ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ራእ. 14:6-7፣ ማቴ. 24:14፣ ገላ. 3:22፣ ሉቃ. 23:32–43፣ ዘፍ. 22:12፣ ራእ. 14:8–12፡፡
የሳምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡- “ከዚያም ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ እርሱም በምድር ላይ ለሚኖሩ ለሕዝብ፣ ለነገድ፣ ለቋንቋና ለወገን ሁሉ የሚሰበከውን የዘላለም ወንጌል ይዞ ነበር” (ራእ. ራእ. 14፡6)፡፡
እኛ እንደ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ክርስቲያንነታችን በመጽሐፍ
ቅዱሳዊው ወቅታዊ እውነት ጽንሰ ሀሳብ እናምናለን (2ጴጥ. 1፡12)፡፡ ይህ
ጽንሰ ሃሳብ እግዚአብሔር አስፈላጊ በሆነበት ትክክለኛው ጊዜ
ወቅታዊነት ያለውን እውነት ገልጦ ይሰጣል የሚል አንደምታ አለው፡፡ ጌታ
በዘመናት እየጨመረ የሚሄድ ብርሃን ለሕዝቡ መስጠቱ የአደባባይ ምስጢር
ነው፡፡ የመጀመሪያው የወንጌል ኪዳን የተሰጠው በዘፍ. 3፡15 ሲሆን ይኸውም
በሴቲቱ ዘር አማካይነት ለወደቁት ጥንዶች ተስፋ በተሰጣቸው ጊዜ ነበር፡፡
“በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ
ይባረካሉ” (ዘፍ. 18፡18) በሚል ለአብርሃም የተሰጠው ኪዳን የወንጌልን ተስፋ
በሙላት የሚገልጽ ራእይ ነው፡፡ “የሰው ልጅ ሊያገለግልና ሕይወቱን ለብዙዎች
ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ መጣ እንጂ ሊገለገል አልመጣም” (ማር. 10፡45) በሚል
የተገለጠው የየሱስ የመጀመሪያ ምጽአት ከመቼውም የላቀ የወንጌል እውነት
መገለጥ ለመሆኑ አንድና ሁለት የለውም፡፡
የሦስቱ መላእክት መልእክት የሆነውን ራእ. 14፡6-12 ከክርስቶስ መገለጥ
አስቀድሞ ባሉት የመጨረሻዎቹ ቀናት ለሚኖሩ ሕዝቦች የተሰጠ ወቅታዊ
እውነትነት መሆኑን እናምናለን፡፡ እንዲሁም እንደ ክርስቲያን የአጠቃላዩ ተስፋ
ፍጻሜ አድርገን እንቀበላለን፡፡
በዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን በመጨረሻው የመከራ ዘመኖች
ታማኝ እንደሆኑ ለመጽናት ምኞታቸው ለሆኑ ወገኖች ወሳኝ እውነት በያዘው
በተለይ በመጀመሪያው መልአክ መልእክት ላይ ልዩ ትኩረት እናደርጋለን፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 14፡6፣ 24፡14፣ 28፡19፡፡ በመልእክቶቹ የምናገኘው
ተመሳሳይ ጭብጥ ምንድን ነው? እንደ ቤተ ክርስቲያን ለቆምንለት ዓላማ
ወንጌልን ወጥቶ መስበክና መመስከር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ማስተዋል
እንድንችል እነዚህ ጥቅሶች በአንድነት የሚረዱን እንዴ ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ለምሳሌ የመጀመሪያው መልአክ መልእክት የሆነውን ታላቁን ተልዕኮ (ማቴ.
