የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

በፈተና ውስጥ ከክርስቶስ ጋር


የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 3ኛ ሩብ ዓመት 2022

ከሐምሌ 16-22

5ኛ ትምህርት

Jul 23 - Jul 29




ከባድ ሙቀት



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ 22, ሆሴ 2:1-12, ኢዮ 1:6-2:10, 2 ቆሮ 11:23-29, ኢሳ. 43:1-7ን ያንብቡ።


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል። (ኢሳ 53:10)።

ሉ ዊስ የተባለች የአንድ ተዋቂ ክርስቲያን ባለቤት በሞት አፋፍ ሆና እንዲህ አለች፡ “እግዚአብሄርን ማመኔን በማቆም አደጋ ውስጥ ነኝ። ትልቁ አደጋ ደግሞ ስለ እርሱ እንደዚህ አደገኛ ነገር ማመን መጀመሬ ነው። የመጨረሻ ማጠቃለያዬ ደግሞ እግዚአብሔር የለም ማለት ነው። ነገር ግን፣ በእርግጥ እግዚአብሔር እንድህ ነው?”—A Grief Observed (New York: Harper Collins Publishers, Inc., 1961), pp. 6, 7. በእውነት ነገሮች ጎጂ ሲሆኑ ፣ አንዳንዶቻችን እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ እንቃወማለን። ለአንዳንዶች ደግሞ ልክ እንደ ሉዊስ ስለ እግዚአብሔር ያለንን አመለካከት እንቀይርና መጥፎ መጥፎውን ማሰብ እንጀምራለን። ጥያቄ የሚሆነው፣ ሙቀቱ ምን ያህል ነው የሚለው ነው? እግዚአብሔር የእርሱን ህዝብ የእርሱ ዋና ዓላማ ወደሆነው፣ የልጁን መልክ ወደምመስል ለማድረስ በእኛ ላይ ምን ያህል እሳት ነው ፈቅዶ የሚለቀው?” (ሮሜ 8:29) የሳምንቱን እይታ: እግዚአብሔር እርሱን በሚወዱትና ሊያውቁት በሚፈልጉት ዘንድ በትክክል ስለ እርሱ ለመስተዋል በሚያስቸግር አደጋ ውስጥ እንዲሆን የሚፈቅደው ለምንድነው? እግዚአብሄር የእርስዎን ማንነት ለመለወጥ እና ‹‹የልጁን መልክ እዲመስሉ›› ለማድረግ ሲል ለማስተዋል በሚያስቸግር ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ ፈቅዶ ያውቃል? *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሀምሌ 23 አጥንተው ይዘጋጁ።

ሐምሌ 17
July 24

አብርሃም በመስቀል ላይ


ዘፍጥረት 22ን ያንብቡ። ምንም በሌለበት እግዚአብሔር ምንም መግለጫ ሳይሰጥ አብርሃም ልጁን ለሚቃጠል መስዋዕት እንዲሰጠው ጠየቀው። አብርሃም ምን እንደተሰማው ማስተዋል ይቻላል? ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር የራስን ልጅ ለመስዋዕት ሲጠይቅ ሙሉ በሙሉ አመጽ የሚመስል ሀሳብ ነው። አብርሃም ራሱ ተቀባይነት ያለው ነገር ነው ቢል እንኳ እግዚአብሔር የገባው የተስፋ ቃልስ የሚፈጸመው እንዴት ነው? አብርሃም የራሱ ልጅ ከሌለው፣ የተስፋው ቃል ሊፈጸም አይችልም።

እግዚአብሔር አብርሃምን ልጁን እንዲሰዋ የጠየቀበት ምክንያት ምንድነው? እግዚአብሔር ሁሉን የሚያውቅ ከሆነ፣ እዚህ የተፈለገው ዋና ነገር ምንድነው?



