
ለዚህ ሳምንት ጥናት፡- ዕብ. 2፡3-4፣ 1 ጴጥ. 4፡14-16፣ ዕብ. 13፡1-9፣13፣ 1 ነገ. 19፡1-18፤ ዕብ. 3፡12-14፤ ዘሁልቅ 13ን ያንብቡ
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።” (ዕብ. 10፡36)
ኢ
የሱስን ወይም ከደቀመዛሙርቱ አንዱ ሲሰብክ መስማትን
በምናባችሁ አስባችሁት ታውቃላችሁ? የተጻፉ ጥቂት ኃሳቦችና
የስብከቶቻቸው ጠቅለል ያሉ ኃሳቦች አሉን፤ ነገር ግን እነዚህ
እነርሱን በአካል የመስማትን ጥቂት ምስል ብቻ ያሳዩናል። እግዚአብሔር ግን
አንድ ሙሉ ስብከትን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስቀመጠልን፡- የጳውሎስ
መልዕክት ለዕብራውያን ሰዎችን።
የዕብራውያን መልዕክት ጸሀፊ የሆነው ጳውሎስ መልዕክቱን “የምክር ቃል”
(ዕብ. 13፡22) ብሎ ይጠራዋል። እንዲህ አይነት አገላለጽ በቤተ መቅደስ
(የሐዋ. ሥራ 13፡15) እና በክርስትያን አምልኮ (1 ጢሞ. 4፡13) ውስጥ ጥቅም
ላይ ይውል ነበር። ስለዚህ የዕብራውያን መልዕክት በእጃችን ያለ ጥንታዊ
ሙሉ የክርስትያን መልዕክት ነው ተብሎ ይታመናል። የዕብራውያን መልዕክት
መጀመሪያ በየሱስ ላመኑና በኋላ ተግዳሮት ለገጠማቸው የተጻፈ መልዕክት
ነው። አንዳንዶች በህዝብ ፊት ይወገዙና ይሰደዱ ነበር (ዕብ. 10፡32-34) ።
ሌሎቹ ደግሞ የገንዘብ ችግር ነበረባቸው (ዕብ. 13፡5-6) ። ብዙዎቹ ደግሞ
ደክመው እምነታቸውን መጠራጠር ጀምረው ነበር(ዕብ. 3፡12-13)። ዛሬ ከእኛ
እንደነርሱ የሆንን አለን?
ሆኖም ሐዋርያው በሚያነቃቃ መልዕክቱ ኢየሱስን በማመን እንዲጸኑ አሁን
በሰማያዊው ቤተ መቅደስ ባለው በእርሱ ላይ አይናቸውን እንዲያደርጉ
ተገዳደራቸው (ለእኛም እንደዚያው) ።
ለታህሳስ 23 ሰንበት ለመዘጋጀት የዚህን ሳምንት ትምህርት ያጥኑ።
መልዕክቱን ተረድተን በህይወታችን ተግባራዊ ለማድረግ መልዕክቱን ከሐዋርያው ሲቀበሉ ሕዝቡ የነበሩበት ሁኔታና ታሪካቸውን መረዳት ያስፈልጋል። ዕብራውያን 2፡3-4ን ያንብቡ። የዕብራውያን ሰዎች መጀመሪያ ሲያምኑና ሲለወጡ ምን አይነት ልምምድ ነበራቸው?
