የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት

የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

በፈተና ውስጥ ከክርስቶስ ጋር


የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 3ኛ ሩብ ዓመት 2022

ከሐምሌ 2- 8

3ኛ ትምህርት

Jul 9 - Jul 15




የወፎች መኖሪያ የብረት ሳጥን



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፦ ዘጸ 14, ዘጸ 15:22-27, ዘጸ 17:1-7, ምሳ 3, ሉቃ 4:1-13, 1 ጴጥ. 1:6-9.


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ በዚህ እጅግ ደስ ይላችኋል …. አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል “(1 ጴጥ 1:6)።

ሙ ሉ በሆነው የቀን በቀን ብርሃን፣ ብዙ የሙዚቃ ድምጾች በሚሰማበት ፣ ለመኖሪያነት በተሰራላት የብረት ሳጥን ውስጥ የምትኖር አንዲት ወፍ ጌታዋ ሊያስተምራት የሚፈልገውን መዝሙር መለማመድ አትችልም። ከዚያም ከዚህም እልፍ ሲል ሀፈፍ አድርጎ የሰማቸውን ድምጾች እንጂ ትክክለኛውን የመዝሙር ቅኝት በፍጹም መማር አትችልም። ጌታው የወፏን መኖሪያ ሸፍኖ እንድትዘምር የሚፈለገውን መዝሙር በትክክል መስማት በምትልበት ሥፈራ ያኖራታል። በጨለማ ይህንን መዝሙር ለመለማመድ ደግሞ ደጋግሞ ይሞክርና አንድ ቀን ትክክለኛውን ዜማ ድምጽ ያወጣል። ከዚያም ወፉ ወደፊት እንድመጣ ተደረጎ፣ ከዚያም መዝሙሩን በአግባቡ ተለማምዳ ይዘምራል። ስለዚህ እግዚአብሔር ከልጆቹ ጋር እንደዚህ ያደርጋል። ሊያስተምረን የሚፈልገው መዝሙር አለ፣ በመከራዎች ውስጥ ሆነን መዝሙሩን ስንለማመድ፣ ከዚያ ጀምሮ ለዘላለም እንዘምራለን። ”—Ellen G. White, The Ministry of Healing, p. 472. ወፉን ወደ ጨለማ ተሸክሞ የሚወስደው ጌታዋ ነው ። ሰይጣን ችግር እንደሚፈጥር ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፣ ነገር ግን ግራ ወደ መጋባት፣ ወደ ጉዳት እግዚአብሔር ራሱ ወደ ፈተና በመምራት በትጋት ይሳተፋል? የሳምንቱ ቅኝት፡ እግዚአብሔር ራሱ እያወቀ መከራ ጭምር ባለበት ልምምድ ውስጥ ሰዎችን የመራበት እርስዎ የሚያውቁት ምሳሌ አለ? እነርሱ እንዲዘምሩ የሚፈልጋቸው አዲስ መዝሙሮች ምንድናቸው? *የዚህን ሳምንት ትምህርት ለሐምሌ 9 ያጥኑ፡፡

ሐምሌ 3
July 10

በሞት ደርቻ ወደ ተስፋይቱ ምድር


“የእስራኤል ልጆችም ዓይናቸውን አቅንተው ሲመለከቱ፣ እነሆ፣ የፈርኦን ጦር ከኋላቸው ተቃርቧል። ከዚህም የተነሳ የእስራኤል ልጆች በጣም ፈሩ ወደ አምላካቸው ጮኁ።” (ዘጸ 14:10) በህይወትዎ ወደ ወጥመድ ተመርተው ወይም ወደ ሞት ጫፍ ደርሰው ያውቃሉ? ያም ቢሆን አንዳንዴ ጥሩ ነው፣ በአንድ ክፍል ውስጥ መልካም ልደት ብለው ለመጮህ የተዘጋጁ መልካም ጓደኞች ሲኖሩ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አስደንጋጭ እና በፍጹም የማይመች ይሆናል። ምናልባትም በትምሀርት ቤት ተደባዳቢ ዱርዬዎች፣ ወይም በስራ ቦታ መጥፎ የሆነ ስሜት እንዲሰማዎት ያደረገ የስራ ባልደረባ ሊኖር ይችላል።

እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር ከተነሱበት ቀን ጀምሮ ወደ የተስፋይቱ ምድር እስከደርሱበት ጊዜ ድረስ “በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በዳመና አምድ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት አምድ እግዚአብሄር በፊታቸው ሄደ” (ዘጸ 13:21):: እያንዳንዱ የጉዞአቸው ክፍል በእግዚአብሄር በራሱ የተመራ ነበር። ነገር ግን በመጀመርያ ወዴት እንደመራቸው ተመልከቱ፣ ባህሩ ከፊት ለፊታቸው ወደሚታይበት ሥፍራ፣ ተራሮች በጎናቸው፣ እና የፈርኦን ሰራዊት ከኋላቸው ነበሩ።

ዘጸአት 14ን ያንብቡ። እግዚአብሔር የሚያስጨንቅ መሆኑን ወደሚያውቀው ሥፈራ እስራኤላውያንን ለምን መራቸው?



የዳመና አምዱን መከተል ሁልጊዜ ደስተኛ ለመሆን ዋስትና አይደለም። ከባድ ልምምድም ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም በጽድቅ መሰልጠን ልባችን ወደሚፈተንበት ስፍራም ይወስደናል፣በተፈጥሮ አሳሳች የሆኑ ማለት ነው። (ኤር 17:9):: በእነዚህ ከባድ ጊዜያት ፣ እግዚአብሔርን ማወቅ ከመከራና ከስቃይ ነጻ መሆን ሳይሆን ነገር ግን ለእግዚአብሔር መመሪያዎች ግልጽ መሆንና አእምሮአችንን ሳያቋርጥ ለእርሱ መሪነት መስጠት ነው። እስራኤላውን ከዚህ ምን ትምህርት ተማሩ? ዘጸ 14:31



እርሱ ለእኛ የሰጠን እጅግ ብዙ የሆኑ ተስፋዎች ያሉን ቢሆንም፣ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን ማመን ከባድ የሚሆነው ለምንድነው እርሱን ‹‹እንድትፈራውና›› ‹‹እንድታምነው›› ሊያደርግ እግዚአብሔር ከባድ ወደሆነ ነገር የመራህን ጊዜ አስታውስ።

ሐምሌ 4
July 11

መራራ ውኃዎች


“የእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከሲና ምድረበዳ ሊጓዙ ተነሱ በረፊድምም ሰፈሩ ፤ ህዝቡም ይጠጡ ዘንድ ውኃ አልነበረም” (ዘጸ 17:1) ምናልባትም የምንፈልገውን ሁሉ ከእግዚአብሔር ላናገኝ እንችላለን፣ ነገር ግን የምንጠይቀውን ሁሉ ለማግኘት ጠብቀን አናውቅም? ዝም ብለን ስላሰብን የምንፈልገው ሳይሆን በእውነት የሚንፈልገውን ነው?

እስራኤላውያን በእርግጥ የሚፈልጉት አንድ ነገር ነበር ፣ እርሱም ውኃ ነበር። እግዚአብሔር በዳመና ሆኖ እስራኤልን በቀይ ባህር መካከል ከመራቸው ጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ለሶስት ቀናት ምንም ውኃ በልነበረበት ደረቅ ምድረ በዳ ተከተሉት። በተለይም ምድረ በዳ ውኃ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ የእነርሱ ጭንቀት ለማስተዋል የሚከብድ ነው። የሚፈልጉትን ውኃ ያገኙት መቼ ነበር?

ስለዚህ፣ እግዚአብሔር የመራቸው ወዴት ነበር? የዳመና አምዱ የመራቸው ወደ ማራ ሲሆን እርሱም ውኃ የሚገኝበት ሥፍራ ነበር። ተደንቀው ይሆናል። ነገር ግን ውኃውን በቀመሱ ጊዜ ፣ ወዲያው ከአፋቸው ተፉት ምክንያቱም ውኃው መራራ ነበር። “ህዝቡም ምን እንጠጣለን ብለው ሙሴ ላይ አጉረመረሙ።” (ዘጸ 15:24)

ከዚያም፣ ከጥቂት ቀናት በኋላ እግዚአብሔር እንደገና ሰረው። ነገር ግን በዚህ ጊዜ የዳመና አምዱ የቆመው ሙሉ በሙሉ ውኃ በሌለበት ቦታ ነበር። (ዘጸ 17:1)

ዘጸ 15- 22-27ን እና ዘጸ 17:1-7ን ያንብቡ። እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በማራና በራፊድም ስለ ራሱ መግለጥ የፈለገው ምንድነው? እነርሱ ስለ ምን ትምህርት ተማሩ?





