የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ሮሜ 15:4, 5; ሮሜ 5:3-5; 1 ሳሙ 26; መዝ 37:1-11።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “የመንፈስ ፍሬ ግን ... ራስን መግዛት ነው” (ገላ 5:22)።
ሳ
ይንቲስቶች የ4 ዓመት ዕድሜ ባላቸው ህጻናት እና ከሆነ ተክል የሚሰራ
አንድ ጣፈጭ በሆነ ምግብ(ማርሽማሎው) ላይ ጥናት አደረጉ።
ሳይንቲስቶቹ ለእያንዳንዱ ህጻን ምግቡ እንደሚሰጣቸው ነገሯቸው፤
ነገር ግን ፣ አንድ ህጻን ሳይቲስቶቹ ትንሽ የእግር መንገድ ሄደው እስኪመጡ
ከቆየ ሁለት እንደሚሰጠው ነገሯቸው ።ጥቂት ህጻናት ልክ ሳይንቲስቶቹ
እንደሄዱ የተሰጣቸውን ማርሽማሎው ጨምድደው አፋቸው ውስጥ ከተቱት፣
ሌሎቹ ደግሞ ሳይንቲስቶቹ እስኪመጡ ጠበቁ። ልዩነቱ ታወቀ።
ሳይንቲስቶቹ ይህን ግኝት በልጆቹ አፍላ ዕድሜ ላይ ምን ለውጥ እንደሚያመጣ
ለማየት አስቀመጡት። እነዚህ የተሰጣቸውን ምግብ ሳይንቲስቶቹ እስኪመጡ
ድረስ የጠበቁት ከልጠበቁት በተሻለ ሁኔታ፣ጥሩ ተማሪዎች፣ ራሳቸውን
መምራት የሚችሉ፣ እና በራሳቸው የሚተማመኑ ሆነው አገኙአቸው። ከዚህ
የተነሳ ትዕግስት በሰው ልጆች ህይወት ባህሪይ በመቅረጽ ላይ በጣም አስፈላጊ
መሆኑ ታይቷል። ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንንከባከበው ቢነግረን አስደናቂ
ነገር አይደለም።
በዚህ ሳምንት፣ ውስጥ በጣም አስቸጋሪ ከሆኑ ፈተናዎች ጀርባ
ያለው ፤ ‹‹የመጠበቅ ፈተና›› ምን እንደሆነ እንመለከታለን።
ሳምንቱን በአጭር እይታ: ለአንዳንድ ነገሮች ብዙ መጠበቅ ያለብን
ለምንድነው? በፈተና ውስጥ ሆነን ስለ ትዕግስት ምን መማር እንችላለን?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለጳጉሜ 5 ያጥኑ።
ሮሜ 15:4, 5ን ያንብቡ። በዚህ ቁጥር ለእኛ የሚሆን ነገር ምንድነው?
ተስፋ ለተሰጠን ወደፊት እንደምናገኝ በተነገሩን ነገሮች ላይ ትዕግስት የለንም ። የምንረካው የናፈቅነውን እና የሚንፈልገውን ነገር እኛ በፈለግነው ጊዜ ስናገኝ ብቻ ነው። የምንፈልገውን ነገር እኛ በፈለግነው ጊዜ የማግኘታችን ነገር ብዙም ባለመሆኑ፣ ለንዴትና ተስፋ ለመቁረጥ ተጥለናል ማለት ነው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ስንሆን፣ ሰለምን ለመጠበቅና በእግዚአብሔር ለማመን አስቸጋሪ ይሆናል። አንድን ነገር መጠበቅ በባህሪዩ በጣም የሚያም ነው። በእብራይስጥ፣ ‹‹ በትዕግስት ጠብቅ›› (መዝ 37 ፡7) የመጣው በእብራይስጥ ‹‹ ብዙ መከራ››‹‹ማወዛወዝ›› ‹‹ መንቀጥቀጥ›› ‹‹መቁሰል›› ‹‹ በሃዘን መከበብ›› ። ከሚሉ ቃላት ነው። ትዕግስትን መለማመድ ቀላል ነገር አይደለም። አንዳንድ ጊዜ በፈተና ውስጥ ማለት መሰረታዊ ስሜቱ ይህ ነው። መዝ 27:14፣ መዝ 37:7፣ እና ሮሜ 5:3-5ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች የሚነግሩን ምንድነው? ትዕግስት ወዴት ይመራናል?
