የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 12፣ ኢሳ. 48:20፣ ኢሳ. 36:6፣ 9፣ ኤር. 2:18፣ ዘፍ. 13፣ ዘፍ. 14፣ ዕብ. 7:1–10።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም፣ እሺ ብሎ ሄደ” ዘፍ. 11፡8)።
አ
ሁን በዘፍጥረት መጽሐፍ መኻከል ላይ ደርሰናል። ይህ አማካይ
ክፍል (ዘፍ. 12-22) እግዚአብሔር በመጀመሪያ (ለካ ለክሃ) “ሂድ”
(ዘፍ. 12፡1) ብሎ ጥሪ ካደረገለት ጊዜ አንስቶ ያለውን የአብርሃም ጉዞ
የሚሸፍን ሲሆን፤ ይህ ሁኔታ አብርሃም ያለፈ ማንነቱን ትቶ “ሂድ” ወደሚለው
የእግዚአብሔር ሁለተኛ ጥሪ እንዲማትርም አድርጎታል (ዘፍ. 22:2)።
ሁለተኛው ጥሪ የወደፊት ማንነቱን (በልጁ የሚኖረውን) እንዲተው የመራው
ነበር። በመሆኑም አብርሃም ሁል ጊዜ በጉዞ ላይ የነበረ፣ ሁል ጊዜ መጻተኛና
“በእንግድነት” (ዘፍ. 17፡8) የሚኖር ሰው ነበር።
የአብርሃም ጉዞ ያለፈ ማንነቱን ፉርሽ አድርጎ በባዶ ያስቀረ ሲሆን፣ የወደፊቱን
ደግሞ የማያየውና ወዴት እንኳ እንደሚሄድ የማያውቅበት ነበር። በእነዚህ
ሁለት የእምነት ጉዞ ጥሪዎች መካከል አብርሃም “‘አትፍራ’” (ዘፍ. 15፡1)
የሚል ድምፅ ሰማ። ይህን አምላካዊ ቃል በሦስት ክፍሎች ከፋፍለን ማለትም
በስድስተኛው፣ በሰባተኛው እና በስምንተኛው ሳምንት የምናጠናው ይሆናል።
አብርሃም የእምነት ምሳሌ ነው (ዘፍ. 15፡6)። እርሱ በዕብራውያን ቅዱሳት
መጻሕፍት የእምነት ሰው ሆኖ ይታወሳል (ነኽ. 9፡7-8)። በተጨማሪ በአዲስ
ኪዳን መጽሐፍት እንደምንመለከተው፣ አብርሃም በብሉይ ኪዳን ከተጠቀሱት
ስመ ጥር የእግዚአብሔር ሰዎች አንዱ ነው። በዚህ ሳምንት ጥናታችን ይህ
የሆነበትን ምክንያት እንመለከታለን።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 12፡1-9። አብራም አገሩን እና ቤተሰቡን ትቶ እንዲሄድ እግዚአብሔር ጥሪ ያደረገለት ለምንድን ነበር? የአብራም ምላሽ ምን ነበር?
