የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ፡ማቴ. 7፡21-27፣ ዮሐ. 11፡40-44፣ 1ጴጥ. 3፡18፣ 1ሳሙ. 28፡3-25፣ ኤፌ. 6፡ 10-18።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ይህም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም፤ ምክንያቱም ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣል፤ እንግዲህ የእርሱ አገልጋዮች፣ የፅድቅ አገልጋዮች ለመምሰል ራሳቸውን ቢለውጡ የሚያስገርም አይደለም፤ፍፃሜአቸውም እንደሥራቸው ይሆናል።” (2 ቆሮ. 11፡14-15)
በ
ዚህ ጊዜ ያለችው አለማችን ሃይማኖታዊ ወይንም በረቀቀ መንገድ
ካምላክ ጋር መገናኘት በሚሉ ፍሬ ሀሳብ ባላቸው ጉዳዮችና
ትርኪምርኪ የሞላባቸው ስህተቶች እና ማታለያዎች በመስራት
በሚታወቀው ሆሊውድ ታግዛ ከተፈጥሮ በላይ እና እጅግ የረቀቁ ነገሮች
የሚንፀባረቁበት ማቅለጫ ማሰሮ ሆናለች። “ሞትን አትሞቱም” (ዘፍ 3፡4)
የሚለው የጥንቱ ማሳሳቻ ላለፉት አስርት አመታት አያሌ ተነባቢ መፅሐፎችና
ብዙ ተመልካች ያላቸው ፊልሞች እንዲሁም ታዋቂ የቪዲዮ ጌሞች እንዲፈጠሩ
መነሻ ሆኗል። በብዙ መልክ በአንዳንዱ ጉዳዮች ላይ በሳይንሳዊ ሽፋን እንኳን
በኩል እራሱን እየገለጠ ባለው የሰይጣን አስማት ትብታብ መጋለጣችንና
መፈተናችንን አንክድም።
በጣም ከሚያታልሉ አያሌ ክስተቶች መካከል አንዱ “የሞት ጫፍ” የሚባለው
ልምምድ ነው፤ ይህም የሞቱ ሰዎች ከህይወት ባሻገር ባለው ታሪክ ወዲያው
ተመልሰው መጥተው የሚናገሩበት ነው። ብዙ ሰዎች ይህንን ክስተት በማየት
ነፍስ እንደማትሞት ማረጋገጫ እንዳገኙ ያስባሉ።
በዚህ ሳምንት በመጨረሻ ጊዜ ባሉ አንዳንድ ማታለያዎች ማለትም በረቀቀ
መንገድ ከአምላክ ጋር መገናኘት፣ የሞት ጫፍ ልምምድ፣ የሞተ ሰው በሌላ
አካል ተመልሶ መወለድ፣ ሙታንን ማናገር እና ቀደምት የዘር ግንድ አምልኮና
የመሳሰሉት ላይ ትኩረታችንን እናደርጋለን። ለነዚህ አደገኛ ርዕሶች ተፅዕኖ
ራሳችንን ሳናጋልጥ ተገቢ የሆኑ ግንዛቤዎችን ልንወስድ ይገባናል።
የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለታህሳስ 1 ሰንበት ይዘጋጁ።
አለማችን በረቀቀ መንገድ ከአምላክ ጋር መገናኘት በሚለው ሃይለኛ ማዕበል
ተጥለቅልቃለች። “mysticism” (በረቀቀ መንገድ ከአምላክ መገናኘት)
የሚለው ቃል ውስብስብ ቃል ሲሆን የተለያዩ ሀሳቦችን ሸብቦ የያዘ ቃል
ነው። ከሃይማኖት አንፃር ግለሰቡ ከመለኮት ወይንም ፍፁም ከሆነው ነገር
ጋር በመንፈሳዊ ልምምድ ወይም እራስን ሰጥቶ መገናኘት ነው። ይህም
የአንዳንድ ቤተክርስቲያናት ልምምድ የባህሪ መገለጫቸውም ጭምር ሆኗል።
ክስተቱ በቅርጽና በስሜት ግለቱ ቢለያይም ነገር ግን ዝንባሌው የተፃፈውን
የእግዚአብሔርን ቃል በአንድ ሰው የግል ስሜት ተነሳሽነት በሚያደርገው
ልምምድ የመተካት ሂደት ነው። በየትኛውም መንገድ ቢሆን መፅሐፍ ቅዱስ
የአስተምህሮ ተግባሩን አጥቷል፤ ክርስቲያኑም ለርሱ/ለርሷ የግል ልምምድ
ተላልፈው እንዲሰጡ ሆነዋል።
ይህ አይነቱ ከሰው ሰው የሚለያይና በራስ
ስሜት ላይ ያተኮረ ሀይማኖት በተለይም በዚህ መጨረሻ ጊዜ ከሚመጣብን
ማንኛውም ማታለያ ሊጠብቀን አይችልም።
ማቴ. 7፡21-27ን ያንብቡ። በኢየሱስ የራሱ ቃላት ብርሃን አንፃር
ስናይ መንፈሳዊ ቤታችን “በአለት ላይ” እና “በአሸዋ ላይ”
መገንባት ማለት ምን ማለት ነው?
