የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ኢሳ. 65:17– 25፣ ኢሳ. 66:1–19፣ ኢሳ. 66:19–21፣ ኢሳ. 66:21፣ ኢሳ. 66:22–24።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡- “ ‘እነሆ እኔ፣ አዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፣ ያለፉት ነገሮች አይታሰቡም፤ አይታወሱም።’ ” (ኢሳ. 65፡ 17)።
አ
ንድ ቀን፣ አንድ የ12 ዓመት ታዳጊ ወጣት የሥነፈለክ (የሕዋ ሣይንስ)
መጽሐፍ ካነበበ በኋላ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አሻፈረኝ አለ።
በሁኔታው ግራ የተጋቡት እናት ልጃቸውን ወደ ቤተሰባቸው ሐኪም ይዘው
ሄዱ። “ቢሊ፣ ጉዳዩ ምንድን ነው? ትምህርትህን ለማጥናትም ሆነ ወደ ትምህርት
ቤት ለመሄድ አልፈልግም ያልከው ለምንድን ነው?” ሲሉ ዶክተሩ ጠየቁት።
“ለዚህ ምክንያቱ ዶክተር” ካለ በኋላ ቢሊ ንግግሩን በመቀጠል “አንድ ቀን ፀሐይ
ነድዳ እንደምትጠፋና በምድር ላይ ያለ ሕይወት በሙሉ እንደሚወድም በዚህ
የሥነፈለክ መጽሐፍ በማንበቤ ነው። በመጨረሻ ሁሉም ነገር የሚጠፋ ከሆነ፣
ምንም ነገር የማድረግ ምክንያቱ አልታይህ አለኝ።”
አነጋገሩ የረበሻቸውና ራሳቸውን መቆጣጠር ያልቻሉት እናት “ይህ የአንተ ጉዳይ
አይደለም! አንተን እዚህ ውስጥ ምን ጥልቅ አደረገህ!” ብለው ጮኹበት።
ሐኪሙ ፈገግ አሉና “ግን ቢሊ፣ ይህ ሊያሳስብህ አይገባም፤ ምክንያቱም ይህ
የሚሆነው ሁላችንም ከሞትን ከረጅም ዘመን በኋላ ነው።” ሲሉ መለሱለት።
ያ የችግሩ ክፍል መሆኑ እርግጥ ነው፡ በመጨረሻ፣ በአይቀሬው ሞት ሁላችንም
ለህልፈተ ህይወት እንዳረጋለን።
ደስ የሚለው ነገር፣ የእኛ ህልውና በሞት ተደምድሞ አይቀርም። በተቃራኒው አዲስ
በተሠራችው ዓለም ህይወት ተሰጥቶናል፣ ዘላለማዊ ህይወት!
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ኢሳ. 65፡17-25። ወደ ቀደመው ደኅንነት መመለስን አስመልክቶ ጌታ በዚህ ስፍራ ምን ዓይነት ተስፋ ሰጥቶናል?
እግዚአብሔር በሚከተሉትን ቃላት በመጀመር ስለ አዲስ ፍጥረት ይናገራል፡ “እነሆ
እኔ፣ አዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፣ ያለፉት ነገሮች አይታሰቡም፤
አይታወሱም” (ኢሳ. 65፡17)። በዚህ አስደናቂ ትንቢት ጌታ “ኢየሩሳሌምን ለደስታ፣
ሕዝቧን ለሐሤት” (ኢሳ. 65፡18) እንደሚፈጥር ይናገራል። በዚህች ከተማ ከእንግዲህ
የልቅሶ ድምፅ አይሰማም (ኢሳ. 65፡19)። ሰዎች ቢያንስ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ
ይኖራሉ (ኢሳ. 65፡20)። በሥራቸውም ሆነ በልጆቻቸው ለረጅም ዘመን ደስ
ይሰኛሉ (ኢሳ. 65፡21-23)። እግዚአብሔርን ከመጣራታቸው በፊት ይመልስላቸዋል
(ኢሳ. 65፡24)።
ይህ የተባለው መልካም ቢሆንም፣ የመጨረሻውን የመዳናችንን ተስፋ
ሥዕል ያልያዘው ለምንድን ነው?
