የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ፊሊ 4:4-7, ኢያሱ 5:13–6:20 መዝ 145, ሐዋ 16:16-34, 2 ቆሮ 20:1-30.
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ!” (ፊሊጵ 4:4) ።
ደ
ስ ሲለን የምስጋና ጩኃት ለአምላካችን ማቅረብ ቀላል ነው። ነገር
ግን ነገሮች መጥፎ ስሆኑብን፣እጅግ አስቸጋሪ በሚበሉ ነገሮች
ውስጥ ስንገባ እና የፈተናው እሳት በሚያቃጥልበት ጊዜ ማመስገን
ቀላል አይሆንም። ሆኖም ግን በዚህን የመከራችን ጊዜ፣ ከቀድሞው ይልቅ
ልናመሰግን ይገባናል ምክንያቱም፣ በመከራ ውስጥ በእምነት የሚያቆመን
ማመስገን ነውና።
በእርግጥ፣ ማመስገን ጨለማ የሆኑብንን ነገሮች እንኳ ቢሆን
በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን እና ሁኔታዎችን በመለወጥ ሳይሆን እኛን በመለወጥ
እኛን የሚገዳደሩንን ነገሮች መቋቋም እንድንችል ያደርገናል።
ምስጋና ማለት እምነት በተግባር ማለት ነው። ለእኛ ምናልባት
የተለመደ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን ምስጋናን ከተለማመድነው የህይወታችን
ክፍል ሊሆን ይችላል፣ እርሱም የመለወጥና የማሸነፍ ኃይል አለው።
ሳምንቱን በአጭር እይታ: ምስጋና ምንድነው? ምስጋና
በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንደዚህ ኃይለኛ የሆነ መንፈሳዊ
መሳሪያ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? ምስጋና እኛንና በዙሪያችን
ያሉ ሁኔታዎችን ሊለውጥ የሚችለው እንዴት ነው?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለነሐሴ 21 ሰንበት ያጥኑ።
ታላቁ የሩስያው ጸሐፊ ፌዶር ድስቶቭስክ በመጨረሻው ሰዓት በተናገረው አንድ አረፍተ ነገር ምክንያት ብቻ ሞት ተፈርዶበት ነበር። በዚህ ፋንታ ብዙ ዓመታትን በእስር ቤት እንዲቆይ ተገዷል። እስር ቤት ስለነበረው ቆይታ ልምድ ሲናገር እንዲህ በማለት ጽፏል፡- “ሰዎች ሁሉ ተቅበዝብዘው እግዚአብሔርን ትተው ቢሄዱና አንተ ብቻህን እንኳ ብትቀር ለእግዚአብሔር ስጦታህን ይዘህ በመምጣት በብቸኝነትህ ምስጋናህን አቅርብለት” በዚህ ትምህርት ጳውሎስ ትልቁን ተቃውሞና ስደት እንዴት ችሎ እንዳለፈ ተመልክተናል። አሁን ግን እርሱ በሮማውያን እስር ቤት ቁጭ ብሏል። ቢሆንም እርሱ ተስፋ አልቆረጠም፤ በዚህ ፋንታ የፊልጵስዩስን አማኞች ለማበረታታት በትጋት ይጽፋል! ፊሊ 4:4-7ን ያንብቡ። ጳውሎስ ራሱ በሮም እስር ቤት ውስጥ ተቀምጦ ሳለ ይህንን ዓይነት ደብዳቤ እንዴት ጻፈ? በዚህ ንባብ ፣ ‹‹የእግዚአብሔርን ሰላም›› ለማግኘት ቁልፎቹ ምንድናቸው?
