የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ

ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ 2ሳሙ. 11:1–27፣ 2ሳሙ. 12:1–23፣ ዘፍ. 3:1–8፣ 1ዮሐ. 1:9.
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “አምላኬ ሆይ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ፣ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ” (መዝ. 51፡10)።
ብ
ዙ ሰዎች ትንሽ ሰላም እና ጸጥታ ለማግኘት በጣም የሚሹ
ይመስላሉ። የሚከፈልም ከሆነ ለመክፈል ፈቃደኞች ናቸው።
በብዙዎቹ ታላላቅ ከተሞች በሰዓት የሚከራዩ ከኢንተርኔት ነፃ
የሆኑ ክፍሎች አሉ። ሕጎቹ ጥብቅ ናቸው--ምንም ዓይነት ጫጫታም ሆነ
እንግዳ ማምጣት አይፈቀድም። ሰዎች በጸጥታ ለመቀመጥ፣ ለማሰብ ወይም
ጋደም ብለው ለሚቆዩበት ጊዜ ለመክፈል ፈቃደኞች ናቸው። በአየር ማረፊያ
ጣቢያዎች ጥቂት ለማረፍ የሚከራዩ ሳጥን መሳይ መተኛዎችን (sleep pods)
መጠቀም ወይም ድምፅ የሚቀንሱ የጆሮ ማድመጫዎችን መሰካት የተለመደ
ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪ በሥራ ቦታ ፈጣን ዕረፍት ለማግኘት የሚረዱ ፊትና
አናት ብቻ የሚሸፍኑ በጭንቅላት የሚጠለቁ የሸራ ጭብሎች መጠቀምም
እንዲሁ እየተለመደ መጥቷል።
በተመሳሳይ እውነተኛ ዕረፍትም ዋጋ አለው። በሕዝብ ግንኙነት ሙያ
የተካንን ነን ባይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የራሳችንን ዕጣ ፈንታ
በራሳችን መወሰን እንችላለን የሚለውን እሳቤ ተንተርሰው፤ ዕረፍት ምርጫ
እና እቅድ ብቻ ነው ብለን እንድናምን ሊያደርጉን ቢዳዱም፣ ቢያንስ ይህን
በሐቀኝነት ስናጤን፣ በልባችን እውነተኛ ዕረፍት ማምጣት አለመቻላችንን
እንገነዘባለን። የአራተኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያን አባት አውግስጢኖስ
የእግዚአብሔርን ፀጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት በታዋቂው የእምነት ቃል
(መጽሐፍ 1) ላይ፡ -“አንተ ለራስህ ሠርተኸናል፣ ልቦቻችን በአንተ ዕረፍት
እስኪያገኙ ዕረፍት የላቸውም ” ሲል በአጭሩ ገልጾታል።
በአንድ ፀደይ ወራት ምሽት በዕረፍት የለሽ መቅበጥበጥ የተሞላው ንጉሥ
ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ሠገነት ወዲያና ወዲያ ይንጎራደድ ነበር። በወቅቱ
በዮርዳኖስ ማዶ ካለው ሠራዊቱ ጋር አብሮ መሆን ነበረበት። የአምላክ
ሕዝቦች አሞናውያንን ድል እንዲያደርጉና በመጨረሻም ለመንግሥቱ ሰላም
እንዲያመጡ መምራት ነበረበት።
ዳዊት መሆን ይገባው በነበረበት ስፍራ አለመገኘቱ ፈተና
የሚፈተንበትን በር ከፈተ። በ 2ሳሙ. 11 1–5 የሚገኘውን
ታሪክ ያንብቡ። ዳዊት ምን ዓይነት ከባድ ኃጢአት ፈጸመ?
