የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ሉቃ 2:7, 22-24; ማቴ 2:1-18; ዮሐ 8:58, 59; ሉቃ 22:41-44; ማቴ 27:51, 52; ሮሜ 6:23; ቲቶ 1:2.
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “በዘጠነኛውም ሰዓት ክርስቶስ በታላቅ ድምጽ፣ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ብሎ ጮኸ? ይህም ማለት አባቴ አባቴ ለምን ተውከኝ ማለት ነው?” (ማቴ 27:46).
የ
መከራን ጉዳይ በምናይበት ጊዜ፣ ጥያቄ ወደ አእምሮአችን ይመጣል፡
ኃጢአትና መከራ መጀመሪያ የተጀመረው እንዴት ነው? በመለኮታዊ
መገለጥ በኩል ጥሩ የሆነ መልስ አለን፤ እነርሱ የተፈጠሩት ነጻ የሆኑ
ፍጥረታት እግዚአብሔር የሰጣቸውን ነጻነት ያለ አግባብ ስለተጠቀሙበት
ነው። ይህ ደግሞ ወደ ሌላኛው ጥያቄ ይመራናል። እነዚህ ፍጡራን
እንደሚወድቁ እግዚአብሔር ያውቅ ነበር? አዎን ነገር ግን ፣ ሉዊስ የሚባለው
ሰው እንደጻፈው “ስለ አደጋው አስብበት”ያዕቆብ ፈርዖንን የባረከው ሲሆን
(ዘፍ. 47፡7-10)፣ ይህም በምድር የሚኖሩ ሕዝቦች በአብርሃማዊው ኪዳን
አማካይነት እንደሚባረኩ (በከፊል) የተገባው ቃል ፍጻሜ ነበር (ዘፍ. 12፡
3)። ኋላ ላይ፣ ያዕቆብ ሊሞት አካባቢ የዮሴፍን ልጆች ባረካቸው (ዘፍ. 48)።
ያዕቆብ የገዛ ልጆቹንም የባረካቸው ሲሆን (ዘፍ. 49፡1–28)፣ በወደፊቶቹ 12
የእስራኤል ነገዶች ዐውድ፣ ስለ እያንዳንዳቸው አስደናቂ ትንቢቶችን ተናግሯል
(ዘፍ. 49፡1–27)።
ስለ አደጋው አስብበት? ለማን? ለእኛ፣ እግዚአብሔር በሰማይ በዙፋኑ
እንደተቀመጠ? በእርግጠኝነት አይደለም። ለአስተዋይ ፍጥረታቱ ሁሉ
ነጻነት የተከለከለ ከሚሆን ይልቅ በትክክል የተጠበቀ ነበር። እግዚአብሔር
ፍጥረታቱ ሁሉ ነጻነታቸውን በአግባቡ ባለመጠቀማቸው የሚመጣውን
መከራ በራሱ ላይ ለመሸከም ወሰነ። እና ይህንን መከራ በክርስቶስ ህይወትና
ሞት አይተነዋል፣ ይህም በህይወታችን በሚሆነው መከራ በኩል፣ በሰማይና
በምድር ለዘላላም የማይቋረጥ አገናኝ ሰንሰለት ሆኗል።
ሳምንቱን በአጭር ዕይታ: ክርስቶስ በእኛ ፋንታ የተሰቃየው ስቃይ
ምን ነበር? ከእርሱ ስቃይ እኛ ምን እንማራለን?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለመስከረም 14 አጥንተው ይዘጋጁ
ቅዱሳት መጻህፍት ስለ ክርስቶስ ህይወት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የሚነግሩን ጥቂት ነው። የተወሰኑ ቁጥሮች ግን ፣ አዳኛችን የመጣበት ዓለም ምን እንደሚመስል ይነግሩናል። ሉቃ 2:7, 22-24 (ደግሞ ዘሁ 12:6-8) እና ማቴ 2:118ን ያንብቡ ። እነዚህ ጥቅሶች ክርስቶስ ከጅምሩ የነበረው ህይወት ምን ዓይነት እንደነበር ምን ይነግሩናል?