28፡19) ለዚህ ዘመን እንደ ተሰጠ መልእክት በመቁጠር ከመጨረሻዎቹ ጊዜያቶች
“ወቅታዊ እውነት” ዐውድ ልንመለከተው እንችላለን፡፡
እዚህ ላይ ሦስቱም ጥቅሶች “ለሕዝብ፣ ለነገድ፣ ለቋንቋና ለወገን” (ውጪያዊ)
የወንጌል ተደራሽነት አጽንኦት እንደሚሰጡ ልብ ይሏል፡፡ በሌላ አባባል እያንዳንዱ
ሰው ይህን መልእክት መስማት ያለበት በመሆኑ ዓለማቀፋዊ አንደምታ አለው፡፡
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ገላ. 3፡22፡፡ መላው ዓለም ለምን ወንጌልን መስማት እንዳለበት
ማስተዋል እንድችል ጥቅሱ የሚረዳን እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የኃጢአት ዓለማቀፋዊ ይዘት የተልዕኮአችንንና የጥሪአችንን አለማቀፋዊነት ገልጦ
ያሳያል፡፡ እያንዳንዱ “ሕዝብ፣ ነገድ፣ ቋንቋና ወገን” በመሳቱና አምላካዊውን ሕግ
በመተላለፉ “የኃጢአት እስረኛ” ሆኖአል፡፡ የአዳም በኤደን መውደቅ እንደ ሰደድ
እሳት ወደ መላው ሰብዓዊ ዘር በመተላለፉ በኃጢአት ቫይረስ ተጠቂ ያልሆነ
ሕዝብ፣ ነገድ፣ ቋንቋ ወይም ወገን አይገኝም፡፡ ቅጽበታዊውን የኃጢአት ውጤት
ሁላችንም እየተጋፈጥን ቢሆንም፤ ነገር ግን ዘላቂው መፍትሔ ባይኖር ኖሮ
ከአይቀሬው ውጤት ይኸውም ከዘላለማዊው ሞት ጋር መጋፈጣችን የግድ በሆነ
ነበር፡፡
በእርግጥ ትክክለኛው መፍትሔ ይኸውም፡ የየሱስ ህይወት፣ ሞት፣ ትንሳዔ እና
የሰማያዊ መቅደስ አገልግሎት ብቸኛው የኃጢአት ችግር መፍትሔ ሆኖ
ቀርቦልናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር በየሱስ ክርስቶስ አማካይነት
ያበረከተለትን ታላቅ ተስፋ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ይህ
እውነት ወዳልተሰማባቸው ወደ ሁሉም የዓለም ክፍሎች በመድረስ የየሱስን
መልእክት ማካፈል ምኞታቸው የሆነው ለዚህ ነው፡፡
ለሌሎች የወንጌልን መልእክት ማሰራጨት ለአገልጋዩ ብርቱ መንፈሳዊ ጥቅም
ያለው ለምንድን ነው? በሌላ አባባል የወንጌልን መልእክት ለሌሎች ተደራሽ
ስናደርግ፤ በተመሳሳይ ራሳችንን ድንቅ በሆነ መንገድ ለዳግም ምጽአቱ እያዘጋጀን
የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው?
በራእ. 14፡6 የቀረበው “የዘላለም ወንጌል” ለዓለም ሊሰበክ የተገባ መልእክት
ነው፡፡ ይህ በራሱ አንዳችም ተስፋ ማበርከት ላልቻለውና ላልነበረው ዓለም
የተሰጠ የተስፋ መልእክት ነው፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ሉቃ. 23፡32-43፡፡ ታሪኩ በኃጢአት ለወደቀው ዘር
የቀረበውን “የዘላለም ወንጌል” ተስፋ የሚገልጸው እንዴት ነው?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከየሱስ አጠገብ ተሰቅሎ ስለነበረው ወንበዴ ኤለን ኋይት ስትጽፍ “ይህ ሰው ልቡ
የደነደነ ወንጀለኛ አልነበረም፡፡ የኅሊና ወቀሳውን አፍኖ ለመያዝ ሲል ቀስ በቀስ
ወደ ኃጢአት ማጥ በመግባቱ በወንጀለኝነት ተያዘ፡፡ ወንጀለኛነቱ በምርመራ
ስለተረጋገጠበት በሥቅላት እንዲሞት ተፈረደበት”—Ellen G. White, The De-
sire of Ages, p. 749.
