
ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ገላ. 3:19፣ ዘዳ. 16:15፣ ዘፀ. 25:10–30:38፣ ገላ. 5:22–26፣ መክ. 9:10፣ 1ቆሮ. 10:31።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡“ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፡፡” (1ቆሮ. 15፡58)
ሥ
ራ ከእግዚአብሔር የመነጨ ሀሳብ ነው። ከኃጢአት አስቀድሞ በነበረው
ተምኔታይ እና ተስማሚ ዓለም አዳምና ሔዋን የአትክልት ስፍራውን
እንዲንከባከቡና እንዲያለሙ እግዚአብሔር ሥራ ሰጥቶአቸው ነበር (ዘፍ. 2፡15)።
በአምሳሉ እንደ ሠራቸው ፈጣሪ--እነርሱም ሀሳብ የማመንጨት ችሎታ የታከለበት
ሥራ እና የፍቅር አገልግሎት መስጠት ነበረባቸው። ይህ ማለት በዚያ ኃጢአት
በማያውቀው፣ ሞት ባልነገሠበት፣ ሥቃይና እንግልት ዘበት በሆነበት ያልወደቀ ዓለም
እንኳ፤ ሰው በሥራ ገበታ መሰየም ነበረበት።
በዚህ መሃል ላይ ባሉት ጊዜያት (ተስማሚ ከነበረው ዓለም በኋላ እና ከተስፋይቱ
ዓለም አስቀድሞ) ሥራን ከእግዚአብሔር በረከቶች እንደ አንዱ እንድንመለከት
ተጋብዘናል። የአይሁድ ማኅበረሰብን ብንመለከት እያንዳንዱ ልጅ የንግድ ሥራ
እንዴት መሥራት እንዳለበት ሥልጠና ይሰጠዋል። እንደውም በዚህ ዙሪያ አንድ
ብሂል አላቸው፡ አባት ልጁን የንግድ ሥራ ያስተምራል--ያለበለዚያ ግን ውሎ አድሮ
ወንጀለኛ ያፈራል!--የሚል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የእግዚአብሔር ልጅ የሱስ
በታማኝነት እየሠራና፣ የእርሱን የሰማያዊ አባቱን ፈቃድ እየፈጸመ በዕደ ጥበብ ሙያ
ብዙ ዓመታት አሳልፎአል። ለናዝሬት ነዋሪዎች አስፈላጊውን የቤት ቁሳቁስ እና የእርሻ
መሣሪያ እየሠራ ሳያቀርብ እንዳልቀረ ይገመታል (ማር. 6፡3)። ይህ የሥራ ክፍል
ወደፊት ለሚጠብቀው አገልግሎት የሥልጠናው አንዱ አካል ነበር። ሐዋርያው
ጳውሎስ በየሰንበቱ በምኩራብ የአይሁድ እና ግሪክ ሰዎችን ለማሳመን ጥረት ያደርግ
በነበረበት ወቅት ከአቂላ እና ጵርስቅላ ጋር ተቀምጦ ድንኳን እየሠፋ ለአንድ ዓመት
ተኩል ቆይቶአል (ሐዋ. 18፡1-4፣ 2ተሰ. 3፡8-12)። በዚህ ሣምንት በአጠቃላይ ከሥራ
ጋር የተጎዳኘ ጥያቄ በክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የሚጫወተውን ሚና
እንመለከታለን።
“ለሰዎች፣ በሕይወት እያሉ ደስ ከመሰኘትና መልካምን ነገር ከማድረግ የተሻለ ነገር
እንደሌለ ዐወቅሁ። ሰው ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፣ በሚደክምበትም ሁሉ ርካታን
ያገኝ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ችሮታ ነው።” (ምሳ. 3፡12-13)።
“ሥራ” የተሰኘው ቃል ብዙ ትርጉሞች አሉት፡ ሌማቱን ሙሉ ገበታውንም የተትረፈረፈ
ለማድረግ፣ የፍጆታ ክፍያዎቻችንን ለመክፈል እና ለችግር ጊዜ የሚሆን አነስተኛ
ገንዘብ ለመቆጠብ--የመሳሰሉ። ሥራ ማጣት ከእጅ ወደ አፍ ሠርቶ ከመግባትም
በላቀ የከፋ ነው።
ሥራ አንድን ሰው ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ሊያደርግ ይችላል። “ምን እያደረክ
ነው?” በሚል ለሚቀርብ የተለመደ ጥያቄ--ሥራ ሁሉን ሊያግባባ የሚችል መልስ
የሚሰጥበት መንገድ ነው። አብዛኞቹ በጡረታ ዘመን ያሉ ሰዎች እስከ ቻሉ ድረስ
በበጎ ፈቃደኝነትም ሆነ በክፍያ መለስተኛ ሥራ መሥራታቸውን ይቀጥላሉ። በሥራ
ገበታ ላይ መሆን ማለዳ የመነሣት ዕድል ይፈጥራል። ለታዳጊው ወጣት ሥራ
በመስጠት በውስጡ ኃላፊነት የመወጣት ተነሳሽነት ይፍጠሩ።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 3፡19። የመልእክቱ ዐውድ ምንድን ነው?
