የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ፊሊ 2:5-9 ሮሜ 12:1, 2; 1 ሳሙ 2:12–3:18; 1 ሳሙ 13:1-14; ዘካ 4:1-14ን ያንብቡ።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፣ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።” (ዮሐ 12:24) ።
የ
ሱስ የምትሞተው የስንዴ ቅንጣት ምሳሌ እኛ ለእግዚአብሔር
ራሳችንን እንዴት ማስረከብ እንዳለብን የሚያሳይ እጅግ አስደናቂ
ምሳሌ ነው። የምትወድቀው የስንዴ ቅንጣት (የምትበቅለው ክፍል)
እንዴት እንደምትወድቅና የት እንደምትወድቅ በራሷ ምንም ቁጥጥር
ማድረግ አትችልም። በእርሷ ዙሪያ ስለ ከበበውና በእርሷ ላይ ተጽዕኖ
በሚያሳድረው አካባቢ ላይ የበላይ የመሆን አቅም የላትም።
ሁለተኛ፣ መጠበቅ አለ። ቅንጣትዋ በምድር ስትውድቅ፣ወደፊት ምን
እንደሚመጣ አታውቅም። ወደ ፊት ምን እንደሚትመስል ‹‹ መገመት››
አትችልም፣ ምክንያቱም እርሷ የስንዴ ቅንጣት ብቻ ስለሆነች።
ሶስተኛ ፤ ሞት አለ። የስንዴዋ ቅንጣት ፣ ያላትን መልካም አጋጣሚ
የተመቻቸ ሁኔታ ካልተወች በቀር ተመልሳ ስንዴ መሆን አትችልም። እርስዋ
መሞት አለባት፤ ከዘርነት ፍሬ ወዳለው ዛፍነት ለመለወጥ ያላትን ሁሉ
መስጠት አለባት።
ሳምንቱን በአጭር እይታ: የእግዚአብሔር ፈቃድ ለእኛ መልካም መሆኑን
ካስተዋልን ፣ ይህን ለመቀበል ለእኛ ከባድ የሚሆንብን ለምንድነው? ራስን
ስለ ማስረከብ ክርስቶስ የሰጠን ምሳሌ ምንድነው? የስንዴ ቅንጣትዋ ምሳሌ
በእርስዎ ህይወት ሊተገበር የሚችለው እንዴት ነው?
*ይህንን ትምህርት ለመስከረም 7 ሰንበት አጥንተው ይምጡ።
ፊሊ 2:5-9ን ያንብቡ። በዚህ ጥቅስ ላይ የምናገኘው ለእኛ አስፈላጊ የሆነ መልዕክት ምንድነው?
ዘመናዊው ባህል ሁላችንም መብታችንን እንድንጠይቅ ይገፋፋናል።
ይህ ሁሉ ደግሞ ጥሩና መሆን ያለበትም ነው። ነገር ግን፣ ክርስቶስ
እንዳደረገው፣ የእግዚአብሔር ፈቀድ መብቶቻችንን ለእግዚአብሔር መንግስት
ዘላላማዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር በሚችልበት ሁኔታ እንድናገለግል በፈቃዳችን
እንድንተው ይጠይቀናል። እነዚህን የመተው ሂደት ግን ቀላል አይደለም።
ከባድ የማይመችና ፈተና ሊመጣ የሚችል ሊሆን ይችላል።
ይህን ክርስቶስ እንዴት እንዳደረገው ተመልከት። ፊሊ 2:5-8):: ይህ
ጥቅስ ክርስቶስ ራሱን አሳልፎ ለአባቱ ፈቃድ በመስጠቱ ሂደት ያለፈባቸውን
ሶስት ደረጃዎች ይነግረናል። ከጅምሩ ጳውሎስ በከፍተኛ ሁኔታ፣ ‹‹ በክርስቶስ
የነበረው ሀሳብ እንዲኖረን›› ያሳስበናል። (ፊሊ 2፡5)።
እኛን ሊያድነን በሚችልበት ሁኔታ ላይ ለመድረስ፣ ክርስቶስ ከአባቱ
ጋር የነበረውን መተካከል በመተው በሰው ደረጃ ዝቅ ብሎ ወደ ምድር መጣ።
ፊሊ 2:6, 7)
የሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው እንደተከበረ ሰው ሳይሆን ፣ ነገር ግን
ሌሎችን እንደሚያገለግል ሰው ነው (ፊሊ 2፡7)
እንደ ሰው ልጅ አገልጋይ ፣ ክርስቶስ ሰላማዊና ረጅም ህይወት
አልኖረም ነገር ግን ‹‹ ለሞት የታዘዘ ሆነ›› እንዲያውም ክብር ባለበት ሁኔታ
አይደለም። ነገር ግን እስከ ሞት ድረስ የታዘዘ በመሆን በመስቀል ላይ ሞተ።
(ፊሊ 2፡8) ።
ይህ የክርስቶስ ህይወት ምሳሌ ሊሆነን የሚችለው በየትኛው
የህይወታችን ክፍል ነው? መብትና እኩልነት ጥሩና ጥበቃ ሊደረግባቸው
የሚገቡ ነገሮች ናቸው። እነዚህን ነገሮች ስለ መተው በምን መልኩ ሊያስረዱ
ይችላሉ? አሁን ፊሊ 2:9ን ያንብቡ ። ይህ ጥቅስ ራስን ለአባት ፍቃድ አሳልፎ
ስለ መስጠት ልረዳን የሚችለው በምን መልኩ ነው?
