የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 37፣ ማቴ. 20:26-27፣ ሐዋ. 7:9፣ ዘፍ. 38፣ ዘፍ. 39፣ ዘፍ. 40:1–41:36።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “እነርሱም እንዲህ ተበባሉ ‘ያ ሕልም ዐላሚ መጣ’ ” (ዘፍ. 37፡19)።
ዮ
ሴፍ በከነዓን ካየው የመጀመሪያው ሕልም (ዘፍ. 37፡1-11) አንስቶ
በግብፅ እስኪሞት (ዘፍ. 50፡26) ያለውን ታሪክ የሚሸፍነው
የዩሴፍ ታሪክ (ዘፍጥረት 37-50) የዘፍጥረት መጽሐፍን መጨረሻ
ክፍል ይሸፍናል። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ በዘፍጥረት መጽሐፍ ከተጠቀሰው
ማንኛውም የኃይማኖት አባት ታሪክ ይልቅ የዮሴፍ ታሪክ ሰፋ ያለ ቦታ ይዟል።
ምንም እንኳ ዮሴፍ ከያዕቆብ ልጆች አንዱ ቢሆንም፣ በዘፍጥረት መጽሐፍ
ከቀረቡ እንደ አብርሃም፣ ይስሐቅ እና ያዕቆብ ካሉ ታላላቅ የእምነት አባቶች
አኳያ ቀርቧል።
ወደፊት እንደምንመለከተው፣ የዮሴፍ ሕይወት ለሁለት ጠቃሚ ሥነ መለኮታዊ
እውነቶችን አጽንኦት ይሰጣል፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔር የገባውን ቃል
ይፈጽማል። ሁለተኛ፡ እግዚአብሔር ክፉን ወደ መልካም መለወጥ ይችላል።
በዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን በዮሴፍ የልጅነት ህይወት ዙሪያ
ትኩረት እናደርጋለን። ዮሴፍ የያዕቆብ ተወዳጅ ልጅ ሲሆን በሚገርም ሁኔታ
ባኣል ሃካሎሞት “ሕልም ዐላሚው” (ዘፍ. 37፡19) ወይም ቃል በቃል-የሕልሙ ጌታ የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶታል። ይህ ደግሞ ሕልምን አስመልክቶ
የተሰጠውን ጸጋ ያሳያል። ይህ ቅጽል ስም በእጅጉ ይስማማዋል፤ ምክንያቱም
ትንቢታዊ ሕልሞችን መቀበል፣ መረዳትና መተርጎም ብቻ ሳይሆን በሕይወቱ
ፍጻሜም ያገኛሉ።
የሰው ልብ በክፋትና እርክስና የተሞላ ቢሆንም እንኳ፣ አምላካዊው በቸርነት
የተሞላ መግቦት የተረጋገጠና የጸና መሆኑን በእነዚህ ምዕራፎች እንደ ገና
እንመለከታለን።
በመጨረሻም ያዕቆብ በምድሪቱ ላይ መኖር ጀመረ። ይስሐቅ “በስደት” ብቻ
የኖረ ሲሆን፣ ያዕቆብ ግን “በከነዓን ምድር ተቀመጠ” (ዘፍ. 37፡1 [1962
ትርጉም])። አዎ፣ በምድሪቱ ላይ መኖር ሲጀምር ችግሮች መከሰት የጀመሩ
ሲሆን፣ ችግሮቹ በቤተሰቡ ውስጥ የተከሰቱ ነበሩ። ይህ ውዝግብ ከመሬት
ወይም ከውኃ ጉድጓድ አጠቃቀም ጋር የተያያዘ አልነበረም፤ ይልቁንም
በዋነኛነት መንፈሳዊ ችግር ነበር።
ጥቅሱቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 37፡1-11። ዮሴፍ ወንድሞቹ ያን ያህል
እንዲጠሉት ያደረጋቸው ምን ዓይነት ቤተሰባዊ ግንኙነት ነው?