ስለ ሌላኛው የሥራ ገጽታስ ምን ይነግረናል?
ከውድቀት አስቀድሞ የተሰጠው ሥራ በድንገት ከውድቀት በኋላ ተለወጠ። ስለ ሌላው
ዓይነት የሥራ ጎን አንዳንድ መረጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል። ለአንዳንዶች ሥራ
ማለት የሞቱ ዕለት የሚያከትም የማያስደስት የዕለት ከዕለት መማሰን ብቻ ነው።
ጤናቸው ሳይታወክ አንድ ቀን ጡረታ እንደሚወጡ ተስፋ እያደረጉ የሚንቁትን
ሥራ እየሠሩ የሚኖሩም አሉ። ሌሎች ደግሞ ሥራን የህልውናቸው መሠረት እና
የዙሪያ ማንነታቸው መገለጫ ምንጭ አድርገው ከመውሰዳቸው የተነሳ መላው
ሕይወታቸውን ሳይቀር እስከ መቆጣጠር ሊደርስ ይችላል። እንደነዚህ ዓይነቶቹ
ሰዎች ከሥራቸው ሲርቁ የጭንቀት ወይም ግራ የመጋባት ስሜት ስለሚሰማቸው
ምን ማድረግ እንዳለባቸው ወይም ወዴት እንደሚሄዱ እንኳ አያውቁም። የጡረታ
ጊዜአቸው ሲደርስ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ሊገጥማቸው ብሎም ያለ
ጊዜአቸው ሊሞቱ ይችላሉ።
ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው እንዴት መሥራት እንዳለባቸው
መማር ይኖርባቸዋል። ሥራ ከኢኮኖሚያዊ ፍላጎት የላቀ ነው። ሰው ባለ ሥራ
ከመሆን በላይ ነው። በትክክል እንደሚስተዋለው የአንድ ሰው የሕይወት ሥራ ከጌታ
ጋር ያለው ግንኙነት መገለጫ፣ የአገልግሎት ጎዳና ነው። ከመምህሩ ሥራ አንዱ
የተማሪዎችን ችሎታ እና ተሰጥኦ ዓለም ከሚያሻው ነገር ጋር በማገናኘት ማገዝ ነው።
ሥራዎ ምንድን ነው? ማለትም--ህይወትዎን ምን እየሠሩበት ነው?
በሥራዎ ጌታን በተሻለ ማክበር የሚችሉት እንዴ ነው?
