የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

በፈተና ውስጥ ከክርስቶስ ጋር


የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 3ኛ ሩብ ዓመት 2022

ከነሐሴ 7- 13

8ኛ ትምህርት

Aug 13 - Aug 19




የማይታየውን ማየት



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ሮሜ 8:2839, ዮሐ 14:1-14, ኤፌ 1:18-23, ኢሳ 40:27-31 ያንብቡ።


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “የንጉሱን ቁጣ ሳይፈራ የግብጽን አገር የተወው በእምነት ነው የማይታየውን እንደሚታይ አድርጎ ጸንቶአልና። (ዕብ 11:27)

በ ዕብራውያን መጸሐፍ ላይ ስለ እምነት የተሰጠው መግለጫ ሁልጊዜ ከባድ ነው። “እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።” (ዕን 11:1) ። በማናየው ነገር እንዴት እርግጠኛ እንሆናለን? ሆኖም ሙሴ በመታሰቢያ ጥቅሳችን የሚገልጽልን ይህንን ነው። “የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአልና።” (ዕብ 11:27) ። ‹‹የማይታየውን እንድናይ›› መጠራታችን ስንረዳ ደግሞ ነገሮች ጥሩ በሆኑ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በተለይም ነገሮች ወደ ከፋ ሁኔታ ሲያመሩብን የበለጠ ከባድ ይሆንብናል። ስለ እግዚአብሔር እና ስለ መንግስቱ ባለው እውነት ላይ የተመሰረተ የክርስቶስን የሚመስል እምነት ያስፈልገናል። ስለ አባታችን መልካምነትና እውነት፣ በኢየሱስ ስም ያለው ኃይል፣ የትንሳኤው ኃይል፣ እና ስለ እግዚአብሔር ርህራሄ የመሳሰሉት እውነቶች በፈተና ውስጥ በምንሆንበትና ሁሉንም ነገር መጠራጠር በምንጀምርበት ጊዜ የሚረዱን በጣም አስፈላጊ የሆኑ እውነቶች ናቸው። ሳምንቱን በአጭር እይታ: በከፉ ነገሮች ውስጥ እንኳ ብንሆን ጸንተን እንድንቆም የሚያስችሉን የትኞቹ የእግዚአብሔር እውነቶች ናቸው? *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 14 ሰንበት ያጥኑ።

ነሐሴ 8
August 14

የአባታችን አባካኝነት


“በትክክል እግዚአብሔር የሚወደን ቢሆን ኖሮ ለእኔ ይህንና ያንን ያደርግልኝ ነበር!” ይህ ዓይነት አስተሳሰብ ምን ያህል ጊዜ ይመላለስ እንደነበር ባውቅ ደስ ይለኛል። ያለንበትን ሁኔታዎች እናይና በእርግጥ እግዚአብሔር እኛን ይወደናል፣ ቢወደን ኖሮ ነገሮች እንዲህ ባልሆኑ ነበር እንላለን። የእግዚአብሔርን መልካምነት እንድንጠራጠር የሚያመሩ ሁለት ማሳመኛ የሚመስሉ ነገሮች አሉ። የመጀመሪያው፣ በአእምሮአችንና በልባችን ጥሩ ነው ብለን ላመንነው ነገር በልባችን ውስጥ የሚቃጠል ፍላጎት ሲኖር፣ እግዚአብሔር ለእኛ የሚፈልገው አንድ የተለየ ነገር ለእኛ አስቸጋሪ ይመስለናል። ሁለተኛ፣ የእኛ ህይወት ተሞክሮና የምናምነው ነገር ስለሚጋጭብን የእግዚአብሔርን መልካምነት እንጠራጠራለን። አንድ ነገር ጥሩ መስሎ ከታየ፣ጥሩ ስሜት ከፈጠረ፣ ጥሩ ጣዕም ካለው፣ አንድ ነገር ጥሩ ነው እንላለን። ስለዚህ ይህ መልም የመሰለንን ነገር ካላገኘን በእግዚአብሔር ላይ እንቆጣለን።

በዚህ ሁኔታ ላይ ነው አሁን እምነት ወደ ተግባር የሚመጣው። እምነት በተግባር የሚገለጸው የእግዚአብሔርን መልካምነት ለማጠናከር ልንፈተን በምንጀምርበት ጊዜ ነው። ሮሜ 8:28-39 ላይ ያለው ጥቅስ እግዚአብሔር ለእኛ ስላለው መልካምነት የሚናገር ኃይለኛ ጥቅስ ነው። በጥቅሶቹ ውስጥ ከጥርጥር አእምሮን ሊጠብቅ የሚችል ምን ነገር እናገኛለን