ዳዊት አንዲት “በጣም ውብ ሴት” በቤቷ ሠገነት ላይ ሆና ገላዋን ስትታጠብ
ተመለከተ። በዚያን ምሽት ወደ ኃጢአት የሚመራ ዝንባሌውን መቆጣጠር
ስለተሳነው የታመነ የጦር መኮንን ሚስት ከሆነችው ቤርሳቤህ ጋር ተኛ።
እንደ ጥንት ነገሥታት ሁሉ ዳዊትም ፈላጭ ቆራጭ የሚባል ዓይነት ፍጹም
ኃይል ነበረው። እንደ ንጉሥነቱ ማንኛውንም ሰው የሚያስተዳድሩትን ደንቦች
መከተል አላስፈለገውም። ሆኖም ይህን ታሪክ የሚቀይር ክስተት መፈጸሙን
ተከትሎ በዳዊት ቤተሰብ ላይ የደረሰው አሳዛኝ ታሪክ--ንጉሥ ቢሆንም
ከእግዚአብሔር ሕግ በላይ እንዳልነበረ ያስታውሰናል።
በእርግጥም ሕጉ ለሕዝቡ ከለላና ጥበቃ ለመስጠት በዚያ እንደመኖሩ፤
ንጉሡ እንኳ ሳይቀር ቢያፈነግጥ አስከፊ መዘዞች ይከተሉት ነበር። ዳዊት
የአምላካዊውን ሕገ ገደብ እንደተላለፈ--ያን ተከትለው የመጡ ውጤቶች
በሁሉም የሕይወቱ ገጽታዎች ይሰሙት ጀመር። የዳዊት በጋለ ስሜት የተሞላ
ቅጽበታዊ እርካታ ሳይስተዋል እንደቀረ ተሰምቶት ነበር። ሆኖም ቤርሳቤህ
ጸነሰች። ባለቤቷ ደግሞ ሩቅ ነው።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ሳሙ. 11፡6-27። ዳዊት ኃጢአቱን
ለመሸፋፈን የሞከረው እንዴት ነው?
ሌላው ቀርቶ ኦርዮን ወደ ሚስቱ ቤርሳቤህ ገብቶ እንዲተኛ ዳዊት ያሰበው
እጅግ የተወሳሰበ ዕቅድ እንኳ ሳይሳካለት ቀረ። የላቀና ድንቅ ስብዕና የነበረው
ኦርዮን ለዳዊት ተንኮለኛ ምክር የሚከተለውን ምላሽ ሰጠ፡ “ ‘ታቦቱ፣ እስራኤልና
ይሁዳ በድንኳን ሆነው፣ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ሰዎች አውላላ ሜታ ላይ
ሰፍረው፣ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋር ለተኛት እንዴት
ወደ ቤቴ እሄዳለሁ?’ ” (2ሳሙ. 11፡11)። በመጨረሻም ተስፋ የቆረጠው ዳዊት
ኃጢአቱን ለመሸፈን በተንኮል ወደ ማስገደል ሴራ አማተረ።
በጨለማ ከተዋጡ የዳዊት ሕይወት ክፍሎች በአንዱ መልካም የምሥራች ተሰማ፡ እነሆ እግዚአብሔር ነቢዩን ላከ። ናታን እና ዳዊት በሚገባ ይተዋወቃሉ። ቀደም ሲል ዳዊት የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመሥራት የነበረውን ውጥን አስመልክቶ ናታንን አማክሮት ነበር (2ሳሙ. 7)። አሁን ግን ነቢዩ ለንጉሡ የሚያከናውነውን ሌላ ሥራ ይዞ ብቅ አለ። ናታን ወዲያውኑ የዳዊትን ኃጢአት ነግሮ እርሱን ከማሸማቀቅ ይልቅ ታሪክ ለመንገር የመረጠው ለምን ይመስሎታል? 2ሳሙ. 12፡1-14።
ምን ማለት እንዳለበት ያውቅ የነበረው ናታን--ዳዊት ሊያስተውለው
በሚችለው መንገድ ነገረው። የቀድሞው ዕረኛ ዳዊት በቀላሉ ራሱን በቦታው
ላይ አድርጎ ማየት የሚችልበትን ታሪክ ነገረው። ናታን የዳዊትን የዳበረ
የፍትሕና ቅንነት ስሜት በደንብ ያውቅ ነበር። በመሆኑም፤ በአንድ በኩል--39-
ናታን ባጠመደው ወጥመድ ውስጥ ዳዊት ሰተት ብሎ ገባ ብሎ አንድ ሰው
ሊናገር ይችላል።
ዳዊት ሳይታወቀው የራሱን የሞት ፍርድ በተናገረ ጊዜ ናታን “ያ ሰው አንተ
ነህ” አለው (2 ሳሙ. 12፡7)። “ያ ሰው አንተ ነህ” ተብሎ የሚነገርባቸው ብዙ
መንገዶች ያሉ ሲሆን--አንዱ በጩኸት፣ ሌላው በክስ እና በግለሰቡ ላይ ጣትን
በመቅሰር ወይም ደግሞ በአሳቢነትና ጥንቃቄ በተሞላው መንፈስ ናቸው።