ሥራ የሕይወት ተግባር ከማከናወን ጋር የተቆራኘ ነው። የኮምፒውተር ቁልፍ ከመነካካት ጋር ብቻ ተዛምዶ ያላቸው የአእምሮ ብቃት የሚጠይቁ ሥራዎችን የሚሠሩ ሰዎችም ቢሆኑ እንኳ፤ አነሰም በዛም በጉልበት ሥራ ውስጥ ማለፋቸው አይቀሬ ነው። እጅ የሥራ ተምሳሌት ሆኖ የቀረበባቸው የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ ሥራ ምን ያስተምሩናል? ዘዳ. 16:15
መክ. 9:10
ምሳ. 21:25
ኤር. 1:16
እርካታ እና ደስታ ማግኘት እንችል ዘንድ እግዚአብሔር በእጆቻችን የምንሠራቸውን
ሥራዎች ሰጥቶናል (ምሳ. 10፡4፣ 12፡14)። በሥነ ልቦናው ዘርፍ “ግላዊ ብቃት”-እያንዳንዱ ሰው በሕይወቱ ውስጥ ትርጉም ያለው ነገር የማከናወን ችሎታ አለው
የሚለውን እምነት ይገልጻል። ግላዊ ብቃት የሚያድገው “ይህን ማድረግ እችላለሁ!”
እያሉ በተደጋጋሚ በመናገር ሳይሆን፤ ግላዊ ብቃትን ሊያጎለብት የሚችልን ነገር
በማድረግ ብቻ ነው።
“የእጆቻችን ሥራ” እግዚአብሔር እኛን የባረከበት መንገድ (መዝ. 90፡17) በመሆኑ
ትርጉም ያለው ህይወት እንድንኖር ይፈቅድልናል። የእግዚአብሔር የመጨረሻው
ዓላማ ሌሎች “በእጆቻችን ሥራ” ይባረኩ ዘንድ ነው። ጳውሎስ በእርግጥም ይህን
መርኅ ተከትሎ ኖሮአል።
“እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ
ራሳችሁ ታውቃላችሁ። በጉልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን
ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለውን
የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ” (ሐዋ. 20፡34-35)።
የነህምያ ቀለል ያለ ጸሎት የእኛም ሊሆን ይገባል፡ “እኔ ግን አሁንም እጄን አበርታ ስል
ጸለይኩ” (ነህ. 6፡9)።
ስለ ሥራዎ ያለዎት አመለካከት ምን ይመስላል? በምን ዓይነት መንገድ
ተጠቅመው ሥራዎን ይበልጥ ለሌሎች በረከት ማድረግ ይችላሉ?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፀ. 25፡10-30፣ 38። ሙሴ ለአምልኮ የሚውለውን የመገናኛ ድንኳን እንዲሠራ እግዚአብሔር ሲጠይቀው ምን ያህል በቂ መረጃ ሰጥቶታል? ይህ ስለ እግዚአብሔር ባህሪ ምን ይነግረናል?
እግዚአብሔር ማደሪያ እንዲሠራለት ለሙሴ ሲነግረው ሙሴ፡ “ምንም ችግር
የለም ጌታ! ከግብፅ ከኮበለልኩ ጀምሮ ላለፉት 40 ዓመታት ድንኳን ስተክል ነው
የኖርኩት… ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ስጠኝ” ሊለው ይችል ነበር። በከፊል አርብቶ
አደር በነበሩት ሜዲዮናውያን ባህል ውስጥ ለኖረ የዚያ ዘመን ማንኛውም ሰው
ድንኳን ሠርቶ መትከል እጅግ ቀላል ከመሆኑ የተነሳ ዐይኖቻቸውን ጨፍነው እንኳ
ሊሠሩት የሚችሉት ነገር ነበር። በእርግጥ ሙሴ እንደዚያ ያለውን በጥንቃቄ የቀረበ
የግንባታ ንድፍ እንዲሁም 150 ገደማ የሚሆኑ ነጥብ በነጥብ የቀረቡ የካኅኑን ልብሰ
ተክህኖ ጨምሮ በውስጡ የሚገኝ እያንዳንዱ ቁስ እንዴት እንደሚሠራ የሚገልጥ
ሰፊ ዝርዝር ፈጽሞ ሊጠብቅ አይችልም። ሙሴ ቀለል ያለውን ጠረጴዛ ለመሥራት
እንኳ ባለ ሰባት ቅደም ተከተል የመገጣጠሚያ የሥራ ሂደቶች ማለፍ ነበረበት (ዘፀ.