በሮሜ 8:32 ላይ ባጋጠሙን ነገሮች ላይ ተውጠን እንዳንቀር የሚጠቅመን በጣም አስፈላጊ የሆነ ለማሳመን የሚያስችል ሐሳብ እናገኛለን። “እግዚአብሔር ራሱን በሚያዋርድ እጅግ በከፋ ሁኔታ ዝቅ በማለት ልጁን ወደ ምድር በመላክ ሁሉንም ነገር ለእኛ በሚሆን መንገድ ካበጀው ፣ እርሱ ለእኛ ሲል በደስታ እና በነጻ ሊያደርግልን የማይችለው ነገር ይኖራልን?” እግዚአብሔር ልጁን ለእኛ እንዲሞት ወደ ምድር እንደ ላከው ካሰብን በኃላ ተመልሰን እንደ ተራ እና ዋጋ እንደሌለው ነገር ማየት የምንችለው እንዴት ነው?

ይህ ማለት እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ርህራሄ እውነታው፣ በክርስቶስ ሞት ከታየ፣ ከጥርጥሮቻችን ሁሉ በላቀ ሁኔታ ፈተና በአስተሳሰባችን እና በውስጣችን ትልቅ ተጽዕኖ ሊያሳድርብን ይገባል። የእግዚአብሔር መልካምነት ከጥርጥራችን በላይ ተጽዕኖ ሊያደርግብን የሚችለው እንዴት ነው በሚለው የተወሰነ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን በእርስዎ ፈንታ እንዲሞት ስለመስጠቱ እና ይህ ከግምት በላይ የሆነው ርህራሄው በተለያዩ ሺህ መንገዶች ዛሬም እንደሚቀጥል ተወያዩ። ይህ ስለ እምነት ምን ይናገራል?

ነሐሴ 9
August 15

በኢየሱስ ስም


“ምንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ” (ዮሐ 14:14)::

ከዚህ በኃላ ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ብዙ አይቆይም። ድጋፋቸውና መጽናናታቸው የሆነው ወደ ሰማይ ሊሄድ ነው፣ እናም ደቀመዛሙርት ግራ ሊጋቡና አቅመ-ቢስ መሆን ሊጀምሩ ነው። ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ በአካል ማየት ባይችሉም፣ ክርስቶስ የማይረሳ በጣም አስፈላጊ የሆነ ተስፋ ሰጥቷቸዋል።

ዮሐ 14፡1-14 ያለውን ያንብቡ። እንደ ቁጥር 13 እና 14፣ ኢየሱስ በስሙ የምንለምነውን ‹‹ማንኛውንም›› ነገር ሊያደርግልን ቃል ገብቶልናል። ከዚህ የተነሳ፣ሁልጊዜ በጻሎታችን መካከል ‹‹ በኢየሱስ ስም አሜን ›› የሚለውን እንጨምራለን።

ይህንን በምንልበት ጊዜ፣ ምን ማለት እንደሆነ ነው የምናስበው? እንዲህ ብለን እንድንጸልይ ሲያበረታታን ክርስቶስ ምን እያለን ነው? እርሱ ሊነግረን የፈለገውን ነጥብ ለማስተዋል እነዚህ ጥቅሶች ፍንጭ የሚሰጡን እንዴት ነው?



ጥያቄያችን ‹‹በክርስቶስ ስም›› በሚሆንበት ጊዜ፣ ሰማያዊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ስለ እኛ መስራት እንደሚጀምሩ እርግጠኞች እንሆናለን። መላዕክት በዙሪያችን እየሰሩ ሲንቀሳቀሱ ላናይ እንችላለን።ነገር ግን እነርሱ በኢየሱስ ስም ከሰማያዊ ዙፋን የእኛን ጥያቄ ለማሟላት ይላካሉ። አንዳንድ ጊዜ በክርስቶስ ስም ስንለምን፣አይናችንን ገልጠን እያያን ያኔውኑ ነገሮች ተለውጠው ለማየት እንፈልጋለን ፣ሆኖም ነገሮች እንደነበሩ ይሆናሉ። ነገር ግን፣ ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ እንዲል በተናገረው ጊዜ እንደነበረ ቅጽበታዊ ምላሽ ቢመጣ ወይም፣ ክርስቶስን በጌተሴመኔ በኃይል እንዳጸናው ዓይነት በዝምታና ማንም ሳያውቀው ሊመጣ ይችላል። አንድ ቅጽበታዊ ነገር በድንገት ላይፈጸም ይችላል፣ ይህ ማለት ግን እግዚአብሔር ለእኛ ምንም እየሰራ አይደለም ለማለት አይቻልም።

