መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እንተርጉም
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 2ኛ ሩብ ዓመት 2020

ግንቦት 15- ግንቦት 21

9ኛ ትምህርት

May 23 - May 29




ፍጥረት፣ ዘፍጥረት እንደ መሠረት ክፍል-2



ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ኢዮብ 26፡ 7-10፣ ዘፍጥረት 1-2፣ ዘፍጥረት 5፣ ዘፍጥረት 11፣ 1ኛ ዜና 1፡ 18-27፣ ማቴ 19፡4፣ 5፣ ዮሐ 1፡1-3


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ ‹‹ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።››( መዝሙር 19፡ 1)

በ ርካታ ታላላቅ አሳቢዎች እግዚአብሔር የፈጠረውን አለም ለመዳሰስ በመጽሐፍ ቅዱስ ተነድተዋል። በውጤቱም ዘመናዊው ሳይንስ ተወለደ። ዮሐንስ ክፐለር ፣ አይዛክ ኒውተን፣ ጆን ሬይ ፣ ሮበርት ቦይል፣ እና ሌሎች ቀደምት ታላላቅ ሳይንቲስቶች የእነርሱ ስራ የገለጸው የበለጠ የእግዚአብሔርን ፍጥረት፣ የእጅ ስራን እንደሆነ ያምናሉ። ከፈረንሳይ አቢዮት በኋላ ግን የ 19ኛው ክፍለ ዘምን ሳይንቲስቶች ከቴስቲክ (ፈጣሪ እንዳለ ያምናሉ) ንጽረተ አለም ወደ ናቹራሊዝም(ለሁሉም ነገር ተፈጥሯዊ ምክንያት የሚሰጥ ፍልስፍና ነው) እና ቁሳዊነት ላይ ብቻ ወደ ተመሰረቱ ንጽረተአለም አስተሳሰብ ተሸጋገሩ። በሁሉም ዘንድ ብዙ ጊዜ ለመንፈሳዊ ነገር ቦታ አልነበራቸውም። ይህ የፍልስፍና ሐሳብ በቻርለስ ዳርዊን የ እሰፒሾች ምንጭ ሐሳብ ታዋቂነትን አገኘ(1859)። ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ሳይንስ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው መሰረቱ እየጨመረ እየራቀ ሄደ፣ በውጤቱም የዘፍጥረት ታሪክ መሰረታዊ የሆነ አዲስ አይነት ትርጓሜን ያዘ።

መጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ ያለፈበት ፣ ሳይንሳዊ ያልሆነ የስነ-ትእይንተ አለም ምልከታን ያስተምራል? የመጽሐፍ ቅዱሳዊው ምልከታ እንዲሁ በዙሪያ ካሉ የጣኦት አምላኪዎች ሕዝብ የተዋሰው ነበር? ከባህል አንጻር መጽሐፍ ቅዱስ በቦታ እና በጊዜ ውስንነት ነበረው ወይስ የእኛ ምልከታ የመጣበት ተፈጥሮው በመለኮታዊ አውታሩ ፍጹም አድርገን ምንጩን ወደማየት ከፍታ ወስዶን ይሆን? እነዚህ በዚህ ሳምንት ጥናታችን የምንዳስሳቸው አንዳንዶቹ ነጥቦች ናቸው ። የዚህን ሳምንት ትምህርት ለ ግንቦት 22 ሰንበት በማጥናት ይዘጋጁ።

ግንቦት 16
May 24

ጠፍጣፋ ምድር?


በጥንቱ አለም ብዙዎች ምድር ጠፍጣፋ ነች ብለው ማመናቸው የተለመደ እምነት ነበር። ቢሆንም ግን ብዙ ሰዎች ለተለያየ መልካም ምክንያት ምድር ክብ እንደነበረች ተገንዝበዋል። ዛሬም እንኳን አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ ምድር ጠፍጣፈ እንደሆነች ያስባል ይላሉ። ራዕይ 7፡1ን እና 20፡8፣8ን ያንብቡ። የእነዚህ ጥቅሶች አውድ ምንድን ነው? በጣም አስፈላጊው ነገር ፣ ምድር ጠፍጣፋ እንደሆነች ያስተምራሉ?