በእርግጥ፣ ከልጅነቱ የድህነትን ኑሮ መኖርና እና የግድያ ሙከራ የተደረገበት እርሱ ብቻ አልነበረም። ነገር ግን ክርስቶስ ከልጅነቱ ጀምሮ የተሰቃየበት የተለየ መሆኑን ለማስተዋል አንድ ነገር አለ። ዮሐ 1:46ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ ወጣቱ ኢየሱስ የተቀበለውን መከራ ለማስተዋል የሚሆን ምን ነገር ይጨምርልናል?
አዳምና ሄዋን ከውድቀት በፊት ከነበራቸው ህይወት በስተቀር፣
ክርስቶስ በምድር ላይ ከኖሩ ሰዎች ሁሉ ኃጢአት አልባው እርሱ ብቻ ነበር።
በንጽህናው፣ በኃጢአት አልባነቱ፣ ወደ ኃጢአተኛው ዓለም ጠልቆ ገባ። ህጻን
እንደመሆኑና ኃጢአት አልባ ለነበረው ህይወቱ ሳይቋረጥ ከኃጢአት ጋር
መገናኘት ምን ያህል አስጨናቂ እንደሆን ያስተውሉ። በኃጢአት ምክንያት
ልባችን የጠነከረ ሆነን ሳለን እንኳ፣ ከሚያስጠላን ለኃጢአት እና ክፉ ራስን
ከማጋለጥ እንቆጠባለን። እንግዲህ ንጹህ ለሆነው፣ የኃጢአትም ነቁጣ
ላልነበረበት ለክርስቶስ ምን ይመስል እንደነበር አስቡት። እንግዲህ በእርሱና
በዙሪያው በነበሩት ዘንድ የነበረውን የሰላ ንጽጽር አስቡት። ይህ ለእርሱ
በጣም የሚያሳምም መሆን አለበት።
“እኔ በዙሪያዬ ላለው ኃጢአት ምን ያህል እጨነቃለሁ?
እነዚህ ኃጢአቶች ይረብሹኛል፣ ወይስ ልቤ ደንድኗል?” ራስዎን
ይጠይቁ። ልብዎ ደንድኖ ከሆነ ፣ ይህ የሆነው ስላነበቧቸው፣
ስላዩአቸው፣ ወይስ ስለተለማመዷቸው ነገሮች ነው? ያስቡበት።
ክርስቶስ መለኮታዊ፣ የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ እና ራሱን ለመላው ኃጢአተኛ ዓለም ለመሰዋት መምጣቱን በአእምሮ ሳይረሱ የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። (ማቴ 12:22-24; ሉቃ 4:21-30; ዮሐ 8:58, 59). እነዚህ ጥቅሶች ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ የተጋፈጠውን መከራ ለማስተዋል የሚጠቅሙን እንዴት ነው?
ሊያድናቸው መጥቶ ሳለ፣ በመሪዎችም ሆነ በተራው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖረው፣ የክርስቶስ ህይወት፣ሥራም ሆነ ትምህርቱ በትክክል አልተስተዋለም። በአንዳንድ ሁኔታዎች ስናየው አንድ እርዳታ የሚያስፈልገው ልጅ ሆኖ ወላጅም ለልጁ የሚያስፈልገውን ሁሉ ነገር ሊሰጠው ፈቃደኛ ሲሆን፣ ምናልባትም ይህንን ልጅ ከመከራና ስቃይ ሊያድነው የሚችለውን አባት በመቃወም ልጁ የወላጁን እርዳታ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ ልጅን ይመስላል። ክርስቶስ በዚህ ምድር ሲኖር ያጋጠመው ያ ነበር። ይህ ለእርሱ ምን ያህል የሚያሳምም ነበር። ማቴ 23 ፡ 37 ያንብቡ። ይህ ክርስቶስን ሲቃወሙት የነበረው ስሜት ምን እንደነበር ምን ይነግረናል? እያነበቡ ሳለ ራስዎን እርሱ በተቃውሞው ምክንያት በራሱ ላይ መጥፎ ነገር ይሰማው ነበር ( አንዳንዴ እኛ ተቃውሞ ሲገጥመን እንደሚሰማን)፣ ወይስ ምክንያቱ ሌላ ነበር ከሆነስ ምክንያቱ ምንድነው?
