የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዮሐ. ራዕይ 13፡8፣ ማቴ. 17፡22-23፣ ማርቆስ 9፡30-32፣ ዮሐንስ 19፡1-30፣ ሮሜ 6፡ 23፣ 1 ቆሮ. 1፡18-24።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል፡፡” (ዮሐ. 3፡14-15)
ከ
ሞትና ከግብር ማምለጥ አይቻልም ተብሎ ይነገራል። ያ ሙሉ በሙሉ
እውነት አይደለም። ሰዎች ከግብር መራቅ ይችላሉ፤ ግን ሞትን
አያመልጡም። ለጥቂት አመታት ሞትን ማስወገድ ይችሉ ይሆናል፤
ሆኖም ይዋል ይደር እንጂ ሞት መምጣቱ አይቀርም። በህይወት የሌሉ
ጻድቃንም ሆኑ ኃጥአን በመጀመሪያ አንድ ቦታ ላይ እንደሚገኙ ስለምናውቅ
የትንሣኤ ተስፋችን ለእኛ ሁሉም ነገራችን ነው። ጳውሎስ እንደተናገረው
ያለዚህ ተስፋ “በክርስቶስ ያንቀላፉት ደግሞ ጠፍተዋል” (1 ቆሮ. 15:18)።
ስለዚህ፣ የክርስቶስ ትንሳኤ የእምነታችን ማዕከል ነው፤ ምክንያቱም በርሱ
ትንሣኤ እኛ ዋስትና አለን። ነገር ግን ክርስቶስ ከሙታን ከመነሳቱ በፊት እርሱ
በእርግጥ መሞት ነበረበት። በጌቴሴማኒ ስቃይ ውስጥ፣ ሞቱን ሲጠብቅ፣
“አሁን ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ነገር
ግን ለዚህ ዓላማ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ።” (ዮሐንስ 12:27) ያለው ለዚህ ነው።
እናም ያ አላማ መሞት ነበር።
በዚህ ሳምንት በክርስቶስ ሞት እና መሞቱም በዘላለም ህይወት ተስፋችን ላይ
ባለው አንድምታ ዙሪያ እንወያያለን።
*ለጥቅምት 26 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
ራእይ 13:8፣ የሐዋርያት ሥራ 2:23ን እና 1 ጴጥሮስ 1:19-20ን ያንብቡ። ክርስቶስ “ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እንደታረደ” እንዴት ሊቆጠር ይችላል?
“ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በታረደው በግ የሕይወት መጽሐፍ ላይ ስሞቻቸው
ያልተጻፈ የምድር ሰዎች ሁሉ ለአውሬው ይሰግዳሉ።”
(ራእ. 13፡8)። እዚህ ጋር ለእኛ ወሳኝ የሆነው የክርስቶስ “ዓለም ከተፈጠረበት
ጊዜ ጀምሮ ታርዷል” የሚለው ኃሳብ ነው። ይህንን እንደ ምሳሌያዊ አገላለፅ
ልንረዳው ይገባል (የራዕይ መጽሐፍ በምልክቶች የተሞላ ስለሆነ)፤ ምክንያቱም
ክርስቶስ የተሰቀለው ምድር ከተፈጠረች በሺዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በኋላ
ነው። ይህ ጥቅስ የሚናገረው የመዳን እቅድ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ተዘጋጅቶ
እንደነበር ነው። የዚያ እቅድ ማዕከል ደግሞ የእግዚአብሔር በግ የሆነው
ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት ነው።
ቲቶ 1:2ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ የክርስቶስን ሞት ያማከለው
የመዳን እቅድ ከስንት ጊዜ በፊት እንደታቀደ ምን ይነግረናል?
“እኛን የመቤዠት እቅድ ከአዳም ውድቀት በኋላ የተነደፈ የኋላ ሐሳብ
አልነበረም። . . . ነገር ግን ከጥንተ ዓለም ጀምሮ የእግዚአብሔር ዙፋን መሠረት
የሆኑት መሠረታዊ መርሆች መገለጥ ነበር።”—ኤለን ጂ. ኋይት ፣ የዘመናት
ምኞት ፣ ገጽ. 22.
ያ እቅድ በመጀመሪያ ለአዳምና ለሔዋን የተገለጠው በኤደን ገነት ነበር (ዘፍ.
