የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- መዝ. 103:13፣ ኢሳ. 49:15፣ ሆስ. 11:1–9፣ ማቴ. 23:37፣ 2 ቆሮ. 11:2፣ 1 ቆሮ. 13:4–8
የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ
እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ እርስዋ ትረሳ
ሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም” (ኢሳ. 49፡15)።
ስሜቶች ብዙውን ጊዜ የማይፈለጉ እና ሊወገዱ እንደሚገቡ ይቆጠራሉ።
ለአንዳንድ ሰዎች ስሜቶች ምክንያታዊነት የጎደላቸው ስለሆኑ፣ ጥሩ
ወንድ ወይም ሴት “ስሜታዊ” ናቸው ተብለው አይገለጹም። በአንዳንድ
ጥንታዊ የግሪክ ፍልስፍናዎች፣ “ምክንያታዊ” ሰው የሚባለው ለስሜታዊነት
የማይዳረግ ወይም ስሜቱን ስሜት-አልባ በሆነ አመክንዩ የሚገዛ ተመራጭ ነው
ተብሎ ይሸለማል።
በእርግጥ ያልተገሩ ስሜቶች ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ። ነገር ግን
እግዚአብሔር ሰዎችን የፈጠራቸው ስሜት እንዲኖራችው አድርጎ ነው፤
እግዚአብሔር ራሱ በቃሉ የተገለፀው ጥልቅ ስሜቶች እንዳሉት ተደርጎ ነው።
እግዚአብሔር በጥልቅ ስሜቶች ውስጥ የሚያልፍ ከሆነ፣ ስሜቶች በተፈጥሯቸው
መጥፎ ወይም ምክንያት አልባ ሊሆኑ አይችሉም - ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱሱ
አምላክ ፍጹም መልካም እና ፍጹም ጥበብ ያለው ነውና።
በርግጥ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ጥልቅ ስሜታዊ ፍቅር መሆኑን
በመገንዘብ ውብ እውነታዎችን ልናገኝ እንችላለን፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር
(ስሜታዊም ሆነ ሌላ) ሁልጊዜ ፍጹም ስለሆነ፣ ከሰው ስሜቶች ጋር ተመሳሳይ
ነው ተብሎ ሊታሰብ አይገባም።
እግዚአብሔር አፍቃሪና ሩኅሩኅ ነው
*የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ።
ምናልባትም ሰዎች ሁሉ የሚቀምሱት ትልቁ ፍቅር ወላጅ ለልጁ ያለው
ፍቅር ነው። እግዚአብሔር ለሰዎች ያለውን አስደናቂ ርኅራኄ ለማሳየት መጽሐፍ
ቅዱስ ብዙውን ጊዜ የወላጅ እና የልጅን ግንኙነት እንደ ምሳሌ ይጠቀማል፡-
ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ርኅራኄ ጥልቅ እና በጣም ውብ ከሆነው የሰው
ርኅራኄ ስሜት እጅግ የላቀ መሆኑን አጽንዖት ቢሰጥም።
መዝ. 103:13ን፣ ኢሳ. 49:15ን እና ኤር. 31:20ን ያንብቡ።
እነዚህ ምስሎች ስለ እግዚአብሔር ርኅራኄ ሁኔታ እና ጥልቀት ምን
ያስተላልፋሉ?
