
ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘፍ. 2:7– 23፣ ዘፍ. 3:1–6፣ 2ጴጥ. 1:3–11፣ 2ጴጥ. 2:1–17፣ ዕብ. 13:7፣ 17፣ 24።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡“እነሆ እግዚአብሔር በኀይሉ ከፍ ከፍ ብሎአል፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?” ኢዮብ 36:22
አ
ብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የመጀመሪያዎቹን የዘፍጥረት መጽሐፍ
ሦስት ምዕራፎች እና የታሪኩን ተዋናዮች ያውቋቸዋል--እግዚአብሔር፣ አዳም፣
ሔዋን፣ መላእክት እና እባብ። ስፍራው “ኤደን” በሚል ስያሜ የሚታወቀው ውብ
የአትክልት ቦታ ነው። ታሪኩ ተከታታይነት ያላቸውን አመክኖአዊ ክስተቶች እግር
በእግር የሚከተል ይመስላል። እግዚአብሔር ይፈጥራል። ለአዳምና ሔዋን ትእዛዝ
ይሰጣል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት ይሠራሉ። አዳምና ሔዋን ከኤደን ይባረራሉ።
የዘፍጥረት መጽሐፍን የመጀመሪያዎቹን ምዕራፎች በተለይ በሥነ ትምህርት መነጽር
ስንከታተል--በገጸ ባህሪያቱ፣ በክስተቱ መነሻ ቦታ ወይም መቼት እና በታሪኩ ዙሪያ
ጥልቅ የዕውቀት ዐይን ምልከታና ግንዛቤ የሚሹ ዐውዶች እንዳሉ እናስተውላለን።
“በምድር ጅማሮ የተቋቋመው ሥርዓተ ትምህርት ለመጪዎቹ ጊዜያቶች
ለሰብዓዊው ፍጡር ምሣሌ እንዲሆን የተሰጠ ነበር። መርኅዎችን ፍንትው አድርጎ
የሚያሳየውና አርአያ የሆነው ትምህርት ቤት፤ የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን መኖሪያ
በነበረው በኤደን ተቋቋመ። የኤደን የአትክልት ስፍራ የመማሪያ ክፍል ሲሆን
ተፈጥሮ መማሪያ መጽሐፍ፣ ፈጣሪ ራሱ መምህር--የሰብዓዊው ቤተሰብ የሆኑት
ወላጆች ደግሞ ተማሪዎች ነበሩ።”—Ellen G. White, Education, p. 20.
ጌታ የዚህ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት መሥራች፣ ርዕሰ መምህርና መምህር ነበር።
ሆኖም እንደምናውቀው፤ ውሎ አድሮ አዳምና ሔዋን ሌላ መምህር በመምረጣቸው
የተሳሳተውን ትምህርት ቀሰሙ። ከዚያስ ምን ተከተለ? ለምን? ከዚህ የቀደመ የሥነ-
ትምህርት መግለጫ ዛሬ ምን ዓይነት እገዛ ሊሰጠን የሚችል ትምህርት መውሰድ
እንችላለን?
ምንም እንኳ ብዙውን ጊዜ የአትክልት ስፍራውን እንደ መማሪያ “ክፍል” ባናስበውም፤
ነገር ግን ባልተበከለ ሙላት የተንሰራፋውን ያን የእግዚአብሔርን የፍጥረት ሥራ-በተለይ ኤደንን በዚህ መልኩ ማሰብ በእርግጥ ትርጉም ይሰጣል። ዛሬ ከምንገኝበት
ሁናቴ አኳያ ይህን ማሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ባልወደቀው ዓለም ይኖሩ የነበሩት
እነዚያ ያልወደቁ አካላት በቀጥታ ከፈጣሪያቸው የተማሯቸውን ትምህርቶች
የቀሰሙት በዚያ “ክፍል” ውስጥ እንደሆነ ይታመናል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘፍ. 2፡7-23። እግዚአብሔር አዳምን ሲፈጥረው፣
በኤደን ገነት ሲያኖረውና የሚሠራውን ሲሰጠው--ከፍላጎቱና ዓላማው ምን
ያስተውላሉ?