ምዕራፉ የዕብራውያን ተደራሾች(አንባቢያን) ኢየሱስ ራሱ ሲሰብክ
እንዳልሰሙት የሚያሳይ ሲሆን ወንጌሉን (የመዳኑን ዜና) የሰሙት ከሌሎች
ወንጌላውያን ነበር።
ጳውሎስን ጨምሮ ወንጌላውያኑ መልዕክቱን እንዳረጋገጡላቸውና
እግዚአብሔር ራሱ “በድንቅና ተዓምራት” ምስክሩን እንዳጸና ተናግሯል።
ይህም ማለት እግዚአብሔር ወንጌሉን በተግባር በሚገልጽ መልኩ በድንቅና
በተዓምራት “የመንፈስ ቅዱስ” ስጦታዎችንም በመስጠት አጽንቶላቸዋል
ማለት ነው። አዲስ ኪዳን በአዳዲስ ቦታዎች ወንጌል ሲሰበክ ተዓምራዊ
ፈውሶች፤ከአጋንንት ነጻ መውጣቶች እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች መፍሰስ
አይነት ምልክቶች ይፈጸሙ እንደነበረ ይገጻል
።
በቤተክርስትያን ታሪክ መጀመሪያ ላይ እግዚአብሔር መንፈሱን በኢየሩሳሌም
በነበሩት ሐዋርያት ላይ አፍስሶ ቀደም ብለው በማያውቁት ቋንቋ ወንጌሉን
መናገርና ተዓምራት ማድረግ ችለዋል (ሐዋ. ሥራ 2፡3) ።ፊሊጶስ ተመሳሳይ
ተዓምራትን በሰማሪያ (ሐዋ. ሥራ 8) ፤ጴጥሮስ ደግሞ በኢዮጴና በቄሳሪያ
(ሐዋ. ሥራ 9፤10) እንዲሁም ጳውሎስ ደግሞ በኤዥያ ማይነርና በአውሮፓ
ሲያገለግል በተዓምራት የታጀበ የወንጌል ሥራ ነበር (የሐዋ. ሥራ 13-28)
። እነዚህ በኃይል የተሞሉ ክስተቶች የድነትን መልዕክት፤የእግዚአብሔር
መንግስት መመስረትንና ከክፉ ኃይላት ነጻ መውጣትን በተግባራዊ ማስረሻ
ያረጋገጡ ነበሩ (ዕብ 12፡25-29)
።
ቀደምት ክርስትያን አማኞች ኃጢአቶቻቸው ይቅር እንደተባለላቸው መንፈስ
ቅዱስ ማረጋገጫ ሰጣቸው። ስለዚህ ፍርድን አይፈሩም ነበር በውጤቱም
ጸሎቶቻቸው ቀጥተኛና በመተማመን የተሞሉ የዕምነት ልምምዶቻቸውም
አስደሳች ነበሩ (ሐዋ. ሥራ 2፡37-47) ። መንፈስ ቅዱስ በክፉው ኃይላት
ባርነት ውስጥ የነበሩትን ነጻ ማውጣቱ የእግዚአብሔር ኃይል ከክፉው ኃይላት
በላይ እንደሆነና በህይወታቸው የእግዚአብሔር መንግስት እንደተቋቋመ
አሳማኝ ማስረጃን ይሰጣል
።
የእርስዎ የለውጥ ታሪክ ምድነው? ኢየሱስ ክርስቶስ የግል
አዳኝዎና ጌታዎ ለመሆኑ ምን ማረጋገጫን አገኙ? ጌታ እርስዎን
ወደ እርሱ ለማምጣት በመጀመሪያ የሠራውን ማስታወስ ለምን
ይጠቅማል?
አማኞች በክርስቶስ ላይ ማመናቸውን ገልጸው ቤተክርስትያንን ሲቀላቀሉ ከሌላው ማህበረሰብ የሚለያቸውን ድንበር አስቀምጠዋል። እንዳለመታደል ሆኖ ይህ የግጭት ምክንያት ሆነ ምክንያቱም በዙሪያቸው በነበሩት ማህበረሰቦችና በእሴቶቻቸው ላይ አሉታዊ መልዕክትን በግልጽ ስለሚያስተላልፉ ነው። ዕብ.10፡32-34ንና ዕብ.13፡3ን ያንብቡ።ዕብራውያኑ ተደራሾች ከተለወጡ በኋላ የነበራቸው ልምምድ ምን ይመስል ነበር?
ዕብራውያኑ በተቃዋሚዎቻቸው በተነሱባቸው አመጾች ምክንያት አካላዊና
መንፈሳዊ ቁስለት ሊገጥማቸው እንደሚችል ይገመታል (የሐዋ. ሥራ 16፡
19-22፣ የሐዋ. ሥራ 17፡1-9)።ታስረዋል እንዲሁም ተገርፈውም ይሆናል
ምክንያቱም በዚያ ዘመን የነበሩ ባስልጣናት ገና ማስረጃ እየሰበሰቡ እንኳን
ትክክለኛውን የፍርድ ሂደት ሳይከተሉ ግርፋትንና ቅጣትን የማዘዝ ስልጣን
ስለነበራቸው ነው(የሐዋ.ሥራ 16፡22-23)
።
ዕብራውያን 11፡24-26ንና 1ጴጥ 4፡14-16ን ያንብቡ። የሙሴና
የ1ኛ ጴጥሮስ መልዕክት ተደራሾች ልምምዶች ክርስትያን አማኞች
የሚሰደዱበትን ምክንያት እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው?