በእነዚህ ጥቅሶች፣ እግዚአብሔር እኛን እንደ ተወደዱ ልጆቹ ያየናል፣
መልካም አባት እና እናት ልጆቻቸውን እንደሚወዱ ይወደናል። ሆኖም ኢሳ. 49:
15 እንደሚገልጸው፣ እናት እንኳን “የምታጠባውን ልጇን ትረሳ ይሆናል” ወይም
“ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ ላትራራ ትችላለች”፣ ነገር ግን አምላክ ልጆቹን
ፈጽሞ አይረሳም፣ ርኅራኄውም ፈጽሞ አያልቅም (ሰቆ. ኤር. 3፡22)።
በተለይም፣ በዚህና በሌሎች ጥቅሶች ርኅራኄ ተብሎ የተተረጎመው
የዕብራይስጥ ቃል ረኸም የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ሩኅሩኅ ፍቅር የሚገልፅ
ሲሆን፣ ማሕፀን ከተባለው የዕብራይስጥ ቃል ሬኼም እንደተወሰደ ይታመናል።
ስለዚህም ሊቃውንት እንዳስተዋሉት፣ የእግዚአብሔር ርኅራኄ “በማኅፀን
የተመሰለ የእናት ፍቅር” ነው። በእርግጥም፣ እናት ለአራስ ልጇ ካላት ርኅራኄ
እጅግ የላቀ ነው።
ምንም እንኳን በተደጋጋሚ በእርሱ ላይ በማመፅ ቢያሳዝኑትም፣
በኤር. 31:20 እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕዝቡን እንደ “ውድ ልጅ” እና “ደስ
የሚያሰኝ ልጅ” አድርጎ ይመለከታቸዋል። እግዚአብሔር “ልቤ ይናፍቀዋል”፣
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
“በእርግጥም እምረዋለሁ” ይላል። እዚህ ላይ ምሕረት ተብሎ የተተረጎመው
ቃል ከላይ መለኮታዊ ርኅራኄ (ረሃም) የተባለው ቃል ነው። በተጨማሪም
“ልቤ ይናፍቃል” የሚለው ሐረግ “ውስጤ ታወከ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
ይህ ገለጻ ከአንጀት ጋር የተቆራኘ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ጥልቅ ፍቅር
የሚያሳይ፣ የመለኮታዊ ስሜት ቋንቋ ነው። ምንም እንኳን ታማኝ ባይሆኑም፣
እግዚአብሔር የተትረፈረፈ ርኅራኄውን እና ምህረቱን በሕዝቡ ላይ ያፈሰዋል -
ያውም ከምንጠብቀው በላይ።
ለአንዳንዶቻችን፣ አምላክ ለእኛ ያለው ርኅራኄ ከአፍቃሪ አባት ወይም
እናት ጋር መመሳሰሉን ማወቃችን እጅግ የሚያጽናና ነው። ሆኖም፣
አንዳንድ ሰዎች ወላጆቻቸው አፍቃሪ ስላልነበሩ ለማስተዋል ሊቸገሩ
ይችላሉ። ለእነዚህ የአምላክ ርኅራኄ በምን ሌሎች መንገዶች ሊገለፅ
ይችላል?
እግዚአብሔር ለሰው ያለው የማይለካው ጥልቅ ፍቅር በሆሴዕ ተገልጿል።
እግዚአብሔር ነብዩን ሆሴዕን እንዲህ ሲል አዞት ነበር፡- “ምድሪቱ ከእግዚአብሔር
ርቃ ታላቅ ግልሙትና ታደርጋለችና፣ ሂድ ጋለሞታን ሴትና የግልሙትናን ልጆች
ለአንተ ውሰድ አለው” (ሆሴ. 1፡2)። ኋላ ላይ በሆሴ. 11 እግዚአብሔር ከሕዝቡ
ጋር ያለውን ግንኙነት በአፍቃሪ አባት ይመስለዋል።
ሆሴ. 11:1-9ን ያንብቡ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያለው ምስል
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ፍቅርና ጥንቃቄ እንዴት ሕይወት
ይዘራበታል?
