የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

የእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ



1ኛ ሩብ ዓመት 2025


መጋቢት 13 - 19

13ኛ ትምህርት

Mar 22 - 28




ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው



ሰንበት ከሰዓት በኋላ

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ዘጸ. 20:1–17፣ ሮሜ 6፡ 1–3፣ ሮሜ 7:7–12፣ ኤር. 31:31–34፣ ማቴ. 23:23, 24፣ ያዕቆብ 2፡1-9


የመታሰቢያ ጥቅስ፡ “እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።” (ሮሜ 13፡8)።

በቦርድ ስብሰባ ላይ ስለ አንድ አስቸጋሪ የቤተክርስቲያን አባል ሲነጋገሩ፣ አንድ ሰው ቄሱን፣ “በርኅራኄ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ማድረግ አንችልም” አለው። አንችልም እንዴ? ቄሱ ይህ ሰው ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሕጉ ያለው ግንዛቤ ምን እንደሆነ ግራ ሳይጋባ አይቀርም። ከሰዎች፣ በተለይም ከተሳሳቱት፣ ጋር ባለን ግንኙነት ርኅራኄ ማዕከላዊ መሆን አለበት። ርኅራኄ የፍቅር አንዱ ክፍል ነው፣ እናም ሮሜ 13፡8 እንደሚናገረው ባልንጀራችንን መውደድ ሕግን መፈጸም ነው።

በእርግጥ ፍቅር የሕግ ፍፃሜ ከሆነ፣ ሕግን ከፍቅር ነጥለን ወይም ፍቅርን ከሕግ ጋር እንደማይገናኝ አድርገን እንዳናስብ መጠንቀቅ አለብን። በቃሉ ውስጥ ፍቅር እና ሕግ የማይነጣጠሉ ናቸው። ሕግን የሰጠን አምላክ ፍቅር ነው፣ በዚህም መሠረት የእግዚአብሔር ሕግ የፍቅር ሕግ ነው። ኤለን ጂ. ኋይት እንደፃፈችው፣ ሕጉ የእግዚአብሔር ባሕርይ መግለጫ ነው። (የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች፣ ገጽ 305ን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ሕግ የማይስተዋል የመርሆች ስብስብ አይደለም፣ ነገር ግን ይሳካልን ዘንድ የተሰጡን ትዕዛዛቶችና መመሪያዎች ናቸው። እግዚአብሔር ራሱ እንደገለፀው፣ ሕጉ የፍቅር መግለጫ ነው። *የሳምንቱን ትምህርት በማጥናት ለሰንበት ይዘጋጁ። ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው

መጋቢት 14
Mar 23

የፍቅር ሕግ


የእግዚአብሔር ሕግ የማይስተዋሉ መርሆዎችን የያዘ አይደለም፣ ይልቁንም ግንኙነትን የሚያሳይ ነው። ይህ ደግሞ በአሥርቱ ትእዛዛት በግልፅ ይታያል። የአሥርቱ ትእዛዛት መሠረታዊ መርሆች በኤደን ገነትም ነበሩ፣ በእግዚአብሔር እና በሰዎች እንዲሁም በሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚቆጣጠሩት የፍቅር መርሆዎች ነበሩ።

በዘጸ. 20 ላይ አሥርቱ ትእዛዛት በድንጋይ ጽላት ሲጻፉ፣ ለእሥራኤል የተሰጡት በቃል ኪዳን ግንኙነት አውድ ነው። ትእዛዛቱ የተጻፉት ጌታ ሕዝቡን ከግብፅ ካወጣቸው በኋላ ነው፣ ትእዛዛቱም የተመሰረቱት በእግዚአብሔር ፍቅርና ለሕዝቡ በገባው ተስፋዎች ላይ ነው (ዘጸ. 6፡7, 8 እና ዘሌ. 26፡12)። በአሥሩ ትእዛዛት ውስጥ ያሉት ሁለት ክፍሎች ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እና እርስ በርስ ያለው ግንኙነት እንዲሰምር ያለሙ መሆኑን ማየት ይቻላል።

ዘጸ. 20:1-17ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሔርን መውደድ እና ሌሎችን መውደድ የሚለውን ሁለቱን መርሆዎች የሚገልጹት እንዴት ነው?