ነገሮች በመልካም ሁኔታ ላይ ሳሉ መደሰት አንድ ነገር ነው። ጰውሎስ
እኛን እያሳሰበን ያለው ሁልጊዜ እንድንደሰት ነው። ይህም እንግዳ አነጋገር
ሊሆን ይችላል። ጳውሎስ የጻፈውን በቀጥታ ከወሰድን ሁለት ጠንከር ያሉ
ወሳኝ ትርጉሞችን ይሰጠናል።
የመጀመሪያው፣ ሁልጊዜ መደሰት ካለብን፣ ነገሮቻችን ለደስታ
ምንም ዓይነት ፍንጭ በማይሰጡ ጊዜም ቢሆን መደሰት አለብን ማለት ነው።
ሁለተኛ፣ ሁልጊዜ መደሰት ካለብን፣ ውስጣችን ደስታ በማይሰማበት ጊዜም
ቢሆን መደሰት አለብን ማለት ነው።
ጳውሎስ ነገሮቻችን ተፈጥሮአዊ ሁኔታቸውን ባልጠበቁ ጊዜም ቢሆን
እንድናመሰግን ጥሪ እያቀረበልን ነው። እንድናመሰግነውም ምክንያታዊ መስሎ
ላይታየን ሁሉ ይችላል። በአጭሩ ስንመለከተው ስናመሰግን ምክንያታፈልገን
ብቻ መሆን እንደሌለበት ነው። በሌላ አነጋገር ምስጋና የእምነት ተግባር
ነው። እምነት በክስተቶች ላይ ሳይሆን መሰረት ማድረግ ያለበት ነገር ግን
ስለ እግዚአብሔር ባለው እውነት ላይ ነው በመሆኑም እምነት እኛ ጥሩ
ስሜት ስለተሰማን ሳይሆን በርግጥ እግዚአብሔር ማን እደሆነ በመረዳትና
እርሱ ለእኛ በገባው ቃል ላይ መሰረት ያደርጋል ማለት ነው። በሚያስገርም
መልኩ በህይወታችን፣ ሀሳባችንን፣ ስሜታችንን፣ እና ሁኔታዎቻችንን ቅርጽ
የሚያስይዝልን፣ ይህ እምነት ነው :፡
ጳውሎስ በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ እግዚአብሔር
ሊያብራራልን የፈለገው እውነት ምንድነው ፣በእስር ቤት
ሊያስደስተው (ሐሴት) እንዲያደርግ የረዳው እውነት? እስቲ ስለ
እግዚአብሔር የሚያውቁትን እውነቶች በዝርዝር በአጭሩ ይጻፉ።
ስለ እያንዳንዱ ነገር እግዚአብሔርን ያመስግኑ። ይህ ስለነገሮች
ያሎትን ስሜት ልለውጥ የሚችለውና እይታዎን ሊያስተካክል
የሚችለው እንዴት ነው?
በእንግሊዝኛ አንድ አባባል አለ፡ “በአንድ አራት ማዕዘን ውስጥ በቀለም መከበብ” እስቲ የአንድን ክፍል ግድግዳ ቀለም ስለ መቀባት ያስቡ ፣ ቅቡን የመጨረሻ ያደረጉት አንድ ኮርነር ቢሆንና ከዚያ መውጫው ብቸኛ መንገድ እርጥቡን ቀለም ረግጦ ብቻ ከሆነ ከዚያ ለመውጣት የግድ ቀለሙ እስኪደርቅ መጠበቅ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ እምነታችን በአንድ ማዕዘን በቀለም እንደተከበብን ያደርገናል። በግድግዳ ላይ እንዳለ እርጥብ ቀለም፣ እምነታችን አጣብቆ ይዞናል ወደሚለው ድምዳሜ እንደርሳለን። ሁኔታዎችን በመመልከት፣ እግዚአብሔርን፣ እምነትን፣ እና ያመንነው ሁሉንም ነገር መቃወም፣ ወይም እምነታችን የማይቻል የሚመስለውን ነገር ሁሉ ማሸነፍ እንደሚንችል እንድናምን ያደርገናል። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ወደ ማዕዘን አመጣቸው። ለአርባ አመታት በምድረበዳ ከተቅበዘበዙ በኋላ፣ እግዚአብሔር ህዝቡን ባዶ ወደሆነ ሰላማዊ የሳር መሬት አልመራቸውም። እግዚአብሄር የመራቸው በዙሪያው ካሉ ከተሞች ሁሉ እጅግ አብልጠው ወደተመሸጉ ከተሞች ነው። ስለዚህ በእያሪኮ ዙሪያ ለስድስት ቀናት በዝምታ መጓዝ ነበረባቸው። እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን እንዲጮሁና ጩኃታቸው ከመለከቱ ድምጽ ጋር ድልን እንደሚመጣ ነገራቸው። ኢያሱ 5፤13 – 6፡20 ድረስ ያንብቡ። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለማስተማር የፈለገው ምንድነው?