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለው ፍቅር፣ ወላጅ ለልጁ ባለው ርኅራኄ የተሞላ
ፍቅር ተመስሏል። ቃሉ ፍቅሩን ለመግለጽ ሌሎች ምሳሌዎችን ተጠቅሟል፡
- ሕጻን ልጅን እንዲራመድ ማስተማር፤ የሚወደውን ልጅ በክንዶቹ ማቀፍ፤
መፈወስ እና በሕይወት ማኖር፤ ለሕዝቡ መጠንቀቅ። “ሰው ልጁን እንደሚሸከም”
እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ “ተሸከመ” ይናገራል (ዘዳ. 1፡31)። “በፍቅሩና
እግዚአብሔር አፍቃሪና ሩኅሩኅ ነው
በረህራሄውም ተቤዣቸው”፣ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንስቶ ተሸከማቸው”
(ኢሳ. 63፡9)።
ከእግዚአብሔር የማይናወጥ ታማኝነት ጋር ሲነጻጸር፣ ሕዝቡ ግን
በተደጋጋሚ ታማኝ አልነበሩም፤ እንዲያውም እግዚአብሔርን በመጋፋትና
በራሳቸው ላይ ፍርድ በማምጣት እጅግ አሳዘኑት። እግዚአብሔር ሩኅሩኅ ነው፣
ነገር ግን ፍትሃዊም ነው። (በቀጣዩ ትምህርት እንደምንመለከተው ፍቅርና ፍትሕ
አይነጣጠሉም)።
በሆነ ነገር ተበሳጭተው አንጀትዎ ተላውሶ ያውቃል? ይህ እግዚአብሔር
ለሕዝቡ ያለውን ጥልቅ ስሜት ያሳያል። የልብ መቃተት እና በርኅራኄ መንሰፍሰፍ
የእግዚአብሔርንም ሆነ የሰዎችን ጥልቅ ስሜት የሚያሳዩ ምሳሌዎች ናቸው።
በርኅራኄ መንሰፍሰፍን (ካማር) የሚያሳው ምሳሌ፣ ወደ ሰሎሞን
በመጡትና ሕጻኑ የራሳቸው እንደሆነ በተናገሩት ሁለት ሴቶች ጥቅም ላይ
ውሏል። ሰሎሞን ሕፃኑን ለሁለት እንዲከፍሉት ባዘዘ ጊዜ፣ ይህ ሥዕላዊ መግለጫ
የእውነተኛዋን እናት ስሜት ይገልጻል (1 ነገ. 3፡26፤ ከዘፍ. 43፡30 ጋር ያስተያዩ)።
ወላጅ የሆነ ሁሉ ትምህርቱ ስለ ምን እየተናገረ እንደሆነ ያውቃል።
ሌላ ምድራዊ ፍቅርም ከዚህ ጋር አይወዳደርም። ይህ አምላክ ለእኛ
ያለውን ፍቅር እንድንገነዘብ የሚረዳን እንዴት ነው? ከዚህ መረዳትስ
ምን የሚያፅናና ነገር ልናገኝ ይገባል?
እንደ ብሉይ ኪዳን ሁሉ፣ አዲስ ኪዳንም የእግዚአብሔርን ርኅራኄ
ለማሳየት ተመሳሳይ ምስል ይጠቀማል። ጳውሎስ አብን “የርኅራኄ አባት
የመጽናናትም ሁሉ አምላክ” ይለዋል (2ቆሮ. 1፡3)። በተጨማሪም ጳውሎስ
በኤፌ. 2፡4 ላይ እግዚአብሔር “በምሕረቱ ባለ ጠጋ” እንደሆነ እና “ከወደደን
ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ” እንደዋጀን ይገልፃል።
ክርስቶስ ራሱ በተለያዩ ምሳሌዎች፣ የአብን ርኅራኄ ለማሳየት ውስጣዊና
አንጀትን የሚያላውስ ስሜትን የሚገልጹ ቃላትን ደጋግሞ ይጠቀማል (ማቴ. 18፡
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
27፣ ሉቃ. 10፡33፣ ሉቃ. 15፡20)። በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን መለኮታዊ ርኅራኄን
ለመግለጽ የተጠቀማቸውን ተመሳሳይ ቃላት፣ ወንጌልም ኢየሱስ ለተጨነቁ ሰዎች
የሰጠውን በርኅራኄ የተሞላ ምላሽ ለማሳየትም ተጠቅሞበታል።
ማቴ. 9:36ን፣ ማቴ. 14:14ን፣ ማር. 1:41ን፣ ማር. 6:34ን እና ሉቃ.