እግዚአብሔር ጥያቄን ሲጠይቅና ለነገሮች ጊዜ ሲመድብ በዘፈቀደ አይደለም። በእርግጥ፣ እግዚአብሔር አብርሃምን እጅግ በጣም ፈተኝ፣ በጣም ጥልቅ፣ አስጨናቂ የሆነውን ጊዜ እና የዘመናት ሸክሙ እጅግ ከባድ ሆኖበት መሞትን እስኪናፍቅ ድረስ የሚያደርሰውን ጊዜ ነበር የጠበቀው። ኤሌን ዋይት አበውና ነብያት ገጽ 147:: ይሄ ፈተና የእብድ አምላክ ፈተና ይሆን? አይደለም፣ በፍጹም አይደለም፣ እነዚያ አብርሃም ያሳለፋቸው የሚያስፈሩ የጭንቅና የመከራ ቀናት የተፈቀዱት፣ አብርሃም ከራሱ ልምምድ የተነሳ የማይገደበው እግዚአብሔር፣ ውስን ለሆነው የሰው ልጅ (ሰብዓዊ ዘር) ያደረገውን ታላቅ መስዋዕትነት ለማስተዋል እንዲችል ለማድረግ ነው። አበውና ነብያት ገጽ 154። ይህ ፈተና እንጂ የአብርሃምን ልጅ ለመግደል የታሰበ ነገር አይደለም። ይህ እግዚአብሄር አንዳንድ ጊዜ ስለሚሰራባቸው መንገዶች ምን ዓይነት እንደሆኑ ዋና ዋና ምልክቶችን ያሳየናል። እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር መጨረሻ የሆነውን ጥያቄ ሊጠይቀን ይችላል። አንድ ቦታ ሊልከን ይችላል፣ እርሱ የሚፈልገው መሄድ መጀመራችንን እንጂ ቦታው ድረስ እንድንደርስ ላይሆን ይችላል። ለእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊው ነገር የሚሆነው መጨረሻው ሳይሆን፣ በነገሮቹ ውስጥ ስናልፍ መቀረጻችን ነው።

ኢየሱስ ‹‹ አባታቸሁ አብረሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴት አደረገ፣ አየም ደስም አለው።›› ያለው የአብረሃምን ልምምድ እያሰበ ሊሆን ይችላል። (ዮሐ8:56) አብርሃም የሰይጣንን ሀሳብ ባያስወግድ ኖሮ በዚህ አመለካከት ሊስት ይችል ነበር። የአብረሃም በመከራ ውስጥ ጸንቶ የመቆየቱ እና በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ መማሩ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለይቶ የሚያውቅ በመሆኑ ነው። የእግዚአብሔርን ድምጽ እንዴት ያውቃሉ? እግዚአብሄር ለእርስዎ እየተናገረ እንደሆነ በምን ይረዳሉ? የእርሱን ሀሳብ ማወቅያ መንገድ ምንድነው?

ሐምሌ 18
July 25

ጠማማ እሥራኤል


የሆሴዕ ታሪክ ለእኛ የሚያስተምረን አንድ ኃይለኛ ትምህርት አለ ። የሆሴዕ ሁኔታ በጣም የተለየ ነው። ሚስቱ ጥላው ልጆቹን ይዛ ሄደች። ሚስቱ ከወንድ ጋር ባላት ግንኙነት ታማኝ ባትሆንም መልሶ አምጥቶ ፍቅር እንዲያሳያት እግዚአብሔር ሆሴዕን ነገረው። ይህ ምሳሌ ማለት የእግዚአብሔርና እስራኤል ምሳሌ ነው።እስራኤል እግዚአብሔርን ትተው ከሌሎች አማልክት ጋር በመሆን መንፈሳዊ ምንዝርን ፈጽመዋል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር አሁንም በመውደድ ፍቅሩን እያሳያቸው ነው። ነገር ግን እስቲ የእግዚአብሔርን አሰራር ተመልከቱ! ሆሴዕ 2:1-12ን ያንብቡ። እግዚአብሔር እስራኤልን ወደ ራሱ ለመሳብ የተጠቀመበት ዘዴ ምንድነው? ይህ ልምድ ምን ስሜት ፈጠረብዎ? ሆሴዕ 2:2-3