የመጀመሪያዎቹ አራት ትእዛዛት ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያመለክቱ ሲሆን፣ የመጨረሻዎቹ ስድስት ትእዛዛት ደግሞ በሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ያሳያሉ። ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት በእግዚአብሔር ሕግ መርሆዎች መመራት አለበት።

እነዚህ የሕጉ ሁለት ክፍሎች ኢየሱስ ሁለቱ ታላላቅ ትእዛዛት ብሎ ከገለጸላቸው ጋር በቀጥታ ይዛመዳሉ—“ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ ውደድ” (ማቴ. 22:37፤ ከዘዳ. 6፡ 5 ጋር ያስተያዩ) እና “ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ” (ማቴ. 22፡39፤ ከዘሌ. 19፡18 ጋር ያስተያዩ)።

የመጀመሪያዎቹ አራት ትእዛዛት እግዚአብሔርን በሙሉ ማንነታችን የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የምንወድባቸው መንገዶች ሲሆኑ፣ የመጨረሻዎቹ ስድስት ትእዛዛት ደግሞ እርስ በርሳችን እንደ ራሳችን የምንዋደድባቸው መንገዶች ናቸው። ኢየሱስ እነዚህ ሁለት ታላላቅ የፍቅር ትእዛዛት ከሕጉ ጋር የተቆራኙ መሆናቸውን በግልፅ ተናግሯል። "በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል" አላቸው (ማቴ. 22:40)።

ስለዚህ የእግዚአብሔር ሕግ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ የተመሰረተ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር እና ሕግ የማይነጣጠሉ ናቸው። ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሕጉን መጠበቅ አያስፈልገንም፣ እግዚአብሔርን እና ሌሎችን መውደድ ነው የሚገባን ሲሉ እንሰማለን። ለምንድነው ይህ ሐሳብ ትርጉም የማይሰጠው? ከአሥርቱ ትእዛዛት አንዱን የምተላለፍ ከሆነ፣ ለእግዚአብሔር ወይም ለሌሎች ያለንን ፍቅር እንዴት ልንገልጽ እንችላለን?

መጋቢት 15
Mar 24

ሕጉ ቅዱስና ጻድቅ በጎም ነው


ፍቅር የእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ነው። እግዚአብሔር ሕግን ሲያፀና፣ ፍቅርንም እንዲሁ ያፀናል። ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ለማዳን የሞተው ሕግን ሲያፀና ሳለ፣ ለእኛም ጸጋውን ይሰጥ ዘንድ ነው። ስለዚህ እርሱ ጻድቅ እና በእርሱ የሚያምኑትን የሚያጸድቅ ሊሆን ይችላል (ሮሜ 3፡25, 26)። እንዴት ያለ የፍቅር መግለጫ ነው! በዚህ መሠረት ሕጉ በደህንነት ሂደት አልተሻረም፤ ይልቁንም የበለጠ ፀና እንጂ።

ሮሜ 6፡1–3ን፣ ከዚያም ሮሜ 7፡7–12ን (ቁጥር 12 ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ) ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ክርስቶስ ከሞተ በኋላም ስለ ሕጉ ምን ይነግሩናል?





አንዳንዶች ጸጋና ቤዛ መሆን ሕግን ያስወግዳሉ ብለው ቢያምኑም፣ ጳውሎስ ግን ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት መቀጠል እንደሌለብን በግልጽ ይናገራል።

ይልቁንም በእምነት በክርስቶስ የሆኑት “ከሞቱ ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ ተጠምቀዋል።” ስለዚህ ራሳቸውን ለኃጢአት እንደሞቱና ለክርስቶስ ሕያዋን እንደሆኑ መቁጠር አለባቸው። ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው

የእግዚአብሔር ሕግ ኃጢአት አይደለም፣ ነገር ግን ኃጢአትንና ኃጢአተኛነታችንን በግልጽ ያሳየናል። ለዚህ ነው “ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት” የሚለው (ሮሜ. 7፡12)። ሕጉ መዳንና መቤዠት እጅግ እንደሚያስፈልገን፣ ያም መዳን እና መቤዠት ደግሞ በክርስቶስ ብቻ እንደሚገኝ ያሳየናል። “እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ” (ሮሜ. 3፡31)።

