የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዮሐ 16:5-15 ቆላ 1:28, 29; 1 ጴጥ 1:13 ማቴ 5:29 ዘፍ 32.
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ለዚህም ነገር ደግሞ በእኔ ኃይል እንደሚሰራ እንደ አሰራሩ እየተጋደልኩ እደክማለሁ” (ቆላ 1:29)።
አ
ንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ለቃለ መጠይቅ መድረክ ላይ ቁጭ
ብለዋል። ሁለቱም ልጆች ተገድለውባቸዋል። የሴትዮዋ ልጅ
የተገደለው ከ20 ዓመት በፊት ቢሆንም ንዴቷና ቁጣዋ ግን አሁንም
ያው ነው። ሰውዬው በጣም ይለያል። የእርሱ ልጅ በአሸባሪዎች ከተገደለች
ጥቂት ዓመታት ሆኗል። እርሱ የሚናገረው ለገዳዩ ይቅርታ ለማድረግ
እግዚአብሔር እንዴት የተለወጠ ልብ እንደሰጠው ነው። ህመሙ ምንም
ያህል የከፋ ቢሆንም፣ ይህ ሰው፣ እግዚአብሔር በጣም ጨለማ ወደሆኑ
የህይወታችን ክፍሎች እንኳ እንዴት ፈውስን እንደሚያመጣ ምሳሌ ሆነ።
ሁለት ሰዎች ለተመሳሳይ ችግር እንዴት በተለየ መንገድ ምላሽ ሰጡ?
በክርስቲያን ህይወት ውስጥ የመከራ እሳት ልምምድ በችግሩ ውስጥ ሰምጦ
ከመቅረት ይልቅ በህይወቱ የጎለመሰ እንዲሆን የሚረዳው እንዴት ነው?
ሳምንቱን በአጭር እይታ፡ ህሊናችንና የህሊናችን ኃይል ከሃጢአት
ጋር በሚደርገው ውጊያ ያለው ሚና ምንድነው? ስሜታችን
በውሳኔያችን ላይ የበላይ እንዲሆን መፍቀድ ስህተቱ ምንድነው?
በፈተና ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ ተስፋ ሳንቆርጥ የምንጸናው
ለምንድነው?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሐምሌ 30 ሰንበት ለመዘጋጀት ያጥኑ።
እግዚአብሔርን ‹‹እባክህ ጥሩ አድርገኝ›› ብለህ ጸልየህ ለውጡ
ግን በጣም ኢምንት ሆኖብህ ያውቃል? ህይወታችን ለውጥ የሌለው ሆኖ
ሳለ፣ እግዚአብሔር በታላቁ የሚቀይረው ኃይሉ አማካይነት ውስጣችንን
እንዲቀይረው ልንጸልይ የምንችለው እንዴት ነው? እግዚአብሄር ውስንነት
የሌለው ከሰው ኃይል በላይ የሆኑ፣ በነጻ ለእኛ ሊሰጠን የሚፈልጋቸው ነገሮች
እንዳሉት እናውቃለን። በእርግጥ ሁላችንም እግዚአብሄር ለእኛ የሚሰጠንን
ሁሉ ነገር የእኛ አድርገን ብንወስድ ደስ ይለናል፣ ሆኖም ግን በህይወታችን
ለመለወጥና እርሱ ለእኛ ሊሰጥ ያዘጋጀውን ነገር ሁሉ ለመቀበል ዝግጁዎች
ባለመሆናችን ልንቀበለው አንችልም።
ለምን? አንዱ ምክንያት በሚደንቅ ሁኔታ ቀላል ነው። መንፈስ
ቅዱስ ሊለውጠን የሚችል ያልተገደበ ኃይል እያለው፣ እኛ በራሳችን ምርጫ
የሚሰራውን የእግዚአብሔርን ኃይል እንገድበዋለን።
ዮሐ 16:5-15ን ያንብቡ። በዚህ ንባብ ጌታ ክርስቶስ መንፈስን
‹‹የእውነት መንፈስ›› ብሎ ነው የሚጠራው (ዮሐ 16:13) ። ይህ
መንፈስ ለእኛ ሊያደርግልን ስለሚችለው ነገር ምን ይነግረናል?