25፡23-30)።
እግዚአብሔር ለመገናኛ ድንኳኑ ግንባታ ዝርዝር የሥራ ሂደት ያሳየው ታላቅ
ትኩረት--ለላቀ ሥራ ያለውን የተሟላና ከፍተኛ የችሎታ መንፈስ ያሳያል። ለግንባታ
ሥራ የዋሉት ግብአቶች ምርጥ ጥራት የነበራቸው፣ የግንባታው ንድፍ እንከን የለሽ፣
አሠራሩ ድንቅ በመሆኑ “በእግዚአብሔር ዘንድ ዝርክርክ ሥራ ተቀባይነት የለውም!”
የሚል መርኅ ያነገበ ነበር።
የግንባታ ሥራው ላቅ ያለውን ደረጃ የጠበቀ ይሆን ዘንድ ንድፉና የግንባታ ግብአቱ
ብቻ ሳይሆን የሰው ኃይል ምልመላውም ጭምር የተካሄደው በራሱ በእግዚአብሔር
ነበር። ለሥራው ተፈላጊ ሙያ እና ችሎታ እየሰጠ የመረጣቸው ራሱ እግዚአብሔር
እንደ ነበር በዘፀ. 31፡1-5፣ 35፡30-36፡1 እናነባለን። የመገናኛ ድንኳኑ እና በውስጡ
የሚኖሩ ቁሳቁሶች ግንባታ “እግዚአብሔር እንዳዘዘው” (ዘፀ. 36፡1) መሠራቱ
ይቀጥል ዘንድ እነዚህ ሰዎች በሁሉም ዓይነት የዕደ ጥበብ ሥራ ችሎታ እና ዕውቀት
“በእግዚአብሔር መንፈስ የተሞሉ” ነበሩ። በተጨማሪ ሁለት በሥራው የተካኑ
የንድፍ ባለሙያ ግለሰቦች ዕውቀት እና ችሎታ--የእስራኤላውያኑ ማኅበረሰብ አካል
ሆኖ ይዘልቅ ዘንድ “ሌሎችን የማስተማር ችሎታ” (ዘፀ. 35፡34) ተሰጥቶአቸው ነበር።
ምንም እንኳ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች በታሪኩ ውስጥ እግዚአብሔር የመረጣቸው
ባለሙያ የሥራ መሪዎች ሆነው ቢቀርቡም፤ ሌሎች ሰዎችም ተመሳሳይ ስጦታዎችን
እየተቀበሉ ሥራውን ተቀላቅለዋል (ዘፀ. 36፡2)
ስለሆነም የሰብዓዊው ፍጡር በኃጢአት መውደቅ ማንኛውንም ኃላፊነት
በለብ ለብ ወይም በግብር ይውጣ ለማቅረብ ምክንያት ሊሆነው አይችልም።
እግዚአብሔር--ሁሉንም ዓይነት ምርጥ ስጦታችንን፣ ችሎታችንን፣ ጊዜአችንን
እና ዕውቀታችንን ለታላቅ ዓላማ ስናውል ለመመልከት ሁሌም ይናፍቃል።
“በመንፈስ የምንኖር ከሆን፤ በመንፈስ እንመላለስ” (ገላ. 5፡25)። የአንድ ሰው ሥራ
እና መንፈሳዊነት የማይነጣጠሉ ናቸው። ክርስትና አንድ ሰው ሰሜቱ በተቀያየረ
ወይም በተለያዩ የሕይወት ምዕራፎች ባለፈ ቁጥር የሚያወልቀው ወይም የሚደርበው
ካባ አይደለም። ይልቁንም ክርስትና ሥራን ጨምሮ በፈርጀ ብዙ የኑሮ ዘርፍ ተገልጦ
የሚታይ አዲስ ስብዕና ይፈጥራል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ገላ. 5፡22-26። ጳውሎስ ከገለጻቸው ስጦታዎች
መሃል እርስዎን እና ሥጦታን ጭምር የሚገልጹት የትኞቹ ናቸው?
