የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ መዝ 23ን እና ሮሜ 12፡ 18-21ን ያንብቡ።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ነፍሴን መለሳት ፣ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ” (መዝ 23:3 )
ሶ
ፍያ በመኝታ ክፍሏ ግድግዳ ላይ ተደግፋ ወደ ታች ተንሸራተተች።
ድምጽ አሰምታ ልትጮህ ጥቂት ቀርቷት እምባ ከዓይኗ በፍጥነት
ይጎርፋል። እርሱ እንዴት? እርሱ እንዴት? ሶፍያ ልቧን የሚሰብር
ወሬ ሰምታለች። አንድ ጓደኛዬ ያለችው፣ያመነችውና የምታከብረው
ሰው የእርሷን ስምና ስራዋን የሚያጠለሽበትን ወሬ በፍጥነት እያዛመተ ነበር።
መጸሐፍ ቅዱሷን ከአልጋዋ ላይ በፍትነት ስትከፍተው ከዚህ በፊት የተለመደ
ጥቅስ ላይ አይኗ አረፈ። ‹‹ ነፍሴን መለሳት ስለ ስሙ በጽድቅ መንገድ መራኝ
በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ ክፉውን አልፈራም አንተ ከእኔ ጋር ነህና
በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል›› (መዝ23:3, 4).
“በእርግጥ ይህ ሊሆን አይችልም!”ሳታስበው በራሷ ላይ አምቧረቀች።
ነገር ግን ሁኔታው በቀላሉ የሚወጡት አይመስልም። በመዝሙር ላይ
ያለው እረኛ በጎቹን በጽድቅ መንገድ ፣ ነገር ግን ተመሳሳዩ መንገድ በጎቹን
ወደ ሞት ጥላ እየመራቸው ያለ ይመስላል። ነገር ግን ይህ የሚያሳምመው
በጓደኛ መካድ፤ ይህ ጨለማ የሆነው ሸለቆ፣እርሷን ለማሰልጠን እግዚአብሔር
ይጠቀመው ይሆን?
ሳምንቱን በአንድ ዕይታ ፡ በየትኛው ጊዜ ነው በመንፈሳዊነት
ያደግከው በቀላል ወይስ በአስቸጋሪ ጊዜ?
*የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሰኔ 25 ሰንበት ያጥኑ።
“እግዚአብሄር
እረኛዬ
ነው፣
የሚያሳጣኝም
የለም”
(መዝ 23:1).
አንዳንድ ህጻናት የእግዚአብሔርን ስዕል እንዲስሉ ተጠይቀው
እያንዳንዳቸው የልብ ቅርጽ ያለበትን ስዕል ስለዋል። ሁላቸውም በተመሳሳይ
መልኩ ያለ ምንም ልዩነት እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን እንዲገልጹ ተጠይቀው
የዚህን ያህል ቀላል መሆኑን ተናግረዋል።
ሁሉም ነገር ሰላም በሆነት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር መልካምነትና
ስለ እርሱ ዓላማ የተሻለ አመለካከት መያዝ ቀላል ነው። ነገር ግን እያደግን
ስንሄድ ህይወት ስትከብደንና ነገሮች ውስብስብ ስሆኑብን ስለ እግዚአብሄር
ያለን አመለካከት ይለወጣል። ሆኖም ግን እግዚአብሔር አልተለወጠም። (ዕብ
13:8 ያዕ 1:17) እኛ ግን እንለወጣለን።
በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነበረው የአርብቶ አደር አኗኗር የተነሳ ፣
መዝሙር 23 እግዚአብሄር ለእኛ የሚያደርገውን ጥንቃቄ ለመግለጽ የእረኛን
ምሳሌ ይጠቀማል። በሁለቱም በአዲስ ኪዳንና በብሉይ ኪዳን እረኛው
በምሳሌነት የሚያሳየው እግዚአብሔርን ነው። አርሱም በፍጹም የማይለወጥና
አስደናቂም ምሳሌ ነው ። መዘሙር 23ን ከማየታችን በፊት የተለያዩ ጸሐፊዎች
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እረኛ ስራ የጻፉትን እንፈትሽ።
ከሚከተሉት
ምንድነው?
