የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 2:2-3፣ ዘፀ. 20:11፣ ዘፀ. 16፣ ዕብ. 4:1–4፣ ዘፀ. 31:12–17፣ ዘዳ. 5:14።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “እስራኤላውያን በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ሰንበትን በመጠበቅ የዘላለም ኪዳን አድርገው ማክበር አለባቸው፡፡” (ዘፀ. 31፡16)፡፡
ሰ
ባተኛ ቀን ሰንበት ልክ በሚስማር እንደ ተጣበቀ--በማይበጠስ መደበኛነት
በየሣምንቱ ወደ ቀደመው የሁሉም ነገር ጽኑ መሠረት የሚመልሰን
ዕለት ነው። ሣምንቱን ሙሉ እዚህና እዚያ ስንባክን፣ ገንዘብ ስናጠፋ፣
ገንዘብ ስናገኝ በመሃል ሰንበት ይደርስና እንደገና ከቀደመው ጽኑ መሠረታችን ጋር
ያጣብቀናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር እና እኛን የፈጠረው እኛ
እንድንጀምርበት ስለሆነ ብቻ ነው።
ሰንበት በማያቋርጥ መደበኛነት እና ያለ ልዩነት በዝምታ፣ በአድማሱ እና በእያንዳንዱ
የሕይወት ክፋያችን ላይ ያርፋል። የእያንዳንዱ ክፋይ ባለቤት--እዚህ ያኖረን፣
“በመጀመሪያ” ሰማያትንና ምድር የፈጠረ ፈጣሪያችን መሆኑን ያስታውሰናል።
በዚህም ሰባተኛው ቀን ሰንበት ለሁሉም የክርስትና እምነት የማይሻር መሠረት ሆኖ
የቀጠለና የተረጋገጠ፣ የማይለዋወጥ ምልክት ነው።
በዚህ ሣምንት ይህንን ምልክት ከሲና ቃል ኪዳን ዐውደ ንባብ አኳያ እንመለከታለን።
ሰንበትን እንዲህ ተስማሚ የቃል ኪዳን ምልክት የሚያደርገው ምንድነው?
“የድሮ የአይሁድ ሰንበት” የሚለውን ሐረግ ስንት ጊዜ ሰምተናል? ሆኖም ሰንበት
የአይሁድ ሕዝብ ከመምጣቱ ረጅም ዘመን በፊት እንደነበረ አምላካዊው ቃል ግልጽ
አድርጎ ያስቀምጥልናል። መነሾው በራሱ በፍጥረት ሣምንት ውስጥ ይገኛል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 2፡2-3፣ ዘፀ. 20፡11። የሰንበትን ጅማሮ
በግልጽና የማያሻማ ሁናቴ በየት ስፍራ ያስቀምጡልናል?
ምንም እንኳ ዘፍ. 2፡2-3 “ሰባተኛውን ቀን” እንደ ሰንበት ባይገልጽልንም (ይህ
መታወቂያ በመጀመሪያ የሚመጣው በዘፀ. 16፡26፣29 ነው) “በሰባተኛው ቀን
አረፈ” (ዘፍ. 2፡2) በሚለው ሃረግ ላይ ግን በግልጽ ተጠቁሟል። ዐረፈ የሚለው ቃል
(በዕብራይስጥ ሻባት)፤ ሰንበት ከተሰኘው (በዕብራይስጥ ሻባት) ስም ጋር ዝምድና
አለው። “ ‘ሰንበት’ የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ባይውልም [ዘፍ. 2:2-3] ነገር ግን
ደራሲው እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ሰንበት ስለ መባረኩና መቀደሱ አጽንኦት
ሊሰጥ መፈለጉ እሙን ነው”—G. F. Waterman, The Zondervan Pictorial
Encyclopedia of the Bible (Grand Rapids, MI: Zondervan Publishing
House, 1975), vol. 5, p. 183.
በግልጽ እንደሚስተዋለው ዘፍ. 2፡2-3 ሰንበት ለመላው የሰው ልጆች የበረከት ቀን
ሆኖ በመለኮት መጀመሩንና መቋቋሙን ያስተምራል።
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ማር. 2፡27። የሱስ፤ ሰንበት የተፈጠረው “ለሰው”
ነው ብሎ ቃል በቃል ሲናገር--ከአይሁዶች ብቻ በተቃራኒ አጠቃላዩን
ሰብዓዊ ዘር እያመላከተ ነበር።
እግዚአብሔር ራሱ በሰባተኛው ቀን ለምን ያርፋል? ለእርሱ
አስፈልጎት ነበር? ማረፉ ምን ሌላ ዓላማ ሊኖረው ይችላል?
