የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ኢሳ. 41፣ ኢሳ. 42:1–7፣ ኢሳ. 44:26–45:6፣ ኢሳ. 49:1–12።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡- “አንተፌ የያዝሁህ አገልጋዬ፣ በእርሱ ደስ የሚለኝ ምርጤ ይህ ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል’ ” (ኢሳ. 42:1)
“ብ
ዙ ሰዎች ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ጊዜውን ያሳለፈባቸውን ቦታዎች
መጎብኘት ማለትም እርሱ በተራመደበት ቦታ ላይ መራመድ፣ ትምህርት
ያካሔደባቸውን ሐይቆች ማየትና ዐይኑ ያርፍባቸው የነበሩትን ኮረብታዎችና
ሸለቆዎች መመልከት ልዩ ዕድል ይመስላቸዋል። ክርስቶስ በሔደበት ለመሔድ
ወደ ናዝሬት፣ ቅፍርናሖም ወይም ቢታንያ መሔድ አያስፈልገንም። የእርሱን ዱካ
ሕሙማን በተኙበት አልጋ አጠገብ፣ ድኽነት በሰፈነባቸው ጎስቋላ ጎጆዎች ውስጥና
መጽናናት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ እናገኘዋለን። የሱስ በዚህ
ዓለም ላይ በነበረ ጊዜ ያደረገውን ካደረግን የእርሱን ዱካ ተከተልን ማለት ነው።”
የዘመናት ምኞት፡ ገጽ 672።
ኢሳይያስ ተመሳሳይ የምኅረት ተልዕኮ ስለ ነበረው የጌታ አገልጋይ እንዲህ ተናግሯል፡
“የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስንም የጧፍ ክር አያጠፋም፤…
የዕውሮችን ዐይን ትከፍታለህ፤ ምርኮኞችን ከእስር ቤት፣ በጨለማ የተቀመጡትንም
ከወህኒ ታወጣለህ።” (ኢሳ. 42፡3፣7)
እስቲ ወደዚህ አገልጋይ ምልከታ እናድርግ። ለመሆኑ ማን ነው?
የሚያከናውነውስ ምንድን ነው?
በኢሳ. 41፡8 “ባሪያዬ እስራኤል” በማለት የሚናገረው እግዚአብሔር በ42፡1 ደግሞ “አገልጋዬ” ብሎ ያስተዋውቃል። ይህ አገልጋይ ማነው?
የእስራኤላውያን ትውልድ ግንድ የሆነው እስራኤል/ያዕቆብ ነው? የእስራኤል ሕዝብ
ነው? በአዲስ ኪዳን የሱስ ተብሎ የተጠራው መሲህ/ክርስቶስ ነው?
ከኢሳ. 41 እስከ 53 ስለ እግዚአብሔር አገልጋዮች የቀረቡ ሁለት ዓይነት ማመሳከሪያዎች
አሉ። ኢሳ. 41፡8፣ ኢሳ. 44፡1-2፣ 21፣ ኢሳ. 45፡4፣ ኢሳ. 48፡20 እንደ ተጠቀሰው
አንደኛው ባሪያዬ “እስራኤል” ወይም “ያዕቆብ” በሚል ስያሜ ይታወቃል። እግዚአብሔር
እስራኤልን/ያዕቆብን በአሁን ጊዜ አቀራረብ ስለሚናገር፤ እርሱ ማለትም ያዕቆብ
የትውልድ ሃረጉ የሆነውን ሕዝብ መወከሉ ግልጽ ነው። ይህ--የጌታ “ባሪያ ያዕቆብ”
መቤዠት አግኝቶ ከባቢሎን በወጣ ጊዜ (ኢሳ. 48፡20) ክንውን አግኝቶ የተረጋገጠ
እውነታ ነው።