በምንጠብቅበት ጊዜ፣ ከሁለት በአንዱ ነገር ላይ እናተኩራለን።
በምንጠብቀው ነገር ላይ ወይም ሁሉንም ነገር በእጁ በያዘው ላይ። ትልቅ ልዩነት
የሚያመጣው የምንጠብቀው ጊዜ ርዝመት ሳይሆን በመጠበቅ ውስጥ ያለው
የእኛ ባህሪይ ነው። በእግዚአብሔር ከታመንን እና ህይወታችንን በእርሱ እጅ
አሳልፈን ከሰጠነው፣ ፈቃዳችንን ለእርሱ ካስረከብን፣ ለማመን ቢከብደንም
መልካም በሆነ ጊዜ ፣ እርሱ ለእኛ መልካም የሆነውን እንደሚያደርግልን
እናምናለን።
በተለየ ሁኔታ እየጠበቁት ያለ ነገር ምንድነው? ሁሉንም
ነገር እግዚአብሔር በወደደው ጊዜ እንዲያደርገው ማስረከብን
የምንማረው እንዴት ነው? ሁሉን ነገር ለእግዚአበሔር የሚያስረከብ
ባህሪይ ለማግኘት ይጸልዩ።
ሮሜ 5:6 እና ገላ 4:4ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሔር ጊዜ ምን ይነግሩናል?
ጳውሎስ በእነዚህ ጥቅሶች፣ ላይ የሚነግረን ፣ክርስቶስ ለእኛ ሊሞትልን የመጣው በትክክለኛው ጊዜ እንደሆነ ነው። ነገር ግን ያ ትክክለኛ ጊዜ የሆነበትን ምክንያት አይነግረንም። ይህን ጥቅስ ስናነብ፣ ክርስቶስ የኃጢአትን ጉዳይ ለመፍታት ወደ ምድር ለመምጣት እነዚህን ሁሉ ሺህ አመታት፣ ለምን ጠበቀ ሰማያት ኃጢአት መጥፎ ነገር መሆኑን ሳይረዱ ቀርተው ነው ወይ? የሚል ጥያቄ እናነሳለን። እናም የሱስ ሁለተኛ ለመምጣትም ጊዜ እየጠበቀ ነው እንዴ የሚል ጥያቄ እንጠይቅ ይሆናል። አምላክ የእኔን ጥያቄ ለመመለስ ረዥም ጊዜ የሚጠብቀው ለምንድነው? ብለንም እንጠይቃለን። ለምሳሌ፣ የዳን 9፡ 24-27 ያለውን ወደ ክርስቶስ መሲህነት የሚመላክተውን የ70 ሳምንት ትንቢት ያስቡ። ይህ ጊዜ ምን ያህል ረዥም ነበር? ለእኛ ረዥም ጊዜ የሚወስድ ቢመስለንም እንኳ፣ ይህ የእግዚአብሔርን ጊዜ ስለ መጠበቅ ምን ያስተምረናል?
ለምን መጠበቅ እንደሚገባን ብዙ መንፈሳዊ ምክንያቶች
አሉ። አንደኛ፣ መጠበቅ ትኩረታችንን ‹‹ከነገሮች›› ላይ አንስተን ወደ
እግዚአብሔር እንድናደርግ ያደርገናል። ሁለተኛ፣ መጠበቅ የፍላጎታችንን
እና የመነሻ ምክንያታችንን በግልጽ እንድናደረጀው ይረዳናል። ሶስተኛ፣
መጠበቅ፣መንፈሳዊ የሆነ ለመጠበቅ የሚያስችል ውስጣዊ ጥንካሬ እንድኖረን
ይረዳናል። አራተኛ፣ መጠበቅ፣ እምነትንና በእግዚአብሔር መታመንን
የመሳሳሉትን መንፈሳዊ ጥንካሬዎችን እንድንለማማድ ይረዳናል። አምስተኛ፣
እግዚአብሔር በትልቅ ስዕል ውስጥ ያሉትን ትናንሽ ነገሮች እንዲተዋቸው
እና ስለ እኛ ብቻ እንዲያስብ ያደርገዋል። ስድስተኛ፣ የምንጠብቅበትን
ምክንያት አናውቅም ሆኖም ግን፣ በእምነት መኖርን እንማራለን። ስለ መጠበቅ
የሚያስቡት ሌላ ምክንያት አለ?