ከመንፈስ ቅዱስ ጥበብን ለማግኘት ይጸልዩ፣ ምን መብቶች
ናቸው ራሴን ለክርስቶስ እንዳልሰጥ መሰናክል የሆኑብኝ፤ ቤተሰቤን
በማገልገል፣ቤተክርስቲያኔን ወይም በዙሪየዬ ያሉትን በማገልገል?
ሌሎችን በጥሩ ሁኔታ ለማገልገል የነገሮችን አለመመቻቸት በምን
ያህል ለመቋቋም ዝግጅት አድርገዋል?
ብዙ ክርስትያኖች እግዚአብሔር ለእነርሱ ህይወት ያለውን ፈቃድ
ለማወቅ አጥብቀው ይፈልጋሉ። “እግዚአብሔር በህይወቴ ያለውን ዓላማ
ባውቅ፣ ሁሉንም ነገር ለእርሱ እሰዋ ነበር›› ። ነገር ግን ለእግዚአብሔር ይህን
ቃል እንደገባን፣ አሁንም ይህ ፈቃዱ ምን እንደሆነ ግራ እንጋባለን። ለዚህ ግራ
መጋባት ምክንያቱ በሮሜ 12፡1 ላይ ይገኛል። ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ
የምናውቀው እንዴት እንደሆነ፣ የተለየ ነጥብ ያስቀምጥልናል። የእግዚአብሔር
ፈቃድ ምን እንደሆነ ማወቅ ከፈለጋችሁ፣ መጀመሪያ መሰዋት ያስፈልጋችኋል!
ሮሜ 12፡1፣2ን ያንብቡ። ‹‹የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ምን እንደሆነ
ቀምሳችሁ እዩ›› (ሮሜ 12፡2) መቼ
1. እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ‹‹እውነተኛ ምህረት›› ስናስተውል።
2. ራሳችንን ህያው መስዋዕት አድርገን ለእግዚአብሔር ስንሰጥ (ሮሜ 12:1).
3. አእምሮአችን ሲታደስ (ሮሜ 12:2).
በእውነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማስተዋል የሚችለው የታደሰ
አእምሮ ብቻ ነው። ነገር ግን ይህ መታደስ የሚያያዘው በመጀመርያ ለራስ
ከመሞት ጋር ነው። ክርስቶስ ለእኛ መሰቃየት ብቻ ሳይሆን፣ መሞት ነበረበት።
መንፈስ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ያልሞቱበትን ነገር እንዲያሳይዎ
ይጠይቁ” ለእግዚአብሔር ‹‹ህያው መስዋዕት ›› ለመሆን መንፈስ
ቅዱስ እንድተው የሚጠይቀው ምንድነው?
የህይወታችን አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለራስ ካልሞቱ፣
እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ወደ ትኩረታችን ለማምጣት ፈተናን ይፈቅዳል።
ይህም ፈተናው ከኃጢአት ጋር እንድንታገል ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ክርስቶስ
ለእኛ ሲል ራሱን መስጠቱን ጭምር እንድናስተውል ያደርገናል። ኤልሳቤጥ
እሎት የሚትባል ጸሀፊ፡ ‹‹ የልባችንን ጥልቅ ፍላጎት ለክርስቶስ ማስረከብ፣
የክርስቶስን መስቀል በጥልቀት እንድናስተውለው ከማድረጉም በላይ የኛ
የራሳችን ልምምዶችን፣ አምላካችን ካደረገው ጋር ለንጽጽር የማይቀርብ
ቢሆንም ፣ እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በእርሱ መከራ ውስጥ
ሆነን ማስተዋል እንድንጀምር ይረዳናል። በየትኛውም መከራ ውስጥ ብንሆን
እርሱ ወደዚህ ከክርስቶስ ጋር ወዳለን ህብረት ይጠራናል።”—Elisabeth Elliot, Quest for Love (Grand Rapids, MI: Fleming H. Revell, 1996),
p. 182.