ከእያንዳንዱ
ጥቅሶች
ስለ
እረኛ
የሚንማረው
ኢሳ. 40:11
ኤር 23:3, 4
ሕዝ 34:12
ዮሐ 10:14-16
1 ጴጥ 2:25
አሁን ወደ መዝሙር 23 እንሂድ። እረኛ ለበጎቹ የሚያደርገው ጥንቃቄ ምንድነው? መዝ 23:2
መዝ 23:3
መዝ 23:4
መዝ 23:5
መዝ 23:6
ለአንተ እንደዚህ የሚጠነቀቅልህ መኖሩን ማወቅ ምን
ማለት ነው? ይህንን የእግዚአብሔርን ማንነት በራሱ የተለያዩ
ችግሮች ውስጥ እየተሰቃየ ያለን ሰው ለማጽናናት የምትጠቀመው
እንዴት ነው?
“ስለ ስሙ ምክንያት በጽድቅ መንገድ መራኝ” (መዝ 23:3). አስቡት “በጽድቅ መንገድ” (መዝ 23:3)እዚያ በሩቅ በፊትህ ተዘርግቷል። መጨረሻውን ማየት አትችልም ነገር ግን የመንገዱ መጨረሻ ላይ ቤት አለ፣ ይኸውም የእግዚአብሄር ቤት። ወደ ራስህ በጥልቀት ስታየው መንገዱ ወዴት እንደሚወስድህ ታውቃለህ? አንዳንድ ቦታዎችን በግልጽ ማየት ትችላለህ፣ ነገር ግን ሌሎቹ ቦታዎች በብዙ አደገኛ እና ትልቅ መሰናክሎች ሙሉ በሙሉ ተሸፍኗል። አንዳንዴ ከተራራው ላይ ባለው ርቀት የተነሳ ይጠፋብሃል። አንዳንዶቹ መንገዶች ለመራመድ ቀላል ናቸው፣ሌሎች ግን ከባድ ናቸው። እስራኤላውያን ከግብጽ ወደ ተስፋይቱ ምድር የተጓዙት ልክ እንደዚህ ነበር፣ እናም በዚህ መዝሙር የተገለጸው በተመሳሳይ መንገድ ነው። ደዊት በመዝሙር 23 ውስጥ እረኛውን ወደ እግዚአብሔር ቤት እየሄደ በጽድቅ መንገድ ሲጓዝ ያያቸውን ቦታዎች ግለጽ።
ነገር ግን እነዚህ መንገዶች‹‹ የጽድቅ መንገዶች›› ወይም ‹‹ትክክለኛ
መንገዶች›› የተባሉት ለምንድነው?እዚህ አራት በጣም አስፈላጊ ነጥቦች
አሉ። አንደኛ፣ ወደ ትክክለኛው መዳረሻ ስለሚያደርሱ ትክክለኛ መንገድ
ናቸው ይኸውም፣ ወደ እረኛው ቤት። ሁለተኛ፤ ከትክክለኛው ሰው ጋር
ያለንን ግኑኝነት መግባባት ያለው ስለሚያደርጉ ትክክለኛው መንገዶች
ናቸው። ይኸውም ከእረኛው ከራሱ ጋር። ሶስተኛ ፤ እኛ ትክክለኛ ሰው
እንድንሆን ስለሚያሰለጥኑን ትክክለኛ መንገዶች ናቸው፣ እንደ እረኛው ።
አራተኛ፣ ትክክለኛውን ምስክርነት የሚሰጡ በመሆናቸው ትክክለኛ መንገዶች
ናቸው። ትክክለኛ ምስክር ስንሆን ትክክለኛ የእግዚአብሔር ህዝብ እንሆንና
ለእግዚአብሔር ክብርን እንሰጣለን። አካሄዱ ቢቀልም ቢከብድም መንገዶቹ‹‹
ጽድቅ›› ወይም ‹‹ትክክል›› ናቸው።
ማወቅ የሚገባን ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ሲመራን ጥያቄው ተራ
ግማሽ ነገርን ወደ ጉዞው መጨረሻ ስለማድረስ አይደለም። ከምሪትና ከለላ
ከመስጠት እጅጉን የላቀ ነው። በመጽሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ እንደሚገኙት
ብዙ ምሳሌዎች እግዚአብሄር ህዝቡን አይመራ እንደሆነ ወይም እንደ ተስፋ
ቃሉ አብረሃምን መምራት ይሁን ወይም እስራኤልን በእሳት አምድና በዳመና
መምራትም ቢሆን) እግዚአብሔር በሚመራበት ጊዜ፣ ሁልጊዜ የእርሱን ህዝብ
በጽድቅ መንገድ ስለ ማሰልጠን ነው።
እረኛው በአንተ ህይወት ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር
ጽድቅ እንደሆነ ምን ያህል ታስተውላላህ? ፈተናዎች በህይወትህ
የክርስቶስን ባህርይ እንድታሳይ ምን ያህል ይለውጡሃል?