እስከዚህ ጊዜ ድረስ፣ ቢያንስ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተዘገበው፣
እግዚአብሔር ለመጨረሻ ጊዜ የተነጋገረው ሰው ኖኅ ሲሆን፤ ይኸውም ከዚህ
በኋላ ሌላ ዓለማቀፋዊ ባህሪ ያለው የጥፋት ውሃ ፈጽሞ እንደማያመጣ ከሥጋ
ለባሽ ሁሉ ጋር ኪዳን የሚገባበትን (ዘፍ. 9፡15-17) ምልክት በሰጠበት ወቅት
ነበር። እግዚአብሔር አሁን “በምድር የሚኖሩ ሕዝቦች” በአብራም አማካይነት
ይባረካሉ ሲል ለአብራም የሰጠው አዲስ ቃል፣ “በምድር ላይ ባሉ” ከሚለው
ከቀደመ ኪዳን ጋር የተሳሰረ ነው።
ትንቢቱ ፍጻሜ ማግኘት የሚጀምረው ያለፈውን ወደ ኋላ ትቶ በመሄድ ነው።
አብራም ለእርሱ የቅርቡ የነበረውን ቤተሰብ፣ አገር አልፎ ተርፎም ከፊል
ማንነት ትቶ ወጣ። ለጉዳዩ ክብደት ስለ መሰጠቱ አመላካች የሆነው “ሂድ”
የሚለው ቁልፍ ቃል፣ በዚህ ዐውድ ለሰባት ጊዜ ያህል ተደጋግሞ ተጠቅሷል።
አብራም በመጀመሪያ አገሩን ማለትም “በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው
ከዑር”፣ ይኸውም ባቢሎን መውጣት ነበረበት (ዘፍ. 11፡31፣ ኢሳ. 13፡19)።
ይህ “ከባቢሎን እንዲወጣ” የቀረበለት ጥሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት ዘንድ
ረጅም ታሪክ አለው (ኢሳ. 48፡20፣ ራእ. 18፡4)።
የአብራም መሄድ በተጨማሪ ቤተሰቡን ይመለከታል። አብራም አብዛኛውን
ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን፣ የዕውቀት፣ የትምህርትና የተጽእኖ ቅርሶች ትቶ
መሄድ ነበረበት።
ሆኖም እግዚአብሔር እንዲሄድ ያቀረበለት ጥሪ ከዚህ የበለጡ ነገሮችንም
ይዟል። የዕብራይስጡ ሌክ ሌካ “ሂድ” ቃል በቃል ትርጉም “ብቻህን ሂድ”
ወይም “ራስህ ሂድ” ማለት ነው። አብራም ከባቢሎን የመውጣቱ ዓላማ
ከአካባቢው ወይም ከቤተሰቡም በላይ ነበር። ዕብራይስጥኛው ራሱ ለሚለው
ቃል አጽንኦት ይሰጣል። አብራም፣ የቀደመ ባቢሎናዊ ማንነት ከተላበሰ ያለፈ
እርሱነቱ ለማምለጥ፣ የኔ ያለውን ክፍል መተው ነበረበት።
የዚህ ትቶ የመሄዱ ግብ፣ እግዚአብሔር የሚያሳየው “ምድር” ይሆናል።
የየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የሚገነባበትን የሞሪያ ተራራ ለማመልከት (2ዜና 3፡
1) ተመሳሳይ ቋንቋ ይስሐቅ ለመሥዋዕት በሚቀርብበት ዐውድ (ዘፍ. 22፡
2) እንደገና ጥቅም ላይ ይውላል። አምላካዊው የተስፋ ቃል አንድ የተወሰነ
መልክአ ምድርን በመውረስ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን የመላውን ዓለም መዳን
ጭምር ያካተተ ነው። ይህ ጽንሰ ሀሳብ እግዚአብሔር የምድር ሕዝቦችን ሁሉ
እንደሚባርክ የሰጠውን የተስፋ ቃል በድጋሚ ያረጋገጠ ነበር (ዘፍ. 12፡2-3)።
የዕብራይስጡ በረካ--“መባረክ” የተሰኘ ግስ በዚህ ጥቅስ አምስት ጊዜ ቀርቧል።
ይህ ዩኒቨርስ አቀፍ በረከታዊ ሂደት በአብርሃም “ዘር” በኩል የሚሠራ ይሆናል
(ዘፍ. 22፡18፣ 26፡4፣ 28፡14)። እዚህ ላይ ጥቅሱ የሚያመለክተው በየሱስ
ክርስቶስ ፍጻሜ የሚያገኘውን “ዘር” ነው (ሐዋ. 3፡25)።
እግዚአብሔር ወደ ኋላ ምን ትተው እንዲሄዱ ጥሪ እያደረገልዎ
ነው? የእግዚአብሔርን ጥሪ በትኩረት ይሰሙ ዘንድ የትኛውን
የሕይወትዎ ክፍል መተው ይኖርቦታል?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 12፡10-20። አብራም የተስፋይቱን ምድር ትቶ ለምን ወደ ግብፅ ወረደ? ፈርዖን ከአብራም በተለየ መልካም ምግባር ያሳየው እንዴት ነበር?
