን ቤታቸው የሄዱና” የሰማይን በረከት እያጣጣሙ ከሆነ የክርስቶስ
ትንሳኤ እንዲሁም ከርሱ ጋር የኛም ትንሳኤ አስፈላጊነት ግራ የሚያጋባ
ይሆናል።
ከዚህ ባሻገር በዚህ ሳምንት ስለ ክርስቶስ ትንሳኤና በዚህ እምነት እንዲኖረን
ለማድረግ የሰጠንን የማረጋገጫ ኃሳብ እንቃኛለን።
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለህዳር 3 ሰንበት ይዘጋጁ።
*የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለህዳር 3 ሰንበት ይዘጋጁ።
ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሞት ተልዕኮው ያበቃለት(የተጨናገፈበት) ይመስል
ነበር። ሰይጣን ይሁዳን በማነሳሳት እና አዳኙን እንዲክድ በማድረጉ ተሳካለት
(ሉቃስ 22፡3-4፤ ዮሐ. 13፡26-27) ሊቀ ካህናት እና ሽማግሌዎች እርሱ
እንዲሞት ጠየቁ (ማቴ. 26፡59፤ ማቴ. 27፡20)። ኢየሱስ ከተያዘ በኋላ “በዚያን
ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ” (ማቴ. 26፡56) ጴጥሮስ ደግሞ ሶስት
ጊዜ ካደው (ማቴ. 26፡69-75)። አሁን ኢየሱስ ከድንጋይ በተጠረበ መቃብር
ውስጥ ተጋደመ፤ መቃብሩንም በትልቅ ድንጋይ አትመው ዘጉት፤ በሮማውያን
ጠባቂዎችም አስጠበቁት (ማቴ. 27፡57-66)፤ በአይን በማይታዩ የአጋንንት
ሃይላትም ይጠበቅ ነበር። “ሰይጣን ቢቻለው ኖሮ ክርስቶስን በመቃብር ውስጥ
ቆልፎ ያስቀረው ነበር” Ellen G. White Manuscript Releases, vol. 12, p.
412
በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ክርስቶስ አስቀድሞ በመስቀል ላይ ስለመሞቱ
ብቻ ሳይሆን ስለ ትንሳኤውም ጭምር ተናግሮ ነበር። በቀን ውስጥ ያለውን
ጥቂት ክፍለ ጊዜ እንደ ሙሉ ቀን የሚቆጥረውን የምስራቃውያን አካታች ቋንቋ
በመጠቀም ኢየሱስ “ዮናስ በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሶስት ቀንና ሦስት ሌሊት
እንደቆየ እንዲሁ የሰው ልጅ ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት በምድር ሆድ ውስጥ
ይቆያል” (ማቴ. 12፡39-40) ብሎ ተናገረ። በሌላ ጊዜም ኢየሱስ እንደሚሞት
ነገር ግን በሶስተኛው ቀን እንደሚነሳ አስምሮ ተናግሯል (ማቴ. 16፡21፤ ማቴ.
17፡22-23፤ ማቴ. 20፡17-19)። ሊቀ ካህናት እና ፈሪሳውያን ይህንን አባባል
ስለተገነዘቡ ትንሳኤውን ለማጨናገፍ ያስችለናል ያሉትን እርምጃ ወሰዱ።
ማቴ 27፡62-66ን ያንብቡ። እነዚህ ሁሉ ተግባራት ከጊዜ በኋላም
ቢሆን ስለ ክርስቶስ ትንሳኤ ለተቀረው አለም ለማረጋገጥ እገዛ
ያደረጉት እንዴት ነው?