7:13 ያንብቡ። በተጨማሪ ማቴ. 23፡37ን ይመልከቱ። እነዚህ ጥቅሶች
ክርስቶስ በሰዎች ሥቃይ የተነካበትን መንገድ የሚገልጹት እንዴት ነው?
ወንጌል ደጋግሞ፣ ክርስቶስ በጭንቀት ወይም በችግር ላሉ ሰዎች
እንደራራላቸው ይናገራል። መራራትም ብቻ ሳይሆን፣ ችግራቸውንም
ፈቶላቸዋል።
በተጨማሪም ኢየሱስ ለሕዝቡ አንብቷል። ክርስቶስ ከተማዋን
ሲመለከት፣ አይኖቹ እንባ እንዳቀረሩ መገመት አይከብድም፡- “ዶሮ ጫጩቶችዋን
ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ!
አልወደዳችሁምም” (ማቴ. 23: 37)። እዚህ ላይ የታየው የክርስቶስ ሀዘን፣
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተገለጸው የእግዚአብሔር ኀዘን ጋር እንደሚመሳሰል
እንመለከታለን። እንዲያውም ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት፣ ወፍ ለጫጩቶቿ
ያላት እንክብካቤ በጥንታዊ ቅርብ ምሥራቅ አገሮች ለመለኮት ብቻ ጥቅም ላይ
መዋሉን አስተውለዋል። ይህን ብዙዎች በዘዳ. 32፡11 ላይ ስለ እግዚአብሔር
ከተገለጸው ጋር ያመሳስሉታል — ወፍ ከጫጩቶቿ በላይ እንደምትሰፍፍ፣
እንደምትጠብቅ እና እንደምትንከባከብ።
እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ታላቅ ፍቅር የሚያሳይ ከኢየሱስ የሚበልጥ
ምሳሌ የለም - ፍቅሩን ለመግለፅ ራሱን ለእኛ አሳልፎ ሰጥቷልና። ሆኖም
ክርስቶስ ፍጹም የእግዚአብሔር አምሳል ብቻ አይደለም። በተጨማሪም
እርሱ ፍጹም የሰዎች ምሳሌ ነው። ሕይወታችንን በክርስቶስ አምሳል
የምንቀርፀው አንዴት ነው? በሌሎች ሰዎች ፍላጎት ላይ በማተኮር፣
በመስበክ ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ መንገድ የአምላክን ፍቅር ማሳየት
የምንችለው እንዴት ነው?
እግዚአብሔር አፍቃሪና ሩኅሩኅ ነው
የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ “ሩኅሩኅ አምላክ” ነው። በዕብራይስጥ
እግዚአብሔር ኤል ራሁም ይባላል (ዘዳ. 4፡31)። “ኤል” የሚለው ቃል
“እግዚአብሔር” ማለት ሲሆን፣ ራሁም ደግሞ ሌላው የርኅራኄ (ራሃም)
ሥርወ-ቃል ነው። ሆኖም እግዚአብሔር ሩኅሩኅ አምላክ ብቻ ሳይሆን ቀናተኛ
አምላክ ኤል ካና ተብሎም ተጠርቷል። ዘዳ. 4፡24 እንደሚናገረው “አምላካህ
እግዚአብሔር የሚበላ እሳት፣ ቀናተኛም (ኤል ካና) አምላክ” ነው (ዘዳ. 6:15ን፣
ኢያ. 24:19ን፣ ናሆ. 1፡2ን ይመልከቱ) ።
1ኛ ቆሮ. 13፡4 “ፍቅር አይቀናም” በማለት ያውጃል። ታዲያ
እግዚአብሔር “ቀናተኛ አምላክ” እንዴት ሊሆን ይችላል? 2ኛ ቆሮ.