“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉውን
አልፈራም። በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል። (መዝ 23፡
4) ”
የጽድቅ መንገዶች መተላለፊያ ሁልጊዜ በጥሩ ሳርና በሚፈስ ውኃ
የተሸፈነ ቢሆን እጅግ መልካም በሆነ ነበር። ነገር ግን ዳዊት የሳለው በዚህ
ዓይነት አይደለም። በዚህ መንገድ በተጨማሪ እና ልንጎበኘው የምንጓጓለት
ሥፍራ የሞት ሸለቆ ይገኝበታል። በዓመቱ የተለያዩ ጊዜያት በእስራኤል
ሀገር የሚገኙ ጥልቅ ቦታዎችና ሸለቆዎች ባልታሰበ ጎርፍ ይሞላሉ። ብርሐን
አያገኙም። እነዚህ ቦታዎች በባህሪያቸው ጠባብ በመሆናቸው በአጠገባቸው
በሚገኙ ከፍታ ቦታዎች ምክንያት የጸሐይ ብርሐን አያገኙም። ከዚህም የተነሳ
‹‹ የሞት ጥላ ›› ማለት በጣም ጥልቅ የሆነውን ጥላ ወይም ‹‹ጥልቅ ጨለማን››
ያመለክታል።
በራስህ‹‹ የሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ የሆንክበትን ጊዜ
አስተውስ›› ምን ይመስል ነበር ፤ ምንም እንኳ እረኛው በዚያ
የሚገኝ ቢሆንም ፈርተህ ነበር? በዚያን ጊዜ ለአንተ በጣም ውድ
የነበሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው ለምን?
እረኛው በሸለቆ ውስጥ ስለመገኘቱ ምን ያስባሉ? በጎቹ እዚያ
የሄዱት በራሳቸው ነው ብለው ያስባሉ? ወይስ እረኛው ራሱ በጎቹን በዚያ
መንገድ መራቸው ብለው ያምናሉ ? መልስዎን አሳማኝ ያድርጉ።
ኤልሳቤጥ እሎት የተባለች ጸሐፊ እንዲህ ብላለች “በሞት ጥላ
መካከል ራሱን ያገኘ ጠቦት ሊያስብ የሚችለው በስህተት መንገድ መመራቱን
ነው። ማሰብ ያለበት እዚያ የተገኘው ለመፍራት ሳይሆን ለመማር እንደሆነ
ነው። ምክንያቱም እረኛው ከእርሱ ጋር በመሆኑ ነው።››
በስህተት ወደ ‹‹ ሸለቆ›› ተመርተው እንደ ነበር አስበው
ያውቃሉ? በዚህ ጊዜ ለእግዚአብሔር ምን ዓይነት ምላሽ ሰጡ?
እረኛው እርሱን ማንም ሊያስተውለው በማይችልበት ሁኔታ
ውስጥ ወደ ሸለቆ ለመምራት ያስፈለገው ለምን ይመስሎታል?