ምንም እንኳ አንዳንድ ተንታኞች እግዚአብሔር ከፍጥረት በኋላ አካላዊ እረፍት
አስፈልጎት እንደ ነበር ቢጠቁሙም፤ እግዚአብሔር ያረፈበት እውነተኛው ዓላማ
ለሰው ልጆች መለኮታዊ ምሳሌ ለመሆን ነበር። ሰብዓዊው ፍጡርም እንዲሁ
ለስድስት ቀናት መሥራትና ከዚያ በሰባተኛው ቀን ሰንበት ማረፍ አለበት። የሥነ
መለኮት ምሑሩ ካርል ባርት በፍጥረት መጨረሻ ላይ የእግዚአብሔር ማረፍ የሰው
ልጆች “ከእርሱ ጋር እንዲያርፉ”…[በአምላክ] ዕረፍት ውስጥ ለመሳተፍ የተጋበዙበት
“የጸጋው ቃል ኪዳን” አካል እንደሆነ ይጠቁማሉ።—Church Dogmatics, vol. 3,
part 1 (Edinburgh, Scotland: T&T Clark Ltd., 1958), p. 98.
እግዚአብሔር ሰውን ወንድ እና ሴት አድርጎ በአምሳሉ በፈጠረ ማግሥት
ከፍቅሩ ብዛት የተነሣ ከእርሱ ጋር ሕብረት ፈጥረው እንዲያርፉና የቀረበ ግንኙነት
እንዲመሠርቱ ጥሪ አቀረበላቸው። ያ ሕብረት እና አንድነት ለዘላለም የሚኖር ነበር።
ሰው ከውድቀት አንስቶ በሕይወቱ ከአዳኙ ጋር ወደ ሣምንታዊ ከፍታ የሚወጣበት
ዕድል ተሰጥቶታል።
አንድ ሰው፡ ሰንበትን ማክበርዎ ከጌታ ጋር ላለዎት ግንኙነት እንዴት
ጠቅሞታል ብሎ ቢጠይቆት መልስዎ ምን ይሆናል?
“እርሱም አላቸው፤ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ ለነገ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ
ሰንበት በመሆን፣ የዕረፍት ቀን ይሆናል። ስለዚህ መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤
መቀቀል የምትፈልጉትን ቀቅሉ። የተረፈውን አስቀምጡ፤ እስከ ጧትም ድረስ
አቆዩት” (ዘፀ. 16፡23)።
በዘፀ. ምዕ. 16፤ ከሲና አስቀድሞ ለእስራኤላውያን በምድረ በዳ
ይቀርብላቸው ስለ ነበረው መና የተጻፈውን ታሪክ ያነባሉ። ዘገባው
የሚያካትታቸውን ነጥቦች ልብ ይበሉ፡
1.በየቀኑ መደበኛ መጠን ያው መና ብቻ መጠቀም ይቻል የነበረ ሲሆን፣
በስድስተኛው ቀን ግን ሁለት እጥፍ መሰብሰብ ነበረበት።
2.በሰንበት ምንም ዓይነት መና አይወርድም ነበር።
3.ለሰንበት ያስፈልግ የነበረው ተጨማሪ መጠን ስድስተኛውን ቀን ሳይበሰብስ
ይቆይ የነበረ ሲሆን፤ ከዚህ ውጪ መናው በሌሎቹ ቀናት ካደረ ይበላሽ ነበር።
ታሪኩ ሕጉ በሲና ከመሰጠቱ አስቀድሞ ስለ ነበረው የሰንበት ቅድስና ምን
ይገልጽልናል? (ዘፀ. 16:23–28)
“እንደ እውነቱ ከሆነ፤ የሰንበት ቀን ከሰባተኛው ቀን ጋር አንድ መሆኑ፣ ጌታ
ለእስራኤላውያን ሰንበትን የሰጠበት መግለጫ እና ሰዎች በእግዚአብሔር ትእዛዝ
በሰባተኛው ቀን ስለ ማረፋቸው የሚናገረው አምላካዊ ቃል--በማያሻማ መንገድ
በመጀመሪያ [በፍጥረት ወቅት] መቋቋሙን ያመለክታሉ።”—G. F. Waterman,
The Zondervan Pictorial Encyclopedia of the Bible, vol. 5, p. 184.