እግዚአብሔር ሰውን ወንድ እና ሴት አድርጎ በአምሳሉ ከፈጠረ በኋላ መኖሪያ
ስፍራና ተገቢ የሆነ ሥራ ሰጣቸው። በዚህ መማር ማስተማር መሃል ያለውን ተውህቦ
ሲመለከቱ--ግንኙነቱን ተስማሚ ሆኖ ያገኙታል። አዳምን የፈጠረው እግዚአብሔር
አምላክ በፍጡሩ ውስጥ ያለውን ክህሎት ጠንቅቆ ያውቃል። አዳም ክህሎቱን
በሚገባ መረዳት እንደሚችል የሚያውቀው አምላክ እርሱን ማስተማር ይችላል።
እግዚአብሔር ለሰው ኃላፊነት ቢሰጥም፤ ደስተኛ እንዲሆንም ፍላጎቱ ነበር።
ምናልባት እርሱን የደስታ ባለቤት ከሚያደርግባቸው መንገዶች አንዱ ኃላፊነት
መስጠት ነው። ለነገሩ--ኃላፊነት በመቀበል እና ያን ኃላፊነት በታማኝነት ከታለመው
ግብ በማድረስ እርካታ እና ደስታ ማግኘት የማይችል ማነው? የአዳምን ልብ
የሚያውቀው እግዚአብሔር ይህ ፍጡሩ ሊያዳብርና ሊያበለጽግ የሚችለውን ነገር
ያውቅ ስለ ነበር እነሆ የኤደንን የአትክልት ስፍራ የመንከባከብ ኃላፊነት ሰጠው።
“እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት
በዔደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው” (ዘፍ. 2፡15)። አዳም የገነት መኖሪያ
ቤታቸውን እያለማ ብሎም እየተንከባከበ ትምህርት መቅሰሙ እሙን ቢሆንም፤
ይህችን ዓለም በኃጢአትና ሞት ብቻ ለምናውቃት ለእኛ ሥራው ይጠይቅ የነበረውን
ጉልበትም ሆነ ትምህርት ማሰብ አዳጋች ነው።
እግዚአብሔር እንስሳትን ጥንድ፣ ጥንድ አድርጎ ለአዳም እንደፈጠረና እንዲሁም
ሔዋንን ለአዳም ሚስት አድርጎ መፍጠሩን በዘፍ. 2፡19-23 እናነባለን። አዳም የህይወት
አጋር እና ረዳት እንደሚያስፈልገው የተገነዘበው እግዚአብሔር፤ እንስት ፈጠረለት።
በተጨማሪ ሰው ከእርሱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደሚያስፈልገው ያውቅ ስለ ነበር፤
እርሱና ሰብዓዊ ፍጡሮቹ የቀረበ ትስስር የሚፈጥሩበትን የተገደበ አካባቢ በኤደን
የአትክልት ስፍራ ፈጠረ። እነዚህ ሁሉ--እግዚአብሔር በፍጥረት ወቅት የነበረውን
ዓላማና ልባምነት እንዲሁም ለሰብዓዊው ፍጡር የነበረውን ፍቅር የሚመሰክሩ
ነበሩ። ዛሬ በእኛ እና በኤደን መካከል ካለው ግዙፍ ልዩነት አኳያ ክስተቶቹ ምን
ይመስሉ እንደነበር ለመገመት አዳጋች ቢሆንም--በዐይነ ህሊና ለመሳል መሞከር ጥሩ
ስሜት ሳይሰጥ አይቀርም!
ምንም እንኳ ከኤደን የአትክልት ስፍራ እጅግ ርቀን ብንገኝም ዛሬም
ከተፈጥሮ መማር እንችላለን። ትምህርቶቹን ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው
መነጽር አኳያ ለመተንተን ስንሞክር--ምን ይመስላሉ? እንዴት
ልንጠቀምባቸውስ እንችላለን?