_ ሆሴዕ 2:5-7



_ ሆሴዕ 2:8, 9



ሆሴዕ 2:10



ይህ ታሪክ እግዚአብሄር እኛን ወደ ንሰሃ የሚያመጣበትን ሁለት ልምምዶች ያነሳል። የመጀመርያ፣ እኛ እግዚአብሔር ሥራ ላይ መሆኑን አውቀን ራሳችን አንጠነቀቅም። እስራኤል በዚህ ሁሉ ከባድ ልምምድ ውስጥ በሚያልፍበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእነርሱን ማዳን እየሰራ እንደሆነ ለማስተዋል ከባድ ነበር። እምነታችን በሹል እሾሆች በሚዘጋበት ጊዜ፣ ወዴት መሄድ እንዳለብን ማወቅ ሲሳነን (ሆሴ 2፡6) ለህይወት የሚያስፈልጉንን መሰረታዊ ነገሮችን ስናጣና ስናዝን (ሆሴ 2:9 10) አባታችን እግዚአብሔር በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ውስጥ አለ? እኛ የሚሰማን ምንም ይሁን ምን ፣ እግዚአብሔር እየሰራ ያለው ግን እኛን ስለሚወደን ወደ ንሰሐ ለማምጣት ነው።

ሁለተኛ፣ እግዚአብሔር በሥራ ላይ እያለ ባለማስተዋል አደጋ ውስጥ እንገባለን። እግዚአብሔር ሥራ ላይ መሆኑን ልንገነዘብ እንችላለን ፣ ነገር ግን እርሱ የሚሰራውን አንወደውም። አዝነንና ተጎድተን እያለ እግዚአብሔርን ስለ ጭካኔውና፣ በችግራችን ውስጥ ዝም በማለቱ፣ ወይም ለእኛ ጥንቃቄ ባለማድረጉ መኮነን ቀላል ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ሁልጊዜ የፍቅር ቃል ኪዳኑን ለማደስ እየሰራ ነው።

ሆሴ 2:14-23ን ያንብቡ። ይህ ንባብ ስለ እግዚአብሔር ምን ይገልጻል? በየትኛውም የኑሮ መንገድ ከእግዚአብሔር እየኮበለሉ እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ እንዲነግርዎ ይጠይቁ። ስህተት መሆንዎን ካመኑ ለምን መከራ ይጠብቃሉ? አሁን ያለዎትን ነገር ሁሉ ለእርሱ እንዳያስረክቡ የከለከለ ምንድነው?

ሐምሌ 18
July 25

በአምልኮ መቋቋም


ኢዮ 1:6–2:10 ያንብቡ። የእዮብ መከራ ምክንያቱ ምንድነው?



እዚህ አንድ አስገራሚ ነገር አለ። መላዕክት እግዚአብሔርን ሊገናኙ መጡ ሰይጣንም ከእነርሱ ጋር መጣ። እግዚአብሔርም ሰይጣንን ከወዴት እንደመጣ ጠየቀው፣ሰይጣንም ‹‹በምድር ወዲያና ወዲህ ሲዞር›› እንደ ነበር ተናገረ። (ኢዮ 1፡7)። ‹‹እግዚአብሔርም አገልጋዬን ኢዮብን አየኸውን›› አለው ኢዮ1:8። የተጠየቀው ጥያቄ ራሱ ግልጽ አልነበረም ሆኖም ጠያቂው ግን ተለይቶ ይታወቅ ነበር። ኢዮብ እንዲፈተን ያደረገው ሰይጣን ሳይሆን እግዚአብሔር ነው። ቀጥሎ የሚከሰተው ነገር ምን እንደሆነ በግልጽ እያወቀ እግዚአብሔር ኢዮብ የሰይጣንን ትኩረት እንዲስብ አደረገ። ኢዮብ በምድር ወደፊት የሚደርስበት ፈተና ምን ዓይነት እንደሆነ ምንም ዓይነት ዕውቀት አልነበረውም። እንድህም ቢሆን በግልጽ የሚታወቀው ነገር ቢኖር መከራውን የሚያደርሰው ሰይጣን እንጂ እግዚአብሔር አይደለም፣ በተጨማሪም ደግሞ የኢዮብ ንብረት፣ ልጆች፣ እንዲሁም በሰውነቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት ጭምር እንደጎዳ ፈቃድ ያገኛው ከእግዚአብሄር ነበር። እግዚአብሔር እዮብ እንዲሰቃይ ፈቃድ እየሰጠ ከሆነ በቀጥታ ስቃዩን እያደረሰ ያለው ሰይጣን ሆነ እግዚአብሔር ምን ልዩነት ያመጣል? እግዚአብሔር እያወቀ በእዮብ ላይ ይህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ተሳትፎ እያደረገ እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል? ይህ እግዚአብሔር በልዩ ሁኔታ ያደረገው ነገር ነው ወይስ ዛሬም ከእኛ ጋር የሚሰራው እንዲህ ነው? በእዮ 1:20, 21 እዮብ ለፈተናው መልስ የሰጠው እንዴት ነበር?