እስካሁን በቀረበው፣ የተስፋይቱ ምድር ሰላማዊ ህይወት ምስል ተሰጥቶናል። ምንም
እንኳ ሰዎች ረጅም ዕድሜ ቢኖሩም አሁንም ይሞታሉ። “አዲስ ሰማያት” እና “አዲስ
ምድር” በመፈጠራቸው የምንጠብቀው መሠረታዊ የተፈጥሮ ለውጥ የት አለ? ቀጣዩ
ቁጥር እንዲህ ይለናል “ተኩላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ
ሣር ይበላል፤ እባብ ትቢያ ይልሳል፤ በተቀደሰው ተራራዬም፣ ጉዳት አያደርሱም
ጥፋት አያመጡም” (ኢሳ. 65፡25)።
እንደ አንበሳ ያሉትን ሥጋ በል እንስሳት ወደ ሣር ተመጋቢነት ለመቀየር፣ ኃጢአት
በኤደን ከመተዋወቁ አስቀድሞ ወደ ነበረው ሁናቴ መመለስ፣ ዓለምን ዳግመኛ ወደ
ቀደመው ንጽህና ማምጣት ይጠይቃል።
በኢሳ. 65 እንደ ተመለከተው እግዚአብሔር “አዲስ ሰማያት” እና “አዲስ ምድር”
የመፍጠሩን ሂደት የጀመረው የሩሳሌምን ዳግመኛ በመፍጠር ነው። መሲሑ
ፍትሕ የሚያመጣበትን ኢሳ. 11 በንጽጽር ይመልከቱ (ኢሳ. 11፡1-5)። በመጨረሻ
“በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ” ላይ ሰላም ይሆናል። በኢሳ. 11 ጥቅም ላይ የዋለው
ሥዕላዊ አቀራረብ ከኢሳ. 65 ጋር ተመሳሳይ ነው፡ “ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል…
አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል” (ኢሳ. 11፡5-7)። ምንም እንኳን “የጌታ ቅዱስ
ተራራ” የሆነው የጽዮን ተራራ በየሩሳሌም የሚጀምር ቢሆንም፤ እግዚአብሔር
በመጨረሻ በአዲሲቱ ምድር ከተዋጁ ሕዝቦቹ ጋር አደርገዋለሁ ብሎ ቃል የገባው
ነገር ተቀዳሚ ተምሳሌት ነበር።
መሰረታዊው ሰብዓዊ ችግር አሁንም ያልተፈታ የሚመስለው ለምንድን
ነው? ጥልቅ ለሆነው ሰብዓዊ ፍላጎታችን ዘላለማዊ ሕይወት ብቸኛው
መልስ የሆነበት ምክንያቱ ምንድን ነው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ኢሳ. 66፡1-19። ኢሳይያስ መልእክቱን የጻፈበትን ጊዜ ሳንዘነጋ፤ በዚህ ስፍራ የሚያስተላልፈው መሰረታዊ መልእክት ምንድን ነው?
እግዚአብሔር በነቢዩ አማካይነት በመጽሐፉ ያቀረበውን ልመና እና ማስጠንቀቂያ
ይደግመዋል፡ እግዚአብሔር ለቃሉ የሚንቀጠቀጡ ትሑታንን በማዳን ወደ ቀደመው
ንጽህና ይመልሳቸዋል (ኢሳ. 2፣5)። በኢሳ. 40፡1 እንደ ተጠቀሰው ያጽናናቸዋል
(ኢሳ. 66፡13)። በእርሱ ላይ የሚያምጹትን ግን ያጠፋቸዋል። ይህ ደግሞ፣ እርሱ
መሥዋዕታቸውን የሚጠላውን የግብዞች ሥርዓታዊ አምልኮ (ያስተያዩ፡ ኢሳ. 66፡
3-4፣ ኢሳ. 1፡10-15) እና የእርሱን ታማኞች የሚጠሉና የሚቃወሙትን (ኢሳ. 66፡5)
ያካትታል። በተጨማሪ በየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ተፈጽመው የነበሩ ዓይነት (ሕዝ.