ለመማር ማስተማር ሂደት ወሳኝ የሆኑ ቁሳቁሶች በየክፍሉ ተሟልተው መገኘት
ለብዙ መምህራን ላቅ ያለ ደስታ ይሰጣል። እግዚአብሔር ለኤደን ገነት የመማሪያ
ክፍል ያለውን ራእይ ስንመለከት የአዳምና ሔዋን የመማሪያ አካባቢን ለማዘጋጀት
ያደረገውን ጥንቃቄ ለማስተዋል አንቸገርም። “ክፍሉ” ውብ በሆኑ ነገሮች የተሞላ
እንዲሆን ምኞቱ ነበር። እያንዳንዱ አበባ፣ ወፍ፣ እንስሳ እና ዛፍ አዳምና ሔዋን
ስለ ዓለማቸው እና ስለ ፈጣሪያቸው አብልጠው መማር የሚችሉበትን ዕድል
እንደሰጣቸው መገመት እንችላለን።
ከዘፍጥረት ምዕ. 2 ወደ ምዕ. 3 ድንገተኛ ለውጥ እንደተደረገ እንመለከታለን።
እግዚአብሔር በመለኮታዊ ዕቅዱ የፈጠራቸውን የመልካም ነገሮች ዝርዝር በሙሉ
ተመልክተናል። ሆኖም በዘፍ. 3፡1 የእግዚአብሔርን የመምረጥ ነፃነት ስጦታ
በትኩረት እንድንመለከት የሚያደርግ አንድ ትዕይንት እናገኛለን። “ከዱር እንስሳት
ሁሉ ተንኮለኛ” የነበረውን የእባቡን በዚያ ስፍራ መገኘት የሚያወሳው አገላለጽ፤
እስከዚያን ጊዜ ድረስ ጥቅም ላይ ሲውል ለነበረው ቋንቋ አዲስ መዝገበ ቃል የፈጠረና
የቀደሙትን አዲዮስ! ሲል የተሰናበተ ነበር። ቀደም ባሉት ምዕራፎች “መልካም”፣
“እጅግ መልካም”፣ “አስደሳች” የተሰኙ ገላጭ ቅጽሎች የእግዚአብሔርን የፍጥረት
ሥራ ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውለው ነበር። ነገር ግን አሁን በእባቡ አማካይነት ለየት
ያለ ቃና ያለው ድምፅት ተደመጠ። “ተንኮለኛ” በሚል የቀረበው ቃል በአንዳንድ
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “አታላይ” በሚል ፍቺ ቀርቧል። ከዚያ ቀደም በፍጽምና
ብቻ ተሞልቶ የነበረው ስፍራ በድንገት ከአሉታዊው ባህሪ ተዋወቀ።
የዘፍጥረት መጽሐፍ “ተንኮለኛ” በሚል ከተጠቀሰው ቃል በተቃራኒ እግዚአብሔርን
ይገልጸዋል። እግዚአብሔር ግልጽና የታወቀ ነገር በአትክልት ስፍራው ይኖሩ ከነበሩት
ጥንዶች ይጠብቅ ነበር ። በዘፍ. 2፡16-17 ከቀረበው መልእክት እንደምናስተውለው
አዳምና ሔዋን የግድ ሊታዘዙ የሚገባቸውን አንድ ቁልፍ ሕግ ደንግጓል--ከተከለከለው
ፍሬ እንዳይበሉ። ከዚህ ታሪክ የቱንም ዓይነት ትምህርት ልናገኝ ብንችልም አንድ ነገር
ግን ከሁሉ ገዝፎ ይወጣል፡ አዳምና ሔዋን ለመታዘዝም ሆነ ላለመታዘዝ ከመምረጥ
ነፃነት ጋር የመፈጠራቸው እውነታ! በመሆኑም ገና ከመጀመሪያውና በዚያ ኃጢአት
ባላውቀ ዓለም እንኳ ሰብዓዊው ፍጡር የተጎናጸፈውን የመምረጥ ነፃነት በተጨባጭ
መመልከት እንችላለን።
በዘፍ. 3፡1-6--እባቡ የተጠቀመውን አገላለጽ እና ሔዋን ደግማ
የተናገረቻቸውን ቃላት ይመርምሩ። እባቡ ለሔዋን ከሰጣት መረጃ ምን
ይገነዘባሉ? ሔዋን በወቅቱ መልካምና ክፉውን በሚያሳውቀው ዛፍ ላይ
ስለነበራት አመለካከት ምን ይገነዘባሉ?