ክርስቶስን በመቃብር ዘግቶ ለማስቀረት የተደረጉ የጥበቃ እርምጃዎች በሞላ
ክርስቶስ በሞትና በክፋት ሰራዊት ላይ የተቀዳጀውን ድል እንዲታወቅ
አደረጉት፤ ምክንያቱም የተደረጉ ጥንቃቄዎች እና በነገሩ ላይ እርግጠኛ
ለመሆን የተወሰዱ እርምጃዎች እርሱ እንዳይነሳ ለማድረግ ነበር።
እነዚህ ሰዎች የኢየሱስን ተአምራት የሰሙና፣ አንዳንዶቹም ደግሞ
በአይኖቻቸው ያዩ ናቸው። ሆኖም መቃብሩ ጋር ያደረጓቸው ጠባቂዎች ብዙ
ተአምራትን የሰራው ጌታ ከሞት እንዳይነሳ ሊከላከሉትና ሊጠብቁት አስበው
ነውን?
ለምን ጉዳይ ነው በመቃብሩ ዙሪያ ጠባቆችን ያደረጉት? ደቀ መዛሙርቱ
አካሉን ሰርቀው ከሞት ተነስቷል እንዳይሉ ነበር። ሰዎች የተነሳው ኢየሱስ የት
አለ ሲሉ እኛ ያልናችሁን ብቻ እመኑ እንዳይሉ ነበር።
ምንም ያድርጉ ምንም ተግባሮቻቸው የሚያሳዩት ክርስቶስ ሞቶም እንኳን
በሊቀ ካህናቱ ዘንድ ምን ያክል ተፈርቶ እንደነበር ነው። በጥልቁ ልባቸው
ውስጥ ምናልባትም እንደሚነሳ አምነው ይሆናል።
ክርስቶስ በሰይጣን እና በክፉ ሃይላት ላይ ድል ስለመቀዳጀቱ ማረጋገጫው
መስቀሉ እና ባዶ መቃብሩ ናቸው። “ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ ሲገባ ሰይጣን
በደስታ ፈነጨ። መልሶ በህይወት ሊኖር እንደማይችል በማሰብ ተስፋ አደረገ።
የክርስቶስን አካል በመጠየቅና በመውሰድ በመቃብሩ ዙርያ ጠባቆችን በማኖር
ክርስቶስን እስረኛ አድርጎ ለማቆየት አሰበ። ሰማያዊ መልዕክተኞች ሲቀርቡ
የእርሱ መላዕክት መሸሻቸው ክፉኛ አበሳጨው። ክርስቶስ በድል ፊት ለፊት
ሲወጣ የመንግስቱ ማብቂያ እንደ ደረሰና በስተመጨረሻም እንደሚሞት
ገባው።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገፅ 782።
ምንም እንኳን የክርስቶስ
ሰብአዊ አካል ቢሞትም መለኮታዊነቱ ግን አልሞተም ነበር። በመለኮታዊነቱ
በኩል ክርስቶስ የሞትን ቀንበር በመስበር ሃይሉን የራሱ አደረገ።
ማቴ. 28፡1-6ን ዮሐ. 10፡17-18ን እና ሮሜ 8፡11ን
ያንብቡ።በክርስቶስ ትንሳኤ ላይ በቀጥታ የተሳተፈው ማን ነበር?