መንፈስ ቅዱስ ስለ እኛ ሐጢአተኝነት እውነታ ሲገልጽልን ንስሐ
እንድንገባ አያደርገንም። ነገር ግን፣ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር
ታላቁን እውነት ያስረዳናል ነገር ግን፣ እንድናምነው ወይም እንድንቀበለው
አያሰገድደንም። እግዚአብሔር ቀለል ባለ መንገድ እንኳ ሊያስገድደን ቢሞክር
፤ የመምረጥ ነጻነታችንን ይጋፋል፣ ሰይጣን እግዚአብሔር የሰውን ልቦናና
አእምሮአችንን ገፋፍቷል በሚል ይከሳል እናም በታላቁ ተጋድሎ ውስጥ
እግዚአብሔር አጭበርብሯል በማለት ክሱን እውነተኛ ለማድረግ ይጥራል።
ታላቁ ተጋድሎ በሰማይ በጀመረ ጊዜ ፣አባታችን ሰይጣንንም ሆነ ኃጢአት
የሰሩትን መላእክት እርሱ ጥሩ ስለመሆኑ ለማሳመን ወይም ንስሐ እንዲገቡ
ለማስገደድ አልሞከረም። በኤደን ገነት ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ በሆኑበት
ጊዜም ቢሆን፣እግዚአብሄር በገነት መካከል ስለምትገኘው ክፉውንና ደጉን
ስለምትለየው ዛፍ ግልጽ የሆነ ነገር ተናገረ እንጂ የመምረጥ ነጻነታቸውን
በመግፈፍ አዳምና ሄዋን የዛፉን ፍሬ እንዳይበሉ አልከለከላቸውም። ለእኛም
ቢሆን እግዚአብሄር የሚሰራው ከዚህ በተለየ መንገድ አይደለም። ስለዚህ ፣
መንፈስ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ኃጢአት እውነታውን በመግለጽ
እንዲህ ይለናል ‹‹ ባሳየሁህ መሰረት አሁን አንተ ምን ታደርጋለህ ይለናል››
እኛም ፈተና ውስጥ ስንሆን የአባታችን አሰራር ተመሳሳይ ነው። አንዳንድ ጊዜ
ፈተናው የመጣው እኛ ኃጢአታችንን ንስሓ ስላልገባን ይሆናል። አባታችን
በእነዚህ ሁኔታዎች እንዲሰራ፣ የልባችንን በሮች ለመክፈትና ንስሃ እንድንገባ
የሚያደርገውን የእግዚአብሔር ኃይል ወደ ውስጣችን ገብቶ እንዲለውጠን
ከልባችን መምረጥ ያሰፈልገናል።
የእውነት መንፈስ በቅርቡ ወደ ህይወትዎ ያመጣው ለውጥ
ምንድነው? የእርሱን ድምጽ ምን ያህል ይሰሙታል? በጣም
አስፈላጊው ነገር ፣ በምርጫ ነጻነትዎ ምን እያደረጉ ነው?