“የክርስቶስን ስድብ መሸከም” ራስን ከክርስቶስ ጋር መቁጠርና ይህ ውሳኔ
የሚያመጣውን ኃፍረትና መገፋት መቋቋም ማለት ነው። በክርስትያኖች ላይ
የነበረው ጥላቻ ልዩ በሆኑት ሃይማኖታዊ አቋሞቻቸው ምክንያት የመጡ ነበሩ።
ሰዎች ለነርሱ በማይገቧቸው ሃይማኖታዊ ልምምዶች ወይም አኗኗራቸው
ሌሎች ሰዎች የአእምሮ ወቀሳና ኃፍረት እንዲሰማቸው በሚያደርጉ ሰዎች
አማካኝነት ሊበሳጩ ይችላሉ። በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ
ይኖር የነበረው ታሲተስ ክርስትያኖች “የሰውን ልጅ በመጥላት” ጥፋተኞች
እንደሆኑ ያምን ነበር።
Alfred J. Church and William J. Brodribb, trans.,
The Complete Works of Tacitus, (New York: The Modern Library,
1942) Annals 15.44.1። ታሲተስ የተናገረው ስህተት ቢሆንም እንዲህም
ለማለት ያስደፈረው ምንም አይነት ምክንያት ቢኖርም ጳውሎስ ይህንን
መልዕክት የጻፈላቸው ቀደምት ክርስትያኖችና መሰሎቻቸው በዕምነታቸው
ምክንያት በስቃይ ውስጥ እያለፉ ነበር።
ሁሉም ሰው ክርስትያን ሆነ አልሆነ በችግር ውስጥ ያልፋል።
ታዲያ ስለ ክርስቶስ መሰቃየት ማለት ምን ማለት ነው? የትኞቹ
ችግሮች ናቸው ስለ ክርስቶስ ብለን የገባንባቸው? በምርጫዎቻችን
ምክንያት የመጡትስ ምን ያክሎቹ ይሆኑ?
የዕብራውያን መልዕክት ተቀባዮች በስቃይና በመገፋት ውስጥ እያለፉ በክርስቶስ ላይ በነበራቸው ዕምነትና ቁርጠኝነት ስኬታማ ነበሩ። ያ ትግል ከረዥም ርቀት በኋላ ሽልማቱን አገኘ። መልካም ገድልን ተጋድለው ቢደክሙም ባለድል ሆነው ወጡ። ዕብ. 2፡18ን፤ዕብ. 3፡12-13ን፤ዕብ. 4፡15ን፤ዕብ.10፡ 25ን፤ዕብ.12፡3፤12-13ንና ዕብ.13፡1-9፤13ን ያንብቡ። አማኞች ይጋፈጧቸው የነበሩት ተግዳሮቶች ምን ምን ነበሩ?
የዕብራውያን መጸሐፍ እንደሚነግረን አንባቢያን ችግሮችን መጋፈጣቸውን ቀጥለዋል።የቃላትና ምናልባትም ሌሎች አይነቶች ክብራቸውን የሚነኩ ጥቃቶች ቀጥለዋል(ዕብ.13፡13)። አንዳንድ አማኞች ያኔም በእስር ቤት ውስጥ ነበሩ(ዕብ.13፡3) ይህም ቤተክርስቲያኒቱን በገንዘብና በስነልቦና ጎድቷት ሊሆን ይችላል። ደክመው(ዕብ.12፡12-13) ልባቸው ሊዝል ይችል ነበር(ዕብ.12፡3)። ከድል በኋላ፤ስነልቦናዊና ሌሎች አይነት መከላከያዎች ከላሉ በኋላ ብዙ ሰዎች እንዲሁም ማህበረሰቦች ለጠላት መልሶ ማጥቃት የበለጠ ተጋላጭ መሆናው በአብዛኛው የሚታይ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ የሚመጣን ችግር ለመጋፈጥ ኃይልን መሰብሰብ ለግለሰብም ሆነ ለማህበረሰብ ከባድ ነው። 1 ነገስት 19፡1-4ን ያንብቡ። ኤልያስ ምን አጋጠመው?