በዘፀ. 16 ዐይናችን ሰንበት ላይ ከማረፉ አስቀድሞ ሌሎች የሚዳሰሱ ብዙ ነጥቦች
አሉ። ምን እንደሚያስተምረን ይመልከቱ፡
1.የሰንበት መዘጋጃ ቀን የትኛው ነው?
2.ሰንበት ከሣምንቱ ቀናት መሃል የትኛው ነው?
3.ሰንበት የመጣው ከየት ነው?
4.ሰንበት ምን ዓይነት ቀን መሆን አለበት?
5.ሰንበት ጾም የሚያዝበት ዕለት ነው?
6.ሰንበት ለእግዚአብሔር የሚኖረን ታማኝነት የሚፈተንበት ቀን ነው?
ስለ ሰንበት ያለዎት ግንዛቤ በዘፀ. 16 በሰንበት ዙሪያ ከቀረበው
ትምህርት ጋር እንዴት ይዛመዳል?
“ ‘ “እስራኤላውያን በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ሰንበትን በመጠበቅ የዘላለም
ኪዳን አድርገው ማክበር አለባቸው፤ በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ለዘላለም
ምልክት ይሆናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን
ሠርቶ፣ በሰባተኛው ቀን ከሥራ ታቅቦ ዐርፎአልና።” ’ ” (ዘፀ. 31:16-17)።
ሰንበት በቅዱሳት መጻሕፍት አራት ጊዜ “ምልክት” በሚል ስያሜ ተጠርቷል
(ዘፀ. 31:13፣ 17፣ ሕዝ. 20፡12፣20)። እዚህ ላይ “ምልክት” እና “ምሳሌ” የተለያዩ
መሆናቸውን ልብ ይሏል። ሰንበት በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ ውጫዊ “ምልክት”፣ ነገር
ወይም ሁኔታ ሆኖ አገልግሎት ይሰጣል። በራሱ በምልክቱ ውስጥ በተለይ ከቃል
ኪዳኑ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም። ሰንበት እግዚአብሔር በተናገረው
መሠረት “ ‘ “በእኔና በእናንተ መካከል ለዘላለም ምልክት ይሆናል” ’ ” (ዘፀ. 31:13)
በሚል በእርሱ የቀረበ የቃል ኪዳን ምልክት ነበር።
ጌታ ሰንበትን ለምን እንደ ቃል ኪዳን ምልክት ይጠቀምበታል?
ከእግዚአብሔር ጋር ለሚኖር አዳኝ ግንኙነት ሰንበትን ተስማሚ ምልክት
የሚያደርገው ምንድን ነው? በሥራ ሳይሆን በጸጋው የመዳናችንን የቃል
ኪዳኑን ወሳኝ ገጽታ በማስታወስ፤ ሰንበትን ራሱን ለዚያ ግንኙነት
መልካም ምሳሌ የሚያደረገው ምን ይመስሎታል? (ዘፍ. 2:3፣ ዕብ.
4:1–4)።
አይሁዳውያን ሰንበትን ለብዙ መቶ ዓመታት የመሲሐዊ መቤዠት ምልክት አድርገው
መረዳታቸው--እንደ ጸጋ ቃል ኪዳን ምልክትነቱ ፍጹም ማራኪ ያደርገዋል። እነዚህ
ሕዝቦች ሰንበትን በመሲሕ እንደሚገኝ ደኀንነት ናሙና አድርገው ተመልክተውታል።
መዋጀት ከጸጋ ብቻ እንደሚመጣ ስለምንረዳ፣ ቃል ኪዳኑ የጸጋ ቃል ኪዳን መሆኑን
ስለምናስተውል--በሰንበት፣ በመዋጀት እና በቃል ኪዳኑ መሃል ያለው ትስስር ግልጽ
ተደርጓል (ዳን. 5፡13-15)።
ስለዚህ ከተለመደው አመለካከት በተቃራኒ--ሰንበት
የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ ምልክት እንጂ በሥራ የመዳን ምልክት አይደለም።
በሰንበት “ማረፍ” ምን ማለት እንደሆነ እንዴት ይረዱታል? በሰንበት የማረፍዎ
ሁኔታ ምን ይመስላል? ዕለቱን “ምልክት” ሊያደርገው የሚችል ምን የተለየ ነገር
ያደርጋሉ? እርስዎን የሚያውቅ ሰው ህይወትዎን ተመልክቶ ሰንበት በእርግጥ
ለእርስዎ የተለየ ዕለት መሆኑን መመልከት ይችላል?