ዘ ኤክስፖዚቶሬ ዲክሸነሪ ኦቭ ኒው ቴስታመንት በመባል የሚታወቀው መዝገበ
ቃላት የአንድ ሰውን “መንፈሳዊነት” ሲገልጽ “የመንፈስን ፍሬዎች በራሱ መንገድ
የሚገልጽ” ሲል ያስቀምጣል። ከዚህ ተነስተን--እኛ ሰብዓዊ ፍጡራን ከክርስቶስ
ጋር ባለን ግንኙነት በዘርፈ ብዙ የሕይወት ምዕራፎች እንደ አማኞች እንንቀሳቀሳለን
የሚል ድምዳሜ ላይ መድረስ እንችላለን።
በፍሎሪዳ ሆስፒታል በሞት አፋፍ የነበረን አንድ በሽተኛ የቅርብ ጓደኛው አጠገቡ
ሆኖ ነቅቶ እየተጠባበቀው ነበር። ነርሶች በሽተኛው የሚያስፈልገውን ለማሟላት
በፍጥነት ወደ ክፍሉ ይገቡና ይወጡ ነበር። በመራወጥ ላይ የነበሩትን ነርሶች
ለማናገር አጥብቆ የፈለገው የበሽተኛው የቅርብ ጓደኛ፤ እንደ ምንም ብሎ የሕክምና
ሥልጠና የት እንደ ወሰዱ ጠየቃቸው። አብዛኞቹ በፍሎሪዳ ሆስፒታል ኮሌጅ እንደ
ተማሩ ነገሩት።
ይህ ሁኔታ በበሽተኛው ጓደኛ ላይ ትልቅ ተጽእኖ መፍጠሩን ተከትሎ፤ ከዚህ በኋላ
በፍሎሪዳ ሆስፒታል ኮሌጅ ተደጋጋሚ ጉብኝት አደረገ። ለምን? ምክንያቱም
በዚህ ኮሌጅ የሰለጠኑ ነርሶች እርሱ ካያቸው በሌሎች ስፍራዎች ስልጠና ከወሰዱ
ይልቅ በሞት አፋፍ ለነበረ ጓደኛው ያላሰለሰ ርኅራኄና በፍቅር የተሞላ እንክብካቤ
አድርገዋል። በሞት አፋፍ ለነበረ ጓደኛው የነበራቸውን አመለካከት አስመልክቶ
በእነርሱ እና በሌሎች መሃል ትልቅ ልዩነት መመልከት ችሎ ነበር።
ስለ ኮሌጁ እና ተልዕኮው አያሌ ጥያቄዎች ከጠየቀ በኋላ በመጨረሻ እርሱ እንዳያቸው
ዓይነት ሌሎች ተጨማሪ ነርሶች ሥልጠና እንዲያገኙ የሚረዳ የአንድ መቶ ሺህ ዶላር
እርዳታ ለኮሌጁ አበርክቶአል። አዎ፤ መንፈሳዊነት የሕይወት መንገድ ነው።
በዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎ የገዛ መንፈሳዊነትዎን የሚያሳዩበት መንገድ
ምን ይመስላል? ምን ዓይነት ተጽእኖ ያደረጉ ይመስሎታል? (ውሎ
አድሮ ተጽእኖ ማድረግዎ አይቀሬ በመሆኑ)
“እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ ሥራው” (መክ. 9፡10)። በጣም
ብልህ የሆኑ ሰዎች መጋቢነትን የተመለከቱትን እነዚህን ምክረ ቃላት በእያንዳንዱ
የሕይወት ፈርጅ ጥቅም ላይ ያውላሉ።
በክርስቲያን መጋቢነት ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ሲጠየቅ፤ ብዙዎች ከክርስቲያናዊው
የገንዘብ አያያዝ ኃላፊነት ጋር ያቆራኙታል። ምንም እንኳ ገንዘብ የመጋቢነት አስፈላጊ
ገጽታ ቢሆንም፤ በገንዘብ ብቻ እንዲወሰን ማድረግ ነገሩን በጣም አጥብቦ ማየት
ይሆናል። በድርጅታዊ ጽንሰ ሀሳብ መሰረት መጋቢነት--ሁሉንም ተጨባጭ ሐብቶች