በድህረ ዘመናዊው የክርስቲያኖች አለም ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን
አስተምህሮ በተመለከተ ጊዜ ያለፈበትና አሰልቺ የሃይማኖት አካሄድ ነው
የሚል ጠንካራ ዝንባሌ ይታያል። በዚህ ሂደት ውስጥ የክርስቶስ ትምህርት
ክርስቶስን በሚሞግቱ ሰው ሰራሽ ሃሳቦች ተተክተዋል- ለምሳሌ ያክል እንዲህ
ይላሉ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች እነርሱ እንደሚረዱት ትክክለኛ
አይደሉም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ በተፃፉት መሠረት ታሪኮቹ እንዲሆኑ ሊፈቅድ
አይችልምና ይላሉ። ግላዊ ስሜትና ፍላጎት መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም
ወይንም ግልጽ የሆነውን እግዚአብሔርን መታዘዝ ያም ክርስቶስ ቤትን በአለት
ላይ ስለመመስረት የተናገረውን የእውነት ቃል ትምህርት ለመቃወም ጥቅም
ላይ ያውሉታል።
በክርስቶስ ኢየሱስ እስካመኑ ድረስ በአስተምህሮው ባናምንም ልዩነት
አያመጣም ብለው የሚያምኑ ሰዎች በአደገኛ መሬት ላይ ቆመዋል። አያሌ
ፕሮቴስታንቶችን ላይ ሞት የፈረዱት የሮም መርማሪዎች በክርስቶስ ኢየሱስ
ያምኑ ነበር። በክርስቶስ ስም “አጋንንትን ያወጡ” (ማቴ 7፡22) የነበሩት ሰዎችም
በእርሱ የሚያምኑ ነበሩ። “ሰው የሚያምንበት ነገር የሚያመጣበት ምንም ነገር
ውጤት የለም የሚለው አቋም አንዱና ዋነኛው ሰይጣን ስኬታማ የሆነበት
ማታለያው ነው። በፍቅር ከተቀበሉት እውነት የተቀባዩን ነፍስ እንደሚቀድስ
ያውቃል። ስለዚህ በተከታታይ የሐሰት ፅንሰ ሀሳቦችን፣ አፈ ታሪኮችን እና ሌላ
ወንጌልን መተካትን ይሻል” ኤለን ጂ. ኋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 520።
ከእግዚአብሔር ቃል ተፃራሪ ነገር እንድናደርግ ከሚያደርገን የሰው
ልጆች ስሜቶች እና ፍላጎቶች ዝንባሌ ጋር በምን መንገድ መታገል
እንችላለን?
ነፍስ በተፈጥሮዋ እንደማትሞት ለማረጋገጥ ከሚሞግቱ አንዳንድ ዝነኛ ፅንሰ
ሀሳቦች መካከል አንዱ “የሞት ጫፍ ልምምድ” ነው። Life After Life: The Investigation of a Phenomenon—Survival of Bodily Death (Atlanta,
GA: Mockingbird, 1975), Raymond A. Moody, Jr.በተሰኘው መጽሐፍ
ላይ ሬሞንድ ኤ.ሙዲ ጂ.አር ለአምስት አመታት ከመቶ በሚልቁ “በህክምና
የተረጋገጠ ሞትን” ሞተው ተመልሰው ስላገገሙ ሰዎች ውጤት ጽፏል።
እነዚህ ግለሰቦች ወደ ህይወት ተመልው ከመምጣታቸው አስቀድሞ በፍቅር
የተሞላና በደማቅ ብርሃን የታጀበን ፍጡር ማየታቸውን ተናግረዋል። በዚህም
የተነሳ “ከሞት ባሻገር የሰው ልጅ መንፈስ ህያው መሆኑን በሚያስደንቅ ሁኔታ
አረጋግጠናል” ብለው ይጠቁማሉ። ላለፉት ብዙ አመታት ሌሎች መጽሐፎች
ይህንን ተመሳሳይ ሃሳብ በማጉላት ታትመው ለንባብ በቅተዋል (2ኛውን
ትምህርት ይመልከቱ)።
ስለ ትንሳኤ የሚናገሩትን የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- 1ነገ.