አዳም ከዛፉ ከበላ “በእርግጥ ትሞታለህ” ሲል ጌታ በዘፍ. 2፡17 ነግሮት ነበር። ሔዋን
ይህን ትእዛዝ በዘፍ. 3፡3 ደግማ በተናገረችበት ወቅት “በእርግጥ” የተሰኘችውን
ቃል በመግደፏ (በማስቀረቷ) አገላለጽዋ ጥንካሬ አልነበረውም። በዘፍ. 3፡4 እባቡ
የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ደግሞ ለመናገር ቢሞክርም ነገር ግን ቃላቶቹ እግዚአብሔር
ከተናገረው የሚቃረኑ ነበሩ። ምንም እንኳ ሔዋን በአትክልቱ ስፍራ ተገቢውን
ትምህርት ከእግዚአብሔር ብትቀስምም፤ ነገር ግን ከተጠቀመችው ቋንቋ አኳያ
ትምህርቱን እንደሚገባ በጽኑ አለመውሰዷን መመልከት ይቻላል።
ምንም እንኳ እግዚአብሔር ግልጽ በሆነ ቋንቋ ግልጽ የሆነ ትእዛዝ ቢሰጥም፤ ሔዋን
ግን ያን የተማረችውን አቃልላ እንዳቀረበች በትናንቱ ጥናታችን ተመልክተናል።
ሔዋን ጌታ የነገራትን በተሳሳተ ትርጉም ባታቀርብም፤ ለጉዳዩ አጽንኦት አለመስጠቷ
ግን እሙን ነው። ከእርሷ ምላሽ አኳያ ጉዳዩን ዝቅ አድርጎ የማየት አዝማሚያ ሊከሰት
እንደሚችል ለመገመት አይከብድም።
ይህን ተከትሎ ሔዋን ከእባቡ ጋር በተገናኘች ጊዜ እግዚአብሔር በአትክልት ስፍራው
ይገኝ ስለነበረው ዛፍ የተናገረውን (በትክክልም ባይሆን) ደግማ ተናገረች (ዘፍ. 3፡
2-3)። ይህ መልእክት ለእባቡ አዲስ ዜና አልነበረም። ይልቁንም ከዚህ ትእዛዝ
ጋር በቅጡ ይተዋወቅ የነበረው እባብ አባባሉን ለመጠምዘዝ የሚያስችለውን በቂ
ዝግጅት ሲያደርግ በመቆየቱ፤ የሔዋን የዋህነት ግዳዩን የተሳካ አደረገለት።
ጥቅሶቹን ይመርምሩ፡ ዘፍ. 3፡4-6። እግዚአብሔር በትክክል
የተናገረውን በቀጥታ ከመካድ ጎን ለጎን እባቡ ሔዋንን ለማሳት
በተጨባጭ ስኬታማ ያደረገው አባባሉ ምን ነበር? ለእቅዱ መተግበሪያ
ያዋላቸው የትኞቹን ምርኅዎች ነበር?
ሔዋን የተሰጣት ይህ የመልእክት ክፍል ትክክል አለመሆኑን እባቡ ሲነገራት በቀጥታ
ወደ እግዚአብሔር ሄዳ በጉዳዩ ዙሪያ መመካከር ነበረባት። እነዚያ ተማሪዎች ወደ
ኃያሉ መምህራቸው በቀላሉ መድረስ የመቻላቸው እውነታ እኛ ዛሬ ልናስተውለው
ከምንችለው በላይ የሆነ--የኤደን ትምህርት ቤት ውበት ነው። የሆነው ሆኖ ሔዋን
ፈጥና መለኮታዊውን እርዳታ መሻት ሲገባት የእባቡን መልእክት አሜን ብላ እንደ
መጨረሻ ቃል ተቀበለች። እባቡ በአምላካዊው ትእዛዝ ላይ ያቀረበው ለወጥ ያለ
አነጋገር ሔዋን ስለ ራሱ እግዚአብሔርም ሆነ እርሱ በነገራቸው ዙሪያ አንዳንድ
ጥርጣሬዎች እንዲያድሩባት ማድረጉ አልቀረም።
ይህን ክስተት ተከትሎ አዳም አስቸጋሪ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ። “አዳም አጋሩ
የእግዚአብሔርን ሕግ መጣሷን፣ የታማኝነታቸውና የአፍቃሪነታቸው ብቸኛ መፈተኛ
የሆነውን ክልከላ መተላለፏን ተረዳ። በአእምሮው ውስጥ ታላቅ ትንቅንቅ ተፈጠረ።
ሔዋንን ከጎኑ እንድትርቅ በመፍቀዱ አዘነ። አሁን ግን ነገሩ ተፈጽሟል፤ አብሮነቷ
ደስታው ከሆነው ከእርሷ መለየት ሊኖርበት ነው። ታዲያ ይህንን እንዴት ያድርገው?”