8፡7-12) አረማዊ እርኩሰቶችን (ኢሳ. 66፡17) ያካትታሉ።
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ኢሳ. 66፡3። ምን ይላል? በዚህ ስፍራ ምን ዓይነት
መንፈሳዊ መርኅዎች ተገልጠዋል? ተመሳሳይ ጽንሰ ሀሳብ፣ በዘመናዊው
ክርስትና እና አምልኮ ዐውድ የተገለጸው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር ሕዝቦችን ወደ ራሱ ለመሳብ እንደ ማግኔት ሆኖ የሚሠራው እንዴት ነው? ኢሳ. 66፡18-19
የጠላቶቹን መጥፋት ተከትሎ (ኢሳ. 66፡14-17) እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ
ማግኔት ወደ የሩሳሌም ለመሳብ ክብሩን ይገልጣል (ኢሳ. 2፡2-4)። በመካከላቸው
“ምልክት” ያኖራል። በዚህ ስፍራ በተለይ ባይቀርብም ነገር ግን በኢሳይያስ
የተጠቀሰው የመጨረሻ ምልክት በግልጽ እንደሚያመለክተው፡ እግዚአብሔር
ለሕዝቡ ደስታና ሰላምን ይሰጣል እንዲሁም ምድራቸውን ይመልሳል (ኢሳ. 55፡
12-13)። እግዚአብሔር ከጥፋት ውሃ በኋላ የቀስተ ደመና ምልክት ለኖኅ እንደ ሰጠ
ሁሉ፤ ከጥፋት በኋላ ሕዝቡን በማዳን ክብሩን መግለጹ እነርሱን ወደ ቀደመው
ንጽህና የመመለሱ ምልክት ነው (ዘፍ. 9፡13-17)።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ኢሳ. 66፡5። በቃሉ መንቀጥቀጥ ምን ማለት
ነው? ጌታ በቃሉ እንድንንቀጠቀጥ ለምን ይፈልጋል? እርስዎ በቃሉ
የማይንቀጠቀጡ ከሆነ፣ ይህ ስለ ልብዎ ሁኔታ ምን ሊል ይችላል?
የተረፉት--ሕዝቦችን ለጌታ ቁርባን አድርገው ከየአገራቱ የማምጣታቸው ፍቺ ምንድን ነው? ኢሳ. 66:19-20
ከእርሱ ፍርድ የተረፉ ሕዝቦች ስለ እርሱ ለማያውቁ ይመሰክሩ ዘንድ እግዚአብሔር
እስከ ምድር ዳርቻ ይልካቸዋል፡ “በሕዝቦችም መካከል ክብሬን ይናገራሉ” (ኢሳ. 66፡
19)። የወንጌል ተልዕኮን ለሌሎች ማድረስ በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ በጣም ግልጽ
ከሆኑ የብሉይ ኪዳን መግለጫዎች መካል ይህ አንዱ ነው። በሌላ አነጋገር፤ ሰዎች
ወደ ዕብራውያን ሕዝቦች መሳብ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከዕብራውያን አንዳንዶቹ
ወደ ሌሎች ሕዝቦች ሄደው ስለ እውነተኛው አምላክ ያስተምራሉ--ይህ በአዲስ
ኪዳን በግልጽ የቀረበ ምሳሌ ነው። ምንም እንኳ ከግዞት በመመለስ እና በክርስቶስ
ጊዜ (ማቴ. 23፡15) መሃል የአይሁድ ሚሲዮናዊ አገልግሎት ቢኖርም፤ የቀደሙት
ክርስቲያኖች ወንጌልን በፍጥነት እና በስፋት አሰራጭተዋል (ቆላ. 1፡ 23) ።
እስራኤላውያን የእህል ቁርባን ለጌታ በመቅደሱ እንዳመጡ ሁሉ፤ ሚሲዮናውያኑም
ቁርባን ይዘው በፊቱ ይቀርባሉ። ሆኖም ቁርባናቸው ሰዎችን ሁሉ ወደ እርሱ ማምጣት
ይሆናል (ኢሳ. 66፡20)። የእህል ቁርባን እንደ እንስሳ ታርዶ በፊቱ የሚቀርብ ስጦታ