ሮሜ 12 ፡1 ፣2ን አንብበው ይጸልዩ።
መስዋዕት
ለመሆን መተው የሚያስፈልጉን ነገሮች ምን እንደሆኑ ያስቡ። ይህ
የክርስቶስን የመስቀሉ ላይ መስዋዕትነት ለማስተዋል የሚጠቅመን
እንዴት ነው? ይህን ማወቅ በክርስቶስ መከራ ተካፋዮች እንድንሆን
የሚረዳን እንዴት ነው?
“እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ ፣ እንደ ቀድሞውም ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለው።” (1 ሳሙ 3:10) ። እስከ ዛሬ ድረስ ቀስ ብሎ የሚናገረውን የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ሰምተው ችላ ብለው ይሁን? በዚህም ምክንያት ሁሉም ነገር ባልሆነ መንገድ ሄዷል፣እናም ከዚያ በኋላ ለራስዎ፣ ለምንድነው ያን ድምጽ ያልሰማሁት ብለው ጠይቀው ይሆን? አንደኛ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ለመስማት ፈቃደኛ ስለልነበሩት ስለ አንድ ሰውና ሁለት ኃጢአተኛ ስለሆኑ ልጆቹ እና አንድ ለመስማት ፈቃደኛ ስለሆነ ልጅ ይተርክልናል። ምንም እንኳ ህይወታቸውን ለመለወጥ በማሰብ ከእግዚአብሔር አንድ ጠንካራ የሆነ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም እነርሱ ግን አልሰሙም። ታሪኩን በአንደኛ ሳሙ 1፡2:12–3:18 ላይ ያንብቡ። በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን ለመስማት ፈቃደኛ በሆኑትና ባልሆኑት መካከል ምን ዓይነት ንጽጽር ተደረገ?
በኤሊ ልጆች አእምሮ ከእግዚአብሔር ሀሳብ የተለየ ነገር ነበር። ኤሊ
እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር ከሰማ በኋላ ለልጆቹ ከመናገር ውጪ ምንም
ለማድረግ የፈለገ አይመስልም። ልጆቹም ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን
ለመስጠት ዝግጁ አልነበሩም። ከህጻኑ ሳሙኤል ጋር ሲስተያይ ምን ዓይነት
ንጽጽር ይሆን!
ሰባኪው እግዚአብሔር በሚጠራበት ጊዜ ድምጹን ለመስማት
ግልጽነትን ኮትኩቶ ስለ ማሳደግ ሲገልጽ ( Charles Stanley) “ወደ
ሚዛናዊነት መለወጥ” በሚለው ርዕስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ መንፈስ ቅዱስ
መልዕክት ለማስተላለፍ ብቻ አይናገርም። እርሱ የሚናገረው መልስ ፈልጎ
ነው። እኛ እንድሆንልን የምንፈልገው ነገር በጣም ትልቅ ትኩረታችንን የወሰደ
ሲሆን እኛ ለምናስበው በተቃራኒ የሚሰጥ ማንኛውም ሀሳብ ወይም ምላሽ
ጊዜን እንደ ማባከን ይቆጠራል። ጉዳዩ እንደዚህ ሲሆን ፣እርሱ ብዙውን ጊዜ
ዝምታን ይመርጣል። እኛ ነገሮችን ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ ማሰብ እስክንችል
እና እስክንታዘዝ ድረስ ይጠብቃል።”—Charles Stanley, The Wonderful
Spirit-Filled Life, (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1992),
pp. 179, 180.
ስታነሊ ‹‹ ሚዛናዊ ሆኖ መገኘት›› ሲል ምን ማለቱ
ይመስልዎታል? ለእግዚአብሔር ግልጽ ስለ መሆንዎ ሲያስቡ፣
እርሱን ለመታዘዝ ወይም ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዳይኖርዎ
የሚያደርጉት ምን ምን ነገሮች ናቸው? የእግዚአብሔርን ድምጽ
ለመስማት እና ለመታዘዝ እንዲሁም ግልጽነትን ኮትኩቶ ለማሳደግ
ምን ያስፈልግዎታል?