ሁላችንም ለማመን እምቢ በሚሉ ሰዎች ምክንያት የመነደፍ ስሜቱን
ተጋርተነዋል። ምናልባትም የእኛ እምቢ መባል ከክርስቶስ ጋር ተመሳሳይ
ሊሆን የሚችለው እኛ ህመም ያሰከተለብን ነገር ተቀባይነት ማጣታችን
አይደለም፣ ነገር ግን ያ ተቃውሞ ማለት ለተቃዋሚው እኛን መቃዎም
ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስለምናውቅ ነው።( ምናልባትም እኛ በጣም
የምንጠነቀቅለት ሰው ከክርስቶስ የተሰጠውን መዳን እምቢ ሲል የሚሰማን
ስሜት ማለት ነው።) እነርሱን ለማዳን ሲል ሊገጥመው የሚችለውን ነገር
ሁሉ ለሚያውቀው እና ይህን መቃወም የሚያስከትለው ቅጣት ምን እንደሆነ
በትክክል ለሚረደው ክርስቶስ ይህ ምን ዓይነት ህመም እንደሚያስከትል
አስቡ። “ክርስቶስ በየዋህነት ነበር የሰይጣንን ክፋት ( መጥፎነት)በትክክል
ያስተዋለው።”—Ellen G. White, Selected Messages, book 3, p. 129.
በተቃውሞ ጊዜ የሚረዳንን ምን ዓይነት ትምህርት ነው
ከክርስቶስ ልናገኝ የምንችለው? የእርሱ ምሳሌ ምን ያሳያችኋል?
ይህንን ለራሳችን ህይወት ለመተግበር የምንችለው እንዴት ነው?
“ነፍሴ እስከሞት ድረስ እጅግ አዘነች፣ በዚህ ቆዩ ትጉም አላቸው” (ማር 14:34). ክርስቶስ በዚህ ምድር በቆየበት 33 ዓመት የተሰቃየው ፣ ለዘመናት መዳረሻ፣ ለመሰቀል ተቃርቦ ከነበረበት ጊዜ ጋር በፍጹም ምንም ነገር ሊነጻጸር የሚችል የለም።(ኤፌ 1:1-4; 2 ጢሞ 1:8, 9; ቲቶ 1:1, 2) ክርስቶስ ለዓለሙ ሁሉ ኃጢኣት መስዋዕት መሆኑ ዓለም ሳይፈጠር የታቀደ ሲሆን ይህ ጊዜ በእርግጥ ደርሶ ነበር። የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ ክርስቶስ የጌቴሴማኒ ስቃይ ምን ይነግሩናል? ማቴ 26:39, ማር 14:33-36, ሉቃ 22:41-44.
“እነርሱ ሊያዩትና ሊሰሙት በሚችሉበት ርቀት ላይ ሆኖ በልቡ
ተደፋ። እርሱም በኃጢአት ምክንያት ከአባቱ የተለየ መሰለው። በመካከል
ያለው ጉድጓድ በጣም ጥልቅ፣ ሰፊ እና ጨለማ የሰፈነበት ነበር። መንፈሱ
እጅግ ተጨነቀ። ይህንን ጭንቀት ለማምለጥ መለኮታዊ ኃይል መጠቀም
አይችልም ። እንደ ሰው ሆኖ የሰዎችን ኃጢአት ውጤት መቀበል ነበረበት።
እንደ ሰው ሆኖ እግዚአብሄር በኃጢአትና መተላለፍ ላይ የሚያመጣውን ቁጣ
መቋቋም ነበረበት።
“ክርስቶስ ከአሁን በፊት ከነበረበት ሁኔታ በጣም ልዩ በሆነ ሁኔታ ውስጥ
ይገኛል። የእርሱ መከራ ‹‹ ሰይፍ ሆይ ባልንጄራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ
ንቃ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፤ እረኛውን ምታ በጎቹም ይበተናሉ
እጄን በታናናሾች ለይ እመልሳለሁ። (ዘካ 13፡ 7) በሚለው በነብዩ ቃላት
አማካይነት በጥሩ ሁኔታ ተገልጾ እናገኘዋለን። ክርስቶስ ኃጢአተኛ ለሆነው
ሰው እንደ ምትክ በመሆን በመለኮታዊ ፍርድ ስር ነበር። በዚህም ቅን ፍርድ
ማለት ምን እንደሆነ ተመለከተ። በዚህ ምክንያት ነው እርሱ የሰብዓዊ ዘር
አስታራቂ ሆኖ በአብ ፊት የሚታየው ቢሆንም ለእርሱ ግን ያኔ አማላጅ
አልነበረውም። ”—Ellen G. White, The Desire of Age, p. 686.