11፡2 አንብበው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ሕዝብ ለእርሱ
ታማኝ ያልሆኑበትን መንገድ ያሰላስሉ (ለምሳሌ መዝ. 78፡58 ይመልከቱ)።
እነዚህ ጥቅሶች መለኮታዊውን “ቅናት” ለመረዳት እንዴት ይረዱናል?
የእግዚአብሔር "ቅናት" ብዙውን ጊዜ በትክክል አልተስተዋለም። አንድን
ሰው ቀናተኛ ባል ወይም ሚስት ነው ካሉ ይህ ሙገሳ አይደለም። ብዙውን ጊዜ ቅናት
የሚለው ቃል በብዙ ቋንቋዎች አሉታዊ ፍቺዎች አሉት። ይሁን እንጂ በመጽሐፍ
ቅዱስ ውስጥ መለኮታዊ ቅናት ምንም ዓይነት አሉታዊ ትርጉም የለውም። ይህም
ንጹህ ፍቅር ሲሆን፣ አፍቃሪ ባል ከሚስቱ ጋር ያለው ብቸኛ ግንኙነት ነው።
ፍቅርን የሚጻረር ዓይነት ቅናት ቢኖርም (1ቆሮ. 13፡4)፣ እንደ 2ኛ ቆሮ. 11፡
2 መልካም እና ንጹህ “ቅናት” አለ። ጳውሎስ “አምላካዊ ቅንዓት” ብሎ ይጠራዋል
(2ቆሮ. 11፡2)። የእግዚአብሔር ቅናት ሁልጊዜ ንጹህ ሲሆን፣ እግዚአብሔር
ለሕዝቡ ያለው ጥልቅ ፍቅር ሊባል ይችላል።
የእግዚአብሔር ፍቅር (ካና) ለሕዝቡ ካለው ጥልቅ ፍቅር የመነጨ ነው።
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ብቸኛ የሆነ (ያልተከፋፈለ) ግንኙነት ይፈልጋል፤
እርሱ ብቻ አምላካቸው ሊሆን ይገባል። ሆኖም እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ምላሽ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የተነፈገው፣ የተናቀ ፍቅረኛ ሆኖ ይገለጻል (ሆሴ. 1-3ን፣ ኤር. 2፡2ን፣ ኤር. 3፡
1-12ን ይመልከቱ)። ስለዚህ የእግዚአብሔር "ቅናት" ወይም "ጥልቅ ስሜት" ያለ
ምክንያት የሚመጣ አይደለም፣ ነገር ግን ሁልጊዜ ለከዳተኞችና ለክፉ ሰዎች ምላሽ
ነው። የእግዚአብሔር ቅናት (ወይም "ጥልቅ ፍቅር") እንደ ሰው ቅናት አሉታዊ
ትርጉም የለውም። ምቀኛም አይደለም፤ ነገር ግን ሁልጊዜ ለጥቅማቸው ብቻ፣
ከሕዝቡ ጋር ሊኖረው የሚፈልገው ብቸኛ የሆነ፣ ትክክለኛና ንጹህ ፍቅር ነው ።
አምላክ ለእኛ ያለውን ዓይነት መልካም “ቅናት” ለሌሎች ማንጸባረቅ
የምንችለው እንዴት ነው?
የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ሩኅሩኅ እና አፍቃሪ ነው፣ እነዚህ መለኮታዊ
ስሜቶች በጥልቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ተገጸዋል። እግዚአብሔር አዛኝ ነው
(ከኢሳ. 63፡9፣ ዕብ. 4፡15 ጋር ያስተያዩ)፤ በሕዝቡ ሰቆቃ ውስጡ ይነካል (መሳ.