17፡22-24፤ 2ነገ. 4፡34-37፤ ማር. 5፡41-43፤ ሉቃ. 7፡1417 እና ዮሐ. 11፡40-44። ከነዚህ ጥቅሶች መካከል ከሞቱ በኋላ
ስለተነሱ ሰዎች ሲናገር ምን ያህሎቸ ናቸው ሲሞቱ አእምሮአቸው
ንቁ ሆኖ የሆነውን ነገር ያውቁ የነበሩት? ይህንን መመለስ አስፈላጊ
የሆነው ለምንድን ነው?
በዘመናዊ ስነ ጽሁፍ ውስጥ የተመዘገቡት የሞት ጫፍ ልምምዶች በህክምና
ሞተዋል ቢባሉም ሙሉ ለሙሉ ያልሞቱ ናቸው በተለይም አራት ቀን
ከሞተው እና አስከሬኑ ከበሰበሰው አልአዛር ጋር ሲነፃፀር (ዮሐ. 11፡39)
የሌሎቹ ሞት ትክክለኛ ሞት የሚባል አይደለም። አላዛርም ሆነ ሌሎች
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ከሞት የተነሱ ሰዎች በሙሉ ከህይወት ባሻገር ስላለው
የህይወት ልምምድ፣ ገነትም ይሁን የማቆያ ስፍራ ወይንም ገሃነም አንዳቸውም
አልጠቀሱም። በርግጥም ይሄ መከራከሪያ ባለመናገራቸው ላይ የተመሠረተ
ቢሆንም የሞቱ ሰዎች ምንም እንደማያውቁ ከሚያስተምረው የመጽሐፍ
ቅዱስ ትምህርት ጋር ሙሉ ለሙሉ የሚስማማ ነው!
ታድያ ዛሬ ዛሬ ሞተው በህሊናቸው ንቁ ስለሆኑትና በተደጋጋሚ ስለሚገጥመን
ነገርስ? መጽሐፍ ቅዱስ ሙታን ምንም እንደማያውቁ የሚያስተምረውን
ሃሳብ ከተቀበልን (ኢዮብ 3፡11-13፤ መዝ. 115፡17፤ መዝ. 146፡4፤ መክ. 9፡10)
ሁለት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን እንገምታለን። ወይ በከባድ ስነ ልቦናዊ ሁኔታ
ውስጥ ሆኖ በምናብ መሠረት የሌላቸውን ነገሮች ማየት አልያም የሰይጣን
ማታለያ ሊሆን ይችላል (2ቆሮ. 11፡14)።
የሰይጣን ማታለያዎች የመሆን እድሉ
ከፍተኛ ነው፤ በተለይም አንዳንዶቹ ሰዎች የሞቱ ዘመዶቻቸውን እንዳነጋገሩ
ስለሚያወሩ ነው! ነገር ግን ከላይ ያየናቸው የሁለቱ ውህደት ውጤትም ሊሆን
ይችላል።
በዚህ ማታለያ መስፋፋትና ለብዙዎች አሳማኝ በመሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ትምህርት ተቃራኒ የሆነን ልምምድ ማንኛውም ሰው አለኝ ብለው ቢናገር
በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ላይ ፀንተን መቆማችን በጣም ወሳኝ ነገር
ይሆናል።
በሞት ጫፍ ልምምድ ህሊና ንቁ እንደሚሆን “ሳይንሱ”
ማረጋገጫ መስጠቱ አስደናቂ ነው። ይህ ሁኔታ ሳይንስ ራሱ
“የሚያረጋግጣቸው” ነገሮች ላይ እንኳን ሳይቀር ጥንቃቄ ማድረግ
እንዳለብን ምን ያስተምረናል?