በሌሎች ክፍሎች ማለትም በኢሳ. 42፡1፣ ኢሳ. 50፡10፣ ኢሳ. 52፡13፣ ኢሳ. 53፡11
የእግዚአብሔር ባሪያ ስያሜ አልተሰጠውም። በኢሳ. 42፡1 ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠቀስ፣
ማንነቱ ወዲያውኑ አልታወቀም። ሆኖም ኢሳይያስ የሚጠቀማቸውን መግለጫዎች
በኋለኞቹ ገጾች እያሻሻለ ሲመጣ፤ እርሱ የያዕቆብን ብሔር (እስራኤልን) መልሶ ወደ
እግዚአብሔር (ኢሳ. 49፡5-6) ማምጣቱና በኃጢአተኞች ምትክ የመሥዋእት ሞት
መሞቱ ግልጽ ይሆናል (ኢሳ. 52፡13፣-53፡12፣ 49፡5-6)። ስለዚህ እንደ ህዝብ አንድ
መሆን አይችልም። ስለዚህ ኢሳይያስ ስለ ሁለት የእግዚአብሔር ባሪያዎች መናገሩ ግልፅ
ነው። አንደኛው ስብስብ (ብሔር)፤ ሁለተኛው ግለሰብ።
ባሪያዬ ብሎ የሚጠራው ህዝብ ሚና ምንድን ነው? ኢሳ. 41፡8-20
ሕዝቡ አሁንም የእግዚአብሔር ባሪያ መሆኑን እግዚአብሔር ለእስራኤል ማረጋገጫ
ይሰጣል፡ “ ‘መረጥሁህ እንጂ አልጣልሁህም” (ኢሳ. 41፡9)። በመቀጠል እግዚአብሔር
በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠቀሱት አስደናቂ ተስፋዎች አንዱን ለእስራኤል ይሰጣል፡ “እኔ
ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፣
በጽድቄም ቀኝ እጅ ደግፌ እይዝሃለሁ” (ኢሳ. 41፡10)። በዚህና በሚቀጥሉት ጥቅሶች
እንደ ቀረበው፤ የእስራኤል መሠረታዊ ሚና ሌሎች አገሮች እንደሚያደርጉት በባዕድ
አማልክትና ምስሎች ከመታመን ይልቅ ያድናቸው ዘንድ በእውነተኛው አምላክ (ከንጉሥ
አካዝ በተቃራኒ) መታመን ነው (ኢሳ. 41፡7፣ 21–24፣ 28-29)።
በኢሳ. 41፡14 እግዚአብሔር ህዝቡን ትል ብሎ እንደሚጠራው ልብ
ይሏል። ምን ለማለት ፈልጎ ነበር? የተሻለ መልስ ለማግኘት መላውን
መልእክት ይመልከቱ። እንዲሁም ሙሉ በሙሉ በጌታ ላይ መመካታችን
አስፈላጊ መሆኑን አስመልክቶ ይህ ምን ሊያስተምረን ይገባል?
እግዚአብሔር የመረጠውና መንፈሱን ያኖረበት የማይታወቀው አምላካዊ
ባሪያ ሚና እና ባህሪ ምንድን ነው? ኢሳ. 42፡ 1-7
ምርጥ የሆነውን መልስ ወይም ጥምር መልሶችን ይምረጡ፡
1.ለሕዝቦች ፍትሕ ያመጣል።
2.ዓላማውን በጸጥታ እና በእርጋታ፣ በተሳካ ሁኔታ ያከናውናል።
3.መምህር ነው።
4.በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል እንደ ኪዳን ሆኖ ያገለግላል።
5.ዐይነ ሥውርነትን በመፈወስና እስረኞችን ነፃ በማውጣት ብርሃን/ ተስፋን
ይሰጣል።
6.ሁሉም መልስ ነው።
የዚህ አገልጋይ ሚና እና ባህሪ የጌታ መንፈስ በእሱ ላይ ከሚያርፍበት
“ከእሴይ ግንድ የወጣ ቁጥቋጦ” ጋር እንዴት ይነጻጸራል (ኢሳ. 11)?