በጌቴሴማኒ በክርስቶስ ላይ እየሆነ ባለው ነገር ላይ ትኩረት
ያድርጉ። የዓለም ሁሉ ኃጢዓት በእርሱ ላይ ወድቋል። ይህ ምን
እንደሚመስል ያስቡበት። እስከዛሬ ማንኛውም የሰብዓዊ ዘር እንዲህ
ዓይነት ነገር ውስጥ እንድያልፍ ተጠርቶ አያውቅም ወደፊትም
አይጠራም። ይህ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ምን ይነግረናል? ከዚህ
ለራስዎ ምን ተስፋ ያገኛሉ?
በሮማውያን ዘንድ በመስቀል መሰቀል በጣም ከባድ ከሚባሉ
ቅጣቶች አንዱ ነበር። ይህም በጣም አስከፊ የሆነው ሞት ዓይነት እንደሆነ
ይታመናል። ስለዚህ፣ ለማንኛውም ሰው ይህ አሟሟት እንዴት አስከፊ ነው፣
በተለይም ለእግዚአብሔር ልጅ እንደ እኛ ሥጋ ለብሶ ሰው ሆኖ ለመጣው
ኢየሱስ። በመገረፍ፣ በመወጋት፤ ሚስማር ወደ ሰውነቱና ወደ እጆቹና
እግሮቹ ተሰክቶ ፤ የራሱ የደከመ ሰውነት ክብደት በተወጋበት ቦታ ሁሉ ቁስሉ
እንዲተረተር ሲያደርገው አካላዊው ህመም ለመሸከም የሚቻል አይደለም።
ይህ ወንጀለኞች ለሆኑት እንኳ በጣም የጭካኔ ቅጣት ሲሆን ትሁት ለሆነው
ክርስቶስ ይህን አስከፊ ሁኔታ መጋፈጥ እንዴት ኢ- ፍትሃዊ ይሆን!!
ሆኖም፣ እንደምናውቀው፣ በእርግጥ እየሆነ ካለው ጋር ስነጻጸር
የክርስቶስ አካላዊ መከራ ቀላል ነው ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ይህ አንድን
በደል የሌለበትን ሰው ከመግደል ያለፈ ነገር ነው።
በክርስቶስ አሟሟት ዙርያ የታዩ ነገሮች ብዙ ሰዎች
ከሚያስተውሉት በላይ ነበር? በእነዚህ በእያንዳንዱ ድርጊት
እየሆነ ያለው ነገር ምን እንደሆነ ለመረዳት የሚያሰችል ምን ዓይነት
ጠቃሚ ነገር ያገኛሉ?
ማቴ 27:45 _______________________________
ማቴ 27:51, 52 _____________________________
ማር 15:38 _______________________________
በግልጽ፣ በዚህ ሥፍራ እየሆነ ያለው ነገር ምንም በደል ለሌለበት
ሰው ተገቢ ያልሆነ የሞት ቅጣት ከመሆኑ ባሻገር አንድ ከሞት ያለፈ ነገር
እየተከናወነ ነው። እንደ እግዚአብሔር ቃል፣ እርሱ በኃጢአት ላይ ያለው
ቁጣ፣ (በእኛ ኃጢዓት ላይ) በእርሱ ላይ እየወረደ ነበር። ክርስቶስ በመስቀል
ላይ የቅዱስ እግዚአብሔርን፣ በዓለሙ ሁሉ ኃጢዓት ላይ ያለውን ቅዱስ
ቁጣ ጭንቀት ተቀበለ። ክርስቶስ የተቀበለው መከራ፣ ጥልቅ፣ ጨለማ የሆነ፣
እንዲሁም ማንም የሰው ልጅ ከሚያውቀው እና ከተለማመደው በላይ በጣም
ትልቅ ህመም ያለው ነው።
በምንም ዓይነት ትግሎች ውስጥ እያለፉ ቢሆን፣
ከክርስቶስ መከራ እና የመስቀል ሞት እውነታዎች ውስጥ ምን
ዓይነት ተስፋና መጽናናት ማግኘት ይችላሉ?