3፡15፣21)፤ እናም በብሉይ ኪዳን ዘመናት ሲቀርቡ የነበሩት የደም መስዋዕቶች
ሁሉ ሲያመላክቱት ቆይተዋል። ለምሳሌ፣ የአብርሃምን እምነት ሲፈትን፣
እግዚአብሔር በይስሐቅ ፈንታ የሚሠዋውን በግ አዘጋጀ (ዘፍ. 22፡11–13)።
ይህ ምትክነት የክርስቶስ በመስቀል ላይ የኃጢአት ክፍያ መስዋዕትነትን
የምትክነት ባህሪ በግልፅ ያሳያል።
ስለዚህ፣ በመዳን አጠቃላይ ዕቅድ ማዕከል የሆነው ለዘመናት በእንስሳት
መስዋዕቶች የተመሰለው ‘’የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር
በግ” የሆነው የኢየሱስ በኛ ምትክ መሞቱ ነው(ዮሐንስ 1:29)።
የእንስሳት መሥዋዕት አሰቃቂ እና ደም አፋሳሽ መሆናቸው እውነት
ነው። ነገር ግን ይህ አስፈሪነት እና ደም መፋሰስ በእኛ ምትክ
ስለሆነው የክርስቶስ ሞት እና የኃጢአት ዋጋ ምን ያስተምረናል?
ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ስለ ራሱ መከራና ሞት ለተናገረው ትንቢት ምን ምላሽ ሰጡ? ይህ ምላሻቸው ቃሉን በስህተት ስለመረዳት አደጋ ምን ያስተምረናል? ማቴ. 16፡21–23
ማቴ. 17:22-23፣ ማርቆስ 9:30–32፣ ሉቃስ 9:44-45
ሉቃስ 18፡31-34
ኢየሱስ የተወለደው ለመሞት ነበር፤ ለመሞትም ኖረ። እያንዳንዷ
እርምጃው በቀራንዮ መስቀል ላይ ወዳለው ታላቅ የስርየት መስዋዕትነት
አቀረበው። ተልእኮውን ሙሉ በሙሉ በመገንዘብ ማንም ወይም ምንም ነገር
እንዲያዘናጋው አልፈቀደም። በእውነትም “ሙሉ ሕይወቱ በመስቀል ላይ
ለመሞቱ መንደርደሪያ ነበር።”—ኤለን ጂ. ኋይት፣ የክርስቲያን ትምህርት
መሠረታዊ ነገሮች፣ ገጽ. 382.
ኢየሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ በመጨረሻው ዓመት፣ ስለሚመጣው ሞቱ
ለደቀ መዛሙርቱ ይበልጥ ግልጽ በሆነ መንገድ ነግሯቸው ነበር። ነገር ግን
የነገራቸውን እውነታ ለመቀበል የማይችሉ እና የማይፈልጉ ይመስሉ ነበር።
የመሲሑን ሚና በተመለከተ በተሳሳቱ ሐሳቦች ተሞልተው የእርሱን ሞት
ሊጠብቁ አልቻሉም። ባጭሩ የነሱ የተሳሳተ መረዳት ለአላስፈላጊ ስቃይ
ዳርጓቸዋል።
አስቀድሞ ለኒቆዲሞስ፣ ኢየሱስ “ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ
እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ
እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል” (ዮሐ. 14፣15) ኢየሱስ በቂሳርያ
ፊልጵስዩስ እያለ ለደቀ መዛሙርቱ “ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ ከሽማግሎችና
ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ተቀብሎ መገደል በሦስተኛውም ቀን
መነሳት’ እንዳለበት ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው። (ማቴ. 16:21) ፣ አኪጄቪ)
በገሊላ በኩል ብቻውን አልፎ (ማርቆስ 9፡30–32) እና ወደ ኢየሩሳሌም
በመጨረሻው ጉዞው (ሉቃስ 18፡31–34) ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በድጋሚ
ስለ ሞቱ እና ትንሳኤው ተናገረ። ምክንያቱም እነሱ መስማት የሚፈልጉት ነገር
አልነበረም, እነሱ አልሰሙም. ለእኛ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ እንዴት ቀላል
ነው.