የሚገርመው ነገር ወደ ተስፋይቱ ምድር ገና የደረሰው አብራም “በዚያ ምድር
ጽኑ ራብ ገብቶ” ስለነበር (ዘፍ. 12፡10) ወደ ግብፅ ለመሄድ ወሰነ። ሰዎች በረሃብ
ወቅት ከከነዓን ወደ ግብፅ ይጓዙ እንደ ነበር የሚያሳዩ በቂ የጥንት ግብፃውያን
የጽሑፍ ማስረጃዎች አሉ። በመካከለኛው መንግሥት ዘመን፣ ቅድመ ልደተ
ክርስቶስ (2060-1700) በግብፃውያን ሜሪካሬ አስተምህሮ መሠረት ከከነዓን
ይመጡ የነበሩ ሰዎች “ምስኪን እስያውያን” (አሙ)፣ “ችጋራሞች”… “የውሃ
እጥረት ያለባቸው”… “በአንድ ስፍራ ተረጋግተው የማይኖሩ”፣ “እግሮቻቸው
በምግብ ፍለጋ የቀጠኑ” በመባል ተገልጸዋል።—Miriam Lichtheim, Ancient Egyptian Literature, Volume I: The Old and Middle Kingdoms (Berkeley, CA: University of California Press, 1973), pp. 103,
104.
በግብፅ መፈተን የብዙዎቹ ጥንታውያን እስራኤላውያን ችግር ነበር (ዘኁ.
14፡3፣ ኤር. 2፡18)። በዚህ የተነሣ ግብፅ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ሳይሆን፣
በሰው ላይ የሚታመንበት ምሳሌ ለመሆን በቃች (2ነገሥ. 18፡21፣ ኢሳ.
36፡6)። ውሃ በየቀኑ ሲፈስ ለሚታይባት ምድረ ግብፅ እምነት አስፈላጊ
አልነበረም። ምክንያቱም የምድሪቱ ተስፋ ሰጭነት እዚያው ላይ የሚታይ
ነበር። እግዚአብሔር ለእርሱ የነገረው ነገር እንዳለ ሆኖ፣ ግብፅ በድርቅ
ከተጠቃው መልአከ ምድር አኳያ ስትታይ መልካም ስፍራ ትመስል ነበር።
አሁን ከነዓንን ትቶ የወጣው አብራም ዑርን ትቶ ከሄደው አብራም የተለየ
ነው። ቀደም ሲል አብራም ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ በመስጠት ዑርን ለቆ
የወጣ የእምነት ሰው ሆኖ ተስሎ ነበር። አሁን ግን አብራም በራሱ ፈቃድና
ውሳኔ የተስፋይቱን ምድር ለቆ ሲወጣ እንመለከታለን። ከዚህ በፊት አብራም
በእግዚአብሔር ይታመን ነበር። አሁን ግን የገዛ ልምዱን የሚከተል፣ ልቡ
የፈቀደውን የሚያደርግ፣ ለመርኅ የማይገዛና ነገሮችን ከግል ጉዳዩ አኳያ ብቻ
የሚመለከት የፖለቲከኛ ባህሪ እንመለከትበታለን። “አብርሃም ግብፅ ውስጥ
በቆየበት ወቅት ከሰው ልጅ ድክመት እና እንከን ነጻ አለመሆኑን አሳይቷል።
ሳራ ሚስቱ እንደሆነች እውነታውን በመሸሸግ በመለኮታዊው ጥበቃና ጥንቃቄ
ላይ ክህደት መፈጸሙ፤ በህይወቱ ግዙፍ የእምነት ጉድለትና የብርታት እጦት
ተምሳሌት ሆኖ ኖሮአል።”—(የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት፡ ገጽ 139)።
እዚህ ላይ በጌታ ፊት ታላቅ የተባለው ሰው እንኳ ሳይቀር እንዴት ስህተት
እንደሠራና፣ ይህም ሆኖ በፈጣሪ ያልተተወ መሆኑን እንመለከታለን። አዲስ