ከዚያ ምን ተከሰተ? በመስቀል ላይ እያለ ስለ የሱስ ማንነት በውልብታ መመልከት
በመቻሉ “‘ኢየሱስ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ’ አለው” (ሉቃ.
23፡42)፡፡
የሱስ የሰጠው ምላሽ ምን ነበር? ወዳጄ፡ ብረዳህ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን
የኅሊና ወቀሳህን አፍነህ ወደ ኃጢአት ማጥ መግባት አልነበረብህም--ነበር ያለው?
ወይስ “ጽድቃችሁ ከከፈሪሳውያንና ከኦሪት ሕግ መምህራን ጽድቅ ልቆ ካልተገኘ
መንግሥተ ሰማይ መግባት አትችሉም” (ማቴ. 5፡20) በማለት ከቀደሙት
መልእክቶቹ አንዱን አካፈለው? ከዚህ ውጪ የሱስ የወንበዴውን ያለፉ ስህተቶች
ሊያስታውሰውስ ሞክሮ ነበር?
የሱስ በዚህ ፋንታ እንከን ወደ ነበረበት፣ አንዳችም የጽድቅ ሥራ መሥራት
ወደማይችለውና ቀደም ሲል የስድብ ናዳ ያወርድበት ወደ ነበረው (ማቴ. 27፡44)
ወደዚህ ወንጀለኛ መልከት አደረገ፡፡ ከዚያም እንደ አዲስ ሰው እየተመለከተው
“እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” አለው (ሉቃ. 23፡43)፡፡ ይህ
ማለት፡ ኃጢአትህ፣ ወንጀልህ፣ የነበረብህ እንከን ይቅር እንደ ተባለ አሁን
እየነገርኩህ፣ እያረጋገጥኩልህ ነው፡፡
ይህ የመጀመሪያው መልአክ መልእክት መሰረት የሆነው “የዘላለም ወንጌል” ነው፡፡
ያለዚህ እውነት ስለ ሕግ፣ ስለ ሰንበት ወይም ስለ ሞቱ ሰዎች ሁኔታ--ምንም ነገር
ማስተማር አንችልም፡፡ የሁሉም የልብ ትርታ ከሆነው “የዘላለም ወንጌል” ውጪ
የእነዚህ አስተምህሮዎች መልካምነት ምኑ ላይ ነው?
ከዚህ ታሪክ ለራስዎ ሊወስዱ የሚችሉት ተስፋ ምንድን ነው?
“የዘላለም ወንጌል” ለመላው ዓለም ስለ መታወጁ ከቀረበው መልእክት በኋላ
የመጀመሪያው መልአክ መልእክት በዚሁ መልእክት ላይ ይበልጥ እየተስፋፋ
ይሄዳል፡፡ የዘላለምን ወንጌል ለዓለም በምናስተጋባበት ወቅት የዚህ ወንጌል አካል
የሆኑ ወቅታዊ እውነቶችን ማካተታችን የግድ ይሆናል፡፡ በሌላ አነጋገር የራእ. 14፡7
መልእክት በመጨረሻዎቹ ጊዜያቶች ወቅታዊ እውነት ውስጥ ይካተታል፡፡
ጥቅሱን ያንብቡ፡ ራእ. 14፡7፡፡ እግዚአብሔርን መፍራትና ለእርሱ ክብር መስጠት
ምን ማለት ነው? ያን የምናደርገው እንዴት ነው? እነዚህ ጽንሰ ሃሳቦች ከወንጌል
ጋር ገጣሚ የሚሆኑት እንዴት ነው?