የእነዚህ ጥቅሶች ጸሐፊ፣ ዩሐንስ የጻፈው የፍጻሜ ዘመን ትንቢትን ሲሆን ስለ አራቱ የሰማይ መላዕክት ይገልጻል ‹‹አራት መላእክት አየሁ፥ እነርሱም ነፋስ በምድር ቢሆን ወይም በባሕር ወይም በማንም ዛፍ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት ያዙ።››(ራዕ 7፡1) ይላል። መላዕክቶቹን ከአራቱ አቅጣጫዎች ጋር ለማያያዝ ‹አራት › የሚለውን ቃል ሶስት ጊዜ ይደግመዋል።

በአጭሩ እየተጠቀመ ያለው ስዕላዊ አገላለጽ ነው፣ ለምሳሌ ዛሬ ‹‹ ጸሐይዋ ገባች›› ወይም ነፋስ ‹‹ከምስራቅ ተነሳ ›› እንደምንለው ማለት ነው። ቃል በቃል ባለው ትርጓሜ ላይ ከተጣበቅን ፣ በስዕላዊ አገላለጽ የሚያመላክታቸውን ሐሳባዊ ሰሜንን፣ ደቡብን ፣ ምስራቅን እና ምዕራብን በሚያነሳበት በዚህ ትንቢታዊ ጽሑፍ ላይ ፣ ይህን ክፍል ከአውዱ በማውጣት እና አስተማሪ ያልሆነን ነገር እንዲያስተምሩ ይሆናል። ከሁሉም በላይ ኢየሱስ ሲናገር ‹‹ ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።›› (ማቴ 15፡ 19) ይላል። በዚህ ላይ ስለ ሰው ተክለሰውነት እየተናገረ አልነበረም ወይም ቃል በቃል ስለ ሰው ልብም አልነበረም። ሞራላዊ የሆነ ነጥብን ሊያስቀምጥ እርሱ የተጠቀመው ምሳሌያዊ ንግግር ነው። ኢዮብ 26፡ 7-10 ፣ እና ኢሳያስ 40፡ 21፣22ን ያንብቡ። ስለ ምድር ተፈጥሮ ምንድን ነው የሚያስተምሩን?





በኢዮብ 26፡7 ምድር የተገለጸችው በባዶ ቦታ ላይ እንደተንጠለጠለች ነው ‹‹ ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም በታችዋ አንዳች አልባ ያንጠለጥላል። ››። ምድር ‹‹ ‹ክብ › ›› ናት ወይም ሞላላ (ኢዮብ 26፡10) ። ኢሳያስ 40፡22 እንደሚያስቀምጠው ‹‹ እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀመጣል፥ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥›› ይላል።

እራስዎን ከሺ አመታት በፊት ይኖር እንደነበረ አይነት ሰው ቦታ ላይ ያስቀምጡ። ምድር እንደምትንቀሳቀስ ምን ማስረጃ ሊኖረዎት ይችላል? ወይም ቀጥ ብላ እንደቆመች ለማስረዳት ማስረጃን ማግኘቱ ይቻላል? ጠፍጣፋ ወይም ክብ መሆኑዋን ለማስረዳት ምን አይነት ማስረጃን ሊያገኙ ይችላሉ?