ደምጽን ከፍ አድርጎ መጮህ ግምብ እስኪያፈርስ ድረስ መሬትን
የማንቀጥቀጥ ኃይል የለውም። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ‹‹እንዲጮሁ››
ሲጠራቸው፣ ዳዊት በመዝሙር 66 ከጻፈው ጋር ተመሳሳይ ጩኃት
ነው።‹‹በምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፡ለስሙ ዘምሩ
ለምስጋናውም ክብርን ሥጡ።›› (መዝ66፡ 1፣2) ይህ ጩኃት ምስጋና ነው!
ለስድስት ቀናት እጅግ ግዙፍ የሆነውን አጥር እየተመለከቱ፤ ይህንን በራሳቸው
ኃይል ማፍረስ እንደማይችሉ ድምዳሜ ላይ ደርሰው ይሆናል።
ይህ ሀሳብ ዕብ 11፡30ን እንድናስተውል የሚረዳን
እንዴት ነው?
እግዚአብሔር በህይወታችን ውስጥ አንድን አዲስ ነገር
በመስራት ጉዳይ ላይ በሚሆንበት ጊዜ ፣ ምናልባትም የማሸነፍ ኃይል
በራሳችን ኃይልና ዘዴዎች መምጣት እንደማይችል ለማስረዳት ሲፈልግ
ወደ ኢያርኮ ሊያመጣን ይችላል። የሚያስፈልገን እያንዳንዱ ነገር
የሚመጣው ከእኛ ውጪ ከሆነ ኃይል ነው። ስለዚህ በፊታችን ያለው ነገር
ምንም ይሁን ምን ፣ ምንም እንኳ በፍጹም የማይገፋ መስሎ ቢታየንም
የእኛ ድርሻ የሚያስፈልግን ነገር ሁሉ ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን
ማመስገን ብቻ ነው። ይህ ነው እምነት በተግባር የሚባለው!
በመልካም ነገሮች ውስጥ እንኳ ሆነን ማመስገን ለእኛ የተለመደ አይደለም። ስለዚህ በክፉ (በአስቸጋሪ) ጊዜ ደግሞ እንዴት ይሆን? ሆኖም ግን እንድናደርግ የተጠራነው ይህንን ነው። ምስጋና፣ በተወሰነ ጊዜ ከምናደርገው ድርጊትነት አልፎ የኑሮ ዘይቤያችን እስኪሆን መለማመድ አለብን። ምስጋና የተለየ ድርጊት ሳይሆን አኗኗር ሊሆን ይገባል። መዝ 145ን ያንብቡ። ዳዊት እግዚአብሔርን ስለ ማመስገን የሰጣቸው ምክንቶች ምንድናቸው? የዚህ መዝሙር ቃላት የእርስዎ መሆን የሚችሉት እንዴት ነው?
ቻርለስ ሃደን ስፓርጅን የተባለው ታላቅ የእንግሊዝ ሰባኪ የምስጋና
ልምምድ የሚል መጽሓፍ ጽፏል። ይህም የተመሰረተው በዚህ በመዝሙር
ቁጥር 7 ላይ ይገኛል። በዚህ አጭር ጥቅስ ስፓርጅን፣ በህይወታችን ውስጥ
ምስጋናን እንዴት ማሳደግ እንደምንችል ሐሳባችንን ወደሚመሩ ሶስት አስፈላጊ
ነገሮች ይመራናል።
1. ምስጋና የሚለመደው ዙሪያችንን ማየት ስንችል ነው።
የእግዚአብሔርን ታላቅነት ለማየት፣ ዙሪያችንን ካላየን እርሱን ለማመስገን
ምንም ምክንያት አይኖረንም። በተፈጠረው ዓለም ወስጥ እንደ እግዚአብሔር
ፍጥረት ውበት የመሳሰሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ለመስጠት የተገባ እንደሆነ
የሚያሳዩ ምን ምን ነገሮችን ታገኛላችሁ? በመንፈሳዊውስ ዓለም ለምስጋና
የሚሆኑ ምን ነገሮችን ታገኛላችሁ ለምሳሌ በአዲስ ክርስቲያን እያደገ የሚታይ
እምነት የመሳሰሉትን?