“ነገር ግን ብዙ ጊዜ ብርቱ ዕምነትና ግሩም ስኬት የሚያስከትለው ስሜት
ኤልያስን ተጫነው። በቀርሜሎስ ተራራ ላይ የተጀመረው መታደስ ዘለቄታ
አይኖረውም ብሎ ሠጋ፤ድባቴም ያዘው። በጲስጋ ተራራ ላይ ወጥቶ የነበረው
ሰው አሁን ሸለቆ ውስጥ ገባ። ከኃያሉ ብርታት(ምሪት) ስር በነበረበት ጊዜ
የዕምነት ፈተናን ተቋቁሞ ነበር። አሁን ግን ተስፋ በቆረጠበት ጊዜ የኤልዛቤል
ዛቻ ድምጽ በጆሮው ሲያሾከሹክ ሰይጣን በክፉዋ ንግስት አማካኝነት
ወጥመዱን ሲጥልበት የእግዚአብሔርን እጅ ለቀቀ። ከልክ በላይ ከፍ ከፍ
ብሎ ሳለ ውጤቱ (በሰው ዘንድ የነበረው ተቀባይነት) ከመጠን በላይ ነበር
።
እግዚአብሔርን ረስቶ ኤልያስ ሽሽቱን በመቀጠል በምድረ በዳ ራሱን ብቻውን
እስኪያገኝ ድረስ ሄደ። ኤለን ጂ ኋይት፤ ነብያትና ነገስታት(በአማርኛው) ገጽ
108-109
በክርስትና ህይወትዎ የወደቁበትን ጊዝ ያስታውሱና ሁኔታዎቹንና
ለመውደቅም ምክንያት የሆኑትን ጉዳዮች ለመረዳት ይሞክሩ።
ምን ሊለውጡ ይችሉ ነበር?
በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ጳውሎስ አንባቢያን ምን እንዲያደርጉ መከራቸው? ለኛ ጥቅም በሚሆን መልኩ ከዕብራውያኑ ምን እንማራለን? ኤልያስ ከተስፋ መቁረጡ እንዲያገግም እግዚአብሔር እንዴት እንደረዳው እንመርምር። 1 ነገስት 19፡5-18ን ያንብቡ። እግዚአብሔር የአገልጋዩን የኤልያስን እምነት ለመመለስ ምን አደረገ?
ከቀርሜሎስ በኋላ እግዚአብሔር ኤልያስን የያዘበት ሁኔታ አስደናቂ ነው
ምክንያቱም እግዚአብሔር የተጎዱትንና እምነታቸውንም መልሰው ለማግኘት
የሚታገሉትን በምን አይነት ጥበብና እንክብካቤ እንደሚይዛቸው ስለሚያሳይ
ነው። እግዚአብሔር ለኤልያስ ብዙ ነገሮችን አድርጎለታል። መጀመሪያ ለስጋዊ
ፍላጎቱ ተጠነቀቀለት። ምግብ እንዲበላና እረፍት እንዲያደርግም አዘጋጀለት።
ከዚያም በዋሻው ውስጥ በትህትና “ኤልያስ ሆይ እዚህ ምን ታደርጋለህ? ብሎ
በመጠየቅ ጌታ እንዴት እንደሚሰራና አላማውንም እንዴት እንደሚያሳካ
በጥልቀት እንዲረዳ አገዘው።
እግዚአብሔር በንፋሱ፤በመሬት መንቀጥቀጡ
ወይም በእሳት ውስጥ አልነበረም ነገር ግን በለስላሳው ድምጽ ውስጥ ነበረ።
ከዚያም እግዚአብሔር ለኤልያስ ስራ ሰጠውና ማረጋገጫ ደግሞ ሰጠው።
ዕብራውያን 2፡1፤ ዕብ 3፡12-14፤ ዕብ 5፡11-6፡3 እና ዕብ
10፡19-25ን ያንብቡ። ጳውሎስ አማኞች ማድረግ ስላለባቸው
ነገር ምን ምክር ሰጠ?