ሄዋን ኃጢአት በሰራች ጊዜ እንኳ ችግሩ የእግዚአብሔርን ቃል መጠራጠር ብቻ አልነበረም። የችግሩ ማዕከል የነበረው እርሷ ለራሷ የሚሆነውን መልካም ሆነ መጥፎ ነገር ለመምረጥ በቂ ጥበብ እንዳላት ማመንዋ ነበር። የራስዋን ፍርድ አመነች። እግዚአብሔርን በመታመን በተቃራኒ በራሳችን ፍርድ ወደ ማመን ስናዘነብል፣ ራሳችንን ለብዙ ዓይነት ችግሮች ክፍት እናደርጋለን። የሳኦል ታሪክ የሚገልጻው ከእግዚአብሔር ተለይቶ ራስን ለመቻል የተደረገ አካሄድና ያንን ተከትሎ በፍጥነት የመጣውን ውድቀት ነው። ሳሙኤል ሳኦልን በእግዚአብሔር የተመረጠ ንጉሥ አድርጎ ቀባው።(1ሳሙ 10፡ 1)። ከዚያም የተለየ የሚመራበትን ሥርዓት ነገረው።(1 ሳሙ 10፡8) ነገር ግን ሳኦል አልታዘዘም። በቀረው የታሪኩ ክፍል በ1 ሳሙ 13 1-14) ሳኦል ወደ ራሱ ውድቀት የሚያመራውን ምን ነገር አደረገ?
ሳኦልን ንጉሥ ከሆነ ጀምሮ ወደ ታች፣ ራስን ወደ መታመን የመሩ
ሶስት ደረጃዎች አሉ። ችግሩ እነዚህ ሶስቱ ደረጃዎች በራሳቸው ምንም ችግር
የሌለባቸው መሆኑ ነው። ነገር ግን እያንዳንዳቸው ደረጃዎች እየተከናወኑ
ያለው በእግዚአብሔር በመሆኑ በውስጣቸው የመከራ ዘር ይዘዋል። የሳኦል
ውድቀት የሄደበትን ቅደም ተከተል ተመልከቱ።
1.ሳኦል ሳሙኤል በሌለበት የሰራዊቱን መበታተን ‹‹አየሁ››(1ሳሙ
13፡11) አለ። ሳኦል የሚሆነውን ነገር የገመገመው በራሱ
እይታ ነበር። ሳኦል ‹‹አየሁ›› ከማለት ወደ ‹‹ፍልሥጤማውያን
ያሸንፉናል ‹‹አለ›› ( 1ሳሙ 13፡12)
2.እርሱ ለሁኔታው ማጠቃለያ የሰጠው በራሱ ዓይን ባየበት እይታ
ነበር።
3. ሳኦል እንደዚህ ‹‹አልኩ›› ከማለት ወደ ‹‹ተሰማኝ›› ስለዚህም
ሳልታገስ የሚቃጠለውን መስዋዕት አሳረግሁ(1 ሳሙ 13:12):: አሁን
የሳኦልን ስሜት የገዛው አስተሳሰቡ ሆነ።
ሁላችንም ይህን አድርገናል። ሁላችንም በራሳችን አስተሳሳብ ላይ
እንድንደገፍ በሚመራን በራሳችን እይታ ላይ ስንሆን በሰብዓዊ ስሜታችን ላይ
በመተማመን ድርጊቶቹን እንፈጽማን።
ምንም እንኳ የእግዚአብሔር ጥርት ያለ መመሪያ በጆሮው
የሚያቃጭል ቢሆንም ሳኦል በራሱ ፍርድ ለመሄድ እንዲህ የቀለለው
ለምን ይመስልዎታል? እኛ እንደዚህ ለውድቀት ቅርብ መሆናችንን እና
ፍጹም ዕውቀት የሌለን መሆናችንን የምውቅ ሲሆን አሁንም በራሳችን
ላይ ለመደገፍ የምናስበው ለምንድነው? ከራሳችን ይልቅ በእግዚአብሄር
መመሪያ ላይ ለመተማመን ምን ማድረግ አለብን?