የእስራኤል ልጆች በራፊድም የጠየቁት ምንድነው? ዘጸ 17:7። ተመሳሳይ ጥያቄን ጠይቀው ያውቃሉ? ጠይቀው ከሆነ ለምን? መልስ ካገኙ በኋላ ምን ተሰማዎት? ምን ትምህርት ተማሩ? ስንት ጊዜ ነው መጠየቅ ከማቆማችን በፊት መልስ ማግኘት የፈለግነው?





ሐምሌ 5
July 12

የምድረበዳው ታላቁ ተጋድሎ


“ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ከዮርዳኖስ ተመለሰ፣ በመንፈስም ወደ ምድረ በዳ ተመርቶ ፣ አርባ ቀን በዲያብሎስ ተፈተነ” (ሉቃ 4:1, 2)::

ሉቃ 4:1-13ን ያንብቡ ። ኃጢአት ውስጥ ሳይገቡ ፈተናን ስለ ማሸነፍ ከዚህ ምን ትምህርት ተማሩ?



ፈተናዎች በጣም የሚከብዱብን የምንመኛቸውን ነገሮች ስለሚቀሰቅሱብን ነው፣ እናም እኛ በተቸገርንበትና በደከምንበት ጊዜ ላይ የሚመጡ በመሆናቸው ነው ።

ሉቃስ 4 የክርስቶስ በሰይጣን የመፈተኑ ታሪክ መጀመሪያው በመሆኑ ወደ አእምሮአችን አንድ ከባድ ነገርን ያመላክተናል። በመጀመሪያ እይታ፣ መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን ወደ ፈተና እየመራው እንደሆነ ይመስላል። ሆኖም እግዚአብሄር እኛን በፍጹም አይፈትንም። (ያዕ 1፡13) ይልቅስ፣ ከዚህ በፊት እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ሊያጠራን ሲፈልግ በፈተና እሳት ውስጥ ያስገባናል። በሉቃስ 4 የሚያስደነግጠው ነገር መንፈስ ቅዱስ ወደ አስፈሪ የሰይጣን ፈተና ወስጥ ገብተን እንድንፈተን የሚመራን መሆኑ ነው። በዚህን ጊዜ፣ ፈተናዎች ከብደው ሲታዩን እግዚአብሔርን በትክክል እየተከተልኩት አልነበረም ብለን ለማሰብ እንፈተናለን። እርግጥ ይህ እውነት ላይሆን ይችላል። “ብዙውን ጊዜ በፈተና ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ እየመራን እንደነበር እንጠራጠራለን። ነገር ግን ክርስቶስን በሰይጣን እንዲፈተን ወደ ምድረበዳ የመራው መንፈስ ቅዱስ ነበር። እግዚአብሔር ወደ ፈተና በሚያመጣን ጊዜ ለእኛ መልካም የሆነ ነገር ሊያደርግልን ሊፈጽምልን ዓላማ አለው። የሱስ የእግዚአብሔርን ተስፋዎች በማመን ዝም ብሎ ሳይጋበዝ ወደ ፈተና አልመጣም፣ ፈተና ወደ እርሱ በመጣ ጊዜም ቢሆን እሸነፍ ይሆን በሚል ተስፋ አልቆረጠም። እኛም እንዲህ ልንሆን ይገባል።”ኤሌን ዋይት ዘመናት ምኞት ገጽ 126, 129::

አንዳንዴ ወደ ፈተና እሳት ውስጥ ስንገባ በመጥራት ፋንታ እንቃጠላለን። ፈተና ፣ ክፉኛ ሲጫንብን ፣ እኛ ተስፋ የምናደርገው ክርስቶስ ፈተናውን ተቋቁሞ በማለፉ እኛም ተስፋ እንዳለን ነው። መልካሙ ዜና ክርስቶስ የኃጢአታችን ተሸካሚ በመሆኑ፣ ምክንያት እርሱ የእኛን ፈተና ያለማሸነፍን ውድቀት ዋጋ የከፈለ በመሆኑ (ፈተናው ምንም ቢሆን) እርሱ ማናችንም ከምንሄድበት ወይም ከምንገባበት የፈተና እሳት የበለጠ ውስጥ ስለ እኛ ገብቶ የተጋፈጠ በመሆኑ፣ እኛ እንዲሁ የተጣልን ወይም የተረሳን አይደለንም። ለትልቁ ኃጢአተኛም ቢሆን ተስፋ አለ። (1ጢሞ 1:15) በአሁኑ ጊዜ ምን አይነት ፈተና እየተጋፈጡ ነው?

በራሳችን ህይወት ውስጥ ለሚያጋጥሙን ፈተናዎች ከክርስቶስ ህይወት የተማርነውን በህይወት ልምምዳችን ልንጠቀመው የምንችለውን ነገር ለማወቅ ጥቂት ሰዓት በጸሎት እናሳልፍ። መቼም ቢሆን ራስን ወደ ፈተና ማስገባት ጥሩ አይደለም። ሆኖም ግን ብንፈተን አዳኝ አለን።

ሐምሌ 6
July 13

ጸንቶ የሚቆይ ውርስ


1 ጴጥ 1:6, 7ን ያንብቡ። ጴጥሮስ እያለ ያለው ምንድነው?



ጴጥሮስ ይህንን የጻፈው ከአስቸጋሪ ነገሮች ጋር ትግል እያደረጉ ብቸኝነት ስለሚሰማቸው ሰዎች ነው። እርሱ የጻፈላቸው“ በጳንጦስ፣ በገለቲያ ፣በቀጳዶቂያ በእስያና በቢታኒያ ለተበተኑ የእግዚአብሔር ምርጦች ነው።” (1 ጴጥ 1:1)። ይህ አካባቢ አሁን ምዕራባዊ ቱርክ ብለን የምናውቀው አካባቢ ነው። ከጥቂት ጥቅሶች በኃላ፣ ‹‹ እነርሱ በልዩ ልዩ ፈተና ማዘናቸውን ይናገራል››(1 ጴጥ 1:6) ጴጥሮስ ‹‹መጸተኞች›› እና ‹‹የተበተኑ›› ሲል ምን ማለቱ ነው? ይህ መከራቸውን የሚጨምረው እንዴት ነው?



በዚህ ዘመን ክርስቲያን መሆን አዲስ ነገር ነበር፤ እነርሱም በቁጥራቸው አናሳ ሲሆኑ በተለያዩ ስፍራዎች በብዙሃኑ ዘንድ በጣም ያልተስተዋሉና እጅግ በከፋ ሁኔታ ስደት ሲደርስባቸው ነበር። ነገር ግን ጴጥሮስ ለእነርሱ ሊያረጋግጥላቸው የፈለገው ‹‹ እነዚህ መከራዎች ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ አለመሆናቸውን ነው።›› (1 ጴጥ 1:6, 7) ‹‹በመከራዎች ሁሉ›› ውስጥ ተፈትኖ የሚያልፍ እምነት የእውነተኛ እምነት ግብ ነው። በመከራ ውስጥ ለሚገኙት ጴጥሮስ ሊሰጣቸው የፈለገው ዋስትና ምን ዓይነት ነው? ይህ ተስፋ ለእኛ ለአማኞች ምን ማለት ነው?



ምንም ዓይነት መከራ ቢሆን፣ ምንም ቢሰቃዩ፣ ክርስቶስ ሲመጣ ከሚያገኙት እነርሱን ከሚጠብቀው ዘላለማዊነት ጋር ሊወዳደር የሚችለው እንዴት ነው? እኛ እየተጋፈጥነው ያለው ምንም ይሁን ምን ፤ጴጥሮስ ለእነርሱ የተናገረው ለእኛም ነው። መከራዎቻችን ምንም ያህል የሚያሳምሙና ከባድ ቢሆኑ፣ በአዲስ ሰማይና በአዲስ ምድር መከራ ስቃይና ሞት የሌለበትን ዘላለማዊ ህይወት እርግጠኛ የሆነ ፍጻሜን ከእይታችን ሊያጠፋብን አይገባም። በክርስቶስ ሞት በተሰጠን ዋስትናና ተስፋ፣ በፈተና ውስጥም ሆነን ፣ እምነት በማጣት ፋንታ፣ ከእምነታችን ፊት የሚቆመውን ማንኛውንም ነገር የምንቋቋምበትን ኃይል እንዲሰጠን መጠየቅ ምንኛ ያስፈልገናል።

ሐምሌ 7
July 14

በእሳት መፈተን


አሌክስ የሚባል ወጣት ነበር። አስከፊ ከሆነው የወጣትነት ችግር ውስጥ የመጣ ነው፤አደንዛዥ ዕጽ እና የእስራት ልምምድም ነበረው። ነገር ግን ከዚያ በኋላ (በአንድ አሌክስ በሰረቀበት) የቤተክርስቲያን አባል መልካምነት አሌክስ ስለ እግዚአብሔር በመማርና በማወቅ ልቡን ለክርስቶስ ሰጠ። ምንም እንኳ ዛሬም ብዙ ትግልና ችግሮች ቢኖሩበትም፣ ያለፉ ልምዶቹ ልቡን የሚያንጠለጥሉ ቢሆንም፣ አሌክስ አዲስ ሰው ነው። እግዚአብሔርን የሚወድና መውደዱን ትዕዛዛቱን በተግባር እያሳየ ያለ ወጣት ነው። (1 ዮሐ 5:1 2):: በአንድ ሁኔታ አሌክስ ልቡ ተነካ ፣ አገልጋይ መሆን አለብኝ ብሎ አሰበ። ሁሉም ነገር ወደዚያ ያመለክታል። ያኔ እርሱ ለእግዚአብሔር ጥሪ ምላሽ እየሰጠ ነበር።

በኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነገሮች መልካም ነበሩ። ከዚያም አንድ ነገር ከሌላው በመከታተል በትክከል መስራትን አቆሙ፤ ህይወቱም የተለየ መሆን ጀመረ። የገንዘብ ምንጮች መድረቅ ጀመሩ፤ የቅርብ የነበሩ ጓደኞች መራቅ ጀመሩ፣ ስሙን የሚያጠፉ እውነት ያልሆኑ ወሬዎችን አወሩበት። ከዚያም ሁልጊዜ ይታመም ጀመር ፤ የህመሙን መንስኤ ማንም ሊያውቅ አልቻለም ፤ ትምህርቱን ማጥናት ባለመቻሉ ሊያቋርጥ እንደሆነ ተሰማው። ከዚያ ሁሉ ነገር በላይ፣ በሚኖርበት ህብረተሰብ በቅርቡ ና በቀላሉ የሚገኘው የአደንዛዥ እጹ ልምድ ታላቅ ፈተና ሆኖበታል። አንድ ጊዜ ሳይታሰብ ወድቆ ተገኘ። አሌክስ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በምን ምክንያት እየሆኑ እንደሆን ለማስተዋል አልቻለም፣ በተለይም እግዚአብሔር ወደዚህ ትምህርት ቤት ለአዲስ ጅምር መርቶ እንዳመጣው ያውቅ ነበር። አሌክስ ስህተት ነበር? እንዲህ ከሆነ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ያ ሁሉ ልምምድ ስህተት ነበር ማለት ነው? እንዲያውም የእምነቱ መሰረታዊ ነጥቦች ሁሉ ጥያቄ ውስጥ ገቡ ።

አስቡ፤ በዚህ ችግር ውስጥ ሆኖ አሌክስ እርስዎን ሐሳብ ቢጠይቅ። ምን ምላሽ ይሰጣሉ? እንደ እርሱ ያሉ ሌሎችን ሊረዳ የሚችል ምን የግል ተሞክሮ አለዎት? የትኛውን የመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይጠቀማሉ? የሚከተሉት ጥቅሶች በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ምን ያህል ጠቃሚ ናቸው? ምሳ 3, ኤር 29:13, ሮሜ 8:28, 2 ቆሮ 12:9, እብ 13:5።