ክርስቶስ የመጣው ሕግን ለመሻር ሳይሆን በሕግና በነቢያት የተሰጠውን የተስፋ ቃል ሁሉ ሊፈጽም ነው። ስለዚህ “ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም” በማለት በአጽንዖት ተናግሯል (ማቴ. 5፡18)።

የእግዚአብሔር ሕግ የአምላክን ቅድስና ያሳያል - ያውም ፍጹም የሆነውን የፍቅር፣ የጽድቅ፣ የበጎነትና የእውነት ባሕርይውን (ዘሌ. 19:2፣ መዝ. 19:7, 8፣ መዝ. 119:142, 172)። በዚህ ረገድ እንደ ዘጸ. 31፡18 እግዚአብሔር አሥርቱን ትእዛዛት በድንጋይ ጽላቶች ላይ ራሱ መጻፉ ትልቅ ትርጉም አለው። በድንጋይ የተጻፉት እነዚህ ሕጎች ስለማይለወጠው የእግዚአብሔር ባሕርይና በፍቅር ላይ ስለተመሰረተው የእርሱ የሞራል መንግሥት ምስክሮች ናቸው— ይህም የታላቁ ተጋድሎ ዋና ጭብጥ ነው።

ይህ በሕግ እና በፍቅር መካከል ያለው ግንኙነት የኢየሱስን “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ” (ዮሐ. 14፡15) የሚለውን ቃል የበለጠ እንድንረዳ የሚረዳን እንዴት ነው?

መጋቢት 16
Mar 25

ሕግ እና ጸጋ


እንዳየነው ሕግና ጸጋ እርስ በርሳቸው አይቃረኑም። ይልቅስ በእግዚአብሔር ፍቅር እና ፍትሕ የተመሰረተ የተለያየ ጥቅም አላቸው። በሕግ እና በጸጋ መካከል አሁን የሚታየው (አላስፈላጊ የሆነ) የጎላ ንፅፅር የጥንት እሥራኤላውያንን ግራ ሊያጋባቸው ይችል ነበር፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕጉን የሰጣቸው የጸጋውን ታላቅነት ሊያሳያቸው እንደሆነ አድርገው ይመለከቱት ስለነበር ነው። በዙሪያቸው የነበሩት ህዝቦች “አማልክቶቻቸው” ተለዋዋጭና የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ግራ የሚያጋቡ በመሆናቸው፣ ሰዎች “አማልክት” ምን እንደሚፈልጉና ምን እንደሚያስደስታቸው የሚያውቁበት መንገድ አልነበረም። የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ግን ለሕዝቡ እርሱን የሚያስደስተውን ነገር በግልጽ ያስተምራቸዋል።

እርሱን የሚያስደስተውም ለሕዝቡ በሙሉ በግልና በጋራ የሚበጃቸው ነው።

ሆኖም ሕጉ ከኃጢአት ሊያድነን ወይም ልባችንን ሊለውጠው አይችልም። በተፈጥሯችን ኃጢአተኛ ስለሆንን፣ መንፈሳዊ የሆነ የልብ ንቅለ- ተከላ ያስፈልገናል።

ኤር.31:31-34ን ያንብቡ። ይህ እግዚአብሔር አዲስ ልብ ሊሰጠን ስለገባቸው ተስፋዎች ምን ያስተምረናል? ይህንን ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ በዮሐ. 3፡1-21 ላይ እንደገና ስለ መወለድ ከተናገረው ጋር ያስተያዩ።

ደግሞም ዕብ. 8፡10ን ይመልከቱ።



አሥርቱን ትእዛዛት በድንጋይ ጽላቶች ላይ የፃፋቸው እግዚአብሔር ራሱ ነበር (ዘጸ. 31፡18)፣ ሆኖም ሕጉ በእግዚአብሔር ሕዝብ ልብ ውስጥም መፃፍ ነበረበት (መዝ. 37፡30, 31)። የእግዚአብሔር የፍቅር ሕግ ለኛ ውጫዊ ሳይሆን የባሕርያችን ክፍል ሊሆን ይገባ ነበር። በሰዎች ልብ ውስጥ ሕጉን መፃፍ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፣ ይህንንም ለማድረግ ለቃል ኪዳን ሕዝቡ ቃል ገብቷል (ዕብ. 8፡10ን ይመልከቱ)።