በድጋሚ ዮሐ 14፡1-14 ያለውን ያንብቡ። እያነበቡ ሳለ ክርስቶስ ፊት ለፊት እየተናገረዎት እንዳለ ያስቡ፣ ከእነዚህ ተስፋዎች ምን ዓይነት መጽናናትና ተስፋ ያገኛሉ? በተመሳሳይ ጊዜ፣ ራስዎን እንዲህ ብለው ይጠይቁ፣ እነዚህ ተስፋዎች በህይወቴ እንዳይፈጸሙ የሚያደርጉ ምን ነገሮች አሉ? በልቤ ምን ዓይነት ለውጥ ለማድረግ ወስኛለሁ?

ነሐሴ 10
August 16

የትንሳኤው ኃይል


ትንሳኤው የሚያመለክተው የሰዎችን የአቅመ-ቢስነት ችግር ነው። ስለ ክርስቶስ ህይወት፤ ሞትና ትንሳኤው ስናስብ፣ እኛን በህጋዊነት ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ያደረገን ክስተት መሆኑን እናስተውላለን። ይህም ደግሞ እውነት ነው።

ነገር ግን፣ ትንሳኤው ሌላ የተለየ የማዳንን ተጨማሪ ጎን ያሳየናል። የክርስቶስ ትንሳኤ የሚያሳየን እርሱ ከሞት እንደተነሳ አንድ ቀን እኛም ከሞት የምንነሳ መሆናችንን ብቻ አይደለም። ትንሳኤ ክርስቶስን ስልጣንና ኃይል ባለበት በአባቱ ቀኝ ከፍ አድርጎ አስቀመጠው። የትንሳኤው ኃይል እግዚአብሔር ዛሬም ለእኛ የሚያዘጋጀው ተመሳሳይ ኃይል ነው! በኤፌ 1:18-23 ጳውሎስ ስለ እግዚአብሄር ኃይል ይናገራል። እነዚህ ጥቅሶች ስለ ትንሳኤው ኃይል ምን ያስተምሩናል? ለራስዎ የሚሆን ከእነዚህ ጥቅሶች ምን ተስፋና ቃል ኪዳን ያገኛሉ?



በዚህ ስፍራ ጳውሎስ የኤፌሶን ሰዎች በመለኮታዊ መረዳት ብቻ በትክክል የሚስተዋሉ ጥቂት ነገሮችን እንዲያስተውሉ እየጸለየላቸው ነው። (1ኛ) የሱስ ክርስቶስ የጠራን ለውጥና የዘላላም ህይወት ተስፋ ያለን ስለመሆኑና፣ (2ኛ) በእኛ ፈንታ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ኃይል የምናስተውል ስለመሆናችን ይሆናል።

ከዚያም ጳውሎስ ይህ ኃይል ምን ዓይነት አስደናቂ መሆኑን ወደ መግለጽ ይመጣል። ዛሬ ለእኛ የተዘጋጀው ኃይል ክርስቶስን ከመቃብር ያነሳውና ወደ ህይወት የመለሰው ብቻ ሳይሆን፣ ኃይል በሚገኝበት በአባቱ ቀኝ ያስቀመጠውም ጭምር ነው።

ነገር ግን ጳውሎስ በዚህ አያቆምም። ትንሳኤው ለክርስቶስ ዝም ብሎ የሆነ ዓይነት ኃይል አይደለም የሰጠው፣ ነገር ግን፣ ለመግዛትና ለህዝቦቹ በዘላላም ዘመናት አስፈላጊ የሆነ ነገርን ሁሉ ለማቅረብ የሚያስችለው ኃይል እንደሆነ ይነግረናል።!

በህይዎትዎ የክርስቶስ የትንሳኤው ኃይል የሚያስፈልገውን አከባቢ ይለዩ። ሲጨርሱ ፣ ይህ ኃይል በአስፈላጊ ስፍራዎች ሁሉ እንዲሰራ ይጸልዩ። ተመሳሳይ ጊዜ ፣ ይህ ኃይል በተሻለ ሁኔታ በህይወትዎ በነጻነት እንዲሰራ ለማድረግ ምን የተለየ ነገር ማድረግ ይችላሉ?