የናታን ቃላት በጸጋ የተሞሉ ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ይታመናል።
በዚያው
ቅጽበት ዳዊት ከልጆቹ አንዳቸው እያወቁ ከፈቃዱ ቢያፈነግጡ እግዚአብሔር
ሊሰማው የሚችለው ዓይነት ህመም እርሱም ሊሰማው ይችላል። በዳዊት
አእምሮ አንዳች ነገር አቃጨለ። የሆነ ነገር ልቡን ሰንጥቆ ሲያልፍ ተሰማው።
ዳዊት “በቤርሳቤህ ላይ በድያለሁ” ወይም “እኔ ነፍሰ ገዳይ
ነኝ” ከማለት ይልቅ “እግዚአብሔርን በጣም በድያለሁ” የሚል
ምላሽ የሰጠው ለምንድን ነው? (2ሳሙ. 12:13፣ በተጨማሪ
መዝ. 51:4)።
ዳዊት ልባችን እንዲቅበዘበዝ የሚያደርገው ኃጢአት በዋነኝነት ፈጣሪ እና
ቤዛ የሆነውን አምላክ ማቃለል እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር። ራሳችንን ጎድተን
በሌሎችም ላይ ቀውስ እንፈጥራለን። በቤተሰባችን ወይም በቤተ ክርስቲያን
ላይ ውርደት እናስከትላለን። ውሎ አድሮ እግዚአብሔርን በመጉዳት በጎልጎታ
ወደ ሰማይ በሚያመላክተው አስጨናቂ ምሰሶ ላይ ሌላ ምስማር እንመታለን።
“የነቢዩ ማስጠንቀቂያ የዳዊትን ልብ ስለነካው ኅሊናው ተነቃቃ፤ የጥፋቱም
ግዝፈት ፈጥጦ ታየው። ነፍሱ በእግዚአብሔር ፊት በጸጸት ተደፍታና ከናፍሮቹ
እየተንቀጠቀጡ “እግዚብሔርን በጣም በድያሁ” አለ። በሌሎች ላይ የተደረገ
በደል
ሁሉ ከተበዳዩ ወደ እግዚአብሔር ይደርሳል። ዳዊት በኦርዮንም ሆነ በቤርሳቤህ
ላይ ከፍተኛ ኃጢአት ፈጽሟል፤ ይህም ከልቡ ተሰምቶታል። ዘላለማዊውን
ያህል የከበደው ግን በእግዚአብሔር ላይ የሠራው ኃጢአት ነበር።” የኃይማኖት
አባቶች እና ነቢያት፡ ገጽ፡ 398።
ዳዊት ሳያውቀው በራሱ ላይ የፍርድ ቃል ከተናገረ በኋላ (2ሳሙ. 12፡5-6)
ናታን የኃጢአቱን ስፋትና ጥልቀት በመግለጽ ተገዳደረው። የዳዊት ልብ
ተሰበረ፤ ኃጢአቱንም ተናዘዘ። ወዲያውኑ ናታን “ ‘እግዚአብሔር ኃጢአትህን
አስወግዶታል’ ” (2ሳሙ. 12:13) ሲል ይቅር መባሉን አረጋገጠለት።
በእግዚአብሔር ይቅርታ ላይ ምንም ዓይነት የጥበቃ ጊዜ የለም። ዳዊት
ይቅርታ ከመቀበሉ አስቀድሞ ጸጸቱ ከልብ የመነጨ ስለ መሆኑ ማረጋገጫ
ማቅረብ አልነበረበትም።
ይሁን እንጂ በ2ሳሙ. 12፡10–12 ዳዊት የፈጸመው ኃጢአት የሚያስከትለውን
መዘዝ አስቀድሞ የተነበየው ናታን፤ የሚወለደው ልጅ እንደሚሞት ተናገረ።
እግዚአብሔር የዳዊትን ኃጢአት አስወግዶታል ማለት ፍቺው
ምንድን ነው? በደሉን ደምስሶ ንጹህ አደረገው? ሁሉም ሰው
ይረሳለት ይሆን? ጥያቄዎቹን እያሰላሰሉ 2ሳሙ. 12፡10-23
ያንብቡ።
በተጨማሪ ዳዊት ሕፃኑ ሲሞት፣ ቤተሰቡ ሲተራመስ (የአምኖንና የአቤሴሎም
ታሪኮች በእውነተኛ የቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች ሁለት ጥሩ
ምሳሌዎች ናቸው)፣ የወደፊት ነገሩ የማያስተማምን እየሆነ ሲሄድ ሲመለከት
በእነዚህ ጥያቄዎች ግራ ሳይጋባ አልቀረም። ምንም እንኳ ኃጢአቱ እንደ ኦርዮን
እና አዲስ የተወለደው ህፃን በመሳሰሉ ንጹሃን ላይ ጉዳትና መዘዝ ቢያስከትልም፤
አምላካዊው ጸጋ ይህን እንደሚሸፍንና ኃጢአት የሚያስከትለው መዘዝ ሁሉ
አንድ ቀን እንደሚወገድ ዳዊት መረዳት ጀምሮ ነበር። እስከዚያው ድረስ ግን
በእግዚአብሔር ጸጋ ውስጥ ኅሊናው ዕረፍት ማግኘት ይችላል።
ዳዊት ምን እንደሚያስፈልገው ሆኖ ነበር በትክክል የተሰማው?