ግንቦት 17
May 25

ፍጥረት በጥንቱ ስነ-ጽሑፍ


የከርሰ ምድር ቅርስ ተመራማሪዎች ከጥንታውያን ግብጾች እና ከጥንት የቅርብ ምስራቅ ስፍራዎች የፍጥረትንና የውሃ ጥፋትን ታሪኮች የያዙ ጽሑፎችን አግኝተዋል። ይህ አንዳንዶችን አስገርሟቸዋል፣ የዘፍጥረት መግለጫ ከዚህ ባህል ተውሶ ነው ወይንስ በእነዚህ ላይ የሆነ ያህል የተደገፈ ነው በሚል ተገርመዋል። ነገር ግን እንደዚህ አይነት ነገር በእውነት ዋና ጉዳይ ነው? ዘፍጥረት 1-2፣4ን በጥንቃቄ ያንብቡ እና ከዚያ ከአትራ ሃሲስ ግጥም ያንብቡ። ‹‹ ከሰዎች ይልቅ አማልክቶች / ስራውን ሲሰሩ፣ ሸክሙን ሲሸከሙ/ የአማልክቶች ጫና እጅግ ታላቅ ነው። ስራው በጣም ከባድ ነው መከራውም ብዙ/ … የማህጸን አምላክ ጽንስን ይፍጠሩ/ እናም ሰው የአማልክትን ሸክም ይሸከም … ጌሽቱ-ኢ ፣ ማስተዋል ያላቸው አማልክት / በመሰብሰቢያቸው ያርዳሉ / ኒንቱ ከሸክላ ጋር ይቀላቀል / ከስጋው እና ከደሙ ጋር… ›› (Stephanie Dalley, Myths from Mesopotamia: Creation, the Flood, Gilgamesh, and Others (New York: Oxford University Press, 1989), pp. 9, 14, 15. ) ምን አይነት ልዩነትን ማየት ትችላላችሁ?

ምንም እንኳን በታሪኮቹ መካከል ተመሳሳይነት ቢኖርም (ለምሳሌ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከሸክላ ነበር የተሰሩት) ፣ ልዩነቶቹ ግን ይበልጥ ጥርት ያሉ ናቸው። (1)በአልትረ ሃሲስ ውስጥ አማልክት እንዲያርፉ ሰዎች ለአማልክት ይሰራሉ ። በዘፍጥረት እግዚአብሔር ምድርን እና በውስጧ ያሉትን በፍጥረት መጨረሻ ለፈጠረው ለሰው ፈጠረ። በዘፍጥረት ሰዎች በአትክልት ቦታው ተቀመጡ እናም ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ይሆኑ ዘንድ እና ስለፍጥረታት እንዲጠነቀቁ ተጋበዙ ፣ ይህ ሐሳብ በአልትራ ሃሲስ ውስጥ አይገኝም። (2)በአልትረ ሃሲስ ሰባት ወንዶች እና ሴቶችን ለመስራት አነስተኛው አማልክት ተገደለና ደሙ ከሸክላ ጋራ ተደባለቀ ። በዘፍጥረት ውስጥ መጀመሪያ አዳም ‹ተሰራ› በቅርበት በእግዚአብሔር የሕይወት እስትነፋስ እፍ ተባለበት እናም ሴት ደግሞ ‹ተሰራች › ኋለም የእርሱ ረዳት ሆነች። እግዚአብሔር አዳምን እና ሔዋንን በተሰዋ አማልዕክት ደም አልሰራቸውም። (3)በዘፍጥረት መግለጫ ውስጥ በአልትራ ሃሲስ እንዳለው የግጭት ወይም የወንጀል ምልክት አይታይም።

የመጽሐፍ ቅዱስ ገለጻ የላቀ በሁሉም ስፍራ የሚኖረውን አምላክ፣ ለሰብአዊያን ለተለየ አላማ በእንከን አልባ አለም ውስጥ እንዳስቀመጠ የገለጸ ነው። ይህ መሰረታዊ ልዩነት ምሁራኖችን በመጨረሻ እነዚህ የተለያዩ የፍጥረት ገለጻዎች እንደሆኑ አንዲደመድሙ አድርጓቸዋል። በፍጥረት እና በየውሃ ጥፋት ታሪኮች መካከል በጊዜ ሒደት በእውነት ከተከሰተው ነገር ላይ ተነስተው በቀላሉ እርስ በእርሳቸው የተጣመሩ እንደሆኑ አንዳንዶች ይከራከራሉ። በታጻራሪው ሙሴ በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ በእርግጥ ምን እንደሆነ ገልጾታል። ለጥቂት መመሳሰሎች ተብሎ ሙሴ ከአህዛብ ታሪኮች ሐሳቦችን ተዋሰ ከማለት ይልቅ ለምንድን ነው ይህ የእርሱ ገለጻ የበለጠ የማይሰራው/ተቀባይነቱ የማይጎላው?