በዚህ ምድር እስካለን ድረስ፣ መከራ እንዳለ ስለተለማመድን እናውቃለን። እንደ ወደቁ ፍጡራን፣ ይህ የእኛ እጣችን ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዚህ የተለየ ምንም ተስፋ አልተሰጠንም። በተቃራኒው . . . የሚከተሉት ጥቅሶች እየተነጋገርን ስለምንገኝበት ርዕስ ምን ይነግሩናል? ሐዋ 14:22, ፊሊ 1:29, 2 ጢሞ 3:12.
በመከራዎቻችን ውስጥ እንኳ ብንሆን፣ ሁለት ነገሮችን መርሳት የለብንም ። በመጀመሪያ፣ ክርስቶስ የእኛ አምላክ፣ ከእኛ ማናችንም ያላየነውን ዓይነት መከራ ተቀብሏል። እርሱ በመስቀል ላይ፣ ‹‹ ህመማችንን ተሸክሟል›› (ኢሳ 53:4) እኛ እርሱ ያደረገልንን ለግላችን እንደሆነ እናውቃለን ፣ እርሱ የተሰቃየው ደግሞ ለሁሉም የሰው ዘር ነው። ‹‹እርሱ ኃጢአት የማያውቀው ስለ እኛ ኃጢአት ሆነ››(2 ቆሮ 5:21) ስቃዩም እኛ ኃጢአተኛ ፍጡር እንደመሆናችን ልንገምተው ከምንችለው በላይ ነው። ነገር ግን ፣ሁለተኛው ፣ በመከራ ውስጥ ሆነን፣ የክርስቶስ መከራ ውጤቶችን ማስታወስ አለብን ምክንያቱም የተሰጠን ተስፋ የእርሱን መከራ ውጤቶች (ለእኛ ያደረገውን ማሰብ ነው።) ዮሐ 10:28ን ያንብቡ። ሮሜ 6:23, ቲቶ 1:2, እና 1 ዮሐ 2:25. የተሰጠን ተስፋ ምንድነው?
በዚህ ምድር ያለው መከራ ምንም ቢሆን፣ ክርስቶስ ምስጋና
ይግባውና፣ የኃጢአታችንን ቅጣት እርሱ ተሸከመልን፣ ስለ ታላቁ የወንጌል
መልዕክት እግዚአብሄር ምስጋና ይድረሰው፣ በእምነት አማካይነት በክርሰቶስ
ፊት ፍጹም ሆነን እንድንገኝ፣ እና ከእርሱ የተነሳ የዘላላም ህይወት አለን።
ክርስቶስ ከሰራው ሥራ የተነሳ እኛ ተስፋ አለን ፣ ምክንያቱም ከእርሱ ሙሉነት፣
ፍጹምነት፣ የተሟላ ህይወት እና መስዋዕትነት የተነሳ እኛ በዚህ ምድር
የሚያገኘን ስቃይ፣ ህመም፣ ተስፋ መቁረጥ፣ እና ማጣት፣ ኃጢአት የሌለበት
፣ ስቃይ እንዲሁም ሞት በማይገኝበት፣ በአዲሱ ሰማይ እና አዲስ ምድር
ከሚጠብቀን ዘላለማዊነት ጋር ሲነጻጻር፣ ምንም እንዳይደለ እናውቃለን።፡
ይህ ሁሉ ነገር እርግጠኛ የሆነውና ተስፋው የተሰጠን በክርስቶስ እና እርሱ
በታላቅ ፈተና ውስጥ በመለፉ ሲሆን፣ አንድ ቀን በቶሎ ይመጣል ‹‹ከነፍሱ
ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል›› (ኢሳ 53 11)።
የዘመናት ምኞት በሚለው የኤሌን ዋይት መጸሐፍ
‹‹ጌቴሴማኒ›› በሚለው ርዕስ ገጽ685-697 እና ‹‹ጎልጎታ›› ገጽ 741-757
ያለውን ያንብቡ።
“ይህንን ጸሎት ሶስት ጊዜ ጸለየ። ሰብኣዊነት ሶስት ጊዜ ዘውድ
ከሚያስጭነው የመጨረሻ መስዋዕት አፈገፈገ። ነገር ግን የሰው ዘር ታሪክ