እግዚአብሔርን መፍራት እና ለእርሱ ክብር መስጠት የማይገናኙ ጽንሰ ሃሳቦች
አይደሉም፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው እሳቤ አኳያ እግዚአብሔርን በእውነት
የምንፈራ ከሆነ ክብር እንሰጠዋለን፡፡
ስለዚህ አንደኛው በቀጥታ ወደ ሌላኛው ማምራቱ የግድ ይሆናል፡፡
የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡፡ ጥቅሶቹ “እግዚአብሔርን ፍሩ” የሚለውን ሃረግ
ፍቺ ማስተዋል እንድንችል እንዴት ይረዱናል? ለእርሱ ክብር ከመስጠት ጋር
የሚዛመደውስ እንዴት ነው? ዘፍ. 22:12፣ ዘፀ. 20:20፣ ኢዮ. 1:9፣ መክ. 12:13፣
ማቴ. 5:16፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ከላይ በቀረቡት ጥቅሶች እግዚአብሔርን መፍራት የሚለው ጽንሰ ሃሳብ እርሱን
ከመታዘዝ ጋር ተያያዥነት አለው፡፡ ትክክል የሆነውን ነገር ስናደርግ ለእርሱ ክብር
እናመጣለን፡፡ ምንም እንኳ እግዚአብሔርን መፍራት ከአድናቆት ወይም
ከአክብሮት ጋር ተያያዠነት እንዳለው በተደጋጋሚ ቢነገርም፤ ከዚያም በጥልቀት
መሄድ ግን ይኖርበታል፡፡ እግዚአብሔርን እንድንፈራ ተነግሮናል፡፡ እኛ እንደ
አምላካዊው ፈቃድ ከመራመድ በመሰናከል ኃጢአት በመሥራታችን ሞት
የሚገባቸው ፍጡራን ለመሆን በቃን፡፡ በየጊዜው በሚስተዋሉ አስገራሚ የክፉው
ድርጊቶች እና ከጻድቁና ፍትሐዊው አምላክ እጅ ምን እንደሚገባቸው በማሰብ
ያልተደመመ ማን አለ? ይህ እንግዲህ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡ ደግሞም
በመጀመሪያ ይቅርታ ለመቀበል ወደ መስቀሉ እንድናመራ የሚያደርገን ይኸው
ፍርሃት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከበደል የሚያነጻንን አምላካዊ ኃይል ፍለጋ
ነው፡፡ መስቀሉ ባይኖር ለዘላለም ጠፍተን በቀረን ነበር (ማቴ. 10፡28)፡፡
እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር በተያያዘ የግል ተሞክሮዎ ምን ይመስላል?
ከመንፈሳዊ ህይወታችንና ከእምነታችን ጋር በተያያዘ ትጋት እንዲኖረንና
እግዚአብሔር የሚጠይቀንን እንድናደርግ በማስቻሉ ረገድ ሚዛናዊ የሆነ የዚህ
ፍርሃት መጠን መልካም የሚሆነው እንዴት ነው?
በመጀመሪያው መልአክ መልእክት እግዚአብሔርን የመፍራትና ለእርሱ ክብር
የመስጠት ጽንሰ ሃሳብ ከፍርዱ ጋር ተያያዥነት አለው (ራእ. 14፡7)፡፡
እግዚአብሔር የፍትሕ እና የፍርድ አምላክ መሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ በእጅጉ ግልጽ
አስተምህሮዎች መሃል አንዱ ነው፡፡ ፍትሕና ፍርድ እጅግ አድርጎ ባጠረው በዚህ
ዓለም--አንድ ቀን ይመጣል፡፡
ሰዎች እግዚአብሔርን መፍራት ቢኖርባቸው ብዙም አያስደንቅም፡፡
“የዘላለም ወንጌል” የፍርድን ተጨባጭነት በመልእክቱ ያካተተበት ምክንያት
ይኸው ነው፡፡ ለመሆኑ በእነዚህ ሁለት መሰረታዊ ነገሮች መካከል ያለው ግንኙነት
ምንድን ነው? የወንጌል “መልካም የምስራች” የሚል ፍቺ ካለው፤ እኛ ሁላችን
ኃጢአተኞች እና አምላካዊውን ህግ የጣስን ሕዝቦች ብንሆንም፤ ነገር ግን
በመስቀል ላይ እንደ ተሰቀለው ወንበዴ ያ የፍርድ ቀን ከተፍ ሲል፤ እንደ
ኃጢአተኝነታችንና እንደ መተላለፋችን ይገባን የነበረውን ቅጣት አንቀበልም፡፡
የሚከተሉትን ጥቅሶች ካነበቡ በኋላ--በራሴ መልካም ሥራዎች ምን ያህል መቆም
እችላለሁ? ብለው ራስዎን ይጠይቁ፡ ማቴ. 12:36፣ መክ. 12:14፣ ሮሜ. 2:6፣ 1ቆሮ.