የእርስዎ ትልቁ ስኬት ምንድነው? እነዚህ ስኬቶች ሁሉም እንዲሁ
ጧት ከእንቅልፍዎ በሚነቁበት ጊዜ በአጋጣሚ የመጡ አይደሉም። በዚህ
ህይወት፣ በመልካም ሁኔታ ስኬት ላይ ለመድረስ፣ጊዜንና ጥረትን ይጠይቃል።
የክርስቶስ ደቀ መዘሙርነታችንም ተመሳሳይ ነገር ነው።
ቆላ 1:28, 29ን ያንብቡ። ምንም እንኳ ጳውሎስ
እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እየሰራ እንደሆነ ቢናገርም፣ በሰው
በኩል መደረግ ስላለበት ነገር ምን ይነግረናል? ዘደ 4:4, ሉቃ
13:24, 1 ቆሮ 9:25, ዕብ 12:4ን ያንብቡ።
በቆላ 1:29 ጳውሎስ በዚህ ሥራ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስላለው
ግንኙነት አስደናቂ መገለጥን አይቷል። እርሱ እንደሚናገረው፣ እየታገለ ነው
ነገር ግን የሚታገለው፣ በእግዚአብሔር ኃይል ነው።
‹‹ሥራ ›› የሚለው ቃል ‹‹ መድከም›› እስክደኪሙ መስራት ማለት
ነው። ይህ ቃል በተለይ የሚያገለግል የነበረው ለሩጫ ተወዳደሪዎች ልምምድ
ላይ ነበር። ቀጥሎ የሚመጣው ‹‹ትግል›› የሚለው ቃል በአንዳንድ ቋንቋዎች
‹‹ማዘን›› የሚል ትርጉም አለው። ስለዚህ የቃሉ ምንነት፣ የሚያሳየው ሯጩ
ሁሉንም ዋጋ ከፍሎ ለማሸነፍ ራሱን ማሰልጠኑን ነው። ነገር ግን ጳውሎስ
ሀሳቡን ሲቀጥል ዘወር ያደርግና፣ እርሱ ራሱን የሚያለማምደው በራሱ ሳይሆን
እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይልን እንደሆነ ይናገራል። ከዚያም ስለ ጳውሎስ
አገልግሎት ቀላል ማጠቃለያ እንድንሰጥ የተደረገ ሲሆን ይህም ሥርዓትንና
የግል ጠንካራ ጥረትን የሚያሳይ አገልግሎት ነው፣ ነገር ግን ይህ ሁሉ
የተከናወነው በእግዚአብሔር ኃይል ነው። ይህ ዓይነት ግኑኝነት የክርስቶስ
ባሕሪይን በእኛ የማሳደግ ሥራ ውስጥ በትክክል ሊሰራ ይችላል።
ይህን ማስተዋል ያስፈልገናል፣ ምክንያቱም አሁን የምንኖርበት ዓለም
በጥቂት ድካም ብዙ መልካም የሆኑ ነገሮችን ለማግኘት ሰዎች የሚጥሩበት
ዘመን ነው። ይህ ሀሳብ ደግሞ ወደ ክርስትና ዓለም ውስጥም ተሹለክልኮ
ገብቷል። አንዳንድ የክርስትና እምነት ወንጌላውያን፣ ብቻ ካመንክ መንፈስ
ቅዱስ ድንቅ በሆነ ሁኔታ በለይህ በኃይል ይወርድና ከሰው በላይ በሆነ ኃይል
አማካይነት ታላላቅ ታዓምራቶችን ታደርጋለህ በማለት ተስፋ ይሰጣሉ። ነገር
ግን ይህ ግማሽ እውነት በመሆኑ፣ እኛ ዝም ብለን ተንደላቀን በሚመች ሁኔታ
ላይ ሆነን የእግዚአብሔር ኃይል እስኪመጣ ድረስ እንድንጠብቅ ያደርገናል።
ጰውሎስ
ስለተናገረው
አንድን
ነገር
ለማሳካት
ስለሚደረገው ጥረት የእርስዎ የግል ልምምድ ምን ይመስላል?
እርሶዎ እንዲታገሉበት እግዚአብሔር በልብዎ ያስቀመጠው ነገር
ምንድነው? ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራስን ማስረከብ እንዴት
ተማሩ?