ኢየሱስ በሰማርያ በነበረው አገልግሎት ወቅት ህይወቱን ለመስጠትና መልሶ
ለማንሳት ሀይል እንዳለው ተናግሯል (ዮሐ. 10፡17-18)። ለማርታም እንዲህ
አላት “ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ” (ዮሐ. 11፡25)። ሌሎች ጥቅሶች ደግሞ
ትንሳኤው የእግዚአብሔር አደራረግ እንደሆነ ይናገራሉ (ሐዋ. 2፡24፤ ሮሜ
8፡1፤ ገላ. 1፡1፤ ዕብ. 13፡20)። በዛ ክብር በተሞላበት ክስተት ጊዜ እንኳን የጌታ
ኃያል መልአክ ተሳትፏል (ማቴ. 28፡1-2)።
በዚሁ ጊዜ ማቴ. 28፡11-15 እንደሚገልጥልን ክርስቶስን ለመቃወም መሪዎች
ፍሬ ቢስና የሞኝ ጥረታቸውን ያከናውኑ ነበር። የሮም ጠባቆች ለካህናት አለቆች
“የሆነውን ሁሉ አወሩ” (ማቴ. 28፡11)። ነገሩ ተብራርቶ ባይለገጽም ጠባቂዎቹ
ትንሳኤውን በአይናቸው አይተዋል። ይህ ካልሆነ ታዲያ ንግግራቸው ምን ሌላ
ትርጉም ይኖረዋል? መልአኩ ከሰማይ ወደ ምድር መጣና ድንጋዩን አንከባሎ
በላዩ ላይ ሲቀመጥ ጠባቂው ራሱን ስቶ ወድቆ ይሆን? በቀጣይ የተረዱት ነገር
መቃብሩ ባዶ መሆኑን ይሆን? ምናልባት ሮማውያኑ ባልነቁበት ሰአት መልዓኩ
የኢየሱስን አካል ወስዶ ይሆንን? ምናልባትም ይህን ያደረጉት ደቀ መዛሙርቱ
ቢሆኑስ ወይንም ሌላ ሰው ሰርቆት ቢሆንስ? የትኛውም ነገር ቢሆን የየሱስ
አካል በዚያ የለም።
የመልአኩ ከሰማይ መውረድ የሰዎቹ በፍርሃት የተነሳ ራሳቸውን መሳት እና
የመቃብሩ ባዶ መሆን የሀይማኖት መሪዎችን በበቂ ደረጃ ግራ ያጋባ ክስተት
ነበር። ነገር ግን “ለወታደሮቹ በቂ ገንዘብ በመስጠት (ማቴ. 28፡12) ዝም
ሊያሰኟቸው መሞከራቸው ወታደሮቹ የሚነግሯቸው ነገር ውስጣቸውን
በእጅጉ እንደረበሸው የሚያሳይ ነው። እነርሱ
የክርስቶስን ከሞት መነሳት ነበር።
የነገሯቸው ነገር ደግሞ
አንዳንድ ዘባቾች የክርስቶስን ከሞት መነሳት ቀድመው
የተመለከቱት ሮማውያን ናቸው በሚለው ኃሳብ ላይ ያሾፋሉ።
ለምን? ይህ እውነት ከፊታቸው ስለነበረው ማለትም ወንጌል ወደ
አህዛብም እንደሚሄድ ምሳሌ የሚሆነን በምን መንገድ ነው?
“በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከታች ለሁለት ተቀደደ፤ ምድር ተናወጠች፤ አለቶችም ተነሰጣጠቁ፤ መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተውም ከነበሩትም ብዙዎች ቅዱሳን ተነሱ፤ ከመቃብርም በመውጣት ከኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ።” (ማቴ. 27፡51-53)። ይህ አስደናቂ ክስተት ስለኢየሱስ ትንሳኤ እና ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ምን ያስተምረናል?
የመሬት መንቀጥቀጡ ኢየሱስ ስለመሞቱ ያመላከተ ክስተት ነው (ማቴ. 27፡
50-51)፤ ሌላኛው የምድር መናወጥ ደግሞ ትንሳኤውን አመላክቷል (ማቴ.
28፡2)። ኢየሱስ በሞተበት ሰዓት “ምድር ተናወጠች፤ አለቶች ተሰነጣጠቁ፤
መቃብሮች ተከፈቱ። አንቀላፍተው ከነበሩትም ብዙዎች ቅዱሳን ተነሱ፤
ከመቃብርም በመውጣት ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው
ለብዙዎች ታዩ።” (ማቴ. 27፡51-53)። እነዚህ ቅዱሳን በክብር ከሞት የተነሱት
የክርስቶስን ትንሳኤ ምስክር ሆነው በመታየት እና በመጨረሻው ትንሳኤ ጊዜ
ለሚነሱ ሰዎች ቀዳሚ በመሆን ነው። ስለዚህ ከክርስቶስ ትንሳኤ በኋላ ብዙ
የአይሁድ ህዝቦች በትንሳኤው ለማመን ጠንካራ ማረጋገጫን ስላገኙ እንደ
አዳኛቸው አድርገው ተቀብለውታል ይህም ቀሳውስትን ያካትት ነበር (ሐዋ.
ሥራ 6፡7ን ይመልከቱ)።
“በአገልግሎቱ ወቅት ኢየሱስ የሞተውን ሰው አስነስቷል። በናይን የነበረችውን
የመበለቲቱን ልጅ፤ የሃገረገዢውን ሴት ልጅ እና አልአዛርን ከሞት አስነስቷል።
ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የማይሞት ስጋን አልተላበሱም፤ ከሞት የተነሱ ቢሆንም
ተመልሰው ለሞት የተሰጡ ነበሩ። በክርስቶስ ትንሳኤ ወቅት ከመቃብር
የተነሱ ሁሉ ግን የተነሱት ለዘላለም ህይወት ነው። እርሱ በሞትና መቃብር
ላይ ለተቀዳጀው ድል እንደ ዋንጫ ሽልማት ሆነው ከእርሱ ጋር አርገዋል…
ወደ ከተማይቱ በመግባት ክርስቶስን ከሞት እንደተነሳና እነርሱም አብረውት
እንደተነሱ በማወጁ ለብዙዎች ታዩ። በዚህም ቅዱስ የሆነው የትንሳኤ እውነት
ህይወት ዘራ።” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገፅ 786
በሰውኛ አነጋገር ሊቀ ካህናት እና ሽማግሌዎች የተሻለ ብልጫ ነበራቸው።
ሃይማኖታዊ ሃይል ከላይ ሆነው ስለተቆናጠጡ የሮም ባለሥልጣናትን
ለማሳመንና ብዙ ህዝብ የነርሱን ሃሳብ እንዲደግፍ ማድረግ ችለዋል። ነገር
ግን የዘነጉት ነገር አለ “ልዑሉ በሰዎች መንግስት ሁሉ ላይ ሙሉ ስልጣን
እንዳለውና እነዚህንም መንግስታት ለወደደው እንደሚሰጥ” ነበር(ዳን 4፡
32)። የሃሰት ትርክታቸው በነዛ ከሞት በተነሱ ቅዱሳን መኖር ምክንያት
ፈራረሰ፤ ዋጋ ቢስም ሆኖ ቀረ።
ምንም ያክል መጥፎ ነገሮች ቢገጥመን በዚህ በወደቀ አለም ውስጥ
አሁንም እየተጋደልን ብንሆን እግዚአብሔር ለኛ በተቀዳጀው ድል
ላይ መተማመን የምንችለው እንዴት ነው?
ዮሐ. 20፡11-29 እና 1 ቆሮ. 15፡5-8ን ያንብቡ። የተነሳውን ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሲያገኙ ምን አይነት ምላሽ ሰጡ?
በባዶ መቃብሩ አካባቢ የነበሩት ሁለቱ መላዕክት ለመቅደላዊት ማርያም እና
ለሌሎችም ሴቶች ኢየሱስ እንደተነሳ ነገሯቸው (ማቴ. 28፡1፤ 5-7፤ ማር. 16፡
1-7፤ ሉቃስ 23፡55፤ ሉቃስ 24፡1-11)። ወዲያውም ኢየሱስ ራሱ ለነርሱ ታያቸው
እነርሱም ሰገዱለት (ማቴ. 28፡1፤ 910፤ ዮሐ. 20፡14-18)። ለጴጥሮስም ታየው
(ሉቃስ 24፡34፤ 1ቆሮ. 15፡5)። ወደ ኤማሁስ ለሚሄዱ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት
በሚያናግራቸው ጊዜም ልቦቻችው ይቃጠልባቸው ነበር (ማር. 16፡12፤ ሉቃስ
24፡13-35)። ኢየሱስ ወደ ላይኛው ክፍል በመጣ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ደቀ
መዛሙርቱ ደንግጠው እና ፈርተው በኋላ ግን በሃሴት ተሞልተውና በሆነው
ነገር ተደንቀው ነበር (ሉቃስ 24፡33-49፤ ዮሐ. 20፡19-23)። ከአንድ ሳምንት
በኋላ የሱስ በር ሳይከፍት ወደዚሁ ክፍል መጣ፤ ቶማስም እንኳን ሳይቀር
በትንሳኤው አመነ (ዮሐ. 20፡24-29)።
በትንሳኤው እና ወደላይ በማረጉ መካከል በነበሩት አርባ ቀናት ኢየሱስ
“ከአምስት መቶ በላይ ለሚሆኑ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ” (1ቆሮ. 15፡6)፤
ለያዕቆብም ታየ (1ቆሮ. 15፡7)። ኢየሱስ በገሊላ ባህር ዳርቻ ከነበሩት ደቀ
መዛርት ጋር ተቀላቅሎ አብሯቸው ቁርስ በላ፤ ከዛም ከጴጥሮስ ጋር ተነጋገረ
(ዮሐ. 21፡1-23)። ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት (ሉቃስ 24፡50-53፤ ሐዋ. 1፡1-11)
ኢየሱስ የታየባቸው ሌሎች ክስተቶች ሊኖሩ ይችላሉ (ሐዋ. 1፡3)። ጳውሎስም
በደማስቆ መንገድ ላይ ስተገናኘው ራሱን የሚቆጥረው የክርስቶስ ትንሳኤ
የአይን እማኝ አድርጎ ነው (1ቆሮ. 15፡8ን ከሐዋ. 9፡1-9 ጋር ያነጻጽሩ)።
ሌሎች ደቀ መዛርት በሰአቱ አብሯቸው ላልነበረው ቶማስ የተነሳውን ጌታ
እንዳዩት ሲነግሩት “በሚስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ
ሚስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ጣቴን ካላደረግሁ፤ በጎኑም እጄን ካለስገባሁ
አላምንም” (ዮሐ. 20፡25) ብሎ መለሰ። ከሳምንት በኋላ ኢየሱስ በድጋሚ
ለደቀመዛሙርቱ ሲታያቸው ቶማስ በዚህ ጊዜ አብሯቸው ነበር። ኢየሱስም
“ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤
ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።” አለው (ዮሐ. 20፡27)። ከዛም ቶማስ
እንዲህ ሲል ተናዘዘ “ጌታዬ፤ አምላኬም!” ኢየሱስም እንዲህ አለው “ቶማስ
አንተ ስላየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው” (ዮሐ. 20፡29)።
“ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው።” ከሞት የተነሳውን ክርስቶስ
ባይኖቻችሁ ባታዩም በኢየሱስ ላይ እንድትተማመኑ የሚያደርጓችሁ
ምን ሌሎች ምክንያቶች አሉ?
በዘዳ. 26፡1-11 ብርሃን 1 ቆሮ. 15፡20ን ያንብቡ። ጳውሎስ ከሞት የተነሳው ኢየሱስን “ላንቀላፉት በኩራት” ነው ብሎ የገለፀው ከምን አንፃር ነው?
በጥንታዊ የእስራኤላውያን የግብርና ልምምድ ውስጥ “በኩራቱን” መስጠት
ጥልቅ ሃይማኖታዊ መልዕክት ነበረው። እግዚአብሔር ምድሪቱ ሰብልን
በማብቀል ለአጨዳ ዝግጁ እንድትሆን በማድረግ ለታመኑ መጋቢዎች
በቸርነቱ ስለሰጠ ለእግዚአብሔር እውቅና የመስጫ የከበረ አገልግሎት ነው
(ዘፀ. 23፡19፤ ዘፀ. 34፡26፤ ዘሌ. 2፡11-26፤ ዘዳ. 26፡1-11)። የበኩራቱ ፍሬ
መከሩ መጀመሩን ብቻ ሳይሆን የምርቱንም የጥራት ደረጃ የሚገልጥ ነው።
ዋይኒ ግሩደም እንደሚለው “ክርስቶስን “በኩራት” ብሎ ሲጠራው ጳውሎስ
የግብርናን ዘይቤያዊ ንግግር የተጠቀመው እኛም ልክ እንደ ክርስቶስ
እንደምንሆን ለመግለፅ ነው። ልክ የፍሬው በኩራት ጣዕም የተቀረውን መከር
ምን አይነት ጣዕም እንደሚኖረው የሚያመለክት እንደሆነ ሁሉ ክርስቶስም
“በኩር” ሆኖ አካላችን በትንሳኤ ጊዜም ልክ እንደዚሁ እንደሚመስልና
እግዚአብሔር በመጨረሻ ጊዜ መከሩን በሚሰበሰብበት ወቅት ከሞት
እንደሚያስነሳንና ወደርሱ መገኘት እንደሚሰበስበን ያሳየናል።” Wayne
Grudem, Systematic Theology (Grand Rapids, MI: ZonderVan,
1994), p. 615.