4:5፡፡
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የፀጉራችንን ቁጥር የሚያውቀው አምላክ እነሆ ዓለምን ሊዳኝ ተቃርቦአል፡፡
እንግዲህ “የዘላለም ወንጌል” በትክክል መልካም የምስራች የሆነው ለዚህ ነው፡፡
አምላካዊው ፍርድ ቢመጣም ነገር ግን በታጠቡት፣ በተቀደሱትና በጸደቁት ታማኝ
የየሱስ ተከታዮች ላይ “ኩነኔ” የለም (1ቆሮ. 6፡11)፡፡ ምክንያቱም የሱስ ክርስቶስ
ጽድቃቸው--ጽድቁም ከፍርድ ነፃ የሚያደርጋቸው ነው፡፡
“ሰብዓዊው ዘር በእነዚህ ክሶች ፊት ብቻውን መቆም አይችልም፡፡ በኃጢአት
የተነከሩት ያደፉ ልብሶች በደለኝነቱን ይመሰክራሉ፡፡ ነገር ግን በንስሐ እና
በእምነት ራሳቸውን ለእርሱ በአደራ ለሰጡ--ስለ እኛ የሚቆመው ጠበቃችን
ተፈላጊውን ውጤት የሚያስገኘውን የክስ መልስ ያቀርባል፡፡ በኃያሉ የቀራኒዮ
እሴቶች ተሟግቶ ከሳሻቸውን ድል ይነሳል፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ እስከ መስቀል
ሞት ድረስ በፍጹም ንጽህና መታዘዙ በሰማይና በምድር ኃይል ሁሉ የእርሱ
እንዲሆን አስቻለው፡፡ ስለዚህ ለጥፋተኛው ሰብዓዊ ዘር አባቱን ምኅረትና እርቅ
ለመጠየቅ ባለ መብት ሆነ፡፡”—Ellen G. White, Testimonies for the Church,
vol. 5, p. 471.
ፍጹም ይቅርታ የሚያስፈልገን መሆኑ ስለ ፍርድ መኖር ምን ያስተምረናል?
እግዚአብሔር በየሱስ አማካይነት የሰጠንን ጸጋና ምህረት ምንነት በደል
ያደረሱቦትን ይቅር በማለት መማር የሚችሉት እንዴት ነው?
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 14፡6-7፡፡ በመጀመሪያው መልአክ አጠቃላይ መልእክት
ውስጥ ለየት ያሉት አላባዎች ምንድን ናቸው? እርስ በርስ ያላቸው ዝምድናስ
ምን ይመስላል?