ሕግን በመጠበቅ ራሳችንን ማዳን አንችልም። ይልቁንም የዳንነው በጸጋው በእምነት ነው፣ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ በራሳችን አይደለም (ኤፌ. 2፡8)። ሕጉን የምንጠብቀው ለመዳን አይደለም፤ አስቀድመን ስለዳንን እንጂ።

ሕጉን የምንጠብቀው ለመወደድ አይደለም፤ ስለተወደድን ነው እንጂ፣ ስለዚህ እግዚአብሔርንና ሌሎችን ለመውደድ እንፈልጋለን (ዮሐ. 14፡15ን ይመልከቱ)።

ሕጉ ኃጢአታችንን ያሳየናል (ያዕ. 1፡22-25፣ ሮሜ 3፡20፣ ሮሜ 7፡ 7)፣ አዳኝ እንደሚያስፈልገን ይጠቁመናል (ገላ. 3፡22-24)፣ መልካም በሆነው የሕይወት ጎዳና ይመራናል፣ የእግዚአብሔርንም የፍቅር ባሕርይ ይገልፅልናል።

በፍርድ ጊዜ ያለህ ተስፋ ምንድን ነው? ተግተህ በታማኝነት ሕጉን ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው መጠበቅህ ነው ወይስ የክርስቶስ ጽድቅ ነው የሚሸፍንህ? መልስህ የእግዚአብሔር ሕግ ሊያደርግ የሚችለውን ወይም የማይችለውን ተግባር በተመለከተ ምን ይነግርሃል?

መጋቢት 17
Mar 26

ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው


በፍቅር እና በሕግ መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ አስፈላጊ ነው።

በእርግጥ ቃሉ እንደሚናገረው ፍቅር ማለት ሕግን መፈጸም ነው።

በሮሜ 13፡8-10 ጳውሎስ “ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታል” ሲል አስተምሯል (ሮሜ 13፡8)። ከአሥርቱ ትእዛዛት ውስጥ ከመጨረሻዎቹ ከስድስቱ ብዙዎቹን ከዘረዘረ በኋላ፣ ጳውሎስ እነዚህ ሁሉ "ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ በሚለው ቃል ተጠቅልለዋል" ይላል (ሮሜ. 13፡9)። በእርግጥም ጳውሎስ በግልጽ “ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው” በማለት ያስተምራል (ሮሜ. 13፡10)። በገላ. 5፡ 14 ደግሞ ጳውሎስ “ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፡- ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው” ሲል ገልጿል (ገላ. 5፡14)። ሕግን የሚፈጽመው ግን ምን ዓይነት ፍቅር ነው? እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ምን ይመስላል? ማቴ. 23:23, 24ን ያንብቡ። “የሕጉ ዋና ነገሮች” ምንድን ናቸው? ዘዳ. 5:12–15ን እና ኢሳ. 58:13, 14ን ያንብቡ። እነዚህ ክፍሎች በሕጉ (በተለይም በሰንበት ትእዛዝ) እና አምላክ ለፍትሕና ለነፃነት ባለው ትኩረት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳዩት እንዴት ነው?



ኢየሱስ “የሕጉ ዋና ነገሮች” ሲል የገለፃቸው “ፍርድና ምሕረት ታማኝነትም ” ናቸው። በተለይም አንዱን ሕግ (ሰንበትን) በተመለከተ፣ በቃሉ ውስጥ ሰንበት ነጻ ከመውጣትና ከፍትሕ ጋር የተቆራኘ መሆኑን እናያለን።