ምን ናፈቀ? መዝ. 51፡1-6።
ዳዊት በመዝ. 51 ልቡን ከፍቶ ኃጢአቱን በይፋ ይናዘዛል። የዳዊት የምሕረት
ጩኸት የእግዚአብሔርን የማይጠፋ ፍቅርና ታላቁን አምላካዊ ርኅራኄ
ይማርካል። መታደስን ይናፍቃል።
በየሱስ ውስጥ ማረፍ ምን ያህል የከበረ ዋጋ እንዳለው ስናስብ፤ በመጀመሪያ
ከእኛ ውጪ እርዳታ የሚሰጥ እንደሚያስፈልገን መገንዘብ ያስፈልገናል።
ኃጢአተኞች እንደመሆናችን አዳኝ ያስፈልገናል። በደለኝነታችንን በመገንዘብ
በብቸኝነት ሊያጥበን፣ ሊያነጻንና ሊያድሰን ወደሚችለው እንጮኻለን። ይህን
ስናደርግ መበረታታትን ማግኘት እንችላለን።
እዚህ ላይ በምንዝር የወደቀ፣
ተንኮለኛ፣ ነፍሰ ገዳይና ከአምስቱ ትእዛዛት ቢያንስ አምስቱን የጣሰው ግለሰብ
የእርዳታ ጥሪ ያቀርባል--አምላካዊውን የይቅርታ ተስፋ ቃል የሙጥኝ ይላል።
እግዚአብሔር የዳዊትን በደል ይቅር ካለ፤ እርስዎስ ምን ተስፋ
ይኖሮታል?
ዳዊት ለኃጢአቱ ምንም ዓይነት ሰበብ ወይም ምክኒያት ለመደርደር ሳይሞክር ከተናዘዘ በኋላ እግዚአብሔርን መማጸኑን ይቀጥላል። እግዚአብሔርን ምን ጠየቀው? መዝ. 51:7–12።
ዳዊት በሂሶጵ ስለ መንጻት ተጠቅሞ ያቀረበውን ማጣቀሻ ወደ ቤተ መቅደሱ
ያመሩ እስራኤላውያን በሙሉ የሚያውቁት ቃል ነው። በሙሴ ሕግ ውስጥ
የተገለጹትን የመንጻት ሥርዓቶች በማጣቀሻነት ሲያቀርብ (ዘሌ. 14፡4) ወደፊት
የዓለምን ኃጢአት ለማስወገድ የሚመጣውን መሥዋዕት--የመሥዋዕት ኃይል
ተገንዝቦ ነበር።
በተጨማሪም ዳዊት “ሐሤትንና ደስታን” እንዲሰጠው ጠየቀ። ከኃጢአቱ
ግዝፈት አኳያ ይህ በመጠኑም ቢሆን እንደ ድፍረት አይቆጠርም?