ነሐሴ 11
August 17

ጭንቀታችንን ሁሉ ለመሸከም


አንዳንድ ሰዎች በቤታቸው ውስጥ በእንጨት ወይም በብረት ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ ተሰቅሎ ይታያል።‹‹ መጨነቅ እየተቻለ ለምን ይጸለያል? ›› ይህ አስቂኝ ነገር ነው፣ ምክንያቱም ነገሮቻችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ስንችል ምን ያህል ጊዜ እንደምንጨነቅ እናውቃለን።

አንድ ጊዜ አንድ ሰው እንዲህ አለ፣ ህይወትህ ሙሉ በሙሉ አስጨናቂ ሲሆንብህ ፣ ለእግዚአብሔር ስጠውና እርሱ ነገሮቹን ይፍታ ብሏል። እግዚአብሔር ለእኛ እንደዚህ ለማድረግ ምን ያህል ይጓጓል! ሆኖም በሚደንቅ ሁኔታ፣ እኛ ነገሮች እስኪያስቆሙን ድረስ በችግሮቻችን ላይ እናተኩራለን። ወደ ጌታ ከመሄዳችን በፊት ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ የምንቆየው ለምንድነው? 1 ጴጥ 5:7ን ያንብቡ። ጴጥሮስ እየጠቀሰ ያለው ከመዝ 55:22 ለይ ነው። በዚህ ስፍራ ለእኛ የሚሆን መሰረታዊ መልዕክት ምንድነው? ማቴ6:25-33ን ጨምረው ይመልከቱ።



1 ጴጥ 5:7 በጣም ግልጽ የሆነ ጥቅስ ነው። የተደበቀ ምስጢር የለበትም፣ ማለት የፈለገውም በቀጥታ የተጻፈውን ራሱን ነው። መጣል ማለት ያንኑ ማለት ነው፣ መወርወር፣ ወዲያ ማድረግ፣ ከዚያም ህመምን የሚያስከትለውን እና የትኩረት ነጥብ የሆነውን ነገር ከአንተ ጋር ምንም ግኑኝነት እንደሌለው ማሰብ ማለት ነው። ነገር ግን ሸክሞቻችን የትም አልተጣሉም አልተወረወሩም። ጭንቀታችን ዝምብሎ ቦታ ላይ አልተጣለም። ሊያስተካክለው ቃል ለገባው ሰማያዊ አባታችን ተሰጥቷል። በማትዎስ ወንጌል ክርስቶስ እየነገረን ያለው ይህንን ነው። ይህንን በማድረግ የተፈጠረው ችግር በጣም ትልቅ አይደለም፤ ግን በጣም ቀላል መስሎ መታየት፣ ከዚያም እንደጥሩ ነገር መታየት ይጀምራል።

ጭንቀት በተለያዩ ነገሮች ምክንያት ይፈጠራል። የሥራ ጫና ሊሆን ይችላል፣ ሳይጠበቁ የሚፈጠሩ ነገሮች፣ የሚወደን ሰው ባለመኖሩ የማንፈለግ መስሎ ሲታየን፣ የጤና ወይም የገንዘብ እጥረት ፣ ለእግዚአብሔር ያልተገባን መስሎ መታየት፣ ይቅር ያልተባልን እንደሆንን ማመን።

ችግሩ ምንም ይሁን ምን፣ ሁላችንም የምንስማማው አንድ ነገር አለ፣ እርሱም ከማንም በተሻለ ሁኔታ ችግሮቻችንን በራሳችን እናስተካክላለን ብለን ማሳባችን ነው። ነገር ግን ጴጥሮስ ይህን አስተሳሰባችንን እንደገና እንድናጤነው ይነግረናል። የማንጨነቅበት ብቸኛ ምክንያት እግዚአብሔር ይጠነቀቅልናል። ነገር ግን እግዚአብሔር ፍቺ በዙሪያችን እያንዣበበ፣ወይም እኛ ምንም የማንጠቅም መሆናችን እየተሰማንም ጥንቃቄ እያደረገልን ነው ማለት ነው?

መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እርሱ ሁልጊዜ ነገሮቻችንን ለመለወጥ ይሰራል። አሁን እንድትጨነቅ የሚያደርግህ ነገር ምንድነው? ምንም ህጋዊ ነገሮች ቢሆኑ፣ ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆኑም፣ ለእግዚአብሔር የሚሳነው አለን? ምናልባትም የእኛ ትልቁ ችግር እግዚአብሄር ነገሮቹን የሚያውቃቸው እና ሊያስተካክላቸው የሚችል ቢሆንም እኛ እንዲፈታልን በምንፈልገው መልኩ ይፈታልናል ብለን አናምንም። በመጨረሻው ነጥብ ላይ ተወያዩበትና ይህ ነገር በህይወትዎ ምን ያህል እውነት እንደሆነ ራስዎን ይጠይቁ።

ነሐሴ 12
August 18

እግዚአብሔር ባይታይም ታማኝ መሆን


በእኛ ላይ እየደረሰ ስላለው ነገር ማንም ጥንቃቄ የማያደርግልን መሆኑን ማሰብ ደስ የማይል ስሜትን የሚፈጥር ነገር ነው። ነገር ግን እግዚአብሄር እንደማያውቅና እንደማይጠነቀቅ ማሰብ ደግሞ ከሁሉ የከፋ ነገር ነው።

በባቢሎን ለነበሩ የይሁዳ ምርኮኞች፣ እግዚአብር ስለ እነርሱ ሁኔታ ግድ የሚለው አይመስልም። እነርሱ አሁንም ምርኮኞች አሁንም በኃጢአታቸው ምክንያት እግዚአብሔር የተዋቸው ይመስላቸዋል ። ነገር ግን ኢሳያስ ለእነርሱ የሚያጽናና ቃል ይናገራል። ኢሳ 40 አጅግ በጣም በተዋቡ ቃላት ኢሳያስ ስለ አምላካቸው የሚናገርበት ክፍል ነው። “መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።” (ኢሳ 40:11)። ነገር ግን ምርኮኞቹ ከረዥም ጊዜ በኃላም እግዚአብሔር አንተ የት ነህ አንተ ስለመኖርህ ወይም ለእኛ የምትጠነቀቅ ስለመሆንህ ምንም አላየንም ይሉ ነበር።

ኢሳ 40:27-31ን ያንብቡ። ኢሳያስ እግዚአብሔርን የሚገልጸው እንዴት ነው? ይህ ለእግዚአብሔር የተሰጠው መግለጫ ‹‹ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ለሚሉ መልስ ሊሰጥ የሚችለው እንዴት ነው” (ኢሳ 40:27)?



ሌሎች መንገዳቸው ከእግዚአብሔር የተደበቀ እንደሆነ የሚያስቡ ሰዎች ቡድን የሚገኘው በአስቴር መጽሐፍ ውስጥ ነው። በዚህ መጸሐፍ የእግዚአብሔር ስም አንድም ጊዜ አልተጠቀሰም። ሆኖም ግን ታሪኩ በሞላ እግዚአብሔር ህዝቡን ለማጥፋት የታቀደውን አዋጅ ለመቀልበስና ህዝቡን ለማዳን በሚያደርገው ድራማ የተሞላ ነው። ይህ ታሪክ ባለፈው ዘመን የተደረጉ ነገሮችን የሚገልጽ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ህዝቦች እንደገና ሲሰደዱ እነርሱን ለማጥፋት የሚወጣውን አዋጅ ጭምር የሚያሳይ ነው። (ራዕ 13:15)። ታያለችሁ እንደዚህ የሚከብዱ ዓይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን እውነትም እግዚአብሔር ህዝቦቹን ትቷቸዋል ብሎ ለማጠቃለል እንዴት ቀላል እንደሚሆን? ነገር ግን መፍራት የለብንም ። በአስቴር ታሪክ ውስጥ ህዝቦቹን ያዳነው ያው አምላክ በመጨረሻው ፈተናና ችግር ጊዜ ህዝቦቹን ያድናቸዋል።

ኢሳያስ እግዚአብሔርን ለምርኮኞቹ የገለጸው እንዴት እንደሆን ተመልክተናል። እርሰዎ እግዚአብሔር እንደተዋቸውና እንደረሳቸው ለሚሰማቸው ሰዎች የሚገልጡት እንዴት ነው? በዙሪያቸው በሚታዩ ነገሮች ብቻ ሳይደገፉ መንፈሳዊ አይኖቻቸውን በመክፈት ተስፋ እንዲደርጉ ሊያስተምሯቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