ትናንት እንደተመለከትነውም፣ በራሳችን ጥንካሬ ስንታመን ፣ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራስን ማስረከብ ይቀራል። እግዚአብሔርን ተክተን በሚናስቀምጣቸው ሌሎች ነገሮች ላይም ልንደገፍ እንችላለን። አንዳንድ ሰዎች (ሲጨንቃቸው)፣ የሚያዝናና ስለሚመስላቸው ዕቃ ለመግዛት ወደ ሱቅ ይሄዳሉ። አንዳንዶች ያልበቁ ሆነው ይሰማቸዋል፣ ሰለዚህም ተዋቂነትን ለማትረፍ ይሽቀዳደማሉ። አንዳንዶች ከሚስቶቻቸውጋር ችግር ስገጥማቸው፣ ለደስታ እና ለፍቅር ሌላ ሰው ይፈልጋሉ። የምንጠቀማቸው ብዙ ነገሮች ውጥረቱን ሊያረግቡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና በሚቀጥለው ጊዜ እንዴት በተሸለ መልኩ ችግሩ መያዝ እንዳለበት ምንም ነገር አያስተምሩም ። ይህን ማድረግ የሚችለው ከሰው አቅም በላይ የሆነው መለኮታዊ ኃይል ብቻ ነው። ችግሩ ብዙ ጊዜ በእግዚአብሔር በመደገፍ ፋንታ በእርሱ ምትክ ባስቀመጥናቸው ነገሮች ላይ መደገፋችን ነው። እዚህ በእግዚአብሔር ምትክ የምንጠቀማቸው ሦስት ነገሮች፡ 1. የእግዚአብሔር መለኮታዊ መገለጥ በሚያስፈልገን ጊዜ ላይ ያለፈውን የህይወት ልምድ ወይም ሰውኛ ግምትን መጠቀም። 2. መለኮታዊ መፍትሔ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ላይ ችግሮችን በአእምሮአችን ዝግ አድርጎ መያዝ። 3. መለኮታዊ ኃይል ከእግዚአብሔር መሸሽ። በሚያስፈልገን ጊዜ ላይ ከእውነታውና ዘካሪያስ በእግዚአብሔር ፈንታ ምትክ የሆኑ ነገሮችን ለመጠቀም በሚንፈተንበት ጊዜ በትክክል አስፈላጊ በሆነው ጉዳይ ላይ ማተኮር እንደሚገባን በማስገንዘብ ይረዳናል። ምርኮኞቹ ከብዙ ዘመን በኋላ ወደ አገራቸው እንደተመለሱ ቤተመቅደሱን መገንባት ጀምረዋል። ነገር ግን በጣም ትልቅ የሆነ ተቃውሞ ገጠማቸው። ስለዚህ ዘካሪያስ ሥራውን ወደሚመራው ሰው ወደ ዘሩባቤል እንዲህ የሚል የማበረታቻ መልዕክት ይዞ መጣ። ይህን መልዕክት በዘካሪያስ 4 ላይ ያንብቡት። በዘካ 4፡6 እግዚአብሔር ምን እያለ ነው? የግንባታ ሥራው በእግዚአብሔር መንፈስ ሊጠናቀቅ የሚችለው እንዴት ነው? ይህ በተግባር በምንፈጽማቸው ነገሮች እና በእግዚአብሄር መንፈስ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገልጸው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር በመቅደሱ ሥራ ላይ የመጣውን ተቃውሞም
ሆነ ዘሩባቤል በዚህ ተቃውሞ ምክንያት እየደረሰበት ካለው ጭንቀት ነጻ
አላደረገውም። እናም እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከተቃውሞ ነጻ አያደርገንም፣
ነገር ግን ምናልባት እኛ በእርሱ ላይ መደገፍን እንድንለማማድ መፈተኛ አድርጎ
ይጠቀመዋል።
ጭንቀት በሚመጣበት ጊዜ፣ የእርስዎ የመጀመሪያ
እርምጃ ምንድነው? ምግብ? ቴሌቭዥን? ጸሎት? ለእግዚእብሔር
መስጠት? መልስዎ ስለ ራስዎ የሚነግርዎት ሊማሩት የሚገባ ነገር
ምንድነው? ለውጥ የሚያስፈልገው ነገርስ ምንድነው?