2.ምስጋና
የሚለመደው
የተመለከትናቸውን
ነገሮች
ስናስታውስ ነው። በምስጋና አየር ውስጥ መቆየት ከፈለግን፣ ለማመስገን
ምክንያት የሆነልንን ነገር ማስታወስ ግድ ይለናል። የእግዚአብሔር መልካምነት
እና ታላቅነት ከአእምሮአችን እንዳይጠፋ የእርሱን ታላላቅ ነገሮች ማስታወስ
የምንችልባቸው የትኞቹ መንገዶች ናቸው (አዲስ የማምለክ መንገዶችን
በመከተል ወይም የእርሱን መልካምነት የሚያስተውሱንን ምልክቶችን
በማድረግ)?
3. ምስጋና የሚለመደው ስለ እርሱ ስንናገር ነው። ምስጋና እና
በአእምሮአችን ውስጥ የምናደርገው ነገር አይደለም። ይህ ማለት ፣ ከአፋችን
የሚወጣ ሆኖ በዙሪያችን ላሉ ሌሎች ሰዎች የሚሰማ ነገር ማለት ነው።
እግዚአብሔርን በቃላት ለማመስገን የሚሆን ምክንያት ምንድነው? የዚህ
ምስጋና ተጽዕኖ ምን ይሆናል፣ እናስ በማን ላይ?
በሶስት ነገሮች ላይ ለመስራት እስክርብቶና ትንሽ ወረቀት
ውሰድ። በህይወትህ የምስጋና ልምድ ለማዳበር ምን ነገሮችን
ማድረግ ትችላለህ?
በሐዋርያት ስራ መጸሐፍ ውስጥ፣ ምስጋና በሰሚዎቹ ዘንድ በጣም አስገራሚ ተጽዕኖ አድርጎ እናያለን። የሐዋ ሥራ 16 ፡ 16-34 ያለውን ያንብቡ። በከባድ ሁኔታ ከተደበደቡና ከተገረፉ በኋላ ጳውሎስና ሲላስ ወደ እስር ቤት ተጣሉ። ክፉኛ በተደበደቡበት ቁስላቸው ላይ ዘይት የሚያፈስላቸው ማንም አልነበረም። በትልቅ ህመምና እግራቸው በግንድ ተጠርቆ፣ በውስጠኛው ክፍል ተጥለው ነበር። ነገር ግን ሌሎቹ እስረኞች እያዳመጡ ሳለ፣ ጳውሎስና ሲላስ ይዘምሩና ይጸልዩ ነበር። የመሬት መንቀጥቀጡ ከሆነ በኋላ፣ ጳውሎስ እና ሲላስን ጨምሮ ከእስር ቤቱ ማንም አስረኛ አለማምለጡን የእስር ቤቱ ሐላፊ ሲያውቅ፣ ‹‹ በጳውሎስና በሲላስ ፊት እየተንቀጠቀጠ፣ ከእስር ቤቱ ወደ ውጪ አውጥቶአቸው፣ ወዳጆቼ እድን ዘንድ ምን ላድርግ? አላቸው” (ሐዋ 16:29, 30) :: ይህ ሁኔታ የእስር ቤቱን አለቃ በራሱ መዳን ላይ ብቻ እንዲያተኩር ያደረገበት ምክንያት ምንድነው? በሌሎች እስረኞች ለማምለጥ ባለመፈለግ እና በዚህ ሰው እና ቤተሰቡ መለወጥ ላይ የጰውሎስና ስላስ መዝሙርና ጸሎት ያደረገው ተጽዕኖ ምንድነው?
ምስጋና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች የህይወት ፍጻሜን በመለወጥ ረገድ
ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ማወቅ በጣም አስገራሚ ነው። ጳውሎስና ሲላስ
እንደተለመደው በእስር ቤቱ ጨለማ ውስጥ ሆነው አጉረምርመው ቢሆን
ኖሮ፣ በዚያ ምሽት አንድም ሰው ይድናል ብለው ያምናሉ?