በኢሳ. 42 እንደቀረበው የኢሳ. 11 ዳዊታዊ ገዢ ከእግዚአብሔር ጋር ስምሙ ተግባር
በመፈጸም፤ ለተጨቆኑ ፍትህ እና ነፃነትን፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ጥበብ እና
እውቀት ይሰጣል። ይህ የእሴይ “ግንድ” እና “ሥር” “በፍትሕና ጽድቅ” (ኢሳ. 9፡7)
ለዳዊት ዙፋን እና መንግሥት ሰላም የሚያመጣ--የኢሳ. 9፡6-7 መለኮታዊ መሲህ
ሆኖ እናገኘዋለን። በኢሳ. 42፡ የተጠቀሰው ባሪያ መሲህ መሆኑ ግልጽ ነው።
አዲስ ኪዳን ፍትሕ የሚያመጣውን የኢሳ. 42 1-7 ባሪያ እንዴት
ይለየዋል? ማቴ. 12፡15–21
ማቴ. 12 የተጠቀሰው ከኢሳ. 42 ሲሆን፤ በእግዚአብሔር የተወደደውና በእርሱ ደስ
የሚሰኝበት (ኢሳ. 42:1፣ ማቴ. 3:16-17፣ ማቴ. 17:5) በጸጥታ ለሚያከናውነው የፈውስ
አገልግሎት ይውላል። ከሕዝቡ ጋር ትስስር ፈጥሮ በአገልግሎቱ አምላካዊውን ኪዳን
ዳግም የሚያቋቁም እርሱ ነው (ኢሳ. 42፡6፣ ዳን. 9፡27)።
የሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ በሰይጣን ጭቆና ከተፈጠረ ሥቃይ፣ እግዚአብሔርን
ካለማወቅና ከክፉ መናፍስት እሥራት ሕዝቡን በማዳን ፍትሕ አስፍነዋል (ሉቃ. 10፡
19)። ከዚያም የሱስ “አዲሱን ኪዳን” (ማቴ. 26፡28) ለማድደቅ እና “ ‘የዚህ ዓለም
ገዢ’ ” የሆነው ባይተዋሩ ሰይጣን ተጥሎ ለዓለም ፍትሕ ለማስገኘት ነው።
በኢሳ. 42፡1-4 ስለ ክርስቶስ የቀረበውን መግለጫ ይመልከቱ። በየሱስ
ሕይወት ዙሪያ ጥቂት ጊዜ ወስደው ያሰላስሉ። ይህ ትንቢት በትክክል
እንዲፈጸም ያደረገው የእርሱ አገልግሎት ልዩ ባሕሪ ምንድን ነው?
እኛም ሌሎችን እንዴት ማገልገል እንዳለብን አስመልክቶ ከዚህ ምን
እንማራለን?
በኢሳ. 44፡26-45፡6 ምን ዓይነት አስገራሚ ትንቢት ተገልጦአል?
የኢሳይያስ አገልግሎት ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ745 እስከ 685 ዘልቆአል።
ከምሥራቅ እና ከሰሜን ስለሚነሣ ኃይል (ኢሳ. 41፡2፣ 3፣ 25) ከገለጸ በኋላ፤ ይህ
ለየሩሳሌም መልካም የምሥራች ሊሆን እንደሚችል (ኢሳ. 41፡27) የሚጠቁመው
ኢሳይያስ፣ ቂሮስን አስመልክቶ በትክክል ስሙን ጠቅሶ በመተንበይ እንቅስቃሴዎቹን
ይገልጻል። ቂሮስ ከሰሜን እና ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ባቢሎን በመገስገስ በ539 ላይ
ድል አድርጎ ግዛቲቱን ተቆጣጠረ። አይሁዳውያንን ከባቢሎን ግዞት ነፃ በማውጣት
እግዚአብሔርን አገልግሏል። እንዲሁም የየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንደገና እንዲገነባ
ፈቃድ ሰጥቶአል (ዕዝ. 1)።
ይህንን ትንቢት ግምት ውስጥ ያስገቡ። ኢሳይያስ ከሞተበት ጊዜ አንስቶ እስከ
ባቢሎን ውድቀት ድረስ አንድ መቶ አርባ ስድስት ዓመት ስለሚሆን፤ የእርሱ ትንቢት
ከጊዜው አንድ መቶ ዓመት የቀደመ ነበር። ነገሩ--ጀነራል ድዋይት አይዘንአወር
በ1945 አውሮፓ ነፃነቷን እንድትቀዳጅ እገዛ ያደርጋል ሲል ጆርጅ ዋሽንግቶን ትንቢት
እንደ ተናገረ አድርጎ መመልከት ይቻላል።
የቂሮስ ድርጊቶች የባቢሎንን ዜና መዋዕሎች፣ የገዛ ራሱን “ቂሮስ ሲሊንደር”፣
መጽሐፍ ቅዱስ (2ዜና 36:22፣ 23፣ ዕዝ. 1፣ ዳን. 5፣ ዳን. 6:28፣ ዳን. 10:1) ጨምሮ
ብዛት ባላቸው ጥንታዊ ምንጮች ጥሩ ሆነው የተጠናከሩ በመሆናቸው፤ የኢሳይያስ
ትንቢት ትክክለኝነት ፈጽሞ አያከራክርም። ይህ እውነተኛ ነቢያት የወደፊቱን
አስቀድሞ ከሚያውቀው እግዚአብሔር አምላክ ትክክለኛውን ትንቢት እንደሚቀበሉ
በማሳየት የሕዝቡን እምነት ያጸና ነበር።
እግዚአብሔር ቂሮስን “ለቀባሁት” ብሎ የጠራው (ኢሳ. 45፡1) ለምን
ነበር?