ነፍስ እንደማትሞት የሚያስተምረው የአረማውያን ትምህርት መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ያልሆነውን ሞቶ ተመልሶ በሌላ አካል የመወለድን ጽንሰ ሀሳብ
ወይንም የነፍስን ወደ ሌላ ነገር መሸጋገር መሠረት ጥሏል። ይህ ጽንሰ ሀሳብ
በአንዳንድ ዋነኛ ሃይማኖቶች ዘንድ ተካቶ ይታያል። አብዛኛዎቹ ክርስቲያኖች
ከሞት በኋላ ነፍስ ሳትሞት ወደ ሰማይ አሊያም ወደ ገሃነም እንደምትሄድ
የሚያምኑ ሲሆኑ ሞቶ ተመልሶ በሌላ አካል መወለድን የሚያምኑ ሰዎች
የማትሞተው ነፍስ በብዙ የሞት ኡደት ታልፍና በድጋሚ ወደ ምድር ተወልዳ
እንደምትመጣ ያምናሉ።
በአንዳንዶች ከሞት በኋላ ተመልሶ መወለድ የመንፈሳዊ ዝግመተ ለውጥ ሂደት
እንደሆነ የሚታሰብ ሲሆን መንፈስ ፍጹም ለመሆን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ
ታላቅ የእውቀት ደረጃዎችንና የባህሪ እድገቶችን አልፋ መሄድ አለባት። የሂንዱ
እምነት ተከታዮች ዘላለማዊቷ ነፍስ በ6 የህይወት ክፍሎች ውስጥ በንቃተ
ህሊና እድገት ደረጃዎች (ሳምሳራ) ታልፋለች ብለው ያምናሉ፤ የህይወት
ክፍሎቹም፡- የውሃ ውስጥ ነዋሪዎች፣ ተክሎች፣ ተሳቢና ነፍሳት፣ አዕዋፍ፣
እንስሳት እና የሰው ዘር የሚያካትት ሲሆን እንደእነርሱ እምነት ይህ የሰማይ
ነዋሪዎችንም ጭምር ይመለከታል።
ዕብ. 9፡25-28ን እና 1 ጴጥ. 3፡18ን ያንብቡ። ኢየሱስ የሞተው
“አንዴ” ብቻ ከሆነ (ዕብ. 9፡28 1ጴጥ. 3፡18 የሰው ልጆችም
የሚሞቱት “አንድ ጊዜ” ብቻ ነው (ዕብ. 9፡27) ታዲያ
ለምንድነው አንዳንድ ክርስትያን ተብለው የሚጠሩ ሰዎች ሞቶ
ተመልሶ በሌላ አካል መወለድ እንዳለ የሚያምኑት?
ብዙ ሰዎች ማመን በሚገባቸው ነገር ላይ ሳይሆን እነርሱ ማመን የሚፈልጉትን
ነው። አንድ ጽንሰ ሀሳብ ለአኗኗራቸው ሰላምና ምቾትን ካመጣላቸው ኃሳቡን
ለመቀበል በቂያቸው ነው። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን በአፅንዖት ለሚከታተሉ
ሰዎች ሞቶ ተመልሶ በሌላ አካል የመወለድ ጽንሰ ሀሳብ የሚቀበሉበት ምንም
መንገድ የለም።
በመጀመሪያ ይህ ፅንሰ ሀሳብ “ነፍስ” ትሞታለች እና ሙታን በትንሳኤ ይነሳሉ
ብሎ ከሚያስተምረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ጋር ይጻረራል (1ተሰ. 4፡
13-18)።
ሁለተኛ መዳን በፀጋ በክርስቶስ የመዋጀት ስራ በማመን የሚለውን
አስተምህሮ ወደ ጎን የተወና (ኤፌ. 2፡8-10) የሰውን ሥራ የተካ ነው።
ሶስተኛ ዘላለማዊ እጣ ፈንታችን የሚወሰነው በዚህ ህይወት በምንወስነው
ውሳኔ ነው ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚጋጭ ነው (ማቴ.