10፡16፣ ሉቃ. 19፡41)፤ ለመስማት፣ ለመመለስ እና ለማጽናናትም ፈቃደኛ ነው
(ኢሳ 49:10, 15፣ ማቴ. 9፡36፣ ማቴ. 14፡14)።
1 ቆሮ. 13:4–8ን ያንብቡ። ይህ ክፍል ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት
የእግዚአብሔርን ርኅራኄ እና አስደናቂ ፍቅር እንድንገልጽ የሚጠራን
በምን መንገዶች ነው?
በ1ኛ ቆሮ. 13፡4–8 ላይ የተገለጸውን ፍቅር ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ወዳጅነት
እንዲኖረን እንናፍቃለን። ለሌሎች እንዲህ አይነት ሰው ለመሆን ግን ምን ያህል
እንፈልጋለን? ራሳችንን ታጋሽ እና ደግ ማድረግ አንችልም፤ ራሳችንን የማይቀና፣
የማይመካ፣ የማይገባውን የማያደርግ፣ ወይም የራሱን የማይፈልግ ማድረግ
አንችልም። “ሁሉን የሚታገስ፥ ሁሉን የሚያምን፥ ሁሉን ተስፋ የሚያደርግ፥ በሁሉ
የሚጸና፣ ለዘወትር የማይወድቅ ፍቅር” በራሳችን ሊኖረን አይችልም (1ኛ ቆሮ. 13፡7፣
8)። እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር በሕይወታችን ሊታይ የሚችለው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ
ሆኖ ነው። መንፈስ ቅዱስም በእምነት የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆኑት በልባቸው ውስጥ
እግዚአብሔር አፍቃሪና ሩኅሩኅ ነው
የእግዚአብሔርን ፍቅር ያፈስላቸዋል፤ እግዚአብሔር ይመስገን (ሮሜ. 5፡5)።
በእግዚአብሔር ጸጋ እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ ለእግዚአብሔር ጥልቅና
ስሜታዊ፣ ግን ሁልጊዜ ፍጹም ንጹህ እና ምክንያታዊ ፍቅር፣ እንዴት ባለ ተግባራዊ
መንገድ ምላሽ ልንሰጥ እና ለሌሎች ልናሳይ እንችላለን? በመጀመሪያ፣ ብቸኛው
ተገቢ ምላሽ ፍቅር የሆነውን አምላክ ማምለክ ነው። ሁለተኛ፣ ለሌሎች ርኅራኄ
እና ደግነት የተሞላበት ፍቅር በማሳየት ለእግዚአብሔር ፍቅር ምላሽ መስጠት
አለብን። በክርስትና እምነታችን ረክተን መቀመጥ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም
ለማጽናናት መነሳሳት አለብን። በመጨረሻም፣ እግዚአብሔር ብቻ እንጂ እኛ
ልባችንን መለወጥ እንደማንችል መገንዘብ አለብን።
ስለዚህ እግዚአብሔርን አዲስ ልብ እንዲሰጠን እንለምነው - መልካሙን
የሚወድ እና ከውስጥ እንክርዳዱን የሚያስወግድ ንጹህ እና የሚያነጻ ፍቅር
እንዲኖረን።
ጸሎታችን "ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥
በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና
ዘንድ፥ … ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ
ይጨምርም” ይሁን (1 ተሰ. 3:12, 13)።
ለምንድነው ለራስ እና ራስ ወዳድነትና ክፋት ለሞላበት ለተፈጥሮአዊ
ልባችን መሞት ይህን አይነት ፍቅርን ለመግለፅ ብቸኛው መንገድ
የሆነው? ለእኔነት እንሞት ዘንድ ምን ምርጫዎች ማድረግ እንችላለን?