“የተቀባ” በሚል ከቀረበው የዕብራይስጥ ቃል መሲህ የተሰኘውን ቃል እናገኛለን።
በብሉይ ኪዳን ሌላ ስፍራ ላይ ይህ ቃል የተቀባውን ሊቀ ካህን (ዘሌዋ. 4:3፣ 5፣
16፣ ዘሌዋ. 6፡22)፣ የተቀባውን የእስራኤል ንጉሥ (1ሳሙ. 16፡ 6፣ 1ሳሙ. 24፡6፣
10፡2፣ ሳሙ. 22:51) ወይም የወደፊቱን ዳዊታዊ ንጉሥ እና አዳኝ የሆነውን መሲህ
ሊያመለክት ይችላል (መዝ. 2፡2፣ ዳን. 9፡25፣ 26)። ከኢሳይያስ አስተያየት አኳያ
ቂሮስ ሕዝቡን እንዲያድን በእግዚአብሔር የተላከ የወደፊት ንጉሥ ነበር። ነገር ግን
እርሱ እስራኤላዊ ባለመሆኑ ያልተለመደ ዓይነት መሲህ ነበር።
የእግዚአብሔርን
ጠላቶች አሸንፎ በግዞት ስር የነበሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦችን ነፃ ማውጣት
የመሳሰሉትን መሲህ የሚያደርጋቸውን አንዳንድ ነገሮች የሚያደርግ ቢሆንም፤ ነገር
ግን እርሱ ከዳዊት ትውልድ ስላልመጣ፤ ከመሲህ ጋር ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም።
እግዚአብሔር ስለ ቂሮስ በመተንበይ እርሱ ብቻ ልዩ በሆነ መለኮታዊ ባህሪው
የወደፊቱን እንደሚያውቅ አስመሰከረ፡ (ኢሳ. 41:4፣ 21–23፣ 26–28፣ ኢሳ.
44:26)። በተጨማሪም ለቂሮስ እንዲህ ብሎታል፡ “በስምህ የምጠራህ የእስራኤል
አምላክ፤ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቅ ዘንድ፣ በተሰወረ ስፍራ የተከማቸውን
ሀብት፣ በጨለማም ያለውን ንብረት እሰጥሃለሁ” (ኢሳ. 45፡3)።
አስቀድሞ በተተነበየው መሰረት ፍጻሜ ስላገኙ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ
ትንቢቶች ያስቡ (ዳን. 2 ከመጨረሻው በቀር፣ ዳን. 7 ወይም ዳን. 9፡2427)። እነዚህ ትንቢቶች እንደ ግለሰብ ምን ዓይነት ተስፋ ይሰጡናል?