22፡1-14፣ ማቴ. 25፡31-46)።
አራተኛ ይህ ፅንሰ ሀሳብ የክርስቶስን ዳግም ምፅዓት ትርጓሜ እና ተገቢነትን
ዝቅ ያደርጋል (ዮሐ. 14፡1-3)
አምስተኛ ከሞት በኋላ አንድ ሰው የህይወቱን ውድቀቶች ለማሸነፍ እድል
እንዳለው ይናገራሉ፤ ይሄ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም (ዕብ. 9፡27)።
በአጭሩ በክርስትና እምነት ውስጥ ከሞት በኋላ በሌላ አካል መወለድ
ለሚለው ሃሳብ ስፍራ የለም።
ከጥንት ጊዜ አንስቶ ሲደረግ የነበረው ሙታንን የማናገር ልምምድ እውቀትን በተለይም የወደፊቱን ክስተት ለማወቅ የሙታንን መንፈስ የመጥራት ሂደት ነው። የቅድመ አያት መናፍስት አምልኮ ለሟች ቅድመ አያቶች ትልቅ የመስጠት ባህል ነው ምክንያቱም አሁንም እንደቤተሰቡ አባል ስለሚቆጠሩ መንፈሳቸው በህይወት ያሉ ሰዎች የኑሮ ጉዳይ ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል። ይህ የአረማውያን ልምምድ ነፍስ እንደማትሞት ለሚያምኑና ይወዷቸው የነበሩ ሙታን ለናፈቋቸው ሰዎች በጣም ማራኪ ሀሳብ ሊሆን ይችላል። 1ሳሙ 28፡3-25ን ያንብቡ። ሳኦል ከአይንደር ሙታን ጠሪ ጋር ከነበረው ክስተት በመነሳት ከሙታን ጋር የመገናኘትን ማንኛውንም አካሄድ በሚቃረን መንገድ ልናገኘው የምንችለው መንፈሳዊ ትምህርት ምንድነው?
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚነግረን ሁሉም አይነት መናፍስት ጠሪዎች፣
ሙታንን የሚያናግሩ፣ ጠንቋዮች እና ሙታን ጠሪዎች በሙሉ በጥንታዊትዋ
እስራኤል ልማድ ለእግዚአብሔር ከፍተኛ ጥላቻ ስላላቸው በድንጋይ
ተወግረው እንዲሞቱ ይደረግ ነበር (ዘሌ. 19፡31፣ ዘሌ. 20፡6፣ 27፣ ዘዳ. 18፡
9-14)። በዚህ ህግ መሠረት ሳኦል ሁሉንም ሙታን ሳቢዎች እና መናፍስት
ጠሪዎች አስወግዷል (1ሳሙ. 28፡3፣ 9)
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ሲያጣ ግን ሳኦል ራሱ በከነዓን ከተማ
በአይንደር ወደምትገኘዋ ሙታን ጠሪ ሴት ሄደ (1ሳሙ. 28፡6-7፤ 15ን
ከኢያሱ 17፡11፤ መዝ. 83፡10 ጋር ያነፃፅሩ)። የሞተውን ነብዩን ሳሙኤልን
እንድታስነሳለት ጠየቃት በመናፍስት ጠሪዋ በኩል ከሳኦል ጋር ተነጋገረ
(1ሳሙ. 28፡13-19)
ሳሙኤልን የሚመስለው አታላይ መንፈስ ለሳኦል እንዲህ አለው “አንተና
ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ” (1ሳሙ. 28፡19)። ይህ አታላይ መንፈስ
ሳሙኤልን በማስመሰል የሳኦልን ሞት ተነበየ፤ ይህም ነፍስ በተፈጥሮዋ
አትሞትም የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ሀሳብ በድጋሚ ያረጋገጠ
መሰለ። ይህ ከባድ ማታለያ ነው፤ ሳኦል አስቀድሞ የኮነናቸው ሰዎች ጋር
መልሶ ከመሄድ ይልቅ ሊያስተውል ይገባው ነበር።
ከሁለት ምዕተ ዓመታት በኋላ ኢሳያስ ሲፅፍ እንዲህ አለ “ሰዎች
የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን
ጠይቁ ቢሏችሁ፣ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ
ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ? ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ! እነርሱም
እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።” (ኢሳ. 8፡1920፤ ኢሳ. 19፡3ንም ያንብቡ)።
በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ስንሆን ስህተት መሆናቸውን እያወቅን
እንኳን እነዛኑ የምናደርጋቸው ምን ያክል ጊዜ ነው? በእግዚአብሔር
ቃል ያለ እምነት፣ ፀሎትና መታዘዝ ከራሳችን ፍላጎት ሊጠብቁን
የሚችሉት እንዴት ነው?