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ለዓለም ምስክር እንድንሆንና እግዚአብሔርን እንድንፈራ፣ ለእርሱም ክብር
እንድንሰጥ የቀረበልን ጥሪ መነሾ እግዚአብሔርን እንደ ፈጣሪ ማምለክ ነው፡፡
ይህ በእርግጥ ብዙም አያስገርምም፡፡ እነዚህ የወቅታዊው እውነት ሌላኛው
ገጽታ የሆኑት--የዘላለም ወንጌል፣ ምስክር እንድንሆን የቀረበልን ጥሪ እና ፍርድ-መሰረታቸው እግዚአብሔርን እንደ ፈጣሪ ከማመንና ከመቀበል ውጪ ሌላ ምን
ሊሆን ይችላል? የእነዚህና የሌሎቹ ሁሉ እውነቶች መነሾ ሁሉንም የፈጠረው
ጌታ መሰረታዊ እውነት ነው፡፡ ከማንኛውም ምድራዊ ፍጡር በተለየ ሰው ማለት
እና በሕይወት መመላለስ ምን እንደሆነ ለማስተዋል ብሎም በእግዚአብሔር
አምሳል ለመሠራት ጌታን እንደ ፈጣሪ በማምለክ ወደ ቀደመው መሰረት
እንመለሳለን፡፡ እርሱን እንደ ፈጣሪ በማምለክ የህልውናችን መሰረት፣
መተማመኛችንና የወደፊት ተስፋችን መሆኑን እናሳያለን፡፡ ሰባተኛውን ቀን
ሰንበት መጠበቅ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ይኸው ነው፡፡ እግዚአብሔር ብቻ
ፈጣሪያችን መሆኑንና እርሱን ብቻ ማምለካችንን በተለይ የምናረጋግጥበት
መንገድ ነው፡፡ እዚህ ላይ ከወንጌልና ከፍርድ ጎን ለጎን ጌታን እንደ ፈጣሪ
እንድናመልክ የቀረበልን ጥሪ በስፋት ይታወቃል፡፡
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ራእ. 14፡8-11፡፡ ጌታን እንደ ፈጣሪ በማስተዋል አምልኮ
የማቅረብን አስፈላጊነት እንድናስተውል ጥቅሶቹ ምን ይነግሩናል
--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
የመጨረሻዎቹ ጊዜያት ክስተቶች በዓለም ዙሪያ መገለጥ ሲጀምሩ፤ በፈጣሪ
ፋንታ ለአውሬውና ለምስሉ እንድንሰግድ የሚደረገው ግፊት እየበረታ
ይመጣል፡፡ ለአውሬውና ለምስሉ ስግደት ለሚያቀርቡ የተሰጠውን አስፈሪ
ማስጠንቀቂያ በሚገባ ማጤን ከቻልን፤ እግዚአብሔር እንደ ፈጣሪነቱ ብቸኛ
ሰብዓዊ አምልኮ እንደሚገባው የተሰጠውን አጽንኦት በተሻለ ማስተዋል
እንችላለን፡፡ ብርቱ ቀውስ በሚከሰትባቸው በእነዚያ የመጨረሻዎቹ ቀናት ይህ
እውነት ከመቼውም በላይ አንገብጋቢ ሆኖ ይወጣል፡፡
በእግዚአብሔር አምላክ ስለ ተፈጠረው ለማመን የሚያስቸግር አስገራሚ ዓለም
ጊዜ ወስዳችሁ ተወያዩ፡፡ የፍጥረት ሥራ ይህን ሁሉ ስለ ፈጠረው አምልክ ምን
ሊያስተምር ይችላል? አምልኮ በብቸኝነት የሚገባው እርሱ ብቻ የሆነው
ለምንድን ነው?
የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች--በራእ. 14፡7 “ሰማይንና
ምድርን፣ ባሕርንና የውሃ ምንጮችን ለፈጠረው ስገዱ” የሚለውን መልእክት
“እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፤ ባሕርንና በውስጡም ያሉትን ሁሉ በስድስት
ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን አርፎአልና” (ዘፀ. 20፡11) ከሚለው አራተኛው
ትእዛዝ ጋር ያለውን ትስስር ቀደም ባሉት ጊዜያቶች መመልከት ችለው ነበር፡፡
ምንም እንኳ በሁለቱ ጥቅሶች ጥቅም ላይ የዋለው ቋንቋ በቅርብ የተሳሰረ
ቢሆንም፤ ነገር ግን ጌታ “የውሃ ምንጮችን” መፍጠሩን በሚያመላክተው የራእይ
ሃረግ ላይ ለውጥ አለ፡፡
ደራሲ ጆን ባልድዊን እንዲህ ሲሉ ይሞግታሉ፡ “‘የውሃ ምንጮች’ ከሚለው
ሃረግ በስተ ጀርባ ሆነ ብሎ የተደረገ መለኮታዊ ፈቃድ ከሌለ በቀር ከዘፀ. 20፡11
ጋር ትይዩ ሆነው በቅደም ተከተል የቀረቡት ነጥቦች ላይ መልእክተኛው ለውጥ
እንዲያደርግ የሱስ ለምን ፈቀደ? መልአኩ ‘የውሃ ምንጮች’ ብሎ በመጥቀስ
ፋንታ--ዛፎች፣ ወፎች፣ ዓሦች ወይም ተራሮች በማለት ሌሎች የፍጥረት
ሥራዎችን ያልተጠቀመው ለምንድን ነው?
“በዓይነቱ ልዩ የሆነው አምላካዊ ፍርድ መድረሱን የሚያስታውቀውና
‘የውሃ ምንጮች’ በሚል ሃረግ ከመለኮታዊው መልእክት ዐውድ የቀረበው
ማስረጃ፤ የአንባቢውን ትኩረት ወደ ቀደመው ዘመን የመለኮት ፍርድ መድረስ
ለማመልከት የተደረገ ሊሆን ይችላል. . . እግዚአብሔር ‘የውሃ ምንጮች’
የሚለውን ሃረግ ጥቅም ላይ ያዋለው ምናልባት የጥፋት ውሃን ጉዳይ በተዘዋዋሪ
በመንካት የፍርድ አምላክ ለመሆኑ አጽንኦት ለመስጠትና ለዘላለም ታማኝና ቸር
አምላክነቱን ለማሳየት ይሆናል፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ከሆነና ‘የውሃ ምንጮች’ በሚል
የቀረበው ሃረግ ዐውደ ሃሳብ ከጥፋት ውሃ ጋር ተያያዥነት ካለው፤ አንባቢው
የጊዜውን መጨረሻ መድረስ አስተውሎ ጉዳዩን በዋዛ እንዳይመለከትና በራእ. 14
የመጀመሪያው መልአክ መልእክት ለተሰጠው መለኮታዊ ፍርድ አጽንኦት
እንዲሰጥ ሊያደፋፍረው ይችላል፡፡—John Baldwin, ed., Creation, Catas-
trophe, and Calvary: Why a Global Flood Is Vital to the Doctrine of
Atonement (Hagerstown, Md.: Review and Herald® Publishing Association, 2000), p. 27.
1.“እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን” (ኢሳ. 53፡6)፡፡ “እኛ ሁላችን”-የሚሉት ቃላት በዕብራውያን ቋንቋ ኩላኑ በሚል ቃል ይታወቃሉ፡፡ በዚያው
ጥቅስ ኢሳያስ “የሁላችንንም በደል” በእርሱ ላይ ጫነው ሲል ይነግረናል፡፡
“የሁላችንንም” የሚለው ቃል ፍቺ አሁንም ኩላኑ የተሰኘው ቃል ነው፡፡
የኃጢአት ችግር የቱንም ያህል ቢገዝፍ መፍትሔው ከበቂ በላይ መሆኑን ይህ
እንዴት ያሳየናል?
2.በመስቀል ላይ ስለ ነበረው ወንበዴ ሌሎች ምን ዓይነት ትምህርቶች ማግኘት
እንችላለን? ምናልባት ይህ ወንበዴ በምድራዊ ገዢዎች ይቅር ተብሎ ከመስቀል
ቢወርድና እንዲኖር ቢፈቀድለት ምን ዓይነት የተለየ ህይወት ይኖር ነበር ብለው
ያስባሉ? ምላሽዎ ክርስቶስ ሕይወታችንን ለመቀየር የሚያስችል ኃይል እንዳለው
ምን ይነግረናል?