እግዚአብሔር ነገሮችን በራሱ ጊዜ እና ለእኛ በሚጠቅም መንገድ
በትክክለኛው ጊዜ እንደሚያደርጋቸውና በእርሱ መታመንን እንደምንለማማድ
የሚያደርጉ ሌሎች የመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሊያገኙ ይችላሉ?
(ለአብረሃምና ለሳራ ስለተነገረው የተስፋው ልጅ ያስቡ) በተመሳሳይ
ጊዜ ፣ ከረዥም ጊዜ በፊት መመለስ የነበረበት የጸሎት ጥያቄ ቢኖረኝ
ምን እያደረግሁ ነው የምጠብቀው? ብለው ራስዎን ይጠይቁ።
በ 1ሳሙ 16:1-13 ወጣቱ ዳዊት በነብዩ ሳሙኤል ለንጉስነት ሲቀባ እናያለን። እናም የአባቱን የእሰይን በጎች ከሚጠብቅበት እስከ ኢየሩሳሌም የንግስና ዙፋን ድረስ በጣም ረዥም ጉዞ ነበር። በዚህ መካከከል በትልቅ ፈተና ውስጥ ማለፉ ምንም ጥርጥር የለውም። አንደኛ ፣ ወጣቱ ክፉ መንፈስ መጥቶ ሲያስጨንቀው ለንጉሱ ሳኦል ሙዚቃ እንዲጫወት ተጠራ (1 ሳሙ 16) ቀጥሎ ጎልያድን በመግደሉ የእስራኤል ጀግና ሆነ (1 ሳሙ 17) ። ከዚያም ደዊት ነፍሱን ለማትረፍ ለብዙ ዘመናት ሲሸሽ ኖረ። ሳኦልም ሆነ ልጁ ዮናታን ዳዊት በእስራኤል ላይ ቀጥሎ የሚነግሰው እርሱ እንደሆነ ያውቃሉ (1 ሳሙ 23:17, 1 ሳሙ 24:20) ። ነገር ግን ዳዊት ይህንን እግዚአብሔር የሰጠውን ንግስና ፈጥኖ ለመያዝ ያደረገው ጥረት አልነበረም። በእርግጥ ያደርግ የነበረው የዚህን ተቃራንውን ነበር። ሰኦል ለመግደል በሚፈልግበት ጊዜ፣ አግንቶት የልብሱን ጫፍ ቆርጦ ይህንን ባላደረግሁ ብሎ ተቆጨ (1 ሳሙ 24:5-7) ። እንደገና ሳኦል ሊገድለው እየፈለገ ባለበት ወቅት ሳኦልን ለመግደል በሚያሰችል ዕድል አግኝቶ አልገደለውም ሳሙ 26:7-11). 1 ሳሙ 26:1-11ን ያንብቡ። ዳዊት ሳኦልን መግደል ያልፈለገበት ምክንያት ምን ነበር? እግዚአብሔር ለህይወታችን ስለሚያመጣቸው እድሎች ምን ያስተምረናል?
አሁን 1ሳሙ 26:12-25 በሳኦል ላይ ያመጣውን ያንብቡ። ደዊት ሳሙኤልን ለመግደል አለመፈለጉ በሳኦል ላይ ምን ተጽዕኖ አመጣ? ይህ እግዚአብሔርን መጠበቅ መልካም እንደሆነ ምን ያስተምረናል?