ማበልጸግ እና በአግባቡ ሥራ ላይ የማዋል የአስተዳደራዊው ኃላፊነት ነው።
በቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር እኛን በምን ዓይነት ሐብቶች ባርኮናል? እያንዳንዱ
ሰው በፈጣሪ የተቸረው ስጦታ እንዳለው ጴጥሮስ በግልጽ በመጥቀስ፤ ይህን ስጦታ
የተቀበሉትን ክርስቲያኖችን “ቅዱሳን ካህናት” (1ጴጥ. 2፡5) ሲል ይጠራቸዋል።
እነዚህ ወገኖች እግዚአብሔር በሰጣቸው ስጦታዎች ሁሉ--ማለትም በገንዘባቸው፣
በጊዜአቸው፣ በጉልበታቸው፣ በመክሊታቸው እና በሌሎች ጭምር ለጌታ ኃላፊነት
ያለባቸው ናቸው።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ መክ. 9፡10 እና ቆሮ. 10፡31። እንዴት መሥራት
እንዳለብን እና ሰዎች እንዲሠሩ እንዴት ማስተማር እንዳለብን
አስመልክቶ በጥቅሶቹ ምን ዓይነት መልእክት እናገኛለን?
በዛሬው ጊዜ በሕይወታችን ከሚያጋጥሙን የተለመዱ ዕንቅፋቶች አንዱ--አንደኛውን
ነገር ነጥሎ በተለየ ዘርፍ ወይም ክፍል የመቀላቀል አዝማሚያ ነው። የሥራ ህይወት፣
የቤተሰብ ህይወት፣ መንፈሳዊ ህይወት እንዲሁም ትርፍ ጊዜ የሚባሉ ነገሮች አሉ።
እነዚህን የህይወት ፈርጆች ሊያስተሳስር የሚችል በመጠኑም ቢሆን አነስተኛ ወይም
ምንም ፍላጎት ባለመኖሩ፤ ለመነጣጠል የሚደረግ አካሄድ በአንዳንድ ሁኔታዎች
የሚመረጥ ሊመስል ይችላል። ለአብነት ያህል ሥራን ቤት ይዞ መምጣት በቤተሰብ
ኃላፊነት ላይ ጣልቃ መግባት ስለሚያስከትል መልካም አይሆንም። እንዲሁም ትርፍ
ጊዜአችን--ከእግዚአብሔር ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ ሊቀንስብን አይገባም።
ሆኖም እንዲህ ዓይቱ ገደብ መንፈሳዊ ህይወታችን በመላው እኛነታችን ሊጫወት
በሚገባው ሚና ዙሪያ ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። የክርስቲያን ሥራ ከኀብረት
ባሻገር በሚያገኘው ዕድገት ከእግዚአብሔር ጋር ይሠራል። ሥራ አምላካዊውን
ሕልዎት የምንለማመድበት አንዱ መንገድ ነው። መንፈሳዊ ህይወታችንን በአንድ
ጎራ ሰቅዘን እግዚአብሔርን በአንድ ቀን፣ በአንድ ሠዓት፣ ወይም ይባስ ብሎ በአንድ
የተወሰነ የአኗኗር ሁኔታ ብቻ መወሰን ጌታ በእነዚህ ሌሎች ክፍሎች የሚኖረውን
መገኘት መቃወም ነው።
እነሆ ሁለት ጥያቄዎች፡ በመጀመሪያ መንፈሳዊ ህይወትዎን በአንድ
የተወሰነ ሁኔታ ብቻ ገድበው እንደሆነ ራስዎን ይጠይቁ። በመቀጠል፤
ይህን አድርገው ከሆነ መንፈሳዊነት በሚያደርጓቸው ነገሮች ሁሉ
እንዲነግሥ መፍቀድ እንዴት መማር ይችላሉ?