አምላክን የሚከተሉ ሁሉም በሚባል ደረጃ እግዚአብሔር አብሯቸው መኖሩን የተጠራጠሩባቸውን አስቸጋሪ ጊዜ አሳልፈዋል። በዚህ ጊዜ በጣም አስፈላጊ የሆነው ነገር በተስፋው ለመጣበቅ ፣እግዚአብሔር ባለፈው ህይወትዎ ያደረገውን ደጋግሞ መቁጠር፣ እና ለእምነትና ለጽናት አጥብቆ መጸለይ ናቸው። እግዚአብሔር በእኛ ተስፋ አይቆርጥም።

ሐምሌ 8
July 15


ተጨማሪ ሀሳብ


የኤለን ዋይትን አባቶችና ነብያት የሚለውን መጽሀፍ ‹‹ ጉዞ›› ገጽ 281–290 “ከቀይ ባህር ወደ ሲና›› ገጽ 291-302 በዘመናት ምኞት ‹‹ፈተና››,” ገጽ 114–123 ያንብቡ።

“ነገር ግን በጥንት ዘመን እግዚአብሄር ህዝቡን ወደ ራፊድም መራቸው፣ እናም ታማኝነታችንን ለመፈተን ወደዚያው ሊመራን ይችላል። ሁል ጊዜ ወደ ሚመች ስፍራ ብቻ አይመራንም። እንደዚህ ካደረገ ፣ ለራሳችን ብቁ ነን ብለን በማሰብ እርሱ ረዳታችን መሆኑን እንረሳለን። ራሱን ለእኛ ለመግለጥ ይናፍቃል፣ በቅርባችን ያሉትን በረከቶች ለማሳየት ይፈልጋል‹ እናም እኛ ረዳተቢስ መሆናችንን እንድንረዳ ስለሚፈልግ መከራንና ተስፋ መቁረጥን ይፈቅዳል፣ ከዚያም ለእርዳታ እርሱን መጥራት እንድንማር ያደርጋል። ከጠንካራ ዓለት ቀዝቃዛ ምንጭን ያፈልቃል። እርሱን ፊት ለፊት እስክናየው ድረስ እርሱ ስለ እኛ ምን ያህል ሸክም እንደተሸከመልን እና ስለእኛ ሸክምን ለመሸከም ምን ያህል ደስተኛ እንደነበር ልንረዳና በፍጹም ልናውቀው አንችልም። ብንረዳው የህጻን በሚመስል እምነት፣ ሁሉንም ወደ እርሱ ባቀረብን ነበር። ”ኤሌን ዋይት ፣ ‹‹ረፍድም›› Advent Review and Sabbath Herald, April 7, 1903.


የመወያያ ጥያቄዎች



1. ብዙውን ጊዜ ፈተናን እንደ ግል ነገር እናያለን ፣ አዎ ልክ ነው! በተመሳሳዩ ሁኔታ እንደ ቤተክርስቲያን ወይም እንደ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ህብረት ልንከላከለው የሚገባ ፈተና አለ? ከሆነ ምን?

2.ወደማይመቹ ቦታዎች የተወሰዱ ለመናገር ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ጠይቅ። ለምንድነው የማይመቹ የነበረው? እነዚህን ነገሮች እንደገና መጎብኘት ቢችሉ በተለየ እይታ ማየት ይችሉ ነበር?

3.እኛ ተፈትነን መንጻት እንዳለብን የሚያደርግበትን የእግዚአብሔርን አሰራር ሁላችንም እናስተውላለን ። ፈተናዎች ዋጋ የላቸውም ብለን በምናስብበት መልኩ ቢከሰቱ፣ ለምሳሌ እንድ ስው በመኪና አደጋ በድንገት ቢሞት ፣ ስለዚህ ሁኔታ ምን ሀሳብ እንዳላችሁ በክፍል ውስጥ ተወያዩበት።

4.ፈተናዎችን ተቋቁማችሁ ታማኛ ሆናችሁ መገኘት እንድትችሉ እርስ በእርሳችሁ አንዱ ለሌለው ለመጸለይ ጊዜ ውሰዱ።

5. በክፍላችሁ ውስጥ የምታውቁት ፈተና የደረሰበት ሰው አለ? ከዚያም የተነሳ መንገዱን ሳተ? እንደ ክፍል ይህንን ሰው ተጨባጭ በሆነ መልኩ ልትረዱት የምትችሉት እንዴት ነው?




Shalom Teleconference Ministries Inc -- Translated by Ethiopian SDA union SSL