ኪዳን በጸጋ ስለሚገኝ ደኅንነት ምሳሌ አድርጎ አብርሃምን ያቀርባል። ከጸጋው
የተነሣ ባይሆን ኖሮ፣ አብርሃም እንደ ማንኛችንም ተስፋ ባልኖረው ነበር።
ከትክክለኛው መንገድ ማፈንገጥ--ታማኝ ለተባሉ ክርስቲያኖች
እንኳ ሳይቀር ምን ያህል ቀላል እንደሆነ አስመልክቶ ይህ ታሪክ
ምን ሊያስተምረን ይገባል? አለመታዘዝ ሁሌም ቢሆን መልካም
ምርጫ ያልሆነው ለምንድን ነው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 13፡1-8። ባህሪ ትልቅ ዋጋ ያለው ሰለመሆኑ ይህ ታሪክ ምን ያስተምረናል?
አብራም ወደ ግብፅ ያደረገው ጉዞ ተገቢ ያልነበረ ዙሪያ ጥምጥም ልፋት
ይመስል፣ እነሆ አሁን በፊት ወደ ነበረበት ተመለሰ። እግዚአብሔር ከአብራም
ጋር የነበረው ታሪክ፣ ወደ ተስፋይቱ ምድር ባደረገው የመጀመሪያ ጉዞ ከቆመበት
እንደገና ይጀምራል። አብራም በመጀመሪያ ያረፈው በቤቴል ሲሆን (ዘፍ. 12፡
3-6) ወደ ተስፋይቱ ምድር ባደረገው የመጀመሪያ ጉዞም ተመሳሳይ ሁኔታ
ተስተውሎ ነበር (ዘፍ. 13፡3)። አብራም ንስሐ ገብቶ ወደ “ራሱ” ተመልሷል፡
አብራም የእምነት ሰው!
አብራም ዳግም ከእግዚአብሔር ጋር የፈጠረው ግንኙነት ከሰዎች ጋር በነበረው
የዕለት ከዕለት መስተጋብር እንዲሁም ከመሬት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ
ከወንድሙ ልጅ ሎጥ ጋር የተፈጠረውን ችግር በፈታበት መንገድ የታየ ነበር።
የሰላም ስምምነቱን ሐሳብ ያመነጨውም ሆነ ሎጥ ያሻውን መልክአ ምድር
የራሱ አድርጎ በመጀመሪያ እንዲመርጥ (ዘፍ. 13፡9-10) የፈቀደው አብራም
መሆኑ፣ እርሱ ምን ያህል ለጋስና ደግ ሰው እንደ ነበር ያመለክታል።
ሎጥ የወደፊት ጎረቤቶቹ ክፋትና ርክስና (ዘፍ. 13፡13) ሳያሳስበው ምርጥ
የሆነውን የምድሪቱን ክፍል እና በቂ የውሃ ክምችት የያዘውን ረባዳ ስፍራ
(ዘፍ. 13፡10-11) ለራሱ የመምረጡ እውነታ፣ ስለ ስግብግብነቱ እና ስለ ባህሪው
የሚገልጸው ነገር አለ። ሎጥ “ለራሱ” መርጦ ስለ መውሰዱ የሚናገረው ሀረግ፣
“ለራሳቸው” (ዘፍ. 6፡2) ሚስት የመረጡትን ከጥፋት ውሃ አስቀድሞ የነበሩ
ሰዎችን ያስታውሰናል።
በአንጻሩ የአብራም እርምጃ እምነትን መሠረት ያደረገ ነበር። ምድሪቱ
በእግዚአብሔር ጸጋ ለእርሱ ተሰጠችው እንጂ እርሱ አልመረጠም ነበር።
ከሎጥ በተለየ መልኩ፣ አብራም ምድሪቱን የተመለከተው ከአምላካዊው
ትእዛዝ አኳያ ነው (ዘፍ. 13፡14)። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አብራም ከዑር
እንዲወጣ ጥሪ ከቀረበለት በኋላ እግዚአብሔር እንዳናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ
ሲዘገብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡ “ ‘ካለህበት ስፍራ ቀና ብለህ ወደ ሰሜንና
ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤ ዐይንህ የሚያየውን
ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ።’ ” (ዘፍ. 13፡14-15)።
ከዚያም አብራም በምድሪቱ ላይ “እንዲመላለስባት” እግዚአብሔር ግብዣ
አቀረበለት። “እንግዲህ ምድሪቱን ስለምሰጥህ ተነሣ፤ በርዝመቷም፣ በስፋቷም
ተመላለስባት።” (ዘፍ. 13፡17)።
ጌታ ግን፣ እርሱ ምድሪቱን ለአብራም እየሰጠው እንደነበር በግልጽ አሳይቷል።
ይህ ስጦታ ነው። አብራም ከእምነት ጋር አዋህዶ ሊይዘው የሚገባ የጸጋ ስጦታ
የሆነ ወደ መታዘዝ የሚመራ እምነት። እዚህ ላይ ጌታ ለአብራም የገባውን ቃል
አንድም ሳይቀር ወደ ተግባር የሚያመጣው የእግዚአብሔር ሥራ ብቻ ነው
(ዘፍ. 13፡14-17)።
ብዙዎች ለእኛ እንዳሰብነው ባይሆኑልንም እንኳ፣ ለሌሎች ደግ
እና ለጋስ መሆንን እንዴት መማር እንችላለን?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 14፡1-17። የተስፋይቱ ምድር በስጦታ ተሰጥታ ወዲያውኑ የዚህ ጦርነት መካሄድ አንደምታ ምንድን ነው? ይህ ታሪክ ስለ አብራም ምን ያስተምረናል?
ይህ በቅዱሳት መጻሕፍት የቀረበ የመጀመሪያው ጦርነት ነው (ዘፍ. 14፡2)።
ከሜሴፖታሚያ እና ፋርስ የተውጣጣ አራት ጥምር ግንባር ሰራዊት፣ ከሌላኛው
ማለትም የሶዶም እና ጎሞራ ነገሥታትን ጨምሮ (ዘፍ. 14፡8) የከነዓናውያን
አምስት ጥምር ግንባር ሰራዊት ጋር ውጊያ መደረጉ፣ በመሃላቸው የነበረው
ውዝግብ ከፍተኛ እንደ ነበር ይጠቁማል (ዘፍ. 14፡9)። የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ
ምክንያት ከነዓናውያን ሕዝቦች በባቢሎናውያን ዙዚማውያን ላይ ማመፃቸው
ነበር (ዘፍ. 14፡4-5)። ምንም እንኳ ይህ ዘገባ ስለ አንድ ታሪካዊ ግጭት
የሚናገር ቢሆንም፣ ይህ “ዓለማቀፋዊ” ባህሪ ያለው ጦርነት እግዚአብሔር
የተስፋይቱን ምድር ለአብራም ከሰጠ በኋላ ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ገቢራዊ
መሆኑ፣ ለዚህ ክስተት የተለየ መንፈሳዊ ትርጉም እንዲጠሰው ያደርጋል።
በጣም ብዙ ከነዓናውያን በውጊያው ተሳታፊ መሆናቸው፣ በግጭቱ ውስጥ
ያለው ጉዳይ የምድሪቱ ሉዐላዊ ገዢ መሆንን ይጠቁማል። የሚገርመው፣ ጉዳዩ
በትክክል የሚመለከተው አካል የአብራም ሠፈር ነበር። እርሱ ብቸኛና እውተኛ
የምድሪቱ ባለቤት ቢሆንም፣ ቢያንስ በመጀመሪያ አካባቢ፣ ከውዝግቡ ውጪ
የነበረ ብቸኛ ኃይል እርሱ ነበር።
አብራም የገለልተኝነት አቋም ያሳየበት ምክንያት እርሱ የተስፋይቱን ምድር