ዘፍ. 3፣ መክ. 2:18–23፣ ኤፌ. 6:5–8፣ የኃይማኖት አባቶች
እና ነቢያት ከተሰኘው መጽሐፍ ከገጽ፡ 45-58 “ፈተናና ውድቀት” በሚል ርዕስ
የቀረበውን ጽሑፍ ያንብቡ።
ለመሆኑ ሥራ--እርግማን ነው ወይስ በረከት? ሥራ የኃጢአትን እርግማን ተከትሎ
የመጣ ይመስላል (ዘፍ. 3፡17)። ነገር ግን መልእክቱን በጥንቃቄ ስናነብ የተረገመው
ሥራ ሳይሆን ምድሪቱ ሆና እናገኛታለን። እግዚአብሔር ሥራን እንደ በረከት
መስጠቱን ኤለን ኋይት እንደሚከተለው ትገልጻለች፡ “ከዚያን ጊዜ አንስቶ የሰው ልጅ
ዕጣ ፈንታ የሆነው የልፋትና የጥረት ህይወት በዚያ መልኩ እውን የተደረገው ከፍቅር
አኳያ ነው። ሰብዓዊው ፍጡር ለሠራው ኃጢአት እራሱን የማነጽ እና የመቆጣጠር
ልምድ እንዲያዳብር፣ እራሱን ለመግዛት በሚያደርገው ትግል ተፈጥሮአዊ ምኞቱ
ላይም ሆነ ስሜቱ ላይ ለከት እንዲኖረው የተጣለበት የሥነ ምግባር ማረቂያ መንገድ
ነው። የልፋትና የጥረት ህይወት የሰው ልጅ ከውድቀት እና ከኃጢአት ውርደት
እንዲያገግም የቀረበለት የታላቁ አምላክ ዕቅድ አንድ አካል ነው። (የኃይማኖት
አባቶች እና ነቢያት፡ ገጽ 55)። ምናልባት--ከድግግሞሽ፣ ከሥራ ብዛት ወይም
ሥራ በህይወታችን ሊኖረው ከሚገባው ሚና በላይ ዋጋ በመስጠት እንደ እርግማን
ቆጥረነው ይሆን? በየትኛውም ሁኔታ ላይ ልንገኝ ብንችልም እንኳ ሥራን በተገቢው
አተያይ ማስቀመጥ መማር ይኖርብናል።
1.ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ መክ. 2፡18-24። ሰሎሞን በተመሳሳይ የመጽሐፍ
ቅዱስ ክፍል ሥራን--በረከት እና እርግማን አድርጎ እንዴት ሊመለከት
ቻለ? ለሥራችን ያለን አመለካከት ምን ዓይነት ልዩነት እንደሚፈጥር
አስመልክቶ በጥቅሱ የቀረቡ ፍንጮች ምን ይመስላሉ?
2.ቤተሰባችንን የምንከባከበው በምንሠራው ሥራ አማካይነት
መሆኑ እሙን ነው። አዎንታዊውን የሥራ አመለካከት ለቤተሰባችን
የምናስተላልፈው እንዴት ነው?
3.እጅግ በጣም ጥሩ ሥራ በመሥራት እና በሥራ ሱስ በመጠመድ
መሃል ያለውን መስመር መገንዘብ መልካም ነው። ያንን መስመር
እንዳናልፍ መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው? መክ. 2፡23።
ጳውሎስ እንዲህ ሲል በግልጽ ይናገራል፡ “ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ፣ ሊሠራ
የማይወድ አይብላ ብለን ይህን ትእዛዝ ሰጥተናችሁ ነበር” (2ተሰ. 3፡10)።
እርግጥ ነው ይህ መርኅ ትልቅ ትርጉም ይሰጣል። አባባሉ የማይተገበርባቸው
ምን ዓይነት ምሳሌዎች ማቅረብ ይቻላል? መቼም ቢሆን ሊሟገቱት ወይም
ጥያቄ ውስጥ ሊከቱት ከማይቻል ከዚህ ሕግ ጋር ላለመቃረናችን እርጠኞች
መሆን ያለብን ለምንድን ነው?