(የኃይማኖትና አባቶችና ነቢያት፡ ገጽ 50።)
ምንም እንኳ አዳም ትክክል የሆነውን--ካልሆነው ለይቶ ቢገነዘብም በሚያሳዝን
ሁኔታ የተሳሳተውን መረጠ።
ከዛፉ ከበሉ “እንደ እግዚአብሔር” እንደሚሆኑ ስለ ተነገራቸው ምጸታዊ
አሳች አባባል አሰብ ያድርጉ (ዘፍ. 3፡5)። ሆኖም መጀመሪያውኑ
በእግዚአብሔር መልክ ስለ መፈጠራቸው--ዘፍ. 1፡27 ተናግሮ አልነበር?
አዳምና ሔዋን እንዳገኙት ዓይነት ምርጥ ትምህርት ቢሰጠንም በቀላሉ
ልንስት ስለ መቻላችንና እምነትና መታዘዝ ብቸኛዎቹ መጠበቂያ
ከለላችን መሆናቸውን አስመልክቶ ይህ ምን ሊያስተምረን ይችላል?
አዳም እና ሔዋን የእባቡን መልእክት ለመከተል ሲመርጡ ከእግዚአብሔር የመማሪያ
ክፍል መባረርን ጨምሮ ውሳኔያቸው ያስከተለውን አያሌ መዘዞች መጋፈጥ
ነበረባቸው። አዳምና ሔዋን በኃጢአታቸው ምክንያት ያጧቸውን ነገሮች እስቲ
ለማሰብ ይሞክሩ። የእነርሱን ውድቀት ማስተዋላችን፤ ዛሬ በዚህ ዘመን ክርስቲያናዊው
ሥርዓተ ትምህርት ለእኛ ያለውን ዓላማ በተሻለ ለመረዳት ያስችለናል። ምንም እንኳ
ጥንዶቹ ከክፍል ቢባረሩም፤ ህይወት ፍጽምና በጎደለው ዓለም በአዲስ የትምህርት
ዓላማ ታጅቦ ብቅ አለ።
ከውድቀት አስቀድሞ የነበረው ትምህርት እግዚአብሔር እርሱነቱን፣ ባህሪውን፣
መልካምነቱና ፍቅሩን በመግለጽ ራሱን ከአዳምና ሔዋን ጋር ያስተዋወቀበት መንገድ
ከሆነ፤ ጥንዶቹ ከአትክልቱ ስፍራ የመማሪያ ክፍላቸው ከተባረሩ በኋላ ያለው
የትምህርት ፋይዳ ሰብዓዊውን ፍጡር ከእነዚህ ነገሮች ጋር ዳግም ለማስተዋወቅና
አምላካዊውን አምሳል እንደገና በእኛ ውስጥ ለማስረጽ እንዲረዳ መሆን ይኖርበታል።
ምንም እንኳ ሰብዓዊው ፍጡር በእግዚአብሔር ፊት በአካል ይቀርብ የነበረበትን
ዕድል ቢያጣም፤ ዛሬም ቢሆን ልጆቹ እርሱን፣ መልካምነቱንና ፍቅሩን ለማወቅ
ወደዚህ አምላክ መምጣት ይችላሉ። በጸሎት፣ በአገልግሎትና ቃሉን በማጥናት-አዳም እና ሔዋን በኤደን እንዳደረጉት እኛም ወደ አምላካችን እግዚአብሔር መቅረብ
እንችላለን።
በየሱስ እና በዘላለማዊው የመቤዠት እቅድ የተነሳ ሁሉም ሳይጠፉ መቅረታቸው
መልካም የምሥራች ነው። እኛ የመዳንና ወደ ቀድሞው ንጽህና የመመለስ ተስፋ
ባለቤቶች ነን። አብዛኛው ክርስቲያናዊ የሥርዓተ ትምህርት ክፍል--ተማሪዎችን
ወደ የሱስ የሚያመላክት፣ እርሱ ለእኛ ያደረገልንን ብሎም ወደ ቀደመው ንጽህና
የሚመልሰንን ስጦታ ማንጸባረቅ ይኖርበታል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ጴጥ. 1፡3-11። ሰብዓዊዎቹ ፍጡራን የአትክልቱን
ስፍራ በለቀቁ ጊዜ እነዚህ ጥቅሶች ወደ ቀደመው ንጽሕና የመመለስን
ማበረታቻ ይዘው ከተፍ አሉ። የእግዚአብሔር መልክ ዳግም በህይወታችን
ይሰርጽ ዘንድ ምን አድርጉ ሲል ጴጥሮስ ይመክራል?
“ለሕይወት እና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገን ሁሉ” እነሆ በየሱስ አማካይነት
ተሰጥቶናል። እንዴት ያለ ግሩም የተስፋ ቃል ነው! ከእነዚህ መሃል አንዳንዶቹ ምን
ሊሆኑ ይችላሉ? ጴጥሮስ እንደሚከተለው ያቀርባቸዋል፡ በጎነት፣ ዕውቀት፣ ራስን
መግዛት፣ መጽናናት--እያለ ይቀጥላል። ዕውቀት ጴጥሮስ ከጠቀሳቸው መሃል አንዱ
መሆኑን ልብ ይሏል። እርግጥ ነው--ይህ ጽንሰ ሀሳብ ወደ ሥነ ትምህርታዊው ንድፈ
ሃሳብ ይወስደናል። እውነተኛ ትምህርት የክርስቶስ ዕውቀት ወደ ሆነው እውነተኛ
ዕውቀት ይመራናል። በዚህም እርሱን በመምሰል ብቻ ሳንወሰን፤ ስለ እርሱ ያለንን
ዕውቀት ለሌሎች የምናጋራ እንሆናለን።
የተከለከለው ዛፍ “መልካምና ክፉን” በተጨባጭ የሚያሳውቅ
ዛፍ እንደነበር አሰብ ያድርጉ። ዕውቀት ሁሉ መልካም አለመሆኑን
አስመልክቶ ይህ ምን ይነግረናል? በመልካምና በክፉ ዕውቀት መካከል
ያለውን ልዩነት እንዴት እናውቃለን?
አንዳንዶች በክፍል “የተማሪ ተፈጥሮ” አላቸው። እጅግ በጣም ጥሩ ውጤት
ለማምጣት እንደ ነገሩ ማጥናት ለእነርሱ በቂ ነው። ገጾችንም ሆነ ምዕራፎችን
እንደ ዋዛ “ፉት” ይሏቸዋል። ዕውቀታቸው እንደ ሙጫ ነው። ክርስቶስን መሰረት
ያደረገው ትምህርታችን ራሳቸውን ለዚህ ለሚመድቡ እኩል ዕድል የሚሰጥ ተሞክሮ
እንደሆነ 2ጴጥ 1 እና 2 ያረጋግጥልናል።
በ2ጴጥ. ምዕ 1 የቀረቡት የማበረታቻ ቃላት በ2ጴጥ ምዕ 2 ከቀረበው ጽኑ
ማስጠንቀቂያ ጋር ይቃረናል።
ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ 2ጴጥ. 2፡1-17። በዚህ ስፍራ ሐዋርያው
የተጠቀማቸው ቃላት ምን ያህል ጉልበት ያላቸው ግሳጼዎች ናቸው?