“ ‘ “ሰንበቴን ማክበር አለባችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል በሚመጡት
ትውልዶች ሁሉ ምልክት ይሆናል፤ ይኸውም የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር እንደ
ሆንሁ እንድታውቁ ነው” ’ ” (ዘፀ. 31:13)።
ለየት ባለ መንገድ ስለ ሰንበት የተሟላ ዘገባ የሚያቀርበው ዘፀ. 31፡12-17--የመገናኛ
ድንኳኑን ለመገንባት ጌታ የሚሰጣቸውን መመሪያዎች ተከትሎ ቀርቧል (ከዘፀ. 25፡
1 እስከ ዘፀ. 31፡11)።
ሰንበት በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል የሚታይ፣ ውጫዊ እና ዘላለማዊ
“ምልክት” ስለ መሆኑ የሚያወሳው ጽንሰ-ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ መልኩ
ተገልጧል። ጥቅሱ በራሱ ለጥናታችን ተገቢነት ያላቸውን ፍጹም ማራኪ ጽንሰ
ሀሳቦች ይዟል። በዚህ ጥቅስ ሁለት አዳዲስ ጽንሰ ሀሳቦች በአንድ ላይ ተጣምረዋል።
1.ሰንበት የእውቀት ምልክት ነው
2.ሰንበት የመቀደስ ምልክት ነው
ከእውቀት ጋር ተዛምዶ ያለውን የምልክት ገጽታ ያስቡ። የዕብራውያን የዕውቀት
አረዳድ፡ የማሰብና መመራመር፣ የግንኙነት እንዲሁም የስሜታዊ ገጽታዎችን
ያካትታል። “ማወቅ” አንድን እውነታ ማወቅ ተደርጎ ብቻ አይወሰድም--በተለይ
ከግለሰብ ጋር በተያያዘ። በመሆኑም መታወቅ ካለበት ሰው ጋር ትርጉም ያለው
ግንኙነት መፍጠር የሚል አንደምታም አለው። ከዚህ በመነሣት ጌታን ማወቅ ማለት
ከእርሱ ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ውስጥ መሆን--እርሱን “ማገልገል” (1ዜና 28፡9)፣
እርሱን “መፍራት” (ኢሳ. 11፡2)፣ እርሱን “ማመን” (ኢሳ. 43፡10)፣ በእርሱ “መታመን”
እና እርሱን “መሻት” (መዝ. 9፡10፣ እርሱን በስሙ “መጥራት” (ኤር. 10፡25) የሚል
ፍቺ አለው።
ከላይ በቀረበው አንቀጽ እያንዳንዱን ጥቅስ ልብ ብለው ይመልከቱ።
ጥቅሶቹ ጌታን “ማወቅ” ምን ማለት እንደሆነ መረዳት እንድንችል
እንዴት ይረዱናል?
በተጨማሪ ሰንበት የመቀደስ ምልክት የመሆን አንደምታ አለው። ሕዝቡ ለጌታ
“ቅዱስ” (ዘዳ. 7፡6) ነው፤ እርሱም “ይቀድሳቸዋል” (ዘሌዋ. 20፡8)።
የመቀደስ ሂደት ልክ እንደ አምላካዊው የሚዋጅ የፍቅር ሥራ--የሚያድን እና
የሚቤዥ የእግዚአብሔር ሥራ ነው። ጽድቅ እና መቀደስ ሁለቱም የእግዚአብሔር
ተግባራት ናቸው። “ ‘የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ’ ” (ዘሌዋ. 20፡8)።
በመሆኑም እርሱ የሚቀድስ አምላክ እንደመሆኑ ሰንበት አምላካዊውን ዕውቀት
የሚያካፍልበት ምልክት ነው። “የእግዚአብሔር ፈጣሪነት ምልክት ተደርጎ ለዓለም
የተሰጠው ሰንበት፤ እርሱ የሚቀድስ አምላክ የመሆኑም ምልክት ነው።”—Ellen G.
White, Testimonies for the Church, vol. 6, p. 350.