እንዳልሆነ ሁሉ፤ ወደ ጌታ እንዲመጡ የሆኑት አዳዲስ ነፍሳትም እንዲሁ “ሕያው
መሥዋዕት” (ሮሜ 12፡1) ሆነው በፊቱ ይቀርባሉ። እጅግ ቀደም ባሉት ጊዜያት
ሌዋውያን እንዴት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አገልግሎት አሳልፈው ይሰጡ እንደ
ነበር ተመልክቷል። “ሌዋውያን የእግዚአብሔርን አገልግሎት ለማከናወን ዝግጁ
እንዲሆኑ ከእስራኤላውያን መካከል እንደሚወዛወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር
ፊት” (ዘኁ. 8፡11) ለአገልግሎት ይቀርቡ ነበር። ይህ ሰዎች ለእግዚአብሔር እንደ
መሥዋዕት ሆነው ሊቀርቡ ይችሉ የነበረበትን ጽንሰ ሀሳብ ለማስተዋል ይረዳል።
እግዚአብሔር “ካህናትና ሌዋውያን ይሆኑ ዘንድ አንዳንዶቹን
እመርጣቸዋለሁ” (ኢሳ. 66፡21) ሲል የሰጠው የተስፋ ቃል አንደምታ
ምንድን ነው?
እነዚህ ወገኖች ቀደም ሲል በቁ. 21 “ወንድሞቻችሁን ሁሉ” በሚል የተጠቀሱት
ናቸው። ከእነዚህ አንዳንዶቹ ከካህናትና ሌዋውያን በተጓዳኝ እግዚአብሔር የአምልኮ
መሪዎች አድርጎ የሚመርጣቸው ከአይሁድ ዝርያ ውጪ የሆኑ አሕዛብ ናቸው። ይህ
ሥር ነቀል ለውጥ ነው። እግዚአብሔር ቀደም ሲል በካህንነት እንዲያገለግል ሥልጣን
የሰጠው ለአሮን ትውልድ ብቻ ሲሆን፤ ሌዊ በመባል የሚታወቀው ጎሳ አባላት ደግሞ
ብቸኛ ረዳቶቻቸው ነበሩ። አሕዛብ በቀጥታ የአሮን ወይም የሌዊ ትውልድ መሆን
ባይችሉም፤ ነገር ግን ከእነርሱ መሃል አንዳንዶች በእነዚህ የኃላፊነት እርከኖች
እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ሥልጣን የሚሰጥበት ሁናቴ ነበር። ቀደም ሲል፣ ይህ
ለአንዳንድ አይሁዳውያን ሳይቀር የተከለከለ ነበር።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 1ጴጥ. 2፡9-10። ጴጥሮስ መልእክቱን የጻፈው
ለማን ነው ምን እያለ ነው? እንደ “ቅዱስ ሕዝብ” አባልነታችን
ለእያንዳንዳችን ያለው መልእክት ምንድን ነው? ከእነዚያ ቀደምት
ሕዝቦች የሚበልጠውን እያደረግን ነው (ዘፀ. 19፡6)?
“የመንግሥት ካህናትና የተቀደሰ ህዝብ” (ዘፀ. 19፡6) የነበሩትን እስራኤላውያን የአምልኮ መሪዎች ሆነው የሚወክሏቸው የተለዩ ካህናት ተመድበው ነበር። ወደፊት ግን፣ ከአሕዛብ መካከል አንዳንዶች የአምልኮ መሪዎች ይሆናሉ (ኢሳ. 66፡21)። ይህ ለውጥ ተሐድሶ ባገኘው የእምነት ማህበረሰብ ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ያሳድራል? ማቴ. 28፡19፣ ሐዋ. 26፡20፣ ገላ. 3፡28፣ ቆላ. 3፡11፣ 1ጢሞቴ. 3፡16.
በአምላካዊው “አዲስ የዓለም ሥርዓት” አሕዛብ የእግዚአብሔርን ሕዝብ መቀላቀል ብቻ ሳይሆን፣ “ንጉሣዊ ክህነት” በሚያጎናጽፋቸው በተጣመረ የእምነት ማኅበረሰብ ከአይሁድ ጋር እኩል አጋር ይሆናሉ። ስለዚህ በአይሁድና በአህዛብ መካከል ያለው ልዩነት ምንም የሚባል ዓይነት ይሆናል። ይህ የኢሳይያስ ትንቢት ፍጻሜ ያገኘው መቼ ነበር?