የፈቃዳችን ታላላቅ ጠላቶች የራሳችን ፍላጎቶች ናቸው። አሁን የምንኖረው ለስሜቶቻችን ብዙ ግፊት በሚያሳድሩ፣ ቁጣን ፍርሃትን እና ግልብ ስሜትን ያለ እኛ ፈቃድ እንዲገዙን በሚያደርጉ ስዕሎችና ሙዝቃ የተሞላ ማህበረሰብ ባህል ውስጥ ነው። ስለሚከተሉት ነገሮች ብዙውን ጊዜ የሚያስቡት እንዴት ነው፣‹‹ ራት መብላት የሚፈልገው ምንድነው›› ‹‹ዛሬ ምን መስራት ነው የምፈልገው›› ‹‹ ይህንን መግዛት ደስ ያሰኝ ይሁን›› ስለዚህ ስሜቶቻችን በምርጫችን ላይ ትልቅ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ መሆኑን ያስገነዝበናል። ስሜቶቻችን ሁልጊዜ መጥፎ ባይሆኑም ነገር ግን፣ ስለሆነ ነገር በማስበው ሐሳብ ውስጥ መልካም ወይም የተሻለ በመምረጥ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በእርግጥ፣ ስሜቶቻችን ይዋሹናል።( የሰው ልብ ከሁሉም በላይ አታላይ ነው።) (ኤር 17፤ 9) ። ስሜት ስለ እውነታው የተሳሳተ ሥዕል በማሳየት ስህተት የሆነ ውሳኔ እንድናደርግ እኛ በራሳችን ውሳኔ ምክንያት ፈተና ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል። ሰዎች በእግዚአብሄር ቃል መሰረት ሳይሆን በራሳቸው ፍላጎት ምርጫ ያደረጉበት ምሳሌ የሚያገኙት የት ነው? ውጤቶቹ ምን ነበሩ? ለምሳሌ ዘፍ 3:6 2 ሳሙ 11:2-4; ገላ 2:11, 12 ይመልከቱ።
1ጴጥ 1:13ን ያንብቡ። ጴጥሮስን ያሳሰበው ጉዳይ ምንድነው፣ አንባቢዎቹ እንዲያደርጉት የሚፈልገው ነገር ምንድነው?
ጴጥሮስ አእምሮአችን ለምንቆጣጠረው ሰውነታችን መሪ መሆኑን
አስተውሏል። አእምሮአችንን የመቆጣጠር ጉዳይን ችላ ካልን ፣ወደ
አእምሮአችን በሚነፍሰው ማንኛውም ስሜት እንነዳለን ማለት ነው።
በጠባቡ መንገድ ወደ በጎች እረኛ ቤት በሚወስደው መንገድ
ሲራመዱ ያስቡት ። በመንገዱ ላይ ብዙ አሳሳች የሆኑ መንገዶች ይገኛሉ።
አንዳንዶቹ መተላላፊያዎች መሄድ ወደማንፈልገው ሥፍራ የሚወስዱ
ናቸው። ሌሎቹ ስሜታችንና ፍላጎታችንን የሚስቡ ሆነው አታላይ ይመስላሉ።
ምናልባትም ከነዚህ መንገዶች አንዱንም ከመረጥን፣ ከትክክለኛው መንገድ
ወጥተን ፣ ለመላቀቅ አስቸጋሪ ወደሆነው ስፍራ እንደርስ ይሆናል።
በጣም አስፈላጊ የሆኑ ምን ውሳኔዎች እየወሰዱ
ነው? ምርጫዎቻችንን በስሜት፣ በግል በፍላጎት ላይ ወይም
በእግዚአብሔር
እናውቃለን?”
ቃል
መሰረት
እያደረግን
እንደሆነ
በምን
“ቀኝ ዓይንህ ካሳተህ፣ አውጥተህ ጣለው፣ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም እሳት ከሚጣል ይልቅ አካላትህ አንድ ቢጠፋ ለአንተ ይሻለሃልና። (ማቴ 5:29) ። እላይ ስላነበብነው ጥቅስ እንወያይበት። ቃሉን ፈጣን ምላሽ ነው ትላላችሁ? ከሆነ ለምን?