በመላው ዕብራውያን መልዕክት ውስጥ አንባዎቹ ወደ ትክክለኛው
ጥንካሬና እምነት እንዲመለሱ ሐዋርያው የሰጣቸውን መመሪያዎች
እናገኛለን።አንደኛው ጉዳይ የተቸገሩ አማኞችን መርዳት ላይ ያተኮረ ነው።
እንግዳ ተቀባዮች እንዲሆኑና የታሰሩትን በመጠየቅ የሚያስፈልጋቸውን
በማሟላት እንዲረዷቸው ይመክራል። እግዚአብሔር እንደማይተዋቸው
በማስታወስ እነርሱም ቸር እንዲሆኑ አስተምሯል(ዕብ.13፡1-6)። በተጨማሪም
ጳውሎስ ሲገስጻቸውና ሲያበረታታቸው ነበር።
ቀስ በቀስ እንዳይንሸራተቱ
ሲያስጠነቅቃቸው(ዕብ.2፡1)፤ “የማያምን ክፍ ልብ” እንዳይኖራቸው
ሲያስጠነቅቃቸው የነበረ ሲሆን ስላመኑት ነገር ባላቸው ማስተዋል እንዲያድጉ
ደግሞ አበረታቷቸዋል(ዕብ.5፡11-6፡3)። በቤተክርስትያን ፕሮግራሞች ላይ
በቋሚነት መገኘት ሰላለው ጥቅምም ኃሳብ ሰጥቷል(ዕብ.10፡25)። ለማጠቃለል
እርስ በርስ በመበረታታት፤ፍቅርንና መልካም ስራን በማበረታታት አብረው
እንዲቀጥሉ በመምከር እንዲሁም በነርሱ ፋንታ በሰማዩ ቤተ መቅደስ እያገለገለ
ያለውን ኢየሱስን ከፍ በማድረግ አብራርቷል(ዕብ.8፡1-2፤ዕብ.12፡1-4)።
ዕብ.1፡2ን፤ ዕብ. 9፡26-28፤ ዕብ. 10፡25፤36-38ንና ዕብ. 12፡25-28ን ያንብቡ ጳውሎስ በዚህ ቦታ በተለይም ጊዜን በተመለከተ እየተናገረ ያለው ነጥብ ምንድነው?
ጳውሎስ በሰጣቸው ምክር ላይ አስቸኳይነትን የሚጨምር ሌላ እጅግ ጠቃሚ
ነገር አለ፤ያም አንባዎቹ “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ላይ መኖራቸው ነው(ዕብ.1፡
2) እና ተስፋዎቹም ሊፈጸሙ መሆናቸው ነው(ዕብ.10፡36-38) ። ወደ ፊት
እንደምንመለከተው በመልዕክቱ ሁሉ ጳውሎስ አንባቢዎቹን ወደ ተስፋይቱ
ምድር ወደ ከነዓን ለመግባት ድንበር ላይ ከደረሱት ሕዝቦች ጋር ማነጻጸሩ
የሚገርም ነው። “ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፤ ሊመጣ ያለውም ይመጣል
አይዘገይምም” በማለት ያስታውሳቸዋል። ከዚያም እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ
ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉት አይደለንም። በማለት
ያበረታታቸዋል(ዕብ.10፡39)። ይህ ምክር አንባቢያኑንና እኛን የእግዚአብሔር
ሕዝብ የእግዚአብሔር ተስፋ ከመፈጸሙ በፊት ስላጋጠማቸው አደገኛ ነገር
ያስታውሳል
።
የዘሁልቁ መጽሐፍም ስለዚሁ ነገር ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን
እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባቱ በፊት ሁለት ጊዜ ተሸንፏል።
የመጀመሪያ በዘሁልቅ 13ና14 ላይ እንደተቀመጠው የተወሰኑ መሪዎች በህዝቡ
መካከል ጥርጥርን ዘርተው የእስራኤል እምነት እንዲላላ ያደረጉበት ታሪክ
ነው። በውጤቱም ህዝቡ አዲስ መሪ መርጠው ከነዓን ሊገቡ ጥቂት ሲቀራቸው
ወደ ግብጽ ለመመለስ ወሰኑ።
ሁለተኛው ደግሞ በብዔል ፌጎር እስራኤላውያኑ በዝሙትና በጣኦት አምልኮ
ተጠልፈው ነው (ዘሁልቅ 24፡25) ። በለዓም እስራኤላውያኑን መርገም
ሲያቅተው ሕዝቡ በስህተት አምልኮ ኃጢያት እንዲሠራና እግዚአብሔር
እንዲያዝንባቸው ለማድረግ ሰይጣን ወሲባዊ ፈተናን ተጠቀመ
።
ሐዋሪያው አንባቢዎቹን ስለ ሁለት አደጋዎች ማስጠንቀቂያ ይሰጣል።
በመጀመሪያ በዕምነታቸው እንዲጸኑና አይኖቻቸውን በኢየሱስ ላይ ብቻ
እንዲያደርጉ ይመክራቸዋል (ዕብ.4፡14፤ ዕብ.10፡23፤ ዕብ.12፡1-4) ። በሁለተኛ
ደረጃ ደግሞ ግብረገብነትን ስለማጣትና ስለ ክፉ ምኞት ያስጠነቅቃቸዋል
(ዕብ.13፡4-6)። በመጨረሻም መሪዎቻቸውን እንዲያዩና እንዲታዘዙ
መክሯቸዋል(ዕብ.13፡7-17)
።
ስለሙታን ሁኔታ ካለን መረዳት ተነስተን እንዲሁም ከሞትን በኋላ
ቀጥሎ የምናውቀው ነገር ዳግም ምጻቱን መሆኑን ከግምት ውስጥ
በማስገባት ሁሉም የኖረው በመጨረሻዎቹ ቀናት ነው ማለት
የምንችለው ለምንድነው?