በዓለም አዳኝ ፊት ቀረበ። እርሱ የህግ ተላላፊዎችን ለራሳቸው ቢተው
ለዘለዓለም መጥፋታቸው መሆኑን ተረዳ። እርሱ ሰው የሚረዳው የሌለው
መሆኑን አየ። እርሱ የኃጢአትን ኃይል አየ። የተረገመው ዓለም ወዮታና ለቅሶ
በፊቱ ከፍ አለ። የዚህን ዓለም እጣ ፋንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በፊቱ መጣ
ስለዚህም እርሱ ውሳኔ አደረገ። ማንኛውንም ዋጋ ከፍሎ የሰውን ልጅ ማዳን
አለበት። እርሱ የደም ጥምቀቱን በመቀበሉ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ጠፊዎች
ህይወትን እንዲያገኙ ፈለገ። እርሱ ሁሉም ነገር ንጹህ፣ፍጹም ደስታ እና ክብር
የሆነውን የሰይማይን ዙፋን ለቆ በኃጢአት ምክንያት የጠፋውን ይህንን ዓለም
ለማዳን መጣ። እናም እርሱ ከመጣበት ተልዕኮ ፍንክች አይልም። ኃጢአትን
ለማድረግ ራሱን ለሰጠው የሰው ዘር የሚያስፈልገውን እርሱ አደረገ። አሁን
የእርሱ ጸሎት ራሱን የመስጠቱ ማሳያ እስትንፋስ ብቻ ነበር። ‹‹አባት ሆይ
ፈቃድህ ከሆነ ይህች ጽዋ ሳልጠጣት ከኔ ትለፍ››
1. እግዚአብሔር ራሱ በክርስቶስ ሥጋ የመልበስ መከራ በዚህች ምድር ማናችንም ያልተሰቃየነውን ያህል መሰቃየቱን ማወቃችን ምን ይጠቅመናል? የክርስቶስ በእኛ ፋንታ መከራ መቀበል ማለት ለእኛ ምን ማለት ነው? ከዚህ አስደናቂ እውነት ምን ዓይነት መጽናናት እናገኛለን? ስለ መልስዎ ሲያስቡ ኤሌን ዋይት የተናገረችውን የሚከተለውን አረፍተ ነገር ያስታውሱ። “የኃጢአት ውጤት የሆነው ነገር ሁሉ ኃጢአት በማያውቀው የእግዚአብሔር ልጅ ጫንቃ ላይ ተጭኗል”—Selected Messages, book 3, p. 129. 2. እንደ ክፍል ፣ በዚህ ሳምንት ትምህርት የነበረውን የክርስቶስን መከራ ተመልከቱ። ክርስቶስ የተጋፈጣቸው ፈተናዎች ምንድናቸው? እነዚህ መከራዎች ልክ እንደኛው ዓይነት ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው ከእኛው የሚለዩትስ በምንድነው? እርሱ እነዚህን ፈተናዎች ያለፈበት ሁኔታ እኛ በመከራ ውስጥ ስንሆን የሚጠቅሙን እንዴት ነው? 3. በመከራ ውስጥና በሚያሳምም እና በሚያሳዝን ፈተና ውስጥ ሆነው ተስፋን እንዲጨብጡ የሚያደርግ በጣም የሚወዱት የመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የትኛው ነው? ይጻፉና ተስፋው ለእርስዎ እንደሆነ ይቀበሉ ለክፍልዎ አባላትም ያካፍሉ። 4.በዚህ ሩብ ዓመት የተማሩትን እያንዳንዱን ትንሽም ቢሆን በአጭሩ አንድ አንቀጽ ይጻፉ። የትኞቹ ጥያቄዎች ናቸው መልስ ያገኙት? እስከ አሁን ያልተመለሱትስ? አሁንም በትልቁ በሚያስጨንቁን ነገሮች እርስ በእርስ ልንረዳዳ የምንችለው እንዴት ነው?