ፈጣን ምላሽ የሚያስፈልገው እግዚአብሔር የክርስትያኖችን ህይወት አስቸጋሪ ሊያደርገው ስለፈለገ ሳይሆን፣ ነገር ግን እኛና ባህሎቻችን እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ዓላማና ስርዓት ወጣ ያሉ በመሆናቸው ነው። ሰዎች ብዙውን ጊዜ በራሳቸው እንዲህ በማለት ይደነቃሉ‹‹ እንዲህ ከእግዚአብሔር ልርቅ የቻልኩት እንዴት ነው›› መልሱ የታወቃ ሲሆን እርሱም ቀስ በቀስ ነው የሚለው ይሆናል። ማቴ 5:29, 30 ያንብቡ። ክርስቶስ እየተናገረ ያለው የዝሙት ኃጢአትን በሚመለከት ነው፣ ሆኖም ግን ሌለውን ኃጢአት በሚመለከት ይህ ወሳኝ መመርያ ወይም አስተምህሮ ሊሆን ይችላል። በእርግጥ መመርያው በአጠቃላይ እኛ በክርስቶስ የማደጋችን ጉዳይ ሁሉ ላይ ሊተገበር የሚችል ነው። ክርስቶስ በማቴ 5፤29-30 ባለው ቃሉ ሊነግረን የፈለገው ዋና ነጥብ ምንድነው? በእርግጥ እየተነገረን ያለው ውጫዊ አካላችንን በዚህ ዓይነት እንድንጎደ ነው?
ክርስቶስ አካላችንን እንድንጎዳ እየነገረን አይደለም፣ በፍጹም! ይልቅ
እርሱ እየነገረን ያለው፣ ምንም ያህል ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም አእምሮአችንን
እና ራሳችንን መቆጣጠር እንዳለብን ነው። ጥቅሱ የሚለው እኛ ስንጸልይ
የእኛን መጥፎ የኃጢአት ባህሪያችንን እግዚአብሔር ያስወግደዋል የሚል
እንዳልሆነ ያስተውሉ። አንዳንዴ እግዚአብሔር በጸጋው እንደዚህ ሊያደርግ
ይችላል፣ነገር ግን እርሱ አንዳንድ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ በራሳችን እንድናቋርጥ
ወይም አዲስ የሆነ እኛ ለማድረግ ፍላጎት የሌለንን ነገር መስራት እንድንጀምር
ይጠራናል። ምንም ዓይነት ፈተና ይሁን! ትክክለኛ ምርጫ ማድረግ ባዘወተርን
መጠን፣ በህይወታችን የሚመጡ የፈተና ጫናዎች እንዲቀሉና ፈተናን የማሸነፍ
ጥንካሬን እንድናገኝ ይረዳናል።
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በዙሪያችን ብዙ የሚረብሹና
አፍራሽ የሆኑ ነገሮች ሲኖሩ፣ ፈተናን አስተሳሰባችን ለመያዝ
ይጠቀማል። ከእግዚአብሔር ምን ያህል እንደራቅን የምንረዳው
ፈተና ሲደርስብን ነው። ምናልባትም ፈተናው አባታችን ለእኛ
ወዳለው ዕቅድ እድንመለስ አስቸኳይ ጥሪ ሊሆነን ይችላል።
ያዕቆብ ከአምላክ ጋር የታገለበትን ታሪክ ያንብቡ። (ዘፍ 32)። በትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ቢሆን እንኳ፣ ይህ ታሪክ ስለ ጽናት ምን ያስተምረናል? ጥያቄውን ከመመለስዎ በፊት ያዕቆብ የነበረበትን ሁኔታ በሙሉ በሃሳብዎ ያሰላስሉ።