አበውና ነብያት በሚለው የኤሌን ዋይት ‹‹ ኤሊና
ልጆቹ››ገጽ 575-580 እና ‹‹የሳኦል የተሳሳተ እምነት›› ገጽ616-626 ያንብቡ።
ለእግዚአብሔር መሰጠት ሊመጣ የሚችለው እኛ ለራሳችን ፍላጎትና ምኞት
የሞትን ስንሆን ብቻ ነው። መስዋዕት ሳንሆንና በቀጣይነት ከእግዚአብሔር
ድምጽ ጋር ግልጽ የሆነ ግንኙነት ሳይኖረን ለእግዚአብሔር መኖር አንችልም።
የእኛን ፈቃድ በእውነት ለእግዚአብሔር ፈቃድ ለማስገዛት፣ በራሳችን
የመደገፍን እና በእግዚአብሔር ቃልና ኃይል ፈንታ የምንተካቸውን ነገሮች
አደገኛነት በትክክል መረዳት ያስፈልገናል። ክርስቶስን በሚመስል ህይወት
ውስጥ ራስን ለእግዚአብሔር ማስረከብ ማዕከል እንደሆነ፣ እግዚአብሔር
በእርሱ መደገፍን ሊያስተምረን ፈተናን ይልካል።
“የኤሊ ግድየለሽነት በምድሩ ለሚኖሩ ለሁሉም አባቶች እና እናቶች
ግልጽ በሆነ ሁኔታ ፊት ለፊት ቀርቦ ነበር። ላልተቀደሰው ለልጆቹ ያለው ፍቅር
ወይም ልጆቹ የማይስማሙ እንኳ ቢሆን ማድረግ ያለበትን ነገር ባለማድረጉ
፣ እርሱ ታዛዥ ባልሆኑ ልጆቹ አማካይነት የኃጢአትን መከር አጨደ።
ልጆቻቸው ኃጢአት እንዲለማመዱ የሚፈቅዱ ወላጆችም ሆኑ ኃጢአትን
የሚያደርጉ ወላጆች ሁሉም በእግዚአብሔር ፊት በደለኛ ናቸው፣ እርሱ ስለ
እነሱ የሚቀርበውን ማንኛውንም መስዋዕት ሆነ ስጦታ አይቀበልም።”—Ellen G. White, Child Guidance, p. 276.
1. እንደ ክፍል፣ የእግዚአብሔር ልጅ ስለ እኛ ኃጢአት መስዋዕት ሊሆን ወደ ምድር ሲመጣ እጅግ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ዝቅ ያለበትን ተወያዩበት። ለሌሎች መልካም እንዲሆንላቸው ራስን ስለ መካድና መስዋዕትነት ስለ መክፈል ይህ ምን ትምህርት ያስተምረናል? እኛ ምንም እንኳ ክርስቶስ እንዳደረገው ለማድረግ የማንችል ብንሆንም ልንመራበት ምሳሌነቱ ሁሌም በፊታችን ነው። እኛ በራሳችን ሁኔታ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የከፈለውንና ያሳየንን ዓይነት መስዋዕትነት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? 2. ለብዙ ሰዎች በሚቀጥለው ጊዜ በህይወት የሚያጋጥም ነገር ምን እንደሆነ ሳያውቁ ራስን ለእግዚአብሔር መስጠት በጣም አስፈሪ ነገር ነው። በእግዚአብሔር ከመደገፍ ይልቅ በራሳቸው ለሚደገፉ ሰዎች ምን ዓይነት ምክር ይሰጣሉ? ወደፊት የሚሆነውን ነገር መቆጣጠር ባለመቻላቸው ከሚመጣ ፍርሃት ወይም ምን እንደሚሆን ከለማወቅ የተነሳ ፍርሃት ላለባቸው ሰዎች፣ ይህን ለማስወገድ ምን ይመክራሉ? 3. እንደ ክፍል ፣ በእግዚአብሔር መደገፍ ለዘላቂ ሰላም ብቸኛው መንገድ እንደሆነ እንዲያውቁ፣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ማስረከብ ላቃታቸው በመጸለይ ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ። በተመሳሳይ ጊዜ እነዚህ ሰዎች የእርሱ መንገድ የተሸለ እንደሆነ ተረድተው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አሳልፈው እንድሰጡ ለመርዳት ልታደርግላቸው የምትችለው ምን ተግባራዊ ነገር አለ? በሌላ አነጋገር፣ ሌሎች ሰዎች እግዚአብሔር ፈቃደኛ እንደሆነ እና የሚወዳቸው እንደሆነ እንዲረዱ ለማድረግ እግዚአብሔር አንተን ሊጠቀምብህ የሚችለው እንዴት ነው?