ሰዎች፣በተለይም በእግዚአብሔር የተመረጡ ሰዎች፣ የመሲሑን
የመጀመሪያ ምጽዓት በተመለከተ የተሳሳተ ፅንሰ-ሀሳብ ነበራቸው። ዛሬ
የኢየሱስን ዳግም ምጽአት በተመለከተ አንዳንድ የተሳሳቱ ፅንሰ-ሀሳቦች
ምንድን ናቸው?
የዮሐንስ 19:1-30ን ያንብቡ። ኢየሱስ “ተፈጸመ” ማለቱ ለእኛ ያለው ወሳኝ መልእክት ምንድን ነው?
በመጨረሻም፣ ለክርስቶስ፣ ለሰው ልጅ እና ለመላው አጽናፈ ሰማይ ወሳኙ ጊዜ
ደረሰ። በጥልቅ ስቃይ ከጨለማ ኃይሎች ጋር ታገለ። ቀስ ብሎ ከጌትሴማኒ
የአትክልት ስፍራ፣ ፍትሃዊ ባልሆነ የፍርድ ሂደት አልፎ ወደ ቀራኒዮ ተራራ
ደረሰ። እርኩስ መላእክት እሱን ለማሸነፍ እየሞከሩ ነበር። ኢየሱስ በመስቀል
ላይ ተሰቅሎ ሳለ የካህናት አለቆች፣ ጻፎችና ሽማግሌዎች፣ “ሌሎችን አዳነ፤
ራሱን ሊያድን አይችልም። የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤
እኛም እናምንበታለን።” (ማቴ. 27፡42) በማለት አፌዙበት።
ክርስቶስ ከመስቀል ወርዶ ራሱን ማዳን ይችል ነበር? አዎ፣ ይችል ነበር፤ ነገር
ግን ፈቃደኛ አልሆነም። እነዚያን ፌዘኞች ጨምሮ ለሰው ዘር ሁሉ ያለው ፍቅር
ተስፋ እንዲቆርጥ አልፈቀደለትም። በእውነቱ፣ “ሊያድናቸው ከሞተላቸው
መካከል ፌዘኞቹም ነበሩበት። ከመስቀል ወርዶ ራሱን ማዳን አልቻለም፤
ምክንያቱም የተያዘው በሚስማሮቹ ሳይሆን እነርሱን ለማዳን በነበረው ፈቃድ
ስለነበር ነው።”— Alfred Plummer, An Exegetical Commentary on
the Gospel According to S. Matthew (London: Elliot Stock, 1910),
p. 397.
ምንም እንኳን የይሁዳን ክህደት ጨምሮ ወደ መስቀሉ የሚያመሩትን ክስተቶች
ያነሳሳው ሰይጣን ቢሆንም (ዮሐንስ 6፡70፤ ዮሐንስ 13፡2፣ 27) በስቃዩ
ክርስቶስ የሰይጣንን መንግስት እያሸነፈ ነበር። “ወንጌላዊው ባይገልፀውም
የኢየሱስ ሞት የሰይጣን ድርጊትና ኢየሱስ በሰይጣን ላይ ድል የተቀዳጀበት
ድርጊት ነው።”— George E. Ladd, A Theology of the New Testament, rev. ed. (Cambridge, UK; Lutterworth Press, 1994), p. 192.
ከመስቀል ላይ ሆኖ “ተፈጸመ” ብሎ ሲጮህ(ዮሐ. 19፡30) ስቃዩ ማብቃቱን
ብቻ ሳይሆን በተለይም ከሰይጣንና ከክፉ ኃይላት ጋር በተደረገው ታላቅ
ታሪካዊ ተጋድሎ የክፉው ኃይላትን እንዳሸነፈ እየተናገረ ነበር። . “ሰማይ ሁሉ
በአዳኙ ድል አሸንፏል። ሰይጣን ተሸነፈ፤ ግዛቱም እንደጠፋ አወቀ።” ኤለን ጂ.
ኋይት፣ The Desire of Ages፣ ገጽ. 758.
እዚህ ላይ አስደናቂውን ንፅፅር ለመረዳት አስቸጋሪ ነው፡- የእግዚአብሔር ልጅ
እጅግ በተዋረደ መንገድ፣ ለእኛ እና ለአጽናፈ ሰማይ፣ ትልቅ እና እጅግ የከበረ
ድል ተቀዳጀ።
ለማስተሰረይ የክርስቶስን ሞት መጠየቁ ኃጢአት ምን ያህል
መጥፎ እንደሆነ ያሰላስሉ። በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ለማግኘት
ሥራችን ምን ያህል ከንቱ እንደሆነ ይህ እውነት ምን ያስተምረናል?