ቅዱስ ሆኖ ስለተሠራው የሰንበት ቀን እና የመቀደስ ሂደት ያስቡ።
በዚህ ሂደት ሰንበትን ማክበር ምን ሚና አለው? ጌታ ሰንበትን የመጠበቅ
ልምዳችንን እኛን ለመቀደስ እንዴት ሊጠቀምበት ይችላል?
“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” (ዘፀ. 20፡8 /1962
ትርጉም/)
ሰንበት ሰው ዕለቱን እንዲያስብ ብሎም እንዲያስታውስ የተሰጠው ምልክት
ነው። አስብ ወይም አስታውስ የሚለው ቃል ለተለያዩ ተግባራት ሊውል ይችላል።
በመጀመሪያ አንድን ነገር ማስታወስ፣ ያለፈውን ወደ ኋላ ማየትንም ያመለክታል።
ከዚህ አኳያ ከባዶ ጀምሮ ሰንበት በተቋቋመበት ወቅት አመርቂ ደረጃ ላይ የደረሰውን
የፍጥረት ሥራ--ሣምንታዊ የዕረፍት እና ከእግዚአብሔር ጋር የተለየ ግንኙነት
የምናደርግበትን ቀን ያመለክተናል።
ዕለቱን አስታውሱ በሚል የተሰጠው ትእዛዝ እነሆ ለእኛ ዘመንም ጉልህ
አንደምታ አለው። እኛ ሰንበትን ማስታወስ (ዘፀ. 20፡8) ብቻ ሳይሆን “ቀድሰን”
“እንድናከብረው” (ዘዳ. 5፡12) ተጠይቀናል። ስለዚህ ሰንበት በዚህ ዘመን ለእኛ
አስፈላጊ አንድምታዎች አሉት።
በመጨረሻም፡ ሰንበትን ማስታወስ እንዲሁም ወደፊት ያመላክተናል። ሰንበትን
ማክበር የሚያስታውስ ሰው፤ ከሰንበት ጌታ ጋር ተስፋ ሰጭ፣ የከበረ እና ትርጉም
ያለው የወደፊት ሕይወት አለው። ግለሰቡ ወይም ግለሰቧ በጌታ ጸንተው ስለሚኖሩ
በኪዳናዊውም ግንኙነት ጸንተው መኖር ያስችላቸዋል። ቃል ኪዳኑ በእግዚአብሔር
እና በሰው ልጆች መካከል ያለ የግንኙነት መስመር መሆኑን ስንረዳ፤ ይህን ግንኙነት
በከፍተኛ ሁኔታ ለማጠንከር የሚረዳው ሰንበት ትክክለኛውን እውቅና ወደ ማግኘት
ይመጣል።
እርግጥ ነው--ፍጥረትን እና ፈጣሪዋን በማስታወስ የእግዚአብሔር ሕዝቦች
አምላካዊውን በቸርነት የተሞላ የማዳን ሥራም እንዲሁ ያስታውሳሉ። (በዘዳ. 5፡14
ዐውድ ሰንበት ከግብፅ የመዳናቸው ምልክት ሆኖ እንደ ቀረበ ሁሉ፤ በእግዚአብሔር
የሚገኘው የመጨረሻው ደኅንነት ምሳሌም ነው።) ፍጥረት እና ዳግም መፈጠር
ከአንድ ጎራ ይመደባሉ። የቀድሞው የኋለኛውን እንዲቻል ያደርገዋል። ሰንበት
እግዚአብሔር የዓለም ፈጣሪ እና የመዳናችን ፈጣሪ የመሆኑ አገናኝ ምልክት ነው።
የእርሱን ሰንበት ቅዱስ አድርገን በመጠበቅ ህዝቦቹ መሆናችንን ማሳየት አለብን።
ሰንበት ትእዛዛቱን የሚጠብቁ ሰዎች የሚለዩበት ምልክት ስለ መሆኑ ቃሉ ያውጃል።…
በሰማይ በሰይጣንና በእግዚአብሔር መካከል በተጀመረው ታላቁ ውዝግብ፤
የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቁ እነሆ ከእርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ።”—Ellen G.
White, Selected Messages, book 2, p. 160.
እኛ “ትእዛዛቱን የሚጠብቁ ሕዝቦች” ተደርገን እንድንታወቅ
መንስኤ የሆነውን ሰንበትን በተመለከተ ምን ይላሉ?--ምናልባት
ከሌሎቹ ትእዛዛት በበለጠ?