የሞቱ ሰዎችን አካል ለብሶ መታየት እና ሌሎች ሰይጣናዊ መገለጦች ሙታንን
ከመጥራት ጋር ይመሳሰላሉ። በአካል የሚታዩትም የሞቱ የቤተሰብ አባላት፣
ወዳጆቻችን ወይንም ሌላ ሰው ሊሆን ይችላል። አካላዊ ቅርጻቸው እና
ድምፃቸው ከሞቱት ሰዎች ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው። እነዚህ ማታለያዎች
በእግዚብሔር ቃል ላይ መሰረታቸውን ያልጣሉትን ሰዎች ለማታለል ጥቅም
ላይ ይውላሉ። ኤለን ጂ. ኃይት ስታስጠነቅቅ “እነዚህ ኃሰተኛ መናፍስት
ሐዋርያትን መስለው በመምጣት በዚህ ምድር እያሉ ከፃፏቸው በተቃራኒ
ይናገራሉ።” ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 557። በተጨማሪም “በማታለሉ ድራማ
ጡዘት ላይ ሰይጣን ክርስቶስን መስሎ ይመጣል።” ታላቁ ተጋድሎ፣ ገፅ 624።
2 ቆሮ. 11፡14-15ን እና ኤፌ. 6፡10-18ን ያንብቡ። ከእንደዚህ
አይነቱ የሰይጣን ማታለያ ሊጠብቀን የሚችለው ምንድነው?
ሐዋርያው ጳውሎስ ሲያስጠነቅቀንም እንዲህ ይላል “ተጋድሎአችን ከስጋና
ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጠናትና ከሀይላት
እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው” (ኤፌ. 6፡
12)። ከዚህ ማታለያ ልንጠበቅ የምንችልበት ብቸኛ መንገድ “የእግዚአብሔርን
ሙሉ የጦር ዕቃ” በመልበስ ነው (ኤፌ. 6፡13)፤ እነዚህም ኤፌ. 6፡13-18 ላይ
ተገልፀዋል።
የሰይጣን በአካል ሌላን መስሎ መገለፅና መታየት በጣም አስፈሪና አታላይ
ሊሆን ቢችልም በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠለሉትንና በእርሱ ቃል ላይ
የተመሰረቱትን ወደተሳሳተ መንገድ ሊመራቸው አይችልም። ከአስተምህሮ
አንፃር ስናየው ስለሰው ልጅ የሞት ሁኔታ የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምህሮ
የሚያምኑ ሁሉ ከሙታን ጋር በተያያዘ በሚታዩ ወይንም ከሙታን ጋር
መገናኘት የሚለው ነገር መነሻው ሰይጣናዊ ስለሆነ በእግዚአብሔር የፀጋ
ሀይል ሊቃወሙት ይገባል። የተገለጠው ነገር ምንም ያክል ከፍ ያለ፣ አሳማኝ
እና እውነት ቢመስልም ሙታን በመቃብር አንቀላፍተው ስለመሆናቸው
በተማርነው ትምህርት ፀንተን ልንቆም ይገባናል።
የምትወዱትን ሰው አጥታችኋል እንበል፤ ያ የምትወዱት ሰው መጥቶ
ቢታያችሁስ? ፍቅሩን ቢገልጽላችሁስ? እንዴት እንደናፈቃችሁ ቢነግራችሁስ?
እርሱ ብቻ ሊያውቅ የሚችለውን ነገር በሙሉ ቢናገርስ? እነርሱ አሁን
በተሻለ ስፍራ ለይ እንደሚገኙ ቢነግሯችሁስ? ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስ
በሚያስተምረው የሙታን ሁኔታ ላይ መሰረት ካልጣለ በዚህ ማሳሳቻ እንዴት
በቀላሉ እንደሚወድቅ ያስቡ። በተለይም እነርሱ ራሳቸውም ይህንን ማመን
ስለፈለጉም ጭምር።
“የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ” ልበሱ ሲል ምን ማለቱ ነው
ስለመጨረሻው ጊዜ መታለሎች ከማውራታችን በፊት በየቀኑ
በሚኖረን የህይወት ልምምድ በሁሉም የህይወት ክፍሎቻችን ላይ
ይህንን ተግባራዊ የምናደርገው እንዴት ነው?