ለእንደዚህ ዓይነት ችግር በሁለት መልኩ ምላሽ መስጠት ይቻላል። በማማረርና በመቆጣት፣ ለምናምነው አምላክ ጀርባ በመስጠት፣ ጨካኝና የሌለ አድርገን ማመን ወይም የበለጠ ወደ እርሱ በመቅረብ መጣበቅ ይሆናል። እዮብ የመጣበትን ውርጅብኝ ያለፈው በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ በመሆንና እርሱን በማምለክ ነበር።

በእዮብ 1:20, 21 በመከራ ጊዜ ሊጠቅሙን የሚችሉ ሦስት የአምልኮ ዓይነቶችን እንመለከታለን። የመጀመሪያው፣ እዮብ ራሱን አቅመ-ቢስ መሆኑን በመረዳት ወደ ምንም ነገር ተስፋ አያደርግም‹‹ራቁቴን ከእናቴ ማህጸን ወጣሁ ራቁቴን እመለሳለሁ››(እዮ1:21) ሁለተኛ፣ እግዚአብሔር አሁንም ሁሉንም ነገር ይቆጣጠራል። “‘እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ” (እዮ 1:21)። ሦስተኛ ፣ እዮብ እምነቱን እንደገና በመፈተሸ በእግዚአብሔር ጽድቅ ላይ ያጸናል። ‹‹ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን›› (እዮ1:21)። በመከራዎች ውስጥ ሲሄዱ ፣እዮብ የሄደባቸውን ደረጃዎች ይሂዱ። እነዚህ ነገሮች ምን ያህል ጠቃሚ ናቸው?

ሐምሌ 20
July 27

በተስፋ መከራን ማምለጥ


“በእስያ ስለደረሰብን መከራችን፣ ወንድሞች ሆይ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ህይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከአቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶን ነበር። አዎን ሙታንን በሚያስነሳ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር” (2 ቆሮ 1:8, 9)።

ጳውሎስ እንደ እግዚአብሔር የተመረጠ ሐዋሪያ፣ ከብዙዎች የበለጠ በፈተናዎች ውስጥ አልፏል። ሆኖም ፈተናው ጳውሎስን አላጠፋውም። ይልቅ ለእግዚአብሔር ምስጋናን በመስጠት አደገ እንጂ። የደረሰበትን የመከራዎች ዝርዝር ከ2ቆሮ 11:23-29ድረስ ያንብቡ። አሁን 2 ቆሮ1:3-11ን ያንብቡ። በ 2ቆሮ 1:4 ጳውሎስ የእግዚአብሄርን ፍቅርና ማጽናናት ለመቀበል “እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፤ ስለዚህ እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን። መከራ ለአገልግሎት መጠራት ሆኖ የሚያገለግለው በምን ያህል ደረጃ ነው? ይህ ሊሆን እንደሚችል በመረዳት ምን ያህል ዝግጁ ሆነን እንጠብቃለን? እግዚአብሄር የተጎዱትን በእኛ በኩል ሊያገለግላቸው ይፈልጋል። ያ ማለት አስቀድሞ እኛ ያንን በመሰለ ጉዳት ወይንም ችግር እንድንፈተን ካደረገን በኋላ መጽናናቱን የሚሰጠው በሐሳብ ደረጃ ሳይሆን ከልምምዳችን በመነሳት ስለ እግዚአብሔር ማጽናናትንና ፍቅር መንገር እንድንችል ያደርገናል። ይህ የክርስቶስ ህይወት ተሞክሮ ነው። (ዕብ 4:15)::