ኢሳይያስ ቂሮስን ስሙን ጠርቶ ስለ እርሱ በትክክል የመተንበዩ እውነታ ነቢያት
ከእግዚአብሔር ትንቢት መቀበላቸውን የማያምኑ ሰዎችን ይረብሻል። ለዚህ እንደ
አጸፋ ይሆናቸው ዘንድ “ሁለተኛው ኢሳይያስ” ይባል የነበረ በቂሮስ ዘመን የኖረ
ነቢይ--ኢሳ. 40-66 ጻፈ የሚል ንድፈ ሀሳብ ተቀብለዋል። በዚህ ንድፈ ሀሳብ መሰረት
የኢሳይያስ መጽሐፍ “ለሁለት ተሰንጥቋል”--በራሱ በነቢዩ ላይ የተከሰተውም ይኸው
ነው ይላል አፈ ታሪኩ (ዕብ. 11፡37)።
ሆኖም ስለ ሁለተኛው “ኢሳያስ” መከሰት አንዳችም ታሪካዊ ምስክርነት የለም። ኖሮ
ቢሆን፤ መልእክቱም ሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ይዘቱ በጣም አስፈላጊ ስለሚሆን መጽሐፍ
ቅዱስ እርሱን አለመጥቀሱ እንግዳ ይሆን ነበር። በጣም ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ
አካል የሆነው የኢሳይያስ የቁምራን ጥቅል ቀርቶ፤ በኢሳ. 39 እና 40 መሃል እንኳን
ወደ አዲስ ጸሐፊ ሽግግር መደረጉን የሚያመለክት የሀሳብ መቆራረጥ የለም።
መሲሁን አዳኝ ጨምሮ ከሌሎች ኃይላት ይልቅ በእውነተኛው አምላክ ስለ
መታመን የሚናገረው የኢሳይያስ መሠረታዊ መልእክት በመላው የመጽሐፉ ገጾች
ስምሙ ይዘት አለው። ከኢሳ. ምዕ. 1 እስከ 39 ከተጠቀሰው የአሦራውያን ዘመን
አንስቶ በምዕ. 40 እና በቀጣይ በቀረበው የባቢሎን ዘመን ላይ ላተኮረው ሽግግር፤
ምሑራን በትክክል አጽንኦት ይሰጣሉ። ሆኖም ኢሳ. ምዕ. 13 እና 14 እንዲሁም
ምዕ. 39 ስለ ባቢሎን ምርኮ አስቀድሞ እንደሚተነብይ ተረድተናል። ኢሳ. 1-39
ስለ ፍርድ አጥብቆ መናገሩ እንዲሁም ከ40 እስከ 66--ስለ መጽናናት የበለጠ ዋጋ
መስጠቱ እሙን ነው። ነገር ግን ቀደም ባሉት ምዕራፎች መለኮታዊ መጽናናት እና
ማረጋገጫም እንዲሁ ተትረፍርፎ የቀረበ ሲሆን፤ በኋለኞቹ ማለትም በኢሳ. 42፡1825፣ ኢሳ. 43፡22-28 እና ኢሳ. 48፡1-11 ይሁዳ እግዚአብሔርን በመተዉ በእርሱ ላይ
ስለ ተሰጠ ፍርድ ይናገራል። የኢሳይያስ የወደፊት መጽናኛ ትንቢቶች በዚህ መሃል
የሚከሰተውን ሥቃይ ማካተታቸው እሙን ነው።
ምንም እንኳ በህዝቡ ኃጢአት የተነሳ አገሪቱ ከባድ ጥፋት ገጥሟት የነበረ
ቢሆንም፤ ከመሀላቸው አንዳንዶቹ በኢሳ. 26፡40-45 የሚገኙትን አምላካዊ
ተስፋዎች የሙጥኝ በማለታቸው ተስፋ አልቆረጡም ነበር። ጥቅሶቹን
በጥንቃቄ ያንብቡ። አገሪቱ በባቢሎን ሽንፈት ከገጠማት በኋላ በሕይወት
ከነበሩት ሕዝቦች አንዱ አድርገው ራስዎን ይቁጠሩ። በእነዚህ ቃላት ምን
ዓይነት ተስፋ ያገኛሉ?
በዘሌዋውያን መጽሐፍ በቀረቡት በእነዚህ ቁጥሮች ምን ዓይነት በሥራ ላይ
የዋለ መንፈሳዊ መርኀ ይመለከታሉ? እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ለእስራኤል
ምን እያለ ነው? ተመሳሳይ መርህ በእኛ ሕይወት ውስጥ የሚሠራው እንዴት
ነው?
በኢሳ. 49፡1-12 የቀረበው የእግዚአብሔር ባሪያ ማን ነው?