ከዚህ ጽኑ ማስጠንቀቂያና ግሳጼ መሃል እንዴት ያለ ታላቅ የተስፋ ቃል
ተሰጥቶናል?
ጴጥሮስ በቁ. 10 መልእክቱ ሥልጣንን ስለሚንቁ መጻፉን ልብ ይሏል። ለዘመናችን
ተጨባጭ ክስተት ለሆነው ለዚህ ጉዳይ እንዴት ያለ ጽኑ ግሳጼ ቀርቦአል! እኛ እንደ
ቤተ ክርስቲያን አካልነታችን ለመንፈሳዊ መሪዎቻችን ልዩ ግምትና አክብሮት መስጠት
ይጠበቅብናል (ዕብ. 13፡7፣ 17፣ 24)። ቢያንስ እነርሱ ራሳቸው ለጌታ ታማኝ በሆኑት
መጠን እኛም እንድንታዘዛቸውና እንድንገዛላቸው ተጠርተናል።
ጴጥሮስ ካሰፈረው ከዚህ ጥብቅ ግሳጼ ጎን ለጎን ልብ የሚነኩ መጽናኛ ቃላቶችንም
ይቸራል (ቁ. 9)። ምንም እንኳ እግዚአብሔር ዐመጻ የመረጡትን ምን ማድረግ
እንዳለበት ቢያውቅም “በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት
እንደሚያድናቸው ያውቃል” ሲል ሐዋርያው ይነግረናል። የክርስቲያናዊው
ትምህርታችን አንዱ ክፍል ፈተናን ስለማስወገድ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር
ሊጠብቀን እንዲሁም እርዳታና ጥበቃ ሊያደርግልን የሚችልባቸውን አያሌ መንገዶች
የሚያስተምረን ብሎም “የስህተት ትምህርት በስውር” (2ጴጥ. 2፡1) ከሚያስገቡ
የሚያስጠነቅቀን አይደል?
ምንም እንኳ አዳምና ሔዋን በሥልጣን ላይ ንቀት አሳይተዋል ብሎ አንድ ሰው
መናገር ባይችልም--በስተመጨረሻ ያንን ሥልጣን ለመታዘዝ አለመምረጣቸው ግን
እሙን ነው። የጥንዶቹን መተላለፍ በጣም የከፋ ያደረገው፤ ስለ እነርሱ መልካም
ሲል ብዙ ያደረገው እግዚአብሔር ራሱ የነገራቸውን በግዴለሽነት መመልከታቸው
ነበር።
በሥልጣን ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮች በቤተ ክርስቲያን ወይም በቤተሰብ ብቻ ሳይወሰን
በአጠቃላይ በህይወትዎ ብርቱ ስፍራ ይኑረው። ሥልጣንን አስመልክቶ--በአግባቡ
ኃላፊነትን መወጣት እና በአግባቡ ራስን መሥዋዕት አድርጎ መስጠት አስፈላጊ የሆነው
ለምንድን ነው? መልስዎን በሰንበት ትምህርት ጥናት ይዘው ለመቅረብ ይሞክሩ።
“ቅዱሳኑ ጥንዶች በእግዚአብሔር አባታዊ ጥበቃ ስር ብቻ
አልነበሩም ነገር ግን ዕውቀቱ የማይመረመረው አምላክ ተማሪዎች ጭምር
ነበሩ። በመላዕክት ይጎበኙ ነበር፤ እንዲሁም ያለ ምንም ከለላ ወይም መጋረጃ
ከፈጣሪያቸው ጋር በቀጥታ ይገናኙ ነበር። ከህይወት ዛፍ በሚተላለፈው ብርታትና
ጥንካሬ የተሞሉና የአእምሮ ኃይላቸውም ከመላዕክት በመጠኑ ብቻ ዝቅ ያለ ነበር።
በዐይን የሚታየው ምስጢሩ የዩኒቨርስ ክፍል “በእውቀቱ ፍጹም የሆነውን የእርሱን
ድንቅ ሥራ” (ኢዮብ 37፡16) ሳይታክት የሚገልጽና የሚያስተምር የደስታ ምንጭ