ነሐሴ 13
August 19


ተጨማሪ ሀሳብ


በኤለን ዋይት ነብያትና ነገስታት በሚለው “በንግስት አስቴር ዘመን,” ገጽ 598–606። “መንፈስ ቅዱስን ለሚፈልጉት እንደሚሰጥ እግዚአብሔር አልተናገረምን? እና ይህ መንፈስ እውነት አይደለምን? ትክክለኛ መሪስ አይደለምን? አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔርን በአእምሮአቸው አስቀድሞ እንዳመኑት በማሰብ እንደ ተስፋ ቃሉ ለመያዝ ያፍራሉ። እነርሱ እግዚአብሔር እንዲያስተምረን ይጸልያሉ ሆኖም ግን ፣ ልመናውን የተሰጠንን የተስፋ ቃል የራስ በማድረግ ሥፍራ ለመስጠት እና ስለ እርሱ የተማርነውን ለማመን ይቸገራሉ። ወደ ሰማያዊ አባታችን ለመማር ፈቃደኛ በሆነ ራስን ዝቅ ባደረገ ፣ መንፈስ የምንመጣ እስከሆነ ድረስ፣ የእግዚአብሔር የራሱ የሆነውን የተስፋ ቃሉን መፈጸም ለምን እንጠራጠራለን? ለጥቂት ጊዜም ቢሆን በመጠራጠር ለምን ክብሩን እናጎድለዋለን። የእርሱን ፈቃድ ለማወቅ በፈለግህ ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሰራ ከአንተ የሚጠበቀው በእርሱ ስትመራ፣ ስትከተለው እና ፈቃዱን ስታደርግ እንደምትባረክ ማመን ብቻ ነው። ምናልባትም የእርሱን ትምህርት በስህተት ከተረጎምነው ራሳችንን በስህተት እናምነዋለን ። ይህንን ራሱን የጸሎት ርዕስህ በማድረግ፣ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራህና የቃሉን ትክክለኛ ትርጉም እንዲገልጽልህ፣ እቅዱንና በአንተ ላይ ያለውን የእርሱን አሰራር፣ እመነው እናም እስከ መጨረሻው እመነው።”—Ellen G. White, Manuscript Releases, vol. 6, p. 225. “እምነት የሚጠነክርው በሚቃረን ሀሳብና በጥርጥር ላይ ግጭት መፍጠር ስንጀምር ነው። በእነዚህ የፈተና ጊዜያት የምናገኘው ልምድ በጣም ትልቅ ዋጋ ካላቸው ጌጣጌጦች እጅግ የበለጠ ነው። ”—Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 3, p. 555.


የመወያያ ጥያቄዎች



1. እንደ ክፍል፣ ሳናይ ስለምናምናቸው ነገሮች፣ የምናያቸውን ነገሮች ሁሉ ደግሞ ከእይታችን በላይ ናቸው። ስለነዚህ ነገሮች ተወያዩባቸው። ‹‹የማይታየውን ማየት›› የሚለውን ለመረዳት ይህ እንዴት ያግዘናል?

2. በረቡዕ ቀን ትምህርት መጨረሻ ላይ ያለው ጥያቄ ላይ ተወያዩበት። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ራሳችንን የምናገኘው ምን ያህል ጊዜ ነው? እኛ የምንፈልገው ዓይነት እንኳ ባይሆን የእግዚአብሔር መንገድ ከሁሉ የተሸለ እንደሆነ ለመቀበል ምን እናድርግ?

3. “ከሚቃረኑ ሀሳቦችና ከጥርጥር ጋር በመታገል እምነት የሚጠነክር ከሆነ” እና ይህ ደግሞ ትልቅ ዋጋ ካላቸው ጌጣ ጌጦች ዋጋው እጅግ ወደ ከበረ ወደ አንድ‹‹ ትልቅ ዋጋ ወዳለው ነገር›› የሚመራን ከሆነ ይህን ግጭት የምንረዳበትን መንገድ ሊቀይርልን የሚችለው እንዴት ነው?

4. ብዙዎቻችን ክርስቲያን የሆኑ ሰዎች እንኳ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የገቡት ለመውጣት እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ አይተናል። በጸሎትና በጥረት ካልሆነ በስተቀር ነገሮች ከዚህ የከፉ እንደሚሆኑ እናውቃለን። ከተማርናቸው ነገሮች አንጻር እነዚህን ሁኔታዎች እንዴት እናያቸዋለን?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA union SSL