ግንቦት 18
May 26

ዘፍጥረት እና ጣኦት አምልኮ


የዘፍጥረት መጽሐፍ አጻጻፍ ከጥንታዊው የአረማዊ /የጣኦት አምልኮ የፍጥረት አፈታሪኮች ላይ ከመደገፍ ይልቅ፣ እነዚህን አፈታሪኮች በሚያፈርስ መልኩ እና እግዚአብሔርን እንደ ፈጣሪ በመግለጽ ከእነርሱ በእጅጉ በአላቀ መልኩ የተጻፈ ነው። ዘፍጥረት 1፡14-19ን ያንብቡ። በአራተኛው ቀን የተከሰቱት አካላት እንዴት ነበር የተገለጹት፣ ተግባራቸውስ ምን ነበር?





‹ፀሐይ› እና ‹ጨረቃ› የሚለው አባባል በእርግጠኝነት ተወግዷል ምክንያቱም በእብራይስጥ ስማቸው በጥንታዊ ምስራቅ ግብጽ የነበሩ የጸሐይ እና የጨረቃ ጣኦታት ስሞች ነበሩ። ‹‹ታላቁ ብርሐን›› እና ‹‹ታናሹ ብርሀን ›› የሚለው አጠራር ለተለየ ተግባር እንደተፈጠሩ ያሳያል። ‹‹ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ ››(ዘፍ 1፡14) ። ያ ጽሁፍ በግልጽ እንሚያሳየው ጸሐይ እና ጨረቃ የሚለው ስም ጣኦታት አይደለም ነገር ግን የተፈጠሩት ነገሮች ዛሬ ልናስተውል ከምንችለው በላይ ግልጽ ለሆኑ ተፈጥሯዊ ተግባሮች ነው። ዘፍ 2፡7፣ 18-24ን ያንብቡ። እግዚአብሔር አዳምን እና ሔዋንን ሲፈጥር ምን ያህል በቅርበት ነበረ?





በጥንት የቅርብ ምስራቅ ያሉ አፈታሪኮች በመስማማት የሰውን አፈጣጠር በተመለከተ የከባድ ስራን አማልክት ለማሳረፍ ከቆይታ በኋላ የመጣ ነው ይላሉ። ይህ አፈታሪካዊ አስተሳሰብ በመጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ምድርን ሊያስተዳድር እንደተፈጠረ ከሚገልጸው አስተሳሰብ ጋር ይቃረናል። በሰው ተፈጥሮ ውስጥ ኋላ የተጨመረ የሚባል ነገር የለም። ያለ ነገር ቢኖር በፍጥረት መግለጫ ውስጥ ከፍተኛውን ስፍራ እንደያዙ ነው። እንዲያውም ምን ያህል የጣኦት አምልኮ እና የመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ ጥርት ባለ መልኩ የት ላይ እንዳረፉ/የተራራቁ እንደሆኑ በግልጽ የሚያሳይ ነው።

ስለዚህ ከጥንታዊው አለም አፈታሪክ ይልቅ የዘፍጥረት መጽሐፍ ትክክለኛውን መረጃ ያቀርባል። ሙሴ ከ ጣኦት አምልኮ ጋራ የማይሔዱ የተወሰኑ ጽንሰ ሐሳቦችን ተጠቅሟል። እናም ይህን ያደረገው በቀላሉ የመጽሐፍ ቅዱስን የእውነታ አገላለጽ በመገንዘቡ እና በፍጥረት ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ሚና እና አላማ በመረዳቱ ነው። ከብዙ ሺ አመታት በፊት የመጽሐፍ ቅዱስ የፍጥረት ታሪክ ከበዛው ባህል አንጻር የተለየ ነበር። ዛሬም የመጽሐፍ ቅዱስ የፍጥረት ታሪክ ከበዛው ባህል አንጻር አሁንም የተለየ ነው ። ለምንድን ነው የማንገረመው?