ያገኘው በሰራዊት ኃይል ወይም በፖለቲካ ስልታዊ ጥበብ ባለመሆኑ ነው።
የአብራም ግዛት የእግዚአብሔር ስጦታ ነበር። አብራም ወደ ጦርነት እንዲገባ
የተገደደበት ብቸኛ ምክንያት የወንድሙ ልጅ ሎጥ በምርኮ መወሰዱ ነበር
(ዘፍ. 14፡12-13)።
“በመምሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ በሰላም ይኖር የነበረው አብራም የጦርነቱን
ታሪክ እና በእህቱ ልጅ ላይ የደረሰበትን መአት አንድ ከምርኮ ያመለጠ ሰው
ይነግረዋል። ሎጥ ስላሳየው ምስጋና ቢስነት የታወሰው መልካም ያልሆነ ትዝታ
አልነበረም። በመሆኑም ለእርሱ የነበረው በጐ ስሜት ተነሳሳና እርሱን ማዳን
እንዳለበት ወሰነ። አብራም ከሁሉም በፊት ሰማያዊ ምክር በመፈለግ ለጦርነት
ተዘጋጀ።” (የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት፡ ገጽ 146)።
ይሁን እንጂ አብራም መላውን ጥምር ኃይል አልተጋፈጠም። ባካሄደው ፈጣን
የሌሊት ኮማንዶ ዘመቻ ሎጥን በምርኮ የያዘውን የጦር ሰፈር ብቻ አጠቃ።
ሎጥ ከምርኮ ነፃ ወጣ፣ የሶዶም ንጉሥም እንዲሁ። በዚህም ይህ ታማኝ
የእግዚአብሔር ሰው ታላቅ ድፍረትና ጥንካሬ ማሳየት ቻለ። ይህን ተከትሎ
በቀጠናው ተጽእኖው እየጨመረ ለመሄዱ፣ ሰዎች ምን ዓይነት ሰው እንደነበር
መመልከት እንደቻሉና እርሱ ስለሚያመልከው አምላክ የላቀ ትምህርት ሳያገኙ
እንዳልቀሩ ይታመናል።
ተግባራችን በሌሎች ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ አለው? ተግባራችን
እምነታችንን አስመልክቶ ምን ዓይነት መልእክት እያስተላለፈ
ይገኛል?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 14፡18-24፣ ዕብ. 7፡1-10። መልከ ጼዴቅ ማን ነበር? አብራም ለዚህ ከወዴት እንደመጣ እንኳ የማይታወቅ ለሚመስል ካኅን አሥራቱን የሰጠው ለምን ነበር?
ምስጢራዊው የመልከ ጼዴቅ ድንገተኛ ክስተት ከዐውድ ውጪ የሆነ ነገር
አልነበረም። አብራም በከነዓናውያን ነገሥታት ምስጋና ከቀረበለት በኋላ አሁን
ደግሞ እርሱ ለካህኑ ምስጋና ያቀርባል። አብራም አስራቱን በመመለስ የተገለጠ
ምስጋናውን ያቀርባል።
መልከ ጼዴቅ የመጣው ሳሌም ከተባለች ከተማ ሲሆን፣ ትርጓሜው “ሰላም”
ማለት ነው። ጦርነት ካስከተለው ውድመት በኋላ የተደመጠ ተስማሚ
መልእክት።
በመልከ ጼድቅ ስም ውስጥ የምናገኘው ጼዴቅ ማለትም “ጽድቅ” ከሶዶም
ንጉሥ ከበላ (ክፉው) እና ከጎሞራ ንጉሥ ብርሳ (“እርክስና”) በተቃራኒ
ቀርቧል። ምናልባት ስማቸው ግብራቸውን ሳይወክል አይቀርም (ዘፍ. 14፡2)።
መልከ ጼዴቅ ብቅ የሚለው በሌሎች ከነዓናውያን ነገሥታት የተወከለው
ዓመጽና ክፋት ከተሻረ በኋላ ነው። በተጨማሪ ይህ ክፍል “ካህን” (ዘፍ.