ከመወለዱ በፊት እግዚአብሔር ጠርቶ ስም ያወጣለታል፣ አፉን እንደ ሰይፍ ያዘጋጃል፣ በእርሱም ይከብራል። እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ የደኅንነት ብርሃንና ኪዳን እንዲሆን ብሎም እስረኞችን ነፃ ለማውጣትና እስራኤልን ወደ ራሱ ለመመለስ ባሪያውን ይጠቀምበታል። በዚህ እና ባሪያው በመሲህነት በተለየበት በኢሳ. 42 በቀረበው መግለጫ ብዙ ተደራራቢነት አለ። አዲስ ኪዳን የባሪያውን ባህሪ በሁለቱም የየሱስ ክርስቶስ ምጽአት ውስጥ ያገኘዋል፡ ማቴ. 1:21፣ ዮሐ. 8:12፣ ዮሐ. 9:5፣ ዮሐ. 17:1–5፣ ራእ. 1:16፣ ራእ. 2:16፣ ራእ. 19:15። ይህ ባሪያ--መሲህ ከሆነ እግዚአብሔር እዚህ ላይ ለምን “እስራኤል” ብሎ ይጠራዋል (ኢሳ. 49፡3)?
ቀደም ሲል በዚህ የኢሳይያስ ክፍል ጥናታችን እንዳገኘነው፣ የእግዚአብሔር ባሪያ “እስራኤል/ያዕቆብ” የሚጠቅሰው አገሪቱን ነበር። እዚህ ላይ ግን “እስራኤል” የሚለው ስም (ከ“ያዕቆብ” ጋር ትይዩ ያልሆነው ማጣቀሻ) በግልጽ የሚውለው አገሪቱን ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር ለሚመልሰው (ኢሳ. 49፡5) ግለሰብ ባሪያ ነው። ይህ ግለሰብ ባሪያ ውድቀታቸው መጠሪያ ስማቸውን “እስራኤል” ላጎደፈ-ተስማሚ አካል ወይም የሕዝቡ ተወካይ ሆነ (ኢሳ. 48፡1)። እዚህ ላይ ምን አዲስ ነገር ይታያል? ኢሳ. 49: 4፣ 7
ባሪያው ከሚያከናውናቸው ተግባራት ጋር በተያያዘ የሚገጥመው ችግር የመጀመሪያው
ምልክት እዚህ ላይ ቀርቧል። “ ‘እኔ ግን ዐላማ ሳይኖረኝ እንዲሁ ደከምሁ፤ ምንም
ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ነገር ጉልበቴን ጨረስሁ’ ” (ኢሳ. 49፡4) እያለ የሚያሰማው
የሰቆቃ ድምፅ በዳን. 9፡26 “ ‘መሲሑ ይገደላል ምንም አይቀረውም’ ” ከሚለው
ሀሳብ ጋር መስተጋብር ይፈጥራል። ነገር ግን በእምነት እንዲህ ይላል፡ “ ‘ሆኖም
ግን ብድራቴ በእግዚአብሔር እጅ፣ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው’ ” (ኢሳ. 49:4)።
በዚህ ዙሪያ ቅኝት ያደረጉት ጄ. አሌክ ሞቴር እንዲህ ይላሉ፡ “ኢሳይያስ አስቀድሞ
የተመለከተው እውነተኛ ሰብዓዊ ተፈጥሮ የነበረው ባሪያ፣ እንደ እኛ ተፈተነ፣
የእምነት መንገድ ደራሲና ፈጻሚ አድርጎ ራሱን አበረከተ፣ ምንም የሚረባ ነገር የሌለ
ሲመስል አምላኬ ብሎ ግላዊ እምነቱን በተጨባጭ አሳየ።”—The Prophecy of
Isaiah: An Introduction and Commentary (Downers Grove, Illinois: InterVarsity Press, 1993), p. 387.
ኢሳ. 49፡7 ያስደምማል። ባሪያው የተናቀና በሕዝብ የተጠላ የገዦች አገልጋይ
ቢሆንም ጌታ ግን እንዲህ ይለዋል፡ “ነገሥታት አይተውህ ይነሣሉ፤ ልዑላንም
አይተው፤ ይሰግዳሉ፤ ምክንያቱም የመረጠህ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር
ታማኝ ነው’ ”
መለስ ብለው ወደ ክርስቶስ አገልግሎት ይመልከቱ። እስከ መጨረሻው
ድረስ ተስፋ አስቆራጭ ምክንያቶች አልነበሩትም? ከውጪያዊ
ገጽታዎች በተቃራኒ እርሱ ግን በታማኝነቱ ጸና። ውጪያዊ ጫና
ቢኖርብንም እኛም ተመሳሳይ እንድናደርግ ከዚህ የምናገኘው ትምህርት
ምንድን ነው?