የበረከት ተራራ ትምህርቶች ከሚላው የኤለን ጂ. ኋይት
መጽሐፍ “ብፁዓን” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 6–44 ያንብቡ።
“ጥልቅ የሆነ የጎዶሎነት ስሜት የሚሰማቸውና በራሳቸው ምንም መልካም
ነገር እንደሌላቸው የሚሰማቸው ሁሉ ወደ ኢየሱስ በመመልከት ጽድቅን እና
ኃይልን ሊያገኙ ይችላሉ። ‘እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ’
ይላል (ማቴ 11፡28)። ድህነትህን በጸጋው ባለጠግነት እንድትለውጥ ይጋብዝሃል።
እኛ የእግዚአብሔር ፍቅር አይገባንም፣ ነገር ግን ዋሳችን የሆነው ክርስቶስ ብቁ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
እና ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ አብልጦ ሊያድናቸው ይችላል። ያለፈው
ልምምድህ ምንም ይሁን፣ አሁን ያለህበት ሁኔታም ተስፋ የሚያስቆርጥህ ቢሆን፣
ከነማንነትህ ማለትም ከነድካምህ፣ አቅመ ቢስነትህና፣ ተስፋ መቁረጥህ ወደ
ኢየሱስ ና። ሩህሩሁ አዳኛችን ከሩቅ ይገናኝሃል፣ በፍቅር እጆቹ ይጠመጠምብሃል፣
የጽድቅ መጎናጸፊያውን ያለብስሃል። የራሱን ባሕርይ የሚያሳየውን ነጭ ልብስ
አልብሶ ወደ አብ ያቀርበናል። የኃጢአተኛውን ቦታ ወስጃለሁ ብሎ ስለ እኛ
በእግዚአብሔር ፊት ይማልዳል። ይህን የሚባዝን ልጅ አትመልከት፣ እኔን እንጂ
ይላል። ምናልባት ሰይጣን ድምፁን ከፍ አድርጎ በኃጢአታችን እየከሰስ የእኔ
ምርኮ ናቸው ቢልም፣ የክርስቶስ ደም በታላቅ ኃይል ይማልድልናል።”—ኤለን
ጂ. ዋይት፣ የበረከት ተራራ ትምህርቶች፣ ገጽ 8, 9
1. ለኢየሱስ ምስጋና ይሁንና እንዴት ወደ አብ እንደምንቀርብ ከላይ
የትንቢት መንፈስ የሚናገረውን ይመልከቱ። "የራሱን ባሕርይ
የሚያሳየውን ነጭ ልብስ አልብሶ ወደ አብ ያቀርበናል።" አንዳንድ
ጊዜ ከስህተቶቻችንና ከድክመቶቻችን የተነሳ የቱንም ያህል ተስፋ
ብንቆርጥ ወይም ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር በእኛ ላይ የሚያፈሰውን
ፍቅር ለሌሎች ማንጸባረቅ ባንችልም፣ ሁልጊዜ በአብ ዘንድ
ተቀባይነት ወደ አገኘንበት ወደ አስደናቂው የምሥራች ያውም
የሱስ "የራሱን ባሕርይ የሚያሳየውን ነጭ ልብስ አልብሶ ወደ አብ
ያቀርበናል" ወደሚለው መመልከት ያለብን ለምንድን ነው?
2. ሁለቱ ሴቶች በሕይወት ያለው ሕፃን ልጃቸው እነደሆነ በመናገር
በሰሎሞን ፊት በቀረቡ ጊዜ፣ እናትየው ምን እንደተሰማት ያስቡ።
በ1 ነገ. 3፡26 ላይ የተገለጸውን ስሜት እንደገና ይመልከቱ። ይህ
በሆሴ. 11፡8 ላይ አምላክ ለሕዝቡ ያለውን ስሜት ለመግለጽ
የተጠቀመበትን ተመሳሳይ ቃል ለማስተዋል እንዴት ይረዳናል?
3. በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ በሰዎች ፍላጎት ልቡ ይነካ
እንደነበረ አይተናል። እና ምን አደረገ? የሕዝቡን ፍላጎት በሚያሟላ
መንገድ ችግራቸውን ፈቶላቸዋል። እንደ ግለሰብ ወይም እንደ
ቡድን፣ መፅናናት የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ፍላጎት ማሟላት
የምትችሉባቸው ተጨባጭ መንገዶች ምንድን ናቸው?