ኢየሱስ ከመቃብር የተነሳው የከበረ የሰው ልጅ አካልን ይዞ ቢሆንም ሲሰቀል
የነበረውን ጠባሳ ይዞ እንደተነሳ ሊታወስ ይገባል (ዮሐ. 20፡20፣ 27)። ይህ
ማለት ታዲያ ከሞት የተነሱ የእግዚአብሔር ልጆች ስቃያቸውን የሚገልጽ
አካላዊ ምልክት ይታይባቸዋል ማለት ነው? ከጳውሎስ አንጻር ነገሩን ስንቃኘው
ደግሞ በከበረ አካሉ ላይ “የስጋ መውጊያውን” ተሸክሞ (2ቆሮ. 12፡7) ወይንም
“የየሱስን ማህተም” ይዞ ይነሳል ማለት ነው (ገላ. 6፡17)?
ጳውሎስ እስከ ሞቱ ቀን ድረስ “የክርስቶስ ክብር ምልክት የሆነውን በሰማያዊ
ብርሃን አይኖቹ የታወሩበትን ክስተት አሻራ ተሸክሞ ኖሯል (ሐዋ. 9፡1-9)”
Ellen G. White, the story of redemption, p. 275። ይህ ማለት ግን
እርሱ ሆነ የተዋጁት በሙሉ በክብር ሲነሱ ከስቃይ ምልክቶቻቸው ጋር ይነሳሉ
ማለት አይደለም (ከ1ቆሮ. 15፡50-54 ጋር ያነፃፅሩ)። ከክርስቶስ አንፃር ስናየው
ደግሞ “የደረሰበትን ጭካኔ ምልክት ሁልጊዜም ተሸክሞ ይኖራል። የእያንዳንዱ
ሚስማር አሻራ ስለ ሰው ልጅ አስደናቂ መዳን እና ስለተገዛበት የከበረ ዋጋ
ይነግረናል።” ኤለን ኋይት፣ ቀደምት ፅሁፎች፣ p. 197። የርሱ ጠባሳዎች የኛ
የሁላችን ጠባሳዎች ለዘላለም እንደሚጠፉ ማስተማመኛ ናቸው።
ክርስቶስ የተሰቀለበት ጠባሳ ለዘላለም አብሮት ይኖራል። ይህ
እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር እና እኛን ለማዳን ምን ያክል
ዋጋ እንደሚያስከፍል የሚገልፅልን እንዴት ነው? ስላሴ እኛን
ለማዳን ምን ያክል ዋጋ እንዳወጣብን የሚያሳየን በምን መልኩ
ነው?