“በጠላቶቼ ፊት ገበታን አዘጋጀህ ፣ ራሴን በዘይት ቀባህ
፤ ጽዋዬም የተትረፈረፈ ነው። መዝ 23 ፡5
በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ማንም ሊከለክለው በማይችል ሁኔታ ከሆኑ
ጠላቶች ጋር እንጋጫለን። ታዲያ ከእነዚህ ጠላቶች ጋር የምናሳልፈው እንዴት
ነው? በህይወትህ በሌሊት ነቅተህ እንቅልፍ እምቢ ብሎህ እየተገላበጥህ ፣
ሊጎዱህ እና ሥራህን ሊያበላሹ የሚፈልጉትን ለመበቀል አልመህ ታውቃለህ?
ለክርስቲያኖች ከጠላቶቻቸው ጋር እንዴት መኖር እንዳለባቸው ማወቅ ከባድ
ነገር ነው።
በህይወትዎ ምን ዓይነት ጠላት አለዎት? ሊጎዱዎት
የነበሩትን ጠላቶች እንዴት አዩአቸው፣ እርስዎን ይንከባከቡ
የነበሩትንስ? በማቴዎስ 5፡44 ፣ ወይም በሮሜ 12፡18-21
የተነገሩትን የክርስቶስን ቃላት እንዴት ተከተሉአቸው?
በመዝ 23፡5፣ ዳዊት ከጠላቶቻችን ጋር እንዴት መኖር እንዳለብን
ደስ የሚል መንገድን ያሳየናል። እግዚአብሔር በእርሱ ፋንታ የሚያደርጋቸውን
ነገሮች በማየት እነርሱ እንደሌሉ ያስባቸዋል። ከዚያም እግዚአብሔር ገበታን
ለእርሱ ያዘጋጃል።
ዳዊት በነበረበት ባህል ፣ አንድ የተከበረ እንግዳ ሰው ወደ ግብዣ
ተጠርቶ ወደ አንድ ሰው ቤት በሚሄድበት ጊዜ ግብዣውን ያዘጋጀው ሰው
ተጋባዡን ወደ ግብዣ አዳራሽ ከመግባቱ በፊት ራሱ ላይ ዘይት ይቀበዋል።
ዘይቱም የሽቶና የወይራ ዘይት ቅልቅል ነው። ከዚያም እንግዳው ከዚህ በፊት
በልቶት በማያውቀው ምግብ ፊት ይቀመጣል።
በመዝሙር 23፡5 ላይ ያሉ ሶስቱ ነገሮች (ገበታ፣
ዘይት እና ጽዋ) ምንም እንኳ እኛ ያለንበት ስፍራ ሸለቆ ቢሆንም
እግዚአብሔር ለእኛ የሚያስፈልገውን እንደሚያዘጋጅ የሚያሳዩን
እንዴት ነው?
ጳውሎስ እንደሚያሳስበን ‹‹ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለም
ከአለቆችና ከስልጣናትጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም
ሥፍራ ካለ ከጥፋት ሰራዊት ጋር ነው እንጂ።›› (ኤፌ 6፡12) ጠላቶቻችን
የሚታዩና የማይታዩ ናቸው። ወደድንም ጠላንም ተከበናል፡ ሆኖም ግን
ከእረኛው ጋር እስካለን ድረስ የሚታይም ሆነ የማይታይ አንድም ጠላት ቢሆን
እርሱ ለእኛ የሚያስፈልገውን አዘጋጅቷል።
እሰቲ እራስዎ በጠላት ተከበው ሳል እረኛዎ ለእርሰዎ
የተጠነቀቀው እንዴት እንደሆነ ይግለጹ። በነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት
ከተደረገልዎ ነገር የተነሳ እግዚአብሔርን ለማመስገን የሚሆን ምን
ነገር አገኙ?