ደግሞስ ክርስቶስ ባደረገልን ነገር ላይ ለመጨመር ምን እናድርግ?
መልስዎን ወደ ሰንበት ክፍልዎ ያምጡ።
ዮሐንስ 3፡14–18 እና ሮሜ 6፡23ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች የክርስቶስ ሞት ስላከናወነልን ነገር ምን ያስተምራሉ?
ኢየሱስ ሊጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በደረሰ ጊዜ፣ መጥምቁ ዮሐንስ፣ “እነሆ!
የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ!’ (ዮሐ. 1፡29) ብሎ
ጮኸ። ይህ አረፍተ ነገር ክርስቶስ የብሉይ ኪዳን እውነተኛ መስዋዕቶች ሁሉ
ያመለከቱት የእግዚአብሔር በግ መሆኑን ያረጋገጠ ነው።
ነገር ግን የእንስሳት መሥዋዕት በራሳቸው ኃጢአትን ሊያስወግዱ አይችሉም
ነበር (ዕብ. 10፡4)። በክርስቶስ የወደፊት የመስቀል ላይ መስዋዕትነት
ውጤታማነት ላይ የተመሰረተ ይቅርታን ብቻ ሰጥተዋል። “በኃጢአታችን
ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ
ነው” (1ኛ ዮሐንስ 1፡9)።
ዮሐንስ 3:16-17ን ያንብቡ። በተለይ ባደረግነው ነገር ልንኮነን
እንደሚገባን ስንገነዘብ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ተስፋ ልናገኝ
እንችላለን?
ይህ ሁሉ ምን ማለት እንደሆነ ያሰላስሉ። ዓለማትን የፈጠረው ኢየሱስ
(ዮሐንስ 1፡1-3) ልንኮነን ሲገባን እንዳንኮነን ስለ እያንዳንዳችን ኃጢአት ራሱን
መስዋዕት አድርጎ አቀረበ። ይህ ታላቅ የወንጌሉ የተስፋ ቃል ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ እንዲሞት “እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ
ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል” በማለት ተናግሯል (ዮሐ. 3:16)። ነገር ግን
ክርስቶስ ስለ እኛ በፈቃዱ ራሱን እንዳቀረበም መዘንጋት የለብንም (ዕብ. 9፡
14)። ሉተር መስቀሉን “በልቡ ውስጥ በተቃጠለው ወሰን አልባ የፍቅር እሳት
ሕያውና ቅዱስ የሆነውን ሥጋውንና ደሙን መሥዋዕት አድርጎ በምልጃ፣
በህመምና በጩኸት(ዕብ. 5:7) ለአብ ያቀረበበት መሠዊያ” ብሎ Luther’s
Works, vol. 13 (St. Louis, MO: Concordia Publishing House, 1956),
p. 319:: ክርስቶስ አንድ ጊዜ ለሁሉ ሞተ (ዕብ. 10፡10) ላያዳግም ለዘላለም
(ዕብ. 10፡12) ራሱን አቀረበ፤ መስዋዕቱ በቂ ስለሆነ ኃይሉን አያጣም።
ደግሞም “አንድ ነፍስ ብቻ የጸጋውን ወንጌል የምትቀበል ብትሆን እንኳን ኖሮ፣
ክርስቶስ ያንን ሰው ለማዳን፣ የድካም እና የውርደት ህይወቱን እና የውርደትን
ሞት ይመርጥ ነበር።” Ellen G. White, The Ministry of Healing, p. 135
“ዓለም” እና “ሁሉ” በሚሉት ቃላት ምትክ የራሳችንን ስም
በመተካት ዮሐንስ 3:16ን እንደገና እናንብበው። በተለይም
ኃጢአት ለመሥራት ስንፈተን ይህን አስደናቂ የተስፋ ቃል