ትክክል የሆነውን ነገር በማወቅ ፈቃዳችንን ትክክለኛ ነገር
እንዲለማመድ እናደርጋለን፣ ነገር ግን በትልቅ ተጽዕኖ ሥር በምንሆንበት
ጊዜ፣ ከእግዚአብሄር ጋር ተጣብቀን ለመቆየትና በተስፋዎቹ ለመጠማጠም
እንቸገራለን። ይህ የሚሆነው እኛ ፈሪዎችና ደካሞች ስለሆንን ነው። ስለዚህ
፣የክርስቲያን ዋንኛው ጥንካሬ፣ ጽናት ነው እርሱም ፣ ተስፋ በሚያስቆርጥ ነገር
ውስጥ፣ወደፊት መጓዝ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ ወስጥ ከሚገኙ፣ በችግር ውስጥ ሆኖ ህይወትን
በጥንካሬ የመምራት አንድ ትልቅ ምሳሌ ያዕቆብ ነው። ያዕቆብ ብኩርናውን
ለማግኘት ወንድሙን ኤሳውንና አባቱን ካታለለበት ከብዙ ዓመታት
ጀምሮ፣(ዘፍ 27) ኤሳው ሊገድለው ስለሚፈልገው የሚኖረው በሽሽት ነበር።
ምንም እንኳ፣ ወደ ሰማይ በደረሰው መሰላል ባየው ህልም፣ እግዚአብሔር
አስደናቂ ተስፋ፣ ምሪትና በረከት የተሰጠው ቢሆንም (ዘፍ 28) እርሱ ይፈራ
ነበር። ያዕቆብ እግዚአብሄር ከብዙ ዓመታት በፊት ይቅርታ አድርጎለት
የሰጠው ዋስትና እስከ አሁን እውነት ስለመሆኑ ለማመን ተቸግሮ ነበር።
እርሱ ከክርስቶስ ጋር በታገለ ጊዜ የጭኑ ሹልዳ እንዲያነክስ ስፍራውን ለቀቀ።
ህመሙ በጣም ከባድ ስለ ነበር ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መታገል አልቻለም። በትንሽ
ጊዜ ከትግል ወደ ልመና ተለወጠ። ያዕቆብ ህመሙ ከባድ ቢሆንም፣ በረከቱንና
ዋስትናውን አስኪያገኝ ድረስ በክርስቶስ ላይ ተጣበቀ። ክርስቶስም እንዲህ
አለ ‹‹ሌሊቱ ነግቷልና ልሂድ›› (ዘፍ 32፡ 26)።
የያዕቆብ በረከት የመጣው በመከራ ውስጥ በጽናት ስለቆመ
ነው። ለእኛም እንዲሁ ነው። እግዚአብሔር ምናልባት የእኛንም ሹልዳ ቦታ
በማስለቀቅ እንድናነክስ በማድረግ፣ በህመማችን በኩል አድርጎ በእርሱ
መደገፍን እንድንለማማድ ሊጠራን ይችላል። በእርግጥ እግዚአብሔር ህመሙ
እንዲቀጥል ሊፈቅድ ይችላል፣ ያዕቆብ ወንድሙን ባገኘው ጊዜ ገና እያነከሰ
ነበር። ይህ በዉጪ ስታይ ድካም ነው፣ ለያዕቆብ ግን የጥንካሬው ምልክት
ነበር።
በወዳጅነት ፣በአኗኗር፣ በሚያነቡት ነገሮች፣የጤናዎ
ልምምድ እና መንፈሳዊ ህይወትዎ፣ በፈተናና ተስፋ በመቁረጥ
መካከል ሆነው በእግዚአብሔር በመጽናት እንዲቀጥሉ የሚያደርግ
ምን ዓይነት ተጨባጭ ምርጫዎችን እየመረጡ ነው?