በዘዳ. 5 ላይ የሰንበት ትእዛዝ የተመሰረተው እግዚአብሔር እሥራኤልን ከባርነት ነፃ ከማውጣቱ ጋር በተገናኘ ነው። ይኸውም ሰንበት የፍጥረት መታሰቢያ ብቻ ሳይሆን፣ ከባርነት እና ከጭቆናም ነፃ የመውጣት መታሰቢያ ነው። ፈቃዳችንን ከማድረግ ተመልሰን ሰንበትን ደስታ ብንለው በጌታም ደስ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት ብንሰኝ (ኢሳ. 58:13, 14) የሚለው ትኩረቱ ለሌሎች የፍቅርና የፍትሕ ሥራዎችን መፈፀም ላይ ነው፡- ይህም በጎ ማድረግ፣ የተራቡትን መመገብ፣ ቤት የሌላቸውን ማስጠጋት ናቸው (ኢሳ. 58፡3–10ን ይመልከቱ)።

ከእነዚህና ሌሎችም ብዙ ትምህርቶች የተነሳ፣ ሕግን በፍቅር ለመፈጸም የሚፈልጉ፣ የሚፈፅሟቸው ኃጢአቶች ብቻ ሳይሆን፣ በጎ መሆናቸውን እያወቁ በቸልተኝነት የማያደርጓቸው ነገሮች ጭምር ሊያሳስቧቸው ይገባል። ፍቅር የሕግ ፍጻሜ እንደመሆኑ መጠን፣ ሕግን መጠበቅ ኃጢአትን ከመሥራት መቆጠብ ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሕንና ምሕረትን በታማኝነት የሚያሰፍኑ በጎ የፍቅር ሥራዎችን በትጋት መሥራትን ይጨምራል። ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን የፊደል ሕጉን ካለመተላለፍ በላይ ነው።

መጋቢት 18
Mar 27

ከሁሉም በላይ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ


ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ከሆነ፣ አንድ ሰው ስህተት የሆኑ ነገሮችን ከማድረግ በመቆጠብ ብቻ የእግዚአብሔርን ሕግ በተሟላ ሁኔታ መጠበቅ አይችልም።

በቃሉ የተገለፀው የፍቅር ሕግ ክፉ እንዳናደርግ የሚያዘን ብቻ ሳይሆን፣ ሕጉ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሌሎች የሚገልፁ ተግባራትን እንድንፈጽም ይገፋፋናል።

ይህም ለቤተ ክርስቲያን አባላት ብቻ ሳይሆን በአለም ላሉ ሁሉ ጭምር እንጂ ምክንያቱም አለማችን እውነተኛ ክርስቲያናዊ ምሥክርነት እጅግ ያስፈገዋልና።

ያዕ. 2፡1-9ን ያንብቡ። እዚህ ላይ ምን ወሳኝ የሆነ መልእክት ተሰጥቶናል?



እዚህ ላይ ያዕቆብ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጸመውን ኢ-ፍትሐዊ ድርጊት፣ በተለይም ድሆችን ማዋረድንና የአንዳንድ ሀብታሞችን ጭቆና ይኮንናል። ከዚያም ለባልንጀራችን ወደተሰጠን የፍቅር ሕግ ትኩረታችንን ስቦ፣ ይህንን ሕግ ብትፈጽሙ "መልካም ታደርጋላችሁ " ይላል (ያዕ. 2፡8)።

ኤለን ጂ. ዋይት እንደገለፀችው፡- “ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው የምንገልፀው ለሰው ባለን ፍቅር ነው። ይህንን ፍቅር በውስጣችን ለማሳደር፣ የአንድ ቤተሰብ ልጆችም ሊያደርገን፣ የክብር ንጉሥ ከእኛ ጋር አንድ ሆነ። እናም ‘እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ’ (ዮሐ. 15፡12) የሚለው የስንብት ቃሉ ሲተገበር፣ ማለትም እርሱ ዓለምን እንደ ወደደ እኛም ዓለምን መውደድ ስንችል፣ ያን ጊዜ ለእኛ ያለው ተልዕኮ ይፈፀማል። ለሰማይም ገጣሚዎች እንሆናለን፣ ምክንያቱም በልባችን ውስጥ ሰማይ አለና።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 641

ክርስቶስ ዓለምን እንደ ወደደ እኛም ዓለምን ስንወድ፣ ያኔ ለሰማይ ገጣሚዎች እንሆናለን። የኢየሱስ ተከታይ ስለ መሆን እንዴት ያለ ግሩም መግለጫ ነው!