የአሕዛብ ሚስዮናዊ የሆነው ጳውሎስ እንዲህ ሲል በይፋ ተናግሯል፡ “በአይሁድና
በግሪክ… መካከል ልዩነት የለም፤ ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ናችሁ።
የክርስቶስ ከሆናችሁ፣ እናንተ የአብርሃም ዘር ናችሁ፤ እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች
ናችሁ” (ገላ. 3፡28-29)።
የተስፋ ቃሉ ወራሾች መሆን እና ከዚያም በከበረ “የንጉሥ ካህናት” ስፍራን መቀዳጀት፤
ለተጣለብን አደራ የርካታ ቁንጮ ላይ መድረሳችንን የሚያሳይ ሳይሆን ነገር ግን
ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራንን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እያወጅን
(1ጴጥ. 2፡9፣ ኢሳ. 66፡19) አይሁዳውያንን እንድንቀላቀል የተሰጠን ተልዕኮ ነው።
እግዚአብሔር ለአይሁዳውያን የሰጠውን ሽልማት አሕዛብን ከፍ ከፍ በማድረግ
በተመሳሳይ ለእነርሱም መስጠቱ ፍትሐዊ አይደለም ብለው አይሁዳውያን
የሚያጉረመርሙበትን መብት አልሰጠም። እንዲሁም አሕዛብ አይሁድ
ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን በንቀት የሚመለከቱበት መብት አልሰጠም።
በመጀመሪያ “የእግዚአብሔር ቃል በዐደራ የተሰጠው” የአምላካዊው መገለጥ
መተላለፊያ መስመር ሆነው ላገለገሉት አይሁዳውያን ነው (ሮሜ. 3፡2)። ጳውሎስ
የሚከተለውን ለአሕዛብ ጽፏል፡ “ከቅርንጫፎቹ አንዳንዶቹ ቢሰበሩ፣ አንተም
የበረሓ ወይራ ሆነህ ሳለ በሌሎቹ ዘይት ሥር የሚገኘውን በረከት ተካፋይ ከሆንህ፣
በእነዚያ ቅርንጫፎች ላይ አትኩራራ። ብትኩራራ ግን ይህን አስተውል፤ አንተ ሥሩን
አትሸከምም፤ ሥሩ ግን አንተን ይሸከምሃል እንጂ” (ሮሜ 11፡17-18)።
ማንኛውም ዓይነት መንፈሳዊ፣ ጎሳዊ ወይም ደግሞ ዕውቀት፣ ሐብት፣
ችሎታ፣ ልምድ--በመስቀሉ ብርሃን፣ በወንጌል ብርሃን ተልዕኮ ሲታይ
አጸያፊ የሆነው ለምንድን ነው? እስቲ ወደ ራስዎ በጥልቀት ይመልከቱ፡
የትኛውም ዓይነት የመንፈሳዊ ወይም የብሔር የበላይነት እየተሰማዎት
ነው? እንዲያ ከሆነ ንስሐ ይግቡ!
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ኢሳ. 66፡22። ጥቅሱ ምን እያለን ነው? በዚህ ስፍራ የምናገኘው ተስፋ ምንድን ነው?
በኢሳይያስ መጽሐፍ ከምናገኛቸው እጅግ አስደናቂ ተስፋዎች አንዱ ኢሳ. 66፡ 22 ነው። ጥቅሱን በጥንቃቄ ያንቡት። አዲስ በሆኑት ሰማያትና አዲስ በሆነችው ምድር ስማችን እና ዘራችን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። ከእንግዲህ መወገድ፣ ተቆርጦ መጣል፣ ለመዳቀል መጣበቅ፣ መቀንጠስ ወይም መነቀል አይኖርም። ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባከናወነልን ነገር የተነሳ የክርስትና እምነታችን የመጨረሻና የተሟላ ፍጻሜ በሚያገኝበት--በዚህች ኃጢአት፣ ሞት፣ ሥቃይ በሌለባት አዲስ የተሠራች ምድር እነሆ የዘላለም ሕይወት ተስፋ አለን። በኢሳ. 66፡23 እንደ ተመለከተው፤ የወር መባቻና ሰንበት ከአዲስ ሰማያትና ምድር ምስል አኳያ የቀረቡት ለምንድን ነው?