“ቸርነትህና ምህረትህ በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፣ በእግዚአብሔር ቤትም ለዘላላም እኖራለሁ” (መዝ 23:6 ):: በጠላቶች በምንከበብበት ጊዜ ወይም በሸለቆ በምንሆንበት ጊዜ ለብቻችን እንደተተውን ለማሰብ እንፈተናለን። እግዚአብሔር ለእኛ እየሰራ እንደሆን እያወቅን አንኳ ሲጀመር እርሱ ካለ ለምን ወደዚህ መራን እንላለን። በእርግጥ ግን እግዚአብሔር ነገሮችን የሚያየው እንዲህ አይደለም። ዳዊት በመዝ 23 ፡6 ላይ ችግሮች ቢኖሩም እርግጠኛ የሆነባቸው ሁለት ነገሮች ምንድናቸው? (ኤፌ 1:4; 2 ጴጥ 1:10;እብ 11:13-15ን ይመልከቱ)
አንዳንድ ትርጉሞች ቸርነትህና ፍቅርህ (የእግዚአብሔር የጸናው ፍቅር )
በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል ይላሉ። ሆኖም ግን በዚህ ስፍራ ሊገለጽ
የተሞከረው ጥንታዊው ግስ ጠንከር ያለ ነው። ጥቅሱም ቸርነትህና ፍቅርህ
በህይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል ። (በእርግጥ ይህ ግስ በዘፍ 14፡14 ፣ ኢያ
10፡19 እና 1ሳሙ 25፡29 ለይ መከተል የሚለው ግስ ጥቅም ላይ በዋለባቸው
ቦታዎች የበለጠ ግልጽ ሆኗል።
እስቲ እናስብበት የእግዚአብሔር ቸርነትና ፍቅር ሲከተለን
ምን ዓይነት ስዕል ነው በአእምሮአችን የሚመጣው ? ዳዊት በዚህ
ሁኔታ እግዚአብሔር ስለ እኛ የሚያደርገውን ጥንቃቄ ሲናገር ምን
ማለት ፈልጎ ይመስሎታል?
የሸለቆው ጥልቀት ወይም ያልተቋረጠ የጠላት ሴራ ቢኖርም
የእግዚአብሔር ቸርነትና ፍቅር እና የእርሱ እርግጠኛ የሆነ ጥንቃቄ ምንም
ጥያቄ የለውም። ይህ ክርስቶስን መስቀሉ ላይ በጽናት እንዲቆም ካደረገው
እኛም ልብ ልንለው ይገባናል።
ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ እኛ ጥንቃቄ የምናደርግላቸው ሰዎች
በጥያቄ የሚሞሉበት ጊዜ አለ። እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎችን መመለስ
የምንችለው የስነ-መለኮት ትምህርት ዕውቀታችንን በመጠቀም እግዚአብሔር
ምን ማድረግ እንደሚችል በመግለጽ አይደለም። ይልቁንም ዳዊት በመዝ
23 ፡6 እንደሚያመለክተው ስለ እግዚአብሔር እውነት ያለንን የራሳችንን
የማያወላውል እምነት ለሌሎች በማካፈል መሆን አለበት።
የእግዚአብሔር ቸርነትና ዘላለማዊ ፍቅሩ እየተከተለዎት
ስለመሆኑ የሚያሳይ
እግዚአሔርን በማወቅ ላይ መሰረት
ያደረገ ምን የግል ተሞክሮ ማስረጃ አለዎት? ከመጽሐፍ ቅዱስ
የሚጨምሩት ሌላ ማስረጃ አለ? ይህንን ስለ እግዚአብሔር
ጥንቃቄ እርግጠኝነት ጥያቄ ለሚያነሱ ሰዎች ለማስረዳት እንዴት
መጠቀም ይችላሉ? መስቀል የእግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር
የሚከተለን ስለመሆኑ ማሳያ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው?