ኢየሱስ ተከታዮቹን “እኔ እንደ ወደድኳችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" ብሎ ያዛቸዋል (ዮሐ. 13:34)። ደግሞም ኢየሱስ “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ” ይላል (ዮሐ. 13፡35)።

ፍቅር የክርስቲያን እምነት ማዕከል ነው ምክንያቱም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና (1 ዮሐ. 4: 8, 16)። እግዚአብሔርን እንወዳለን የሚሉም እርስ በርሳቸው ሊዋደዱ ይገባል (ከ1ኛ ዮሐ. 3፡11፤ 4፡20, 21 ጋር ያስተያዩ)።

በዚህም መሠረት 1 ጴጥ. 4: 8 ክርስቲያኖችን:- “ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና፣ ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ " በማለት ይመክራል።

ክርስቶስ አለምን እንደ ወደደ፣ እኛም እንደ እርሱ አለምን መውደድ ይኖርብናል የሚለውን ሃሳብ ያሰላስሉ። ይህ ስለ ክርስቲያን ፍጽምና ጽንሰ-ሐሳብ እና ለዘለአለም ሕይወት እንዴት ገጣሚ እንደምንሆን በተሻለ ሁኔታ እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት ነው? መልስዎን በሰንበት ወደ ክፍልዎ ይዘው ይምጡ።

መጋቢት 19
Mar 28


ተጨማሪ ሀሳብ


የዘመናት ምኞት ከተባለው የኤለን ጂ. ኋይት መጽሐፍ “ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ” የተሰኘውን ርዕስ ከገጽ 637–641 ያንብቡ።

“ሌሎችን የሚያገለግሉ፣ በእረኞቹ አለቃ አገልግሎትን ያገኛሉ። እነርሱ ራሳቸው የሕይወትን ውኃ ይጠጣሉ፣ ይረካሉም። አስደሳች ፈንጠዝያዎችን ወይም በሕይወታቸው ውስጥ ለውጦችን አይመኙም። የሚያንገበግባቸው ርዕስ የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት የሚጠፉ ነፍሳትን እንዴት እናድን የሚለው ይሆናል። ማህበራዊ ግንኙነታቸውም ፍሬአማ ይሆናል። ለዋጃቸው ያላቸው ፍቅር ልቦናቸውን አንድ ያደርገዋል።

“ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ መሆናችንን ስንገነዘብ፣ የሰጠንን የተስፋ ቃሎች በግዴለሽነት አንናገራቸውም። ተስፋዎቹ በልባችን ውስጥ ይቀጣጠላሉ፣ በከናፍሮቻችንም ላይ ይንቦገቦጋሉ። እግዚአብሔር ሙሴን አላዋቂ፣ ሥነ-ምግባር የጎደለውን እና ዓመፀኛ ሕዝብን እንዲያገለግል በጠራው ጊዜ፡- ‘እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ' ብሎ ተስፋ ሰጠው (ዘፀ. 33:14)። ደግሞም 'በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ' አለው (ዘፀ. 3፡12)። ይህ ተስፋ የክርስቶስ ወኪል ሆነው የተቸገሩትንና የሚሰቃዩትን ለሚያገለግሉ ሁሉ የተሰጠ ነው።”—ኤለን ጂ. ዋይት፣ የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 641


የመወያያ ጥያቄዎች




1. 1 ቆሮ. 13:4–8ን ያንብቡ። 1ኛ ቆሮ. 13 ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለብን የሚገልጸው እንዴት ነው?

2. በማቴ. 25፡31-46 በጎቹን ከፍየሎቹ የሚለያቸው ምንድን ነው? ኢየሱስ እዚህ ላይ የተናገረውን፣ መዳን በሥራ እንደሆነ በማያስተምር መልኩ፣ እንዴት ልናስተውለው እንችላለን?

3. "እርሱ ዓለምን እንደ ወደደ እኛም ዓለምን መውደድ ስንችል፣ ያን ጊዜ ለእኛ ያለው ተልዕኮ ይፈፀማል። ለሰማይም ገጣሚዎች እንሆናለን፣ ምክንያቱም በልባችን ውስጥ ሰማይ አለና” የሚለው አባባል ለእርስዎ ምን ማለት ነው? (የሐሙሱን ጥናት ይመልከቱ) ይህ ስለ እግዚአብሔር ማንነትና ስለ ሰማይ ሁኔታ ምን ይገልጽልናል? የእግዚአብሔርን ፍቅር ለተጨቆኑ ተስፋንና ፍትሕን በሚያመጣ መልኩ በማስፋፋት፣ እንደ ሰማይ ዜጎች መኖር የምንችለው እንዴት ነው?