ምንም እንኳን ይህን አስቸጋሪ ጥቅስ መመልከት የሚቻልባቸው ብዙ መንገዶች
ቢኖሩም፤ አንዱ አካሄድ የሚከተለው ነው፡ እግዚአብሔር ሰንበትን የፈጠረው
የመሥዋዕት ሥርዓት ከመፈጠሩ አስቀድሞ ነው (ዘፍ. 2፡2-3)። ስለዚህ ሰንበታት
በሜዳዊው ሥርዓት አምልኮ ይከበሩ የነበረ ቢሆንም፣ የሥርዓቶቹ ጥገኞች ግን
አልነበሩም። በዚህ የተነሳ ከዘመናት አንስቶ እስከ አዲሲቱ ምድር ሳይቋረጡ
የሚዘልቁ ለመሆን በቅተዋል። አዲስ ጨረቃዎች ወይም የወር መባቻዎች
ከመሥዋዕት ሥርዓቱ ተነጥለው ሕጋዊ የአምልኮ ቀናት የሆኑባቸውን አጋጣሚዎች
መጽሐፍ ቅዱስ አያመለክትም። ምናልባት ከሕይወት ዛፍ ወርሃዊ ዑደት ቁርኝት
አኳያ (ራእ. 22፡2) በአዲሷ ምድር የአምልኮ ቀናት ሊሆኑ ይችላሉ (እንደ ሰንበት
የእረፍት ቀናት ሳይሆኑ)።
የኢሳ. 66፡23 ፍቺ ምንም ይሁን ምን፣ ወሳኙ ነጥብ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እርሱን
ለዘላለም ማምለካቸው ይመስላል።
የዳኑት ሰዎች በእግዚአብሔር የጠፉትን ዐመጸኞች ሬሳ በሚመለከቱበት
በዚህ አሉታዊ ገጽታ ባለው መልእክት የአሳይያስ መጽሐፍ ለምን
ተደመደመ? (ኢሳ. 66፡24)
ኢሳይያስ ከባቢሎን ጥፋት የሚተርፉ ታማኞችን እና የሚያምጹትን ይኸውም
የሚደመሰሱትን የማነጻጸር ስሌት በመሥራት ለዘመኑ ሕዝቦች ጉልህ ማስጠንቀቂያ
ይሰጣል። ይህ ዘላለማዊ ሥቃይ ስላልሆነ ያመጹ ሞተዋል፣ የማውደም ሥራውን
ሠርቶ እስኪጨርስ በማይጠፋው “እሳት” ተገድለዋል። ይህ ደግሞ የሩሳሌም ዳግም
መፈጠር እንድትጀምር ያስችላታል።
የኢሳይያስ ማስጠንቀቂያ ነጥቦች በራእይ መጽሐፍ የተተነበየውን የመጨረሻ ትንቢት
ፍጻሜ ያመለክታሉ፡ በኃጢአተኞች እና በሰይጣን ላይ የሚደርሰውን የመጨረሻ
ውድመትና በእሳት ባሕር የመጣል ሞት (ራእ. 20)፣ ከዚያ በኋላ እውን የሚሆነው
“አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር”፣ ቅድስቲቱ “አዲሲቱ ኢየሩሳሌም”፣ እንባ ወይም
ህመም አለመኖሩ፣ “ ‘የቀደመው ሥርዓት’ ” ማለፉ (ራእ. 21፡1-4፣ ኢሳ. 65፡17-19)፣
በዘላለማዊ ህይወት ከምድር የተዋጁ ሁሉ አዲስ ማንነት ማግኘታቸው…።
በመጨረሻ ገቢራዊ በሚሆነው በምድር ከኃጢአት መንጻት ዙሪያ
የተጻፉትን የሚከተሉትን የኤለን ኋይት መልእክቶች ያንብቡ፡ “The Controversy
Ended,” in The Great Controversy, pp. 662–678.