የየሱስ ፈውስ እና አስተምህሮ “በቅፍርናሆም” በሚል ኤለን
ኋይት ያቀረበችውን መግለጫ በዘመናት ምኞት መጽሐፍ ከገጽ 241- 252 ያንብቡ።
“ነፍስን የማሸነፍ ሥራ ታላቅ ዘዴ እና ጥበብ ይጠይቃል። አዳኙ ሁሌም በፍቅር
ከመናገር ውጪ እውነትን ተጭኖ አያውቅም። ከሌሎች ጋር በነበረው ግንኙነት ታላቅ
ዘዴ ይጠቀም የነበረው እርሱ፤ ሁሌም ደግ እና አስተዋይ ነበር። ከዚህ ውጪ ፈጽሞ
ግብዝ አልነበረም፣ አላስፈላጊ በሆነ ሁኔታ ኃይለኛ ቃል አልተናገረም፣ ለሐዘን ቅርብ
ለነበረው ነፍስ አላስፈላጊ ህመም አልሰጠም። ሰብዓዊውን ድክመት አልተጸየፈም።
ግብዝነትን፣ አለማመንንና ክፋትን በድፍረት አወገዘ። ሆኖም ይህን መራር ግሳጼ
ሲሰነዝር የዕንባው ሳግ በድምፁ ውስጥ ይሰማ ነበር።
እውነትን በደግነትና ርኅራኄ
አለስልሶ ለሰብዓዊው ፍጡር ከመንገር ውጪ ጨካኝ አድርጎ አቅርቦ አያውቅም።
እያንዳንዱ ነፍስ በፊቱ የከበረ ነበር። እርሱ በራሱ መለኮታዊ ክብር ተሸካሚ
ቢሆንም፤ ነገር ግን ማንነቱን ዝቅ አድርጎ እያንዳንዱን የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል
በርኅራኄ ተመለከተ። የእርሱ የሆነውን ወገኖችን የማዳን ተልዕኮ በሁሉም ነፍሳት
ውስጥ ተመለከተ።”—Ellen G. White, Gospel Workers, p. 117.
1.ክርስቶስ እንዴት ሌሎችን እንዳገለገለ የሚገልጸውን ከላይ የቀረበ
የኤለን ኋይት ጽሑፍ እንደ ክፍል ተመልከቱ። በመርኅዎቹ ላይ
ከተወያያችሁ በኋላ ቤተ ክርስቲያናችሁ እነዚህን መርኅዎች ምን ያህል
በትክክል እንደምታንጸባርቅ ተነጋገሩ።
2.“የተቀጠቀጠ ሸምበቆ” ወይም “የሚጤስ የጧፍ ክር” (ኢሳ. 42፡
3) ያውቃሉ? “ሳይሰበር” ወይም “ሳይጠፋ” ይህን ሰው ሊረዱት
የሚችሉት እንዴት ነው? እንደነዚህ ዓይነቶቹን ሰዎች ወደ ጌታ
ማመላከት የሚችሉት እንዴት ነው? ፈውስ እና እርዳታ በተጨባጭ
ማግኘት ይችሉ ዘንድ ምን እንዲያደርጉ ይነገሯቸዋል?
3.በኢሳይያስ መጽሐፍ የተለያዩ ደራሲዎች ዙሪያ የተነሱ የክርክር
ሀሳቦች መንስኤ፤ ሰዎች ኢሳይያስ በተናገረበት መንገድ የወደፊቱን
መናገር ካለመቻላቸው የመነጨ ነው። የዚህ ክርክር መሰረታዊ ችግር
ምንድን ነው? እንደ ክርስቲያን ይህንን መሠረተ ሀሳብ ሙሉ በሙሉ
መቃወም ያለብን ለምንድን ነው?
ማጠቃለያ፡ ለመዳን አዳኝ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ባሪያ ህዝብ በሁለት
አዳኞች አርነት ያገኛል፡ ምርኮኞቹን ከባቢሎን ቀንበር ነፃ የሚያወጣው
ቂሮስ እና ስኬታማ የመሲህ ማንነት በእርሱ የተገለጠው፣ ስሙ ያልተጠቀሰ
ባሪያ። ይህ ባሪያ ፍትሕን ይመልሳል ትሩፋን የማህበረሰብ አባላትንም ወደ
እግዚአብሔር መልሶ ያመጣል።