14፡18) ለተሰኘው ቃል የመጀመሪያውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻ ይዟል።
መልከ ጼዴቅ አብራም የራሱን አምላክ ከሚጠራበት (ዘፍ. 14፡22) ከ
“ልዑል እግዚአብሔር” (ዘፍ. 14፡18) ጋር ካለው ጉድኝት የተነሣ፣ አብራም
የሚያመልከው አምላክ ካህን አድርጎ እንደተመለከተው በግልጽ ይታያል።
ሆኖም መልከ ጼዴቅ ክርስቶስ እንደሆነ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። እርሱ
በዚያ ዘመን ሕዝብ መሃል የነበረ የእግዚአብሔር ተወካይ ነው--(see Ellen
G. White Comments, The SDA Bible Commentary, vol. 1, pp. 1092,
1093).
መልከ ጼዴቅ በእርግጥ የሰጠው መደበኛውን የካህን አገልግሎት ነበር።
እርሱ በ “እንጀራና የወይን ጠጅ” አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ
አሥራት የመመለስ ዐውድ (ዘዳ. 14፡23) ከአዲስ የወይን ጭማቂ ጋር (ዘዳ.
7፡13፣ 2ዜና 31፡5) ትስስር አለው። ከዚህ በተጨማሪ አብራምን ይባርከዋል
(ዘፍ. 14፡19)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ “ሰማይንና ምድርን ለሚገዛ” (ዘፍ. 14፡9 [1962
ትርጉም]) እና ፈጣሪ ለሆነው አምላክ በምላሹ “አብራም ካመጣው ሁሉ
አሥራትን ሰጠው” ((ዘፍ. 14፡20)። ይህ መጠሪያ ማዕረግ የፍጥረት ታሪክ
መግቢያን (ዘፍ. 1፡1) የሚያነሣ ሲሆን፣ “ሰማይንና ምድርን” የሚለው ሃረግ
ሙሉ በሙሉ ወይም “በሙሉ” የሚል ትርጉም አለው። በመሆኑም፣ አሥራት
የሁሉም ነገር ባለቤት ለሆነው ፈጣሪ አምላክ የምሥጋና መገለጫ እንደሆነ
ተደርጎ ይስተዋላል። (ጥቅሶቹን ያስተያዩ፡ ዕብ. 7፡2–6 እና ዘፍ. 28፡22)።
አሥራት አምልኮ የሚያቀርበው ወገን ለእግዚአብሔር እንደሚሰጠው ስጦታ
ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር እንደሚቀበለው ስጦታ አድርጎ ነው የሚያየው።
ምክንያቱም ሲጀመር እግዚአብሔር ሁሉንም በረከቶች ሰጥቶናል።
አሥራትን መመለስ ብርቱ የእምነት ማሳያ፣ ብሎም ታላቅ
እምነትን የመገንቢያ ድርጊት የሆነው ለምንድን ነው?