የኤሌን ዋይት፡‹‹ሚሽነሪ ኢን ዘ ሆም›› የቤተክርስቲያን
ምክሮች ጥራዝ 4 ገጽ143፣ አባቶችና ነብያት በሚለው መጽሐፍ ‹‹መለኮታዊ
እረኛ›› ገጽ. 476-484 እና በዘመናት ምኞት እንዲህ ትላለች።
“እነዚያ በስተመጨረሻ ድል የሚያደርጉ በክርስትና ህይወታቸው
ችግርና መከራ ስቃይ የሚሆንባቸው ጊዜ አለ፣ ነገር ግን እነርሱ በእግዚአብሔር
ላይ ያላቸውን መተማመን አይጥሉትም፣ ምክንያቱም ያላስፈላጊ የሆኑ
ነገሮችን ሁሉ ለማስወገድ በክርስቶስ ትምህርት ቤት ይህ አስፈላጊ በመሆኑና
የህይወታቸው መመሪያ ስለሆነ ነው። የእግዚአብሔር ተከታይ በመንገዱ ላይ
የሚያጋጥመውን የጠላትን ጥቃትና ሀዘን የሚያስከትሉ ስድቦች እንዲሁም
መሰናክሎቹን ለማሸነፍ ድፍረትና የአእምሮ ዝግጅት ያስፈልገዋል።
“ነገር ግን በአጠገብህ ያለውን ችግር ለማየት ዝቅ ማለትን ትተህ
፣ወደ ላይ ብትመለከት ተስፋ ሳትቆርጥ በቶሎ ሊረዳህ ወደ አንተ የተዘረጋውን
የክርስቶስን እጅ ታያለህ እናም እንዲረዳህ በድፍረት ወደ እርሱ እጅህን
በመዘርጋት እንዲመራህ ፍቀድ። ባመንከው ልክ ባለ ተስፋ ትሆናለህ።
“ጠንካራና ጥሩ የሆነ ከክርስቶስ ጋር በፍጹም የሚመሳሰል ባህሪይ
ለመለማመድ ከክርስቶስ እርዳታ እናገኛለን። ከእንደዚህ ዓይነት ባህሪይ
በሚፈልቀው ብርሃን ላይ ሰይጣን ምንም ተጽዕኖ ሊያመጣ አይችልም.
. . እግዚአብሔር እኛን ከፍ ለማድረግ፣በጣም ጠቃሚዎች እና ብቁዎች
እንድንሆን፣ በመንግስቱ ቤት እንዲኖረን፣ የእርሱን ፍጹም የሆነውን ባህሪይ
በእኛ ላይ በማስቀመጥና የእርሱን በጣም ጥሩ የሆነውን ሥጦታ ብቸኛውን
ልጁን በመስጠት አሳይቶናል።
መልዕክት ለወጣቶች ገጽ 63፣ 64.
1. በህይወትዎ መንገድ ላይ የሚያጋጥሙ ‹‹ችግሮች ፈተናዎች
መከራዎች ‹‹በክርስቶስ ትምህርት ቤት ገዥ መመሪያዎች
መሆናቸውን ምን ያህል አስተውለዋል?
2. የእኛ እርዳታ፣ ማበረታታትና፣ ማጽናናት በሸለቆ ላሉት
ክርስቶስ ባደርገው መልኩ በመከራ ውስጥ የሚገኙትን መድረሻ
መንገድ የሚሆነው እንዴት ነው? በችግር ውስጥ ያሉትን ለመርዳት
የበለጠ ዝግጁ ለመሆን ሌላ ምን ማድረግ ይችላሉ?
3.በክፍል ውስጥ በመዘዋወር የእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት
እንዴት እንደተከተለዎት
ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለዎትን
ልምምድ ይነጋገሩ። አንዱ ከሌላው ልምምድ ምን ይማራል?
4. ክርስቶስ ወደ ፈተና የገባበትን የመጨረሻ ሰዓት ያስቡ።
ክርስቶስ በሰውነቱ ይህን መከራ እንዴት እንደተቋቋመ ከመጽሐፍ
ቅዱስም ሆነ ከኤለን ጂ ዋይት ጽሁፎች በመጥቀስ ተናገሩ። እኛ
የሚያጋጥመንን ፈተና ለመመከት ከዚህ ምን ትምህርት ማግኘት
እንችላለን?