ዳዊት ወደ ዙፋን የተጓዘበትን መንገድ በሙሉ በማየት እንዲህ
በሚል አጭር አረፍተ ነገር ማጠቃለል እንችላለን፡- እግዚአብሔር ሊሰጥህ
ጊዜው ያልደረሰን ነገር በራስህ አትመንትፈው። የእግዚአብሔርን
ፍጹም በረከቶች የምንቀበለው በጊዜው ከራሱ እጅ ነው። ይህ ምናልባት
ረዥም ጊዜ ሊያስጠብቀን ይችላል። የአደንጓሬ ዘር ለመብቀል የሚፈጀው
ጥቂት ደቂቃዎችን ሲሆን፣ የኦክ (oak)ዛፍ ግን ብዙ ዓመታትን ይፈጃል። ነገር
ግን ይህ ዛፍ ታላቅ ነፋስ የመጣ ጊዜ በፍጹም አይነቀልም።
ዳዊት ሳኦልን ቢገድለው ሊያቀርብ የሚችላቸውን ምክንቶች
ያስቡ። ነገር ግን የእርሱ ተግባር የሚያሳየው በእግዚአብሄር ላይ ያለውን
እውነተኛ እምነት ነው። እርስዎ በሚጠባበቁት ጉዳይ ሆነ በማንኛውም
ነገር ከዚህ ሊወስዱት የሚችሉት ምሳሌ ምንድነው?
በቀርሜሎስ ተራራ ጫፍ የነበረው ድባብ አልፏል። (1ነገ 18) ከሰማይ እሳት ወርዷል፣ ሰዎች ሁሉ እውነተኛውን አምላክ ተቀብለዋል፣የሐሰት ነብያት ሁሉ ተገድለዋል። እግዚአብሔር ከወቀሳ ነጻ ሆኗል። ምናልባት እነዚህ ቀናት ሲያልፉ ኤልያስ በመንፈሳዊ ነገር እያደገ የመጣ ሊመስላችሁ ይችላል። እርሱ ግን በድንገት መሞት አስኪናፍቅ ድረስ አጅግ የሚያስጨንቅ ነገር ሰማ። የቀረውን ታሪክ በ1ነገ 19፡ 1- 19 ያንብቡ። በዚህ ጥቅስ የመጨረሻ ቃላት አስጨናቂ ናቸው። ‹‹ የእግዚአብሄር ቃል ወደ እርሱ እንዲህ ሲል መጣ፡ኤልያስ ከዚህ ምን ታደርጋለህ? (1 ነገ 19 ፡9) በዚህ ጊዜ የኤልያስ ፍርሃት ትክክለኛ ባልሆነ ስፍራ እንዲገኝ አድርጎታል። በቀርሜሎስ ተራራ ከታየው የእግዚአብሔር ታላቅ ጣልቃ ገብነት በኋላ ፣ኤልያስ በእግዚአብሔር ታላቅነት ሙሉ እምነትና መታመን ሊኖረው ይገባ ነበር፣ ነገር ግን በዚህ ፋንታ፣ በፍርሃት ህይወቱን ለማትረፍ ሸሸ። ከዚህ መጥፎ ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?
ይህ ታሪክ አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገርን ይገልጽልናል፤ በምንቸኩልበት ጊዜ ራሳችንን በቀላሉ በተሳሳተ ቦታ እናገኛለን። በኤልያስ ጉዳይ ስንመለከት፣ እርሱ ወደ ምድረበዳ እንድሸሽና ባልተወለድኩ እንዲል ያደረገው በፍርሃት መዋጡ ነው። ነገር ግን ሌሎች ነገሮች እግዚአብሔር ለእኛ ካዘጋጀልን ዕቅድ ፈጥነን እንድንወጣ ያደርጉናል። የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብበቡ። ዘፍ 16:1-3፣ዘዳ 20:1012፣ መሳ 14:1-3፣ ማቴ 20:20, 21፣ ሉቃ 9:52-56 ሐዋ 9:1ን ያንብቡ። በዚህ ስፍራ ያሉትን ተዋናዮች ከእግዚአብሄር ሀሳብ ፈጥነው እንዲርቁ ያደረጋቸው ምንድነው?