:- የዘመናት ምኞት ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ “በዮሴፍ
መቃብር ውስጥ”፣ “ጌታ ተነስቷል”፣ “ለምን ታለቅሻለሽ?”፣ “ጉዞ ወደ
ኤማሁስ”ና “ሠላም ለናንተ ይሁን” የሚል ርዕስ ያላቸውን ምዕራፎች ያንብቡ።
ዘመናዊው አለም እንደ ክርስቶስ ትንሳኤ በመሳሰሉት ነገሮች ላይ እምነት
የለውም። ሆኖም ይህንን የትንሳኤ እውነታ መቀበል የሚቸገሩት እንኳን
ከታሪካዊ ማስረጃዎች የተነሳ ማለትም ብዙ ሰዎች የተነሳውን ኢየሱስ
ማየት ስለቻሉ እነርሱም ሊያምኑ በቅተዋል። ስለዚህ የትንሳኤው ተቃዋሚ
ፅሁፎች የተነሳውን ክርስቶስ አይተናል የሚሉትን ብዙ ሰዎች እንደዚያ ብለው
እንዲያምኑ ያደረጋቸውን ነገር ለማብራራት በመሞከር ላይ ያተኮሩ ናቸው።
አንዳንዶች እንደሚሞግቱት ሁሉም ደቀዛሙርቱ ኢየሱስ ተነስቷል ብለው
በምናቦቻቸው የፈጠሩት መሰረተ ቢስ የሆነ ስዕል ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ
ኢየሱስ አልሞተም፤ ከመስቀል ላይ ከወረደ በኋላ ራሱን ስቶ ወደቀ፤ ከዛም
ተመልሶ ነቃና ህያው ሆነ፤ ከዛም ሲታያቸው ተከታዮቹ ከሞት ተነስቷል
ብለው አሰቡ ይላሉ። አመናችሁም አላመናችሁም አንዳንዶች ደግሞ ደቀ
መዛሙርቱ የተነሳው ክርስቶስ ነው ብለው በስህተት ያዩት የኢየሱስን መንታ
ወንድም ነው ብለው ይሞግታሉ። በሌላ አባባል ለክርስቶስ መነሳት ታሪካዊ
ማስረጃዎች ጠንካራ ሆነው ቢቀርቡም ይህንን ነገር ለማጥፋት ሲሉ ሰዎች
የተለያዩ የመከራከሪያ ሃሳቦችን ያዘጋጃሉ። ትንሳኤው ራሱ በጣም አስፈላጊ
ስለሆነ እንድናምንበት በተሰጡን አሳማኝ ምክንያቶች ላይ እምብዛም ልንደነቅ
አይገባንም።
“ “ተፈፀመ” ተብሎ ከመስቀል ላይ የተነገረው የጩኸት ቃል ለሙታን ተሰማ።
ከድንጋይ የተዋቀሩትን መቃብሮች በስቶ ያንቀላፉት እንዲነሱ ጠራቸው።
ስለዚህ የክርስቶስ ድምጽ ከላይ ከሰማይ ሲሰማ ይኸው ይሆናል። ያ ድምጽ
መቃብሮችን ሰርጎ ገብቶ፣ የቀብር ሳጥኖችንም ይከፋፍታል፤ በክርስቶስ አምነው
የሞቱትም ይነሳሉ። ክርስቶስን ከሞት ያስነሳው ያ ሃይል ቤተክርስቲያቱን
አስነስቶና ከራሱ ጋር አክብሮ በዚህ አለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣው አለም
ከስልጣናት፣ ከሃይላትና ከተሰየሙ ስያሜዎች በላይ ያደርጋታል።” ኤለን ጂ.
ኋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ገፅ 787.
:
1.“ተፈፀመ” (ዮሐ. 19፡30) እና “ተነስቷል” (ማቴ. 28፡6)
ሁለቱ ከፍ ያለ ትርጉም ያላቸው አባባሎች ናቸው። በድነት ታሪክ
ውስጥ እርስ በርሳቸው የሚመጋገቡት እንዴት ነው? በእነዚህ
ቃላት ውስጥ የምናገኘው ታላቅ ተስፋ ምንድነው?
2.የየሱስ ደቀ መዛሙርት መቃብሩን እንዳይሰርቁ ለማድረግ
የሃይማኖት መሪዎች መጀመሪያ ጠባቂዎችን አቆሙ። በኋላ
ደግሞ ጠባቂዎቹ ደቀ መዛሙርቱ ሰረቁት ብለው እንዲናገሩ
ክፍያ ከፈሏቸው። ይህ ነገር ስለ ክርስቶስ ባዶ መቃብር እውነታ
እንድንረዳ የሚያደርገን እንዴት ነው? ለክርስቲያኖች የባዶ
መቃብሩ አስፈላጊነት ምን ያክል ነው?