Read Ellen G. White, “Dealing With False Science,
Cults, Isms, and Secret Societies,” pp. 602–609, in Evangelism;
and “Spiritism,” pp. 86–93, in Confrontation.
የሞቱ ሰዎችን “በአጭር የሞባይል መልዕክት፣ በስልክ ጥሪ እና የቪዲዮ
ስብሰባ” በኩል ለማግኘት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ለማድረግ እየሠራ ያለ ድርጅት
አለ። የሞተውን ሰው ለመጥራት የሚያስችሉ ድረ ገፆች ያሉ ሲሆን ሲሞቱ
“ሌላ አካላዊ ለውጥ በማድረግ ወደ ዘላለማዊነት” ይሸጋገራሉ፤ ነገር ግን
“ህሊናቸው፣ ማንነታቸው እና መሰረታዊ የሚባሉ አካላዊ ቅርፆቻቸው
አይለወጡም” ይላሉ። ነገር ግን እነዚህ ነፍስን በስልክ የሚጠሩ ሰዎች የሙታን
መናፍስትን ከሕያዋን ጋር ማገናኘት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በሶስት
ደረጃዎች እያዘጋጁ እንደሆነ ተናግረዋል።
የመጀመሪያ ደረጃ “ህይወቱን ካጣው ቤተሰብ፣ ጓደኞች እና ሌሎች ባለሙያዎች
ጋር በሞባይል አጭር መልዕክት በኩል መላላክ መጀመር ነው”። ሁለተኛው
ደረጃ ደግሞ “በሌላኛው ስፍራ ዘላለማዊ ቦታ ላይ ከሚገኙ የምትወዷቸው
ሰዎች ጋር መነጋገር ያስችላል”። በሶስተኛ ደረጃ “ሞተው ያሉ ሰዎችን ከተለያየ
አቅጣጫ መስማት እና ማየት እንዲችሉ መንገዱን ይከፍትላቸዋል” ብለዋል።
ሞቶ ልታናግሩት የምትፈልጉትን ሰው ራሱ መሆኑን ለመለየት የሚያደርጉት
ሙከራ ደግሞ አስፈሪ ነው።
ለምሳሌ “ድረ ገፁ እንዲህ ይላል “ልጅ የሞተባቸው
ወላጆች የሚከተሉትን ጥያቄዎች ወንድ ወይንም ሴት ልጆቻቸውን
ይጠይቃሉ፡- “ልጅ እያለህ/ሽ ስኑፒ ተብሎ የሚጠራ ውሻ ነበረህ/ሽ? የአስር
ዓመት ልደትህን ስታከብር በኪስ የምትያዝ ቢላዋ ሰጥተንህ ነበር?”
ይህን ከዚህ በታች ካለው ማስጠንቀቂያ አንፃር ስንመለከተው በጣም አስገራሚ
ነው። “መናፍስት አንዳንዴ የሞቱ ጓደኞቻቸውን አካል ለብሰው ይታዩና
በህይወት በነበሩ ጊዜ ካጋጠማቸው ክስተቶች ወይንም ከተገበሯቸው ነገሮች
ጋር በማገናኘት ራሳቸውን ለሰዎች ያሳያሉ” ኤለን ጂ. ኋይት፣ የሃይማኖት
አባቶችና ነቢያት፣ ገፅ 684።
1. ኢየሱስ ሁሉንም ፈተና ‹‹ይመዝናል እና ይለካል›› ማለት
ምን ማለት ነው። ይህ በመጠበቅ ላይ ሳለን ምን ይጠቅመናል?
2.በትዕግስት መጠበቅ ምን እንደሆነ ሰዎች የግል ምስክርነት
እንዲሰጡ ያድርጉ። በዚህን ጊዜ ፍርሃታቸው ምን ነበር፣
ደስታቸውስ? ምን ትምህርት ተማሩ? የሙጥኝ ያሉበት
(የተደገፉበት) ተስፋስ?
3.እንደ ቤተክርስቲያን ሌሎች በፈተና ውስጥ ሆነው ስለሆነ ነገር
የእግዚአብሔርን ጊዜ በመጠባበቅ ለሚኖሩ ሰዎች ምን ያደርጋሉ?
4. ትዕግስትን ለማሳደግ የጸሎት ሚና ምንድነው? መንፈስ ቅዱስ
በህይወታቸው ትዕግስትን እንዲያሳድግላቸው የምትጸልዩላቸው
ነፍሳት አሉ?