የጳውሎስ በግልጽ የተጻፉት የመከራ ዝርዝሮች እኛ ለእርሱ እንድናዝንለት አይደለም። እነርሱ የተጻፉት እኛ በምንም ዓይነት መከራ ጥልቀት ውስጥ እንኳ ብንሆን እርሱ ፍቅሩንና ማጽናናቱን እንደሚያመጣልን ለመግለጽ ነው። ስለ ህይወታችን ሰግተን ሊሆን ይችላል፣ እንገደላለን ብለን ሰግተንም ይሆናል፣ነገር ግን አትፍሩ እግዚአብሄር በእርሱ እንድንደገፍ እያስተማረን ነው። በእርሱ መታመን እንችላለን፣ ‹‹ አምላካችን የሞቱትን ያስነሳልና›› (2ቆሮ 1:9)

ጳውሎስ ትኩረቱን ወንጌልን በማወጅ ላይ ሲያደርግ በሚመጣው ዘመን እግዚአብሔር እርሱን ከመከራ እንደሚያስጥለውም ያውቅ ነበር። የጰውሎስ በእግዚአብሔር ጸንቶ የመቆየቱ አቅም 2 ቆሮ1:10, 11 በሦስት ነገሮች ተደግፏል። አንደኛ፣ የእግዚአብሔር የበላይነት ‹‹ እርሱም ይህን ከሚመስል ሞት አዳነን፣ ያድነንማል።›› (2ቆሮ:10):: ሁለተኛ ፣ የጳውሎስ ትኩረት በእግዚአብሔር ላይ ብቻ በመሆኑ ‹‹ ወደፊት ደግሞ እንዲያድነን በእርሱ ተስፋ እናደርጋለን›› (2 ቆሮ 1:10)ሦስተኛ የቅዱሳን ያልተቋረጠ ጸሎት‹‹ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን››(2ቆሮ 1:11)::

በራስዎ ከደረሰብዎ ነገር የተነሳ ከሚሰመዎት ችግር ውስጥ ለመውጣት በሚያደርጉት ትግል የጳውሎስ ተሞክሮ ምን ትምህርት ይሰጥዎታል?

ሐምሌ 21
July 28

ከባድ ሙቀት


ከአሁን ቀደም በዚህ ሩብ ዓመት ፣ እግዚአብሔር በህይወታችን ክርስቶስን የሚመስል ባህሪይ እንድንለማመድና በህይወታችን ንጹሃን እንድንሆን ሊያደርገን የሚጠቀማቸውን የተለያዩ ፈተናዎችን በስፋት አይተናቸዋል። ነገር ግን፣ አንዳንድ ሰዎች ይህን ምሳሌ በማየት እግዚአብሔር ሥራን የሚጠይቅ አምላክ ነው ብለው ሊደመድሙ ይችላሉ። በእርግጥ አንዳንዶች፣ ‹‹ እግዚአብሔር ለእኛ መልካም እንዲሆንልን ይፈልጋል፣ ነገር ግን እነዚህ ምሳሌዎች ፍቅርንና ርህራሄን አያሳዩም ይላሉ›› በዚህ ፈንታ እግዚአብሔር ጨካኝ ይመስላል። እግዚአብሔር በዓላማ፣ በፊታችን የምንፈተንባቸውን ከባድ ጊዜያት በሚያመጣበት ጊዜ እኛ የምናደርገው ምንም ነገር አይኖርም።