“ዘላለማዊዎቹ ዓመታት በተገለጡ ቁጥር በአምላካዊው ማንነት ዙሪያ ይበልጥ የከበሩና
በላቀ ክብር የተሞሉ መገለጦችን ይዘው ይመጣሉ። ዕውቀት በማያቋርጥ የዕድገት
ግስጋሴ ውስጥ እንደመሆኑ ሁሉ፤ ፍቅር፣ አምልኮ እና ደስታም እንዲሁ እየጎለበቱ
ይሄዳሉ። ሰዎች ስለ እግዚአብሔር በተማሩ ቁጥር አብልጠው ባህሪውን የሚያደንቁ
ይሆናሉ። የሱስ የመዋጀትን ሙላት በፊታቸው ሲከፍትላቸው እና ከሰይጣን ጋር
ለነበረው ታላቅ ውዝግብ ያስመዘገበውን አስደናቂ ክንዋኔ ሲገልጽላቸው፤ እነዚህ
የከበረ ዋጋ የተከፈለላቸው ወገኖች፤ ከፍ ባለ የጋለ አምልኮ ሐሴት ያደርጋሉ፤ የወርቅ
በገናዎቻቸውን ያነሣሉ። አሥር ሺ ጊዜ አሥር ሺ እና ሺ ጊዜ ሺ ድምፆች እጅግ ገናና
የሆነውን የምስጋና አዝማች ይዘምራሉ።
“ ‘በሰማይና በምድር፣ ከምድር በታችና በባሕር፣ በእነርሱ ውስጥ ያሉ ፍጡራንም
ሁሉ እንዲህ ብለው ሲዘምሩ ሰማሁ፤ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉ፣ ምስጋናና
ሞገስ፣ ክብርና ኀይል፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን።’ ራእ5፡13።
“የታላቁ ተጋድሎ ምዕራፍ ተዘግቷል። ኃጢአትና ኃጢአተኞች ከእንግዲህ የሉም።
ዩኒቨርስ ጸድቶአል። ለዛ ያለው ስምምነትና የደስታ ድባብ የተጎናጸፈ አንድ ዓይነት
ትርታ በመላው ፍጥረት ውስጥ ይደመጣል። ሁሉን ከፈጠረው ከእርሱ ወሰን
የሌለው ግዛት--ህይወት፣ ብርሃን እና ደስታ ይመነጫል። ኢምንት ከሆነችው የአቶም
ቅንጣት እስከ ግዙፉ ዓለም--ሁሉም ሕይወት ያላቸውና የሌላቸው ነገሮች ባልተጋረደ
ውበታቸውና ፍጹም ደስታቸው--እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን ያውጃሉ”—Ellen
G. White, The Great Controversy, p. 678.
1.በአዲስ ሰማይና ምድር የተዘጋጀልን የዘላለማዊ ሕይወት የተስፋ ቃል
ለክርስቲያናዊ እምነታችን መሠረት የሆነው ለምንድነው? ያለዚህ ተስፋ
እምነታችን ምን ያህል መልካም ሊሆን ይችላል?
2.ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ጴጥ. 3፡10-14። ጥቅሶቹ በኢሳ. 66 የቀረቡትን
ጽንሰ ሀሳቦች በተመሳሳይ የሚያንጸባርቁት እንዴት ነው?
ማጠቃለያ፡ ኢሳይያስ አስገራሚ ስፋትና ጥልቀት ያለው ራእይ ያቀርብልናል።
እግዚአብሔር የእምነት ማኅበረሰቡን ማንጻትና ወደ ቀደመው ንጽህና
መመለስ ብቻ ሳይሆን ድንበሩን ወደ ሁሉም ብሔራት የማስፋፋት ሥራ
ይሠራል። የእርሱ ማኅበረሰብ እንደገና መፈጠር ውሎ አድሮ ወደ ምድር
ዳግም መፈጠር ይመራል። እነሆ አምላካዊው ህልዎት ለሕዝቡ የመጨረሻ
ምቾት ያመጣል።