ምናልባት ለዚህ የሚከተለውን ሐረግ ማድመጥ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡
“አንተን የሚያመልኩህን ሐሤትና ደስታ ልሰማ ወደ ምችልበት መቅደስህ
ዳግመኛ ለመግባት ይቅር መባሌን ንገረኝ።”
አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ ከእግዚአብሔር ፊት ተሰወሩ
(ዘፍ. 3፡8)። ዳዊት ኃጢአት ከሠራ በኋላም እንኳ ያቀረበው
ጥያቄ ከዚህ የተለየ የሆነው ለምንድን ነው? መዝ. 51፡ 11-12።
ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት መመላለስ የሚያስችለውን ኅሊና ማጣት
አልፈለገም። ያለ መንፈስ ቅዱስ አንዳችም ኃይል እንደሌለው ተገንዝቧል።
ከቤርሳቤህ ጋር በቀላሉ በኃጢአት እንደወደቀ ሁሉ ዳግመኛ ሸርተት ሊል
እንደሚችል ተገንዝቧል። ስለዚህ በራሱ የመተማመኑ ነገር አብቅቷል።
ዳዊት ወደፊት የሚቀዳጃቸው ድሎች ምንጩ የእርሱ ብርታትና
ጥንካሬ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ በሚኖረው መተማመን--ይኸውም
ከእግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር።
በድል ላሸበረቀው የክርስትና ሕይወት መንስኤው የሱስ እንጂ እኛ
አይደለንም። የእርሱን መገኘት እንናፍቃለን፣ መንፈሱን እንመኛለን፣ የማዳን
ደስታውንም እንሻለን። መታደስ ብሎም ወደ ቀደመው ንጽህና መመለስ
እንደሚያስፈልገን እንገነዘባለን። በመለኮት ዳግም መፈጠር የሚያስችለን
የእርሱ ዕረፍት ያስፈልገናል። የፍጥረት ዕረፍት ይቅር ከመባል ብዙም የራቀ
አይደለም። “አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ
በውስጤ አድስ” (መዝ. 51፡10) በተሰኘው ጥቅስ ውስጥ የፍጥረት ስያሜ ጥቅም
ላይ ውሎ እንመለከታለን። በብሉይ ኪዳን “መፍጠር” (ባራ) የእግዚአብሔር
ብቻ እንደመሆኑ፤ አንዴ ዳግመኛ ከተፈጠርን--ማረፍ እንችላለን።
ከጥፋተኝነት ስሜት ነጻ መውጣት የሚያስገኘውን ደስታና ሐሴት
ካልተለማመዱ--ይህ እንዳይሆን ምን አገዶት? የጥፋተኝነት ስሜት
ከሆነ ከዚህ ሊረዳዎ ከሚገባ ታሪክ ምን ይማራሉ?
በአሳፋሪ ውድቀትና ይቅርታ ውስጥ ካለፍን በኋላ ልናደርግ የምንችለው በጣም ተፈጥሯዊ ነገር ሁኔታው መቼም እንዳልተከሰተ አድርጎ መርሳት ሊሆን ይችላል። የውድቀት ትዝታዎች ብርቱ ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ዳዊት ከገጠመው አሳዛኝ ተሞክሮ አኳያ ምን ማድረግ ፈለገ? መዝ. 51፡13-19።
አንድ ከሸክላ የተሠራ ጎድጓዳ ሳህን ወይም ውድ የአበባ ማስቀመጫ ቢወድቅና
ቢሰባበር--ውይ ብለን ካዘን በኋላ ያን ፋይዳ ቢስ ስብርባሪ ጠራርገን እንጥላለን።
በጃፓን የሸክላ ስብርባሪዎችን ዳግመኛ በመሥራት የተካነ ኪንትሱጊ የተባለ
ባሕላዊ የሥነ ጥበብ ተቋም አለ። እንደ ፈሳሽ ወርቅ ወይም ብር ያሉ ውድ
ማዕድናት የተሰበሩትን ቁርጥራጮች አንድ ላይ ለማጣበቅና የተሰበረውን ዕቃ
ወደ ቀደመ ውበቱ በመመለስ ዋጋ ያለው አድርጎ ለመቀየር ያገለግላሉ።
እግዚአብሔር በደላችንን ይቅር ብሎ እንደገና በፈጠረን ቁጥር--አንዳች
ነገር ይለወጣል። የእግዚአብሔር ውድ ይቅርታ ስብራታችንን በአንድ ላይ
ያጣብቃል፤ በዐይን የሚታዩት ስብራቶች ትኩረትን ወደ ጸጋው መሳብ
ይችላሉ። የእግዚአብሔር ድምጽ ማጉያዎች መሆን እንችላለን፡ “አንደበቴም
ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል” (መዝ. 51፡14)። ራሳችንን በራሳችን
ለመጠገን (ደረጃ በደረጃም ቢሆን) አይሞከርም። የተሠበሩ መንፈሶቻችንና
የተጸጸቱ ልቦቻችን ለእግዚአብሔር ውዳሴ ለማቅረብ በቂ እንደመሆናቸው፤
ዓለም በእኛ ዙሪያ ሊያያቸው የሚችላቸው የብርሃን ጨረሮች ናቸው።
በመዝ. 51 እና በ1ዮሐ. 1፡9 መካከል ምን ዓይነት ግንኙነት
አለ?