በስተመጨረሻ የእስር ቤቱ አለቃ ምን እንደሆነ አናውቅም፣ ነገር ግን
ጳውሎስ በሌለው አስር ቤት ሆኖ በፊል 1፡ 29፣30 ላይ ‹‹ ይህ ስለ ክርስቶስ
ተሰጥቶአችኃልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ እንድትቀበሉ እንጅ በእርስ ልታምኑ
ብቻ አይደለም። በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት ያው
መጋደል ደርሶባችኃል›› በማለት የጻፋቸውን ቃላት ያስቧቸው። እነርሱ ይህንን
መልዕክት በማንበብ የእርሱን ህይወት ካንጸባረቁ በህይወታቸው ደስታን
አምጥቶላቸዋል፣ በእርግጠኝነት ለልባቸው ደስታን በማምጣት እንዲዘምሩ
አድርጓቸዋል፣ እናም ግድድሮሾች ምንም ያህል ዋጋ የሚያስከፍሉ እንኳ ቢሆን
ታማኝ ሆነው እንዲቆሙ አድርጓቸዋል ማለት ነው።
ከእርስዎ አንደበት
ስንት ሰው ለእግዚአብሔር
ለእግዚአብሔር በሚሰጡት
በትክክል ይታወቅ፣ ከዚያ
እንደሚያሰድር ያያሉ።
በሚወጣው የምስጋና ዝማሬ የተነሳ
ተማርኳል? በሌሎች ዘንድ እርስዎ
ምስጋና ልዩ ትኩረት እንዳለዎት
በኋላ ምን ያህል አዎንታዊ ተጽዕኖ
2ዜና 20 1- 30 ያለውን ያንብቡ። ኢዮሳፍጥ ምስጋና ታላቅ አሸናፊ መሳርያ መሆኑን ተረድቷል።‹‹ታላቅ ሰራዊት›› ወደ እርሱ እየመጣ እንደሆነ መልዕክት እንደደረሰው ኢዮሰፍጥ፣ ወደ ወታደራዊ እርምጃ አልሔደም፣ ነገር ግን ‹‹ የእግዚአብሔርን ፊት ፈለገ›› ( 2 ዜና 20:3):: የይሁዳ ሰዎች ለጻሎትና ለጾም ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ፣ ኢዮሳፍጥም ሁኔታውን እንዲህ በማለት ገለጸው ‹‹ ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፣የምናደርገውንም አናውቅም፤ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው›› (2 ዜና 20፡12)። እርስዎ ታላቅ ሰራዊት በሚያዩበት ጊዜ ቶሎ ብለው የሚወስዱት ኤርምጃ ምንድነው? በ2 ዜና 20 2-12 ታላቅ ግድድሮሽን አስመልክቶ ኢዮሳፍጥ ከሰጠው ምላሽ ምን ትምህርት ወሰዱ?
የእግዚአብሔር መንፈስ በየሕዝቅኤል ላይ እንደመጣ ‹‹ በዚህ ሰልፍ
እናንተ የምትዋጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ ተሰለፉ ዝም
ብላችሁ ቁሙ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔር
ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ ነገም ውጡባቸው››(2 ዜና 20:17) ከዚያ በኋላ
እግዚአብሔርን አመለኩ‹‹ በታላቅ ድምጽም›› ምስጋናንም ሰጡት ። (2 ዜና
20:19):: እግዚአብሔር የሚዋጋላቸወ እንኳ ቢሆንም፣ እነርሱ በጠላት ፊት
መቆም አለባቸው።
ነገር ግን ይህ ወደ ጦርነት የሚደረግ ተራ ሰልፍ አይደለም። ኢዮሳፍጥ
ወደ ጦርነቱ ጉዞ ሲያደርጉ ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር የሚያዜሙ
መዘምራንን ሰየመ። “ዝማሬውንና ምስጋናውን በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ
በመጡት በአሞንና በሞአብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር
ድብቅ ጦር አመጣባቸው፤ እነርሱም ተመቱ” (2ዜና 20:22)። እንደ መጸሐፉ
ጸሐፊ፣ እነርሱ እንደ ተስፋ ቃሉ እግዚአብሔርን ስለምህረቱና ቅድስናው
ማመስገን ሲጀምሩና እምነታቸውን ሲለማመዱ እርሱ ጣልቃ ገባ።
እርስዎ ከእግዚአብሔር ጋር በሚያደርጉት ጉዞ በተለየ ሁኔታ
በችግርና በመከራ ጊዜ የሚጠቅም ምን መንፈሳዊ መርህ አገኙ?
