የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ያንብቡ።ዕንባ. 1:1-4, ኢዮ 38-41, ኢሳ 41:8-14, ኤር 29:1-10,እብ 12:1-13.
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር አሁን በልባችን ስለፈሰሰ ተስፋው አያሳፍረንም” (ሮሜ 5:5)።
ቤ
ተክርስቲያን ፈገግታ በተሞሉ ሰዎች ተከባ ሳለች፣ ስለ ተስፋ
ማውራትና መዘመር እንዴት ቀላል ነው። ነገር ግን ራሳችንን ፈተና
ውስጥ በምናገኝበት ጊዜ፣ ተስፋ ማድረግ ሁልጊዜ ቀላል አይሆንም።
ሁኔታዎች በዙሪያችን ጫና እያሳደሩ፣ በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሔር ጥበብ
ላይ ስለ ሁሉም ነገር ጥያቄ መጠየቅ እንጀምራለን።
ስ.ኤስ ሉዊስ የተባለ ጸሐፊ ከመጽሐፎቹ በአንዱ ‹‹አንበሳውን እንሰዲያምን
ማድረግ›› በሚለው ርዕስ አንድ ሰው አንበሳውን ለመገናኘት በመፈለግ ፣
አንበሳው አደጋ አያደርስም? በማለት ጠየቀ። ለሰውዬው መልስ ስሰጠው
አንበሳው አደገኛ እንደሆነ ተነገረው። ‹‹ነገር ግን አንበሳው ጥሩ ነው››
ምንም እንኳ እግዚአብሔር የሚያደርጋቸውን ነገሮች ለምን
እንደሚያደርግ ባናውቅም፣ እግዚአብሔር የሚያደርጋቸው ነገሮች ከእኛ
በተቃራኒ ነው ማለት ግን አይደለም። ይህ ማለት እኛ ስለ ሁኔታው ሙሉ
ዕውቀት የለንም ማለት ነው። ነገር ግን ሰላም፣ በራስ መተማመን፣ እና ተስፋ
እንዲኖረን እግዚአብሔር የሚስተዋልና ወደፊት የሚያደርገው ነገር ግልጽ
የሆነ መሆን አለበት ከሚለው አስተሳሰብ ጋር እንታገላለን። በአስተሳሰባችን
ሁልጊዜ፣ ‹‹ከእርሱ ጋር ሁሉም ሰላም ነው›› ብለን ልናስብ ይገባናል።
ሳምንቱን በአጭር እይታ: የእግዚአብሔርን ባህሪይ ማወቅ በፈተና
እሳት ውስጥ ስንሆን የሚጠቅመን እንዴት ነው?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 7 ሰንበት ያጥኑ።
በምንጎዳበት ጊዜ፣ በህይወታችን ውስጥ ዋና ጉዳይ እርሱ ብቻ እንደሆነ ለማመንና በዚያ አስተሳሰብ ለመግፋት ቀላል ነው። ነገር ግን፣ ከዚህ በጣም ከፍ ያለ ስዕል አለ።(ራዕ 12:7, ሮሜ 8:22). እምባቆም 1:1-4ን ያንብቡ። ዕንባቆም ያጋጠመው ምንድነው?
ምናልባትም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለው አስበው ሊሆን ይችላል።‹‹ይህ በጣም ከባድ ነው›› ዕንባቆም፣ ቶሎ መጥቼ ላግዝህ ይላል ብለው አስበው ይሆናል። ነገር ግን የእግዚአብሔር መልስ የዚህ ተቃራኒ ይሆናል። ለእምባቆም የተነገረው ችግሩ ከዚህ የባሰ እንደሚሆን ነው ። ይህንን በእምባቆም 1 5-11 ያንብቡ። የእስራኤል ልጆች በሶርያውን ለምርኮ ተወሰዱ፣ነገር ግን እግዚአብሔር ከዚያ የከፋ ነገር እየመጣ እንደሆን ተናገረ። ባቢሎናውያን ህዝቡን ይዘው እንደሚሄዱ ተናገረ። ዕንባቆም እንደገና በቁጥር 12-17 እየጮሀ እግዚአብሔር ምን እንደሚናገር ይጠብቃል። እግዚአብሄር በዕንባ. 2፡2-3 የተናገረው በባቢሎናውያን አማካይነት እየመጣ በነበረው ጥፋት ውስጥ ሶስት ተስፋዎችን የሚያመጡት እንዴት ነው?
ዕንባቆም 2 እግዚአብሔር ስለ ባቢሎናውያን ጥፋት የተናገረበት
ነው። እብ 10፡ 37 እም 2፡3 በመጥቀስ በሚመጣው ዘመን የነብዩን መምጣት
ተስፋ እንዴት ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ይሰጣል። በተመሳሳይ ሁኔታ
(አይቀሬ) የሆነውን የባቢሎንን ውድቀት ይነግረናል። ስለዚህ ‹‹የታላቂቷ
ባቢሎን ውድቀት›› የማይቀር መሆኑን እንረዳለን። (ራዕ 18:2)
ዕንባቆም ፣ ዙሪያውን በከበበው ብዙ ክፉ ነገርና እግዚአብሔር
እየተናገረ ባለው ጥፋት መካከል ባለው ነገር ግራ ተጋብቷል። ሆኖም ይህ
በመዳን ታሪክ ውስጥ እኛ ራሳችንን የምናገኝበት ስፍራ ነው። ታላቅ ጥፋት
ዙሪያችንን ከቦናል፣ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የባሰ መጥፎ ነገር እየመጣ እንደሆነ
ይነግረናል። በዚህ ውስጥ የዕንባቆም መጽናት ዋና ምስጢሩ፣ የታሪኩን ሙሉ
ሀሳብ እንዲያውቅ መደረጉ ነው። ስለዚህ በምዕራፍ 3 እግዚአብሔር ወደፊት
በሚያደርገው ነገር ምክንያት በምስጋና ትልቅ ጸሎት ሲጸልይ ይደመጣል።
ዕንባ 3፡16-19ን ያንብቡ። እምባቆም የተስፋው ምክንያት
አድርጎ የሚያስቀምጠው ምንድነው? ወደፊት ሊሆን ያለውን
ትንቢታዊ ነገር ስንጠብቅ የእግዚአብሔር ህዝቦች ተስፋችን
ምንድነው? ይህንን ተስፋ የራስዎ ሊያደርጉ የሚችሉት እንዴት
ነው?
ኦስዋለ ወድ ቻንበርስ የሚባል ሰው ሲጽፍ፣ ‹‹ እግዚአብሔርን ምን እንደሚደርግ ስትጠይቅ ቆየህ? እርሱ በፍጹም አይነግርህም። እግዚአብሄር ምን እንደሚያደርግ ሳይሆን እርሱ ማን እንደሆን ግን ይገልጽልሃል›› ብሏል። ቻምበርስ በዚህ ሀሳቡ ምን እያለ ነው? እንደምናውቀው ፣ የእዮብ መጸሐፍ የምጀምረው በእዮብ የግል ህይወት ታላቅ መከራ ነው። ከራሱ ህይወት እና ከሚስቱ ህይወት በስተቀር ሁሉንም ካጣ በኋላ ሚስቱም ‹‹እግዚአብሔርን ረግመህ ብትሞት ይሻላል›› አለችው (ኢዮ 2፡9) ። ከዚህ የሚቀጥለው ነገር የኢዮብ ወዳጆች ይህ ሁሉ ነገር ለምን እንደሆነ የሚናገሩበት ንግግር ነው። በእነዚህ ውይይቶች ወቅት ሁሉ እግዚአብሔር ዝምታን መርጧል። በምዕራፍ 38 ድንገት እግዚአብሔር ይገለጥና መናገር ይጀምራል። “ያለ እውቀት በሚናገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው?” (ኢዮ 38:2): ከዚህ በኃላ እግዚአብሔር ያለማቋረጥ 60 የሚሆኑ አፍ የmeያስከፍቱ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ እናገኛለን። መጽሐፍ ቅዱሳችሁን በመክፈት ይህንን ከኢዮብ 38 እና 39 ይፈልጉ። ከመጨረሻው ጥያቄ በኋላ፣ ኢዮብ እንዲህ ሲል መለሰ፡- “እነሆ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ የምመልስልህ ምንድነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ፤ አንድ ጊዜ ተናገርሁ ሁለተኛ አልመልስምም” ኢዮ40: 4,5):: ነገር ግን እግዚአብሄር አልጨረሰም ነበር። እናም እንደገና ይጀምርና አንድ ‹‹ትልቅ›› ጥያቄ ያስከትላል። በኢዮ 42:1-6 የኢዮብን የመጨረሻ ምላሽ እና በእርሱ ላይ ያመጣውን ተጽዕኖ ያንብቡ።
እግዚአብሔር ማንኛውንም‹‹ ለምን›› የሚሉ የኢዮብ ጓደኞች
ጥያቄዎች አይመልስም። ነገር ግን እግዚአብሔር የእርሱን ተወዳዳሪ የሌለውን
ትልቅነት በፍጥረት ላይ እንዳሳየ አሁንም ይገልጻል። ከዚህ በኋላ ኢዮብ ምንም
ዓይነት ምላሽ አይፈልግም ። ለጥያቄዎች መልስን መሻት አስደናቂ በሆነው
የእግዚአብሔር ታላቅነት ነጸብራቅ ተሸፍኗል።
ይህ ታሪክ አስገራሚ የሆነ ተቃራኒ የሚመስል አገላለጽ ያሳያል።
ካለን ከትንሽ መረዳት ውስጥ ተስፋና መጽናናት ይመነጫል። በሀሳብና
በትምህርት ላይ በተመሰረተ ሁሉን ነገር በማወቅ መጽናናትን እንፈልጋለን
ከዚህም የተነሳ ሳናውቅ ስንቀር ተስፋ እንቆርጣለን። ነገር ግን አንዳንንድ ጊዜ
እግዚአብሔር የእኛን ድንቁርና እንድናውቅ ብልጭታ በመስጠት የሰው ተስፋ
ሊመጣ የሚችለው ከእኛ እጅጉን በላይ ከሆነ አካል ብቻ መሆኑን እንድናውቅ
ያደርገናል።
በአሁኑ ሰዓት ለማስተዋል የሚያስቸግሩ ነገሮች
በህይወትዎ እየተከናወኑ ይሆን? እንዲህ ከሆነ ፣ በእግዚአብሔር
ባህሪይ ላይ ያትኩሩ ። ይህን ማድረግዎ አሁን ከማስተዋል በላይ
ለሆነው ነገርዎ የሚፈልጉትን ተስፋ ሊሰጥ የሚችለው እንዴት
ነው?
“እኔ አምላክህ እግዚአብሔር አትፍራ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና” (ኢሳ 41:13) ። አንድ ሰው እንዲህ አለ “እግዚአብሔር የራቀ ሲመስል፣ ማን ነው ከስፍራው ያልተንቀሳቀሰው?” ችግሮች በሚመቱን ጊዜ፣ እግዚአብሔር ተወን ብለን እናስባለን። እውነቱ ግን እርሱ የትም አልሄደም። ለይሁዳ ምርኮኞች እግዚአብሔር ከእነርሱ እጅግ የራቀ መስሎአቸው ነበር። ሆኖም በኢሳያስ አማካይነት እግዚአብሔር ወደፊት ነጻ እንደሚያወጣቸው ቃል ገባለቸው። ምንም እንኳ ወደ አገራቸው የመመለሱ እውነት ገና ብዙ ዓመት ወደፊት የሚቀረው ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ከህዝቡ ርቆ ያልሄደ እንደሆነ እና ተስፋ ለማድረግ ብዙ ምክንያቶች መኖራቸውን ሊያረጋግጥላቸው ፈለገ። ኢሳ 41:8-14ን ያንብቡ። በጉጉት ወደፊት ነጻ መውጣትን እየተጠባበቀ ላለ ህዝብ ሊነገረው የሚችል ምን ተስፋ ታገኛለህ? ይህ ተስፋ ሊያበቃ እየሄደ ባለ ምድር ላይ ለምንኖር ምርኮኞች ምን ይረዳናል?
ይህንን የሚመስል መልዕክትን ከሚያጎሉ ጥቅሶች ሁሉ የሚበልጠው
የሚገኘው በኢሳ 41:13 ላይ ነው። በዓለማት ሁሉ ላይ ሥልጣን ያለው
እግዚአብሔር ህዝቡን አትፍሩ ይላል፣ ምክንያቱም ቀኝ እጅህን የሚይዘው
እርሱ ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር በብርሃን ዓመታት ርቀት በዙፋኑ ቁጭ
ብሎ በምድራችን ላይ የሚከናወኑ ነገሮችን የሚመራ መሆኑን ማወቅ አንድ
ነገር ነው። ነገር ግን የተወደዱ ህዝቦቹን ቀን እጃቸውን ለመያዝ በሚያስችል
ቅርበት መሆኑን ማወቅ ደግሞ ከሁሉም የበለጠ የተለየ መረዳት ነው።
በስራ በምንወጠርበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር በቅርባችን መሆኑን
ለማስተዋል አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን እርሱ አማኑኤል እንደሆነ ስናስብ
‹‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር›› መሆኑን ስናውቅ ሁኔታው በፍጹም ልዩ
ይሆናል። የእግዚአብሔር መገኘት ከእኛ ጋር በሚሆንበት ጊዜ ፣ ዓላማዎቹም
፣ተስፋዎቹም እና የመለወጥ ኃይሉም ከእኛ ጋር ይሆናል።
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት፣ አንድ ሙከራ ያድርጉ።
በተቻለ መጠን ሁሉ፣ እግዚአብሔር የዓለማት ፈጣሪ፣ የእርስዎን
እጅ ለመያዝ በሚያስችል ቅርበት ላይ እንዳለ ለራስዎ በማሳሰብ
ተስፋ ሰጭ መሆናቸውን ያስታውሱ። የነበረውን አኗኗርዎን
ለመለወጥ የተደረገ ነገርን መዝግበው ይያዙ። በሰንበት ትምህርት
ክፍል ያለዎትን ልምድ ይዘው ይቅረቡ።
እያንዳንዱ ሰው ተስፋን ይፈልጋል። ነገር ግን የት ነው የሚገኘው? ለአንዳንድ ሰዎች ተስፋ የሚገኘው በጓደኛቸው ፈገግታ ውስጥ ነው። ለአንዳንዶች ተስፋ የሚገኘው በቂ ገንዘብ በመኖሩ ላይ ወይንም ከተረጋጋ ቤተሰብ ውስጥ ነው። ተስፋንና መጽናናትን በትክክል የምናገኘው የት ነው?
በኤርምያስ መጽሐፍ ነብዩ ህዝቡ በምርኮ አገር ሆነው ተስፋ ለቆረጡ ህዝቦች ጽፈዋል። “በባቢሎን ወንዞች ማዶ ተቀምጠን ጽዮንን ባሳብናት ጊዜ አለቅስን ”መዝ 137:1)ነገር ግን ምንም እንኳ ነገሩ ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም ፣ ኤርሚያስ ተስፋ መቁረጥ የሌለባቸውን ምክንያት ይናገራል። በኤር 29:1-10 የተሰጠው ተስፋ ምንድነው?
በዚህ ንባብ ለተስፋ የሚሆኑ 3 ሊታመኑ የሚችሉ ምንጮች
አሉ። አንደኛ፣ እግዚአብሔር ለህዝቡ ተስፋ እንዳይቆርጡ እየተናገረ
ያለው የደረሰበባቸው ችግር ሳይታወቅ በድንገት የተከሰተ ነገር አለመሆኑን
በመንገር ነው። እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ ብሎ ነበር። “እኔ የይሁዳን ህዝብ
ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን እወስዳቸዋለሁ።”(ኤር 29:4):: ክፉ ዙርያቸውን
የከበበ ቢመስልም ፣ ይሁዳ ከእግዚአብሔር እጅ መካከል አላመለጠም።
ሁለተኛ፣ እግዚአብሔር ህዝቡ ተስፋ እንዳይቆርጥ ፣ አሁን ባሉበት
ችግሮቻቸው ውስጥ ለእነርሱ ይሰራል። “በእርሷ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና
ወደ እርሷ ላስማረክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ ስለ እርስዋም ወደ
እግዚአብሔር ጸልዩ ምክንያቱም ከእርስዋ ጋር እናንተም ትበለጽጋላችሁ”
(ኤር 29:7)
ሶስተኛ፣ የእግዚአብሔር ህዝብን ተስፋ እንዳይቆርጡ የሚነግራቸው
፣ እርሱ የምርኮአቸውን ዘመን ወደ ፍጻሜ ስለሚያመጣው ነው። “እግዚአብሔር
እንዲህ ይላልና ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጎበኛችኋለሁ
ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ”
(ኤር 29:10)
እግዚአብሔር በባለፈው ህይወታቸው ውስጥ እንዴት ኃላፊነት
እንደወሰደ በወደፊት ህይወታቸውም እንደሚጠነቀቅላቸው ከገለጸ በኋላ፣
ከልብ የሆነውን ፍቅሩን ለህዝቡ ያሳያል።(ኤር 29:11-14)
ኤር 29:11-14 የራስዎን ስም በማስገባት ያንብቡና
እግዚአብሔር ለራስዎ ሶስት ተስፋዎችን እየሰጠ መሆኑን ይቀበሉ።
አሁን እያጋጠመዎት ያለ ነገር ምንም ይሁን ምን እነዚህን
ተስፋዎች የራስዎ ያድርጉዋቸው።
ዕብ 12 ፡ 5-13 ያንብቡ። ለእኛ መልዕክቱ ምንድነው ፣ በዚህ ሩብ ዓመት ከምንማረው ትምህርት ጋር የሚጣጣመው እንዴት ነው?
በዕብ 12:5-13 ጳውሎስ መከራን እንደ ቅጣት በሚመስል አውድ
ይገልጻል። ይህ ንባብ በአዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅጣት የሚለው ቃል አስር
ጊዜ ተጽፏል። በግሪኩ ዓለም ይህ ቃል ለትምህርት መሰረታዊ ቃል ነበር።
ስለዚህ ፣ ቅጣትን ማስተዋል ማለት ጳውሎስ በዕብራውያን 11 አስቀድሞ
እግዚአብሔር በእምነት ትምህርት ቤት እንዴት እንደሚያሰለጥን የገለጸበት
ማሳያ ነው።
ጳውሎስ በዕብራውያን መጸሐፍ በሙሉ፣ የእምነት ወንዶችንና
ሴቶችን ይገልጻል። እምነታቸው ባጋጠማቸው ታላቅ ፈተና ውስጥ አጽንቶ
ያቆማቸው እንደሆን ተነግሯል። በምዕራፍ 12 ጳውሎስ አንባቢዎቹን እጅግ
ብዙ ሰዎች በታላቅ ፈተና ውስጥ ያለፉ እስካሉ ድረስ፣ እኛም የህይወት
ሩጫችንን ሮጠን እንጨርሳለን። ቁልፉ ዓይናችንን በክርስቶስ ላይ መትከል
ብቻ ነው።(ዕብ 12፡2) ምክንያቱም እርሱ በፈተና ውስጥ ላሉ ሁሉ ምሳሌ
ሊሆን ይችላል። (ዕብ 12:3)::ምዕራፍ 12ን ማንበብ ማለት ልክ የማንበብያ
መነጽር እንደማድረግ ማለት ነው። ያለ እነዚህ መነጽሮች ስለ ስቃይና መከራ
ማስተዋል ሁልጊዜ ከባድ ነው። በእነዚህ መነጽሮች በመመልከት ባህላችን
በእኛ ላይ ከቸጫነብን እና ስለ ፈተናዎች እንዳናስተውል ካጨለመብን ነገር
ሁሉ ነጻ እንሆናለን። ከዚያ በኃላ ስለ ፈተና ትክክለኛ አመለካከት ኖሮን
በዕውቀት ምላሽ እንሰጣለን።
በዕብራውያን 12 1-13 መነጽር ያንብቡት። በቁጥር
5-12 ትኩረት በማድረግ የሚከተለውን ጥያቄ መልሱ፡
የቅጣት ምንጩ ምንድነው? ______________________
ስለ ቅጣት ያለን ምላሽ ምንድነው? _________________
የቅጣት ግቡ ምንድነው? ________________________
ዕብ 12:1-13ን እንደገና ያንብቡ። ለተስፋ ምክንያት
ይሆናሉ የሚሏቸውን ነገሮች በሙሉ ይመዝግቡ። ይህንን ተስፋ
በመንፈሳዊ ህይወትዎ ውስጥ የተለማመዱት እንዴት ነው?
Read Ellen G. White, “The School of the Hereaf-
ter,” pp. 301–309, in Education; “Help in Daily Living, pp. 470, 471,
in The Ministry of Healing.
“በዚህ ሁሉ ከፍተኛ በሆነ ተስፋ በሚያስቆርጥ ልምምድ መካከል እና ግልጽ
በሆነ ኃዘን ውስጥ፣ ሐዘን እድል ፋንታ በሆነ ጊዜ፣ ነፍስን መከራ ሲያስጨንቃት፣
ከመኖር መሞት የተሸለ መስሎ በሚታይበት ጊዜ አሁንም እግዚአብሔር
በምድር ላሉ ልጆቹ ግድ የሚለው አምላክ እንደሆነ ማመን አስቸጋሪ ነው።
በዚህን ጊዜ ነው ብዙዎች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን መተማመን በመተው
የጥርጥር ባሪያ በመሆን ባለማመን ባርነት ሥር የሚወድቁት። በዚህን ጊዜ
መንፈሳዊ ዓይኖቻችን በርተውልን የእግዚአብሔርን ሙላት በማየት፣ እኛን
ከእኛው ከራሳችን ሊያድኑን፣ እግሮቻችን በማይናወጠው ለዘላለም እንደ ጸኑ
ተራሮች ባለው ዓለት ላይ እንዲተከሉ ለማድረግ፣አዲስ እምነት፣አዲስ ህይወት
እንድንጀምር ሊደርጉን የተላኩትን መላዕክት ማየት እንችላለን። ኤሌን ዋይት፣
አባቶችና ነገስታት ገጽ 162።
1.ኤለን ዋይት ፣ ሁላችንም አስቸጋሪ የሆኑ የመከራና ተስፋ የመቁረጥ ጊዜያቶች ያጋጥሙናል ትላለች። በእንዲህ ዓይነት ጊዜያት አንዳችን ሌላችንን የምናስታውሰው እንዴት ነው? አንዳችን ለሌላችን የተስፋ ምንጭ ልንሆን የምንችለው እንዴት ነው? 2. እንደ ክፍል ለሐሙስ ቀን ጥያቄ መልስ ለመስጠት ተወያዩበት። ሁልጊዜ እግዚአብሔር ቅርብ መሆኑን ስትገነዘብ በህይወትህ ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል? 3. በክፍል ውስጥ ኢዮ 38-41 ያለውን ድምጽዎትን ከፍ አድርገው ያንብቡ። ስለ እግዚአብሔር ምን ዓይነት ስዕል ያሳየናል። ተስፋና መጽናናትን የሚሰጠን ምን ትምህርት አገኙ? ሰንበት ከዚህ ስዕል ጋር የሚስማማው እንዴት ነው? ይህ የእግዚአብሔርን ባህሪይና ተፈጥሮ እንድንጠብቅ የሚረዳን እንዴት ነው? 4. የሚለውጥ ተስፋ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚመጣ እንመን ። ይህን ማለት በእያንዳንዳችን ህይወት ተስፋ እንዲመጣ እንጸልያለን ። ይህ ማለት መጽናናት ወደ እያንዳንዳችን ህይወት እዲመጣ እንጸልያለን ማለት ነው። በአሁን ጊዜ በተለያዩ ነገሮች ምክንያት እምነታቸው እየተሸረሸረባቸው ላሉ ወገኖች ተስፋቸው እንዲመለስላቸው እንጸልይላቸው። ተስፋቸውን እያጡ ላሉ ወገኖች ምን ታደርጋለህ? 5. በክፍላችሁ ውስጥ በመከራ እና ስቃይ ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ አልፎ የሚያውቅ ሰው ልምምዱን እንዲያካፍል ይደረግ። ያ ሰው አዲስ ህይወት እንዲጀምር የረዳው ነገር ምንድነው? ከዚህ ውስጥ በጭንቀትና በጥርጥር ጊዜ የሚጠቅመን ነገር ምን እናገኛለን?