በየሰዓቱ የራሳችን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
1 ቆሮንቶስ 1:18–24ን ያንብቡ። ጳውሎስ ስለ መስቀሉ ምን እየተናገረ ነው? ይህንንስ ‘ከዓለም ጥበብ’ ጋር ያነፃፀረው እንዴት ነው? “ቁሳዊነት” (እውነታው ሁሉ ቁስ ብቻ ነው የሚለው ሃሳብ፣ ይህም ማለት አምላክ የለም ወይም ከተፈጥሮ በላይ የሆነ የሕልውና ዓለም የለም ብሎ የሚያምን እምነት) “የዓለምን ጥበብ” በተቆጣጠረበት በዚህ ዘመንም ቢሆን የመስቀሉ መልእክት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
የክርስቶስ መስቀል የመዳን ታሪክ ማዕከል ነው። “ዘላለም የሚባለው ጊዜ
በቀራንዮ መስቀል ላይ የተገለጠውን የፍቅር ጥልቀት ፈጽሞ ሊመረምር
አይችልም። ወሰን የሌለው የክርስቶስ ፍቅር እና ወሰን የለሽ የሰይጣን ራስ
ወዳድነት ፊት ለፊት የቆሙት እዚያ ነበር።”— Stephen N. Haskell, The
Cross and Its Shadow (South Lancaster, MA: Bible Training School,
1914)
ክርስቶስ በትህትና ራሱን ለሰው ዘር ቤዛ አድርጎ በማቅረብ ላይ ሳለ፣ ሰይጣን
በራስ ወዳድነት ክርስቶስን በመከራና በስቃይ እያንገላታው ነበር። ክርስቶስ
የሞተው እያንዳንዱ ሰው ሊገጥመው የሚገባውን የተፈጥሮ ሞት ብቻ
አይደለም። እርሱን የሚቀበሉት ሁሉ ለራሳቸው ፈጽሞ እንዳይለማመዱ እርሱ
የሞተው ሁለተኛውን ሞት ነው።
የመስቀልን ትርጉም በተመለከተ ልናስታውሳቸው የሚገቡ በርካታ ጠቃሚ
ጉዳዮች አሉ። በመጀመሪያ፣ መስቀል በኃጢአት ላይ ያለው የእግዚአብሔር
ፍትህ ከፍተኛ መገለጥ ነው (ሮሜ. 3፡21-26)። ሁለተኛ፣ መስቀል
የእግዚአብሔር ለኃጢአተኞች ያለው ፍቅር ከፍተኛ መገለጥ ነው (ሮሜ. 5፡
8)። ሦስተኛ፣ መስቀል የኃጢአትን ሰንሰለት ለመስበር ታላቅ የኃይል ምንጭ
ነው (ሮሜ. 6፡22፣ 23፤ 1 ቆሮ. 1፡17–24)። አራተኛ፣ መስቀል ብቸኛው
የዘላለም ሕይወት ተስፋችን ነው (ፊልጵ. 3፡9–11፤ ዮሐ. 3፡14–16፤ 1 ዮሐንስ
5፡11፣ 12)። እና አምስተኛ፣ መስቀል በዓለማት ውስጥ ወደፊት ሊመጣ ለሚችል
አመጽ ብቸኛው ቅድመ-መፍትሄ ነው (ራዕ. 7፡13–17፣ ራዕ. 22፡3)።
ስለ መስቀሉ ካሉት ወሳኝ እውነቶች መካከል አንዳቸውም “በዓለም ጥበብ”
ሊገኙ አይችሉም። በተቃራኒው አሁንም እንደ ያን ጊዜው፣ የመስቀሉ ስብከት
ለዓለማዊ ጥበብ “ሞኝነት” ነው፣ ይህም ብዙውን ጊዜ ፈጣሪ ስለመኖሩ ያለውን
በጣም ግልጽ እውነት እንኳ የማይቀበል (ሮሜ. 1፡18-20ን ይመልከቱ) ነው::
“ሞኝነት” የሚለው የግሪክ ቃል “ሞሮን(እብድ)” ከሚለው የእንግሊዝኛ ቃል
ጋር የተቆራኘ ነው። ማለትም መስቀሉን መስበክ “በዓለም ጥበብ” መሠረት
“ማበድ” ነው። ዓለማዊ ጥበብ ኢየሱስን ወይም በኛ ፈንታ በመስቀል ላይ
በመሞት የሰጠንን መዳን ሊያውቅ አይችልም።
አንዳንድ “ዓለማዊ ጥበብ” ምንም ያህል ቢጠቅመን ስለ ኢየሱስ
የምናምነውን ነገርና “በስብከት ሞኝነት” (1 ቆሮ. 1:21)
የተቀበልነውን ተስፋ እንዲያስተጓጉል መፍቀድ የማይኖርብን
ለምንድን ነው?