ጉጉት፣ ቅጣት፣ ፍቅር፣ እምነት ማጣት፣ ወይም ‹‹ ለእግዚአብሔር
ቀናሁ›› ብለን የምናስበው ነገር ሳናውቀው እንዴት መሄድ በማይገባን ቦታ
በቀላሉ ራሳችንን እንድናኝ እንደሚያደርጉን ተመልከቱ። ይህንን አደጋ
ለመከላከል ማንም አይችልም። ቁልፉ እንደሚወደን በምናውቀውና ለእኛም
መልካም የሆነውን በሚመኘው በአምላካችን በእግዚአብሔር መልካምነትና
ምህረት ላይ በእምነት ለመደገፍ ራስን ማለማመድ ብቻ ነው። ይህ በአንዴ
ዝም ብሎ የሚከሰት ነገር አይደለም። እምነት ሥጦታ ቢሆንም፣ መኮትኮትን፣
መመገብንና ጥንቃቄን ይፈልጋል።
“በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ የልብህን መሻት ይሰጥሃል” (መዝ 37:4).
መዝሙር 37:4 በጣም አስገራሚ የሆነ ተስፋ ነው። የሚፈልጉትና
ሁልጊዜ ማግኘትን አስቡት። ነገር ግን የልባችንን መሻት ማግኘት
ከእግዚአብሔር ጋር በጥሩ ሁኔታ እንድንግባባና በእርሱ ደስ የሚሰኝ ልብ
እንዲኖረን ያደርገናል። ስለዚህ ፣‹‹በእግዚአብሔር ደስ መሰኘት›› ማለት ምን
ማለት ነው?
መዝ 37:1-11ን ያንብቡ። የመዝሙር 37፡ 4 አውድ ምናልባትም
አስደናቂ ይሆናል። ዳዊት እየተናገረ ያለው በእግዚአብሔር እና በእርሱ ተቃራኒ
በሚሰሩ ሰዎች ተከቦ ነው። ሰዎች በእኛ ተቃራኒ ነገሮችን በሚያደርጉበት ጊዜ
ተፈጥሮአዊ ምላሽ የሚሆነው፣ መቆጣትና ራሳችንን ነጻ ለማድረግ ምክንያት
ማቅረብ ነው። ነገር ግን ዳዊት የሚመክረን ሌላ የተለየ ነገር ነው።
ዳዊት በሚከተሉት ጥቅሶች በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ
ለሚገኙ ሰዎች የሚመክረው ምክር ምንድነው?
መዝ 37:1 ________________________________
መዝ 37:5 ________________________________
መዝ 37:7 ________________________________
መዝ 37:8 ________________________________
መዝ 37:4ን እንደገና ያንብቡ። ባነበባችኋቸው ጥቅሶች
አውድ ‹‹በእግዚአብሔር መደሰት›› ማለት ምን ማለት ነው?
ዳዊት በተደጋጋሚ በተለያየ መንገድ ‹‹ በእግዚአብሔር ታመኑ››
እያለ ነው። እርሱ እንዲሰራ ታመን። ተስፋ አትቁረጥ፣ እግዚአብሔር
አሁን በዚህ ሰዓትም ለአንተ የሚሰራ የአንተ አምላክ ነው። በራስህ ነገሮችን
ለማስኬድ መሞከር የለብህም። የሰማይ አባትህ ኃላፊነትህን ይወስዳል።
እርሱን እመነው። በፍጹም ተማመነው።
ዳዊት በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ ያለው በዚህ አውድ ነው።
በእግዚአብሔር ደስ መሰኘት ማለት በፍጹም ታምኖ መኖር ማለት ነው።
እግዚአብሔር እዚህ በሥራ ላይ በመሆኑ ምንም ነገር ሰላማችንን ሊረብሽ
አይችልም። የእኛን አምላክ ማንም የሚበልጠው ስለሌለ፣እርሱን ማመስገን
፣እንዲሁም ፈገግ ማለት እንችላለን። ይህን ማድረግ ስንማር፣ ልባችን
የሚመኘውን እናገኛለን፣ ምክንያቱም የምንቀበለው የሚወደን አምላካችን
ለመንግስቱ እና ለእኛ የበለጠ የሚጠቅመንንና ሊሰጠን የፈቀደውን ነው።
በእግዚአብሔር ሀሴት ማድረግን የምንማረው እንዴት
ነው? ይህ በህይወትዎ እውን የሚሆንበትን ሁኔታ እና አመራር
ከእግዚአብሔር ለማግኘት የተወሰነ ጊዜን በጸሎት ያሳልፉ።
‹‹ የዳዊት መቀባት›› አባቶችና ነብያት ገጽ 637–642።.