አበውና ነብያት በሚለው ገጽ 195-203፣ ወደ ክርስቶስ
የሚያመራ መንገደ ገጽ 43-48 ያለውን አንብቡ።
“ይህ እንግዲህ በሰው ባህሪይ ላይ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገርን
የሚፈጥር የሆነው ፣ያኔ የሰው ልጆች በሰይጣን ቁጥጥር ውስጥ በወደቁ ጊዜ፤
እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የራሱን ደስታ በሰዎች ላይ ለመጫን ብቻ ሳይሆን
በአጠቃላይ የሰዎችን ህይወት ምስቅልቅል ያለ ለማድረግና ለማሰቃየት
ሳያቋርጥ እየሰራ ነው።
“የእግዚአብሔርን እርዳታ ለማግኘት፣ ሰዎች ድካማቸውንና
የጎደለባቸውን ነገር ማወቅ አለባቸው፤ ሰው በራሱ ላይ ለሚመጣው ለውጥ
አእምሮውን ለመጠቀም፣ጽኑ ለሆነው ለማይነወጥ ልባዊ ጻሎት መነሳሳት
ያስፈልገዋል። ትክክለኛ ያልሆኑ ልምዶችና ባህሎች መወገድ አለባቸው፣ እናም
እነዚህን ትክክል ያልሆኑ ባህሎችና ልምዶች ለማስወገድ በሚደረገው ውሳኔ
በተሞላበት ሥራ እና ትክክለኛ መርሆዎችን ለማስጠበቅ በሚደረግ ትግል
ብቻ ድል ይገኛል። ብዙዎች እግዚአብሔርን በመጠበቅ ብቻ፣ ለራሳቸው
እንዲሰሩ የሰጣቸውን ኃይል ሳይጠቀሙ የታቀደላቸው የስልጣን ደረጃ
ላይ ሊደርሱ አይችሉም። እግዚአብሔር እንዲጠቀማቸው ገጣሚ የሚሆኑ
ሰዎች በጣም ከባድ በሆነ አእምሮአዊና ግብረ-ገባዊ ሥርዓት የሰለጠኑ መሆን
አለባቸው፣ እነዚህን ደግሞ መለኮታዊውን ኃይል ከሰው ጥረት ጋር በማገናኘት
እግዚአብሔር ይደግፋቸዋል። ኤሌን ዋይት አበውና ነቢያት ገጽ 248።
1. የእኛ ፈቃድ ብዙውን ጊዜ ‹‹በሰይጣን ቁጥጥር ሥር የወደቀ›› ስለመሆኑ ምን ያህል ያስተውላሉ? በክርስቶስ ባህሪ ላይ በማትኮር የወደቅን መሆናችንን በመረዳት የእግዚአብሔር ጸጋ በእኛ ላይ ምን ያህል እንደሆነ የምንረዳው እንዴት ነው? 2. በጌቴሴማኔ የነበረውን የክርስቶስን ታሪክ ያንብቡ። (ማቴ 26:3642)::የትኞቹ የክርስቶስ የግሉ ባህሪያት ናቸው ከእግዚአብሄር ባሀሪይ ጋር ይቃረኑ የነበሩት? ከዚህ ምን እንማራለን? 3. እንደ ክፍል ፣ በባህላችን ውስጥ ስለሚገኙ የተለያዩ ለሰይጣን ጥቃት የተጋለጥን እንድሆን የሚያደርጉ እና የመከላከል አቅማችንን ስለሚያዳክሙ ነገሮች ተነጋገሩ። ሌሎች የቤተከርስቲያን አባሎቻችን ከዚህ አደጋ እንዲጠነቀቁ ምን እናደርጋለን? 4. አንድ በቤተክርስቲያን ለረዥም ጊዜ ያልነበረ ተስፋ ሊቆርጥ የተቃረበ ወይም ተስፋ የቆረጠ የምታውቁት ሰው ይኖር ይሆን? ይህን ሰው ለማበረታታት ከክርስቶስ እንዳይርቅ ለማድረግ እንደ ቡድን ምን ታደርጋላችሁ?