ግንቦት 19
May 27

ፍጥረት እና ጊዜ


ዘፍጥረት 5 እና 11 ያንብቡ። መጽሐፍ ቅዱስ የሰብአዊ ዘርን ታሪክ ከ አዳም እስከ ኖህ፣ ከኖህ እስከ አብርሐም እንዴት ነው የሚያስቀምጠው/ የሚዘረዝረው?





በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህን የዘር ግንዶች ለየት የሚያደርጋቸው አንድ ነገር አለ። የጊዜን ነገር በውስጣቸው ይዘዋል፣ አንዳንድ ምሁራን በትክክል እንዲጠሯቸው ያደርጋሉ ‹‹ chronogenealogies ›› (ቅደምተከተላዊ የዘርግንድ)። እርስ በእርሳቸው የሚያስተሳስር አሰራር አላቸው ተከታትሎ የሚሔድ መረጃ፣ የጊዜ መጠን። ስለዚህ ‹‹ ግለስብ አንድ ሀ ያህል አመታትን ኖረ ፣ ግለሰብ ሁለትን ወለደ፣ ግለሰብ አንድ ግለሰብ ሁለትን ከወለደ በኋላ መ ያህል እድሜን ኖረ እናም ሌሎች ወንዶችን እና ሴቶችን ወለደ ›› ይላል ። ምዕራፍ 5 ደግሞ ሌላ የቀመር ሐረግ ይጨምራል ‹‹ የግለሰብ አንድ ቀናቶች ሠ ያህል አመታት ናቸው›› ይህ እርስ በእራሱ የተሳሰረ ስርዓት፣ የሆነን ትውልድ ማጥፋት ወይም መጨመር እንዳይቻል ያደርገዋል።

ዘፍጥረት 5 እና 11 ቀጣዮችን ዘሮች /ትውልዶች ይዘዋል። በ 1ኛ ዜና 1፡ 18-27 እንደተረጋገጠው ምንም የጎደለ ወይም የተጨመረ ትውልድ የለም። በዚህ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ እራሱን ይተረጉማል። ወደ 2000አመታት ወደሚጠጋ ጊዜ አይሁድ እና ክርስቲያን ተመራማሪዎች የእነዚህን ጽሁፎች ታሪክ ሲያቀርቡ እና በትክክል የውሃ ጥፋት ጊዜን ሲያስቀምጡ እንዲሁም የምድርን እድሜ ሲያስቀምጡ ቢያንስ ከሰባቱ የፍጥረት ቀናት በዘፍጥረት 1-2 የተገለጹትን ይተረጉሙ ነበር።

በቅርብ ጊዜ ባለፉት አስርት አመታት የአንዳንድ የስነ-ቅርስ ተመራመሪዎች እና ታሪክ ተመራማሪዎች መረጃ ሐሳብ እንዲሰጥ ዘፍጥረት 5 እና 11 እረዥም አመታትን እንዲይዙ እና አንደገና ለመተርጎም ተሞክሯል (በቀላሉ በሚሳሳተው ሰበአዊ ፍጥረት)። ነገር ግን የእግዚአብሔርን የጊዜን ሐሳብ እና በታሪክ ውስጥ ያለውን አካሔዱን ከተረዳን እነዚህ ሁለት ምዕራፎች ‹‹ በታሪክ እና በስነ-መለኮት አስተምህሮ ሰፊ በሆነው ቦታ እና ጊዜ ውስጥ አዳምን ከሌላው ሰብአዊ ዘር እና እግዚአብሔርን ከሰው ያገናኛሉ።