የእግዚአብሔር እቅድ መጠበቅ ምናልባት ብዙ መጠበቅ ያስፈልገው
ይሆናል፣እና ይህም በእርግጥ ፈተና ልሆንብን ይችላል። በዚህ ጊዜ ትእግስትን
መማር ሊሆን የሚችለው ለእኛ እየሰራ ባለው በእግዚአብሔር በፍጹም በማመን
ብቻ ነው። ለመጠበቅ ምክያት የሚሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ፣ ነገር ግን ሁሉም
እግዚአብሔር ለእኛ ላቀደው ዕቅድ በእግዚአብሔር በመታመንና በመንግስቱ
ሀሳብ የሚተኩሩ ናቸው። ከእግዚአብሔር ቀድመን ወደፊት የምንሮጥ ከሆነ
ብዙ ነገር እናጣለን፣ ነገር ግን ብዙውን የምናገኘው በእግዚብሔር መታመንን
እና በእርሱ መደሰትን በመለማመድ ነው።
እግዚአብሔር ሁሉንም መከራዎች ይመዝናቸዋል። “በእኔ መከራ
ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ዓላማ አላውቅም በጣም የተሸለውን
እርሱ ያውቃል፣ ስለዚህ ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብያለሁ፣ ‹‹
ነገር ግን ስለዚህ ምክንያት ይህንን መከራ ደግሞ ተቀብያለሁ፣ ነገር ግን
አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን
ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቸያለሁ›› 2ጢሞ 1፡12 ። ነፍሳችንን የበለጠ
እምነት፣በሰማያዊው አምለክ ላይ የበለጠ መታመንን፣ የበለጠ ፍቅር፣ እና
ትልቅ ትዕግስት፣ እንዲኖራት አስተምረናል አሰልጥነናል። በዚህ ህይወት ዕለት
ተዕለት በሚያጋጥመን ስቃይ ደስታና ሰላም እንደሚኖረን አምናለሁ።
“አምላክ ከክርስቶስ እቅፍ ውስጥ ወጥተን በጠላት እንድንነደፍ
ወይም እንድንሰቃይ እንዲሁም ራሳችንን በጭንቀት በመኖራችን አይደሰትም።
የበለጠ በትኩረት መመልከትና መጠበቅ የሚያስፈልገን ነው። እኛ ያለንበት
በትክክለኛ መንገድ አይደለም ብለን ካላሰብን በቀር፣ እና አንድ ላጋጠመን
ሁኔታ ለእኛ የምስማማ ምልክት ለማግኛት ወደ ውስጣችን ካላየን በስተቀር ፣
ነገሮችን የምንመዝነው በእምነት ብቻ ይሆናል። የተመረጡ መልዕክቶች 2ኛ
መጽ ገጽ 242.
1. ኢየሱስ ሁሉንም ፈተና ‹‹ይመዝናል እና ይለካል›› ማለት
ምን ማለት ነው። ይህ በመጠበቅ ላይ ሳለን ምን ይጠቅመናል?
2.በትዕግስት መጠበቅ ምን እንደሆነ ሰዎች የግል ምስክርነት
እንዲሰጡ ያድርጉ። በዚህን ጊዜ ፍርሃታቸው ምን ነበር፣
ደስታቸውስ? ምን ትምህርት ተማሩ? የሙጥኝ ያሉበት
(የተደገፉበት) ተስፋስ?
3.እንደ ቤተክርስቲያን ሌሎች በፈተና ውስጥ ሆነው ስለሆነ ነገር
የእግዚአብሔርን ጊዜ በመጠባበቅ ለሚኖሩ ሰዎች ምን ያደርጋሉ?
4. ትዕግስትን ለማሳደግ የጸሎት ሚና ምንድነው? መንፈስ ቅዱስ
በህይወታቸው ትዕግስትን እንዲያሳድግላቸው የምትጸልዩላቸው
ነፍሳት አሉ?