የሚከተለውን ጽሑፍ ያንብቡ፡ --“አብራም በከነዓን” ገጽ
142 – 159፡ የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት።
“የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በረከት የሚፈልቅባት ስፍራ ልትሆን ይገባል።
አባላቶቿ ሌሎችን ሲባርኩ እነርሱ ራሳቸው በረከት ይቀበላሉ። እግዚአብሔር
አንድን ሕዝብ በመላው ዓለም ፊት የመምረጡ ዓላማ እንደ ገዛ ወንዶች
እና ሴቶች ልጆቹ አድርጎ ሊቀበላቸው ብቻ ሳይሆን፤ በእነርሱ አማካይነት
የመለኮታዊውን ብርሃን ጥቅሞች ለዓለም ለመስጠት ጭምር ነው። ጌታ
አብርሃምን የመረጠው ለእግዚአብሔር የተለየ ወዳጅ እንዲሆን አልነበረም።
ይልቁንም ጌታ ለሕዝቦች ለመስጠት የተመኘውን የከበሩ እና በዓይነታቸው ልዩ
የሆኑ መብትና ጥቅሞች የሚያስተላልፍ መሣሪያ ይሆን ዘንድ ነው። ዙሪያው
በምግባረ ብልሹ ጽልመት ቢዋጥም፣ እርሱ ግን ብርሃን መሆን ነበረበት።
“እግዚአብሔር ልጆቹን በብርሃንና በእውነት የሚባርከው የዘላለማዊ ሕይወት
ስጦታ ባለቤት እንዲሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በዙሪያቸው ያሉ መንፈሳዊ ብርሃን
እንዲያገኙ ጭምር ነው… ‘እናንት የምድር ጨው ናችው’። እግዚአብሔር
ልጆቹን ጨው የሚያደርጋቸው ራሳቸው ተጠብቀው እንዲቆዩ ብቻ ሳይሆን፣
ሌሎችም ተጠብቀው በመኖራቸው ረገድ ወኪል እንዲሆኑ ጭምር ነው…
“እርስዎ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ሕያው ድንጋዮች እያንጸባረቁ ይገኛሉ?…
በእያንዳንዱ የዕለት ከዕለት ተግባር አዎንታዊ ተጽእኖ እስካላሳደረብን
ድረስ ትክክለኛ ኃይማኖት አለን ብለን መናገር አንችልም። በሕይወት
ዘመን እንቅስቃሴአችን የሚሸመን ተጨባጭ መልካምነት ሊኖረን ይገባል።
የሚለውጠው የክርስቶስ ጸጋ በልቦቻችን ሊኖር የግድ ነው። እኔነትን
ልናኮሰምን፣ ክርስቶስን ግን ልናገዘፍ ይገባናል፤፡”— Ellen G. White, Reflecting Christ, p. 205.
1.“ ‘እባርክሃለሁ… ለሌሎች በረከት ትሆናለህ’ ” (ዘፍ. 12፡
2)። መባረክ ማለት ምን ማለት ነው? እኛም እንደ አብራም ያንኑ
አምላክ የምናገለግል ሰዎች እንደመሆናችን፣ ለሌሎች በረከት
መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
2.አብርሃም ሚስቱን እህቴ ናት ብሎ በተናገረው ግማሽ ውሸት
ውስጥ የነበረው ችግር ምንድን ነው? የከፋው የቱ ነው--ሙሉ
በሙሉ ውሸት መናገር ወይስ ጥቂት እውነት መቀላቀል? ይህም
ሆኖ በቴክኒክ ደረጃ ሲታይ መዋሸት ነበር?
3.የሶዶም ንጉሥ ለአብራም ያቀረበለትን የድርድር ሀሳብ
የተመለከቱትን እነዚህን ጥቅሶች በድጋሚ ያንብቡ፡ ዘፍ. 14፡
21-23። እንዲህ ዓይነቱን ምላሽ ለምን ሰጠ? ከዚህ ታሪክ ምን
ጠቃሚ ትምህርት ማግኘት እንችላለን? ንጉሡ ያቀረበለትን
የድርድር ሀሳብ ለመቀበል ቢወስን ኖሮ አብራም ፍትሐዊ ሊሆን
የማይችለው ለምን ነበር?