:
የዘመናት ምኞት ከሚለው መጽሀፍ “ጌትሰማኔ”ና
“ቀራንዮ” የሚል ርዕስ ያላቸውን ምዕራፎች ያንብቡ። እንዲሁም ወደ ክርስቶስ
የሚመራ መንገድ ከሚለው መጽሐፍ ላይ “ንስሐ” የሚል ርዕስ ያለውን
ምዕራፍ ያንብቡ።
“መላው ሰማይ ስለመዳናችን ጉዳይ በትኩረት እንደሚከታተል አየሁ፤ ታድያ
እኛ ግዴለሽ መሆን ይኖርብናል? መዳን ወይም መጥፋታችን ትንሽ ነገር ይመስል
ቸልተኞች እንሁን? የተከፈለልንን መስዋዕትነት እናቃልል? አንዳንዶች ይህን
አድርገዋል፤ ምሕረትን አቃልለዋል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በእነርሱ ላይ
ሆኗል። የእግዚአብሔር መንፈስ ሁልጊዜ እያዘነ አይኖርም።
ብዙ ካዘነ ጥሎ
ይሄዳል። አምላክ ሰዎችን ለማዳን ሊያደርግ የሚችለውን ሁሉ ካደረገ በኋላ፣
ሰዎች በሕይወታቸው የኢየሱስን ምሕረት ካቃለሉ ሞት እጣቸው ይሆናል።
አስፈሪ ሞት ይሆናል፤ ምክንያቱም እነርሱ እምቢ ያሉትን ቤዛነት ሊያስገኝ
ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሰማው ሥቃይ ሊሰማቸው ስለሚገባ ነው። እናም
ያጡትን ነገር ይረዳሉ፡- የዘላለም ህይወት እና የማይሞት ርስትን። ነፍሳትን
ለማዳን የተከፈለው ታላቅ መስዋዕትነት የነፍሳትን ዋጋ ይገልፃል። ውድ
የሆነችው ህይወት አንዴ ስትጠፋ ለዘላለም ትጠፋለች።”—Ellen G. White፣
Testimonies for the Church፣ vol. 1, p. 124
:
1. ዕብራውያን 10፡4 “የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን
እንዲያስወግድ የማይቻል ነው” ይላል። ታዲያ በብሉይ ኪዳን
ዘመን ሰዎች እንዴት ነበር ይድኑ የነበረው? የስልክ የአየር ሰዓት
ከቴሌ ብድር ወስደው መጠቀምና በኋላ መክፈል ይህን ርዕሰ
ጉዳይ በተሻለ ለመረዳት የሚረዳን እንዴት ነው?
2. 2ኛ ቆሮንቶስ 5:18-21ን ያንብቡ። ክርስቶስ ለዓለሙ
ሁሉ ኃጢአት ከሞተ፣ ሰው ሁሉ ለምን አይድንም? በእነርሱ
ስም የተከፈለ ታላቅ መስዋዕትነት ቢኖርም ማን በመስቀሉ
እንደሚድንና እነማን እንደሚጠፉ ለመወሰን የግል ምርጫ ወሳኝ
ሚና የሚጫወተው ለምንድነው?
3. “ዓለማዊ ጥበብ” የሚያስተምራቸውና ለአምላክ “ሞኝነት”
የሆኑ ነገሮች ምን ምን ናቸው? አስደናቂው የአለም ዲዛይን እና
ውበት ሁሉ በድንገት በእድል የተከሰተ ነው የሚለው ሀሳብስ?
አጽናፈ ሰማይ ከምንም ውስጥ ድንገት ሆኗል የሚለውስ? ምን
ሌሎች ምሳሌዎችን ማሰብ ይችላሉ?
4. በማክሰኞ ጥናት ላይ የመጨረሻውን ጥያቄ ያሰላስሉ። መስቀሉ
እና እዚያ የሆነው ነገር፣ በሥራ የመዳንን ሐሳብ ከንቱ፣ በጣም
የተሳሳተ፣ እና ከመዳን ዕቅድ ጋር የሚጻረር የሚያደርገው እንዴት
ነው?