ገና ከመጀመሪያው፣ ያዕቆብ በስተ እርጅናው የወለደው ልጁ ዮሴፍ (ዘፍ. 37፡
3) ከአባቱ ጋር የተለየ ግንኙነት እንደነበረው እንመለከታለን። ከሌሎቹ ልጆቹ
ይልቅ “አብልጦ የሚወደው” (ዘፍ. 37፡4) እርሱን ነበር። እንዲያውም አልፎ
ተርፎ የልዑል ልብስ የሆነውን (2ሳሙ. 13፡18) “በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ
ጠባብ” (ዘፍ. 37፡3) አለበሰው። ይህ ደግሞ አባት፣ የራሔል የመጀመሪያ ወንድ
ልጅ የሆነውን ዮሴፍ፣ ልክ እንደ በኩር ልጅ ከፍ ከፍ የማድረግ ምስጢራዊ
ዕቅድ እንደነበረው ያሳያል።
መጪው ጊዜ የያዕቆብን ምኞት ያረጋግጣል ምክንያቱም ዮሴፍ በመጨረሻ
የበኩር ልጅ መብቶችን ይቀበላል (1ዜና፡ 5፡2)። ከዚህ አኳያ የዮሴፍ ወንድሞች
አብልጠው ቢጠሉትና በቅን አንደበት ሊያናግሩት ባይሹ፣ ብዙም የሚገርም
አይሆንም (ዘፍ. 37፡4)።
ከዚህ በተጨማሪ ዮሴፍ ወንድሞቹ የሚፈጽሙትን ማንኛውንም መጥፎ
ድርጊት ለአባቱ ይነግር ነበር (ዘፍ. 37፡2) (ዘፍ. 37፡2)። መቼም ሰብቀኛን
ማንም አይወደውም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከፍ ባለ ቦታ እንደሚያስቀምጠውና ወንድሞቹም
በፊቱ እንደሚሰግዱለት የሚጠቁመውን ሕልሙን ሲነግራቸው ወንድሞቹ
ይበልጥ ጠሉት። ሕልሞቹ ከአንዴም ሁለቴ በማያወላዳ ሁናቴ መቅረባቸው፣
እውነተኛ ትንቢታዊ ባህሪ መላበሳቸውን ያሳያል (ዘፍ. 41፡32)። ምንም እንኳ
ያዕቆብ ልጁን በግልጽ ቢገስጸውም (ዘፍ. 37፡10)፣ ክስተቱን በልቡናው ይዞ
ትርጉሙን እያሰላሰለ ፍጻሜውን ይጠብቅ ነበር (ዘፍ. 37፡11)። ምናልባት
እነዚህ ሕልሞች አንድ የሆነ ነገር ሊኖራቸው ይችላል ብሎ በልቡ ሳያስብ
አልቀረም። ምንም እንኳ በወቅቱ ትርጓሜውን ባይረዳም--ነገር ግን ትክክል
ነበር።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 20፡26-27። በዚህ ስፍራ የተገለጠው
ወሳኝ መርኅ ምንድን ነው? መርኁ የሚያስተምረንን ነገር
በሕይወታችን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ይህን ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ክስተቶች እጅግ ዘግናኝ ቢሆኑም፣ ለመረዳት
አስቸጋሪ አይደሉም። ከሚጠሉት ጋር ቀረቤታ ወይም ዝምድና ያሎት ከሆነ፣
ጥላቻው ብዙም ሳይቆይ ወይም ዘግየት ብሎ፣ ወደ ችግር ብቻ ማምራቱ
አይቀሬ ነው።
በዚህ ቤተሰብ መሃል የሆነውም ይኸው ነበር።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 37፡12-36። አደገኛ፣ ክፉ እና ዕቡይ
ልቦች ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ እና ማናችንንም ቢሆን ወዴት
ሊመሩን እንደሚችሉ አስመልክቶ ከዚህ ምን እንማራለን?
ዮሴፍን ወንድሞቹ የጠሉት እግዚአብሔር በሰጠው ሞገስ ቀንተው ስለነበር
ሲሆን (ሐዋ. 7፡9)፣ ይህ አምላካዊ ሞገስ በቀጣዩ ሂደት እያንዳንዱ እርምጃ
የሚረጋገጥ ይሆናል። ዮሴፍ በምድረ በዳ ሲባዝን አንድ ሰው ያገኘውና
ይመራዋል (ዘፍ. 37፡15)። የዮሴፍ ወንድሞች ሊገድሉት ሲያሴሩ ሮቤል
ጣልቃ ገብቶ በምትኩ ጉድጓድ ውስጥ እንዲጣል ሐሳብ አቀረበ (ዘፍ. 37፡
20–22)።
በዚህ ስፍራ የተገለጠውን የጥላቻ ዓይነት--በተለይ ደግሞ በገዛ የቤተሰብ
አባል ላይ፣ ለመገመት ይከብዳል። እነዚህ ወጣቶች ይህን ያህል ጭካኔ
የተሞላበት ድርጊት እንዴት ሊፈጽሙ ቻሉ? ውሳኔአቸው የገዛ አባታቸው ላይ
ሊያሳድር የሚችለውን ተጽእኖ ለአፍታ እንኳ ማሰብ አይችሉም? አባታቸው
ለዮሴፍ ማድላቱን ተከትሎ በእርሱ ላይ የቱንም ዓይነት ቅሬታ ሊኖራቸው
ቢችል እንኳ--ከልጆቹ በአንደኛው ላይ ይህን ማድረግ የለየለት ወራዳ ተግባር
ነው። ይህ፣ የሰው ልጆች ምን ያህል ክፉ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያሳይ ብርቱ
መግለጫ ነው።
“አንዳንዶቹ ግን በፈጸሙት ተግባር ምቾት አልተሰማቸውም። ከበቀል
ተግባራቸው እናገኘዋለን ብለው የጠበቁትን እርካታ አላገኙትም። ከጥቂት ጊዜ
በኋላ የተወሰኑ ነጋዴዎች ወደ እነርሱ ሲቃረቡ አዩ። እነርሱም የእስማኤላውያን
ነጋዴዎች ሲሆኑ ከዮርዳኖስ ባሻገር ወደ ግብፅ ለመውረድ ቅመማ ቅመም እና
ሌሎች ሸቀጦችን በግመል ጭነው ይዘው ይመጡ ነበር። ይሁዳ ወንድማቸውን
በዚያ እንዲሞት ከመተው ይልቅ ለእነዚህ ነጋዴዎች እንሽጥላቸው የሚል ሀሳብ
አቀረበ። ከሸጡት ከአጠገባቸው ሙሉ በሙሉ የሚገለል ሲሆን እነርሱም
ከደሙ ንጹህ ይሆናሉ።”--ኤለን ጂ. ኋይት፡ የኃይማኖ አባቶችና ነቢያት፤ ገጽ፡
235።
የግድያውን ዕቅድ አዘግይተው ወደ ጉድጓድ ከጣሉት በኋለ በንግድ ጉዞ ላይ
የነበሩ ነጋዴዎችን አዩ። በዚህ ጊዜ ይሁዳ ወንድማቸውን ለነጋዴዎቹ የመሸጥ
ዕቅድ አቀረበ (ዘፍ. 37፡26-27)። ዮሴፍ ለምድያማውያን ከተሸጠ በኋላ (ዘፍ.
37፡28)፣ እነርሱ ደግሞ በግብፅ ለሚገኝ ሰው የሸጡለት ሲሆን (ዘፍ. 37፡2627)፣ ይህም በክብር ለተሞላው የወደፊት ማንነቱ ላይ የተስፋ ጭላንጭል
የፈነጠቀ ነበር።
አጉል የሆነው ባህሪ አንድ ሰው አደርገዋለሁ ብሎ ፈጽሞ
አስቦ በማያውቀው ድርጊት የሆነ ጊዜ ከመገለጡ አስቀድሞ
መጥፎ ባሕርያትን ለመለወጥ አምላካዊውን ኃይል መሻት በጣም
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
በዚህ መሃል የምናገኘው የትዕማር ታሪክ ያለ ቦታው የተሰነቀረ አይደለም።
የዮሴፍን በግብፅ መሸጥ (ዘፍ. 38፡1) የሚዘክረውን የታሪክ ፍሰት ተከትሎ
የሚመጣው ይህ ክስተት፣ ይሁዳ ወንድሞቹን ተለይቶ ከመሄዱ ሐቅ ጋር
ስምሙ ሲሆን፤ ይህም ከእነርሱ ጋር አለመስማማት እንደነበረው ይጠቁማል።
ከዚህ በተጨማሪ ጥቅሱ በርካታ ቃላትና መርኅዎችን ከቀደመው ምዕራፍ ጋር
የሚጋራ ሲሆን፣ ክፉው ድርጊት ከደኅንነት ጋር ትስስር ወደሚኖረው መልካምና
አዎንታዊ ክስተት መለወጡ፣ ተመሳሳይ ሥነ መለኮታዊ አስተምህሮዎችን
እንደያዘ ያሳያል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. ምዕ. 38። የይሁዳን ባህሪ ከከነዓናዊቷ
ትዕማር ጋር ያወዳድሩ። ከሁለቱ ይበልጥ ጻድቅ የሆነው ማን
ነው? ለምን?
ይሁዳ ከነዓናዊት ሚስት ያገኘ ሲሆን (ዘፍ. 38፡2) ከእርሷ፡ ዔር፣ አውናን እና
ሴሎም የሚባሉ የዘር ሐረጉን ያረጋገጡለትን ሦስት ወንዶች ልጆች ወልዷል።
ሆኖም ዔር እና አውናን በሠሩት ዕኩይ ተግባር እግዚአብሔር ስለ ቀሰፋቸው፣
ይሁዳ ሦስተኛውን ልጁን ሴሎምን ለትዕማር ቃል ገባላት።
ሆኖም ከጊዜ በኋላ ይሁዳ የገባላትን ቃል የረሳ መሰለ። ሚስቱ በሞት
ከተለየችው በኋላ ራሱን ከሐዘን ለማጽናናት በሄደበት ወቅት፣ ትዕማር ያን
የገባላትን ቃል እንዲፈጽም ለማስገደድ የዝሙት አዳሪ ገጸ ባህሪ ለመጫወት
ወሰነች። ይሁዳ ማንነቷን ላልተገነዘበው ለዚህች ዝሙት አዳሪ የሚከፍላት
ገንዘብ ስላልነበረው ከመንጋው ፍየል እንደሚልክላት ቃል ገባ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለፍየሉ ክፍያ ዋስትና የሚሆን የማኅተም ቀለበቱን
ከነማሰሪያው እንዲሁም በትሩን ለጊዜው በመያዣነት እንዲሰጣት ጠየቀችው።
ይህን በዓይነቱ ልዩ የሆነ ግንኙነት ተከትሎ ትዕማር ታረግዛለች። ኋላ ላይ
አመነዘረች ተብላ በተከሰሰች ጊዜ ለከሳሹ ለይሁዳ የማኅተም ቀለበቱን
ከነማንጠልጠያውና በትሩ ታሳየዋለች። ይሁዳም እውነቱን በተረዳ ጊዜ
ይቅርታ ጠየቃት።
የዚህ አጸያፊ ታሪክ መደምደሚያው የፋሬስ መወለድ ሲሆን፣ ፋሬስ “ጥሶ
መውጣት” የሚል ፍቺ አለው። ልክ እንደ አያቱ ያዕቆብ እርሱም ሁለተኛ ሆኖ
ቢወለድም፣ ነገር ግን የበኩር ልጅ በመሆኑ በዳዊት የትውልድ ሀረግ (ሩት.
4፡18-22) ከዚያም አልፎ በየሱስ ክርስቶስ (ማቴ. 1፡3) የትውልድ መስመር
የደኅንነት ታሪክ ለመጠቀስ በቅቷል። ትዕማርን በተመለከተ ከእርሷ በኋላ
ለሚመጡት አራት ሴቶች--ረዓብ (ማቴ. 1፡5)፣ ሩት (ማቴ. 1፡5-6)፣ የኦርዮ
ሚስት (ማቴ. 1፡16) እና የየሱስ እናት ማሪያም--የመጀመሪያዋ ናት።
ከዚህ ታሪክ አንድ ትምህርት መውሰድ እንችላለን፡ እግዚአብሔር ትዕማርን
በጸጋው እንዳዳናትና ክፉውን ወደ መልካም እንደለወጠ ሁሉ በየሱስ መስቀል
ህዝቡን ያድናል። ዮሴፍን አስመልክቶ-- የዮሴፍን ችግር ለያዕቆብና ልጆቹ
መዳን ይለውጠዋል።
የትዕማር ታሪክ ጣልቃ መግባቱን ተከትሎ አሁን ወደ አቋረጥነው የዮሴፍ
ታሪክ እናመራለን። ዮሴፍ በዚህ ወቅት ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ ለሆነው
“የዘበኞች አለቃ” ባሪያ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል (ዘፍ. 40፡3-4፣ ዘፍ. 41፡
10–12)።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. ምዕ. 39። ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤት ኃላፊ
ሆኖ መሾሙን ስንመለከት፣ ለእንዲህ ያለው ስኬት ያበቁት
ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ዮሴፍ ወዲያውኑ ብሎ ለመናገር በሚያስደፍር መልኩ፣ ስኬታማ እንደሆነ
እንመለከታለን (ዘፍ. 39፡2-3)። ዮሴፍ በጣም ጥሩ ሰው ስለነበር ጲጥፋራ
“በቤቱ ላይ ሾመው” እንደውም ከዚያ አልፎ ተርፎ “ያለውን ሀብት ሁሉ
በኃላፊነት ሰጠው” (ዘፍ. 39፡4)።
ይሁን እንጂ፣ ዮሴፍ ስኬታማ መሆኑ እንዲታበይ አላደረገውም። የጲጥፋራ
ሚስት ዐይኗን ስለጣለችበት አብራው ለመተኛት ፈለገች። ዮሴፍ ግን “ይህን
ክፉ ድርጊት” በመፈጸም “በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት” (ዘፍ. 39፡9)
ከሚሠራ ይልቅ ሥራውን እና ደኀንነቱን ቢያጣ እንደሚመርጥ በማያሻማ
መልኩ ገለጸላት። በዮሴፍ እምቢተኛነት ውርደት የተሰማት ይህች ሴት፣ ዮሴፍ
አስገድዶ ሊተኛት መሞከሩን ለአገልጋዮቿና ለባሏ የሐሰት ክስ አቀረበችበት።
በዚህ ምክንያት ዮሴፍ እስር ቤት ተወረወረ።
እዚህ ላይ ዮሴፍ ያጋጠመው ነገር ሁላችንንም አጋጥሞን ያውቃል፡ ይህ ስሜት
በእግዚአብሔር የመተው ስሜት ነው! ሆኖም በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ እንኳ
“እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ” (ዘፍ. 39፡21)።
በመጨረሻ እግዚአብሔር በሰጠው ሞገስ የወህኒው አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች
ሁሉ አለቃ አደረገው። እዚህም ልክ እንደ ጌታው ቤት፣ እግዚአብሔር ዮሴፍን
ባረከው። በእርግጥ እርሱ ልዩ ተሰጥኦ ያለው ሰው ነው። ምንም እንኳ አሁን
የሚገኝበት ሁናቴ የከፋ ቢሆንም (ለነገሩ በፊትም ሆነ አሁን ያው ባሪያ
አይደል!?) ምርጥ የሆነውን ለማድረግ በተቻለው ይጥራል። ይሁን እንጂ
የቱንም ዓይነት ስጦታ ቢሰጠውም፣ በመጨረሻ ስኬታማ እንዲሆን ያደረገው
እግዚአብሔር አምላክ ብቻ እንደሆነ ጥቅሱ በግልጽ ያሳያል። “እግዚአብሔር
ከዮሴፍ ጋር ሆኖ ሥራውን ሁሉ ያሳካለት ስለነበር፣ የወህኒ ቤት አዛዡ በዮሴፍ
ኃላፊነት ስር ስላለው ሰለማንኛውም ጉዳይ ሐሳብ አይገባውም ነበር።” (ዘፍ.
39፡23)።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 39፡7-12። ዮሴፍ የጌታውን ሚስት
የምንዝር ግፊት እንዴት መቋቋም ቻለ? እርሷ የጠየቀችውን
መፈጸም በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት መሥራት እንደሆነ
የተናገረው ለምንድን ነው? ስለ ኃጢአት ባሕርይና ስለ ኃጢአት
ምንነት የነበረው አረዳድ ምን ያሳያል?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 40፡1-41፡36። የፈርዖን ሕልሞች ከመኮንኖቹ ሕልሞች ጋር እንዴት ይዛመዳሉ? የዚህ ዝምድና አንደምታ ምንድን ነው?
ሁናቴዎች አሁንም ቢሆን ሰናይ ገጽታ ይዘው መሄዳቸውን እንደቀጠሉ ነው።
ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ በእስረኞች ላይ በአለቅነት መሾሙን ተመልክተናል። በእስር
ቤት ከነበሩት መሃል ሁለቱ የፈርዖን የቀድሞ ሹሞች ነበሩ--የመጠጥ አሳላፊዎች
አለቃ እና የእንጀራ ቤት አዛዥ (ዘፍ. 41፡9-11)። ሁለቱም ሕልም አይተዋል፤
ነገር ግን የሚተረጉምላቸው ሰው በማጣታቸው ተክዘዋል (ዘፍ. 40፡8)።
ሆኖም በዚህ ወቅት ዮሴፍ የሁለቱንም ሕልም በየተራ ተረጎመላቸው።
እንደ ሁለቱ የፈርዖን ባለሟሎች ሁሉ ፈርዖንም ማንም ሊተረጉመው ያልቻለ
ሕልም ያያል (ዘፍ. 41፡1-8)። በዚህ ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ በአምላክ
ቸርነት ዮሴፍን ስላስታወሰው ጉዳዩን ለፈርዖን ነገረው (ዘፍ. 41፡9-13)።
እንደ ሁለቱ የፈርዖን ባለሟሎች ሁሉ፣ ፈርዖንም ባየው ሕልም ተረብሾ
የነበረ ሲሆን፣ እርሱም እነርሱ እንዳደረጉት ሕልሙን ለዮሴፍ ይነግረዋል
(ዘፍ. 41፡14-24) ዮሴፍም ይፈታለታል። ከባለሟሎቹ ሕልሞች በተመሳሳይ
የፈርዖን ሕልሞችም ተምሳሌታዊ ይዘት አላቸው፡ ሁለቱ ተያያዥነት ያላቸው
ሰባት ላሞች (የደለቡ እና ከሲታዎች) ልክ ተያያዥነት እንዳላቸው የእሸት
ዛላዎች (ፍሬአቸው የተንዠረገገ እና የቀጨጨ) ሁለት ተከታታይ ዓመታትን
የሚወክሉ ሲሆን፣ አንደኛው ሰናይ ሌላው ደግሞ ዕኩይ ናቸው። ሰባቱ ላሞች
እንደ ሰባቱ የእሸት ዛላዎች ሁሉ ተመሳሳይ መልእክት የያዙ ሲሆን፣ ይህም ልክ
እንደ ዮሴፍ ሕልሞች (ዘፍ. 41፡32 ያስተያዩ ዘፍ. 37፡9) ምንጫቸው መለኮት
መሆኑን ያሳያል።
ምንም እንኳ የፈርዖንን ሕልም የፈታው ዮሴፍ ቢሆንም፣ ነገር ግን እነዚህን
አምላክ ሊያደርጋቸው ያሉ ነገሮች (ዘፍ. 41፡25፣28) ለንጉሡ ያሳየው
እግዚአብሔር ኤሎሒም መሆኑን ዮሴፍ ለፈርዖን በእርግጠኝነት ያቀርብለታል።
ከሚከተለው የንጉሡ መግለጫ አኳያ ፈርዖን ምድሪቱን ከእርሱ በታች ሆኖ
የሚገዛ አንድ ሰው ለመሾም በወሰነበት ወቅት ይህን መልእክት ያገኘ ይመስላል።
“ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፣
አንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም። አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ
ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ
ብቻ ይሆናል’ ” (ዘፍ. 41፡39-40)። እንዴት ያስገርማል! ለእግዚአብሔር ምስጋና
ይግባውና ዮሴፍ በጲጥፋር ቤት ላይ ከነበረው ሹመት ወደ እስር ቤት አለቃነት፤
እነሆ አሁን ደግሞ ወደ መላው ግብፅ ግዛት ገዢነት ተሸጋገረ። ሁናቴዎች እጅግ
አስጨናቂ በሚመስሉበት ወቅት አምላካዊው ቸርነት ተገልጦ የታየበት እንዴት
ያለ ብርቱ ታሪክ ነው!
እግዚአብሔር ዝም ያለ በሚመስልበት ወቅት እንዴት በእርሱ
መታመንና የገባውን ቃል መጠበቅ እንዳለብን አስመልክቶ ከዚህ
ምን መማር እንችላለን?
ኤለን ጂ. ኋይት ፡ “ዮሴፍ
በግብፅ” ፡ ገጽ
237-247--የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት።
“ዮሴፍ እና ዳንኤል የወጣትነት ዕድሜያቸውን እያገባደዱ በነበረበት
በቀደመው የሕይወታቸው ምዕራፍ ከሞቀ ቤታቸው ተነጥለው በምርኮ ወደ
አረማዊ አገሮች ተወሰዱ። በተለይ ዮሴፍ በተትረፈረፈ ሐብት ሊያማልሉ
ለሚችሉ ፈተናዎች ተጋልጦ ነበር። በአባቱ ቤት በፍቅር የተወደደ ልጅ፣
በጲጥፋራ ቤት ደግሞ ባርያ፣ ከዚያም የቅርብ ወዳጅና የሥራ አጋር። ከሰዎች
ጋር መልካም ግንኙነት በመመሥረት የተካነ። በጥናት፣ በጥልቅ ምልከታ እና
ከሰዎች ጋር በነበረው ግንኙነት ራሱን ያስተማረ። በፈርዖን እስር ቤት የተጣለ፣
በግፍ የተወነጀለ፣ ጥፋተኛ አለመሆኑ የሚረጋገጥበት ወይም የመለቀቅ ተስፋ
ያልነበረው፣ ነገር ግን በታላቅ ቀውስ ወቅት አገሪቱን እንዲመራ ጥሪ የቀረበለት
ዮሴፍ--ንጽሕናውን ጠብቆ እንዲቆይ ያስቻለው ምንድን ነው? . . .
“ዮሴፍ በልጅነቱ እግዚአብሔርን መውደድንና መፍራትን ተምሯል። በአባቱ
ድንኳን ውስጥ ሆኖ፣ ምሽት ላይ በሶሪያ ከዋክብት ሥር፣ ከሰማይ ወደ ምድር
ስለ ተዘረጋው የቤቴሉ ራእይ መሰላል እና በላዩ ይወጡና ይወርዱ ስለነበሩ
መላእክት እንዲሁም በዙፋኑ ሆኖ ራሱን ለያዕቆብ ስለ ገለጠለት አምላክ
ተደጋግሞ ተነግሮታል። ከያቦቅ አጠገብ ተነስቶ ስለነበረው ግጭት ታሪክ
ሰምቷል። ያዕቆብ በደለኝነቱን ተገንዝቦ መተላለፉን ሲናዘዝ አሸናፊ እንደሆነና
የልዑል አምላክን ማዕረግ እንደ ተቀበለ ተነግሮታል።
“የአባቱን መንጋዎች የሚጠብቅ እረኛ የነበረው የዮሴፍ ንጹሕና ቀለል ያለ
የሕይወት ዘይቤ፣ አካላዊም ሆነ አእምሯዊ ማንነቱ እንዲዳብር ረድቶታል።
በተፈጥሮ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት በማድረግና ከአባት ወደ
ልጅ የሚፈሱትን የተቀደሱ ታላላቅ እውነቶች በማጥናት፣ የአእምሮ ጥንካሬን
አግኝቷል፣ ለመርኅ ጥብቅ መሆንንም ተምሯል።
“በሕይወቱ ላይ ብርቱ ቀውስ ተፈጥሮ፣ ከልጅነቱ አንስቶ ከኖረበት የከዓን
ቤቱ ተለይቶ በግብፅ ለሚጠብቀው ባርነት ባደረገው በዚያ ዘግናኝ ጉዞ
መሃል፣ ዮሴፍ የቤተሰቡን ድንኳን ወደ ሸሸጉት ኮረብቶች ለመጨረሻ ጊዜ
ዞር ብሎ በመመልከት የአባቱን አምላክ አስታወሰ። በልጅነቱ የተማራቸውን
ትምህርቶች በማስታወስ፣ ምንም ይሁን ምን እንደ ሰማይ ንጉሥ ልጅነቱ
ንጽህናውን ለማሳየት በሚያደርገው ውሳኔ ነፍሱ ሐሴት አደረገች።”—Ellen
G. White, Education, pp. 51, 52.
1.ዮሴፍን ከዳንኤል እና ከየሱስ ጋር ያነጻጽሩ። በአንድ የሚጋሯቸው
ነጥቦች ምንድን ናቸው? ዮሴፍ እና ዳንኤል የየሱስን ገጽታዎች
ያሳዩባቸውና የሱስ ምን እንደሚመስል በየራሳቸው የገለጹባቸው
መንገዶች ምን ይመስላሉ?
2.በሐሙስ ትምህርት መጨረሻ በተነሣው ጥያቄ ዙሪያ በክፍል
ውስጥ ተወያዩ። እንደ ዮሴፍ ሁሉ፣ ነገሮች መሆን እንዳለባቸው
መሆን የማይችሉ ሲመስሉ፣ በእግዚአብሔር መታመንን እንዴት
መማር እንችላለን?