ዘፍጥረት 5 እና 11፡10-26 በዚህች ምድር በስድስት ቀናት የፍጥረት ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለው ስፍራ ላይ ያለውን ሰው፣ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር የሚያስተሳስሩ ሰንሰለቶች እና የጊዜ አውታር ናቸው›› (Gerhard F. Hasel, “The Meaning of the Chronogenealogies of Genesis 5 and 11,” Origins 7/2 [1980], p. 69.) ምንም እንኳን እነዚህ የብሉይ ኪዳን ጽሑፎች በዚያ ያሉት ለመልካም እና ለአስፈላጊ ምክንያት ቢሆኑም፣ ጳውሎስ በ 1ኛ ጢሞ 1፡4 እና በቲቶስ 3፡9 ላይ ስለነዚህ ጽሑፎች ስናወራ እንድንጠነቅቅ ምንድን ነው ያለው?

ግንቦት 20
May 28

ፍጥረት በቅዱሳት መጽሐፍት


የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ያንብቡ፣ እናም እነዚህ ጸሐፊዎች እንዴት አድርገው ዘፍጥረት 1-11 ያለውን እንደማጣቀሻ እንደተጠቀሙበት ይጻፉ። ማቴ 19፡4፣5



ማር 10፡ 6-9



ሉቃ 11፡50፣51



ዮሐ 1፡1-3



ሐዋ 14፡15



ሮሜ 1፡20



2ኛ ቆሮ 4፡6



ኤፌ 3፡9



1ኛ ጢሞ 2፡12-15



ያዕ 3፡9



1ኛ ጴጥ 3፡20



ይሁ 11፣14



ራዕ 2፡7፣ 3፡14፣ 22፡ 2፣ 3



ኢየሱስ እና ሁሉም የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ዘፍጥረት 1-11 ያለውን ሲያጣቅሱ እንደ አስተማማኝ ታሪክ ወስደው ነው። ኢየሱስ ስለ ወንድ እና ሴት ፍጥረት የሙሴ ጽሑፎችን ጠቅሷል። ጳውሎስ በተደጋጋሚ የፍጥረትን መግለጫ በደብዳቤዎቹ ላነሳቸው ነጥቦች እንደ ስነ-መለኮታዊ ማስረጃ ጠቅሷቸዋል። ለተማሩት የአቴንስ ሰዎች ተናግሯል ‹‹ ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤ ›› (ሐዋ 17፡24) በእነዚህ መንገዶች የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ተፍጥሯዊ መሰረት ባለው ዘፍጥረት ላይ ተመስርተው ይህ ቃል በቃል የሆነ ኩነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ለዘመኑ አንባቢ አሳይቷል።

ለምሳሌ ሮሜ 5ን ያንበቡ። ከ ግማሽ ደርዘን በላይ ጊዜ ጳውሎስ ከአዳም እስከ ኢየሱስ ያለውን ግንኙነት ጠቅሷል (ሮሜ 5፡12፣ 14-19ን ይመልከቱ)። እሱ አዳም በአካል በታሪክ ውስጥ መኖሩን ተቀብሏል፣ የዝግመተ ለውጥ አስተሳሰብ መጥቶ በቀጥታ ይነበብ የነበረውን መጽሐፍ ቅዱስን በተካ ጊዜ ይህ አቋም አደገኛ በሆነ መልኩ ድርድር ውስጥ ወደቀ። የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው እና ኢየሱስ እራሱ የፍጥረትን መግለጫ እንደ አስተማማኝ ታሪክ ተመልክቷል፣ ስለምንድንነው ለእኛ በወደቀው እና አደገኛ በሆነው ሰበአዊ ፍጡር ላይ በመመስረት ተመሳሳይ ነገር አለማድረግ ለእኛ ሞኝነት የሚሆነው?