በዚህ ኃጢአት በሞላበት ምድር ስንኖር ፣ ነገሮች ለምን እንደሚከሰቱ የምናውቀው በጣም በጥቂቱ ብቻ ነው። በሰማይ እጅግ ብዙ ነገሮችን እናውቃለን።(1ቆሮ 4:5, 1ቆሮ 13:12)ነገር ግን ለአሁኑ ነገሮች መልካም መስለው ባይታዩንም እንኳ እግዚአብሔር እንዳለና ለጉዳዮቻችን እንደሚጠነቀቅልን በማመን እንኖራለን። ኢሳያስ ይህንን ውጥረት ጥሩ አድርጎ ይገልጸዋል። ኢሳ 43:1-7ን ያንብቡ። በቁጥር 2 ፣ ህዝቡ በእሳትና በውኃ መካከል እንደሚያልፉ ይናገራል። እነዚህ በጣም አስቸጋሪ (አደገኛ) የሆኑትን ጊዜያት የሚያሳዩ ምሳሌዎች ቢሆኑም፣ ነገር ግን ቀይ ባህርንና የዮርዳኖስን ወንዝ ስለ መሻገር፣ ሁለቱን አስፈሪ ጊዜያት፣ የሚያሳዩ ሲሆኑ ሁለቱም ግን ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገርን የሚያመለክቱ ናቸው ። ምናልባትም እግዚአብሔር ህዝቦቹን ከእነዚህ አደገኛ ጊዜያት እንደሚጠብቃቸው እና ቀላል በሆነው መንገድ ሊመራቸው ይችል እንደ ነበር ልትጠብቁ ትችላላችሁ። ነገር ግን ልክ በመዝሙር 23 እንደተጻፈው እረኛ፣ የእግዚአብሔር ህዝብ አስቸጋሪ ጊዜያት በሚመጡበት ጊዜ፣ እርሱ ከህዝቡ ጋር ስለሚሆን መሸበር የለባቸውም። ወደ ኋላ መለስ ብለው ኢሳ 43:1-7ን ያንብቡ። በውኃና በእሳት ውስጥ እግዚአብሔር ህዝቦቹን እንዴት እንደሚያጽናናቸው ጻፉ። ይህ ጽሁፍ በአእምሮ ውስጥ የሚፈጥረው ነገር ምንድነው? ከዚህ ለራስዎ እንደሆነ አድርገው የሚወስዱት ተስፋ የትኛው ነው?

በተማርነው መሰረት እግዚአብሔር የሚያቀርባቸውን ፈተናዎች በሶስት እናጠቃልላቸዋለን። አንደኛው፣ የእግዚአብሔር ከባድ እሳት ኃጢአትን እንጂ እኛን ለማጥፋት አይደለም። ሁለተኛ፣ የእግዚአብሔር ከፍተኛ እሳት እኛን ግራ ለማጋበት ሳይሆን፣ ከፍጥረታችን እንደነበርነው ንጹህ ሊያደርገን ነው። ሦስተኛ፣ በሚደርስብን ማኝኛውም ነገር፣ ለብቻችን የማይተወንና የሚያደርግልን ጥንቃቄም በፍጹም የማይለዋወጥ መሆኑን እንረዳለን። የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር አሰራርና ባህሪይ ምን ይነግሩናል? መዝ 103:13 14 ማቴ 28:20 1 ቆሮ 10:13 1 ጴጥ 1:7 በህይወትዎ ስለነዚህ ጥቅሶች ጭብጥ ያለዎት ልምምድ ምንድነው?