1 ዮሐ. 1፡9 የመዝ. 51 አጭር ማጠቃለያ ነው። ዳዊት እንደሚያውቀው እርሱ
“የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አይንቅም” (መዝ. 51፡17)። ዮሐንስ ደግሞ
እንዲህ ሲል ማረጋገጫ ይሰጠናል “ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን
ይቅር ሊለን፣ ከአመጸ ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው” (1ዮሐ. 51፡
17)።
ይህም ሆኖ ዳዊት በፈጸመው ድርጊትና በቤተሰቡ ላይ በተወው ምሳሌ
ያደረሰውን ከፍተኛ ጉዳት ማስተካከል አልቻለም። ውሳኔዎቹ እና ድርጊቶቹ
ባስከተሉት መዘዝ ሥቃይ ተቀብሏል። ሆኖም ዳዊት ይቅር እንደተባለ ያውቅ
ነበር። አንድ ቀን እውነተኛው የእግዚአብሔር በግ መጥቶ በእርሱ ቦታ
እንደሚቆም በእምነት መቀበል እንዳለበት ያውቅ ነበር።
በ 1ዮሐ. 1፡9 ላይ የሚገኙትን ተስፋዎች በራስዎ ሕይወት ላይ
ተግባራዊ ማድረግን መማር የሚችሉት እንዴት ነው? ይህን ካደረጉና
የተስፋ ቃሉ ለእርስዎም እንደተሰጠ ካወቁ በኋላ ምን ሊሰማዎ ይገባል?
፡
1.ኃጢአተኝነታችንን አምነን በመቀበላችን እና ይቅር በመባላችን
አስፈላጊነት መካከል ያለውን ትክክለኛ ሚዛን ማግኘት የምንችለው
እንዴት ነው? (ይቅር እንደ ተባሉ ወንዶች እና ሴቶች የአጽናፈ
ዓለም ንጉሥ ልጆች እየኖርን።)
2.ኃጢአት ሁሉ--ውሎ አድሮ በእግዚአብሔር ላይ የሚፈጸም
በደል የሆነው ለምንድን ነው? በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት
መሥራት--ምን ማለት ነው?
3.እንደ ኦርዮን ወይም አዲስ የተወለደው የዳዊትና የቤርሳቤህ
ልጅ በመሳሰሉት ንጹሐን ሰዎች ላይ ከሚደርሰው መከራ ጋር
ለሚታገል አማኝ ያልሆነ ሰው ምን ማለት እንችላለን? እንዲህ
ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም አምላካዊውን ፍቅርና ፍትሕ ማስረዳት
የምንችለው እንዴት ነው? የታላቁ ተጋድሎ ጽንሰ ሀሳብ፤ ጠቃሚ
አመለካከት ለመያዝ እንዴት ይረዳናል?
4.መጽሐፍ ቅዱስ የዳዊትንና ቤርሳቤህን ታሪክ በሁለት ሙሉ
ምዕራፎች የዘገበው ለምንድን ነው? የዚህ ታሪክ መነገር ዓላማ
ምንድን ነው?
5.ኃጢአት ከእግዚአብሔር የሚለየን ስለመሆኑ በመዝ. 51፡11-12
የተገለጸውን ሐሳብ በጥልቀት ለመመልከት ይሞክሩ። ይህ እንዴት
እንደሚሆን አስመልክቶ የእርስዎ ተሞክሮ ምን ይመስላል? ምን
ይሰማዎታል? ይህ መለያየት የሚሰማውን ስሜት እንዴት ለሌላ
ሰው መግለጽ ይችላሉ? ጉዳዩ ምቾት የማይሰጠው ለምንድን
ነው? የጸጋ ተስፋ ብቸኛው መድኃኒት የሆነው ለምንድን ነው?