ቀደምት ክርስቲያኖች ለምን ስደት እንደሚደርስባቸው
ዴቪድ ኤ. ዴሲልቫ ሲገልጽ ክርስትያኖች ለህብረት የማይመቹ እንዲሁም
አፍራሽ የሚባል የአኗኗር ዘይቤን ይከተላሉ። በመስዋዕት ጊዜያት እና
በመሳሰሉት የመሰባሰቢያ ጊዜያት በመሳተፍ የሚገለጸው ጣኦትን መታመን
ልክ ለሀገር፤ለባለስልጣናት፤ለጓደኞችና ለቤተሰብ የመታመን ምልክት እንደሆነ
ይታሰብ ነበር። ጣኦታቱን ማምለክ ለተረጋጋና ለበለጸገ ማህበረሰብ መኖር
መሰጠትን የሚገልጽ ምልክት ተደርጎ ይታሰብ ነበር። ያንን ባለማድረጋቸው
ክርስትያኖች (ልክ እንደ አይሁዳዊያን) በግዛቱ ውስጥ ህግ እንደሚጥሱና
ሀገር እንደሚያፈርሱ ተደርገው ይታሰቡ ነበር። Preseverance in gratitude
(Grand Rapids, MI: Eerdmas publishing company,2000, p,12)
።
“ልባቸው ለተጎዳ የተረጋገጠ መፍትሄ አለ፡- እምነት፤ጸሎት፤ሥራ። እምነትና
ተግባር በየቀኑ የሚጨምር ማረጋገጫንና እርካታን ይሰጣሉ። ምን ይመጣብኝ
ይሆን ብለው በፍርሃት ተውጠዋል? በተስፋ መቁረጥስ ውስጥ ነዎት? ቀኑ
ሲጨልም የሚታየው ነገር ሁሉ ደስ የማይል ሲሆን አይፍሩ። በእግዚአብሔር
ይመኑ። የሚያስፈልግዎትን ያውቃል፤ኃይል ሁሉ አለው። የበዛው ፍቅሩና
ርህራሄው አያልቅም።ቃሉን ያጥፋል ብለው አይፍሩ። እርሱ ዘላለማዊ እውነት
ነው።
ከሚወዱት ጋ የገባውን ኪዳን መቼም አይቀይርም። ለርሱ ታማኝ
የሆኑት አገልጋዮቹ የሚያስፈልጋቸውን አቅም ሁሉ ይሰጣቸዋል። ጳውሎስ
ስለዚህ ሲመክር “እርሱም ጸጋዬ ይበቃሃል፤ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና
አለኝ።…….ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም
በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።”2 ቆሮንቶስ 12፡9-10
ነቢያትና ነገስታት፤ገጽ 164፤165።
1. እንደ ክርስትያን በያዝነው አቋም ልዩ ሆነን ከሌሎች በመራቅና
ሌሎችን ችላ በማለት ላንወነጀል የምንችልበት መንገድ ይኖር
ይሆን? ከኖረስ እንዴት
?
2.“የምክር ቃል” ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ የተቀመጠው ቃል
ተግሳጽንም ወይም ማበረታቻንም ሊገልጽ ይችላል። ተስፋ
የቆረጠውን ሰው ስንመክር እንዴት ልንጠነቀቅ ይገባናል
?
3.በዕብራውያን መልዕክት አንባቢዎችና በራዕይ 3፡14 ላይ
በምትገኘው በላዶቂያ መካከል ምን መመሳሰል ይታያችኋል?
ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ የኛ ልምምድ ከዕብራውያኑ ጋር
ተመሳሳይ የሚሆነው እንዴት ነው? ከነዚህ መመሳሰሎችስ ምን
ትምህርት እናገኛለን?