ሐምሌ 22
July 29


ተጨማሪ ሀሳብ


በኤለን ዋይት ጽሁፍ “የእምነት መፈተን ”አበውና ነብያት ገጽ 145–155 ‹‹እግዚአብሔርን አመስግኑ” በቤተክርስቲያን ምክሮች ገጽ 315– 319 እንድህ ይላል፡:

“እግዚአብሔር ህዝቡን ሁልጊዜ በመከራ እሳት ይፈትናቸዋል። ከክርስቲያን ህይወት ባህሪይ ውስጥ ፣ እግዚአብሔር እውነተኛውን ወርቅ ከቆሻሻው የሚለየው በዚህ ትልቅ እሳት አማካይነት ነው። ክርስቶስ ፈተናውን ይመለከተውና፣ ይህንን የከበረ ማዕድን ንጹህ ለማድረግና የእርሱን ፍቅር ለማንጸባረቅ ምን እንደሚያሰፈልግ ያውቃል። እግዚአብሔር የእርሱን አገልጋዮች የሚቀጣው በቅርበት በመሆንና ፈተናን በማቅረብ ነው። እርሱ በአንዳንዶች ውስጥ ሥራውን ወደፊት ሊያስቀጥሉ የሚችሉበት ኃይል እንዳላቸው ያይና፣ እነርሱን ወደ ፈተና በማቅረብ ባህሪያቸው ላይ ያለውን ድካም እንዲገነዘቡ በማድረግ በእርሱ ለይ እንዲደገፉ ያደርጋቸዋል። በዚህም ዓላማውን ይፈጽማል። እነርሱ የተማሩ፣ የሰለጠኑና፣ሥነ-ምግባር ያላቸው፣ ሲሆኑ ኃይል የሰጣቸው ወሳኝ ዓላማ ለማከናወን ዝግጁ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። አበውና ነብያት ገጽ 129, 130::

“በእግዚአብሔር አቅራቢነት ፈተናን እንድንቋቋም ከተደረግን ፣ ደግፎ የሚይዘን የእግዚአብሔር እጅ መሆኑን በመገንዘብ፣ መስቀሉን በታዛዥነት ተቀብለን መራራውን ጽዋ ለመጠጣት እንዘጋጅ። በቀንም ሆነ በማታ እርሱን እንመነው። እርሱ ሁሉንም ነገር የሚሰጠን ለመልካም እንደሚሆንልን አናምንምን? . . . በስቃይ ምሽቶች እንኳ ሆነን በጎልጎታ መስቀል ላይ የተገለጸውን ፍቅር በማሰብ በምስጋና ከፍ ብለው የሚሰሙ ድምጾችን እርሱ ቸል ይላቸዋልን?” ኤሌን ዋይት የቤተክርስቲያን ምክሮች ገጽ 316 ጥራዝ 5።


የመወያያ ጥያቄዎች



1. በክፍላችሁ ውስጥ አንድ ሰው የደረሰበት ፈተና እንደ አብረሃም ፈተና ዓይነት እንኳ ባይሆን፣ አሁንም ድረስ ከባድ የሆነበት ካለ ደጋግሞ ይቁጠር። ከዚህ ሰው ድል ስኬት ወይም ውድቀት ምን ትምህርት ያገኛሉ?

2. ክርስቶስ ወደ መስቀሉ ከመሄዱ በፊት የነበሩትን 24 ሰዓታት ክለሳ ያድርጉ። ምን ዓይነት ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ናቸው የገጠሙት? እንዴት አለፋቸው? እና በራሳችን ፈተናዎች ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ በገጠሙን ነገሮች ወይም ፈተናዎች ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ምን ዓይነት መርሆዎች ከእርሱ ማግኘት እንችላለን?

3. በዚህ ሳምንት በመከራ ውስጥ ሆነን ሌሎችን እንዴት ማገልገል እንዳለብን የተማርነውን ትምህርት እንወያይበት። ይህ ምንም ያህል እውነት ቢሆንም እንኳ ሊያጋጥመን የሚችለው ፈተና ምን ይሆን?

4. ኤሌን ዋይት ‹‹በብርሃንም ሆነ በጨለማ እርሱን ተስፋ እናድርግ›› ያለችው ከማድረግ ይልቅ ለመናገር የሚቀል ነው። እንደዚህ ለማድረግ የሚያሰችል እምነት ለማደበር፣ አንዳችን ሌላችንን ለመርዳት የምንችለው እንዴት ነው? በመጥፎ ጊዜ እግዚአብሔርን ማመን አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA union SSL