ሆኖላቸው ነበር። ላለፉት ስድሰት ሺህ ዓመታት የሰውን ዘር ሲያመራምሩ የኖሩት
የተፈጥሮ ህግጋትና አሠራር ጉዳይ ለእነርሱ ግን ሁሉን አቅፎና ደግፎ በያዘው አምላክ
ተገልጦላቸው ነበር።
“አዳምና ሔዋን ከቅጠሎች፣ ከአበቦችና ከዛፎች ጋር በመነጋገር ከእያንዳንዳቸው
የህይወታቸውን ምስጢር ይሰበስቡ ነበር። አዳም ከግዙፉ የባህር ውስጥ ፍጥረት
ኢምንት እስከሆነው ነፍሳት ድረስ ትውውቅ ነበረው። ለእያንዳንዱ እንስሳ ስም
ያወጣው አዳም ከሁሉም ሥነ-ተፈጥሮ ጋር ትውውቅ ነበረው። የእግዚአብሔር
ሰማያዊ ግርማ፣ ሥርዓታቸውን ጠብቀው የሚኖሩ በቁጥር ሊገለጹ የማይችሉ
ዓለማት፣ ‘ደመናት ሚዛን ጠብቀው እንዴት እንደሚንሳፈፉ፣’ የድምጽና የብርሐን
እንዲሁም የቀንና የሌሊት ምስጢር ጥናቶች ለቀደምት ወላጆቻችን ይፋ ነበር።
የእግዚአብሔር ስም በሁሉም ደን ቅጠሎች ወይም በእያንዳንዱ ተራራ ላይ በሚገኝ
አለት፣ በአንጸባራቂ ከዋክብት፣ በምድርና በአየር እንዲሁም በሰማይ ላይ ተጽፎ
ነበር። መላው የፍጥረት ሥርዐትና የተጣጣመ ውበት ስለ ዘላለማዊው ጥበብና ኃይል
ያወሳቸው ነበር። በምርምራቸውም ዘወትር ልባቸው በጥልቅ ፍቅርና አዲስ ምስጋና
ለማቅረብ በሚያነሳሳ ስሜት ይሞላ ነበር።--(የኃይማኖት አባቶች እና ነቢያት ገጽ፡
43-44)
1.ትምህርት እና ሥራ--ሰብዓዊው ፍጡር ከፈጠረው አምላክ እና
ከፍጥረት ሥራው ጋር ግንኙነት የሚፈጥርበት መንገድ ይሆን ዘንድ
እግዚአብሔር በመጀመሪያ ያወጣው ዕቅድ ከሆነ፤ ዛሬ በሥራችን
የእርሱን እቅድ ጠብቀን እየተራመድን ነው? በሥራችን (ክፍያ
በምንቀበልበት፣ በትምህርት፣ በበጎ ፈቃደኝነት፣ በአገልግሎት ወዘተ)
አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር በተሻለ መተዋወቅ የምንችለው እንዴት
ነው?
2.ሰይጣን በኤደን የአትክልት ስፍራ የሠራውን የረቀቀ ደባ ስንመለከት
በገዛ ሰብዓዊ ደካማነታችን በቀላሉ ተስፋ እንድንቆርጥ ሊያደርገን
ይችላል። አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔር ምን ያህል አጠገባቸው
እንደነበረ እያወቁ እባቡ የነገራቸውን ግማሽ እውነት ተቀበሉ። እነርሱ
ከእግዚአብሔር ጋር ከነበራቸው ያን የመሰለ አካላዊ ቅርበት የተገለልን
እኛ--ፈተናን ለማሸነፍ የሚያስችለንን ኃይል ዛሬም ከእርሱ ማግኘት
የምንችለው እንዴት ነው?
3.በሥልጣን ዙሪያ ስለሚነሱ ጥያቄዎች እና ሥልጣንን መታዘዝ አስፈላጊ
ስለሆነበት ምክንያት ተወያዩ? የሥልጣን መዋቅሮች እየደበዘዙ መሄድ
ምን ያስከትላል? ሥልጣን ያለ አግባብ ጥቅም ላይ የሚውለው እንዴት
ነው? እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲከሰት እንዴት ምላሽ መስጠት እንችላለን?