አበውና ነብያት በሚለው የኤለን ዋይት መጸሐፍ ፣ ‹‹
ኢዮሳፍጥ›› የሚለውንና ‹‹የኢያርኮ አወዳደቅ›› የሚለውን ክፍል ያንብቡ።
“ወደር ለማይገኝለት ፍቅሩ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን
ልባችንንና አፋችንን እናለማምደው። ከመስቀሉ ላይ በሚፈነጥቀው ብርሃኑ
ነፍሳችን እንድትጸናና ተስፋ እንድታደርግ ልናስተምራት ይገባናል። እኛ የሰማዩ
ንጉስ ልጆች የሰራዊት አለቃ ወንዶችና ሴቶች መሆናችንን በፍጹም ልንዘነጋ
አይገባንም። በእግዚአብሔር የተረጋጋ ምላሽ ላይ መጽናት ለእኛ ትልቅ እድል
ነው። The Ministry of Healing, p. 253.
“እርሱን ሳከብረውና ከፍ ሳደርገው፣ አንተ ከእኔ ጋር እንድታከብረው
እፈልጋለሁ። በጨለማ ውስጥ ብትሆን እንኳ እግዚአብሔርን አመስግነው።
በፈተና ውስጥም ስሙን ከፍ አድርገው። ‹‹ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ››
‹‹ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ›› ። ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ይህ ጨለማንና
ጭጋግን ያመጣ ይሆን? አይደለም፣ የጸሐይን ጨረር ይፈነጥቃል እንጅ።
ስለዚህም፣ ከክብር ዙፋኑ ዘላላማዊ የሆነውን ብርሃን በዙሪያዎ ይሰበስባል።
ይህን ብርሓን በራስዎ ህይወትና መንገድ ብቻ ሳይሆን አብረዎት ባሉ ወገኖች
ሁሉ ዙርያ እንዲያደርጉና በዚህ ሥራ ተካፋይ እንዲሆኑ ልጋብዝዎት
እፈልጋለሁ። በዙሪያዎ የሚገኙ ሰዎችን ህይወት ምድራዊ ከሆነው ነገር ሁሉ
በላይ ጠፊ ከሆነው ርስት እና ምድራዊ ሀብት ይልቅ ወደ ሰማይና ወደ ክብሩ
ወደ ከፍታ ማድረስ ዓላማዎ ይሁን።›› Ellen G. White, Testimonies for
the Church, vol. 2, pp. 593, 594.
1. የማህበረሰቡ የምስጋና ህይወት በክርስትና ላይ ምን ተጽዕኖ አለው? ምስጋናን በሰንበት አምልኮ ውስጥ እንዴት ይገልጹታል? ወደ ጌታ ከፍ የሚያደርግ ነው? አባላትን በችግሮች ውስጥ ታማኝነታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የሚያበረታታ ነው? ይህ ካልሆነ መደረግ ያለበት ምንድነው? 2. “በጨለማ ውስጥ ብትሆን እንኳ እግዚአብሔርን አመስግን” ወይም “በፈተና ውስጥም ቢሆን አመስግነው ማለት ምን ማለት ነው”? በእነዚህ ነገሮች ውስጥ ምስጋና የሚጠቅመን እንዴት ነው? 3. አባላት ምስጋና በህይወታቸው ላይ ያመጣውን ተጽዕኖ ምስክርነት ይስጡ። አንዱ ከሌላው የህይወት ልምምድ ምን መማር ይችላል? 4. እንደ ሰንበት ትምህርት ክፍል፣ አንድ የምስጋና መዝሙር ለማንበብ ጊዜ ውሰዱ። ስለ ምስጋና ምን ያስተምራችኋል? ምስጋና በእምነትዎ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምንድነው?