| 11ኛ ትምህርት | ዮሴፍ የህልሞች አለቃ |
|---|
በወንድሞቹ የተጠላው ዮሴፍ
ሀ) ታላላቅ ወንድሞቹ ዮሴፍን የጠሉበት ምክንያት ምንድን ነበር? ዘፍ 37፡2-4ለ) የወንድሞች ጥላቻ እንዲጨምር ያረገው የትኛው የዮሴፍ ባህሪ ነው፡፡ዘፍ 37፡5
ሐ) ለምንድን ነው ዮሴፍ ህልሙን ለወንድሞቹና ለአባቱ ያካፋላቸው? ዘፍ 37፡6-11
መ) እንዴት ነበር የዮሴፍ ታላቅ ወንድሞች ለሱ ያላቸውን ጥላቻ የገለጹት? ዘፍ37፡12-27
ሠ) ከነሱ ውድቀት ምን እንማራለን?
ረ) በዚህ መጥፎ ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔርን ስራ የት ታዩታላችሁ? ዘፍ 37፡28,36(ሮሜ 8፤28)
የግብጽ ባርያ ዮሴፍ
ሀ) እንደባሪያ ሆኖ ወደግብጽ ከሔደ በኃላ እግዚአብሐየር ዮሴፍን እንዴት ነው የባረከው?ዘፍ 39፡1-6ለ) እግዚያብሔርን በማክበርና ጶጢፋርን በታማኝነት ሲያገለግል ዮሴፍ የገጠመው ትልቁ ፈተና ምን ነበር? ዘፍ 39፡6,7,10
ሐ) የጶጢፋን ሚስት ጾታዊ ትንኮሳ ስታደርስበት ከዮሴፍ መልስ ምን እንማራለን? ዘፍ39፡8-9,11-12
መ) የጶጢፋን ሚስት የውሸት ክስ ስታቀርብ ጶጢፋር ካሳየው ምን እንማራለን ? ዘፍ 39፡16-20
ሠ) ዮሴፍ በውሸት ክስ ተከሶ ወደ እስር ቤት ሲገባ ለምን እግዚአብሔር ጣልቃ አልገባም?
በሀሰት የተከሰሰው እስረኛው ዮሴፍ
ሀ) እንዴት ነው እግዚአብሔር ዮሴፍን በእስር ቤት ቆይታው ያከበረው ? ዘፍ 39፡21-23ለ) ዮሴፍ በእስር ቆይታው እግዘኢአብሔር የሰጠው መንፈሳዊ ስጦታ ምንድን ነው?ዘፍ 40፡7-8
ሐ) ዮሴፍ ጠጅ አሳላፊውን ምን ጠየቀው? ውጤቱስ ምን ነበር ዘፍ 40፡14-15,23
መ) ነፃ የምትወጡበት ጊዜ ተስፋ ባደረጋችሁበት ሰዓት ሳይመጣ የቀረበትን ጊዜ አካፋሉ። መዘግየቱ ምን ተፅዕኖ አለው?
የፈርኦን ህልሞች የፈታው ዮሴፍ
ሀ) እግዚሐብሔር እንዴት ነው የዮሴፋን ነፃ መውጣት ከግብፅ ጋር ያገናኘዉ?ዘፋ 47:1-8ለ) ለምንድን ነው ፈርኦን ህብራዊ እስረና ህልሙን እንዲፈታለት የጠራው ዘፍ41፡1-8
ሐ) ዮሴፍ ለፈርኦን ከመለሰለት ምላሽ እኛ ምን እንማራለን?
መ) ዮሴፍ ለፈርኦን ከሰጠው ምክር የቱ አስገረማችሁ? ዘፍ 41፡15-16,25,28
ሠ) ፈርኦን ሴፍን ለታላቅ አመራር እንዲመርጠው ምን አነሳሳው? ዘፍ 41፡37-41
ረ) ከዮሴፍ የህይወት ጉዞ እኛ ምን እንማራለን? ይህ የጥናት ጽሑፍ የተዘጋጀው በሆፕ ቻናል (https://www.hopetv.org/hopess/) ሲሆን ወደ አማርኛ የተተረጎመው ደግሞ በትንቢት ቃል የወንጌል አገልግሎት (https://www.youtube.com/user/YetnbitKalMinistry) ነው። እነዚህን የጥናት ጽሑፎች በእንግሊዝኛ https://www.hopetv.org/shows/hopess/study-guides/ ላይ ያገኛሉ።