Read Ellen G. White, pp. 968-970, in The SDA Bible
Commentary, vol. 7; “The Observance of the Sabbath,” pp. 349–351,
in Testimonies for the Church, vol. 6; “ከቀይ ባህር ወደ ሲና” ገጽ፡ 324-338
የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት።
ዐሥርቱ ትእዛዛት በመለኮት እና በሰው እንዲሁም ሰው--ከሰው ጋር ስለሚኖረው
ግንኙነት የተሟላ መሠረታዊ ፍቺ ይሰጣሉ። በዐሥርቱ ትእዛዛት አማካይ ላይ
የተቀመጠው ትእዛዝ፣ የሰንበት ትእዛዝ ነው። የሰንበት ጌታ የሆነውን አምላክ
ለይቶ ይገልጻል፣ ሥልጣኑን እና ባለቤትነቱንም ያሳያል። እነዚህን ሁለት ገጽታዎች
ልብ ይበሉ፡ (1) የአምላክነቱ መታወቂያ፡ ያሕዌ (ጌታ)፣ ፈጣሪ (ዘፀ. 20፡11፣ ዘፀ.
31፡17) በዓይነቱ የተለየ ስፍራ የሚይዝ፤ (2) የባለቤትነቱ እና የሥልጣኑ ግዛት--“
‘ሰማይና ምድር፤ ባሕርና በውስጡም ያሉ ሁሉ’ ” (ዘፀ. 20፡11፣ ዘፀ. 31፡17)።
በእነዚህ
ሁለት ገጽታዎች--የሰንበት ትእዛዝ የተለመዱት ዓለማቀፋዊ የጥንት ቅርብ ምሥራቅ
ስምምነት ሰነዶች ባሕሪያት አላቸው። እነዚህ ማኅተሞች በተለምዶ በውሎቹ አማካይ
ስፍራ ላይ የሚውሉ ሲሆን በተጨማሪ የሚከተሉትን ይይዛሉ (1) የአማልክቱን
ማንነት (ብዙውን ጊዜ የጣዖት አምላክ) እና (2) የባለቤትነት እና የሥልጣን ግዛት
(አብዛኛውን ጊዜ ውሱን መልክአ ምድራዊ ክልል) ይይዛሉ።
“በመንፈስ ቅዱስ መቀደስ የእግዚአብሔር ማኅተም ባላቸው እና ሐሰተኛውን
የእረፍት ቀን በሚጠብቁ መካከል ያለውን ልዩነት ያሳያል።
“ፈተናው ሲመጣ የአውሬው ምልክት ምንነት በግልጽ ይታያል። ይኸውም
እሑድን ማክበር ነው . . .
“እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን የራሱ ሰንበት አድርጎ ሰየመው [ዘፀ. 31:13፣16፣17]
“በመሆኑም ታማኝ በሆኑ እና ታማኝ ባልሆኑ መካከል ያለው ልዩነት ተሰምሯል።
የእግዚአብሔርን ማኅተም በግምባራቸው ለመቀበል የሚፈልጉ ሁሉ የአራተኛውን
ትእዛዝ ሰንበት ማክበር አለባቸው።”—Ellen G. White, The SDA Bible Commentary, vol. 7, pp. 980, 981.
1.ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘሌዋ. 19፡30። መቅደሱን እና ሰንበትን እንዴት
እንደሚያገኛኝ ልብ ይበሉ። ሰንበት የምን ምልክት እንደሆነ አስመልክቶ
እስካሁን የተረዳነውን ከግምት በማስገባት፤ ትስስሩ ያን ያህል አብልጦ
ትርጉም የኖረው ለምንድን ነው?
2.ይህን ጥያቄ ራስዎን ይጠይቁ፡ በሰንበት ማረፌ ከጌታ ጋር ያለኝ
ጉዞ እንዲጠነክር ረድቶኛል? ካልሆነ ምን ዓይነት ለውጦች ማድረግ
ይችላሉ?
ማጠቃለያ፡ ሰንበት የደኅንነት ዕቅድ ፍጻሜ የሚያገኝበት ጊዜ እስኪመጣ
የሚቆይ ኪዳናዊ ምልክት ነው። ሰንበት እንደ ቃል ኪዳናዊ ጸጋ ምልክትነቱ
እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር እንደ ገና አዲስ ወደ ሚያደርግበት፣ ወደ ቀደመው
የፍጥረት መጀመሪያ ወደ ሆነው--የመጨረሻው ዕረፍት ያመላክተናል።