4. እግዚአብሔር ለፍቅር እና ለፍትሕ ያለውን ተቆርቋሪነት በዙሪያችሁ ላሉ ለማሳየት፣ በአጥቢያ ቤተክርስቲያንዎ ምን ተግባራዊ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው? በማህበረሰባችሁ ውስጥ እየሰራችኋቸው ያሉ መልካም ነገሮች ምንድን ናቸው? ማሻሻልና የበለጠ ትኩረት ማድረግ ያለባችሁ ነገሮችስ ምንድን ናቸው? ስለ አምላክ ፍቅርና ፍትሕ የተማርነውን ተግባራዊ ለማድረግ፣ በግልም ሆነ በቡድን ምን ዓይነት ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ እንችላለን?



የትንቢት መንፈስ መጻሕፍትን ተርጉሞና አሳትሞ ማሰራጨት ለሚፈልጉ የተደራጁ ቤተከርስቲያናት ሆነ ፈቃድ ያላቸው ደጋፊ የአገልግሎትድርጅቶች የተሠጠ

ማሳሰቢያ


የትንቢት መንፈስ(Spirit of Prophecy - SOP )መጻሕፍት በሙሉ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ንብረት ናቸው፡፡

እነዚህን ጽሁፎች በከፊልም ሆነ በሙሉ ወደ አማርኛም ሆነ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ቋንቋዎች በማስተርጎምና በማሳተም ለማዳረስ የሚፈልግ የተደራጀ ቤተከርስቲያንም ሆነ በዋናው መስሪያ ቤት ፈቃድ ያለው ደጋፊ የአገልግሎት ድርጅቶች ሥራውን ከመጀመሩ በፊት የኢትዮጵያ ዩኒየን ሚሽን በበላይነት በሚያስተዳድራቸው ሰበካዎችና ኮንፍራንስ የጽሁፍ ከፍል ጥያቄውን በጽሑፍ በማቅረብና በአካልም ቀርቦ በመወያየት ወደ ሰምምነት ከተደረሰ በኋላ አንዲያስተረጉም ፈቃድ ይሰጠዋል ትርጉሙም ሲጠናቀቅ የመጽሐፉን የመጀመሪያ ገጽ በታተመ ወረቀትና ሙሉውን መጽሐፍ በሲዲ ካስረከበ በኋላ ህትመቱና ስርጭቱ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ተከናውኖ ሥራውን መፈፀም ይቻላል።

በዚሁ መሠረት የትንቢት መንፈስ ጽሁፎችን በማሳተም ወንጌልን ለማዳረስ የሚጥሩ የተደራጁ ቤተክርስቲያናት ሆነ ፈቃድ ያላቸው ደጋፊ የአገለግሎት ድርጅቶች በእጅጉ ይበረታታሉ፡፡

ሆኖም ግን ይህንን በመተላለፍ ያለ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ዓለም አቀፍ ቤተ ከርስቲያን ፈቃድ በቤተክርስቲያኗ ስም የትንቢት መንፈስ ጽሁፎችን አሳትሞ ማስራጨት፤ በአገሪቱም ሆነ በዓለም ዓቀፍ የሥነ ጽሁፍ ህግ ያስጠይቃል፡፡ በተጨማሪም ድርጅቱ እያስተረጎመ ያለውን መጽሐፍ ሌላ አካል ተመሳሳዩን መጽሐፍ በመተርጎም ላልተፈለገ የጊዜ፣ የጉልበትና የገንዘብ ወጪም ይዳርጋል፡፡

ሰለሆነም የቤተክርስቲያኗ ህግና መተዳደሪያ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት ሁላችንም ጽሁፎችን በማሳተምም ሆነ በማሰራጨት የሶስቱን መላዕከት መልዕከት ለማዳረስ እንድንችል ጌታ ይርዳን፡፡

ድርጅቱ




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA Union SSL