ግንቦት 21
May 29


ተጨማሪ ሐሳብ


የጌራልድ ኤ. ከሌንግብይልን The Genesis Creation Account and Its Reverberations in the Old Testament (Berrien Springs, MI: Andrews University Press, 2015). ያንብቡ። ‹‹ መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ሰፊ እና ምሪትን በመስጠት ተወዳዳሪ የሌለው የሰው ልጅ ታሪክን የያዘ ነው። ከዘለአለማዊው እውነት ምንጭ የተቀዳ እና የመለኮት እጆች በዘመናት መካካል ቅድስናውን ጠብቀውለት ያለ ነው … በዚህ ብቻ ነው የዘራችንን ታሪክ ልናገኝ የምንችለው። በሰብአዊ አግባብ ጥላቻ የሌለው ወይም ከሰብአዊ ኩራት የጸዳ ነው። ››(Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol. 5, p. 25.) ‹‹ ያለመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ የዘር ሐረግ ብቻውን ምንም ማረጋገጫ እንደማይሆን አይቻለሁ።

በምድር ውስጥ የሚገኝ ቅርስ አሁን ካለው አንጻር በነገሮች ሁኔታ ላይ የተለየ መረጃን ይሰጣል። ነገር ግን ለምን ያህል ጊዜ እነዚህ ነገሮች በምድር ውስጥ እንደቆዩ ሊስተዋሉ የሚችሉት በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ነው። ሐሳባችን በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ ካሉ ሐቆች ጋር የማይጋጭ እስከሆነ ድረስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በላይ መገመት የዋህነት ነው። ነገር ግን ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ከፍጥረት ታሪክ አንጻር ሲተው እና በተፈጥሮአዊ መርሆች የእግዚአብሔርን ፈጠራዊ የእጅ ስራዎች መግለጫ ሲሻ ፣ ድምበር በሌለው የመጠራጠር ውቂያኖስ ውስጥ እንደመሆን ነው። እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ ቃል በቃል በሚጠቀሱ በስድስት ቀናት የመፍጠር ስራውን እንደጨረሰ ለፍጡራን የሰጠውን ገለጻ የመሰለ ሌላ ምንም ገልጾ አያውቅም ›› (Ellen G. White, 10 Spiritual Gifts, book 3, p. 93.)


የመወያያ ጥያቄዎች




1.አሁን ስላለንበት እውነታ ሳይንስ ሲገልጽ ሳለ፣ በሚያዝ፣ በሚሰማ፣ በሚታይ እና በመፈተን ደግሞ እንደገና በሚፈተን ነገር ሁሉ ክርክር እና የሐሳብ ልዩነቶች ሲኖሩ ፣ ለምንድን ነው በጣም በርካታ ሰዎች ከሚሊዮን ወይም ቢሊዮን አመታት በፊት እንደተከሰቱ በሚታሰቡ እና የሚታወጁ ኩነቶችን ያለምንም ጥያቄ የሚቀበሉት?

2.ዘመናዊው ሳይንስ የሚሰራው ተቀባይነት ካለው ግምት ላይ በመነሳት ነው (በሚመለከተው ፊት ተቀባይነት ባለው) በዚያም ተፈጥሮአዊ ኩነቶችን ለመግለጽ መንፈሳዊ ነገሮችን መጠቀም አይቻልም። ያም ማለት ለምሳሌ በአንድ ጠንቋይ እርግማን ምክንያት ወደ ምድር እንደመጣ የሚነገር ድርቅን መግልጽ አይቻልም እንደማለት ነው። ቢሆንም ግን በዘፍጥረት ላይ ስለፍጥረት ባለው መግለጫ እንደተገለጸው ፣ የዚህ አቀራረብ ውሱንነት ምኑ ላይ ነው? በሌላ አባባል በዘፍጥረት ላይ ያለው መግለጫ በግልጽ መንፈሳዊ ኩነት ነው። ቢሆንም ግን ፍጥረትን ለመፍጠር መንፈሳዊው ሐይል እንደ ሕግ ቢቀመጥ ለምንድን ነው ይዞት የሚመጣው ሌላ ሞዴል የግድ ስህትት የሚሆነው?